tgindex
Voa Amharic

መረጃዎችን ለመላክ @Voa_News_Amharic_bot

Последний пост
12 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
10
Всего постов
44
Тип
открытый
Язык
mg
Категория
Новости и СМИ
В каталоге с
12 авг.
Подписчики
26 433
−1 за 6 дн.
Сутки
−11
−0,04%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
3 817
34 постов
Вовлечённость
14,4%
к подписчикам
Постов в день
1,4
всего 44
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
по 10 постам
1/24сутки в ленте
2 788
1/48двое суток
3 195
1/72трое суток
3 445

Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.

Посты

  • 12 авг.4 2634

    без подписи

  • 12 авг.4 3024

    በ ግብጽ የጭነት መርከብ ላይ ሁቲዎች በባብ ኤል-መንደብ በተፈጸሙት አዲስ ጥቃት ስድስት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች አስር ቆሰሉ በ ኢራን የሚደገፉት የመን የሁቲ ኃይሎች ባብ ኤል-መንደብን በማቋረጥ ላይ በነበረችውና «ቲሃማህ» በተሰኘችው የግብጽ የጭነት መርከብ ላይ በባሊስቲክ ሚሳኤሎች ባካሄዱት ጥቃት ስድስት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች አስር መቆሰላቸውን የየመን መንግሥት አስታወቀ። ማክሰኞ ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. በታንዛኒያን የተመዘገች መርከብ በሶስት ሚሳኤሎች ተመታለች። በጥቃቱ ሶስት ፓኪስታናውያን እና አንድ ኢንዶኔዥያዊ በአጠቃላይ አራት ሰራተኛች መግደላቸውን ተገልጿል። ጥቃቱ ከፍተኛ የእሳት አደጋ ማስከተሉም ተዘግቧል። በታጣቂዎቹ የተወነጨፈው ሁለተኛው ሚሳኤል የነፍስ አድን ሥራ እተከናወነ በነበረበት ወቅት መሆኑና፣ በጥቃቱም የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ተገልጿል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1

  • 12 авг.4 0442

    “ኢራን የኒውክሌር ቦምብ ለመሥራት ረዥም ጊዜ ያስፈልጋታል” የሞሳድ የቀድሞ አዛዥ የእስራኤል የስለላ ድርጅት ሞሳድ የቀድሞው አዛዥ ዮሲ ኮኽን ኢራን በተፈጸመባት ተከታታይ ጥቃት ምክንያት የኒውክሌር ቦምብ የመሥራቅ አቅሟ መዳከሙን ተናገሩ። ባለሥልጣኑ የእስራኤል የስለላ ድርጅት ፎርዶ የተባለው የኢራን ከመሬት በታች የሚገኝ የኒውክሌር ተቋም ላይ በቅርበት ባደረገው ክትትል ከፍተኛ ጉዳት ስለደረሰበት መልሶ ለመገንባት ረዥም ጊዜ ያስፈልጋታል ብለዋል። አሜሪካ በተቋሙ ላይ ያደረሰችውን ጉዳት ሲያልሙት የነበረው “ሕልም ስኬት ነው” ሲሉ የገለጹት ቢሆንም፤ ይህንን ሲሉ ምን ማለታቸው እንደሆነ ግን ማብራሪያ አልሰጡም። የቀድሞው የሞሳድ አዛዥ ተቋማቸው ኢራን ለዓመታት ከመሬት በታች ስትገነባው የቆየውን ፎርዶ የኒውክሌር ተቋምን በቅርበት እና በዝርዝር ሲከታተለው እንደቆየ ማክሰኞ ዕለት በተደረገ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል። ጨምረውም ኢራን 60 በመቶ የዳበረ ዩራኒየም አዘጋጅታለች በማለት ምንም እንኳን ንጥረ ነገሩ በከፍተኛ ደረጃ የዳበረ ቢሆንም የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንዲኖራት ያስችላል ማለት አይደለም ብለዋል። “60 በመቶ ዩራኒየም ማዳበር ማለት ቦምቡን ለማሥራት ገና ብዙ ርቀት መጓዝ የሚሰስፈልገው ነው” ብለዋል። አሜሪካ ፎርዶ የተባለውን ከተራሮች በታች የሚገኝ የኒውክሌር ተቋምን በልዩ እና ከባድ ቦምብ የደበደበችው ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ በፈጸመችው ጥቃት ነበር። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1

  • 12 авг.3 2041

    በ2019 በጀት ዓመት 13.4 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ እየተሠራ ነው ተባለ በ2019 በጀት ዓመት 13.4 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ እየተሠራ ነው ተባለ ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ ከ11.2 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ ማግኘት መቻሏን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ። ይህም ከአጠቃላይ ዕቅዱ የ119 በመቶ በላይ አፈጻጸም የተመዘገበበት መሆኑ ተገልጿል። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ዶክተር ካሳሁን ጎፌ ከወጪ ምርት ላኪዎች ጋር ባካሄዱት የምክክር መድረክ እንደገለጹት፤ የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት ሀገራዊ የማክሮ-ኢኮኖሚ መረጋጋትን ለማምጣት ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል። በቀጣዩ የ2019 በጀት ዓመት ደግሞ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ይበልጥ ለማሳደግ 13.4 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መረጃ አሳውቋል። ይህንን ዕቅድ ለማሳካት በሥራ ሂደት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታትና ላኪዎችን በቁርጠኝነት ለመደገፍ ከስምምነት መደረሱም ተገልጿል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1

  • 12 авг.2 7071

    በኮሎምቢያ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ከ200 በላይ ሰዎች የሞቱ ሲሆን፣የነብስ አድን ሰራተኞች እስካሁን ወደ መንቀጥቀጡ ማዕከል መድረስ አልቻሉም። በምዕራብ ኮሎምቢያ በኃይል መጠኑ 7.4 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ከተከሰተ በኋላ፣ የአደጋ ጊዜ ደራሾች በሕይወት የተረፉ ሰዎችን ለማግኘት በውድድር ላይ ይገኛሉ። አደጋው ከ200 በላይ ሰዎችን ገድሏል መንግሥት ብሔራዊ የአደጋ ጊዜ ያወጀ ሲሆን፣ የዓለም መሪዎችም ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል። አንድ ከፍተኛ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባልደረባ በቀጣዮቹ ቀናት የምግብ ስርጭት በጣም ወሳኝ እንደሚሆን ያሳሰቡ ሲሆን፣ በመንቀጥቀጡ ማዕከል አቅራቢያ የሚኖሩ አንድ የነባር (ኢንዲጂነስ) ማህበረሰብ መሪ እስካሁን ምንም ዓይነት እርዳታ እንዳልደረሳቸው ተናግረዋል።   ሌሎች በሕይወት የተረፉ ሰዎችም የገጠማቸውን አስፈሪ ሁኔታ በማስታወስ በመናገር ላይ ናቸው። በፔሬራ ከተማ ፍርስራሽ ውስጥ የተያዙ ሰዎችን ለማዳን የሕይወት አድናኞች እና በጎ ፈቃደኞች የሰው ሰንሰለት ሲሠሩ ተመልክቷል።   ከካሊ ከተማ የተገኘ አስደናቂ ቪዲዮ ደግሞ አንድ ሕፃን ከፍርስራሽ ሥር ሲወጣ ያሳያል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1

  • የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የሱዳን ጦር በሚቆጣጠራቸው የተለያዩ ከተሞች የድሮን ጥቃት ፈፀመ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በምህጻሩ (RSF) የሱዳን ዋና ከተማ ኻርቱምን ጨምሮ የሱዳን ጦር በሚቆጣጠራቸው የተለያዩ ከተሞች ላይ ዛሬ በሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) ጥቃት አድርሷል። የዓይን ምስክሮችና የጦር ምንጮች እንዳሉት የዛሬው ጥቃት ለወራት ከተፈጸሙት ጥቃቶች በከፍተኛ ደረጃ የተቀነባበረ ነው። ፈጥኖ ደራሹ ኃይል ኻርቱምን ፣ በኮርዶፋን የምትገኘው ኤል ኦቤይድ እና የሰሜን ሱዳን ከተሞችን አትባራን እና ኤል ዳመርን ብዛት ባለቸው ድሮኖች መደብደቡን የሱዳን ጦር ምንጭ ተናግረዋል። የሱዳን ጦር የፈጥኖ ደራሹን ኃይል አስወጥቶ መልሶ የያዛት እና ከዚህ ቀደምም የድሮን ጥቃቶች ዒላማ የሆነችው ካርቱም ለወራት አንፃራዊ መረጋጋት ሰፍኖባት ነበር። በኻርቱም ጥቃቱ የደረሰው ከማለዳው 11 ሰዓት ላይ እንደነበር በወቅቱም ከኦምዱርማን በስተሰሜን በሚገኘው ዋዲ ሴይዲና ከተባለው የሱዳን ጦር ሰፈር በኩል ደግሞ የፀረ-አውሮፕላን ሚሳይሎች ድምጽ መሰማቱ ተዘግቧል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1

  • የአሜሪካ ሴኔት ለ32 የአፍሪካ ሀገራት የሚሰጠውን የአጎዋ የንግድ ፕሮግራም ለማራዘም ወሰነ የዩናይትድ ስቴትስ ሴኔት የአፍሪካ የእድገትና የዕድል ስምምነትን ለሁለት ዓመታት እንዲራዘም ያጸደቀ ሲሆን፤ ይህም ብቁ ከሆኑ ሀገራት የሚገቡ ከ1 ሺህ 8መቶ በላይ ምርቶች እስከ ታህሳስ 2028 ድረስ ከቀረጥ ነፃ ወደ አሜሪካ ገበያ እንዲገቡ ያስችላል። ለ25 ዓመታት የአሜሪካ-አፍሪካ የንግድ ግንኙነት መሰረት ሆኖ የቆየው አጎዋ፤ አሜሪካ 32 ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር የሚያወጡ መኪናዎችን፣ ልብሶችን እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ከቀረጥ ነፃ እንድትገዛ ዕድል ሰጥቷል። አሁን ያለው ስምምነት በመስከረም ወር መጨረሻ ላይ ሊያበቃ የነበረ በመሆኑ፤ ይህ ማራዘሚያ በአሜሪካ የኤክስፖርት ንግድ ላይ ለሚደገፉ የአፍሪካ የንግድ ተቋማት ትልቅ እፎይታ ሆኗል። ለማራዘሚያው መሳካት ድጋፍ ያደረጉት የአሜሪካው ሴናተር ራፋኤል ዋርኖክ፤‹‹ይህ ውሳኔ የዕለት ተዕለት ዕቃዎችን ዋጋ ከመቀነሱም በላይ፤ የዓለም አቀፍ አጋሮቻችንን ኢኮኖሚ በማረጋጋት የሀገራችንን ብሄራዊ ደህንነት ያሻሽላል›› ብለዋል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1

  • без подписи

  • без подписи

  • ከሰሜን ኮሪያ የተተኮሰው ሚሳኤል የቀጣናውን ውጥረት አናግቷል   አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ሊያካሂዱት ካዘጋጁት ግዙፍ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ፣ ሰሜን ኮሪያ ሌላ አዲስ የባሊስቲክ ሚሳኤል በማስወንጨፍ ቀጣናውን አስበርግጋለች።  የደቡብ ኮሪያ እና የጃፓን ወታደራዊ ባለስልጣናት እንደገለፁት፤ ውጥረት በነገሰበት የኮሪያ አካባቢ የተደረገው ይህ ድርጊት አዲስ የፖለቲካ እና የደህንነት ስጋት ደቅኗል።   የፒዮንግያንግ አስተዳደር ሚሳኤሉን የተኮሰው ከምስራቃዊ የወንሳን የባህር ዳርቻ ሲሆን፤ የጦር መሳሪያው በምስራቅ ባህር (የጃፓን ባህር) ላይ ከ700 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት ተጉዞ አርፏል።    ይህ ድርጊት አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ "ኡልቺ ፍሪደም ሺልድ" የተሰኘውን አመታዊ መጠነ-ሰፊ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለመጀመር በሚዘጋጁበት ወቅት መከናወኑ ድንገተኛ እንዳልሆነ ይነገራል።  ሰሜን ኮሪያ እነዚህን የጋራ ልምምዶች ሀገሬን ለመወረር የሚደረጉ ማደናገሪያዎች ናቸው በማለት አጥብቃ የምትቃወም ሲሆን፤ የአሁኑ ማስወንጨፍም ለዋሽንግተን እና ለሴኡል የተላከ ግልፅ ማስጠንቀቂያ እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1

  • 10 авг.5 0017

    በ መተሀራ አቅራቢያ በሬክተር ስኬል 4.6 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ ትላን እሁድ ምሽት በኦሮሚያ ክልል መተሀራ አቅራቢያ በሬክተር ስኬል 4.6 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ ሲሆን፣ የመሬት መንቀጥቀጡ ንዝረት በአቅራቢያው በሚገኙ የአፋር አካባቢዎችም መሰማቱን ቮልካኖ ዲዝከቨሪ ዘገበ። የመሬት መንቀጥቀጡ ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ.ም. ከምሽቱ 2፡11 ሰዓት ገደማ የተከሰተ ሲሆን፣ የመነሻ ማዕከሉም ከመተሀራ በደቡብ ምስራቅ 19 ኪሎ ሜትር እንዲሁም ከአዋሽ 23 ኪሎ ሜትር ርቀት ለይ መሆኑን ቮልካኖ ዲዝከቨሪ ገልጿል። ከአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ (USGS) እና ከአውሮፓ-ሜዲትራኒያን ሴስሞሎጂካል ሴንተር (EMSC) የተገኙ መረጃዎችን የጠቀሰው ድረ-ገጹ፤ የመሬት መንቀጥቀጡ በ10 ኪሎ ሜትር ጥልቀት ውስጥ የተከሰተ መሆነን አመልክቷል። በመተሀራ አቅራቢያ በሚገኙ ነዋሪዎች የመሬት መንቀጥቀጡ እንደተሰማቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ከመተሀራ የተገኙ ሪፖርቶች ከቀላል እስከ መካከለኛ ደረጃ ያለው ንዝረት እንደተከሰተ አመላክተዋል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1

  • без подписи

  • በቀጣናው ውጥረት እና ግጭት በቀጠለበት ወቅት ሱዳን ከ ሞቃዲሾ እና ከ ካይሮ ጋር ውይይቶችን አደረገች ሱዳን ከሶማሊያ እና ከግብጽ ጋር በቀጣናዊ ክስተቶች፣ በሁለትዮሽ ትብብሮች እና በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮሩ የተናጠል ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶችን ማካሄዷን የሶማሊያ ብሔራዊ ዜና ኤጀንሲ (SONNA) እና የግብጹ አህራም ኦንላይን ዘገቡ። እንድ ሶና ዘገባ፤ በሞቃዲሾ የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አብዲሰላም አሊ በጽህፈት ቤታቸው የሱዳኑን አምባሳደር አብደልራህማን ኸሊል አህመድ አባክር አፋንዲን ተቀብለው አነጋግረዋል። ሁለቱ ወገኖች በቅርብ ጊዜያት በተከሰቱ ቀጣናዊ ሁነቶች እና ለውጦች፣ እንዲሁም በሶማሊያ እና በሱዳን መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር ማጠናከር እና ማስቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ዘገባው አመላክቷል። በተጨማሪም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለማስቀጠል እና በጋራ ጉዳዮች ላይ ትብብርን ለማስፋፋት ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። ሆኖም ከሁለቱም ወገኖች የተሰጠ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ የለም። ይህ በእዲህ እያለ፣ የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሂ ኤል-ዲን ሳሌም ከግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ ጋር በስልክ ተወያይተዋል። ውይይቱ በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ መሆኑን የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሶ አህራም ኦንላይን ዘግቧል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1

  • እስራኤል የትራምፕን የጋዛ ዕቅድ ውድቅ አደረገች፤ ስለ ሆርሙዝ ሰርጥ እና ሌሎች የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳይ ተጨማሪ ዝርዝሮች ወጡ እስራኤል እሁድ ዕለት በ አሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይፋ የተደረገውን የጋዛን ስምምነት ውድቅ አደረገች። በሌላ በኩል ቴህራን የ“ጠላት ሀገራት” መርከቦች እንዳያልፉ በከለከለችበት ወቅት፣ በ ኢራን እና በ ኦማን መካከል የሆርሙዝ ሰርጥን ለማስተዳደር ሊደረግ ስለሚችል ስምምነት ላይ ዝርዝር መረጃዎች ወጥተዋል። በተጨማሪም ኢራን ከፍተኛ የደኅንነት የኃላፊነት ቦታ ላይ አዲስ ሽግሽግ አድርጋለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በኢራን የሚደገፉት የየመን ሁቲ አማፂያን በሀገሪቱ የቀይ ባሕር ዳርቻ በሚገኝና በመንግሥት ቁጥጥር ስር ያለ ወደብ ላይ ጥቃት የሰነዘሩ ሲሆን፣ ይህም በስትራቴጂካዊ የመርከብ መጓጓዣ ላይ የተጋረጠውን ስጋት እና ወደ የእርስ በእርስ ጦርነት የመመለሱን ስጋት አብብሶታል። ኔታንያሁ ሃማስ ትጥቅ እስኪፈታ ድረስ የእስራኤል ጦር ጋዛን ለቆ እንደማይወጣ አስታወቀዋል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1

  • 10 авг.3 3011

    ኃይለኛ አውሎ ንፋስ በቻይና በመነሳቱ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ከቤታቸው ለቀው ወጡ ዶልፊን' የተሰኘው ኃይለኛ አውሎ ንፋስበቻይና ምሥራቃዊ ክፍል ላይ መነሳቱን ተከትሎ፣ የቻይና ባለሥልጣናት የፋይናንስ ማዕከል የሆነችውን ሻንጋይን ጨምሮ ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎችን ከቤታቸው አስወጥተዋል። አውሎ ንፋሱ ከፍተኛ ዝናብ ያስከተለ ሲሆን በመላው ክልሉ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዲስተጓጎል አድርጓል። ሰኞ ዕለት ብቻ በሻንጋይ ብቻ ወደ 1,000 የሚጠጉ በረራዎች ተሰርዘዋል።ባለሥልጣናት፣ አውሎ ነፋሱ ወደ ሰሜን ሲንቀሳቀስ ኃይለኛ ዝናብ፣ ከባድ የጎርፍ መጥለቅለቅ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ እስከ ረቡዕ ድረስ እንደሚከሰት ማስጠንቀቃቸውን ቀጥለዋል። የቻይና ባለሥልጣናት ቀደም ሲል ዶልፊን የተሰኘውን አውሎ ንፋስ በተመለከተ ከፍተኛውን የቀይ ማስጠንቀቂያ አውጥተው ነበር፣ ይህም በዚህ ዓመት ቻይናን የመታው ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ነው። እሁድ በዠይጂያንግ ግዛት ዩሁዋን ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ አውሎ ንፋሱ ሲመታ፣ በሰዓት 150 ኪ.ሜ ከፍተኛውን የንፋስ ፍጥነት አስተናግዷል፣ ይህም ከአንድ ሰዓት ገደማ በኋላ በዌንዙ ከተማ ሁለተኛ ዝናብ መጣሉን የሜትሮሎጂ ባለስልጣናት ተናግረዋል። ሰኞ ዕለት በሻንዶንግ፣ ሄናን፣ ሁቤይ፣ አንሁዊ፣ ጂያንግሱ፣ ዠይጂያንግ እና የሻንጋይ ከተማ ግዛቶች ከባድ ዝናብ እንደሚዘንብ ተንብየዋል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1

  • በኢትዮጵያ በኤልኒኖ ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን የድርቅና የጎርፍ አደጋ ለማቃለል አጣዳፊ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግሥታት የምግብና እርሻ ድርጅት (FAO) አስታወቀ ​እንደ ድርጅቱ ሪፖርት፣ በክረምቱ ወቅት በሚጠበቀው የእርጥበት እጥረትና ከጥቅምት እስከ ታህሳስ ባለው ጊዜ ሊከሰት በሚችለው የጎርፍ አደጋ ምክንያት የዜጎች የምግብ ዋስትናና የሕይወት መሠረት አደጋ ላይ ወድቋል። ይህ አደጋ ከ70 በመቶ በላይ የሀገሪቱን የሰብል ምርት በሚሸፍነው የክረምት ወቅት ላይ ትልቅ እንቅፋት እንደሚፈጥር ተገልጿል። ​በተለይም በአፋር፣ በአምሃራ፣ በትግራይና በሰሜን ሶማሌ ክልሎች በሚገኙ 114 ወረዳዎች ውስጥ የሚኖሩ ወደ 9.3 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ለአደጋው ተጋላጭ በመሆናቸው ቀድሞ የመከላከል ሥራ ያስፈልጋቸዋል። ​ድርጅቱ  አፋጣኝና ቅድመ-አደጋ ምላሽ ካልተሰጠ የአርሶ አደሩና የአርብቶ አደሩ የሕይወት እጣፈንታ ይበልጥ እንደሚከፋ በማስጠንቀቅ፣ የዓለም አቀፍ አጋሮች ድጋፍ በአስቸኳይ እንዲደርስ ጥሪ አቅርቧል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1

  • የዳንጎቴ ማጣሪያ ፋብሪካ በሐምሌ ወር ለአውሮፓ ትልቁ የጄት ነዳጅ አቅራቢ መሆን ቻለ የናይጄሪያው አሊኮ ዳንጎቴ ማጣሪያ ፋብሪካ በሐምሌ ወር ብቻ ለአውሮፓ ከገባው አጠቃላይ የጄት ነዳጅ ውስጥ አምስተኛውን ድርሻ በመያዝ (ከ2.06 ሚሊዮን ቶን ውስጥ ከ400 ሺህ በላይ ቶን በማቅረብ) ለአሁኑ ወርም ከአሜሪካ እና ከመካከለኛው ምስራቅ ቀድሞ የአውሮፓ ትልቁ የውጭ አቅራቢ መሆን መቻሉ ተገለፀ። ይህ አፈጻጸም የተመዘገበው በፋብሪካው ላይ በተከሰተ የቴክኒክ ችግር ምክንያት የጥገና ሥራዎች ተከናውነው የነዳጅ ማጣሪያ አቅሙ ከነበረበት በቀን ከ600 ሺህ በላይ ወደ 350 ሺህ ቀንሶ በነበረበት ወቅት ጭምር ነው። በሆርሙዝ ሰርጥ ዙሪያ የተፈጠሩ መስተጓጎሎች እና የአውሮፓ አገራት የኃይል አቅርቦታቸውን ለማብዛት ያላቸው ፍላጎት ለዚህ ስኬት መሠረት ሆኗል። የፋብሪካው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዴቪድ በርድ እንዳሉት ተቋሙ የናፍጣ እና ቤንዚን ምርቶችን ወደ ውጭ መላክ ጀምሯል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ፋብሪካው በጥቅምት ወር 5 ቢሊዮን ዶላር ለመሰብሰብ የአክሲዮን ሽያጭ እንደሚያካሂድ ይጠበቃል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1

  • በኩርሙክ ከተማ የጅምላ መቃብሮች ተገኙ በሱዳን ብሉ ናይል ክልል በፈጣን ድጋፍ ኃይሎች (RSF) የተገደሉ የ25 ሰላማዊ ሰዎችን አስከሬን የያዘ የጅምላ መቃብር መገኘቱን አንድ የአካባቢው ባለሥልጣን እሁድ ዕለት አስታወቁ። መቃብሩ የሴቶች፣ የሕፃናት እና የሆስፒታል ሠራተኞች አስክሬን የያዘ መሆኑ ተገልጿል። በኩርሙክ ከተማ የጅምላ መቃብሩ መገኘቱ የተሰማው፣ የሱዳን ሰራዊት ካርቱም እና ጌዚራ ግዛቶችን ከአርኤስኤፍ ነፃ ካወጣ በኋላ ተመሳሳይ የጅምላ መቃብሮች መገኘታቸውን ተከትሎ ነው። የኩርሙክ ከተማ ኮሚሽነር አብደል አቲ ሞሐመድ አል-ፋኪ በሰጡት መግለጫ፣ የሰራዊቱ አባላት ታጣቂ ቡድኑን ከከተማዋ ካባረሩ ከአንድ ወር በላይ በሆነ ጊዜ ውስጥ በሰሜን ምስራቅ የከተማዋ ክፍል ባካሄዱት የማፅዳት እንቅስቃሴ መቃብሮቹን ማግኘታቸውን ገልጸዋል። አል-ፋኪ አክለውም፣ ተጎጂዎቹ የተገደሉት አርኤስኤፍ በከተማዋ ላይ ጥቃት በሰነዘረበት ወቅት የአጥፍቶ ጠፊ ድሮኖችን ለማስወንጨፍ ይጠቀምበት በነበረው ጄበል ፋንካት በተባለ ኮረብታ አቅራቢያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1

  • ኢዜማ ከሀገራዊ ምክክሩ ምን ይፈልጋል? የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) መሪ አቶ እዮብ መሳፍንት ፓርቲያቸው ወደ ሀገራዊ ምክክሩ መድረክ የገባው ለአጭር ጊዜ የሥልጣን መጋራት ስምምነት ሳይሆን መሠረታዊና ሥርዓታዊ ለውጥ ለማምጣት ታግሎ ለመለወጥ መሆኑን አሳሰቡ። መሪው አክለውም ኢዜማ እስከ ምክክሩ መዝጊያ ቀን ድረስ በማይበገር አቋም የዜግነት ፖለቲካን፣ የነፃና ገለልተኛ መንግሥታዊ ተቋማትን ግንባታ እንዲሁም በብቃት ላይ የተመሠረተ ፍትሐዊ የኢኮኖሚ ሥርዓት መዘርጋትን እንደ ዋና መሠረታዊ ምሰሶዎች አድርጎ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።   ትውልዱን ከግጭትና ከመከፋፈል አዙሪት ነፃ ለማውጣትና ጠንካራ ሀገራዊ ሥርዓት ለመገንባት እነዚህን መርሆዎች እውን ማድረግ እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት አቶ እዮብ፣ የዜጋ ክብር ፍጹምና የማይደፈር የሆነባትን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ በጋራ እውን እስከሚደረግ ድረስ ፓርቲያቸው ያለማቋረጥ እንደሚታገል አጽንኦት ሰጥተዋል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1

  • 6 авг.8 5223

    የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከዓመታት የተከማቸ ዕዳና ኪሳራ በመውጣት 39 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ተቋሙ በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት ከነበረበት 168 በመቶ ኪሳራ ወደ 39 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማሸጋገሩን አስታወቁ። ይህ የተገለፀው በዚህ ሳምንት የተቋሙ የሥራ አመራር ቦርድ የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን በመገምገም፣ የድርጅቱን የፋይናንስ ስኬት የሚያሳይ ሪፖርት ባቀረበበት መድረክ ነው። ለዚህ አበረታች የትርፍና የልማት ስኬት መገኘት የመንግስት፣ የተቋሙ የሥራ አመራር ቦርድ እንዲሁም የተቋሙ ሠራተኞችና አመራሮች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን የጠቆሙት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ምስጋናቸውን አቅርበዋል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1