tgindex
Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
3
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
18 626
−52 за 4 дн.
Сутки
−14
−0,08%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 109
20 постов
Вовлечённость
6,0%
к подписчикам
Постов в день
0,4
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
по 3 постам
1/24сутки в ленте
616
1/48двое суток
705
1/72трое суток
760

Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.

Посты

  • ሁሉንም ዝጋ! ለስራ ስትነሳ፣ መራመድ ስትጀምር፣ ሩቅ ማሰብ፣ ትልቅ ማለም ስትጀምር ሊጠልፍህ የሚሰናዳውን፣ ከፊትህ የሚቆመውን፣ የሚያዘናጋህን፣ የሚያሸብርህን እያንዳንዱን ነገር ዝጋው። ፈተናዎችህን ቀንስ፣ ጥረትህን ጨምር፤ መሰናክሎችህን አስወግድ በምትኩ ጥሩ መሻገሪያ ድልድይ አዘጋጅ፤ ግፊቶችህን አርቅ በምትኩ ድንቅ መወጣጫ አሰናዳ። በስሜት ለመጓዝ ማወቅ የሚገባህ የሌሎችን ህልም ሳይሆን የእራስህን ህልም ነው፤ እራስህን ነው፤ ማንነትህን ነው። አንተ ባለህበት ሁሉ የሚረብሽህ ነገር ሁሌም አለ፤ ወደፊትም ይኖራል። ስራዬ ብለህ ጊዜ ከሰጠሀው፣ ከሰማሀው፣ በጥልቀት ካዳመጥከው ይጥልሃል፤ ተሻግረህ ጥለሀው ካለፍክ ግን እርምጃህን ያስተካክላል፤ መንገድህን ያቃናል። አዎ! ጀግናዬ..! ሁሉንም ዝጋ! ሁሉንም አስወግዳቸው። ከማይሆኑ አመለካከቶች ጀምሮ፣ የሚረብሹ እየታዎችን ጨምሮ፣ ተስፋ አስቆራጭ ሁነቶችን አካቶ። ወደፊት መጓዝ ከፈለክ ትኩረትህን መሰብሰብ፤ አንድ ነገር ላይ ብቻ ማዋል ይኖርብሃል። የተበተነ ትኩረት ለተበተነ ጥረት ይዳርጋል፤ ያልተጨበጠ፣ የማይታይ እንዲሁ ድካምና ልፋት ብቻ የሆነ አሰልቺ ጉዞ ይሆናል። አሸንፋለሁ ካልክ በዙሪያህ የሚያሰናክሉህን፣ የሚረብሹህን ነገሮች ማስወገድ ተለማመድ። በSocial Media ሱስ ተጠምደህ፣ ካንተ ከማይሻሉ ሰዎች ሃሳብ እየተቀበልክ፣ ህልምና ራዕይ በሌላቸው ሰዎች ተከበህ፣ ችሎታህን የሚያሳንስ፣ አቅምህን የሚገድል ስራ ጀምረህ ትልቁን የስኬት አለም ሳይሆን በትንሹም እራስህ ላይ ተፅዕኖ መፍጠር አትችልም። አዎ! ሃሳብ ስላለህ ብቻ ሳይሆን በሃሳብህ ዙሪያ የሚያንዣብቡትን አሰናካይ ሃሳቦች ማስወገድ ስትችል ከከፍታው ትደርሳለህ፣ ለስኬቱ ትበቃለህ። በጊዜ እንዳትነሳ ስለሚያደርጉህ፣ ማንበብ እንዳትችል፣ አዳዲስ ሰዎችን እንዳትተዋወቅ፣ ህልምህን እንዳትኖር፣ እቅዶችህን እንዳታሳካ፣ ቤተሰቦችህን እንዳትረዳ፣ ለጓደኞችህ እንዳትደርስ፣ በሃሳብህ ልክ እንዳትጓዝ፣ ለራዕይህ እንዳትፋለም የሚረብሹህ፣ የሚያሰናክሉህ፣ ወደኋላ የሚጎትቱህ ነገሮች ምንድናቸው? የኋላቀርነትህ ምክንያት ችሎታህ ሳይሆን ከባቢህ ሊሆን እንደሚችል አስታውስ፤ ድክመተህ ካንተ ሳይሆን ከጫናዎች ብዛት ሊሆን እንደሚችልም አስተውል። በአለማችን ትልቁ የስኬት ጠላት ትኩረት ማጣት ወይም በብዙ ነገሮች መረበሽ (distraction) ነው። በትልቁ ታስባለህ ነገር ግን ሃሳብህን መኖር አልቻልክም፤ በፈለከው መጠን በንቃት ልታደርገው አልተሰናዳህም፤ ትክክለኛውን ጊዜ እየጠበክ መረበሽህን ቀጥለሃል፤ የተሻለ ነገ እስኪፈጠር በሃሳብህ እየተብሰለሰልክ ነው። እያንዳንዱን የሚረብሹህን መንገዶች ዝጋ፤ ሙሉ ትኩረትህን የአምላክህ ሃይል ላይ፣ እራስህ ላይና ህልምህ ላይ ብቻ አድርግ። በቅርቡ ካንተም በላይ ከባቢህ ተቀይሮ ትመለከተዋለህ።

  • ሁሉም ይቀናብሃል! አንድን ሰው የተራራው ጫፍ ላይ ብንመለከተው ሁሉም ሰው የሚቀናው የተራራው ጫፍ ላይ በመውጣቱ እንጂ በአወጣጡ አይደለም። እንዴት እዛ ይድረስ? ምንያህል ቀን ይፍጅበት? ስንቴ ወደቀ? ስንቴ ተነሳ? የማንም ጉዳይ አይደለም። ሰው የሚቀናው አስቀድማችሁ ባለፋችሁት ስቃይ ሳይሆን በስተመጨረሻ በምትጎናፀፉት ድል ነው። ብዙ ሰው ደስታችሁን ይመኛል ነገር ግን ከዛ በፊት ምንያህል ጨለማ ጊዜ እንዳሳለፋችሁ ማወቅም አይፈልግም፤ ብዙ ሰው ስኬታችሁን ይናፍቃል ነገር ግን ስኬታማ ለመሆን ያደረጋችሁት ከባድ ነገር ለማድረግ ፍቃደኛ አይደለም። ህይወት በምኞት ብቻ የምትሳካ አይደለችም። ሁሉም በየደረጃው ስራ ይፈልጋል። ህልምን ሲተኙ ብቻ መመልከትና ቆሞ የስኬታማ ሰዎችን ህይወት መመኘት አንድ ናቸው። ሁለቱም በምናብ ወደምንፈልገው ስፍራ ይወስዱን ይሆናል እንጂ በፍፁም በተጨባጭ እዛ አያደርሱንም። ዓለም የህልመኛ እጥረት የለባትም፣ ምድር የባለራዕይ ችግር የለባትም። ዋናው ችግሯ ህልሙን ለማሳካት መሱዓትነት የሚከፍል ሰው ነው። አዎ! ጀግናዬ..! ሁሉም ይቀናብሃል! ትንሹም ትልቁም፣ አዋቂውም አላዋቂውም፣ ሰነፉም ብርቱውም አንተ የደረስክበትን ከፍታ ይመኘዋል። ነገር ግን ምኞት ብቻውን ግን ያንተ ስፍራ እንደማያደርሳቸው አልተረዱም። ብዙ ምርጫ ነበረህ ነገር ግን ስኬትን ብቻ መርጠሃል፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ጀምሮ ማቆም፣ ሌላ ነገር መሞከር ትችል ነበር ነገር ግን አላደረከውም። ህልምህን ከደምህ ጋር አስተሳስረሀዋል፣ ውስጥህን በማይበገር ፅኑ ማንነት አንፀሀዋል፣ መንፈስህን እስከ ጥግ አጠንክረሀዋል። ይህን ሁሉ ማደረግ የሚችል ያንተ ቦታ አይደለም አንተ ካለህበት ቦታ የሚበልጥ ቦታ መድረስ ይችላል። የትኛውም የሚያስቀና ህይወት የሚያስቀናው መጨረሻው እንጂ መጀመሪያው አይደለም። ተቀምጦ መመኘት ተነስቶ እንደመስራት ከባድ አይደለምና ብዙዎች ይመኛሉ ጥቂቶች ብዙዎች የሚመኙትን ህይወት ይኖራሉ። አንድ ጠጠር እንኳን ሳይጥሉ የተሳካ ህይወት ለመኖር መሞከር ከንቱ የሀሳብ ድካም ነው። አዎ! አሸናፊዎች ሁሌም ያሸንፋሉ፤ ተሸናፊዎች ሁሌም ይሸነፋሉ። ከዚህ የተለየ ህግ የለም። ማሸነፍ እንደምትችል ከልብህ አምነሃል፣ ለአሸናፊነት የሚያበቃህን ስራ ሰርተሃል፣ መክፈል ያለብህን ዋጋ ከፍለሃል፣ የሚገባህን አሸናፊነት በእጅህ አስገብተሃል። ተሸናፊውም ሽንፈትን መርጧል፣ በቀላሉ ተስፋ ለመቅረት ወስኗል፣ ጀምሮ ማቆምን እጣፋንታው አድርጎታል። ከአዕምሮው ስሜቱ በልጦበታል፣ ከዘላቂው ስኬት ጊዜያው ደስታ ሚዛን ደፍቶበታል፣ ከአላማው ወቅታዊው አጀንዳ ስሜት ሰጥቶታል፣ በእቅድ ሳይሆን በስሜት ይጓዛል፣ ብዙ ይመለከታል ብዙ ያውቃል ነገር ግን ሚዛናዊ ውሳኔ መወሰን አይችልም። ይሔ ሰው አሸናፊነት ከባህር ማዶ እንዳለች ደሴት ርቆታል፣ ምኞት እንጂ እውነታው ሊሆንለት አይችልም። ህይወት ምርጫ ነች ሲባል ቀላል ምርጫ እንዳልሆነች መረዳት ያስፈልጋል። ሰው አዝኖልህ እንዲረዳህ ከፈለክ ምርጫው ያንተ ነው፤ በስራህ ተደስቶም እንዲሸልምህ ከፈለክ ምርጫው ያንተ ነው። "ምንም የለኝም፣ ምን ላድርግ? ሰው የለኝም፣ እንዴት ብቻዬን ልስራ?" ካልክ አሁንም ምርጫህ ነው። "ባለኝ ጀምሬ ላሳይ፣ ብቻዬን የምችለውን አድርጌ ውጤቱን ልመልከት" ካልክም ምርጫው ያንተ ነው። አሸናፊነትን እስከመረጥክ ድረስ ስሜትህን ጥለህ በማይናወጠው አቋምህ እንደምትመራ አስታውስ።

  • ልባችሁን ተከተሉ! የሁለት ሃሳብ ግጪት መሃል ብትሆኑ፣ ግራመጋባት ፋታ ቢነሳችሁ፣ ምርጫ ቢበዛባችሁ፣ ከዚህም ከዛም ጫናዎች ቢያይሉባችሁ፣ ወደህም ወዲያም ለመሔድ ብትቸገሩ፣ በጭንቀትና ስጋት ካላችሁበት ስፍራ መንቀሳቀስ ቢሳናችሁ ምንም ከማድረጋችሁ በፊት ቆም ብላችሁ ውስጣችሁን አዳምጡ፣ ልባችሁ የሚመራችሁን አቅጣጫ ተመልከቱ፣ ከስሜታችሁ በላይ ሚዛናዊው አዕምሯችሁ ወዳዘነበለበት አዘንብሉ። በህይወት መንገድ ግራ መጋባት፣ አጣብቂኝ መሃል መውደቅ፣ ከቀረቡት አማራጮች የተሻለውን ለመምረጥ መቸገር ያለና ወደፊትም የሚኖር ነው። ነገር ግን በዚህ ሁኔታ ውስጥ ልባችንን ማዳመጥ የተሻለውን አማራጭ ያቀርብልናል። ሃሳብ ሁሌም አለ፣ ስሜት ዘወትር ይቀያየራል፣ ማንም ይጨነቃል፣ ያወጣል ያወርዳል መጨረሻው ግን ከሁለት አንዱ ነው። ወይም አንዱን  ይወስናል ወይም ከሁሉም አማራጮች ሳይሆን ይቀራል።  አዎ! ጀግናዬ..! በስሜትህ እየተገዛህና የውስጥ ፍላጎታህን እያዳፈንክ የምትጓዝ ከሆነ፣ ለውጫዊ ጫናዎች እራስህን አሳልፈህ ከሰጠህ፣ ለጊዜያዊ ጥቅም ቅድሚያ ከሰጠህ የአጣብቂኝ ብዛት፣ የሃሳብ ዥረት፣ የጭንቀት መዓትና የግራመጋባት አባዜ ሊለቅህ አይችልም። በስሜታዊነት ከምትፈታው ችግር በላይ የምትፈጥረው ችግር ይበዛል፣ የልብ መሻትህን ወደጎን እያልክ በውጫዊ ተፅዕኖ ብትመራ ትክክል ከምትሆነው በላይ የምትሳሳተው መንገድ ይበዛል። እራስን ማወቅ ከጫናዎች ነፃ ያወጣሃል፣ እራስህን ባወከው ልክም በተግባር ሚዛናዊና የልብ መሻትን ያማከለ ውሳኔ መወሰን ለተሻለው ምርጫ ያበቃሃል። በህይወትህ ውስጥ ያለውን ምርጫ የተባለውን ትልቁን የእግዚአብሔርን ስጦታ በጥንቃቄ ተጠቀም። አዎ! ልባችሁን ተከተሉ፣ ውስጣችሁን አዳምጡ፣ ከስሜታችሁ በላይ ሚዛናዊው የአዕምሮ ሃሳባችሁ ላይ አተኩሩ፣ ለጭንቀትና ለፍረሃት ከሚዳርጓችሁ አማራጮች በላይ ምንም እንኳን የተለየ ዋጋ ቢያስከፍሏችሁም ውስጣዊ ሰላማችሁን የሚያረጋግጡና የሚያረጋጓችሁን አማራጮች ምረጡ። ከምንም በላይ የውስጥ ፍላጎታችሁን አስቀድሙ፣ ከማንም ተፅዕኖ በላይ እራሳችሁን አዳምጡ። ማንም ቢወስንላችሁ ሃላፊነቱን አይወስድላችሁም፣ ማንም ቢመርጥላችሁ ምርጫውን አስታኮ ለሚመጣው አደጋ እራሱን አሳልፎ አይሰጥላችሁም። አጣብቂኝ ውስጥ ብትገቡ፣ ግራ ቢገባችሁ፣ ለውሳኔ ብትቸገሩ ተረጋጉ፣ ከማንም በላይ እራሳችሁን ለማወቅ ሞክሩ፣  ውስጣችሁን አዳምጡ፣ ፍላጎታችሁን በጥልቀት መርምሩ፣ ለልብ መሻታችሁ ቅድሚያ ስጡ፣ በጥበብ በማስተዋል ህይወታችሁን ምሩ፣ ሰላማዊና አስደሳች ህይወትንም ኑሩ።

  • 10 авг.1 5642110

    ብትውልም መልካም ውለታ ስለሰው ብትንገላታ ከኬለህ ማን አለ ደጅህ ኪስህ ነው የቅርብ ወዳጅህ ✅ የችግር ያሳብ ሰቀቀን ቢገጥምህ ባልታሰበ ቀን ቢጎድል ጓዳ ማጀትህ እርሾ ቢጠፋ ከቤትህ ተወጣው አትሂድ ከሰው ሆድህን እንዳታስበሰው ✅ ሆድህን ቢርብ ቢጠማህ ልብህን ጭንቀት ቢሰማህ ሀላፊ ነው እንደዋዛ ለሰው ምፅዋት አትገዛ ✅ ከኬለ ማን አለ ደጀህ ኪስህ ነው የቅርብ ወዳጅህ ✅ ከጎጆህ ጥሪት ቢታጣ ችግር ሰንደቁን ቢያወጣ በሀሳብ ገላህ ቢከሳ አንተነትህነ አትረሳ ቢለይም ሚዛን ክበድቱ ሰው ነው ሰው በሰውነቱ

  • 9 авг.1 767333

    ክፉ አልናገርም ስለፋ ስደክም እኔ ለኑሮዬ፣ ሰዎች ቢቆፍሩ ጉድጓድ ከኋላዬ። ባልሰራሁት ስራ ስለኔ ቢያወሩ፣ ኑሮዬን ለማምረር እንክርዳድ ቢዘሩ። ውድቀቴንም ቢሹ ሞቴንም ቢመኙ፣ እኔ ስንከራተት እነሱ ቢተኙ። ቢወድቁ ቢነሱ ያሻቸውን ቢሉኝ፣ ባአልቧልታ ወሬ ስጋዬን ቢበሉኝ። ዝምታ ነው መልሴ ክፉ አልናገርም፣ የኔን ህይወት እንጅ የነሱን አልኖርም።

  • 8 авг.1 69332

    በ 130,000 ብር ብቻ ቤቶን ሙሉ ያድርጉት!! 📍 አድራሻችን፦ 📍 ዊንጌት ብርጭቆ 40/60 ኮንዶሚኒየም 📞 ለማግኘት፦ 0936358805, 0942342619

  • 8 авг.1 741116

    በድካምህ አትዘናጋ! ሰውነት ደካማ ነው። የሆነ ጊዜ ሃይሉን ያጣል፣ የቀደመ ተነሳሽነቱ ይመክናል፣ እንደ በፊቱ መነቃቃትና ጠንክሮ መስራት ይሳነዋል። ይሔ ተፈጥሮ ነውና ምንም ብታደርግ ልትቀይረው አትችልም። ነገር ግን መቀየር የምትችለው አንድ ነገር ይኖራል እርሱም በሁነቱ መዘናጋት ማቆም ነው። ለድካምህ እጅ አትስጥ፣ በድብርት አትሸበር፣ በዝለት ውስጥህን አታውክ። ምርጫው የአንተ ነው። ማንም የማይደክም የለም ድካሙን ውጦ፣ ዝለቱን ችሎ፣ ድብርቱን ጥሎ የሚያልፍ ግን በጣም ጥቂት ነው። ወደኋላ መመለስ፣ ራስን ማደስ፣ ስሜትን ማስተካከል የብስለት እንጂ የሞኝነት ምልክት አይደለም። በደከመህ ሰዓት ራስህን ጫና ውስጥ አትክተት ፋታ ውሰድ፣ ራስህን ዳግም አንፅ እንደገናም ወደ ጀመርከው መንገድ ተመለስ። ሁሌም የሚከተሉህ ነገሮች አሉ። እነርሱም የሚረብሹህ ነገሮች ናቸው። አያስፈልጉህም ነገር ግን እንደሚያስፈልጉህ ሌት ከቀን ይከተሉሃል፤ አይጠቅሙህም ነገር ግን ሁሌም እንደሚጠቅሙህ እንድታምን ያደርጉሃል። በሂደት ስሜትህን ያውኩታል፣ ተነሳሽነትህን ይገድሉታል፣ የሃሳብ ውቂያኖስ ውስጥ ይከቱሃል፣ ድካምና ዝለት እንዲቆጣጠሩህ ያደርጉሃል። አዎ! ጀግናዬ..! በድካምህ አትዘናጋ፣ ለዝለትህ አትበገር። ሲመጣ ዘላለም የሚደክምህ ይመስልሃል፣ ስትገናኙ እንደሚቆጣጠርህ ሊያሳይህ ይጥራል። በእርግጥ ግን ያላንተ ፍቃድ እርሱ ምንም አቅም የለውም። የሆነ ጊዜ ሊሰብርህ ይችላል ነገር ግን ሁሌም ሊሰብርህ አይችልም፤ የሆነ ጊዜ ስሜትህን ሊያውከው ይችላል ነገር ግን ሁሌም ሊያውከው አይችልም። ለቀጣዩ ከፍታህ አሁን ዝቅ ማለትህን አትፍራ። ነገሮች በትናንቱ መንገድ አይቀጥሉም። ማግኘት ማጣት፣ መውደቅ መነሳት፣ ማትረፍ መክሰር ያለና የሚኖር ነገር ነው። ተሰብሮ መቅረትን በፍጹም ምርጫህ አታድርግ፣ ለውጣውረዱ መሸነፍን መቼም ምርጫህ አታድርግ። ብርቱ ጦረኞች ተዋግተው እስኪያሸንፉ አያቆሙም፤ ጠንካራ ሰራተኞች የሚፈልጉትን እስኪያገኙ ወደኋላ አይመለሱም። ያንተ ጦርነት ከህይወት ፈተና ጋር ነው፤ ያንተ ግብግብ ከስሜት ውጣውረድህ ጋር ነው። ሳታሸንፍ የሚያቆም ጥረት አይኖርም፤ አላማህን ሳታሳካ የሚታጠፍ እጅ የለም። ፍረሃት ሊያስርህ ቢፈልግ አሻፈረኝ ትለዋለህ፣ ጭንቀት አቅም ሊያሳጣህ ቢሞክር አቅምህን ታሳየዋለህ። አዎ! ከጫናዎች ብዛት ትወድቅ ይሆናል ነገር ግን ዳግም ትነሳለህ፣ በድካምህ ምክንያት ስሜትህ ይረበሽ ይሆናል ነገር ግን እነደገና ወደ ትክክለኛው መንገድ ታገኘዋለህ። ያንተን ምርጫ ብዙዎች አይመርጡትም ምክንያቱም ምርጫህ እጅግ ከባድ ነውና፤ ባንተ መንገድ ብዙዎች አይጓዙበትም ምክንያቱም ምቾት የለውምና። ዝቅ መደረግ ብርቅህ አይደለም፤ በሰዎች እይታ ትንሽ መምሰል አዲስህ አይደለም። የግል ህይወትህ ተቆጣጣሪ አንተ ነህ። ዓለም ቢያብርብህ፣ ሰው ሁሉ በተቃራኒህ ቢቆም ከእውነተኛው ማንነትህ ጋር ከተሰለፍክ ማንም ሊያንቀሳቅስህ አይችልም። አቅም አለህና አቅምህን አውጥተህ ተጠቀም፤ ችሎታው አለህና ለውጤት አብቃው። አውቀቱ አለህ እርሱንም ከጊዜያዊ ሙቀት በላይ ለዘላቂው ውጤት ተጠቀመው። ብዙ ሰው የማያየውን በውስጥህ መመልከት ትችላለህ፣ ብዙዎች የተሰናከሉበት ጊዜያዊ ድካምና ድብርት አያቆምህም። አንተ ስትበረታ ፈተናው ጉልበት ያጣል፣ አንተ ስራህን ስትመርጥ የናቁህ ያፍራሉ። ስራህን ወጥረህ ስራ፣ ለምርጫህ እንደምትገባ አስመስክር፣ እንቅፋቶችህን ሁሉ ጥለህ ማለፍ እንደምትችል አሳይ።

  • 8 авг.1 12861

    በግድ ውደቁ! የዓለም አስተምህሮ እንጂ እውነታው የውድቀትን አስከፊነት አያሳይም። ውድቀት ዘርፈ ብዙ ነው። ለአንዳንዱ በሰዎች ተቀባይነት አለማግኘት ውድቀት ነው፤ ለጥቂቶች የሚፈልገውን ህይወት አለመኖር፣ ለሌላው በገንዘብ በንብረት የተሻለ ሰው አለመሆን ውድቀት ነው። ነገር ግን ብዙዎቹ ውድቀት ባሉት ነገር ከማዘን በቀር የውድቀታቸውን አስፈላጊነት ማሰብ አይፈልጉም። በህይወት አላችሁ ስለዚህ ደጋግማችሁ ትወድቃላችሁ፤ ከሰው ጋር እየኖራችሁ ነው ስለዚህ የሰውን አስከፊ ገፅ ደጋግማችሁ ትመለከታላችሁ፤ አላማችሁን ለማሳካት ወስናችኋል ስለዚህ በየጊዜው መውደቃችሁ አይቀርም። ባትፈልጉም የተሻለ ነገር ይገባችኋልና መፈተናችሁ የግድ ነው፤ ባትዘጋጁበትም ጥሩ ሰው ይገባችኋልና በሆነ ሰው መጎዳታችሁ የግድ ነው። እንደማይሳካላችሁ ተነግሯችኋል እውነት ነው የሆነ ጊዜ አይሳካላችሁ ይሆናል ህይወታችሁ ግን ሙሉ በሙሉ ያለ ስኬት አይጠናቀቅም። ማንም ሰው እጣፈንታው ተወስኖ ወደ ምድር አልመጣም። ቢያሻው ያሳምረዋል፣ ካላሻውም እንዲሁ እያበላሸው ይኖራል። አዎ! አስባችሁ ፈልጋችሁ በግድ ውደቁ፤ በግድ ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ። ውድቀታችሁ ግን ለላቀው ከፍታችሁ መዘጋጂያ ይሁናችሁ፣ ዝቅታችሁ ግን ትልቁን የህይወት ትምህርት መማሪያ ይሁናችሁ። ዛሬ ላይሳካ ይችላል፣ ነገ ላይሳካ ይችላል፣ እንዲሁ ከነገወዲያም ላይሳካ ይችላል ነገር ግን ተስፋ ከቆረጣችሁ አንድ ማረጋገጫ አላችሁ እርሱም መቼም እንደማይሳካ ነው፤ በዛሬ ውድቀታችሁ ካቆማችሁ መቼም ያሰባችሁበት ቦታ አትደርሱም። ለብዙዎች ውድቀት የህይወታቸው ፍፃሜ ይመስላቸዋል። ፍፃሜው ግን ውድቀት ሳይሆን ተስፋ ማጣት፣ የነገን ብረሃን መመልከት አለመቻል ነው። "የት ይደርሳል የተባለ ዛፍ ቀበሌ ቆረጠው" ተብሎ የተተረተው ለእናንተ እንዳልሆነ በተግባር አሳዩ። የት ትደርሳላችሁ ተብሎ ሲጠበቅ በሰው ትቺት ምክንያት ወድቃችሁ አትቅሩ፤ ለስንተ ነገር ስትጠበቁ በትንሽ የአሰራር ህፀፅ ምክንያት ከጥረታችሁ አትገቱ። ለውጥና እድገታችሁን የማይፈልግ በጣም ብዙ አካል አለ፣ ያ ግን የእናንተ ሳይሆን የዛ አካል ፍላጎት ነው። የእናንተ ፍላጎት ያላመነባችሁን ማሳፈር ነው፤ የእናንተ ምርጫ ከናቃችሁ በላይ ደምቆ መታየት ነው፤ የእናንተ ውሳኔ በየቀኑ ጥራታችሁን መጨመር ነው። አዎ! ጀግናዬ..! አንድ ቀን ሳይሆን በዛሬው ቀን አንድ ቀና ብለህ መራመድ ትጀምራለህ፣ በዛሬው ቀን ውድቀትህን ሽረህ ትመለሳለህ፣ በዛሬው ቀን ተስፋህን አድሰህ በልበሙሉነት ትቆማለህ። የራስ መሰናክል መሆን ዛሬ ያበቃል፣ ራስን ማጣጣል ዛሬ ያበቃል፣ ከራስ ጋር ባላንጣ መሆን ዛሬ ይቋጫል። ከፈጣሪና ካንተ በላይ ያንተ ህይወት ግድ የሚሰጠው አካል እንደሌለ አስተውል። ወድቀህ ብትቀር የብዙዎች መቀለጃ ትሆናለህ፤ ተስፋህን በሰዎች ላይ ብትጥል ባዶህን ትቀራለህ፣ ፍረሃትህን አምነህ ብትቀበል ለህይወትህ የጨለማ ክፍል ትጋለጣለህ። ስኬታማዎች ደፋሮች ናቸው፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የውድቀት አለቆች ናቸው። ለመውደቅ ደፋር ሁን፤ ለራስህ ለመታገል ልብህን አደንድን። ፅኑ ታጋዮች ያሸንፋሉ፣ ከልብ የሚፋለሙም ድልን ይቀዳጃሉ። ከልብህ ከህይወት ጋር ተፋለም፣ ያጠቁህን በስልት አጥቃ፣ ያሸበሩህን በብልጠትም ይሁን በንቀት ጥለሃቸው እለፍ። በፀሎትህ በርታ፣ ከመቼውም በላይ መንፈሰ ጠንካራ ሁን። ለሚገባህ የተሻለ ህይወት ራስህን ግዛ፣ ግዛትህንም አስጠብቅ።

  • ጠላትህን ሻረው! ፨፨፨////////፨፨፨ ትልቁ ጠላትህ ራስህ ነህ። ውዱን ጊዜህን ዛሬ በአግባቡ ከመኖር ይልቅ ስለነገ አብዝትህ በመጨነቅ እያባከንከው ነው፤ ነገ ቶሎ ውጤት እንዲያመጣልህ የምትሰራው ምንም ነገር የለም፣ አሁን የምትኖረው በግማሽ ነው። አዕምሮህ በብዙ ሀሳቦች ተውጧል፣ ውስጥህ ለመረጋጋት ተቸግሯል፣ ለችግሮችህ መፍትሔ መፈለግ ተስኖሃል። ምክንያቱም ዛሬን መኖር አልቻልክም፣ ባለህ ነገር ማመስገን አልቻልክም፣ በረከቶችህን መቁጠር አልቻልክም፣ አይንህ ሁሌም ጉድፍ ይመለከታል፣ ጆሮህ ሁሌም መዓቱን ይሰማል፣ ውሎህ በሚመርዝህ ስፍራ ነው፣ ለሆነብህ ክፉ ነገር ሌላውን ትወቅሳለህ፣ ላጋጠመህ መልካም ነገር ደግሞ ዋጋውን ለራስህ ትሰጣለህ። ሁሉን እያወቅክ ከራስህ ጋር አታካራ ውስጥ አትግባ። ዛሬም ቢሆን እውነታውን አምነህ እስካልተቀበልክ አንዳች የሚቀየር ነገር የለም፣ ሊኖርም አይችልም። ማንም ከሚያውቅህ በላይ ራስህን ታውቃለህ፣ ትኩረትህ ምን ላይ እንደሆነ፣ ተስፋህ ምን እንደሆነ፣ የዛሬው ሁኔታህ የት እንደሚያደርስህ ካንተ በላይ የሚያውቅ የለም። አዎ! ጀግናዬ..! ጠላትህን ሻረው፣ ዛሬን በአግባቡ እንዳትኖር፣ ምናባዊው ዓለም ላይ እንድትንሳፈፍ፣ ያለህን ጥሩ ነገር እንዳታጣጥም የሚያግድህን ውስጣዊ ጠላትህን ሻረው፣ ትኩረት አትስጠው፣ እንዲቆጣጠርህም አትፍቀድለት። አውቀህም ይሁን ሳታውቅ ራስህን በውሱንነት መቅጣትህን አቁም። ልበ ብሩህ ከሆንክ የሚታይህ ብረሃን ነው፣ ውስጥህ የተረጋጋ ከሆነ ማንም ትኩረትህን አይበትነውም። እርግጥ ነው ፈጣሪ ነገን መልካም ያደርገዋል፣ አንተ ግን ለመልካሙ ነገህ ዛሬ ምን እያደረክ ነው? እውነት ነው ወደፊት የሚታይህ ብሩህ ቀን ይመጣል፣ አንተ ግን ዛሬህን ምንያህል ብሩህ ለማድረግ እየጣርክ ነው? የትኛውም በጎ ነገር ስራ ይፈልጋል። ከሀሳብ መዓበል ራሳቸውን የታደጉ፣ ትናንቱን እንደ ትናንት፣ ነገንም እንደ ነገ አምነው ተቀብለው ዛሬ የሚችሉትን ብቻ የሚያደርጉ ሰዎች ምነኛ ጥበበኞች ናቸው? ህይወትስ ምንያህል ገብታቸው ይሆን? ህይወትን በሚገባ ካልተረዳህ እድሜ ቁጥር ብቻ እንደሆነ አስታውስ። አዎ! የሚያውቁትን የሚኖሩ እነርሱ ከፍታቸው ከማንም ይልቃል፣ የያዙትን ይዘው ለወደፊታቸው ጠንክረው የሚሰሩ እነርሱ ብልሆች ናቸው፣ ከውሳኔ በፊት ነገሮችን በጥልቀት የሚመረምሩ፣ ከሀሳባቸው በላይ ለድርጊታቸው ቦታ የሚሰጡት እነርሱ ብልጦች ናቸው። የሚጥልህም የሚያነሳህም ምርጫና ውሳኔህ ነው። ዛሬ ላይ ሆነህ የነገን አስከፊነትና ከብደት ማሰብ ትችላለህ፣ ነገር ግን ዛሬም ይሔን ሀሳብህን የሚቀይረውን ተግባር መፈፀም ካልቻልክ ሀሳብህ ማብቂያ አይኖረውም፣ ደጋግመህ ያሰብከው መጥፎ ሁነትም በፍጥነት ወደ አንተ ሲመጣ ትመለከታለህ። ትናንትና ነገን ተዋቸው፣ ልክ እንደ ብልጦቹ የያዝከውን ይዘህ አልቅስ። ዛሬ ቀላል የመሰሉህ ነገ ላይ ሊከብዱህ እንደሚችሉ አስቀድመህ አስብ። በዙሪያህ ያሉ ነገሮች ይቀየሩ ዘንድ ራስህን ቀይር፣ አንተ ትቀየር ዘንድም እይታዎችህን፣ አመለካከትህንና የየለት ተግባርህን ቀይር። አንተ ፈልገህ ካላመጣሀው ሀብትም ሆነ ደስታ ኬትም አይመጣም። ሀሳብህን ግታ፣ ስራህ ነፃ እንዲያወጣህ ፍቀድ።

  • 8 авг.1 1015

    ይቅርታህ አኖረኝ! ከራስ ጋር ንግግር፦ "ደካማ ነኝና ብዙ ስቼያለሁ፣ ልፍስፍስ ነኝና በብዙዎች ላይ ፈርጄያለሁ፣ ወንድሜን ገፍቼያለሁ፣ ባየሁት ቁጥር ፊቴን ቋጥሬበታለሁ፣ ከእራሴ በደል በላይ የእርሱን ደጋግሜ እመለከታለሁ፣ በየቀኑ ወቀሳዬን እሰነዝርበታለሁ፣ በየሰዓቱ በሃሜት ቁም ስቅሉን አወጣዋለሁ። አንደበቴ እንደሚወደው ይነግረዋል የውስጤ ጥላቻ ግን ከአቅሜ በላይ ሆኖብኛል። በወንድሜ ጨክኜ፣ ውድቀቱን ተመኝቼ ምን እንደማገኝ አላውቅም ነገር ግን በዚሁ ጥላቻ ስመላለስ ከርሜያለሁ። ይህን ግብሬን አንተ እንደማትወደው ባውቅም፣ የነፍሴም ፍቃድ እንዳልሆነ ባውቅም የምሰማው መጥፎ ትርክት፣ የሚነገረኝ የጥላቻ ንግግር ማስተዋል አሳጣኝ፣ በጥራት እንዳላስብ አደረገኝ፣ የዋህነቴን ሰወረው፣ ሀዘኔታዬን አጠፋው። አንዳች ያየውት ሳይኖር፣ ምኑንም ሳልረዳ እንዲሁ ከአጥፊው መንጋ ጋር ለጥፋት እቸኩላለሁ፣ ትንሽ የሳተው ላይ ለመፍረድ እፋጠናለሁ፣ የወደቀውን ከማንሳት በላይ እዛው በወደቀበት እረግጠዋለሁ። ጭካኔዬ ይታወቀኛል ነገር ግን ምክንያቱ ጥላቻ የሚባል በሽታ፣ ዘረኝነት የተባለ ቆሻሻ ትርክት ብቻ ስለመሆኑ እርግጠኛ አይደለሁም። አዎ! አንተ አምላኬ ነህ፣ አንተ ፈጣሪዬ ነህ፣ እያንዳንዱን ስራዬን ታውቃለህ። ፃድቅ መስዬ በሀጥዑ ፈረድኩ፣ ፍፁም መስዬ ያጠፋውን ኮነንኩ፣ የተሻልኩ መስዬ ትሁቱን አዋረድኩ። ፈራጅነቴ ከበደሌ ነፃ ያወጣኝ ይመስል ያየውት ላይ በሙሉ ጣቴን እቀስራለሁ፣ እንከኑን እለቅማለሁ፣ መጥፎን እየመረጥኩ እመለከታለሁ። ይሔ ልማዴ ኬት እንደመጣ አላውቅም ነገር ግን እለት እለት ሳደርገው እገኛለሁ። አንተ አባቴ ቅዱስ እግዚአብሔር የይቅርታ አምላክ ባትሆን፣ የቸርነት ጌታ ባትሆን፣ ለበደሌ ተገቢውን ቅጣት የምቀጣኝ ቢሆን ምን ልሆን እንደምችል ሳስብ እጅጉን ደነግጣለሁ፣ ፍረሃት ይወረኛል፣ ለአፍታም ቢሆን ወደ ቀልቤ እመለሳለሁ። ነገር ግን ይቅርታህ አኖረኝ፣ ርህራሔህ በደሌን ተወልኝ፣ ቸርነትህ በምህረት ጎበኘኝ፣ ትዕግስትህ አንተን እንድፈልግ፣ መንገድህን እንድከተል፣ ወዳንተ እንድቀርብ አደረገኝ። የጥላቻን እሾህ ከውስጤ ንቀልልኝ፣ በወንድሜ ጥፋት እንዳልሳለቅ ጠብቀኝ፣ ከፈራጅነት አንተ ሰውረኝ፣ በቀናው መንገድ አንተ ምራኝ።" አዎ! ጀግናዬ..! ፍርድ የእግዚአብሔር ነው፣ ተግሳፅም ይሁን ቅጣት ከፈጣሪ ነው። ወንድምህ ቢያጠፋ ፍርዱን የሚሰጠው እርሱ እንጂ አንተ አይደለህም፣ እህትህ መንገድ ብትስጥ እያስተማረ የሚገስፃት እርሱ እንጂ አንተ አይደለህም። ከፍርድ ተጠንቀቅ፣ ጥፋትን ለማጯጯህ አትቸኩል። መፅሐፍ ቅዱስ እንደሚለው "በወንድምኽም ዐይን ያለውን ጕድፍ ስለ ምን ታያለኽ፥ በዐይንኽ ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም?" ቀዳሚው የእራስን ክፍተት መሙላት፣ የእራስን ድክመት ማረም እንጂ በሰው ክፍተት ላይ አስተያየት መስጠት፣ ድክመቱንም ማጋነን አይደለም። ማንም ከጥፋትና ከሀጢአት የፀዳ ሰው የለም። የሰውን ጉድፍ ባየን ልክ የእኛውን ምሰሶ የሚያህል በደል መመልከት ይኖርብናል። ፈራጅና አስተያየት መስጠት እንደ አዋቂና እንደ ንፁ በሚያስቆጥርበት በዚህ ግዜ እራስን ከፍርድና ከአስተያየት ሰጪነት መጠበቅ ታላቅነት ነው። የተሸፈነልንን ነውር እናስብ፣ የተከደነልንን በደል እናስብ፣ በአምላካችን ቸርነት እንጂ ማናችንም በስራችን ለዛሬ እንዳልበቃን እንረዳ።

  • አይናችሁን ግለጡ! አንድ ተደጋግሞ የሚነገር ምሳሌ አለ። ምሳሌውም ይሔንን ይላል፦ "ትናንት በመንገዳችሁ ስንት ቀይ መኪና እንደተመለከታችሁ አስታውሱ። ብትመለከቱ እንኳን በእርግጠኝነት ቁጥሩን መናገር አትችሉም። ነገር ግን አስቀድሞ ባያቿቸው መኪና ቁጥር ልክ ሁለት መቶ ብር ይሰጣችኋል ብትባሉስ? በእርግጠኝነት ያያቹትን የመኪና ብዛት ከነቦታው መናገር ትችላላችሁ። በህይወት የሚመጡልን እድሎችም እንደዚህ ናቸው። አይናችሁን ገልጣችሁ በህይወት መንገዳችሁ የሚመጡላችሁን እድልና አጋጣሚዎች መመልከት ካልቻላችሁ ሳታስተውሉ እንዳለፉት ቀይ መኪኖች እያለፉ ይሔዳሉ።" እድሎችን ለመጠቀም ዝግጁ ለሆነና ማስተዋል ለሚችል ሰው ህይወቱ በሙሉ በጥሩ አጋጣሚዎች የተሞላች ነች። አንድ ነገር ሲበላሽባችሁ፣ የፍቅር ወይም የትዳር ህይወታችሁ ክፍተት ሲበዛበት፣ አግኝታችሁ ስታጡ፣ ሳታስቡት ውስብስብ የህይወት መንገድ ውስጥ ስትገቡ አይናችሁን ገልጣችሁ ከዚህ አጋጣሚ ምን መጠቀም እንደምትችሉ በጥልቀት አስቡ። ጨለማ ሲመጣ ብረሃንን የመጠበቅን ፅናት እንደሚያስተምር አስታውሱ። በህይወት ዝቅታ ውስጥ መውደቅም ዳግም እራስን አጠንክሮና አርሞ ለመውጣት እንደሚያዘጋጅ አስተውሉ። አዎ! አይናችሁን ግለጡ! "እኔ እድል የለኝም፣ የነካውት ሁሉ ይበላሻል፣ ገደኛ አይደለውም፣ እድሌ ጠማማ ነው።" ብላችሁ ከመደምደማችሁ በፊት በዙሪያችሁ የሚመጡላችሁን እድሎች መመልከት ስለመቻላችሁ እርግጠኛ ሁኑ። እናንተ መመልከት ካልቻላችሁ ሁሌም እድለቢስ መሆናችሁ አይቀርምና አይናችሁን ግለጡ፣ እድላችሁን ተመልከቱ፣ አጋጣሚዎችን አጢኑ፣ አንድ ነገር ስታጡ ምን ልታገኙ እንደሆነ አስተውሉ፣ አንደኛው በር ሲዘጋባችሁ የትኛው በር ሊከፈትላችሁ እንደሆነ አጢኑ። በህይወት ብዙ ተስፋ አስቆራጭና የውድቀት ጊዜያት ቢኖሩም ተስፋ ቆርጦ፣ እጅ ሰጥቶ፣ በውድቀቱ እያማረሩ መቀመጥ ብቸኛው አማራጭ ሆኖ አያውቅም። ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚለው "አይን አላችሁ አታዩም፣ ጆሮ አላችሁ አትሰሙም፣ ልብ አላችሁ አታስተውሉም።" ምንምእንኳን እድል ከፊታችን ቢመጣም ማስተዋል ካልቻልን እጣፋንታችን ምሬትና ብስጭት ብቻ ይሆናል። የደፈረሰ መጥራቱ አይቀርም፣ የመጣ መሔዱ አይቀርም፣ መከራም ማለፉ አይቀርም። በዚህ መሐል ግን "እኔ ምን ማትረፍ እችላለሁ?" ብለው የሚጠይቁ ሰዎች ብቻ አጋጣሚዎችን እንደ እድል ይጠቀማሉ። አዎ! ጀግናዬ..! አቀርቅረህ ስትሔድ የምትመለከተው መሬቱን ብቻ ነው፣ ቀና ብለህ አካባቢህን እየቃኘህ ስትሔድ ግን ከምድር በላይ ያሉ ክስተቶችን እያስተዋልክ ከእነርሱም ውስጥ የሚጠቅሙህን እየመረጥክ መጠቀም ትጀምራለህ። በዙሪያህ ምን እየተከናወነ ነው? ረጅሙን ጊዜህን ከነማን ጋር እያሳለፍክ ነው? አብረውህ ካሉ ሰዎች ጋር ምን መስራት ትችላለህ? አንተ ጋር ምን አለ? ከቅርብ ሰዎችስ ምን ማግኘት ትችላለህ? ዓለም በእድል ብትሞላ እንኳን አንተ መመልከት ካልቻልክ ስለመኖሩ እርግጠኛ መሆን አትችልም። ህይወት በአጋጣሚዎች የተሞላች ነች፣ አጋጣሚውን እንደ እድል መጠቀም ወይም እየፈሩ ማሳለፍ የእኛ ድርሻ ነው። እድላችሁን አታሳልፉ፣ እድለቢስ እንደሆናችሁ ቢሰማችሁ እንኳን አዲስ ነገር መሞከራችሁን እንዳታቆሙ፣ የተለየ ቦታ መገኘታችሁን እንዳትተው። ወድቆ መቅረትን፣ ተስፋ ቆርጦ መቆምን፣ ተሰብሮ አንገት ደፍቶ መቅረትን በፍፁም የመጨረሻ አማራጫችሁ አድርጋችሁ እንዳትቀበሉ። "ወድቋል፣ አብቅቶለታል፣ ዋጋ የለውም፣ ተስፋው ተማጧል" ባሏችሁ ማግስት እንዴት አፈር ልሳችሁ፣ ክንዳችሁን አጠንክራችሁ በፈጣሪያችሁ እርዳታና በእናንተ ብርታት ቀና ማለት እደምትችሉ አሳዩአቸው። አይናችሁን ግለጡ፣ ሁሌም አጋጣሚዎችን ወደ እድል ለመቀየር ተዘጋጁ።

  • ለሰው ፊት አትስጡ! ክፍት ቤት ለማንም ክፍት ነው በራችሁን ዝጉ፤ ልፍስፍስ ልብ የማንም መፈንጫ የማንም መጫወቻ ነው ልባም ሁኑ፤ እምቢ የማለት ድፍረት፣ ሰውን የማስቀየም ብርታት የሌለው ሰው የሰው ሁሉ መቀለጃ ነው። የማንም መቀለጃና መጫወቻ መሆን ካልፈለጋችሁ አንድ መረር ጠጠር ያለ ነገር አድርጉ። እርሱም ለሰው ፊት አትስጡ፣ ሰው ህይወታችሁን እንዲያውክ አትፍቀዱ፣ ሰው በውሳኔያችሁ ጣልቃ እንዲገባ አታድርጉ። ከማንም በላይ ለራሱ መሆን የሚችል፣ ራሱን የሚያስከብር ሰው ሁኑ። ዙሪያችሁ በሙሉ በአስመሳዮች ቢታጠር፣ ከፊት ከኋላችሁ ፈሪና በይሉኝታ የታሰረ ሰው ቢበዛ እንናንተ ግን ከዛ መሃል ውጥታችሁ ራስን የማዳኑን ብርቱ ጀብድ ለመፈፀም አትፍሩ። ሰው በሰጣችሁት እድል ልክ ቦታ ይሰጣችኋል። ሰው ሊንቃችሁ ሲሞክር እምቢ ማለት ልመዱ። ሁን ብላችሁ አስባችሁበት ያሰመራችሁት የሚያስከብራችሁ ቀይ መስመር ሲነካ ዝም አትበሉ። ድንበራችሁ ትርጉም እንዲኖረው አድርጉ። በዚህ ዓለም ፈሪና ደካማ ሰው ቦታ የለውም። አንድም ቦታ እንዲሰጣችሁ ሌላም ራሳችሁን ለመጠበቅና ማንነታችሁን ለማሳየት አንዳንዴም ቢሆን በሚገባው ቦታ ልካችሁን ከማሳየት ወደኋላ አትበሉ። አዎ! ለሰው ፊት አትስጡ፤ የማንም ወሬ ማሞቂያ አትሁኑ። ተሸሽጋችሁ ኑሩ፣ ሲያስፈልጋችሁም በሚገባ ጠንካራ ማንነታችሁን ግለጡ። ሰዎች ሁን ብለው የሚያደርጉባችሁ ክፉ ነገር አያስደንግጣችሁ፤ ዓለም አሳቻ ሰዓት ጠብቃ የምትለቅባችሁ ሸክም አያስበርግጋችሁ። በስነልቦናም ሆነ በአካል ብቃት ራሳችሁን ለምንም ነገር ዝግጁ አድርጉ። ምድራዊ ህመም መጨረሻው የተሻለ ማንነትን መግንባት ነው፣ በሰው መገለልና መገፋት መጨረሻው ራስን ሆኖ መገኘት ነው። ያለምንም ቅድመሁኔታ ሰውን ፊት መንሳት ልመዱ፤ ለማያከብራችሁ ሰው ዝቅ ማለት አቁሙ። ራሱን የሚያከብር ሰው የሰው መጥፎ ተግባር አይረብሸውም። በሰው ምክንያት ማለቃቀስ አያዋጣም፤ በህይወት ውጣውረድ ተስፋ መቁረጥ የትም አያደርስም። ቆፍጣና ልብ ሰንሰለቱን ይበጥሳል፣ ብርቱ ሰው መከራውን ይሻገረዋል። ሰው ፊት ውደቁ ነገር ግን ወድቃችሁ አትቅሩ እያዩዋችሁ ተነሱ፤ ለምድር ፈተና ተጨነቁ ነገር ግን ጭንቀታችሁ ፍሬ አልባ እንዲሆን አታድርጉ። ማንም አቅማችሁን እንዲገምት እድል አትስጡት፣ የማንም መላምት በህይወታችሁ እውን እንዲሆን አትፍቀዱ። አዎ! ጀግናዬ..! የተቹህን አፍ የምታዘጋው አንተ ነህ፣ የሳቁብህን፣ የተሳለቁብህን፣ ከጀርባህ ሊጥሉህ የጣሩትን የምታሳፍረው አንተ ነህ። ስራህ ታላቅ ያደርግህ ዘንድ ጠንክረህ የምትሰራበትን ትልቅ ምክንያት ስጠው፣ ሁሉም ሰው ይከተልህ ዘንድ አንተ ብቻ የምታውቀውን ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰው ሆነህ አሳይ። ዴቪድ ጎጊንስ (David Gogins) ምን ይላል "ታላቅ መሆን በጣም ቀላል ነው ምክንያቱም የዚህ ዘመን ሰው በጣም ደካማ ነው።" ትንሽ ብትሰራ ትናንተ የናቁህ አይደሉም ትናንት የማያቁህ ሁላ ተነስተው ያጨበጭቡልሃል፤ ትንሽ አንገትህን ቀና ብታደርግ አንተ ሳትሆን ሰዎችና ስራህ ታላቅነትህን ይመሰክሩልሃል። በሰው ምላስ ውስጥ ገብቶ ወደኋላ መመለስን እንዳታስበው፣ የሰው መዘባበቻ፣ የሰው መቀለጃ ሆኖ ተስፋ መቁረጥን በፍፁም እንዳታስበው። ለሰው በምትሰጠው ቦታ ልክ ትሞታለህ ወይም ትነሳለህ። አንዳንዴ ቸልተኝነት ተገማች አያደርግምና አዋጭ ነው። አታወላውል፣ ራስህን ግራ አታጋባ ያንተ የሆነውን የራስህ ለማድረግ ጊዜ አታጥፋ። ህጉን እወቀው፣ ጫወታውን ተጫወት፣ የሚገባህን ስፍራም በእጅህ አስገባ። የአንድ ወቅት አሸናፊ ብቻ ሳይሆን ሁሌም እያሸነፈ የሚቀጥል ሰው ብቻ ክብሩን አስጠብቆ እንደሚቆይ እወቅ።

  • ላንተ ብቻ አልተዘጋጀም! ህይወት የምልልስ መንገድ ነች። የከፍታውና የዝቅታው መንገድ ምልልስ፣ የመጎዳትና የመንፃት ምልልስ፣ የመሰበርና የመጠገን ምልልስ፣ የማዘንና የመደሰት ምልልስ። ስለዚህም ነው የነዚህን ምልልስ አይቀሬነት ተገንዝቦ ችግሮችን ከማጉላትና በደስታም ጫፍ ከመንካት መቆጠብ አስፈላጊ የሆነው። የዝቅታ ጊዜያት፣ የመረበሽ ወቅቶች የሚባሉት የፍራቻ፣ የሃዘን፣ የመገለል፣ የመጎዳት፣ የመቸገር፣ የመሰቃየትና አስጨናቂ ጊዜያት እንዲሁ መጥተው የሚሔዱና የተለመዱ (normal) የሚባሉ የህይወት ክስተቶች ናቸው። ብቻህን መፍታት ያልቻልከው ችግር ካለ እርዳታ ጠይቅ፣ እንቅልፍ የሚነሳህ አስጨናቂ ሃሳብ ካለብህ ለልብ ወዳጅህ ተንፈስ በል፣ እንደ ከባድ ጭነት የከበደህ ሸክም ካለብህ ለአምላክ አዋየው፣ ለእርሱ አስረክበው፣ በእርሱ ላይ ጣለው። ያንተን ችግር በማቅለሉ የሚመፃደቅ አምላክ እንዳልሆነም አስታውስ። አዎ! ጀግናዬ..! አንተን መርጦ አልመጣም! ላንተ ብቻ አልተዘጋጀም፣ አንተ ላይ ስለሆነ ብቻ ተዓምርና የማይሆን አይነት ነገር እንዳይመስልህ። ማንኛውም ሰው እንደሚወድቀው ትውድቃለህ፣ እንደማንኛው ሰው ትሰበራለህ፣ ተስፋ ትቆርጣለህ፣ ታዝናለህ። ማንም እንደሚሆነው ትከዳለህ፣ ትናቃለህ፣ ትገፋለህ። ይህ ሁሉ ግን አንተ ላይ ብቻ የተከሰተ እንዳልሆነ አስታውስ። በሰወኛው ባህሪ ለብቻ ከፍ ማለት እንጂ ለብቻ መጎዳትን አንወድ ይሆናል። ነገር ግን የሰውነት ማንነታችን ማለፍ የሚገባንን አስቸጋሪና አስከፊ ጊዜም እንድናልፍ ያደርገናል። በውስጣችን የገነባነው ጠንካራው ስብዕና ወደፊት ያሻግረናል። አዎ! የሆነብህ፣ የደረሰብህ፣ እየሆነብህ ያለው ሁሉ አዲስ አንዳልሆነ አስተውል። አመጣጡ ያንተ መዳረሻ እርሱን አልፈህ፣ እርሱን ተሻግረህ የምትደርስበት መሆኑን ለማስገንዘብ እንደሆነ እወቅ። መጨነቅህ፣ ማዘንህ፣ ተስፋ ማጣትህ አዲስ አይደለም፤ ሰው ነህና ከእነዚህ ከባድ ሁኔታዎች መንፃት አትችልም። ከመጡ ቦሃላ ግን ማንፃትና ማስተካከል ትችላለህ፤ ከእነርሱ ነፃ መውጣት ትችላለህ። በነገሮች መበላሸት አትደነቅ፣ በእቅድህ አለመሳካት እትረበሽ፣ በሚያስጨንቁና በሚያናድዱ የህይወት አጋጣሚዎች የውድቀትና የበታችነት ስሜት አይሰማህ፣ ብዙ እንቅልፍ አልባ ምሺቶችን ማሳለፍህ፣ ረፍት አልባ ጊዜያት ውስጥ መገኘትህ የማይታመንና ይበልጥ ጫና ውስጥ ከከተተህ ማመንንና መቀበልን የመጀመሪያ አማራጭህ አድርገው። ለብቻ የመብሰልሰልን፣ በውስጥ የመያዝን፣ በጉዳዩ ዙሪያ መነጋገር መፍራትን እንመፍትሔ መቁጠር አቁም። ካንተ ችግር በላይ አሳልፈው ዛሬም ደስተኛ የሆኑ ሰዎች እንዳሉ አስታውስ። እንዲያልፍ የፈቀድክለት የትኛውም ከባድና አስቸጋሪ ጊዜ ያልፋልና በማካበድና ብዙ በመጨነቅ ስሜትህንና ጊዜህን አታባክን።

  • ማንንም አትጠይቁ! ውስጣችሁ የሚነግራችሁ አንድ ነገር አለ። እርሱንም ማድረግ የምትችሉት እናንተ እንደሆናችሁ ታውቃላችሁ። ስለዚህ ማድረግ ካለባችሁ ማንንም ሳታማክሩ ዝም ብላችሁ አድርጉት። ያገኛችሁትን ሰው ሁሉ ማማከር ይቅርባችሁ። የብዙ ሰዎችን ስህተት አትድገሙ። ጥቂት የማይባል ሰው ምን ያደርጋል? በግሉ የመጣለትን ሀሳብ በሙሉ ለሚመለከተውም ለማይመለከተውም በማጋራት ጊዜውንና ኢነርጂውን ያባክናል። አንድ ስራ መጀመር አስባችሁ እናንተ ያሰባችሁት ስራ እንደማይዋጥለት ከምታውቁት ሰው ጋር ለምን ትወያያላችሁ? እቅዳችሁ የሶሻል ሚድያ ስራ መጀመር ሆኖ ስለሶሻል ሚድያ ምንም እውቀት የሌለው፣ ቪድዮ ከማየት በስተቀር እንዴት እንደሚሰራ ምንም እውቀቱ የሌለው ሰው በምን ሚዛን የእናንትን የContent Creation ሀሳብ እንዲደግፍ ትጠብቃላችሁ? ወደዳችቹም ጠላችሁም ዋናው ጉዳይ ማለቅ ያለበት እራሳችሁ ጋር ነው። ምንም ነገር ለመጀመር ስታስቡ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ለማስገባት አትቸኩሉ። ብዙ ሰው ባማከራችሁ ቁጥር ብዙ ሀሳብ ታገኛላችሁ የበዛው ሀሳብ ደግሞ ግራአጋብቶ የእናንተን መነሻ ሀሳብ ዋጋቢስ የማድረግ ከፍተኛ እድል አለው። አዎ! ማንንም አትጠይቁ፣ ከአቅማችሁ በላይ ካልሆነ በቀር ማንንም አታማክሩ። የውሳኔ ሰው ሁኑ፣ ሃላፊነት ውሰዱ፣ ከከሰራችሁም ክሰሩ ትማሩበታላችሁ፣ ከተበላሸም ይበላሽ ድጋሜ በተሻለ መንገድ ትሰሩታላችሁ፣ ከወደቃችሁም ውደቁ ዳግም መነሳት እንደሚቻል ውስጣችሁን አሳምኑት። የዓለም እውነታ ይሔ ነው፣ በጣም ብዙ ሰው በሀሳባችሁ አይስማማም፣ ከምትጠይቁት አብዛኛው ሰው ሀሳባችሁ አይዋጥለትም፣ ሊደግፋችሁም ፍቃደኛ አይሆንም። ስለዚህ ይሔንን እውነታ ተረድታችሁ እቅዳችሁን ማባከንና መና ማስቀረት ካልፈለጋችሁ በስተቀር ድጋሜ እቅዳችሁን ለማንም አታማክሩም፣ ለማንም አትናገሩም። ከማንም በሚመጣ ሀሳብ ለመሞላትም ሆነ ማንም የሚነግራችሁን ሀሳብ ተቀብላችሁ ለመፈፀም ጊዜ የላችሁም። ያላችሁ ጊዜ በጣም ጥቂት ነው። ጊዜያችሁን የእራሳችሁን ሀሳብ ወደ ምድር በማምጣት ተጠቀሙት። ማንንም የማባበል ግዴታ የለባችሁም፣ ማንም እንዲደግፋችሁ የማስገደዱም መብት የላችሁም። ውሳኔው በእጃችሁ ነው። የሚደግፋችሁን ሰው እስክታገኙ ሰዎችን መጠየቃችሁን መቀጠል ወይም በሀሳባችሁ ተማምናችሁ ወደ ተግባር መግባት። አዎ! ጀግናዬ..! ማንንም ጣልቃ አታስገባ፣ እንዴትም ውጫዊ ግፊትና ጫና ሀሳብህን እንዲያስቀይርህ አትፍቀድ። ሀሳብህን እንደ ሀሳብ በልብህ ያዘው፣ እቅድ አውጣለት፣ ከእራስህ ጋር ተማከርበት፣ አዋጭነትቱን በሚገባ አጥና፣ በደምብ እወቀው፣ ግልፅም አድርገው። ላንተ ግልፅ እስከሆነ፣ አንተ እስከተረዳሀውና አንተ እስካመንክበት ድረስ የማንም ድጋፍ እንደማያስፈልግህ እወቅ። የማያዳግም ቆራጥ ውሳኔ መወሰን ከፈለክ ብዙ ሰው ማማከር አቁም፣ ሀሳብህን ወደ ተግባር መቀየር ከፈለክ ለማንም ማብራራት ሳይኖርብህ በልበሙሉነት አድርገው። የምታማክረው ሰው ብትወድቅ አብሮህ አይወድቅም፣ ሀሳብ የምትጠይቀው ሰው ብትከስር አብሮህ አይከስርም፣ የሚያስፈራራህ ሰው ሃሳብህ መና ቢቀር ካንተ ጋር አይጎዳም። በስተመጨረሻ ከሀሳብህም ሆነ ከውጤትህ ጋር የምትቀረው አንተ ብቻ ነው። በእርግጥ ሰውን ማማከር ትልቅ ጥቅም አለው፣ ነገር ግን የምታማክረው ሰው በሀሳብህ እንደሚስማማና የተሻለ አማራጮችን እንደሚጠቁምህ እርግጠኛ ካልሆንክ ባታማክረው ብታተርፍ እንጂ አትጎዳም። ውስጥህን አዳምጥ፣ እርምጃ ውሰድ፣ ማድረግ ያለብህን በጊዜ አድርግ፣ መውሰድ ያለብህን ትምህርትም በተግባር ውሰድ።

  • ስሜታችሁን አትስሙ! የትኛውም ምቾት መነሻው ለጊዜያዊ ስሜት መገዛት ነው። ስሜት ከመቅፅበት ይቀያየራል፣ ውስጣችሁ ወዲያው ወዲያው ይላወሳል፣ አንዴ ይደሰታል አንዴ ያዝናል፣ አንዴ ዘና ይላል አንዴ ይደብረዋል። ሁሉም ስሜቶች መነሻ አላቸው፣ ምክንያት ይኖራቸዋል። ምክንያታቸው ምንም ቢሆን ስሜታችሁን አምናችሁ እርሱን የምትንከባከቡ ወይም ከዛ ስሜት ለመውጣት የምትጠብቁ ከሆነ እንዴትም የገዛ ህይወታችሁ ላይ ስልጣን ሊኖራችሁ አይችልም። ገዢያችሁ ስሜታችሁ ሳይሆን እናንተ መሆን አለባችሁ፣ መሪያችሁ ወቅታዊ ሙዳችሁ ሳይሆን ውስጣዊ ፍላጎትና ማንነታችሁ መሆን አለበት። ራሳችሁን ማባበል አቁሙ። ሲከፋችሁ ዓለም ሁሉ እንደምትከፋ ማሰብ አቁሙ፤ እናንተ ስትደሰቱ ዓለም ሁሉ እንደምትደሰት ማሰብ አቁሙ። የእናንተ ስሜት ለዓለም ምኗም አይደለም። ሃዘንን እስከ ጥግ ታዩታላችሁ፣ የድብርትን ጣሪያ ትነኩታላችሁ፣ ብቸኝነት ደጋግሞ ያሰቃያችኋል፣ በዛው ልክ በአንድ ወቅት የዓለማችን ቁጥር አንድ ደስተኛ ሰው ትሆናላችሁ፣ ህይወት በፈገግታ ትቀበላችኋለች፣ ዓለም እጅ ነስታ ታስተናግዳችኋለች። የስሜት መውጣት መውረድ ሁሌም አለ። ነገር ግን ስሜታችሁ መሪያችሁ እንዳልሆነ አስተውሉ። አዎ! ስሜታችሁን አትስሙ! ማንን መስማት ነፃ እንደሚያወጣችሁ ጠንቅቃችሁ እወቁ። ስልጡን ሰው በዋናነት የሚሰለጥነው ስሜቱ ላይ ነው፣ ሃይለኛ ሰው አስቀድሞ የራሱ የሚያደርገው ጥበብ የስሜት ብልህነት የተሰኘውን ጥበብ ነው። አንተ ሳታውቅ ስሜትህ መርቶ አዘቅት ውስጥ እንዲከትህ አትፍቀድለት። አልቃሻ ሰው ስሜቱን ከማሸነፍ በላይ ተደብቆት ሊያመልጠው ይጥራል፣ ልፍስፍስ ሰው ሃላፊነቱን ላለመወጣቱ ወቅታዊ ስሜቱን ይወቅሳል። የትም ሒዱ የት ከሃላፊነታችሁ በላይ ስሜታችሁን የምታስቀድሙ ከሆነ ውድቀት መገለጫችሁ መሆኑ አይቀርም። ሰው ናችሁና መቼም ቢሆን ሁሌም የተስተካከለ ጥሩ ስሜት ሊሰማችሁ አይችልም። ስሜታችሁን እየመጣ እንደሚሄደው ሰው ቁጠሩት ይመጣል ይሔዳል እንደገና ይመጣል እንደገና ይሔዳል እናንተ ከሰለጠናችሁበት ሔዶ እንደሚቀረው ሰው በዛው በሔደበት ይቀራል። ለራሳችሁ ከልክ በላይ ርህራሔ አታሳዩ። መጨከን ካለባችሁ ጨክንቡት፣ ማሰቃየት ካለባችሁ አሰቃዩት። እሹሩሩ እያላችሁ የማትፈልጉትን ልፍስፍስ ማንነት አትፍጠሩ። አጉል ርህራሔ መደምደሚያው ቂልነት እንደሆነ አስተውሉ። አዎ! ጀግናዬ..! በምናብህ ውስጥ ያለው ዓለም የተለየ ነው፣ ስሜትህም እንዲሁ የተለየ ነው። የትኛው ስሜት በምናብህ ውስጥ ወደተፈጠረው የተለየ ዓለም እንደሚወስድህ ጠንቅቀህ እወቅ። ማንንም ለመርዳት ከመፍጨርጨርህ በፊት ራስህን መርዳት፣ ራስህ ላይ መሰልጠን፣ ስሜትህን መምራት እንዳለብህ አስተውል። ሰውነት ብዙ ደካማ ጎኖች አሉት። በአንዲት ቅፅበት ሙሉ ህይወትህ ሊቀየር ይችላል። ማጣት የስቃይ ሁሉ መነሻ ነው፣ ድህነት ከሰው ሁሉ በታች ያደርጋል፣ ድምፅ እያለህ ድምፅ አልባ ያደርግሃል፣ አዋቂ ሆነህ እንደአላዋቂ ያኖርሃል። የዛሬ ማጣትህ ልብህን እንዳይሰብረው ተጠንቀቅ፣ ይልቅ ዘመንህን በሙሉ በማጣት ስትዳክር መቆየትህ ያሳስብህ። አሁን የድህነት ተምሳሌት መሆንህ አያስጨንቅህ፣ ይልቅ እድሜ ልክህን የድህነት መጫወቻ መሆንህ ያስጨንቅህ። ስሜትህን በአዎንታዊነት ከመነዘርከው ሃብትህ ነው፣ በአሉታዊነት ካዳመጥከው ግን መጥፊያህ ነው። በስሜትህ ቁጥጥር ስር በመውደቅ ባርነትን አትለማመድ። ስሜትህ ጥሩ ሆነም አልሆነም፣ በሰዓቱ ተደሰትክም አዘንክም ጥርስህን ነክተህ መስራት ያለብህን ስራ ስራ። ከስሜትህ በላይ የሚያነግስህ ምግባርህ እንደሆነ አስተውል።

  • መርሁን አስተውል! በአስራ ስምንት ዓመትህ ሰዎች ሁሉ ስላንተ የሚያወሩ፣ አንተን ብቻ የሚመለከቱ፣ የሚከታተሉህ፣ የዘወትር ጉዳያቸው አንተ እንደሆንክ ታስባለህ። በዚህም ልክ ከእራስህ በላይ ሰዎች ስለሚሰጡህ ስምና ከእነርሱ ስለምታገኘው ምላሽ በመጨነቅ ጊዜህን ታባክናለህ፤ እራስህን ከማስደሰት በላይ ለሰዎች ደስታና እርካታ ትልቅ ዋጋ ትከፍላለህ፤ ሰው ምን ይለኛል በሚል ሃፍረት ትታሰራለህ፤ ነፃነትህን ለማወጅ ባሰብክ ቁጥር የሰው ምላስ ከፊትህ ተደቅኖ ትመለከታለህ፤ ባጠቃላይ ህይወትህ በሙሉ ለሰዎች በሚከፈል መሱዓትነት ይሞላል። በአርባ ዓመትህ የሰው ነገር ምንም አይመስልህም፤ ምንም ብትባል ግድ አይሰጥህም፤ ስለፈለጉት ቢያወሩብህ፣ ስምህን ቢያጠፉ፣ ስራህን ቢተቹ፣ አንተን ቢነቅፉህ ምርጫቸው እንደሆነ ይገባሃል። በቀደሙት አመታት ሲያስጨንቁህ የነበሩ ጉዳዮች ማስጨነቃቸውን ያቆማሉ፤ ሌላ የተለየ አጀንዳ ውስጥ ትገባለህ። በስልሳ ዓመትህ የሁለቱንም ልዩነት ማመዛዘን ትጀምራለህ፤ ለሰዎች ብለህ ያጣሀው ነገር ካለ በእርሱ ትቆጫለህ፤ ማንም ግድ በማይሰጠው ጉዳይ ስትጨነቅ እንደነበር ታስተውላለህ፤ የሰዎች ስጋትና ፍራቻ ሁሉ የውሸት እንደነበር ይገባሃል። አዎ! ጀግናዬ..! መርሁን አስተውል፤ በሚገባ ተረዳው። ብዙዎች ስላላወቁት ይሸወዳሉ አንተ ግን ካወከው ዘንዳ፣ ከተረዳሀው፣ ከገባህ ለመተግበር ወደኋላ አትበል። ማንም ሰው ግድ ለማይሰጠው ጉዳይ እየፈራህና እየተጨነክ አትኑር። ያዩኛል፣ ይከታተሉኛል፣ ይተቹኛል፣ ምን ይሉኛል ብለህ የምትጨነቅላቸው ሰዎች በሙሉ የእራሳቸው የማያልቅ ጉዳይ አለባቸው። ማንም ያንተ አዲስ ነገር መጀመር፣ በተለየ መንገድ መጓዝ፣ በአዲስ አቋም መታደስ አያሳስበውም። ሁሉም የግሉ ሩጫ ላይ ነው። ምናልባት በአጋጣሚ ሲያይህ የመጣበትን ቃል ሊሰነዝርብህ ይችላል ከዛ ቦሃላ ግን ትዝም አትለውም። እያንዳንዱ ሰው በግል ጡዘት በተጠመደበት ጊዜ አይኖች ሁሉ እኔ ላይ ናቸው ብለህ አትሸወድ። ማንም ስታልፍ ያይህ ይሆናል እንጂ ጉዞህን በሙሉ እየተከታተለ አይኖርም። የእራስህን ኑሮ መኖር ላይ አተኩር፣ ከፈጣሪህና ግድ የሚሰጠሁን ሰዎች እስካላሳዘንክ ድረስ ሌላው ነገር ትርፍ ነው። መጀመሪያ የምትኖረው ለእራስህ እንጂ ለሰው አይደለም። አዎ! ሰበብ አታብዛ ደስታ የሚሰጥህን፣ ያመንክበትን፣ የሚጠቅምህን ነገር በጊዜ አድርግ። ህይወትህን በፍረሃት አትሰራት፤ መኖርን በማይሆን ገደብ አትከልላት። በትንሹም ቢሆን ጥረትህን ጀምር፤ ደስታህን ወደ መፍጠር ተሸጋገር፤ የእራስህን አለም አበጃጅ፤ ፈጣሪህ ያይሃል፤ አምላክ ያውቅልሃል፤ ይረዳሃል፤ ይቀድምልሃል። ስለመጪው ጊዜ ቁጪትና ብትስጪት የምትጨነቅበት ምክንያት የለህም። በአጋጣሚ ያገኘህና የተመለከተህ ባላወቀህ መጠን ሊናገር ይችላል፤ አስቦና ፈልጎ የሚመለከትህ ግን በእርግጥም ሊደግፍህ እንደሚመጣ አትጠራጠር። ልዩነት መፍጠሩን አሁኑኑ ጀምር፤ በልብህ የያዝከውን፣ በአዕምሮህ ያነገብከውን ሃሳባዊ አለም ከምድራዊው ተጨባጭ አለም ጋር ቀላቅለው። የመጣው ይምጣ፤ የሆነው ይሁን፤ የማይቀር ነገር እንደሆነ የመጣውን ተቀበል። በእራስህ ተመማመን፤ ለእራስህ ብለህ ድፈር፤ ጠንክር፤ ለእራስህ ብለህ ህይወትህን በሙላት ኑር።

  • አይንህን ጣልባቸው! በሮች ሲዘጉ መስኮቶች ይከፈታሉ፤ ጨለማ ሲውጥህ ትንሽዬ የብረሃን ጭላንጭል ትታይሃለች፤ በእራስህ ስታዝን የሆነ የሚያጓጓህ ነገር ይከሰታል፤ ተስፋ ስታጣ አምላክህ አብሮህ መሆኑን ስታስብ ተስፋ ማድረግ ትጀምራለህ። ህይወት እንዲህ ነች፤ ፅናትህን ትፈልጋለች እንጂ እድሎችን ዘግታ አትዘጋም፤ እምነትህን ትሻለች እንጂ እስከ ወዲያኛው ተስፋ የምታስቆርጥ አይደለችም፤ ብርታትህ ያስፈልጋታል እንጂ እንዲሁ እንደ ቀላል ቆላልፋ አታስቀርህም። ብዙ በሮች ይዘጉብህ፣ አንተ ግን ወደ ተከፈቱት መስኮቶቾ ማማተርህን ቀጥል፤ ጨለማ ይክበብህ፣ አንተ ግን ወደ ትንሿ የብረሃን ጭላንጭል ተጠጋ፤ ተስፋ ማጣት ይፈታተንህ፣ አንተ ግን የመኖርህ ምክንያት፣ የተስፋህ ሚስጥር ወደ ሆነው አምላክህ ቅረብ፤ ተነሳሽነት ይጉደልህ፣ ድካም ይሰማህ አንተ ግን ጠንክረው የሚያጠነክሩህ፣ በርትተው የሚያበረቱህ ላይ አተኩር። አዎ! ጀግናዬ..! ጨለማውን ለመግፈፍ፣ ህይወትን በተስፋ ለመሙላት፣ የተሻለውን ክስተት ለመፍጠር ተስፋን ወደሚሰንቁት፣ ብረሃን ወደሚያስገቡት የተከፈቱ መስኮቶች አይንህን ጣልባቸው፤ ተስፋ ወደሚሰጥህ አምላክ ተጠጋ፣ የሚያዋጣህን አቅጣጫ ያዝ። ህይወት ላከበዳት ከባድ፣ ላወሳሰባት ውስብስብ፣ ለደከመላት አድካሚ፣ ተስፋ ለቆረጠባት ተስፋ አስቆራጭ ነች። በተቃራኒውም ለተማመነባት ታማኝ፣ ለተደሰተባት አስደሳች፣ ላመሰገነባት አትራፊ፣ ላቀለላት ቀላል፣ ለሚኖራትም በፍቅር የምትኖር ነች። በትግል እደሰታለሁ፣ በውጪው ጫጫታ እረካለሁ፣ በከባቢው እረካለሁ ካልክ መቼም እንደማይሆንልህ አስታውስ። ከውስጥህ የሚወጣ እንጂ ከውጭ የሚመጣ ነገር አያሳርፍህም፤ የሆንከው እንጂ ያስመሰልከው ረፍት አይሰጥህም፤ ለእራስህ የተሰጠው እንጂ የቀማሀው አያስደስትህም። አዎ! ማንንም ሳትጠብቅ ወደ ውስጥህ መመልከት ከጀመርክ ዙሪያህ በሙሉ ይቀየራል። ሁን ብለህ የምታጠፋው ጥፋት፣ አስበህበት የምትጋፈጠው ውድቀት፣ ፈልገህ የምታጣው ተስፋ የለም። ከእያንዳንዱ ድርጊቶች ጀርባ አስገዳጅና ከባድ ምክንያቶች ይኖሩሃል። ነገር ግን እስካልፈቀድክለት ድረስ የትኛውም ከባድ ነገር መኖርህን ሊያስጠላህ፣ ህይወትህን ሊያጨልም፣ ተስፋህንም ሊያሳጣህ አይችልም። ምንም ውስጥ ብትሆን በህይወት በመኖርህ የምትኮራበት፣ በመተንፈስህ የምታመሰግንበት ጊዜ አታጣም። የመጀመሪያው ሽንፈትህ እስከወዲያኛው ሽንፈትን እያፈራረቀ፣ ውድቀትን እያስከተለ፣ ሃፍረትን እያከናነበ አይቀጥልም። አዎ! ሽንፈትህን ብቻ ከቆጠርክ ብዙ ተሸንፈሃል፤ ወደፊት እየተሸነፍክ ትቀጥላለህ። አሸናፊነትህን ከቆዘርክ፣ ድልህ ላይ ካተኮርክ፣ የተሻገርካቸውን መሰናክሎች፣ ያለፍካቸውን ፈተናዎች ካስታወስክ የአሁኑን ጨምሮ መጪዎቹን ፈተናዎችና መከራዎች እየተሻገርክ፣ እያሸነፍክ ትቀጥላለህ። ምንም ለማሰብ፣ ምንም ላይ ለማተኮር፣ ምንም ለማድረግ ማንም እጅህን በካቴና አስሮ የሚያስገድድህ አካል የለም። እራስህን የምታስረው፣ ማንነትህን የምታሳንሰው፣ አቅምህን የምትገድበው፣ ሰውንተህን የምትቀብረው አንተ እራስህ ነህ። ትኩረትህን በመቀየር ህይወትህን ቀይር፤ እይታህን በማሻሻል የህይወት አረዳዳህን አሳድግ፤ ክብርህን እያሰብክ፣ ከፍታህን እያስተዋልክ በልኩ ተንቀሳቀስ።

  • 7 авг.1 5022010

    ❤️አ😍ፈ😍ቅ😍ር😍ሻ😍ለ😍 ሁ❤️ አ🥰= አንድ ነገር ቀረኝ ከጥፋት መታቀብ ፈ🥰= ፈልጌው አደለም አላበዛም ሰበብ ቅ🥰= ቅንነትሽ ደስታ ስሜትን ይስባል ር🥰= ርሀብን ያስታግሳል ጥምንም ያስቆማል ሻ🥰= ሻማ ሁነሽኛል በጨለመው ጎኔ ለ🥰= ለማንም አልፈቅድም እንዲለዩሽ ከ #እኔ👈 ሁ🥰  = ሁሌም ወድሻለሁ ትናፍቂኛለሽ እስከማይሽ በ#አይኔ😢

  • 6 авг.1 618161

    አንዳንድ ጊዜ መናገር የማይገባሽን ቃል ትናገሪያለሽ ፡፡ ማድርግ የማይጠበቅብሽን ነገር ታደርጊያለሽ ፡፡ ምንም ማድረግ አትችይም ሰው ነሽ ፡፡ ስትኖሪ ትሳሳቺያለሽ ፡፡ ከስህተትሽ ትማሪያለሽ ፡፡ ስትማሪ ታድጊያለሽ ፡፡ የተሻልሽ ሰውም ትሆኚያለሽ ፡፡ ይህ ሰው የመሆን ሂደት ነው ፡፡ መሳሳት ፣ መማርና ማደግ...!

  • 6 авг.1 54084

    ምናልባት እኔ ምርጥ አይደለሁም ግን ቢያንስ ለጊዜያዊ መዝናኛ ብቻ ብዬ የአንድ ሰው ልብ አልሰብርም 💔