Bright Minds Academy☀️
СтатистикаIn our channel : ✅ entrance exam ✅extreme book & referance book ✅Textbook ( 9-12 ) ✅Teachers Guide (9-12) ✅worksheet ( 9-12) ✅students info and news 👇👇👇👇👇👇👇 @Ethio_Students_only For comment @EthioStudentsOnly_bot
- Последний пост
- 11 окт. 2025 г.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የኮሌጅ መግቢያ ውጤት አልመጣልህምና ምን ? ....... በስሙ ከአንድ ሺህ በላይ የፈጠራ ስራዎችን ያስመዘገበው the father of modern innovation በሚል ስም የሚታወቀው ቶማስ ኤድሰን ፡ አደለም ዩኒቨርስቲ ፡ አደለም ኮሌጅ ፡ በህይወቱ የትምህርት ቤት ደጃፍ ረግጦ አያውቅም ። አምፖል ፡ የኤሌትሪክ ጄኔሬተር ፡ ተንቀሳቃሽ ምስል ካሜራ እና ሌሎቹም የፈጠራ ስራዎች የበሩለት እናቱ ቤት ውስጥ ባስቆጠረችው መሰረታዊ ትምህርት በመጠቀም በንባብ አዳብሮ ባገኘው እውቀት ነው ። ...... ሳይማሩ አለምን መለወጥ የቻሉት እነዚህ ብቻ አይደሉም የማይክሮሶፍቱ መስራች ቢልጌትስ ... የአፕል መስራቹ ስቲቭ ጆብስም ፡ ይህን የምንጠቀምበትን ፌስቡክ የሰራልን ማርክ ዙከርበርግ ዲግሪ የሚባል ነገር አያውቃቸውም ። .... የፎርድ ካምፓኒ መስራች ሄነሪ ፎርድ በ16 አመቱ ትምህርቱን ያቋረጠ ሰው ነበር ። ሪቻርድ ብራንሰን ፡ ኦፕራ ዊንፍሬ የኮሌጅ ሽፍታ ናቸው ። ... እዚህ ላይ መማርን ፡ ተምሮ ለኮሌጅ መብቃትን የምናበረታታው ነገር ቢሆንም ፡ የስኬት ዳር ፡ የብቃት እና የመቻል ብቸኛ መለኪያ ግን አይደለም ። ... በዘንድሮው የማትሪክ ውጤት አልመጣልህም ? በቃ ያንተ መክሊት እዛ አይደለም ። እና የተዘጋብህ የኮሌጅ በር ብቻ እንጂ ሺህ የስኬት መንገዶች ከፊትህ ተዘርግተው የሚጠብቁትን አንተን ነው ። ... ውጤት ስላላመጣህ ተናደሀል ? ይህንን ንዴት ወደ እልህ ቀይረውና ፡ ወደውስጥህ እይ ፡ መክሊቴ ምንድነው ? አዲስ ነገር መፍጠር ? የተፈጠረን ነገር ማሻሻል ነው ? ወይስ ንግድ ወይስ ምን ብትሰራ የሚሳካልህ ይመስልሀል ፡ ይህን አጥና ። .... ደሞ ስልክ ይዘህ መፍትሄ ይጠፋሀል እንዴ ? ስልክህን ክፈት ፡ ስልክህ ኮሌጅ ነው ። እንደዝንባሌህ የፈለከውን ነገር መማር የፈጠራ ስራዎችን እየየህ አዶፕት ለማድረግ ሞክር ፡ አእምሮህን በይቻላል ስሜት ሙላው ፡ እንጂ አትቆዝም ።
በ 5 ዓመቱ አባቱ ሞተ በ16 አመቱ ትምህርቱን አቋረጠ። በ17 ዓመቱ አራት ስራዎችን አጥቷል። በ18 ዓመቱ አገባ ከ18 እስከ 22 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ በውትድርና አግልግሎት ውስጥ ተሳትፏል፤ ቀጥሎ የባቡር አገልግሎት ሠርቷል በዚህም አልተሳካለትም። ለሕግ ፋኩልቲ አመልክቶ ማመልከቻውን ውድቅ ተደርጓል። የኢንሹራንስ ኩባንያ ሻጭ ሆነ እና እንደገና አልተሳካም። በ19 ዓመቱ አባት ሆነ። በ20 ዓመቱ ሚስቱ ትታው ልጃቸውን ወሰደችበት!እና በትንሽ ካፌ ውስጥ ሰሃን አጣቢ ሆነ። ሴት ልጁን ከሚስቱ ለመውሰድ ያደረገው ሙከራ አልተሳካለትም እና በመጨረሻም ሚስቱን ወደ ቤት እንድትመለስ አሳመነ። በ65 ዓመቱ የጡረታ ዕድሜ ላይ ለመድረስ ለጡረታ ተላከ በጡረታ የመጀመሪያ ቀን ከመንግስት 105 ዶላር ቼክ ተቀበለ። ከዚህ በኋላ መኖር እንደማይገባው ስላየ ራሱን ለማጥፋት ወሰነ። ምክንያቱም ብዙ ውድቀቶችን አስተናግዷል የመጨረሻ ቃሉን ሊጽፍ ከዛፉ ስር ተቀምጦ ነበር፤ ነገር ግን በህይወቱ ያከናወናቸውን ነገሮች መጻፍ ጀመረ። እናም ጥሩ የሆነበት አንድ ነገር እንዳለ አወቀ እሱም "ምግብ ማብሰል" ነበር። 95 ዶላር ተበድሮ ድንች እና ዶሮ ገዛ በራሱ የፈጠራ ዘዴ ተጠቅሞ ከቤት ወደ ቤት ሄዶ ለኬንታኪ ጎረቤቶቹ መሸጥ ተያያዘው። በ88 አመቱ የኬንታኪ ብስል ዶሮ (KFC) ግዛት መስራች ቢሊየነር ሆነ። በህይወት ውስጥ ተስፋ መቁረጥ አለ፤ ግን ደግሞ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ህይወት የለም!። አየየ .✍️
የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ሆነ። በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ መደረጉን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። ተማሪዎች ከአሁን ሰዓት ጀምሮ፦ Website: https://student.ethernet.edu.et Telegram bot: @moestudentbot አማራጮች ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል። የRemedial ፕሮግራም ምደባ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። #MoE @Ethio_Students_only
የሪሜዲያል መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ። ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን በተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት መስኮች ከ49.5% በታች ያስመዘገቡ ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የRemedial ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆናቸውን አሳውቋል። 1. በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 33% ከመቶ እና ከዚያ የተቆረጠ መሆኑን። 2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥቡን ያሟሉ ብቻ ይሆናሉ። የመቁረጫ ነጥብ ፦ ➡️ የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 216 ➡️ የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 204 ➡️ ታዳጊ ክልል እና አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 198 ➡️ የማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 198 ➡️ ማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ዓይነስውራን ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 165 #MoE @Ethio_Students_only
"የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ እያለሁ ሁለት ቁልፍ ፈተናዎች ነበሩብኝ ሆኖም ሁለቱንም ወደኩ….የመካከለኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁም ፈተና ከመውደቅ አልዳንኩም ለውድቀት ሶስት ጊዜ እጄን ሰጠሁ፡፡ ኮሌጅ ለመግባት ፅኑ ፍላጎት ቢኖረኝም መግቢያ ፈተናዎቹን ሁለቴ ወስጄ በሽንፈት ተመለስኩ፡፡ የሚገርመው ደግሞ ያመጣሁት ውጤት አሳዛኝ ነበር። መውደቅ አንድ ነገር ቢሆንም በሂሳብ ትምህርት ከ120 ነጥብ 1 ማምጣት ግን በርግጥም ከባድ ነበር፡፡ ውድቀቴ ይቀጥላል…ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ 10 ጊዜ አመልክቼ ውድቅ ተደርጎብኛል፡፡ ከኮሌጅ ተመርቄ ከወጣሁ በኋላ ስራ የመቀጠር ፅኑ ፍላጎት ቢኖረኝም 30 ስራ እድሎች በተከታታይ ብሞክርም አልተሳካልኝም፡፡ KFC ስራ አወጣ ተደሰትኩ በዚህኛው ግን ስራ ለማግኘት የማደርገው ጥረት በድል እንደሚደመደም አስቤ ተራመድኩ፡፡ ብዙ ፈተናዎችን አልፈን ለስራ የመጣነው 24 ነን፡፡ 23 ሰው አለፈ በሚደንቅ ሁኔታ የወደቀው አንዱ ሰው እኔ ነበርኩ፡፡" ይህንን ያለው ጃክ ማ ነው። ይህ ሰው ከዚህ ሁሉ ውድቀት በኋላ ቻይናን የቀየረ አማዝኦንን መሰል የአሜሪካ ካምፓኒዎችን የሚገዳዳረውን አሊባባን የመሰረተ እና እዚህ ያደረሰ ስኬታማ ሰው ነው፡፡ "በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ! ዛሬ ከባድ ነው…ነገም የከፋ ሊሆን ይችላል… ከነገወዲያ ግን መልካም ይሆናል!!!" – Jack Ma👏
ውጤት መታየት ጀምሯል👏👏👏👏👏 በኔትዎርክ መጨናነቅ ምክንያት ላይሰራላችሁ ስለምችል ተረጋግታችሁ ሞክሩ መልካም እድል 🫶 @Ethio_Students_only
#ኃይማኖት_ዮሐንስ #ሲምቦ_ደረጄ👏 በ2017 ዓ.ም በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ሴት ተማሪዎች ኃይማኖት ዮሐንስ እና ሲምቦ ደረጄ ናቸው። ኃይማኖት ዮሐንስ ውብሸት የብስራተ ገብርኤል ትምህርት ቤት ተማሪ ስትሆን በተፈጥሮ ሳንይንስ 579 አምጥታለች። ሲምቦ ደረጄ አያና የሴንይት ጆን ካቶሊክ ትምህርት ቤት ተማሪ ስትሆን በማኅበራዊ ሳይንስ 548 አስመዝግባለች። @Ethio_Students_only
без подписи
#ካሊድ_በሽር👏 የዶዶላ ኢፈ ቦሩ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ የሆነው ካሊድ በሽር በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 591 በማምጣት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል፡፡ የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ይፋ ባደረገው መረጃ ተማሪ ካሊድ በሽር ፦ - እንግሊዘኛ 96፣ - ሒሳብ 100፣ - ፊዚክስ 100 - ኬሚስትሪ 98፣ - ባዮሎጂ 99፣ - አፕቲትዩድ 98 አምጥቷል፡፡ የዶዶላ ኢፈ ቦሩ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር ደቱ ዲቦ " ተማሪ ካሊድ በሽር በትምህርቱ በጣም ጎበዝ፣ ጥሩ ሥነ ምግባር ያለው እና አርአያ የሆነ ተማሪ ነው " ሲሉ ለኤፍ ኤም ሲ ተናግረዋል። @Ethio_Students_only
#Update ውጤት በምን ማየት ይቻላል ? የ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች የሚያገኙበት አድራሻዎች ይፋ ሆኑ፡፡ የ2017 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተፈተኑ ተፈታኞች በሚከተሉት አድራሻዎች ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ፡፡ ዌብ ሳይትና ቴሌግራም አድራሻ የሚጠቀሙ ተፈታኞች ጊዜያዊ ሰርቲፊኬታቸውን ወዲያውኑ አውርደው (download አድርገው) መውሰድና መጠቀም ይችላሉ፡፡ አድራሻዎቹ፡ 1. ዌብ ሳይት፡ https://result.eaes.et 2. ቴሌገራም፡ https://t.me/EAESbot 3. አጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS)፡ 6284 (የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት) @Ethio_Students_only
ከፍተኛውን ውጤት ያስመዘገበው ተማሪ 👏 ካሊድ በሺር ከዶዶላ ኢፋ ቦሩ አዳሪ ትምህርት ቤት በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ከተፈተኑ ከፍተኛውን 591/600 ነጥብ ያመጣው ተማሪ @Ethio_Students_only
без подписи
без подписи
#MoE #መሉመግለጫው የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ የተዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ሙሉ ይዘት ከላይ ተያይዟል። #TikvahEthiopia @Ethio_Students_only
ውጤት መቼ ይለቀቃል ? " ውጤት እስከ ነገ 6:00 ሰዓት ይለቀቃል " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ @Ethio_Students_only
ከፍተኛ ውጤት የት ተመዘገበ ? በተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 ➡️ 591 ወንድ ተማሪ ከዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት ➡️ 579 ሴት ተማሪ ከብስራተ ገብርኤል ትምህርት ቤት በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 562 ከአምቦ ቦርዲግ ትምህርት ቤት ከሴት 548 ከሴንት ጆሴፍ ትምህርት ቤት። @Ethio_Students_only
በሀገር ደረጃ 8.4 በመቶ ተማሪ 50% በላይ በማምጣት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን አልፏል። ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች 48,929 ተማሪዎች አልፈዋል https://t.me/Ethio_Students_only
Breaking news የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይደረጋል። የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ እንደሚደረግ አሳውቋል። የፈተና ውጤቱን አስመልክቶ ነገ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ መግለጫ ይሰጣል። #MoE https://t.me/Ethio_Students_only https://t.me/Ethio_Students_only
без подписи
#AAU #ScholarshipOpportunity አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ትምህርት ዘመን የሚተገበር የተቋሙ ፕሬዝዳንት ነጻ የትምህርት ዕድል (Presidential Scholarship Program) ይፋ አድርጓል፡፡ ይህ ዕድል በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለወሰዱ እና የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም ለመግባት የሚያስችል ውጤት ላመጡ የላቁ 200 ተማሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡ ነጻ የትምህርት ዕድሉ ሙሉ የትምህርት ክፍያ ሸፋን እና ጥሩ የሚባል የማበረታቻ ጥቅል ያስገኛል፡፡ በእድሉ ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ተጠቃሚ ለመሆን በየሴሚስተሩ አጠቃላይ ውጤት (CGPA) 3.5 እና በላይ ማምጣት ያስፈልጋል፡፡ የPresidential Scholarship Program ተመራቂዎች የድኅረ ምረቃ ትምህርታቸውን ወዲያው እንዲቀጥሉ እና ነጻ የማስተርስ እና የሦስተኛ ዲግሪ እንዲማሩ ዕድል ይሰጣል፡፡ ለማመልከት 👇 https://admission.aau.edu.et/UGAnnouncements የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው 👇 መስከረም 09/2018 ዓ.ም (ተማሪዎች በነጻ የትምህርት ዕድሉ ተጠቃሚ የሚሆኑባቸው የትምህርት ኮሌጆች ክፍፍል ከላይ ተያይዟል።) ©tikvahuniversity https://t.me/Ethio_Students_only https://t.me/Ethio_Students_only