tgindex
Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

Статистика

Official Great Ethiopian Run Telegram Channel. Call 0116635757 for more details.

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
30
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
6 170
+4 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
2 980
28 постов
Вовлечённость
48,3%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 30
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
934
1/48двое суток
1 070
1/72трое суток
1 154

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 13 авг.1 054166

    🔥እየደረሰ ነው⏳ 100 ቀናት ብቻ ቀርተዋል! 🔥 በ100 ቀናት ውስጥ የአፍሪካ ትልቁ 10 ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ሩጫ ይከሔዳል 🇪🇹 እርስዎም ሌላ የማይረሳ የሩጫ ቀን ለማሳለፍ ይዘጋጁ! 🏃🏾‍♀️🏃🏾‍♂️ 2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. በባንክ ኦፍ አሜሪካ የቀረበ 💫 #GreatEthiopianRun #MyRunMyColor #100DaysToGo #Ethiopia

  • 7 авг.2 436

    без подписи

  • 7 авг.2 435

    без подписи

  • 7 авг.2 21618

    без подписи

  • 7 авг.2 180157

    የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10 ኪ.ሜ. የመደበኛ ምዝገባ በሰባት ቀናት ጊዜ ውስጥ ተጠናቀቀ 60,000 ሯጮችን የሚያስተናግደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. ምዝገባ ባለው ከፍተኛ ፍላጎት ምክንያት በግለሰቦች እና ድርጅቶች የሚደረገው የምዝገባ ጊዜ እያጠረ መጥቷል። በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ካለው ከፍተኛ ምላሽ የተነሳ በባንክ ኦፍ አሜሪካ የስያሜ አጋርነት የሚቀርበው የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. መደበኛ ምዝገባ ተጠናቋል። ከማክሰኞ እስከ ማክሰኞ የዘለቀው የሰባት ቀናት የምዝገባ ጊዜ ውድድሩ ከተጀመረበት 1994ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት የ26 ዓመታት ታሪክ ውስጥ አጭሩ የምዝገባ ጊዜ ሆኖ ተመዝግቧል። የዘንድሮው ምዝገባ ይበልጥ የቀለለው ግለሰቦች በቴሌብር (telebirr) መተግበሪያ በኩል በመጠቀም እና ሙሉ በሙሉ ዲጂታል በሆነ የምዝገባ ሂደት ነው። ነፃ የውድድር ምዝገባ፣ የበጎ አድራጎት ስራዎች ገቢ ማሰባሰብ እና የሰዓት መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂን በስፋት መጠቀም ከባንክ ኦፍ አሜሪካ ጋር በተደረገው አጋርነት የመጡ አዳዲስ ስኬቶች አንዱ ተደርጎ ተወስዷል። ለዘንድሮው ውድድር ከተዘጋጁት ጠቅላላ 60,000 ቦታዎች ውስጥ 3000 የሚሆኑት ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተናን ለሚወስዱ ተማሪዎች በነፃ የሚሰጡ ሲሆን፣ ይህም አጋርነቱ ሰፊ የኅብረተሰብ ክፍል በውድድሩ ላይ እንዲሳተፍ ለማድረግ ያለውን ዓላማ የሚያሳይ ነው። በተጨማሪም በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተመረጡ ሦስት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ገቢ ለማሰባሰብ የታለመውን ‘ሌሎችን ለመርዳት ሮጣለሁ’ የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻ በጥቅምት ወር 2019ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ ይጀመራል። ቀሪ ጥቂት የምዝገባ አማራጮች የዚሁ ዘመቻ አካል ለሆኑት እና ለሽያጭ ከሚቀርቡት የበጎ አድራጎት ቦታዎች ላይ ይደረጋል። ሁሉም የበጎ አድራጎት ቦታዎች ሙሉ በሙሉ ሲያዙ፣ ውድድሩ በአጠቃላይ 60,000 ተመዝጋቢዎች ይኖሩታል።

  • 3 авг.3 3911447

    የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. ምዝገባ ነገ ይጠናቀቃል። ምዝገባው በቴሌብር በኩል ብቻ እየተከናወነ ሲሆን ያሉን ጥቂት ቀሪ ቦታዎች ሳይሞሉ በፊት ይመዝገቡ። ✨ሩጫዬ ቀለሜ ✨ ✨ 2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. በባንክ ኦፍ አሜሪካ የቀረበ ✨ #GreatEthiopianRun #MyRunMyColor #Telebirr

  • 2 авг.4 1761651

    ለታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ - በቴሌብር ይመዝገቡ! ከ60ሺህ ተሳታፊዎች መሐከል አንዱ ይሁኑ! የምዝገባ ዋጋ - ከመስቀል አደባባይ ለሚጀምረው ቀይ መነሻ 790 ብር - ከግዮን ሆቴል ፊት ለፊት ለሚጀምረው እና የመሮጫ ቁጥር ለሚኖረው አረንጓዴ መነሻ 950 ብር የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. በባንክ ኦፍ አሜሪካ የቀረበ ✨ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ✨ #GreatEthiopianRun #MyRunMyColor

  • 19 июл.4 638134

    አትሌት ሴና ገመቹ እና ራሔል እምቢበል የኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በሐረር አሸናፊዎች ሆኑ መነሻ እና መድረሻውን ሐረር በር ላይ በማድረግ ፕሮፌሽናል አትሌቶችእና ከአዲስ አባባ ተጓዥ ተሳታፊዎችን ያካተተ ልዩ የ10ኪ.ሜ. ውድድር የተደረገ ሲሆን በወንዶች አትሌት ሴና ገመቹ በ32:04:77 በመግባት የአንደኛነት ደረጃን ሲይዝ ምህረት አወቀ ሁለተኛ እና ኢብራሒም መሐመድ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ውድድራቸውን ጨርሰዋል። በሴት አትሌቶች ውድድር ራሔል እምቢበል በ41:43:23 በመግባት ቀዳሚውን ደረጃ ይዛ ስታጠናቅቅ አምራን ሸምሱ ሁለተኛ እና አዚዛ ሙክታር ሶስተኛ ደረጃ ተከታትለው ገብተዋል።   በተመሳሳይ ርቀት ውድድራቸውን ያደረጉት የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ተጓዥ ተሳታፊዎች መሐከል በተካሔደው ውድድር በወንዶች ዮሐንስ አየልኝ እንዲሁም በሴቶች ርብቃ ግርማ አሸናፊዎች ሆነዋል። ዛሬ በድምቀት በተከናወነው ውድድር ላይ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ መኪዩ መሀመድ፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር)፣ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች በክብር እንግድነት ታድመዋል። ከ16 አመት በታች ታዳጊ አትሌቶች የተሳተፉበት የ1.5 ኪ.ሜ.ውድድር እና ከ11 አመት በታች ልጆች የተሳተፉበት የ1 ኪ.ሜ.ውድድር ሌላው የዕለቱ ድምቀት ነበር፡፡ ሐረር የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ስድስተኛ እና የመጨረሻዋ መዳረሻ ከተማ ስትሆን ዛሬ ከተካሔደው የሩጫ ውድድር ባሻገር ትናንት የጀጎል ግቢ የተጎበኘበት የእግር ጉዞ ተካሂዷል፡፡ በተጨማሪም ምሽት ላይ በዘንድሮው የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ በሁሉም ከተሞች በስኬት እና በድምቀት ለመካሄዱ አስተዋፅዖ ላበረከቱ አካላት እና ግለሰቦች የምስጋና፣ ዕውቅና እና ሽልማት ምሽት ተካሂዷል፡፡ የ2018 ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ መነሻውን ደብረብርሃን በማድረግ በሐዋሳ፣ ጅማ፣ ቦቆጂ፣ አርባምንጭ እና ዛሬ ማጠቃለያውን ሐረር ላይ አድርጓል። በስድስቱም ከተሞች ላይ በመገኘት ዉድድሮቻቸውን ላደረጉ 43 ተወዳዳሪዎች ሲገጣጠም የኢትዮዽያ ካርታ ቅርፅ ያለው ልዩ ሜዳሊያ ተበርክቶላቸዋል። ይህን ውድድር ከታላቁ ሩጫ በኢትዮዽያ ጋር በመሆን በስያሜ አጋርነት አብሮ የሚሰራው ኢትዮ ቴሌኮም ነው። በተጨማሪም የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ዳሽን ባንክ፣ ፔፕሲ፣ ፋብ ሳሙና፣ ቶፕ ውኃ፣ አፍራን ሆስፒታል፣ ቻናል 1 ቲቪ እና የሐረር ቱሪዝም ኮሚሽን የውድድሩ አጋሮች ናቸው።

  • 19 июл.2 9711

    без подписи

  • 19 июл.3 6641

    без подписи

  • 19 июл.3 8782

    без подписи

  • 19 июл.3 4741

    без подписи

  • 19 июл.3 0371

    без подписи

  • 19 июл.3 1193

    без подписи

  • 19 июл.2 79531

    без подписи

  • 18 июл.3 08744

    ጋዜጣዊ መግለጫ የ2018 ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ውድድር ነገ በሐረር ፍፃሜውን ያገኛል፡፡   የ2018 ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ውድድር የመጨረሻ መዳረሻ የሆነውና ለመጀመሪያ ጊዜ በሐረር ከተማ የሚደረገው የ2018 ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በሐረር ነገ ጠዋት ይካሔዳል። ዛሬ ረፋድ በሐረር ኢኮ ቱሪዝም ፓርክ በነበረ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተነገረው ውድድሩ ነገ ማለዳ ከ1:00 ሰዓት ጀምሮ መነሻ እና መድረሻውን በዱቅ በር / ሐረር በር ፊት በማድረግ ይከናወናል።   ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሐረር ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያዘጋጀው ውድድር ከመደበኛው የሩጫ ውድድር ባሻገር ዛሬ ማምሻውን የእግር ጉዞ እና የጀጎል ግንብን ውስጥ የመጎብኘት እንዲሁም በአጠቃላይ የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ጉዞ ላይ አብረውት ለነበሩ ተሳታፊዎች እና አጋሮች ዕውቅና የሚሰጥባቸው መርኃ-ግብሮችንም ያካተተ መሆኑ ይፋ ተደርጓል፡፡ በመግለጫው የሐረር ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሚ አብዱልዋሲ በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸው “ይህ ታላቅ ስፖርታዊ ክንውን ሀገራችንን እና ውብቷን ሐረርን በስፖርት ቱሪዝም (Sports Tourism) ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ትልቅ ፋይዳ አለው። በዚህ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የመጣችሁ ሁሉ ፤ በሐረር ቆይታችሁ የማይረሳ ውብ ጊዜን እንደምታሳልፉ ሙሉ እምነት አለኝ” የሐረርን ዝግጁነት አመላክተዋል።   በነገው የሩጫ ውድድር ፕሮፌሽናል አትሌቶችን ጨምሮ ከአዲስ አበባ ወደ ሐረር የመጡ 110 ተሳታፊዎች በ10ኪ.ሜ. ርቀት ይወዳደራሉ፡፡ በተጨማሪም 2500 የሐረር እና አካባቢው ነዋሪዎች በ5ኪ.ሜ. ውድድር ላይ ተሳታፊ ሲሆኑ ለወደፊት ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት ታስቦ በሚዘጋጀው የታዳጊዎችና ህፃናት ውድድሮች ላይ 500 ተሳታፊዎች እንደሚወዳደሩ ይጠበቃል። በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የቱሪዝም ሚኒስቴርን በመወከል ንግግር ያደረጉት አቶ ንጉሴ ክብሩ በበኩላቸው “የዘንድሮውን የዓመቱን የመጨረሻ ማጠቃለያ ውድድር በታሪካዊቷ የሐረር ከተማ ሲደረግ ያለ ምክንያት አይደለም። ሐረር ባህላዊ፣ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ መስህቦቿን በማስተዋወቅ፣ ከስፖርት ባሻገር ቱሪዝምን ለማሳደግ ከተከናወኑ በርካታ ስራዎች አንጻር በለውጡ ሂደት በሞዴልነት የምትታወቅ ከተማ  በመሆኗ ነው” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።   ኢትዮ ቴሌኮምን በመወከል ንግግር ያደረጉት የኢትዮ ቴሌኮም የምዕከላዊ ምስራቅ ክልል ዳይሬክተር አቶ ቸሩ ጅማ “በግንባር ቀደምት ከ132 ዓመታት በፊት፤ ከአዲስ አበባ እስከ ሐረር በተዘረጋው ቀጭን ሽቦ በኩል የተገመደው የሐረርና የኢትዮ ቴሌኮም የታሪክ ግንኙነት፤ ዛሬም በረቀቀው ዲጂታል ሞገድ ይበልጡኑ ጠብቋል። የ2018 ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በሐረር የስያሜ አጋር በመሆኑ ታላቅ ኩራት ይሰማዋል” ብለዋል።   ይህን ውድድር ከታላቁ ሩጫ በኢትዮዽያ ጋር በመሆን በስያሜ አጋርነት አብሮ የሚሰራው ኢትዮ ቴሌኮም ነው። በተጨማሪም የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ዳሽን ባንክ፣ ፔፕሲ፣ ፋብ ሳሙና፣ ቶፕ ውኃ፣ አፍራን ሆስፒታል፣ ቻናል 1 ቲቪ እና የሐረር ቱሪዝም ኮሚሽን የውድድሩ አጋሮች ናቸው።

  • 18 июл.3 1673

    без подписи

  • 18 июл.3 3153

    без подписи

  • 18 июл.2 3143

    без подписи

  • 18 июл.2 2463

    без подписи