WORLD CUP 2026 || የዓለም ዋንጫ
Статистикаየ2026 የዓለም ዋንጫ ወቅታዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ቻነል ነው። ስለተቀላቀሉን እናመሰግናለን።
- Последний пост
- 7 июн.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ልዮኔል ሜሲ ክብረወሰኑን በዕጁ ያስገባ ይሆን ? በዓለም ዋንጫ ታሪክ በርካታ ግቦችን በማስቆጠር ቀዳሚው ተጫዋች የጀርመኑ ሚሮስላቭ ክሎዝ በ16 ግቦች ነው። የ2022 ዓለም ዋንጫ ሻምፒዮኑ ልዮኔል ሜሲ በአምስት የአለም ዋንጫዎች ተሳትፎው 13 ግቦችን አስቆጥሯል። ከአራት ቀናት በኋላ በሚጀምረው የዓለም ዋንጫ ላይ አራት ግቦችን ማስቆጠር ከቻለ የሚሮስላቭ ክሎዝን ክብረወሰን ማሻሻል ይችላል። ከልዮኔል ሜሲ በተጨማሪም በ2 የዓለም ዋንጫዎች 12 ግቦችን ያስቆጠረው ኪልያን ምባፔ ሌላኛው የክብረወሰኑ ተፎካካሪ ተጫዋች ነው።
የ17 ዓመቱ የሜክሲኮው ጂልቤርቶ ሞራ በ2026 የዓለም ዋንጫ በዕድሜ ትንሹ ተጫዋች ነው። በመክፈቻው ጨዋታ የመሰለፍ ዕድል ካገኘ ከፔሌን በመቀጠል በዓለም ዋንጫ ታሪክ 6ኛው በዕድሜ ትንሹ ተጫዋች ይሆናል። በዓለም ዋንጫ ታሪክ በትንሽ ዕድሜያቸው የተጫወቱ ተጫዋቾች ...... 🇮🇪ኖርማን ኋይትሳይድ (17 ዓ ፤ ከ41 ቀናት) 🇨🇲ሳሙኤል ኤቶ (17 ዓ ፤ ከ99 ቀናት) 🇳🇬ፌሙ ኦፓቡንሚ (17 ዓ ፤ ከ101 ቀናት) 🇨🇲ሰለሞን ኦሎምቤ (17 ዓ ፤ ከ185 ቀናት) 🇧🇷ፔሌ (17 ዓ ፤ ከ235 ቀናት)
በ2022 የዓለም ዋንጫን ካሳካው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች መካከል 17 በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ሀገራቸውን ይወክላሉ።
ኬፕ ቨርዴ ፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ፣ ኮትዲቯር ፣ ዩራጋይ ፣ ኩራካኦ እና ሴኔጋል በዓለም ዋንጫ ቡድናቸው አንድም ተጫዋች ከሀገራቸው ሊጎች አላካተቱም። ኳታር እና ሳዑዲ አረቢያ ደግሞ ከመረጧቸው 26 ተጫዋቾች 25 በሀገራቸው ሊግ የሚጫወቱ ናቸው።
የ43 ዓመቱ የስኮትላንድ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ክሬይግ ጎርደን በ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ በዕድሜ አንጋፋው ተጫዋች ነው።
የ2026 ዓለም ዋንጫ 5 ቀናቶች ብቻ ቀርተዋል
አጫጭር የዝውውር መረጃዎች 👉ባየር ሙኒክ የሊቨርፑሉን የ17 ዓመት ተጫዋች ርዮ ንጉሞሀን ለማስፈረም እንቅስቃሴዎች ማድረግ መጀመሩ ተገለፀ። 👉አርሰናል የባየር ሊቨርኩሰኑን የ19 ዓመት የመስመር አጥቂ ከሪም አላጅቤጎቪችን ለማስፈረም ከወኪሎቹ ጋር ንግግር ማድረግ ጀምሯል። 👉ኒውካስትል ዩናይትድ የኦሳሱናውን የ22 ዓመት ሁለገብ አጥቂ የአንቶኒ ጎርደን ምትክ አድርጎ ለማስፈረም ፍላጎት አሳይቷል። 👉ኤነሪኬ ሪኬልሜ የሪያል ማድሪድ ፕሬዝዳንት ሆነው ከተመረጡ የርገን ክሎፕን በዋና አሰልጣኝነት እንደሚሾሙ አስታወቁ። 👉አሰልጣኝ ሉችያኖ ስፓሌቲ የአትሌቲኮ ማድሪዱን የፊት አጥቂ አሌክሳንደር ሶርሎዝን ለማስፈረም ከተጫዋቹ ጋር በግል መነጋገራቸው ተገለፀ። 👉የፌነርባቼው ዕጩ ፕሬዚዳንት ሀካን ሳፊ ሜሰን ግሪንዉድን ለማስፈረም ከተጫዋቹ ጋር በግል ጥቅማጥቅሞች ዙሪያ ከስምምነት መድረሳቸውን ሲዘገብ ተጫዋቹም ሳፊን ኢነስታግራም ላይ በመተከል የማረጋገጫ ምልክት ሰጥቷል።
⚽ አርሰናል በርንሌይን 1 ለ 0 ባሸነፈበት ጨዋታ ላይ ግቡን ያስቆጠረው ካይ ሀቨርዝ የለበሰው ማልያ በ30,872 ዩሮ ተሽጧል።
без подписи
⚽ በዓለም ዋንጫ የሚደረጉ ጨዋታዎች ከመጀመራቸው አስቀድሞ በምስሎቹ ላይ በምትመለከቱት መልኩ ዝግጅቶች ይደረጋሉ። የሁለቱ ቡድን ተጫዋቾች በሜዳ መሀል ክቡን ይዘው ብሔራዊ መዝሙራቸውን ይዘምራሉ።
⚽ "ኔይማር ጁንየር በቀጣይ ሳምንት ወደ ቡድን ልምምድ ሊመለስ ይችላል" አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ
ምድብ አስራ ሁለት 🏴 እንግሊዝ 🇭🇷 ክሮሽያ 🇵🇦 ፓናማ 🇬🇭 ጋና
ምድብ አስራ አንድ 🇵🇹 ፖርቹጋል 🇨🇩 ኮንጎ 🇺🇿 ኡዝቤኪስታን 🇨🇴 ኮሎምቢያ
ምድብ አስር 🇦🇷 አርጀንቲና 🇩🇿 አልጄሪያ 🇦🇹 ኦስትሪያ 🇯🇴 ጆርዳን
ምድብ ዘጠኝ 🇫🇷 ፈረንሳይ 🇸🇳 ሴኔጋል 🇮🇶 ኢራቅ 🇳🇴 ኖርዌይ
ምድብ ስምንት 🇪🇸 ስፔን 🇨🇻 ኬፕ ቨርዴ 🇺🇾 ዩራጋይ 🇸🇦 ሳዑዲ አረቢያ
ምድብ ሰባት 🇧🇪 ቤልጅየም 🇪🇬 ግብፅ 🇮🇷 ኢራን 🇳🇿 ኒው ዝላንድ
ምድብ ስድስት 🇳🇱 ኔዘርላንድስ 🇯🇵 ጃፓን 🇸🇪 ስዊድን 🇹🇳 ቱኒዚያ
ምድብ አምስት 🇩🇪 ጀርመን 🇨🇼 ኩራካኦ 🇨🇮 ኮትዲቯር 🇪🇨 ኢኳዶር
ምድብ አራት 🇺🇸 አሜሪካ 🇵🇾 ፓራጓይ 🇦🇺 አውስትራሊያ 🇹🇷 ተርኪዬ