tgindex
G

Geez Laws Center ግእዝ የሕግ ማእከል

Статистика
@GeezLawsанглийский

www.geezlaw.com | +251948449999 geezlaw@gmail.com #Free_Services #All_Business_Laws & Businesses

Последний пост
8 июн.
Последнее чтение
ещё не заходили
Постов за неделю
0
Всего постов
94
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
4 398
+5 за 4 дн.
Сутки
−1
−0,02%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 745
40 постов
Вовлечённость
39,7%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 94
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 8 июн.1 671123

    የግብርና ቢዝነስ ኩባንያዎች ለሥራቸው የሚያስፈልጓቸውን የግብርና ግብዓቶች፣ መሣሪያዎችና፣ ተሽከርካሪዎችን ከውጭ "ከታክስ ነፃ" እንዲያስገቡ የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ። የሚኒስትሮች ምክር ቤት የግብርና ዘርፍን ከተለምዶአዊ አሰራር ወደ ቢዝነስ መር ስርአት ለማሸጋገር ያግዛል ያለውን "የግብርና ቢዝነስ ኩባኒያ አዋጅ" ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መምራቱ ይታወቃል። ይህ አዋጅ ኋላ ቀር የግብርና አሠራር ተወስነው የቆዩ አነስተኛ አርሶ አደሮችን፣ አርብቶ አደሮችንና ከፊል አርብቶ አደሮችን ወደ ዘመናዊና ተወዳዳሪ የንግድ ሥርዓት ለማሸጋገር ያለመ ነው። የዚህ ሪቂቅ አዋጅ ዋነኛ ትኩረት አነስተኛ ይዞታ ያላቸውን አምራቾች በ "ክላስተር" በማደራጀት ወደ ግብርና ቢዝነስ ኩባኒያነት መለወጥ ነው። አዲሱ ሕግ አርሶ አደሩ ያለውን መሬት የመጠቀም መብት፣ የእንስሳት ሀብትና ጉልበት ወደ ካፒታል በመለወጥ የኩባኒያ ባለቤትና ባለድርሻ እንዲሆን ዕድል ይከፍታል። ይህም አርሶ አደሩ በግል ከመልፋት ይልቅ በጋራ በመደራጀት በገበያ ላይ የመደራደር አቅሙን እንዲያሳድግ፣ ምርቱን እንዲያሰባስብና እሴት በመጨመር የተሻለ ዋጋ እንዲያገኝ እንደሚያስችለው አዋጁ ያስረዳል። በአዋጁ መሠረት አንድ የግብርና ቢዝነስ ኩባኒያን ለመመስረት ዝቅተኛ የአባላት ቁጥር ተቀምጧል። በአዝርዕት ዘርፍ የተሰማሩ ከሆኑ ቢያንስ 300 አባላት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ወይም በእንስሳት እርባታ ዘርፍ ከሆነ ደግሞ ቢያንስ 150 አባላት ሊኖሩት ይገባል። ኩባኒያዎቹ ሲመሰረቱ ዝቅተኛ የተከፈለ ዋና ካፒታላቸው ከ1.5 ሚሊዮን ብር ማነስ የለበትም። እያንዳንዱ አባል በኩባኒያው ውስጥ ሊኖረው የሚችለው የአንድ ድርሻ (Share) ዋጋም ከ1,000 ብር በታች እንዳይሆን ተደንግጓል። የግብርና ቢዝነስ ኩባኒያዎቹ እንደ ማንኛውም ዘመናዊ የንግድ ተቋም በጠቅላላ ጉባኤ፣ በሥራ አመራር ቦርድ እና በዋና ሥራ አስኪያጅ የሚመሩ ይሆናሉ። ከዚህ በተጨማሪ ኩባኒያዎቹ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎችን የሚጠቁሙና ሙያዊ ምክር የሚሰጡ፣ "የአማካሪ ቦርድ" እንዲኖራቸው አዋጁ ይፈቅዳል፣ የአማካሪ ቦርድ የስራ አባላት ዘመንም ሦስት አመት ነው። ይህም የኩባኒያዎቹ አመራር በሳይንሳዊና በዘመናዊ የቢዝነስ ዕውቀት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ለማድረግ ነው። ይህንን ሽግግር ለማገዝም ልዩ ልዩ ማበረታቻዎችን ረቂቅ አዋጁ አካቷል። የግብርና ቢዝነስ ኩባኒያዎቹ ለሥራቸው የሚያስፈልጉ የግብርና ግብዓቶችና ቴክኖሎጂዎችን፣ የእርሻ መሣሪያዎችንና ተሽከርካሪዎችን እንዲሁም መለዋወጫዎችን ከውጭ ሲያስገቡ "ከታክስ ነፃ" የመሆን መብት ይኖራቸዋል። የግብርና ቢዝነስ ኩባኒያ አባላት ያመረቱተትን የግብርና ምርት ሲሽጡ ወይም ከኩባኒያው በሚያገኙት የትርፍ ክፍፍል ላይ የገቢ ግብር አይከፍሉም፡፡ ሆኖም ኩባንያው ከሚያገኘው ገቢ ላይ በገቢ ግብር አዋጁ መሰረት ግብር ይከፍላል፡፡ በተጨማሪም ኩባንያዎቹ ግብዓቶችን ለማስገባት ለሚያስፈልጋቸው የውጭ ምንዛሬ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሲሆን፣ ለሥራ አመራር ቦርድና ለአባላት የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች እንደሚመቻቹ እንደሚደረግ ረቂቅ መመሪያው ያሳያል። ግንቦት 18 በተካሄደው 55ኛው የሚኒስትሮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ፣ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቶታል።l #All_Business_Laws_and_Businesses_Free_Service https://t.me/GeezLaws

  • 8 июн.1 402910

    ከ190 በላይ ጠበቆች ገንዘብ ሚኒስቴርን ከሰዋል። • የጥብቅና ሙያ የንግድ ስራ አይደለም፤ የፍትህ አካል ነው? በጠበቆች ላይ የተጫነው የግዴታ የቫት (VAT) ምዝገባ እና የፍትህ ስርአቱ አደጋ!? • የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያዎች (ጠበቆች) በታሪካቸው ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በሙያዊ ነፃነታቸው እና በኢኮኖሚያዊ ህልውናቸው ላይ የመጣባቸውን የተሳሳተ የመንግስት መመሪያ በመቃወም ለፍትህ ቆመዋል። የገንዘብ ሚኒስቴር ያወጣው መመሪያ ቁጥር 1104/2017፣ ማንኛውም ጠበቃ የገቢ መጠኑ ምንም ይሁን ምን ለተጨማሪ እሴት ግብር (VAT) እንዲመዘገብ እና እንደ ማንኛውም የንግድ ድርጅት በየወሩ ሪፖርት እንዲያደርግ ያስገድዳል። ይህ መመሪያ የህግ ባለሙያዎችን መብት ከመጣስ ባለፈ፣ ተራው ዜጋ ፍትህ እንዳያገኝ ትልቅ የገንዘብ እንቅፋት የሚፈጥር በመሆኑ ከ190 በላይ ጠበቆች በጋራ ክስ መስርተዋል። ዋና ዋና የመከራከሪያ ነጥቦች 1. ህገ-ወጥ እና ከአዋጅ ውጪ የሆነ መመሪያ፡- • የቫት አዋጅ ቁጥር 1341/2024 በግልፅ እንደሚደነግገው፣ የቫት ምዝገባ ግዴታ የሚሆነው አመታዊ ገቢያቸው ከ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ለሆኑ ድርጅቶች ብቻ ነው። ሆኖም የገንዘብ ሚኒስቴር ይህንን የአገሪቱን ከፍተኛ ህግ በመጣስ፣ ለጠበቆች ብቻ የተለየና መዳረሻው ዜሮ (Zero Threshold) የሆነ መመሪያ ማውጣቱ "ከስልጣን በላይ" (Ultra Vires) የሆነ ተግባር ነው። 2. ጠበቃ የፍትህ ባለድርሻ እንጂ፣ ነጋዴ አይደለም፣ • የጥብቅና ሙያ በባህሪው የዜጎችን ህገ-መንግስታዊ መብት ለማስከበር የሚቆም እንጂ እንደ ሸቀጥ የሚሸጥና የሚለወጥ ንግድ አይደለም። ጠበቆች ፈቃዳቸውን ለማደስ በየዓመቱ የነፃ የህግ አገልግሎት (Pro Bono) የመስጠት ግዴታ አለባቸው። ይህንን ማህበራዊ ኃላፊነት ያለበትን ሙያ እንደ ተራ የችርቻሮ ንግድ ቆጥሮ ታክስ መጫን የሙያውን ክብር ዝቅ ማድረግ ነው። 3. የዜጎች ፍትህ የማግኘት መብት አደጋ ላይ መውደቅ፡- • በጥብቅና አገልግሎት ላይ 15% ቫት መጫን ማለት፣ ደንበኛው ወይም ተከሳሹ ለፍትህ የሚከፍለው ዋጋ በ 15% ይጨምራል ማለት ነው። ይህ ደግሞ አቅም የሌላቸው ዜጎች በፍርድ ቤት የመከራከር መብታቸውን እንዲተዉ ያስገድዳቸዋል። ፍትህ ለሀብታም ብቻ የሚሸጥ ሸቀጥ መሆን የለበትም። 4. ምክንያታዊ ያልሆነ የወጪ አያያዝ፡- • የጠበቆች ስራ አእምሯዊ እንጂ ግዙፍ ግብዓቶችን (Raw materials) የሚጠቀም አይደለም። በመሆኑም እንደ ነጋዴ "የወጪ ደረሰኝ" (Input VAT) አሰባስቦ ለማቅረብ የሙያው ባህሪ አይፈቅድም። መንግስት ይህንን ከግምት ውስጥ ያላስገባ "ሂሳብ ያዙ" የሚል ትዕዛዝ ማውጣቱ በተግባር ሊተገበር የማይችል እና ሙያውን ለማፈን የታለመ ነው። የፍርድ ቤት ሂደት እና የእግድ ጥያቄ መዘግየት፡- • ጉዳዩ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረበ ቢሆንም፣ የፍርድ ቤቱ የእግድ ጥያቄውን በተደጋጋሚ መቅጠር እና ውሳኔ አለመስጠት ጠበቆችን እያሳዘነ ይገኛል። እግዱ ሳይሰጥ መመሪያው ስራ ላይ መዋሉ ጠበቆች ፈቃዳቸውን እንዳያድሱ እና ስራቸውን እንዳይሰሩ እያገዳቸው ነው። • ጠበቆች ፍትህ ከዘገየ እንደተነፈገ ይቆጠራል እንደሚባለው፣ ፍርድ ቤቱ የጉዳዩን አሳሳቢነት ተረድቶ በአስቸኳይ እግድ እንዲሰጥ በችሎት ቀርበን ጠይቀን ነገር ግን ችሎቱ ለቀጣይ ወር ቀጠሮ በመስጠት አልፎታል። #የጠበቆች_ጥሪ፡- • አዋጁን የሚቃረነውና የጥብቅና ሙያን ታሳቢ ያላደረገው መመሪያ በአስቸኳይ እንዲሰረዝ ወይም እንዲሻሻል። • የፍትህ አካል የሆኑት ጠበቆች ላይ የሚደርሰው ጫና የፍትህ ስርአቱን እንዳያናጋ የሚመለከተው አካል ጣልቃ እንዲገባ። ይህ የጥቂት ጠበቆች ጥቅም ሳይሆን፣ የሁሉም ዜጋ የፍትህ መብት ጥያቄ መሆኑን ተረድታችሁ ድምፃችንን እንድታስተጋቡልን። ለሙያችን ክብር፣ ለዜጎች ፍትህ በጋራ እንቆማለን‼️🙏 @የሕግ_ጉዳይ #All_Business_Laws_and_Businesses_Free_Service https://t.me/GeezLaws

  • 7 июн.1 358612

    የገንዘብ ሚኒስቴር መመርያ 07/2011 እና ዲቪደንድ ታክስ በ ብርሃኑ በየነ ብርሃኑ (የሕህ ኣገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር - ዘመን ባንክ) #All_Business_Laws_and_Businesses_Free_Service https://t.me/GeezLaws

  • 7 июн.1 35156

    የጋራ ኢንቨስትመንት ፈንድ ረቂቅ መመሪያ የካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 የጋራ ኢንቨስትመንት ፈንዶችን ምስረታና አስተዳደር በብቃት ለመምራት፣ ለመከታተልና ቁጥጥር ለማድረግ የሚያስችሉ ዝርዝር መስፈርቶችን የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በመመሪያ አማካኝነት እንዲወስን የተደነገገ በመሆኑ፣ እና ...(ዝርዝርሩን ይምልከቱ)፣ ባለሥልጣኑ በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 አንቀጽ 86(4)፣ 87(1) እና (2)፣ 90(3) እና 108(2) መሰረት ይህን መመሪያ አውጥቷል። #All_Business_Laws_and_Businesses_Free_Service https://t.me/GeezLaws

  • 22 мая2 2341340

    ማንኛውም ሰው በአስተዳደር ኣካላት ያልተፈጠረ/ ያልተፈጠረ መብት ይዞ በቀጥታ ወደ ፍርድ ቤት መብት እንዲፈጠርለት የሚያቀርበው ክስ ከመጀመርያውኑ ፍ/ቤቶች በተፈጠረ ወይም በተቛረጠ መብት ላይ ኣከራክሮና  ከህግና ማስረጃ ኣንፃር መርምሮ የመወሰን ስልጣን እንጂ ያልነበረ መብት የመፍጠርም ሆነ ያልተቛረጠ መብት በራሳቸው ተነሳሽነት የማቛረጥ ስልጣን ስለሌላቸው ክሱ  የክስ ምክንያት የለውም ተብሎ ዉድቅ ሊደረግ ይገባል፣ በሌላ በኩል የኣስተዳደር ኣካላት ዜጎች ለሚያቀርቡት የመብት ጥያቄ ህጉ በዘረጋው ስርዓትና ኣሰራር መሰረት ኣገልግሎት የመስጠት ግዴታ እንዳለባቸው ግልፅ ነው፣ ስለሆነም ማንኛውም ሰው መጀመርያ ለኣስተዳደር ኣካሉ በህጉ መሰረት መብት እንዲፈጠርለት ጥያቄ ኣቅርቦ ከህግ ዉጭ ከተከለከለ ወይም ከህግ ዉጪ ተከልክያለው ብሎ ስያምን መብቱን ለማስከበር ፍ/ቤት ላይ የሚያቀርበው ክስ የክስ ምክንያት የለዉም ሊባል ኣይገባም፣ ምክንያቱም ፍ/ቤቶች  የኣስተዳደር ኣካላት መብት ለመፍጠር የከለከሉበት ምክንያት ትክክል መሆን/ኣለመሆን ከህግ ኣኳያ መርምሮ የመወሰን ስልጣን ስላላቸው ነው፣ ሲጠቃለል መብት እንዲፈጠርልኝ ይወሰንልኝ ብሎ በቀጥታ ክስ ማቅረብ እና የኣስተዳደር ኣካሉ ከህግ ዉጭ መብት እንዳይፈጠርልኝ ከልክሎኛል ብሎ ክስ ማቅረብ ሁለት የተለያዩ የክስ ምክንያቶች ናቸው። #ያልታተመ_ውሳኔ_ሰመቁ_213046 #All_Business_Laws_and_Businesses_Free_Service https://t.me/GeezLaws

  • 22 мая2 111614

    #The_Financing_Dictionary! • A pocket guide to the technical vocabulary of loan agreements, bond indentures, security, intercreditor & hedging documents, bridging London (English law) & New York practice.  #On_the_Vocabulary_of_Financings • By Herman, Henry & Dominic, a finance & corporate law firm active across loan agreements, secured lending, intercreditor arrangements, financing leases & hedging documentation. Their work spans bilateral facilities to cross‑border syndicated & capital markets transactions.  • Born from daily practice, this dictionary brings together LMA & LSTA terms, English‑law charges & UCC Article 9 interests, waterfalls & indenture trustees. It is a practical reference, a navigation tool for the complex language of financing.  #All_Business_Laws_and_Businesses_Free_Service https://t.me/GeezLaws

  • 20 мая1 089714

    ቼክ እና የቼክ ሰነድ በመያዣነት መስጠት ከሕግ አኳያ ያለው ትርጓሜ። በድምፅ #Voice የቀረበ 🗣 #Business_Law 🗣 #Corporate_Law Geez Laws & Businesses 👋 our𝑻𝒆𝒍𝒆𝒈𝒓𝒂𝒎 𝑪𝒉𝒂𝒏𝒏𝒆𝒍🔗👇 🌐https://t.me/GeezLaws

  • 20 мая1 54871

    Empowering young lawyers to rise beyond inherited limits... Success in law isn’t born from family connections, it’s built through visibility, responsiveness & genuine relationships. Read our latest insight: “6 Ways Young Lawyers Can Start Getting Clients Without Family Connections.” 📧 geezlaws@gmail.com 🤳 +251948449999 #All_Bzs_Law_Services https://t.me/GeezLaws

  • 18 мая1 53597

    • የጤና ማስታወቂያ የሚያሰሩ ተቋማት ማስታወቂያ ሲያወጡ "የሁሉም ምርጫ" ወይም "ተቀዳሚ ምርጫ" የሚሉ ቃላትን መጠቀም የሚከለክል መመሪያ ወጥቷል። • የጤና ሚኒስቴር በሀገሪቱ የሚሰራጩ የጤና አገልግሎት ማስታወቂያዎች ሙያዊ ስነ-ምግባርን የተከተሉና ህብረተሰቡን የማይበድሉ እንዲሆኑ ለማስቻል "የጤና አገልግሎት ማስታወቂያ ዝግጅት እና ስርጭት መመሪያ ቁጥር 1134/2018" የተሰኘ አዲስ መመሪያ አውጥቷል። • መመሪያው በዋናነት በጤና ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶች ለህዝብ ሲተዋወቁ ሊከተሏቸው የሚገቡ የይዘት፣ የቋንቋ እና የሥነ-ምግባር መስፈርቶችን በዝርዝር አስቀምጧል። • ዝርዝር ይዘቱ መመርያውን ይመልከቱ። geezlaws@gmail.com #Free_Services +251948449999 #All_Business_Laws & Businesses https://t.me/GeezLaws

  • 17 мая1 8231125

    የግል ንግድ /sole proprietorship/ እና ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ልዩነት እና አስፈላጊነት ከኢትዮጵያ ንግድ ህግ ማእቀፍ መግቢያ ለዚህ ጹሁፍ መነሻ የሆነኝ ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና የግል ንግድ /sole proprietorship/ ያሉት ባህርያት ፥ የሚለያዩበት መሠረታዊ ነጥብ ፥ የሁለቱም ጥቅም እና የንግድ እንቅስቃሴ ከመደምደሚያ የህግ ምክር ጋር አጠቃለን ለህግ ግንዛቤ ይሆን ዘንድ ለእናንተ አቅርበናል። 1. የግል ንግድ ድርጅት/Sole proprietorship/ የህግ ትርጉም የግል ንግድ ድርጅት (Sole Proprietorship) ማለት በአንድ ግለሰብ ብቻ የሚመሰረት፣ የሚንቀሳቀስ እና በባለቤትነት የሚተዳደር የንግድ አይነት ነው። ይህ የንግድ መዋቅር በአንድ ሰው የሚመራና ከባለቤቱ የተለየ የህግ ሰውነት የሌለው ንግድ ነው።የንግድ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 5 ፥38 እና ተከታዮችን በመረዳት መገንዘብ የሚቻል ነው። 2. ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ትርጓሜ ባለ አንድ አባል ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ማለት አንድ ሰው በግሉ በሚሰጠው መግለጫ መሠረት የተቋቋመ የንግድ ማኅበር ነው።ማኅበሩ ከአባሉ የተለየና የተነጠለ የራሱ የሕግ ሰውነት አለው።አባሉ የራሱን መዋጮ ሙሉ በሙሉ እስከ ከፈለ ድረስ ማኅበሩ ላይ ለሚፈለገው ዕዳ በግሉ እንደማይጠየቅ በንግድ አዋጅ ቁጥር 1243/13 አንቀጽ 534 ላይ ተደንግጓል። 3. የግል ንግድ ድርጅትና ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መካከል ያለው ልዩነት 3.1 በግል ንግድ/Sole proprietorship/ ያለውን እንመልከት በግል የንግድ ስራ ሲከናወን በግል የሚሰራው ሰው ራሱ ለሚመጣው ጥቅም ራሱ ተጠቃሚ ሲሆን ለሚከሰተውም እዳ ደግሞ ከድርጅቱ ጋር በተናጠልም ሆነ በአንድነት ተጠያቂ ይሆናል። ኃላፊነቱ ያልተወሰነ ነው። ነጋዴው ከድርጅቱ የሚለይበት አይደለም። ነጋዴው ከሞተ በመሰረቱ የግል ንግዱ ይቆማል። ወራሾች ግን በራሳቸው ስም የመቀጠል መብት አላቸው። ቢቀጥሉም በቀድሞ በንግዱ ስም ሳይሆን በራሳቸው ነው። ወራሽ ከሌለው ደግሞ እስከ መጨረሻው ድርጅቱ ይሞታል ወይም ይጠፋል። ወራሾች ግን መቀጠል ከፈለጉም ሆነ ንግዱ በራሳቸው እንዲቀጥል ካልፈለጉ የንግድ ስሙን ከንግድ መዝገብ ማሰረዝ አለባቸው። ግብር አከፋፈል በተመለከተ ከትርፉ ላይ አንዴ ብቻ የሚከፈል ነው። አባሉም ድርጅቱም አንድ ነው። የአባላት ትርፍ ክፍፍል/dividend/ የሚባል የለም። ይህ የንግድ ድርጅቱ ከነጋዴው የተለየ ህጋዊ ሰውነት ስለሌለው ነው። 3.2 ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ይህ ማህበሩ ከአባሉ የተለየ ህጋዊ ሰውነት ያለው በራሱ ህጋዊ ጉዳይ ማስኬድ የሚችል ነው። አባሉ አንድ ሰው ሲሆን ኃላፊነቱ የተወሰነ ነው። ማህበሩ ባለው እዳ ኃላፊነት አባሉ አይጠየቅም። ማህበሩ እራሱ የሚጠየቅበት ነው። አባሉ ቢሞት ፣ ቢወጣ ማህበሩ ራሱን ችሎ ይቀጥላል። ባለሀብቶች ይህንን አንድ አባል ሆነው ኃላፊነቱ የተወሰነ ስለሆነ ይመርጡታል። ግብር አከፋፈል ከማህበሩ ትርፍ ከተከፈለ በኋላ አባሉ ካገኘው ትርፍ በድጋሜ ግብር ይከፈላል። አባሉ በአንድነት እና በነጠላ ሊጠየቅ የሚችለው በተለየ ሁኔታ ማህበሩን ለጉዳት የሚዳርግ ጥፋት ከፈጸመ በንግድ ህጉ አንቀጽ 543 መሠረት ተጠያቂ ይሆናል እንጂ በመሠረቱ አይጠየቅም። 4. ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጥቅምና ስጋት በአዲሱ ንግድ አዋጅ ቁጥር 1243/13 አንቀጽ 534 እንደተቀመጠው ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የህግ እውቅና የተሰጠው ሲሆን ይህ ለብቻቸው ኃላፊነቱ በተወሰነ የግል ማህበር ለመስራት ለሚፈልጉ ባለሀብቶች እንዲሰሩ ከሌሎች ሀገሮች ልምድ ተሞክሮ በመውስድ የወጣ የህግ ድንጋጌ ነው። በዚህ መሰረት በግል ንግድ ድርጅት ይልቅ አንድ አባል ሆኖ በኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መሥራት ለሚፈልግ ነጋዴ ይህን አማራጭ መምጣቱ ለሀገራችን አማራጭ የንግድ እንቅስቃሴ ስረአት ከፍተኛ ሚና ያለው ነው። ምክንያቱም ብቻውን አባል ሆኖ በግል ድርጅት ለሚመጣው እዳ ኃላፊነት ባለቤቱ በነጠላ እና በአንድነት ከመጠየቅ ይልቅ ድርጅቱ ብቻ በኃላፊነቱ እንዲጠየቅ አባሉ በማህበሩ እዳ እንዳይጠየቅ እንዲሁም ደግሞ ባለሀብቱ ብቻውን ለመስራት ከፈለገ ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርን መመሥረት አዋጭ ነው። የማህበሩ እዳም ወደ አባሉ የማይመጣ ማህበሩ በራሱ የሚጠየቅ ነው። አባሉ ቢወጣ፣ቢሞት ማህበሩ ዘላቂ በመሆኑ ለንግድ እንቅስቃሴ ዋስትና ወሳኝ ሚና አለው። ለሶስተኛ ወገኖች ባለገንዘቦች ግን አንድ አባል ሆኖ ኃላፊነቱ የተገደበ መሆኑ እዳን ከመክፈል አንጻር የሚተማመኑበት አይሆንም። ግብር አከፋፈል ላይ ከማህበሩም ከአባል ትርፉም አንድ ሆኖ ሳለ ሁለቴ መክፈሉ ባለሀብቱን በዚህ ንግድ ማህበር እንዳይሳተፍ የሚገፋው ነው። አንድ አንድ ሀገሮች አንድ ግብር ክፍያ በማድረግ የሚያበረታቱ ሲሆን አሜሪካ ለዚህ ተጠቃሽ ናት። 5. የግል ንግድ ጥቅምና ስጋት የግል ንግድ/sole proprietorship/ ለሚሰራ ሰው ለ3ኛ ወገኖች ባለገንዘቦች ይህ ተመራጭ ሲሆን ግብር አከፋፈል ላይም አንዴ በንግድ ድርጅቱ ብቻ የሚከፍልበት ነው። አባል ባለ አክስዮን ስለሌለበትም ትርፍ ድርሻ ከፍፍል የለም። እንደ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሁለት ጊዜ ግብር አይከፍልም። ያለው ስጋት እዳ ጠያቂዎች ከድርጅቱ አልፈው በግል ሀብቱ ጭምር የሚጠይቁት በመሆኑ ለቤተሰቡ ለግል ሀብቱ ከባድ አደጋ ሲሆን ለእዳ ጠያቂዎች ግን ዋስትና እና ጠቃሚነት ያለው ነው። ነጋዴው ሲሞት ንግዶ ከንግድ መዝገብ የሚለይ ሲሆን ወራሾች ካሉ በውርስ ማጣራት ሂደት የሚከናወን ሲሆን የገንዘብ ጠያቂዎችን ከንግዱና ከውርሱ ሀብቱ እዳ ከከፈሉ በኋላ ላይ ለራሳቸው የሚወርሱ ይሆናል። 6. የጹሁፉ መደምደሚያ እና የህግ ምክር የግል ንግድ እና ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሁለቱም ጋር የአንድ ሰው ሀብት ሲሆኑ ከኃላፊነት ፣ ህጋዊ እንቅስቃሴ እና ውጤት አንጻር የራሳቸው የሆነ ጸባይ ያላቸው በመሆኑ ቀድሞ በማጤን የህግ ባለሙያ በማማከር እንደ ባለሀብቱ የሀብት አቋም እን የንግድ ፍላጎት አንጻር መመስረት ፣ ሊመጣ ከሚችለው ኪሳራ እና ጉዳት በመጠበቅ ለታለመለት የንግድ ትርፍ ሊረዳ የሚችል ነው። ማጣቀሻዎች/References/ 1. የንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/13 2. ፍቃዱ ጴጥሮስ የኢትዮጵያ የህግ ኩባንያ 3ኛ እትም geezlaws@gmail.com #Free_Services +251948449999 #All_Business_Laws & Businesses https://t.me/GeezLaws

  • 15 мая1 669136

    የተእታ መመሪያው በጠ/ፍ/ቤት በይግባኝ ታግዶአል:: ● በከሳሽ ጠበቆች እና በተከሳሽ ገንዘብ ሚ/ር መካከል በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ባለው የተጨማሪ እሴት ታክስ መመሪያ ቁጥር 1104/2017 ክለሳ ክርክር ፍ/ቤቱ መመሪያው በመጀመሪያ ክሱን ላቀረብን 7ቱ ጠበቆች ሳይፈጸም ታግዶ እንዲቆይ ኅዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ትእዛዝ መስጠቱ ይታወሳል:: ● ከዚህ ቀን በኋላ የተለያየ ቁጥር ያላቸው አድራሻቸውን በፌደራልና በክልል ያደረጉ ጠበቆች በተለያዩ 30 በላይ መዝገቦች ክስ ያቀረቡ እነዚህን ጠበቆች አስመልክቶ ግን እግድ እንዳልተሰጠም ይታወቃል:: ● በዚህ የእግድ ክልከላ ብይኑ ቅር የተሰኙ ጠበቆች ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ እንዳቀረቡ እና እያቀረቡ እንደሆነም ይታወቃል:: ● ከእነዚህ የይግባኝ መዝገቦች መካከል ቀድሞ በተከፈተው መዝገብ ላይ ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ሰሞኑን አቤቱታውን ሰምቶ ያስቀርባል በማለት ተለዋጭ ትእዛዝ እስኪሰጥ ድረስ የመመሪያ ቁ.1104/2017 አፈጻጸም ይግባኝ ባይን አስመልክቶ ታግዶ እንዲቆይ በማለት ዛሬ ግንቦት 06 ቀን 2018 ዓ.ም ትእዛዝ ሰጥቷል:: @EthiopianLaw geezlaws@gmail.com #Free_Services +251948449999 #All_Business_Laws & Businesses https://t.me/GeezLaws

  • 15 мая1 556814

    በሕፃን ልጅ ስም የተመዘገበ የማይንቀሳቀስ ንብረት በፍቺ ንብረት ክፍፍል ጊዜ የማን ይሆናል? • በትዳር ፍቺ ምክንያት በሚደረግ የንብረት ክፍፍል መመለስ ካለባቸው አሻሚ ጥያቄዎች መካከል አንዱ ከጋራ ንብረታቸው የተገዛ የማይንቀሳቀስ ንብረት በህፃን ስም ያስመዘገቡ ባልና ሚስት በፍቺ ሰዓት በዚሁ ንብረት ክፍፍል ላይ ጭቅጭቅ መነሳቱ አይቀርም:: • ከዚህ በፊት ሕፃኑ ከራሱ ሀብት ወጪ አድርጎ የገዛው ወይም ያፈራው ንብረት መሆኑን ካላስረዳ የባልና ምስት ሀብት ነው ተብሎ ይወሰናል ነበር::ይሁን እንጂ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አድስ ውሳኔ ሰቷል:: በዚህ ጉዳዩ ሕጉ ምን ይላል? • አካለ መጠን ባልደረሰ ልጅ ስም የተመዘገበ የማይንቀሳቀስ ንብረት በህፃኑ በሕጋዊ መንገድ የተፈራ ንብረት ስለመሆኑ ግምት ሊወሰድ ይገባል፡፡ • ህፃኑ ንብረቱን ከራሱ የሃብት ምንጭ ወጪ አድርጎ ስለመግዛቱ አላስረዳም በሚል ምክንያት ንብረቱን ባልና ሚስት በጋብቻ ውስጥ ያፈሩት እንጂ የህፃኑ አይደለም በማለት መወሰን አግባብነት የለውም፡፡ • ባልና ሚስቱ ንብረቱን በራሳቸው ፈቃድ ከጋራ ንብረታቸው ወጪ በማድረግ አካለ መጠን ባልደረሰ ልጅ ስም የገዙ ቢሆንም እንዲህ ዓይነት ህፃናትን የሚመለከቱ ጉዳዮች የህፃናትን ደህንነትና ጥቅም በቀደምትነት ታሳቢ ማድረግ እና ለህፃኑ ጥቅም ተብሎ እንደተገዛ (እንደተፈራ) ንብረት ተደርጎ ሊወሰን የሚገባው ነው ተብሎ ተወስኗል። • ሰበር መ.ቁ 41/2010 geezlaws@gmail.com #Free_Services +251948449999 #All_Business_Laws & Businesses https://t.me/GeezLaws

  • 13 мая1 64963

    без подписи

  • 10 мая2 361743

    የመሬት ይዞታ መብት በይርጋ ኣይታገድም ፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ geezlaws@gmail.com #Free_Services +251948449999 #All_Business_Laws & Businesses https://t.me/GeezLaws

  • 5 мая2 3646

    https://www.youtube.com/live/09wACN5fAUk?si=g2IZQg5DuIbha-rH

  • 4 мая2 235716

    ስለ ኑዛዜ ከውርስ ሕግና ከሰበር ውሳኔዎች አንፃር! *** የኢትዮጵያ የውርስ ሕግ ኑዛዜ ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሰጠው ትርጉም ባይኖርም አንድ ኑዛዜ ህጋዊ ውጤት እንዲኖረው ማሟላት የሚገባቸውን መስፈርቶች ምን ምን እንደሆኑ በዝርዝር የሚያስቀምጡ የሕግ ድንጋጌዎችን ከፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 857 እስከ 908 ተደንግጎ እናገኘዋለን፡፡ በዚህ ጽሁፍ ኑዛዜ በምን አግባብ ቢደረግ በሕግ ዘንድ ውጤት ይኖረዋል፤በውርስ ሕጋችን ላይ የተቀመጡት የኑዛዜ አደራረግ ስርዓቶች አስገዳጅነታቸው እስከምን ድርስ እንደሆነና ኑዛዜ በፍርድ ቤት ቢጸድቅ ሊያስገኝ የሚችለው ውጤትና ባለመጽደቁ የሚያመጣው ተጽእኖ ምን እንደሆነ ከውርስ ሕግ እና አስገጋጅ ከሆኑ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ውሳኔዎች አንጻር በአጭሩ ዳሰሳ ለማድርግ ተሞክሯል፡፡ ለኑዛዜ ዋጋ መኖር አስፈላጊ የሆኑ የስረ ነገር ሁኔታዎች በፍትሐ ብሔር ህግ ከአንቀጽ 857 እስከ 879 የተደነገጉት ድንጋጌዎች ለኑዛዜ ዋጋ መኖር አስፈላጊ የሆኑ የሥረ ነገር ሁኔታዎች (essential condition of wills) አካትተው ተደንግገዋል፡፡ ከእነዚህ አጠቃላይ ደንጋጌዎች ለመረዳት እንደሚቻለው ለኑዛዜ ዋጋ መኖር አስፈላጊ የሆኑ የሥረ ነገር ሁኔታዎች በሁለት ከፍሎ ማየትና መተንተን ይቻላል፡፡ የመጀመሪያው የኑዛዜ ሁለንተናዊ ወይም ተፈጥሯዊ አስፈላጊ ነገር( inherent or intrinsic elements of will) የሚባለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በኑዛዜው ይዘት ላይ የሚያተኩርና ለሕግና ሞራል ተቃራኒ መሆን ወይም አለመሆኑን የሚቆጣጠሩ ናቸው፡፡ የኑዛዜ ሁለንተናዊ ወይም ተፈጥሯዊ ነገር የሚባለው ተናዛዡ ኑዛዜውን በሚፈጽምብት ወቅት የነበረው የአእምሮ ሁኔታ ወይም ኑዛዜ የማድረግ ሀሳብ የነበረው መሆኑ( animus testandi ) የምንለው ነው፡፡ የኑዛዜ ክርክር የሚነሳው ኑዛዜ አድርጊው ከሞተ በኋላ ስለሆነ ኑዛዜ አድርጊው በሙሉ ፍላጎቱና ሀሳቡ ኑዛዜውን ያደረገ ስለመሆኑ እንዴት እርግጠኛ መሆን ይቻላል የሚለው ነጥብ ነው፡፡ ይህን ለመረዳት የሚከተሉት ነጥቦች ከግምት ውስጥ መግባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሀ) ተናዛዡ ራሱ በሙሉ ሀሳቡ ኑዛዜ የፈጸመ መሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 857 በተገለጸው መሰረት ሟች ኑዛዜ የማድረግ ሀሰብና ፍላጎት ኖሮት እንደዚሁም የኑዛዜው ይዘት በመረዳት ኑዛዜ ማድረግ ያለበት እሱ ራሱ ብቻ መሆን እንዳለበት በግልጽ ደንግጓል፡፡ ህጉ የሟች ሀሳብ በሌሎች ሰዎች ማለትም በወኪሎች በኩል በኑዛዜ ላይ መግለጽ እንደማይገባው በመከልከል ኑዛዜውን የሟች የግል ስራና የራሱ የሀሰብ መግለጫ መሆን እንዳለበት በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ አንድ ሰው በሌላ ሰው በስሙ ኑዛዜ እንዲያደረግ ፤እንዲለውጥ ወይም እንዲሽር ስልጣን ሊሰጠው እንደማይችል አንድ ሰው ሌላ ሶስተኛ ወገን ወራሹን እንዴት እንደሚወስንና ውርሱ ለማን መተላለፍ እንዳለበት እንዲፈጽም ሊያደርግ እንደማይችል የውርስ ህግ ደነግጋል፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰበር መ/ቁጥር 134836 በቅጽ 22 ላይ በሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጓሜ ላይ እንደተመላከተው “ ኑዛዜ ጥብቅ የሆነ የግል ጠባይ ያለው እና በሟች ብቻ የሚፈጸም በመሆኑ ብዙ ሰዎች አንድ በሆነ ጽሁፋ በጋራ ማናዘዝ የማይቻልና ኑዛዜው ፈራሽ የሚያደርገው ነው፡፡ በመሆኑም በተደረገው ኑዛዜ በሟች የግል ንብረት ላይ ሌላ ሰው ጭምር በአንድ የኑዛዜ ሰነድ ላይ ተናዘው ከተገኙ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 858፤857 እና 880 ተከታዩ ድንጋጌዎች አንጻር ፍርድ ቤቶች ኑዛዜውን ፈራሽ ነው በማለት የሚሰጡት ውሳኔ የሚነቀፍበት ሕጋዊ መክንያት የለም” ሲል የሕግ ትርጓሜ ሰጥቷል፡፡ ለ የተናዛዡ ኑዛዜ የመፈጸም ችሎታ በሁለተኛ ደረጃ የኢትዮጲያ ሕግ የተናዛዡን ኑዛዜ የመፈጸም ሀሳብ (animus testandi) እያለው ኑዛዜ የፈጸመ መሆኑን ለማረጋገጥና ለኑዛዜው ዋጋ ለመስጠት ወይም ላለመስጠት እንደ መስፈርት የያዘው የተናዛዡን ኑዛዜ የመፈጸም ችሎታ (capacity make a will) ነው፡፡ የተናዛዡ ኑዛዜ የመፈጸም ችሎታ የሚመዘነው የተናዛዡ የሚፈጽመው ተግባር ኑዛዜ መሆኑንና የሚፈጽመው ኑዛዜ ይዘት በአግባቡ የሚረዳ መሆኑን ወይም አለመሆኑን በመመዘን ነው፡፡ እዚህ ላይ ግንዛቤ ሊያዝበት የሚገባው ነገር አንድ ሰው በሕግ ችሎታ ያለው መሆኑ አለመሆኑ ጉዳይ ኑዛዜ ለመፈጸም ካለው ችሎታ ጋር በቀጥታ ማይገናኝ መሆኑን ነው፡፡ በሕግ ችሎታ የሌላቸው ሰዎች ኑዛዜ ለመፈጸም ችሎታ ሊኖራቸው ይችላል። ======||===== geezlaws@gmail.com #Free_Services +251948449999 #All_Business_Laws & Businesses https://t.me/GeezLaws

  • 2 мая1 1347

    London Court Dismisses Bulk of Turkish Contractor’s Claims Against Ethiopia #Ethiopia: The London Court of International Arbitration has dismissed the bulk of a USD 979.9 million claim filed by Turkish company Yapi Merkezi Insaat against the Ethiopian Railway Corporation (ERC), according to sources familiar with the case. The company had sought compensation for damages and losses incurred during the construction of the Awash–Kombolcha–Woldia–Hara Gebeya railway infrastructure proje... 🔗 Read the full story: https://www.thereporterethiopia.com/50527/ ----------||---------- Stay connected with us for breaking news and updates: Facebook ↠ bit.ly/3fmc8YE X (Twitter) ↠ bit.ly/3nJLRpR Telegram ↠ bit.ly/37OFEnC YouTube ↠ tinyurl.com/5b798kj3 Instagram ↠ bit.ly/3RUPUB1 LinkedIn ↠ bit.ly/3H14CE8 Threads ↠ bit.ly/3Zn3Ib7 🔎 Looking for jobs? Visit EthiopianReporterJobs.com 📩 Got a tip? news.tips@ethiopianreporter.com

  • 29 апр.1 72095

    “Transformative Company Support Programme in Field of Digital Economy” (Call for Proposals), by GIZ’s Private Sector Dev't ETH (PSD-E) Project geezlaws@gmail.com #Free_Services +251948449999 #All_Business_Laws & Businesses https://t.me/GeezLaws

  • 28 апр.2 06581

    የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሰሚ ችሎት መዝገቦች ከፋይዳ መታወቂያ ጋር በማያያዝ ባላችሁበት ሆናችሁ መገልገል እንደምትችሉ ተገልፃል። ጥሩ እርምጃ ነው። geezlaws@gmail.com #Free_Services +251948449999 #All_Business_Laws & Businesses https://t.me/GeezLaws

  • 26 апр.2 03487

    የውጭ አገር የሕክምና አገልግሎት ቅብብሎሽ ሥርዓት (ሪፈራል) ማስፈፀሚያ መመሪያ ቁጥር 1128/2018 Abroad Medical Service Referral Directive No 1128/2026 www.geezlaw.com | https://geezlaw.com/ geezlaws@gmail.com #Free_Services +251948449999 #All_Business_Laws & Businesses https://t.me/GeezLaws