tgindex
የደጉ ሳምራዊ መልካምነት®

የደጉ ሳምራዊ መልካምነት®

Статистика

ይህ ትክክለኛ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት የቴሌግራም ቻናል ነው:: /በመምህር ሲራክ ሰሎሞን/ በዚህ የቴሌግራም ቻናል:- ➮አስተማሪ እና መንፈሳዊ ፅሁፎችን ➮የቅዱሳን ገድላት ➮ መዝሙሮችን ➮መንፈሳዊ ትምህሮቶችን ያገኛሉ። የመወያያ ግሩፕ: https://t.me/+QKiTJYGJvYpmNWM0 የዚህ ግሩፕ ዓላማ ለበጎ ምግባር ቃለ እግዚአብሔርን መማማር ነዉ::

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
19
Всего постов
47
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
12 авг.
Подписчики
1 160
+1 за 3 дн.
Сутки
+1
+0,09%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
100
40 постов
Вовлечённость
8,6%
к подписчикам
Постов в день
2,7
всего 47
Упоминаний
4
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
74
1/48двое суток
84
1/72трое суток
91

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • #ደሀ_ሰዉ_መሆኑን_እወቁ "....ሀብታምን ዕድለኛ ድሀን ደግሞ ዕድለ ቢስ ብለን መጥራት እንደሌለብን ከአልዓዛር እንማር፡፡እዉነቱን ለመናገር ግን ባለጸጋዉ ጥቂት ንብረቶችን የሚፈልገው እንጂ ብዙ ንብረቶችን የሰበሰበው አይደለም፡፡ ድሀ የሚባለው ደግሞ ምንም ንብረት ሳይኖረዉ ብዙ ፍላጎቶች ያለዉ ነዉ፡፡ የሀብትና የድህነት መገለጫዉም ይህ እንደሆነ ልናዉቅ ይገባናል፡፡ ለብዙ ነገሮች የሚስገበገብና የሁሉንም ሀብት በእጁ ያስገባዉን ሰዉ ብትመለከቱ እንዲህ ዓይነቱ ሰዉ የመጨረሻው ደሀ ሰዉ መሆኑን እወቁ፡፡ በአንጻሩ ምንም ባያገኝ እንኳ ጥቂት ፍላጎቶች ያሉትን ሰዉ ብትመለከቱ እንዲህ ያለዉን ሰዉ የባለጸጎች ሁሉ ባለጸጋ አድርጋችሁ ቁጠሩት፡፡ ድህነትንና ሀብታምነትን በአንድ ሰዉ ዉጫዊ መገለጫ መጠን ሳይሆን እንደ አዕምሯችን ሚዛናዊነት ማስቀመጥ ልማዳችን አድርገነዋል፡፡ በቅምጥልነት ቢደሰትና በወንዞችና በምንጮች አጠገብ ቢኖር እንኳ ሁልጊዜ የሚጠማን ሰዉ ጤነኛ ነዉ ብለን አንጠራዉም፡፡ በባለጸጎችም ዘንድ ያለዉ ልክ እንደዚህ ነዉ፡፡ የሌሎች ሰዎችን ንብረት ለማግኘት ሁልጊዜ የሚጓጉና የሚጠሙ ሰዎችን ጤነኞች ብለን አንጠራቸዉ፡፡ እንደዚህ ያሉ ሰዎች የተትረፈረፈ ነገር ቢያገኙ እንኳ ይረካሉ ብለን አንዳናስብ፡፡ አንድ ሰዉ የሰዎችን ሁሉ ንብረት ለራሱ አድርጎ እየወሰደ የራሱን ስስት መቆጣጠር ካልቻለ እንዴት ባለጸጋ ሊሆን ይችላል? ነገር ግን ዓይኖቻቸዉን ከሌሎች ንብረት ላይ ሳይጥሉ ባላቸዉ ረክተዉና የራሳቸው በሆነ ንብረት ደስ ተሰኝተዉ የሚኖሩት እነዚህ ሰዎች የድሆች ሁሉ ድሀ ቢሆኑም እንኳ የባለጸጋዎች ሁሉ ባለጸጎች ናቸዉ፡፡ በሌሎች ንብረት ላይ ምንም ዓይነት ፍላጎት የሌለውና ራሱን በመቻሉ ደስተኛ የሆነዉም ሰዉ የባለጸጎች ሁሉ ባለጸጋ ነዉ፡፡" የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ! ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ:👇🏽 ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

  • በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን:: ነሐሴ ፰(8) በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ ወንጌልና ምስባክ 🔊ዲያቆን 📖ሮሜ 9÷24....... 🔊ንፍቅ ዲያቆን 📖1ኛ ጴጥ 4፥12..... 🔊ንፍቅ ካህን 📖ግብረ ሐዋርያት 16÷35..... 🔊ምስባክ 📖መዝ 57፥8-10 ✍️"ወድቀት እሳት ወአርኢክም ለፀሐይ ዘእንበለ ጺትዐወቅ ሦክክሙ ሕለተ ኮነ ከመ ሕያዋን በመዓቱ ይውህጠ ክሙ" 🔊ትርጉም 👉"እሳት ወደቀች ፀሐይንም አላዩአትም እሽኳችሁ ሳይታወቅ በትር ሆነ ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ይነጥቃችዋል" 🔊ወንጌል 📖ማቴ 7÷12-26 ✍️"እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው ሕግም ነቢያትም ይህ ነውና...." 🔊ቅዳሴ ዘእግዝእትነ የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ! ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ:👇🏽 ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

  • ✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል" 📖ምሳ 1፥33 የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ! ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ:👇🏽 ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

  • #የዓርብ_ውዳሴ_ማርያም_ትርጓሜ ድንግል ሆይ! የደናግል ኹሉ መመኪያቸው አንቺ ነሽ፡፡ ከእናንተ መካከል “መመኪያነቷ እንዴት ነው?” ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፡- ፩ኛ) ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ሲል ይመልስልናል፡- “ወበከመ አውፅአ ብእሲ ብእሲተ ዘእንበለ ብእሲት ከማሁ አውፅአት ብእሲት ብእሴ ዘእንበለ ብእሲ ወሀሎ ዕዳ ላዕለ ትዝምደ አንስት፤ ወበእንተዝ ኮነት ፈዳዪተ ዕዳሃ ለሔዋን - ለወንዶች የሚከፈል ዕዳ በሴቶች ላይ ነበረ፤ ያለ እናት ሔዋን ተገኝታ ነበርና፡፡ ስለዚህም የሔዋንን ብድራት ለአዳም ትከፍለው ዘንድ ድንግል ያለ ዘርዐ ብእሲ (ያለ ወንድ ዘር) ክርስቶስን ወለደችው፡፡ አዳም ያለ እናት ሔዋንን ስላስገኘ እንዳይመካ ድንግል ያለ አባት ክርስቶስን ወለደችው፡፡ ድንቅ በሚኾን አንድነት ይህ አንድ የፍጥረት እኩልነት ይታወቅ ዘንድ” /ሃይ.አበ.፷፮፥፳፱/፤ ፪ኛ) ቀድሞ ወንዶች ሴቶችን በእናንተ ምክንያት ከገነት ወጣን እያሉ ርስት አያካፍሏቸውም ነበር፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ፡- “ብእሲ ወብእሲት አሐደ እሙንቱ በክርስቶስ - ወንድም ሴትም የለም፤ ኹላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና” ብሎ እስኪያስተምር ድረስ /ገላ.፫፡፳፰/ በሔዋን ምክንያት ከገነት ብትወጡ በእመቤታችን ምክንያት ገነት መንግሥተ ሰማያት ገብታችሁ የለምን? ብለው የሚመኩ ኹነዋልና፤ ፫ኛ) ደግሞ ለደናግላን አስበ ድንግልናቸውን (የድንግልናቸውን ዋጋ) ስለምታሰጣቸው ሊቁ “ምክሆን ለደናግል” ብሏታል፡፡ ቅድመ ዓለም የነበረ እርሱ ሰው ኹኗልና (ካንቺ ተወልዷልና) የእኛን ሥጋ ነሥቶ የርሱን ሕይወት ሰጥቶ ከርሱ ጋራ አስተካከለን፡፡ በቸርነቱ ብዛት እንድንመስለው አደረገን /ፊል.፫፥፲-፲፩/፡፡ ከብዙ ሴቶች አንቺ ትበልጫለሽ፡፡ ክብር የክብር ክብር ካላቸው ከብዙ ሴቶች አንቺ ትበልጫለሽ /ሉቃ.፩፥፳፰/፡፡ ንጉሥ በከተማው እንዲኖር ዘጠኝ ወር ካምስት ቀን ማኅፀንሽን ዓለም አንድርጎ ኖሮብሽልና አምላክን የወለድሽ ድንግል ማርያም ሆይ! ልዑል እግዚአብሔር የከተመብሽ ረቂቅ ከተማ ነሽ፡፡ በኪሩቤል በሱራፌል አድሮ የሚኖረው እርሱን በማኽል እጅሽ ይዘሽዋልና ልዑል እግዚአብሔር የከተመብሽ ረቂቅ ከተማ ነሽ፡፡ በቸርነቱ ብዛት ፍጥረቱን ኹሉ በዝናም አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ የሚመግበው እርሱ ጡትሽን ይዞ ጠባ፡፡ አንድም ለሰውን (ለመንፈሳውያን) ኹሉ ሥጋውን ደሙን ሰጥቶ የሚመግበው እርሱ ጡትሽን ይዞ ጠባ፡፡ ይኸውም ፈጣሪያችን መድኃኒታችን ነው፡፡ እንሰግድለት እናመስግነውም ዘንድ በሐዲስ ተፈጥሮ በጥንተ ተፈጥሮ ፈጥሮናልና ለዘለዓለሙ ይጠብቀናል /ዮሐ.፮፥፴፯/፡፡ ሰጊድ (አምልኮ) ከሚገባው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡ ፬ኛ) ድንግል ማርያም ዕፍረተ ምዑዝ (መዓዛው የጣፈጠ) የተባለ ጌታችንን የወለደች ሙዳየ ዕፍረት (የሽቱ መኖርያ) /፩ኛ ሳሙ.፲፥፩ አንድምታው/፤ ዳግመኛም የማየ ሕይወት (የሕይወት ውኃ የክርስቶስ) ምንጭ ናት /መኃ. ፬፥፲፪ አንድምታው/፡፡ የማኅፀኗ ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውን ኹሉ አድኗልና፡፡ ከእኛ መርገመ ሥጋን መርገመ ነፍስን አጠፋልን፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ፡- “በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ኹሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና” እንዲል /ቈላ.፩፡፲፱-፳/ በመካከል ኾኖ በመስቀሉ አስታረቀን፡፡ ልዩ በኾነ ትንሣኤውም ሰውን ዳግመኛ ወደ ገነት መለሰው፡፡ ከእናንተ መካከል፡- “ልዩ በኾነ ትንሣኤ ሲል ምን ማለቱ ነው?” ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፡- ከእነ አልዓዛር ትንሣኤ የተለየ መኾኑን ለማሳየት ነው፡፡ ምክንያቱም፡- ፩ኛ) እነ አልዓዛር አስነሺ ይሻሉ፤ እርሱ ግን “ላኖራት ሥልጣን አለኝ፤ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ” ብሎ እንደተናገረ /ዮሐ.፲፥፲፰/ የተነሣው በገዛ ሥልጣኑ ነውና፡፡ በተለያየ ሥፍራ “አብ አንሥኦ (አብ አስነሣው)፤ መንፈስ ቅዱስ አንሥኦ (መንፈስ ቅዱስ አስነሣው)” ቢልም አንድ ነው፡፡ ምክንያቱም ዕሪናቸውን መናገር ነውና፡፡ ፪ኛ) የእነ አልዓዛር ትንሣኤ በብሉይ ሥጋ ነው፤ የእርሱ ግን በሐዲስ ሥጋ ነው፡፡ ፫ኛ) የእነ አልዓዛር ትንሣኤ ሞትን ያስከትላል፤ የእርሱ ግን ሞትን አያስከትልም፡፡ ፬ኛ) የእነ አልዓዛር ትንሣኤ ትንሣኤ ዘጉባኤን ይጠብቃል፤ የእርሱ ግን አይጠብቅምና፡፡ አዳምን ዳግመኛ ወደ ገነት ከመለሰ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡ ፭ኛ) አንዳንድ ተረፈ ንስጥሮሳውያን እንደሚሉት ንጽሕት ድንግል ማርያም ላቲ ስብሐትና “ወላዲተ ሰብእ” አይደለችም፤ የታመነች አምላክን የወለደች ናት እንጂ፡፡ የመናፍቃን መዶሻ የተባለው፣ በተለይም የቅድስት ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክነት የካደውን ንስጥሮስን የረታው ቅዱስ ቄርሎስ እሳተ መለኮት አምላክን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኗ የተሸከመች፣ በጀርባዋ ያዘለች፣ በዝናብ አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ የፈጠረውን ፍጥረት የሚመግበው አማኑኤልን የድንግልና ጡቶቿን ወተት የመገበችውን የወላዲተ አምላክን ክብር ያልተረዱትን ንስጥሮሳውያን መናፍቃንን ሲወቅስ “ወለዛቲ እንተ መጠነዝ ዐባይ ጾረት መለኮተ እፎ ይከልእዋ እምክብራ ለወላዲተ አምላክ ወላዲተ አምላክኬ ቅድስት ድንግል - ይኸንን ያኽል ታላቅ ኾና መለኮትን የተሸከመችቱን የአምላክ እናት ክብርን እንደምን ይነፍጓታል፤ ይከለክሏታል፡፡ የአምላክ እናት ማለት ድንግል ማርያም ናታ” በማለት የተሰጣትን ክብር በማድነቅ አስተምሯል /ተረፈ ቄርሎስ/፡፡ እንዲህም ስለኾነ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የታመነች የምሕረት አማላጅ ናት፡፡ የዚህ ዓለም ሰዎች አማልዱኝ ቢባሉ ነገር አጽንተው ይመለሳሉ፤ እርሷ ግን “ማእምንት ሰአሊተ ምሕረት - የታመነች የምሕረት አማላጅ ናት” /ዮሐ.፪፥፩-፲፩/፡፡ ሰአሊተ ምሕረት ሆይ! ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ከልጅሽ ዘንድ አማልጅን፡፡ ኃጢአታችንን ከሚያስተሠርይልን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡ ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

  • በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን:: ነሐሴ ፯ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት ወንጌልና ምስባክ 🔊ዲያቆን 📖ዕብ 9÷1-11 🔊ንፍቅ ዲያቆን 📖1ኛ ጴጥ 2፥6-18 🔊ንፍቅ ካህን 📖ግብረ ሐዋርያት 10÷1-30 🔊ምስባክ 📖መዝ 86፥1-3 ✍️"መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን ያበድሮን እግዚአብሔር ለአናቅጸ ጽዮን እምኩሉ ተዐይኒሁ ለያዕቆብ" 🔊ትርጉም 👉"መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ነው ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል" 🔊ወንጌል 📖ማቴ 16÷13-29 🔊ቅዳሴ ዘእግዝእትነ 👉 https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

  • ✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል" 📖ምሳ 1፥33 የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ! ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ:👇🏽 ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

  • #የሐሙስ_ውዳሴ_ማርያም_ትርጓሜ (ማብራሪያ) ✍🏽ይህ ዕለት ለምስጋና አራተኛ ለፍጥረት አምስተኛ ቀን ነው፡፡ በዚህም ቀን እመቤታችን ትመጣለች፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፤ የብርሃን ዙፋን ይነጸፋል፡፡ ከዚያ ላይ ኹናም ሊቁን ባርካው ምስጋናዉን ጀምሯል፡፡ ከወትሮ ይልቅም ነቢያትንና ሐዋርያትን አስከትላ መጥታለች፡፡ ፩. ነደ እሳት ሰፍሮባት፣ በነደ እሳት ተከባ፣ ጫፎቿ ሳይቃጠሉ ሙሴ በደብረ ሲና ያያት ዕፅ ድንግል ማርያምን ትመስላለች /ዘጸ.፫፡፩-፫/፡፡ አካላዊ ቃል ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው ኹኗልና፤ ባሕርየ (እሳተ) መለኮቱም አልለወጣትምና (አላቃጠላትምና) ሐመልማላዊቱ ዕፅ እመቤታችንን ትመስላለች፡፡ ዳግመኛም እርሱን ከወለደችው በኋላ ማኀተመ ድንግልናዋ አልተለወጠምና ሐመልማላዊቱ ዕፅ እመቤታችንን ትመስላለች፡፡ እርሱም ምንም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷም ነፍስ ነስቶ ፍጹም ሰው ቢኾንም ባሕርየ መለኮቱ አልተለወጠምና እሳቱን ይመስላል፡፡ ሰውም ቢኾን ባሕርየ መለኮቱ አልተለወጠምና ሰው ኾኖ ያዳነን የባሕርይ አምላክ ነው፡፡ ሰው ኾኖ ካዳነን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋዉን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡ ፪. ይቅርታሽ (ምልጃሽ) ለኹላችን ይኾን ዘንድ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ! ኹላችን እናከብርሻለን፤ እናገንሻለን፡፡ ሔዋን ባደረገችው ዐመፅ በባሕርያችን ጸንቶ የነበረ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ በእርሷ ምክንያት የጠፋልን አምላክን የወለደች ድንግል ማርያም የኹላችን መመኪያ ናት፡፡ “ሔዋን ምን አደረገች?” ትለኝ እንደኾነም ዕፀ በለስን በልታለች እልሃለሁ፡፡ “ወአዘዞሙ ለኪሩቤል ወሱራፌል ዘውስተ እደዊሆሙ ሰይፈ እሳት እንተ ትትመያየጥ ከመ ይዕቀቡ ፍኖተ ዕፀ ሕይወት - ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔድን ገነት ምሥራቅ አስቀመጠ” እንዲል /ዘፍ.፫፡፳፬/ በሔዋን ምክንያት የገነት ደጅ ተዘጋ፡፡ “ወአግኃሦ ለሱራፊ ዘየዐቅብ ፍና ዕፀ ሕይወት፤ ወአእተተ እምእዴሁ ኵናተ እሳት - ” እንዲልም በድንግል ማርያም ምክንያት ዳግመኛ ተከፈተልን፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግም፡- “አዳምን እንዲሞት ያደረገች ያቺ ቀን ተለወጠች፡፡ እርሱም ከሞት የሚድንባት ሌላ ቀን መጣች፡፡ እባቧ ሳትኾን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ይናገር ዘንድ ተነሣ፡፡ ሔዋን ሳትኾን ድንግል ማርያምም ቃሉን ትቀበል ዘንድ ተዘጋጀች፡፡ በተንኰል የሚያስተው ሳይኾን ሕይወትን የሚያውጀው ቃል ወጣ፡፡ በሞት ዛፍ መካከል የሞት ዕዳዋን በጻፈችው ሔዋን ፈንታ ልጇ (ማርያም) የአባቷን ዕዳ ኹሉ ከፈለች፡፡ ሔዋንና እባቡ በቅድስት ድንግል ማርያምና በቅዱስ ገብርኤል ተተኩ፡፡ ያ ከመጀመርያው የተበላሸው ነገር አሁን ተስተካከለ፡፡ የሔዋን ጀሮና ቀልብ አታላዩ በሚናገርበት ጊዜ እንደምን እንዳዘነበለ አስተውሉ፤ ያ በገነት ሲመለከታቸው የነበረው መልአክ አሁን በድንግል ማርያም ጀሮ የድኅነትን ተስፋ ሲያሰርጽና የእባቡን ከፉና መርዛማ ቃል ሲያጠፋ ደግሞ አስተውሉ፡፡ ሔዋን ያፈረሰችው ሕንፃ ገብርኤል ገነባው፡፡ በዔደን ገነት ውስጥ ኹና ሔዋን ያፈረሰችውን መሠረት ዳግሚት ሔዋን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር ኹና ገነባችው፡፡ ከኹለት መልእክተኞች መልእክት የተቀበሉ ኹለት ደናግላን ኹለት ትውልድን ቀጠሉ፡፡ አንዱም የአንዱ ተቃራኒ ኾነ፡፡ በእባብ ምክንያት ሰይጣን ምሥጢርን ለሔዋን ላከ፡፡ በሌላ ቅዱስ መልአክ አማካኝነት ደግሞ ጌታ የምሥራቹን ወደ ቅድስት ድንግል ማርያም ላከ፡፡ እባብ ለሔዋን የሐሰትን ቃል ለሔዋን ስትናገር ቅዱስ ገብርኤል ግን የእውነትን ቃል ለቅድስት ድንግል ማርያም ተናገረ፡፡ እውነትን በሚናገር አንደበቱ የቀደመውን የእባብ ቃል አደሰው፡፡ እውነትን ተናገረና ሐሰቱን አስወገደው፡፡ አስቀድሞ ሐሰትን ከራሱ አንቅቶ ሰይጣን ሔዋንን በዔደን ገነት አታለላት፡፡ ይህንንም ታላቅ ስሕተት በጀሮዋ አልፎ እንዲሰማት ፈቀደች፡፡ አሁን ግን በመጀመርያዋ ድንግል ፈንታ ሌላ ድንግል ተመረጠች፡፡ በዚህች ድንግል ጀሮም ከአርያም የተላከ የእውነት ቃል ገባ፡፡ ሞት በገባበት በዚያ በር (ጀሮ) ሕይወት ገባ፡፡ ክፉው (ዲያብሎስ) ያጠበቀው ጽኑ የሞት ማሰርያም ተፈታ፡፡ ኀጢአትና ሞት ሠልጥነውበት በነበረ ቦታ ጸጋ ከመጠን ይልቅ በዝቶ ታየ፡፡ … እባብ የስሕተትን ዜማ ለሔዋን ዘመረላት፤ ሐሰትንም ረጨባት፡፡ በተፈጥሮዋ ገና ድንግል በምትኾን በሔዋን ላይ ክፉ ምክርና ስሕተት አፈሰሰባት፡፡ በመርዝ የተለወሰና ደምን የተጠማ ክፉ ምክር በአዳም ቤት ውስጥ አስገባ፡፡ ኃይለ ልዑል የላከው መልአክ ግን እነዚህን የክፋት ሰይፎች ለመቆራረጥ ክንፉን እያማታ እየበረረ መጣ፡፡ ለሰው ኹሉ የሚኾን የድኅነት ሰነድ ይዞ መጥቶም ለድንግሊቱ (ለማርያም) አበሠራት፡፡ ሰገደላት፡፡ ሕይወትን በውስጧ አሰረጸ፡፡ ሰላም ዐወጀ፡፡ በፍቅር ቀረባት፡፡ የቀድሞውን የሞት ዳባ በጣጠሰው፡፡ እባብ የገነባውን የማታለል ግንብ ዳግም ላይገነባ በወልደ እግዚአብሔር እንደሚናድ ነገራት፡፡ በእባብ የታጠረው የሞት ቅጽር በወልድ መውረድ እንደሚሰባበር ቀጠሮው እንደደረሰ ነግሮ የምሥራች አላት” በማለት ከማር የጣፈጠ ትምህርቱን እያነጻጸረ አስተምሯል፡፡ ከዕፀ ሕይወትም እንበላ ዘንድ አደለን፡፡ ይኸውም እኛን ስለ መውደድ ሰው ኾኖ ያዳነን የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ነው፡፡ ወዮ! ሰውን የሚወድ ሰውም የሚወደው እግዚአብሔር፣ ማኅደርም ኀዳሪም ያይደለ አካላዊ ቃል፣ ሳይለወጥ ቅድመ ዓለም የነበረ እግዚአብሔር ወልድ፣ ከአብ አንድነት ሳይለይ መጥቶ ንዕድ ክብርት ከምትኾን ከእመቤታችን ሰው ኾኗልና፤ እርሱንም ከወለደችው በኋላ እንደ ቀድሞ ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ ኑራለችና፤ ስለዚህም ነገር አምላክን የወለደች እንደኾነች በጎላ በተረዳ ነገር ታውቃለችና ለርሷ ድንቅ ኾኖ የሚነገረውን ነገር መናገር የሚቻለው ምን አንደበት ነው? መስማትስ የሚቻለው ምን ጆሮ ነው? ማወቅስ የሚቻለው ምን አእምሮ ነው? የእግዚአብሔር የጥበቡ ምላት ስፋትስ ምን ይረቅ? ምን ይጠልቅ? አንድም ለእግዚአብሔር ለጥበቡ ምላት ስፋት አንክሮ ይገባል፡፡ “በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል” /ዘፍ.፫፡፲፮/ ብሎ የፈረደባት ማኀፀን የሕይወት፣ የድኅነት መገኛ ኾነች፡፡ Telegram: ☞https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

  • #ከሌሎች_ይልቅ_ብዙ_የሚደክመው_ያ_ሰው ሰባኪው በአንድ ቤተ-ክርስቲያን እየተገኘ ዘወትር ያስተምራል። በየእለቱ በርካታ ምእመናን በቦታው እየተገኙ ይሰበካሉ (ይማራሉ)። ከእነዚህ በርካታ ምእመናን ውስጥ አንደኛው ራቅ ካለ ቦታ ነው ሚመጣው። ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጣም ሆነ ሲመለስ መሻገሪያ ድልድይ የሌለውን ወንዝ እየዞረ ስለሆነ ከሌሎች ይልቅ ብዙ የሚደክመው እሱ ነው። #አንድ_ቀን_ግን_እንዲህ_ሆነ፦ ሰባኪው የሚያስተምረው ስለ ጽኑ እምነት ነበር። " የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ፦ ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም።” የሚለውን ማቴ. 17፥20 ያለውን የመጽሃፍ ቅዱስ ኃይለ ቃል ጠቅሶ ሰው በእምነቱ ጽኑ ሲሆን የሚሳነው ነገር እንደሌለ ለምእመኑ አስረዳና የዕለቱን ስብከት አጠናቀቀ። መሻገሪያ በሌለው ትልቅ ወንዝ ምክንያት ከሌሎቹ ምእመን ይልቅ ብዙ የሚደክመው ያ ሰው ከቤተክርስቲያኑ ቅጥር ወጥቶ ወደ ቤቱ ሲያቀና እንደተለመደው እዛ ድልድይ አልባ ወንዝ ላይ ደረሰ። ወንዙን ሲያየው ሰባኪው ያስተማረው የእምነት ትምህርት ድቅን አለበት። ወዲያውኑ "እኔ እኮ በእግዚአብሔር አምናለሁ እግዚአብሔርም ይህን ለእኔ ማድረግ አይሳነውም" በማለት በፍጹም እምነት ወደ ጥልቁ ወንዝ በመሄድ ረገጠው እንዳለውም ተሳካለት መራመድም ቻለ። ያን ዙሪያ ጥምጥም የሆነ የቤቱን ጎዳና በጣም አጭር በሆነ ደቂቃ አጠናቆ ቤቱ ግባ። ሚስቱም በመደንገጥ "ቤተ-ክርስቲያን አልሄድክም እንዴ? ምነው በጊዜ መጣህ?" ብላ ብትጠይቀው የሆነውን ሁሉ ነገራት። እሷም በጣም ተደንቃ "ባለቤቴ ይህ ተዐምር ከተደረገለት መምህሩማ ምን ያህል ኣምላክ የመረጠው ቅዱስ ነው" ብላ "በል ነገ ይዘኸው ና! ቤታችንን በበረከት ይጎብኝልን።" በማለት ባለቤቷን ተማጸነች። በማግስቱ የዋሁ ባል ያለምንም ፍርሃት እና ጥርጣሬ በወንዙ ላይ ተረማምዶ ከተሻገረ በኋላ ትምህርቱን ተከታትሎ ጉባኤው ሲፈጸም ሰባኪውን ሄዶ፥ "ባለቤቴ እቤት እየጠበቀችን ነው እባክህን አብረን እንሂድ አለው።" ሰባኪውም ግብዣውን ተቀብሎ ጉዞ ጀመሩ። ሁለቱም እዚያ ወንዝ አጠገብ ሲደርሱ የዋሁ ሰውዬ እንደለመደው በውሃው ላይ እየተራመደ ጥቂት ከተጓዘ በኋላ ዞር ብሎ ሰባኪውን ሲመለከት ከወንዙ ዳር እንደቆመ ነው። በሰባኪው መቆም ተገርሞ "ና እንጂ መምህር ምን ሆነሃል?" ሲል ጠየቀው። ሰባኪውም "ፈራሁ" ሲል ይመልስለታል። ውሃውን እየረገጠ ወደኋላ ተመልሶ "ምነው መምህር? እኔን ለዚህ አብቅተህ እንዴት ትፈራለህ? ና ተሻገር እባክህን" ሲል ጠየቀው በሰውዬው ንግግር ጭንቅላቱ የተነካው መምህርም፡ "ወዳጄ እኛ #እናሻግራለን እንጂ #አንሻገርም!" ሲል መለሰለት። እኛስ የምንናገረውንና የምናዳምጠውን፣ የምናስተምረውንና የምንማረውን፣ የምንሰብከውንና የምንሰበከውን እየኖርን ነውን? የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንንቤተሰብ ይሁኑ! ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ:👇🏽 ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

  • #የረቡዕ_ውዳሴ_ማርያም_ትርጓሜ (ማብራሪያ) ለምስጋና ሦስተኛ፣ ለፍጥረት አራተኛ ቀን በሚኾን በዚህ ዕለት ከወትሮ ይልቅ መላእክትን አስከትላ እመቤታችን ትመጣለች፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፤ የብርሃን ምንጻፍ ይነጸፋል፡፡ ከዚያ ላይ ኾናም፡- “ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ ኤፍሬም” ትለዋለች፡፡ እሱም ታጥቆ እጅ ነሥቶ ይቆማል፡፡ ከባረከችው በኋላም ምስጋናዋን “ኵሉ ሠራዊተ ሰማያት ይብሉ ብፅዕት አንቲ…” ብሎ ይጀምራል፡፡ ፩. ኵሉ ሠራዊተ ሰማያት ይብሉ ብፅዕት አንቲ ሰማይ ዳግሚት ዲበ ምድር - ከምድር በላይ ያለሽ ኹለተኛ ሰማይ ሆይ! በሦስቱ ሰማያት (በኢዮር፣ በራማ፣ በኤረር) ያሉ መላእክት ንዕድ ነሽ፤ ክብርት ነሽ ይላሉ፡፡ ማርያም የምሥራቅ ደጅ ናት፤ ከእርሷ የጽድቅ ፀሐይ ክርስቶስ ተኝቷልና፡፡ ማርያም ሙሽራዋ ንጹሕ የሚኾን ንጽሕት የሠርግ ቤት ናት፡፡ በሠርግ ቤት የመርዓዊና የመርዓት (የሙሽራና የሙሽሪት) ተዋሕዶ ይደረግበታል፡፡ በእመቤታችንም እንደ መርዓዊና እንደ መርዓት ተዋሕዶ፤ ትስብእትና መለኮት አንድ ኹነዋልና፡፡ በሠርግ አዝማደ መርዓዊና አዝማደ መርዓት አንድ እንዲኾኑባት በእመቤታችንም ምክንያት ሰውና መላእክት፣ ሰውና እግዚአብሔር፣ ነፍስና ሥጋ፣ ሕዝብና አሕዛብ አንድ ኹነዋልና እመቤታችን ንጽሕት የሠርግ ቤት ናት /ኤፌ.፪፡፲፭/፡፡ አባ ሕርያቆስ “አስተንፈሰ ወአጼነወ ወኢረከበ ዘከማኪ፤ ወሠምረ መዓዛ ዚኣኪ ወአፍቀረ ሥነኪ ወፈነወ ኀቤኪ ወልዶ ዘያፈቅር” እንዲል /ቅዳ.ማር.ቁ.፳፬/ አብ ከሰማይ ኾኖ አየ፤ ነገር ግን እንዳንች ያለ ባያገኝ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለውን ልጁን ሰዶ ካንቺ ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ሰው ኾነ፡፡ ተቀዳሚ ተከታይ ከሌለው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት (ክብርት) በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡ እዚህ ጋር አንዳንድ ወገኖች የሚያነሡትን ጥያቄ መልሰን እንለፍ፡፡ “ልመናስ ከዚያ በኋላ ስንኳን በሷ (ከበቁ በኋላ) በሌሎችም የለባቸውም፡፡ በቀደመ ልመናዋ የምታስምር ስለ ኾነ እንዲህ አለ እንጂ” ስለተባለ ምሥጢሩን ሳይረዱ “ቅዱሳን በአጸደ ነፍስ አያማልዱም” ለማለት የሚጠቅሱት ወገኖች አሉ፡፡ የዚህ ኃይለ ቃል ትርጓሜ ግን ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የዕብራውያንን መልእክት በተረጐመበት በ፲፫ኛው ድርሳኑ ላይ፡- “ጻድቃን ይረክቡ ኵሎ በአሐቲ ተምኔቶሙ በአሐቲ ስእለት - ጻድቃን አንድ ጊዜ በለመኑት ልመና የሚሹትን ኹሉ ያገኛሉ” እንዳለው /ቁ.፻፶፱/ ቅዱሳኑ በአጸደ ሥጋ ሳሉ እግዚአብሔር አንድ ጊዜ “በስምሽ/ህ ለታረዙ ያለበሰ፣ ሕሙማንን የጐበኘ፣ ዝክርሽ/ህን የዘከረ…” እያለ በገባላቸው ቃል ኪዳን መሠረት በስማቸው የዘከረ፣ በስማቸው ሕሙማንን የጐበኘ፣ የመጸወተ እንደሚምርላቸው የሚያስረዳ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- እግዚአብሔር፣ ዓለምን ዳግም በንፍር ውሃ የማያጠፋትና በየዕለቱ ቀስተ ደመናን የምንመለከተው ፡- “ቃል ኪዳኔንም ለእናንተ አቆማለሁ፤ ሥጋ ያለውም ኹሉ ዳግመኛ በጥፋት ውኃ አይጠፋም፤ ምድርንም ለማጥፋት ዳግመኛ የጥፋት ውኃ አይኾንም” ብሎ /ዘፍ.፱፡፲፩/ ለኖኅ አንድ ጊዜ በገባለት ቃል ኪዳን መሠረት እንጂ ኖኅ በየዕለቱ እንዲህ ስለሚለምን አይደለም፡፡ “አይለምንም” ሲባል ግን ክብሩን፣ ልዕልናውን፣ መንፈሳዊ ብቃቱን የሚያስረዳ እንጂ ማማለድ አይችልም ለማለት አይደለም፡፡ እንደውም ይህ ኃይለ ቃል ከማማለድ በላይ የኾነ ክብር እንደተሰጣቸው የሚያመለክት ነው፡፡ ምክንያቱም አንድ ጊዜ ለምኖ በየጊዜው የሚሹትን ማግኘት፤ ዕለት ዕለት እየለመኑ የሚሹትን ከማግኘት በላይ ልዕልናን፣ ክብርን፣ መንፈሳዊ ብቃትን ያሳያልና፡፡ አሁን ቅዱሳንን አማልዱን ስንላቸው አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው ደጋግሞ እንደገለጸው ቃል ኪዳናችሁን አሳስቡልን ስንል ነው /ቅዳ.ማር. ቁ.፻፷፬-፻፸፩ ይመልከቱ/፡፡ ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

  • በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን:: ነሐሴ ፮ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ ወንጌልና ምስባክ 🔊ዲያቆን 📖1 ቆሮ 3÷10-22 🔊ንፍቅ ዲያቆን 📖1 ጴጥ 3፥1-7 🔊ንፍቅ ካህን 📖ግብረ ሐዋርያት 16÷13-19 🔊ምስባክ 📖መዝ 44፥12-14 ✍️ "ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ። ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኩሎሙ አሕዛብ ብዑላነምድር። ኩሉ ክብረ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን" 🔊ትርጉም 👉"የጢሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መንሻ ይዘው ይሰግዱለታል የምድር ባለጠጎች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ ለሐሴቦን ንጉስ ልጅ ሁሉ ክብሯ ነው" 🔊ወንጌል 📖ማር 16÷9... ✍️"ከሳምንቱም በመጀመሪያ ቀን ማልዶ በተነሳ ጊዜ አስቀድሞ ሰባት አጋንንት ላወጣላት ለመግደላዊት ማርያም ታየ......" 🔊ቅዳሴ ዘእግዝእትነ የቴሌግራም #ቻናሉን_ይቀላቀሉ ቤተሰብ ይሁኑን! 👉 https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

  • 11 авг.66из degusamraw

    ✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል" 📖ምሳ 1፥33 የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ! ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ:👇🏽 ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

  • #የማክሰኞ_ውዳሴ_ማርያም_ትርጓሜ ለምስጋና ኹለተኛ፣ ለፍጥረት ሦስተኛ ቀን በሚኾን በዚህ ቀንም እመቤታችን ትመጣለች፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፤ የብርሃን ምንጻፍ ይነጸፋል፡፡ ከዚያ ላይ ኾናም፡- “ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ ኤፍሬም” ትለዋለች፡፡ እርሱም ታጥቆ እጅ ነሥቶ ይቆማል፡፡ ክርክር በዕለተ ሰኑይ አልቋልና “ባርክኒ” ብሎ ተባርኮ “አክሊለ ምክሕነ” ብሎ ምስጋናውን ይጀምራል፡፡ ፩. ዳዊት ምንም ንጉሠ ነገሥት ቢባል የመመኪያችንን ዘውድ ማምጣት አልተቻለውም /፩ኛሳሙ.፲፮፥፲፫/፡፡ ኢያሱ ምንም የስሙ ትርጓሜ መድኃኒት ቢኾንም የደኅንነታችን መጀመሪያ መኾን አልተቻለውም፡፡ ኤልያስም ምንም ንጹሕ፣ ድንግል ቢኾንም የንጽሕናችን መሠረት መኾን አልተቻለውም፡፡ የመመኪያችን ዘውድ፣ የደኅንነታችን መጀመሪያ፣ የንጽሕናችን መሠረት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ የመመኪያችን ዘውድ “አክሊለ ሰማዕት” የሚባል ጌታችን ነው፡፡ የደኅንነታችን መጀመርያ “ጥንተ ሕይወት” የሚባል ጌታችን ነው፡፡ የንጽሕናችን መጀመርያም ኹሉ በእጁ የተጨበጠ፣ ዓለምንም በመዳፉ የያዘ፤ በጠፈር ላይ የሚቀመጥ ፣ ዳግመኛም መሠረቱን ከታች የሚሸከም “መሠረተ ዓለም” የሚባል ጌታችን ነው /ቅዳ.ማር. ቁ.፶፩/፡፡ እርሱም አካላዊ ቃልን በወለደችልን በድንግል ማርያም ተገኘልን፡፡ እኛን ስለማዳን ሰው ኾነ፤ ሰውም ከኾነ በኋላ ግን ፍጹም አምላክ ነው፡፡ ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ እንደ ወለደችው ኹሉ እርሱም አምላክነቱ ሳይለወጥ ሰው ኾነ፡፡ እርሷ “ድንግል ወእም (ድንግልም እናትም)” ስትባል እንደምትኖር ኹሉ እርሱም “አምላክ ወሰብእ (ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው)” ሲባል ይኖራል /ሃይ.አበ.፷፯፡፯/፡፡ ተፈትሖ ሳያገኛት (ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ) እንደምን እንደወለደችው ግን የማይመረመር አንድም ሊነገር የማይችል፣ ከኅሊናት ኹሉ የሚያልፍ ድንቅ ነው፡፡ በማይመረመር ግብር ከወለድሽው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡ ፪. “ቃል ሥጋ ኾነ” እንዲል በእርሱ ፈቃድ /ዮሐ.፩፡፲፬/፣ “ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና” እንዲል በአባቱ ፈቃድ /ዮሐ.፫፡፲፮/፣ “በመንፈስ ቅዱስ በኀይልም እንደ ቀባው” እንዲልም /ሐዋ.፲፡፴፰/ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ሰው ኾኖ አዳነን፡፡ ሊቁ እንዲህ ማለቱ “ወልድ ያለ ፈቃዱ ሰው ኾነ” የሚሉ መናፍቃን ስላሉ ነው፡፡ ሌሎች ሊቃውንትም፡- “የእግዚአብሔር ልጅ ያለ ፈቃዱ ሰው እንደ ኾነ የሚያምን፤ የሚያስተምር፤ ወይም የአብ ፈቃድ ሌላ ነው፤ የወልድ ፈቃድ ሌላ ነው፤ የመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ ሌላ ነው የሚል ቢኖር፤ ፈቃዳቸው አንድ፤ መንግሥታቸውም አንድ እንደኾነ የማያምን ሰው ቢኖር ውጉዝ ይኹን” ብለው አስተምረዋል /ሃይ.አበ.፻፳፫፡፪/፡፡ በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ፍጽምት የምትኾኚ እመቤታችን ሆይ! በድንግልና ጸንተሽ ብትገኚ ላንቺ የተሰጠሸ ጸጋ ፍጹም ነው፡፡ እግዚአብሔር ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ካንቺ ጋራ አንድ ባሕርይ ቢኾን አንድም በጸጋ ቢያድርብሽ ባለሟልነትን አግኝተሸልና ለአንቺ የተሰጠ ክብር ፍጹም ነው፡፡ ይህ ከቃላት በላይ የሚያልፈው ባለሟልነቷ ቅዱስ ባስልዮስ ከሌሎች ቅዱሳን ጋር እያነጻጻረ ሲያብራራው፡- “የዚህ ዓለም ነገር ኹሉ አይመጥናትምና የሚመጥናትን ምን ዓይነት ምስጋና እናቅርብላት? ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ቅዱሳን ሲናገር ዓለም አልተገባቸውም /ዕብ.፲፩፡፴፰/ ካላቸው ከከዋክብት በላይ ኾና እንደምታበራው ፀሐይ ለኾነችው ለአምላክ እናትማ ምን ልንል እንችል ይኾን?... ምን ምሥጢር እንደተከናወነ ተመልከት፤ ኅሊናን አእምሮን የሚያልፍ ነገር እንደኾነም አስተውል፡፡ ታድያ የአምላክ እናት ታላቅነት እንደምን ኹሉም ሰው አይናገር? ማንስ ነው ከቅዱሳን ኹሉ በላይ እንደኾነች ያላስተዋለ? እግዚአብሔር ለአገልጋዮቹ የሚልቅ ጸጋን ከሰጠና የሚነኩት ኹሉ ሰው ከበሽታው ከተፈወሰ፣ ጥላቸው ያረፈበት ተአምር ከተፈጸመለት፣ ጴጥሮስ በጥላው ካዳነ /ሐዋ.፭፡፲፭/፣ የጳውሎስ የልብሱ ዕራፊ መናፍስትን ካወጣ /ሐዋ.፲፱፡፲፩/ ለእናቱማ ምን ዐይነት ሥልጣንና ኀይል ተሰጥቷት ይኾን? በምን ዓይነትስ ሥጦታ አስጊጧት ይኾን? ጴጥሮስ፡- ክርስቶስ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ስላለው ብፁዕ ነህ ከተባለና የመንግሥተ ሰማያት ቁልፍ ከተሰጠው /ማቴ.፲፮፡፲፮-፲፱/ እርሷማ ከኹሉም ይልቅ እንዴት ብፅዕት አትኾን? /ሉቃ.፩፡፵፭/ ጳውሎስ ታላቅ ክብር ያለውን የክርስቶስን ስም በመሸከሙ ምርጥ ዕቃ ከተባለ /ሐዋ.፱፡፲፭/ የአምላክ እናትማ የምእመናን ምግብ የኾነ መናውን ሳይኾን የሕይወት ሰማያዊ እንጀራን ያስገኘች እርሷ ምን ዓይነት ልዩ ዕቃ ትኾን? … ነገር ግን ስለ እርሷ ብዙ እናገራለሁ ብዬ ስለ ክብሯ ጥቂት በመናገር ራሴን በኀፍረት ውስጥ እንዳልጨምር እፈራለኁ፡፡ ስለዚህ ከአሁን ወዲህ የንግግሬን መልሕቅ ስቤ በዝምታ ወደቤ ላይ ማረፍን መርጫለሁ” ይላል /መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ፣ ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን፣ ገጽ ፺-፺፩ ይመልከቱ/፡፡ ከምድር እስከ ሰማይ ደርሳ፣ በላይዋ ዙፋን ተነጽፎባት በዚያ ላይ ንጉሥ ተቀምጦባት፣ መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ያያት የወርቅ መሰላል አንቺ ነሽ /ዘፍ.፳፰፡፲፰-፲፱/፡፡ መተርጕማኑ ይህ ምን ማለት እንደኾነ ሲያብራሩ፡- “ከምድር እስከ ሰማይ መድረሷ የልዕልናዋ፣ በላይዋ ላይ ዙፋን ተነጽፎባት ንጉሥም ተቀምጦባት ማየቱ ፱ ወር ከ፭ ቀን በማኅፀኗ ለመሸከሟ፣ መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት ማየቱ ደግሞ ጌታችን ከእመቤታችን ሰው ከመኾኑ አስቀድሞ ሰው የጸለየውን ጸሎት ያቀረበውን መሥዋዕት ለማሳረግ አይወጡም አይወርዱም ነበር፤ ጌታችን ከእመቤታችን ሰው ከኾነ በኋላ ግን ለተልእኮ የሚወጡ የሚወርዱ ኾነዋልና ሲል ነው” ይላሉ /ሉቃ.፪፡፲፬፣ ሐዋ.፲፡፫-፬፣ የኦሪት ዘልደትን ትርጓሜ ይመልከቱ/፡፡ ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ በአምሳለ ንጉሥ ካየው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡ ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

  • "ኦ ማርያም በእንተዝ ናፈቅረኪ" "ማርያም ሆይ እንወድሻልለን"        ቅዱስ አባ ሕርያቆስ በአዳም ዘር መካከል በእሾህ ውስጥ እንዳጌጠች ጽጌረዳ በማዕዛ ቅድስና ተጠብቃ የንጉስ ክርስቶስ አማናዊት መቅደስ በመሆን ዓለም ሁሉ የሚድንበትን እውነተኛውን መብልና መጠጥ ስላስገኘችልን ዛሬም እንላታለን እንደ ቅዱስ  አባ ሕርያቆስ " ኦ ማርያም በእንተዝ ናፈቅረኪ ወናዐብየኪ እስመ ወለኪ ለነ መብልዐ ጽድቅ ዘበአማን ወስቴ ሕይወት ዘበአማን" የቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ! ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

  • #ሕፃናትና_እኛ_ስንነፃፀር እስኪ ንገረኝ ! ሕፃናት ቤት እንሥራ ብለው የሚጫወቱት ጨዋታና እኛ በዚህ ዓለም የሚያማምሩ ቤቶችን ስንሠራ ልዩነታችን ምንድን ነው? ሕፃናት እራት እናሰናዳ ብለው በሚጫወቱት ጨዋታና እኛ በምናዘጋጀው ጣፋጭ ማዕድ ልዩነቱ ምንድን ነው? ምንም ምን ልዩነት የለውም፡፡ እንዲያውም እኛ እንደዚህ በማድረጋችን በእኛ ላይ የሚያመጣው ከፍ ያለ ቅጣት (ኵነኔ) አለው፤ [የሕፃናቱ ግን የለውም፡፡] ይህን የምናደርገው ነገር ፍጹም የጎስቋላነት ተግባር እንደ ኾነ ያልተገነዘብነው እንደ ኾነም ይህ ምንም አያስደንቅም፡፡ ገና እስከ አሁን ድረስ ዐዋቂ ሰዎች አልኾንንምና፡፡ ያን ጊዜ ግን ዐዋቂዎች ስንኾን ግን [ረብ ጥቅም የለውም እንጂ] አሁን የምናደርገው ተግባር ኹሉ የሕፃን ሥራ እንደ ኾነ እናውቃለንና፡፡ ሕፃናት እያለን ስናደርጋቸው የነበሩት ተግባራት ዐዋቂዎች ስንኾን እንንቃቸዋለንና፡፡ ሕፃናት እያለን ግን እነዚህን ልናገኛቸው ብለን አስበን የምንጨነቅባቸው የነበሩ ናቸው፡፡ ሕፃናት ኾነን ገልና ሸክላ ስንሰበስብና ካብ ስንከምር ረጃጅም አጥሮችን ከሚሠሩ ሰዎች እንደማንተናነስ አድርገን እናስብ ነበር፡፡ ነገር ግን እነዚያ ያቆምናቸው የድንጋይ ክምሮች ወዲያውና እዚያው ፈራርሰው የሚወድቁ ነበሩ፤ ጸንተው ቢቆሙም እንኳን የሚሰጡን ረብ አልነበረም፡፡ አሁንም እኛ በዚህ ዓለም የምንሠራቸው የሚያማምሩ ቤቶች ያው እንደ እነዚህ የሕፃንነታችን ጊዜ ካቦች ናቸው፡፡ አሁን የምንሠራቸው ቤቶች ሀገሩ በሰማይ የኾነውን ሰው ተቀብለው ማኖር የሚቻላቸው አይደሉምና፤ እነርሱ ተቀብለው ማኖር አለመቻላቸው ብቻም ሳይኾን በላይ በሰማይ ሀገሩ የኾነ ሰውም በእነዚህ ቤቶች መኖርን የሚሻ አይደለምና፡፡ ሕፃናት የከመሩአቸው ካቦች እኛ በእግራችን ነካ ብናደርጋቸው የሚፈራርሱ ናቸው፡፡ ልክ እንደዚሁ በመንፈስ ልዑል የኾነ ሰውም እነዚህን እኛ የምንደነቅባቸው ቤቶች የሚመለከታቸው እንደዚህ ነው፡፡ ሕፃናቱ ቤት ብለው የከመሩአቸው ካቦች በእግራችን ነካ ብናደርግባቸውና ብናፈርስባቸው ስቅስቅ ብለው ሲያለቅሱ ተመልክተን [የማያስለቅስ ያስለቅሳቸዋል ብለን] እኛ እንደምንስቅ ኹሉ፥ እነዚህ በመንፈስ ልዑላን የኾኑ ሰዎችም እኛ በእነዚህ ቤቶች መፍረስ ስንተክዝ ተመልክተው [በማያሳያዝን ያዝናሉ በማያስተክዝም ይተክዛሉ ብለው] ይስቃሉ፡፡ እንዲያውም መሳቅ ብቻም ሳይኾን ያለቅሳሉ፡፡ ምክንያቱም፡- [አንደኛ] ርኅሩኀን ናቸው፤ [ኹለተኛ ደግሞ] እኛ ከእነዚህ ቤቶች ጋር ይህን ያህል በመጣበቃችን ምክንያት የሚመጣብን ጉዳት ብዙ የብዙም ብዙ እንደ ኾነ ያውቃሉና ያለቅሳሉ፡፡ ስለዚህ ዐዋቂዎች እንኹን፡፡ እስከ መቼ ድረስ ነው በምድር ላይ የምንንፏቀቀው? እስከ መቼ ድረስ ነው በድንጋዮችና በምድራዊ መኖሪያ ቤቶች ራሳችንን የምናስታብየው? እስከ መቼ ድረስ ነው ዕቃ ዕቃ የምንጫወተው? (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ የማቴዎስ ወንጌል፣ ድርሳን 23፥10) ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

  • 10 авг.81из degusamraw

    ✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል" 📖ምሳ 1፥33 የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ! ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ:👇🏽 ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

  • በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን:: ነሐሴ ፭ በዕለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልእክታት ወንጌልና ምስባክ 🔊ዲያቆን 📖2ኛ ቆሮ 12፥10-17 ✍️"ስለዚህም ስለ ክርስቶስ መከራ መቀበልን መሰደብን መጨነቅን መሰደድን መቸገርንም ወደድሁ መከራ በተቀበልሁ ጊዜ ወዲያውኑ እበረታለሁና፤.......እኔ አልከበድሁባችሁም ነገር ግን ምክር ዐዋቂ ሆኜ በመጠበብ ወሰድኋችሁ" 🔊ንፍቅ ዲያቆን 📖1ኛ ዩሐ 5፥14.... ✍️"በእግዚአብሔር ዘንድ ያለችን መወደድ ይህች ናት በስሙ ከእርሱ ዘንድ የምንለምነውን ይሰማናልና፤.......ልጆቼ ሆይ ጣዖታትን ከማምለክ ራሳችሁን ጠብቁ" 🔊ንፍቅ ካህን 📖ግብረ ሐዋርያት 15፥1-13 ✍️"ከይሁዳ ሀገርም የወረዱ ሰዎች እንደ ሙሴ ሕግ ካልተገዘራችሁ ልትድኑ አትችሉም እያሉ ወንድሞችን ያስተምሩ ነበር፤......ያንጊዜም ሕዝቡ ሁሉ ጸጥ ብለው እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያደረገላቸውን ተአምራትና ድንቅ ሥራ ሁሉ ሲናገሩ ጳውሎስንና በርናባስን አዳመጡአቸው" 🔊ምስባክ 📖መዝ 17፥43-44 ✍️"ወትሠይመኒ ውስተ ርእሰ ሕዝብ ሕዝብ ዘኢየአምር ተቀንየ ሊተ ውስተ ምስማዐ እዝን ተሰጥዉኒ" 🔊ትርጉም 👉"የአሕዛብም ራስ አድርገህ ትሾመኛለህ የማላውቀው ሕዝብም ይገዛኛል በጆሮ ሰምተው ተገዙልኝ" 🔊ወንጌል 📖ሉቃስ 15፥1-11 ✍️"ቀራጮችና ኀጢኣተኞችም ሊሰሙት ወደ እርሱ ይቀርቡ ነበር፤........እንዲሁ ንስሓ ስለሚገባ ስለ አንድ ኀጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት በሰማያት ደስታ ይሆናል" 🔊ቅዳሴ ዘእግዝእትነ 👉 https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

  • #ተወዳጁ_ልጅሽ_እንዲመግበኝ_ትለምኝልኝ_ዘንድ_እማጸንሻለሁ እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። የመድኃኒት እናት ሆይ በመዓልትም በሌሊትም አማላጅ ትሆኝኝ ዘንድ እሰግድልሻለሁ። እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ከእርሱ የሚገኘውን ኃይልን ይሰጠኝ ዘንድ ከአንቺ ወደ ተወለደው ልጂሽ እንድትለምኝልኝ እማጸናለሁ። በመወለዱ ድኅነት የተገባሽ ሆነሻልና። በሔዋን ውድቀት ሆነ። አብ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ገብርኤል አማካኝነት ሰላምን የላከልሽ እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። ሰላምታን ሰጠሽ ሰገደልሽም። ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና ሰላምታ ይገባሻል። እነሆ ትጸንሻለሽ ልጅም ትወልጃለሽ፣ ስሙንም አማኑኤል ትይዋለሽ። የልዑል ኃይል ይጸልልሻል፤ ከአንቺ የሚወለደውም ቅዱስ ነው፤ እርሱም የልዑል ልጅ ይባላል አለሽ። በተቀደሰው ስሙ ኅሊናዬን ልቡናዬን እንዲቀድስ ትለምኝው ዘንድ እማጸንሻለሁ። ንጽሕት ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። የሕይወት ቃል ከአንቺ ሰው ይሆን ዘንድ በሥጋ ከአንቺ ይወለድ ዘንድ የተገባሽ የመድኃኒት እናት እመቤታችን ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። ከአንቺ በመዋሐዱም እኛ ዳንን። እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። በእናታቸው ማሕፀን ሕፃናትን የሚስላቸው ከአባቱ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም ሁሉን የፈጠረው በማሕፀንሽ የተቀረጸብሽ የብርሃን እናት ሆይ እሰግድልሻለሁ። ረቂቅ ድንቅ ምሥጢርን ዓለምንም ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣውን እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እለምንሻለሁ። በመንፈሳዊ ልደት ይወልደኝ ዘንድ ወደ እርሱ ዓለምና አዳኝ ወደ ሆነች ዕውቀት ከፍ ያደርገኝ ዘንድ ወደ እርሱ እንድትለምኝልኝ እለምንሻለሁ፣ አማጸንሻለሁ። የሕይወት መገኛ የነገሥታት ንጉሥ የባለሥልጣናቱ ባለሥልጣን የአምላኮችን አምላክ በበረት ያስተኛሽው እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። አዳኝ ስለሆነው ስለስምሽ እንዲረዳኝ ትለምኝልኝ ዘንድም ወደ አንቺ እለምናለሁ፤ እማልዳለሁም። በማየቱ አዳምንና ከእርሱ ጋር ያሉትን ሁሉ ነጻ ያወጣውን በክንድሽ የታቀፍሽው እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። በረቂቅ መመልከቱ እንዲመግበኝ ከሰይጣን መሰናክልም እንዲያድነኝ ትለምኝልኝ ዘንድ እለምንሻለሁ፤ እማጸንሽማለሁ። ዓለማትን ሁሉ ለሚመግበው ጡትሽን ያጠባሽው የመድኃኒት እናት እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ፤ የሰማይ ኃይላት የሚመገቡትም ከእርሱ ነው። ነፍሴን በፈቃዱ ከጸጋው ይመግባት ዘንድ ወደ እርሱ እንድትለምኝልኝ እማጸንሻለሁ። እመቤቴ ድግል ማርያም ሆይ ተወዳጁ ልጅሽ እንደ ፍጹም ፈቃዱ እንዲመግበኝ በየጊዜው በየሰዐቱ አማላጅ ሁኚኝ። ይህችም ወደ እርሱ የምትለምኝውን ልመና የተመላች መጽሐፍ ናት ። የለመንሁትን ሁሉ እርሱ ያደርግልሻልና። ኃጢአቴን ይቅር ይለኝ ዘንድ ወደ እርሱ እንድትለምኝልኝ እማጸንሻለሁ። ሰላምን ስለሰጠሽ ስለ አብ ከአንቺ ስለተወለደው አንቺንም ስለተዋሐደው ከአንቺም ሰው ስለሆነው ስለወልድ፣ ስለቀደሰሽ፣ ከሦስቱ ቅዱስ ለአንዱ ማደሪያ ለመሆን እስከሚገባሽ ድረስ ስላነጻሽ ስለመንፈስቅዱስም እለምንሻለሁ። አገልጋይሽን ተወዳጁ ልጅሽ እንዲመግበኝ ትለምኝልኝ ዘንድ እማጸንሻለሁ። ለዘለዓለሙ አሜን። #ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሳርያ! ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

  • 10 авг.93из degusamraw

    ✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል" 📖ምሳ 1፥33 የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ! ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ:👇🏽 ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

  • በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን:: ነሐሴ   ፬   በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ ወንጌልና ምስባክ 🔊ዲያቆን 📖ሮሜ 1÷3-18.... 🔊ንፍቅ ደያቆን 📖1ኛ ጴጥ 3፥10-18 🔊ንፍቅ ካህን 📖ግብረ ሐዋርያት 17÷23-28 🔊ምስባክ 📖መዝ 20፥1-2 ✍️"እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሣሕ ንጉሥ ወብዙኃ ይትሐሠይ በአድኅኖትከ ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ"                                     🔊ትርጉም 👉"አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል በማዳንህ እጅግ ሐሴትን ያደረጋል የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው"                               🔊ወንጌል 📖ሉቃ  14÷31.... ✍️"ይህ ሰው ሊሠራ ጀመሮ ሊደመድመውም ቢያቅተው ያዮት ሁሉ ወይም ሌላውውን ንጉስ በጦርነት ሊጋጠም የሚሄድ ከሁለት እልፍጋር የሚመጣበትን.............." 🔊ቅዳሴ      ዘእግዝእትነ              👉 https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

  • #ፍቅር_ከሌለ_ሁሉ_ጨለማ_ይሆናል "የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ቤት መራቅ ሲጀምር ፍቅር ከእርሱ ትርቃለች ከሚያየውም ነገር ጋር ሁሉ  ይጋጫል። ከሰዎች ጋር ብቻ አይደለም ግጭቱ ከተፈጥሮ ጋር፣ ከአካባቢው ጋር፣ ከማህበረሠቡ ጋርና ከራሱ ጋር ጭምር እንጂ፡፡ ፍቅር ከሌለ ባዶነት ነው፡፡ ፍቅር ከሌለ የውስጥ ሰላም አይገኝም፡፡ ፍቅር ከሌለ ሁሉ ጨለማ ይሆናል.....ስለዚህ የሰው ልጅ ሆይ ሙሉ ፍቅርን እንድታገኝ ሁሌም እግሮችህን ወደ እግዚአብሔር ቤት ምራቸው ያኔ ፍፁም ሰላም ያኔ ፍፁም ፍቅር ታገኛለህ ያኔ ባዶ የሆነው ሙሉ ጨለማውም ብርሃን ይሆንልሃል!" #ቻናሉን_ይቀላቀሉ ቤተሰብ ይሁኑን! 👇👇👇 https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

የደጉ ሳምራዊ መልካምነት® — tgindex