tgindex
Ethiopian Students Network 🇪🇹( ESN)

Ethiopian Students Network 🇪🇹( ESN)

Статистика
@EthiopianStudentsTMанглийский

A space for every Ethiopian student — elementary, highschool, or university. Discussion: @EthioStudentsChat

Последний пост
15 февр.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
40
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
5 838
+16 за 3 дн.
Сутки
+6
+0,10%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
4 344
40 постов
Вовлечённость
74,4%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 40
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 15 февр.3 765163

    #Haramaya_University #Biomedical_Engineering 🔬 Haramaya University has announced the opening of a new department, "Biomedical Engineering." @EthiopianStudentsTM @EthiopianStudentsTM

  • 11 февр.3 69171

    #NationalExam ትምህርት ሚኒስቴር ፤ " የዚህ አመት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መቶ በመቶ በበይነ መረብ ይሰጣል " አለ። በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ2018 የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና መቶ በመቶ በበይነ መረብ ለመስጠት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ " በዚህ ዓመት የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና መቶ በመቶ በበይነ መረብ ይሰጣል " ሲሉ ተናግረዋል። ይህን ያሉት በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የግማሽ ዓመት አፈፃፀም መድረክ ላይ ተገኝተው ነው። ባለፉት ሁለት ዓመታት ፈተናው በወረቀትና በበይነ መረብ ሲሰጥ እንደነበር አንስተው በዚህ ዓመት የሚሰጠውን ማጠናቀቂያ ፈተና ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ ለመስጠት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ጠቁመዋል። ለዚህም የተለያዩ ግብዓቶች ለክልሎች ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው በፈተና ጣቢያዎች በቂ የኢንተርኔት አቅርቦት እንዲኖር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመነጋገር ይሰራል ብለዋል። ክልሎች በዚህ ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮች እንዳይኖሩ በቂ ኮምፒዩተር ፣ ኔትዎርክና አማራጭ የሀይል አቅርቦት እንዲኖር ልዩ ትኩረት ሰጥተው መዘጋጀት እንዳለባቸው አሳስበዋል። ለተማሪዎችም በቂ ሥልጠና መስጠት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የክልልና ከተማ መስተዳድሮች ይህንን አውቀው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። በትምህርት ሚኒስቴር የዲጅታል ትምህርትና አይሲቲ ሥራ አስፈፃሚ ዘላለም አሰፋ (ዶ/ር) ፤ ተማሪዎች የሚለማመዱባቸው ሞዴል ፈተናዎች በበቂ ሁኔታ የተጋጁ መሆኑን ገልጸዋል። " ተማሪዎች አስቀድመው እንዲለማመዱና ሥልጠና እንዲያገኙ ማድረግ ይገባል " ብለዋል። #MoE @EthiopianStudentstm @EthiopianStudentstm

  • 2 янв.7 1871219

    🚀 Level up your learning! Top 100 YouTube Channels to Learn Almost Anything — coding, science, languages, and more. #LearnOnline @EthiopianStudentsTM

  • ለ Fresh ተማሪዎች ምክር ቢጤ 🤹‍♀ ህይወት ብዙ ምርጫዎች አሏት የሰው ልጅም ከእነዚህ ምርጫዎች በአንዱ መወሰን ግዴታው ነው ። የምንመርጠው ምርጫ የወደፊት መንገድ ነው ። ዛሬም አንዱን ትመርጣለህ ወደድክም ጠላህም ። 📌 በዩንቨርሲቲ ቆይታህ በትምህርቱ ዘርፍ ሀ ..ብለህ ለመጀመር ምርጫ ትመርጣለህ በተለይ ለመጀመሪያ አመት ተማሪወች 👉ምን የትምህርት አይነት መማር አለብኝ ? 👉የኔ ዝንባሌ እና አቅሜ የሚችለው  ምንድነው ? 👉እሆናለሁ ብዬ አስብ የነበረው ህልሜ ምንድነው ?? 🎯 እነዚህ ጥያቄዎችን መመለስ ከቻልክ የምትፈልገውን ለማግኘት አትቸገርም ። ነገር ግን መሆን የምትፈልገውንና መማር ምትፈልገውን መምረጥ ካቃተህ  ዛሬውኑ እራስህን ጠይቅ ወይም 👨‍👩‍👧‍👧ቤተሰብ :ጓደኛህን/ሽን አማክር /ሪ ። ስታማክር የራሴ የምትለውን ነገር ይዘህ እንጂ ያማከርካቸው ሰወች ያሉህን አትውሰድ ። 📌በሰው ምርጫ አትወሰን ይልቅ ሰው መርጦልህ ከምትበሳጭ በራስህ ምርጫ ብትበሳጭ ይሻልህል ። 📌 በመረጥከው ምርጫ ስኬታማ ለመሆን ያለህን አቅም አሟጠህ ተጠቀም: የሚያስፈልገውን መስዋዕትነት ክፈል ትርጉም ያለው ህይወት ለመኖር ስትል ። የምትማረውን ትምህርት በተግባር ኑረው‼️ 🔨ህግ ተምረህ የግቢው አስበጥባጭ ተማሪ ከሆንክ ትምርቱ አልገባህም ማለት ነው!! 👷ኢንጂነሪንግ እየተማርክ ህንፃና ንብረት ለማጥፋት ከተነሳህ  ምርጫህ ልክ አይደለም!! 👉ሶሺዮሎጂ እየተማርክ ማህበረሰብህን  ካላወቅህ  ባክነሀል ማለት ነው ትምህርቱን አቋርጥ!! 📙ታሪክን አጥንተህ በአድዋ ኮርተህ  ስለአንድነት መስበክ ካልቻልክ ይቅርብህ አቋርጠው!! 🎯 የምትማረው ስርዓት ያለው ዜጋ ለመሆን ነውና መርጠህ ተማር የመረጥከውን ኑረው እየኖርክም ህዝብህን አገልግል ። የምትማረው በኢትዮጲያ ህዝብ ገንዘብ ነውና ። A space for every Ethiopian student — elementary, highschool, or university. @EthiopianstudentsTM

  • የ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች የሚያገኙበት አድራሻዎች ይፋ ሆኑ፡፡ የ2017 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተፈተኑ ተፈታኞች በሚከተሉት አድራሻዎች ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ፡፡ ዌብ ሳይትና ቴሌግራም አድራሻ የሚጠቀሙ ተፈታኞች ጊዜያዊ ሰርቲፊኬታቸውን ወዲያውኑ አውርደው (download አድርገው) መውሰድና መጠቀም ይችላሉ፡፡ አድራሻዎቹ፡ 1. ዌብ ሳይት፡ https://result.eaes.et 2. ቴሌገራም፡ https://t.me/EAESbot 3.  አጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS)፡  6284 ስለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ትክክለኛ መረጃን ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ማህበራዊ ሚዲያዎች ያገኛሉ፡፡  የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መስከረም 05/ 2018 ዓ/ም @EthiopianStudentsTM

  • 📈12ኛ ክፍል ተማሪዎች በአዲስ የምዘና ሥርዓት መመዘን ከጀመሩበት 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2017 ድረስ በጠቅላላው 🔗 3,011,607 ለፈተና ተቀምጠዋል 🔗 የማለፊያ ነጥቡን (50%) ያገኙት 🔗 በጠቅላላው 142,514 ተማሪዎች ወይም 4.7% ብቻ ናቸው 🔗 2,869,093 የሚሆኑት ወይም 95.3 % ተማሪዎች ማለፊያውን ማግኘት አልቻሉም:: JOIN:@EthiopianStudentsTM ✅

  • " ስንጠብቅ ያነበረው ይህንን ውጤት ነው " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በ2017 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከተፈተኑት 585,879 ተማሪዎች መካከል 48,929 ተማሪዎች 50 በመቶ አምጥተው አልፈዋል። ይህም 8.4 በመቶ ነው። በ2016 ዓ/ም ከ674,823 ተማሪዎች ያለፉት 36,409 ወይም 5.4 በመቶ ነበሩ። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በ2017 ዓ/ም ተማሪዎች ስላስመዘገቡት ውጤት ምን አሉ? " ስንጠብቅ ያነበረው ይህንን ውጤት ነው። የመጀመሪያ ሾክ ነበር ከዛ ግን በራሱ ውጤት የሚያልፍ ተማሪ እየመጣ ነው። የፈተና ስርአታችን ሊያመጣው የሚፈልገው ውጤት እየመጣ ነው ትክክለኛው መስመር መሆኑን የተረዳንበት ነው። ይህንን ሃገር የሚጠበቅበት ቦታ ለማድረስ ለእዛ የሚበቃ ትውልድ እያፈራን ነው። በእዚሁ እንዲቀጥል ነው የምንሰራው። 15-20 በመቶ የሚሆን ማክሲመም ተማሪ እንዲያልፍ ነው የምንሰራው ሁለት እና ሦስት አመት ይፈጅብናል ነገር ግን እንደርስበታለን። ዘንድሮም ጥሩ ውጤት ነው የመጣው ነው ነገር ግን የሚያኩራራ አይደለም በሚቀጥሉት ሦስት አመታት የተሻለ ውጤት ይመጣል " ብለዋል። @EthiopianStudentsTM

  • ውጤት መቼ ይለቀቃል ? " ውጤት እስከ ነገ ቀን 6:00 ሰዓት ይለቀቃል " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

  • ውጤት መቼ ይለቀቃል ? " ውጤት እስከ ነገ ቀን 6:00 ሰዓት ይለቀቃል " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

  • ዘንድሮ የሬሜዲያል /አቅም ማሻሻያ/ ፕሮግራም ይኖራል ? በዘንድሮ ዓመት ሬሜዲያል /የአቅም ማሻሻያ/ ፕሮግራም እንደሚኖር የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል። " ከባለፈው ዓመት መግቢያውን ከፍ በማድረግ ሬሚዳል ይሰጣል " ነው ያሉት። ምን ያህል ተማሪዎች ሬሜዲያል ይገባሉ ? ለሚለው ጥያቄ ሚኒስትሩ " አልወሰንም " ሲሉ መልሰዋል። " ዘንድሮ ሪሚዲያል እድል የሚሰጣቸውን ተማሪዎች ቁጥር አልተወሰነም። 40-50 በመቶ መካከል ይሁን የሚለው ላይ በውይይት ላይ ነው " ብለዋል። ካለፈው አመት ግን መግቢያው ከፍ እንደሚደረግ እና የሚገባው ተማሪ ቁጥርም ቅናሽ እንደሚኖረው ተገልጿል። 📨 @EthiopianStudentsTM

  • የዘንድሮ ከፍተኛ ውጤት 591 ዶዶላ ኢፋቦሩ ትምህርት ቤት

  • 2384 ተማሪዎች ዘንድሮ ከ 500 በላይ ያመጡ ተማሪዎች ተገኝተዋል

  • የዘንድሮ ከፍተኛ ውጤት 591 ዶዶላ ኢፋቦሩ ትምህርት ቤት

  • በኦንላይን ከተፈተኑት ተማሪዎች 21.7 በመቶ አልፈዋል በወረተት የፈተኑት ግን ባለፈውም 4.4 ነበረ አሁንም 4.4 ነው።

  • ካለፋት ተማሪዎች ተማሪዎች ሴት 18,478 የቀሩት ወንዶች ናቸው

  • ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች 48,929 ተማሪዎች አልፈዋል። @EthiopianStudentsTM

  • በሀገር ደረጃ 8.4 በመቶ ተማሪ 50% በላይ በማምጣት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን አልፏል። @EthiopianStudentsTM

  • ወንዶች 30, 444 ሴቶች 18,478 @EthiopianStudentsTM

  • አጠቃላይ 48, 929 ተማሪ አልፏል @EthiopianStudentsTM

  • 48,929 ያክሉ ተማሪ ከ50% በላይ አምጥቶ አልፏል ተብሏል።

Ethiopian Students Network 🇪🇹( ESN) — tgindex