ማርዳ ሚዲያ-Marda Media
Статистика- Последний пост
- 30 мая
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
"መንገድ ተዘግቷል" የሚለው ወሬ የጽንፈኛው የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ነው ተባለ የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር) "መንገድ ተዘግቷል" በሚል የሚወራው ወሬ የጽንፈኛ ኃይሉ የተለመደ የሐሰት ፕሮፖጋንዳ መሆኑን ገለጹ። በአሁኑ ወቅት በክልሉ መደበኛም ሆኑ ወቅታዊ ተግባራት ያለምንም ችግር እየተከናወኑ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው፣ የምርጫ ቁሳቁስና የአፈር ማዳበሪያ በተፈለገው አካባቢ ሁሉ በአግባቡ እየደረሰ መሆኑን አስታውቀዋል። በመሆኑም ኅብረተሰቡ ለዚህ ዓይነቱ ማደናገሪያ ጆሮ ሳይሰጥ ዕለታዊ ሥራውን ያለምንም ስጋት እንዲያከናውን አሳስበዋል። በተጨማሪም ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅና መራጩ ሕዝብ ያለ ምንም ስጋት ድምፁን መስጠት እንዲችል በየጣቢያዎቹ በቂ የጸጥታ ዝግጅትና ስምሪት መደረጉን ኃላፊው አረጋግጠዋል። የጸጥታ ኃይሉ ሰላምን የማስከበር ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ ከመሆኑ ባለፈ፣ መላው ማኅበረሰብ በተለይም ወጣቶች አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ለጸጥታ አካላት በመጠቆም ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ በንቃት እየተሳተፉ እንደሚገኙ የአሚኮ ዘገባ ያመላክታል።
"ከፅምዶ ጋር የሽብር ጋብቻ አልፈፅምም" ፋኖ አስረስ ማረ የአፋብን አፈ ቀላጤ ፋኖ አስረስ ማረ ከፅምዶ ጋር የሽብር ጋብቻ እንደማይፈፅም በይፋ አቋሙን ገልጿል። ፋኖ አስረስ ማረ በኢኤምኤስ (EMS) ሚዲያ ቀርቦ እንደተናገረው፣ ፅምዶ በሻዕቢያ የጦረኝነት ስሌት የሚዘወር፣ ጦር ሰባቂ እና እንደ ተርብ ተናዳፊ የሽማግሌ አሸባሪዎች ስብስብ ነው። አክሎም ዱር ለቤቴ ብለው የሚታገሉ ንጹህ አርበኞች ዘላለም አፈሙዝን ይዘንና ቃታ ስበን እንድንኖር እንዲሁም ለእነሱ የተንጋደደ አስተሳሰብ ታዛዥና አጎብዳሽ እንድንሆን ነው የሚፈልጉት ሲል አብራርቷል። ፅምዶን በይፋ በመቃወሙ እና አቋሙን በአደባባይ በመግለፁ ምክንያት፣ የሻዕቢያ እና የህወሓት ሰዎች ፋኖ አስረስ ማረ ከአፋብን ኃላፊነቱ እንዲታገድና እርምጃ እንዲወሰድበት ለዘመነ ካሴ ጥብቅ ትዕዛዝ መስጠታቸው ታውቋል።
ቀይ ባህር የኢትዮጵያ መልህቅ ፣የዜጎች ሚና ከብሔራዊ ጥቅም ዓይን አሁንም መነሻችን በተለይ በእኔ ዘመን ላሉ የትውልዱ አካል እና በትናንትና ሀቲት ላይ ሳይኖሩ ለአገራቸው ቀና ሀሳብ ላላቸው በውስጣቸው የአገር ፍቅር ንዳድ ሌት ከቀን ለሚሳስባቸው ለእኔ ዘመን ትውልድ አካል(As a member of this generation)ይህ እይታዬ (perspective )እንዲሆንልልኝ እመኛለሁ ። ትናንት የታላቁ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሲገነባ በቀንነት ልማትን እና እድገት ሲደገፉ የነበሩ ዜጎች ይደርስባቸው የነበረው ያልተገባ አስተያየት ቆም ብሎ በማስተዋል ማን ያውራ የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ እንዲሉ አባው ሳይረፍድብን በክቡር የኢ.ፊ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከሰሞኑ በህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት ያቀረቡትን ሀሳብ በመመልከት እንደ ዘመኑ የትውልድ አካል በትንሹ ከቀሰምኩት (Global studies and international relations ) የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት አኳያ የግል ምልከታዬን አካፍላለሁ ። የኢትዮጵያ ወደብ አልባነት (Landlocked status) ለኢኮኖሚያዊና ለፀጥታ ችግሮች ዋነኛ መንስዔ መሆኑን በማመን፣ቀይ ባህርን በሰላማዊ መንገድ ማግኘት የሀገር ህልውና ጉዳይ ነው። ይህን ታሪካዊና ስትራቴጂያዊ መሻት ለማሳካት ዜጎች የሚከተሉትን ሚናዎች መጫወት ይገባቸዋል።በሀገራዊ መግባባት እና አንድነት ላይ መስራት (የውስጥ መደመር) ብሔራዊ ጥቅም ማስከበር የሚጀምረው በጠንካራ የውስጥ አንድነት ነው፥ዜጎች በሁሉም ልዩነታቸው "በመደመር" መንፈስ በመተባበር፣ የጋራ ሀገራዊ አጀንዳዎችን መደገፍ አለባቸው። የዜጎች ሚና በተለያዬ ሀሳቦች ያለመከፋፈል በቀይ ባህር ዙሪያ ያሉ ጥያቄዎችን ከፓርቲና ከማንነት ፖለቲካ በላይ በማስቀደም፣ለብሔራዊ ዓላማ በጋራ መቆም ይገባል።አሉባልታዎችን መዋጋት በዘመነ ድህረ እውነት ( misleading content deliberately spread to deceive people ) በዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ዙሪያ የሚነሱ የውስጥና የውጭ የጥላቻና የጥፋት ወሬዎችን በእውነት ላይ በተመሠረተ ግንዛቤ በማሸነፍ በሁሉም አውዶች ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል። በዲፕሎማሲያዊ ጥረት ዙሪያ ድምጽ መሆን (የውጭ መደመር) ኢትዮጵያ የምትመርጠው መንገድ የኃይል ሳይሆን የሰላማዊ ድርድርና ትብብር መሆኑን ለዓለም ማሳመን(Collaboration,not confrontation)። የዲያስፖራው ሚና በውጭ ሀገር በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን( ከምናባዊ ሀገር )በመውጣት የአገራቸውን የባሕር በር ጥያቄ ዓለም አቀፍ ሕጎችንና ምክንያቶችን መሠረት በማድረግ ለሚመለከታቸው አካላት ማስረዳት፣ የሎቢ( Looby )ሥራ መሥራት እና ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን መደገፍ ይገባቸዋል ።ይህ ጊዜ እንደትናንቱ እንዳይቆጨን በአስታውሎት ማጤን ያስፈልጋል ። እውቀትን ማጋራት(Dissemination, knowledge transfer, communication, and education) የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ፣ምሁራን፣ የሕግ ባለሙያዎችና የታሪክ ተመራማሪዎች ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት መብቷን የሚያረጋግጡ ታሪካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ዓለም አቀፍ የሕግ መረጃዎችን አጥንተው ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ( International community) በማቅረብ ለህዝባቸው ያላቸውን ወገንተኝነት ማሳየት አለባቸው ። ለቀይ ባህር ተጋሪነት ጥያቄ መሠረቱ ጠንካራ ኢኮኖሚና ብሔራዊ አቅም ነው። ወደብ ማግኘት ዋናው ግብ አይደለም፤ ነገር ግን ወደቡን በብቃት መጠቀም መቻል ነው።ምርታማነትን ማሳደግ እያንዳንዱ ዜጋ በየሥራው ምርታማነትን በመጨመር የሀገርን ኢኮኖሚ ማጠናከር ይኖርበታል።ጠንካራ ኢኮኖሚ የዲፕሎማሲው አውራ ክንድ ነው በእጥፍ እያደግን እና እየተለወጥን ስንመጣ በኢንቨስትመንት አቅም እና እድል የኢትዮጵያ ዲያስፖራና ባለሀብቶች (የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ) ወደፊት ለሚከፈቱ የሎጂስቲክስና ወደብ ልማት ፕሮጀክቶች ፋይናንስና እውቀት በማፍሰስ የባህር በርን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይችላሉ ። ለቀጣናዊ ሰላም መስበክ (የሰላም መደመር) ቀይ ባህር መልህቅ እንዲሆን የሚቻለው ቀጠናው ሲረጋጋ ብቻ መሆኑን በመገንዘብ በልዩ ልዩ መንገድ ስለ ሰላም አስፈላጊነት እና ጥቅም በሚገባ መግለጥ ይገባል ከእያንዳነዱ ሀገር ወዳድ ዜጋ ይጠበቃል ። አዎንታዊ ትርክት መፍጠር ( Pragmatic narratives-self-interests, national aspirations, and global complex interdependence) ኢትዮጵያ ወደብ የምትፈልገው ጎረቤቶቿን ለመጉዳት ሳይሆን የሁሉንም ወገን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር መሆኑን የሚያሳይ አዎንታዊ መልእክት ማስተላለፍ፤ቀይ ባህር የኢትዮጵያ መልህቅ እንዲሆን የዜጎች ተግባር የተናጠል ትርፍን ትቶ ለጋራ ብሔራዊ ጥቅም በጠንካራ የ"መደመር" መንፈስ መቆም ነው። ይህ የአስተሳሰብ ለውጥ ወደ አንድነት፣ ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬ እና ቀጣናዊ ሰላም የሚያደርስ ዘላቂ የሀገር ህልውና ዋስትና በመሆኑ ዛሬን ከተጉበት ለሀገር እና ለህዝብ የሚጠቅም ዘላቂ ውጤት በትብብር መስራት ያስፈልጋል ። በቀጣይነትም ከዚህ አጀንዳ እና ሀገራዊ ጥቅም አንፃር የሚኖረኝን መረዳት አካፍላለሁ ። በሀብታሙ ደባሱ አዲሱ
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
የ2 ደቂቃ ቪዲዮ በማየት ብቻ የሚከፍል አፑ አውርደው እንደከፈቱ 10 $ ይከፍላል። https://app.getlee.co/r/25b8262ccf
በማህበራዊ ሚዲያ በከንቱ የምናጠፋውን ጊዜ በኦንላይን ገንዘብ እንስራበት። ምንም ክፍያ አትጠየቁም። Let’s make money online by using the time we waste on social media. No payment required. ዝርዝር መረጃ ለማግኘት 👇 https://t.me/+PVdCedKTPuI3MDg0
ዝርዝር መረጃ ለማግኘት 👇 https://t.me/+PVdCedKTPuI3MDg0
አቢሲኒያ ባንክ አንዱ የክፍያ አማራጭ ሆኖ መጥቷል
በትላንቱ የኢትዮጵያ የደረጃ ሰንጠረዥ መሰረት ይህ ሰው በቀን 60ሺ ብር ገቢ አግኝቷል።
250 የነዳጅ ቦቴዎች እና 19 ማደያዎች ለስድስት ወራት ከግብይት ታገዱ አለአግባብ ትርፍ ለማግኘት በማሰብ ከ10 እስከ 15 ቀናት በጢሻ ውስጥ ተደብቀው በነበሩ 250 የነዳጅ ቦቴዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ። ከነዳጅ ምርቶች ስርጭትና ግብይት ጋር ተያይዞ በሚስተዋሉ ሕገወጥ ተግባራት ላይ መንግስት ጠንካራ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑንም አስታውቋል። የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ ከሰሞኑ አለአግባብ ትርፍ ለማግኘት በማሰብ ከ10 እስከ 15 ቀናት በጢሻ ውስጥ ተደብቀው በነበሩ 250 የነዳጅ ቦቴዎች ላይ ቅጣት መጣሉን ገልጸዋል። በዚህም ቦቴዎቹ ለስድስት ወራት ምንም አይነት የነዳጅ ምርት እንዳያዘዋውሩ ታግደዋል። በዚህ ሕገወጥ ተግባር ተባባሪ የነበሩ 19 ማደያዎችም ለስድስት ወራት ከግብይቱ መታገዳቸው ተገልጿል። ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ቅጣት እንደተጣለባቸውም ጠቅሰዋል። 35 ማደያዎች ተመሳሳይ እርምጃ እንደተወሰደባቸውም ሚኒስትሩ አክለው ተናግረዋል። 385 ሺህ ሊትር ነዳጅ በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወር ተወርሶ 27 ሚሊዮን ብር ለመንግስት ገቢ መደረጉንም ጠቅሰዋል። በቀጣይ ከዲጅታል የግብይት ሥርዓት ውጭ ግብይት የሚፈጽሙ ማደያዎችን ከንግድ ሥርዓቱ የማስወጣት እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል ብለዋል። ሚኒስትሩ መንግስት እየወሰደ ያለው ጠንካራ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል። በሌላ በኩል፤ ባለፉት ስድስት ወራት መንግስት 137 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ጥቅል የነዳጅ ድጎማ ማድረጉን ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገልፀዋል።ከጥቅል ድጎማው ውጪ የህዝብ ትራንስፖርት ማመላለሻና የከተማ አውቶብሶችን ታሳቢ ላደረገው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ባለፉት ስድስት ወራት 463 ሚሊዮን ብር መንግስት ድጎማ ማድረጉን አንስተዋል። (ኢቢሲ)
የደቡብ ምዕራብ ክልል መንግሥት ሠራተኞች ደሞዛቸው ያለ ፈቃዳቸው በመቆረጡ ምክንያት የሥራ ማቆም አድማ ጀምሩ‼️ የደቡብ ምዕራብ ክልል ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በተለይ የመምህራንን ደሞዝ በማዘግየት ይቀርብበት የነበረው ተደጋጋሚ ቅሬታ፣ አሁን ላይ ከሠራተኛ ፈቃድ ውጭ ደሞዝ ወደ መቁረጥ መሸጋገሩ የመንግሥት ሠራተኞችን አስቆጥቷል፡፡ ሠራተኞቹ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ለአንድ ዓመት ያክል በየወሩ ከደሞዛቸው ላይ 10 በመቶ እንዲቆረጥ የተላለፈው ውሳኔ ተግበራዊ ተደርጓል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በከፋ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች የሥራ ማቆም አድማ መደረጉን ከቅሬታ አቅራቢዎች ሰምታለች፡፡ ለልማት በሚል ምክንያት የመንግሥት ሠራተኛው ሳይስማማ የተጀመረው የደሞዝ መቁረጥ ቅሬታ የፈጠረው፣ ከሕግ አግባብ ውጪ የሆነና ከወቅቱ የኑሮ ውድነት ጋር የማይስማማ ሀሳብ በመሆኑ ነው ተብሏል፡፡ በትናንትናው ዕለት የሥራ ማቆም አድማ አድርገው ሰልፍ ከወጡ የመንግሥት ሠራተኞች መካከል በከፋ ዞን የጊምቦ ወረዳ የሃይስኩል መምህራን ይገኙበታል፡፡ መምህራኑ ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፣ ክልሉ ከተመሠረተ ጀምሮ እስካሁን የዘለቀው የደሞዝ መጓተት ችግር ሳይፈታ፣ በችግር ላይ ችግር የሚፈጥር የደሞዝ መቁረጥ ውሳኔ መምህራንን በእጅጉ አስቆጥቷል፡፡ “ልማት የሚጠላ ሰው የለም።” ያሉት መምህራኑ፣ መጀመሪያ የመንግሥት ሠራተኛው ራሱንና ቤተሰቡን በአግባቡ ማስተዳደር ሳይችል ደሞዝ መቁረጥ “ሳትሠሩ ሥሩ እንደማለት ነው” ሲሉ አቋማቸው አስታውቀዋል፡፡ ገንዘብ የማዋጣት ሐሳቡ ከክልሉ መንግሥት እንደቀረበ፣ ከመንግሥት ሠራተኛው ጋር በተደረገው ውይይት መሠረት መንግሥት ሠራተኛው በፍቃደኝነት ላይ ተመሥርቶ፣ አቅሙ የፈቀደውን ገንዘብ የማዋጣት ሐሳብ አቅርቦ ነው የሚል ሐሳብ ተሰምቷል፡፡ ይሁን እንጂ በአንጻሩ መንግሥት ሠራተኛው ሳይስማማ ነው ደሞዝ የተቆረጠው በማለት በመቃወም ሥራ የማቆም እድማ እንቅስቃሴው ተጀምሯል ተብሏል፡፡ ይህን ተከትሎም ሠራተኞች ለክልሉ ዕምባ ጠባቂ ተቋም ቅሬታ አቅርበዋል፡፡ የሠራተኛ ደሞዝ የሚቆረጥበት ሁኔታን በተመለከተ በሕግ የተደነገገው፣ ሠራተኛው እንዲቆረጥ የፈቀደውን መጠን ካስቀመጠና ይሁንታውን በፊርማ ካረጋገጠ ብቻ ነው፡፡ አዲስ ማለዳ
ሰሞኑን ሰው ሁሉ በ19 ሚሊዮን ብር ስለተገዛው አዲሱ ባስ ሲያወራ ለምን ሄጄበት አልሞክረውም ብዬ ዛሬ ከጀሞ 1 ወደ ሜክሲኮ ሄጄ ነበር። ... ባስ ስቴሽኑ ጋ የደረስኩት ከጠዋቱ 12 ሰአት ሲሆን ከተደረደሩት አዲስ ባሶች ውስጥ አንዱን መርጩ ገባሁ። በር ላይ ሚኒ ስከርት የለበሰች አስተናጋጅ በፈገግታ ተቀብላኝ ጉንጬን ከሳመችኝ በኋላ ስልኳን ሰጥታኝ ወደ ውስጥ አስገብታ ወንበር አስያዘችኝ። ... በጣም ብርድ ስለነበር ከወንበሬ አጠገብ የነበረውን Heat የሚለውን በተን ክሊክ ሳደርገው ወዲያውን ከወንበሬ ዙሪያ ጠርዝ ላይ ነጭ ጋቢ ወጥቶ ሙሉ ሰውነቴን አለበሰው። በዚህ ተገርሜ እንደምንም ከጋቢ ውስጥ እጄን አውጥቼ ፊት ለፊቴ ያለውን ስክሪን ሳበራው መኪናው ላይ ስለተገጠሙት ቴክኖሎጂዎች የሚገልፅ ፅሁፍ መጣልኝ። ... ፅሁፍ ላይ እንዳነበብኩት ከሆነ ክረምት ክረምት መንገዶች በጎርፍ ሲሞሉ ይሄ ባስ ወዲያውን ቅርፁን ወደ ዝርግነት በመቀየር ወደ መርከብነት የሚለወጥ ሲሆን በውስጡም መለስተኛ ኳስ ሜዳ እና የባስኬት ቦል ኮርቶች እንዲሁም ለፈረስ ግልቢያ የሚሆን ሰፊ ሜዳ ይዟል። ... ምናልባት ከቤቱ ተቻኮሎ ፊቱን ሳይታጠብ የመጣ ተሳፋሪ ካለ ባሱ የራሱን የፊት ሳሙና እና የጥርስ ብሩሽ ከኮልጌት ጋር እንዲሁም ከማይመለስ አንድ ፎጣ ጋር የሚያቀርብ ሲሆን ስቲም እና ሳውናም ከሾፌሩ ጀርባ ባለው ክፍል ውስጥ ዝግጁ ሆኖ ተሳፋሪዎቹን ይጠብቃል። ... በተጨማሪም መንገድ በሚዘጋበት ጊዜ ከጎን እና ከጎን ክንፎቹን በመዘርጋት ልክ እንደ ዴር 33 ከራዳር እይታ ውጪ መብረር የሚችል ሲሆን ምናልባት በሰማይ ላይ እያለ የሰማይ ትራፊክ መጨናነቅ ቢያጋጥመው እንኳን ከስሩ እሳት በመፍጠር ራሱን ወደ መንኮራኩነት በመቀየር ወደ ጨረቃ የሚያምዘገዝግ የሮኬት ቴክኖሎጂ ተገጥሞለታል። ... ለባለስልጣኖች ራሱን የቻለ መኝታ ቤት ያለው ሲሆን ለሰፊው ህዝብ ደግሞ ትኬት ሳይቆርጥ የገባን ቆርጦ ከገባው የሚለይ ሴንሰር ተገጥሞለታል። የሚገርመው ትኬት ያልቆረጡትን ሰዎች በስም መለየት የሚችል ሲሆን አንዱ ተሳፋሪ ሳይቆርጥ ገብቶ ወዲያኑ "ደጀኔ እባክህ ወይ ቁረጥ ወይ ውረድ አትሞላፈጥ" በሚል ድምፅ ተሳፋሪውን ሲያስጠነቅቅ በጆሮዬ ሰምቻለሁ። ... በመጨረሻም ሜክሲኮ ባስ ስቴሽን ደርሰን ስንወርድ ለሁላችንም የጫማ ማስጠረጊያ እና ለቀጣይ ታክሲ መሄጃ ስልሳ ስልሳ ብር የተሰጠን ሲሆን ሾፌሩን ጨምሮ ሁሉም የባሱ ሰራተኞች በእግራቸው የተወሰነ መንገድ ሸኝተውናል። በእኔ እይታ ይሄ ባስ 19 ሚሊየን ሲያንስበት እንጂ ከዚህም በላይ ይገባዋል። Thank you አዴክስ ጭሷ! ዳጊ ነኝ ከገፈርሳ ወንዝ ማዶ :))
በልደታ ክፍለ ከተማ ከ55 ሺህ ብር በላይ ሀሰተኛ የብር ኖቶች መያዙን ፖሊስ አስታወቀ *************** በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ከ55 ሺህ ብር በላይ ሀሰተኛ ባለ 200 የብር ኖቶች ከአራት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ። በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ተግባረዕድ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድ ግለሰብ አዲሱን ባለ200 የብር ኖቶች በመቶ ብር ለመቀየር በማፈላለግ እያለ ከኅብረተሰቡ ለፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሠረት ግለሰቡ ከ7400 ሀሰተኛ ባለ 200 የብር ኖቶች ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ገልጿል። በፖሊስ ከተያዘው አንድ ተጠርጣሪ መረጃ በመነሳት በተደረገው የክትትል እና የኦፕሬሽን ሥራ ከተያዘው ተጠርጣሪ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሦስት ተጠርጣሪዎች እና 48 ሺህ 200 ሀሰተኛ ባለ 200 የብር ኖቶች በቁጥጥር ስር ውሎ በምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ ፖሊስ ያስታውቋል። ከአዲሱ የብር ኖት ቅያሬ ጋር ተያይዞ በርካታ አዲስ ሀሰተኛ የብር ኖቶች ተመሳስለው እየተሠሩ ወደ ኅብረተሰሰቡ እየተሰራጩ በመሆኑ የሚመለከተው አካል ትኩረት ሊሰጥበት እንደሚገባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል። #ebc
#Ethiopia : በመቀሌ ከተማ እስከ ዛሬ ተመተው የማያውቁ የተመረጡ ቦታዎች ከቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ እስካሁን ድረስ የኢትዮጵያ አየር ሀይል በመድብድብ ላይ ነው:: መቀሌ ከወትሮው የተለይ ፍፀም ሰው አልባ ከተማ ሆናለች ሱቆች ንግድ ቤቶች ቢሮዎች በሙሉ ዝግ ናቸው:: ትራስፓርት የለም ህዝቡ ወደ አቅራቢያው የሚገኝ ከተማ በእግሩ ከተማዋን ለቆ በመውጣት ላይ ነው::
የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን ዕዝ ሬዲዮ ግንኙነት በማቋረጥ በጦሩ ላይም አሰቃቂ የግድያ ወንጀል፤ የአካል ጉዳትና የጦር መሳሪያ ዝርፊያ እንዲፈፀም አድርገዋል ተብለው የተጠረጠሩ 7 ከፍተኛ መኮንኖች እና ሌሎች ከወታደራዊ መኮንኖች ውጪ ያሉ 5 ግለሰቦች ለ2ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው በቀዳሚ መዝገብ ጉዳያቸው የታየው የመከላከያ ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ሜጀር ጄነራል ገብረመድህን ፍቃዱ፣ የመከላከያ ሰራዊት ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ይርዳው ገብረ መድህን፣ የደቡብ ዕዝ ሰው ኃብት ልማት አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ገብረህይወት ሲስኖስ፣ የሰሜን ዕዝ መረጃ ዘርፍ ኃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል ኢንሶ ኢጳጆ እራሾ፤ ብርጋዴል ጄኔራል ፍስሃ ገብረስላሴ፣ ኮሌኔል ደሳለኝ አበበ እና ኮሌኔል እያሱ ነጋሽ ናቸው። ተጠርጣሪዎቹ መንግስትና ህዝብ የጣለባቸውን ኃላፊነት ወደጎን በመተው መቀመጫውን ትግራይ ክልል ካደረገ የፀረ ሰላም ቡድን ከፍተኛ አመራሮች ተልዕኮ በመቀበል ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም የሀገር መከላከያ የሰሜን ዕዝ ሬዲዮ ግንኙነት በማቋረጥ ሰራዊቱ እርስ በርስ እንዳይገናኝ በማድረግ በጦሩ ላይም አሰቃቂ የግድያ ወንጀል፤ የአካል ጉዳትና የጦር መሳሪያ ዝርፊያ እንዲፈፀም አድርገዋል ተብለው በመጠርጠራቸው ነው መርማሪ ፖሊስ ምርመራ እያደረገ የሚገኘው። በተጨማሪም የፌደራል መርማሪ ፖሊስ እንዳመላከተው በሀገር ውስጥና ከውጭ የሚቃጣበትን ጥቃት እንዳይከላከልና የሰሜን ዕዝ ጦር እንዲፈርስ በማድረግ በተቀናጀ መልኩ ኦነግ ሸኔ ከተባለና ከሌሎች የፀረ ሰላም ሃይሎች ጋር በመተባበር በተለያዩ ክልሎችም ሐይማኖትን ሽፋን አድርገው የብሄር ግጭት በማስነሳትም ሀገርን ለመበተን ሲሰሩ እንደነበር መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ ገልጾ ነበር። መርማሪ ፖሊስ እነዚህ ተጠርጣሪዎች የመከላከያ ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ሜጀር ጄነራል ገብረ መድህን ፍቃዱን ጨምሮ ሃገርን በመክዳት ወንጀልና ህገ መንግስታዊ ስርአቱን ለመናድ በማሰብ ወንጀል የተጠረጠሩ ሰባት የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች ዛሬ ፍርድ ቤት አቅርቧቸዋል። ተጠርጣሪዎቹ በፌዴሬል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው ቀርበው ጉዳያቸው ለሁለተኛ ጊዜ የታየው። የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ ሁለት የምርመራ ባለሙያዎች ከዚህ በፊት በተሰጣቸው የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ የሰሯቸውን የምርመራ ስራዎችን ለችሎቱ ይፋ አድርገዋል። መርማሪ ፖሊስ የስድስት ሰዎች የምስክርነት ቃል ተቀብሎ ከመዝገቡ ጋር ማያያዙን፣ የተጠርጣሪዎችን ቃል መቀበሉን፣ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በተጠርጣሪዎችን ቤት እና ቢሮ ፍተሻ ማደረጉንና በፍተሻውም በርካታ ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት ያላቸው የጦር መሳሪያዎችን ማግኘቱን እና በኢግዚቢትነት መያዙን እንዲሁም የተጠርጣሪዎች የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ለሚመለከተው ተቋም ለምርመራ ተልኳል ነው የተባለው። በተጨማሪም ተጠርጣሪዎች በሃላፊነት በነበሩበት ወቅት ይህን የወንጀል ተግባር ለመፈጸም ከሌሎች ግብረ አበሮቻቸው ጋር በህቡዕ ስብሰባና ምክክር ሲያደርጉ እንደነበር መረጃ ያገኘና የቪዲዮ ማስረጃም እንዲላክ መጠየቁን መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አስታውቋል። መርማሪ ፖሊስ ቀሪ ያላቸውን የቴክኒክ ማስረጃ ለማስመጣትና ቀሪ ስራ ለመስራት ተጨማሪ ጊዜ ያሰፈልገኛል ሲል ችሎቱን ጠይቋል። ተጠርጣሪዎች በበኩላቸው እኛ ለበርካታ ዓመታት ለሃገር ታግለናል፤ ምርመራው በአብዛኛው የተጠናቀቀ መሆኑን ተረድተናል ስለዚህም ተጨማሪ ጊዜ ሊሰጥ አይገባም፤ ዋስትና የፈቀድልን እና ጉዳያችንን በውጭ ሆነን እንከታተል ብለዋል። እንዲሁም የቤተሰብ አስተዳደሪ ነን የባንክ ሂሳባችን ታግዷል ለቤተሰብ ቀለብ መስጠት አልቻልንም ፍርድ ቤቱ ለቀለብ እንድንሰጥ ይፍቀድልን፤ ከቤተሰብ ምግብ እና አልባሳት ከማስገባት ውጪ ለመነጋገር ይፈቀድልን፤ ክሳቸን በቡድን ነው በተናጠል ይታይልን የሚሉ አቤቱታዎቸን አቅርበዋል። የጤና እክል አለብን ያሉ ተጠርጣሪዎችም ነበሩ፡፡ የተጠረጠሩበትን ወንጀል ክብደት ውስብስብነት ከግምት በማስገባት ለመርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ 13 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል። መርማሪ ፖሊስ የተጠርጣሪዎቹን የባንክ ሂሳብ ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት መኖሩን እና አለመኖሩን በማጣራት ግንኙነት ከሌለው ለቤተሰብ ቀለብ እንዲጠቀሙ አዟል። #fbc
የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂ ተማሪዎች ከጥቅምት 1 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጥሪ ይደረግላቸዋል በሚል የተሰራጨው ዜና ስህተት መሆኑ ተገለፀ፡፡ ከሰሞኑ ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮችን የተሳተፉባቸው ውይይቶች ተካሂደዋል፡፡ በዋናነት በጅማ ዩንቨርሲቲ ሲካሄድ የቆየው የሦስት ቀናት ጉባኤ እንዲሁም በጠቅላይ ሚንስትር ፅህፈት ቤት የተካሔዱ ውይይቶችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ባለፈው ሳምንት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የ2013 ዓ.ም ትምህርት በሚጀመርበት ሁኔታ ላይ የመከረው ጉባኤ የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂ ተማሪዎች ከጥቅምት 1 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጥሪ እንደሚደረግላቸው በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መገለፁን ከተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ሰምተናል። ይሁን እንጂ ኢትዮ ኤፍ ኤም ያነጋገራቸው የባህርዳር ፤ የድሬደዋ እና የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንቶች ባለፈው ሳምንት የ45 ዩኒቨርሲቲ አመራሮች በጅማ ሲያካሂዱት በቆየው የሦስት ቀናት ጉባኤ ከጥቅምት 1 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎቻችሁን ተቀበሉ የሚል አቅጣጫ አለመቀመጡን ገልፀዋል፡፡ ኢትዮ ኤፍ ኤምም የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂ ተማሪዎች ከጥቅምት 1 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጥሪ ይደረግላቸዋል የሚለው ዜና ከመሰራጨቱ በፊት በጊዜ ገደቡ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እንዲጠሩ የተቀመጠ አቅጣጫ ሳይኖር መረጃውን ለምን ማሰራጨት አስፈለገ ስንል የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደቻሳ ጉርሙ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለፁት በወቅቱ በነበረው ውይይት ላይ የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂ ተማሪዎች ከጥቅምት 1 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጥሪ እንደሚደረግላቸው ስምምነት ላይ ተደርሷል በሚል የተሰራጨው ዘገባ ስህተት ነው ብለዋል፡፡ በውይይቱ ወቅት በምክረ ሀሳብ ደረጃ የተነሳ እንጂ ውሳኔ ላይ ያልተደረሰበት ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው በሰዓቱ የተገኙ ሚዲያዎች የተሳታፊዎችን ሀሳብ በመውሰድ በስህተት የዘገቡት መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡ ትምህርት ማስጀመርን በተመለከተ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች መመሪያ የተሰጠ መሆኑን ያስታወሱት አቶ ደቻሳ ከዛሬ ጀምሮ ይህንን የሚገመግም ቡድን እናሰማራለን ብለዋል፡፡ ቡድኑ አጠቃላይ የግምገማ ሪፖርቱን እንዳደረሰን እያንዳንዱ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎቹን የሚጠራበትን ጊዜ ወደ ፊት እናሳውቃለን በማለት ነግረውናል፡፡ #Ethiofm
ክብር ለጤና ባለሞያዎች! (በዶ/ር ኤልያስ ገብሩ ኣዕምሮ) #Ethiopia : ከላይ የምትመለከቱት ፎቶ ጣሊያን፣ብራዚል ወይም አሜሪካ አይደለም የተነሳው። እዚሁ ኢትዮጵያ ያሉ ኮሮናን የሚዋጉ የጤና ባለሙያዎች ናቸው እንዲህ ከወለሉ ላይ ተዘርረው የምታዩት። "ጽኑ ህሙማን" ክፍል የሚገቡ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች ቁጥር በጣም እየጨመረ ስለመጣ የሥራው ጫና እጅግ እየበዛባቸው ይገኛል። ወንዝ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው እንዲሉ ኮሮናም ባገራችን ቀስ በቀስ ስር ሰዷል። ቀጣዮቹ ጥቂት ሣምንታት ከፍተኛውን ተጽእኖ የምናይበት ጊዜ ይመስለኛል። ስለዚህ እንደምንም የራሳችንን ፍላጎት ገድበን ጥንቃቄዎችን ማድረግ ያስፈልጋል። ማስክን ባግባቡ ማድረግ ፣ ርቀት መጠበቅ ፣ አውቶብሶች እና ታክሲዎች ውስጥ መስኮቶችን በመክፈት ማናፈስ ፣ ቢያንስ ለቅሶን መሰል ብዙ ሰው የሚሰበሰብባቸውን ኹነቶች መገደብ ፣ እጆችን በሳሙና መታጠብ፣ ንክኪዎችን መቀነስ ሌሎችም የጥንቃቄ መንገዶች በመተግበር ራስንና ወገንን መጠበቅ ያስፈልጋል። በተረፈ ለእነዚህ ጀግና ኢትዮጵያዊ ሐኪሞች እና ነርሶች አክብሮታችሁን ለግሷቸው!