Prosperity Party - ብልፅግና
СтатистикаThis is an official telegram channel of prosperity party.
- Последний пост
- 10 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 45
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 2 154
- 1/48двое суток
- 2 468
- 1/72трое суток
- 2 662
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
ሣምንታዊ መልዕክት! ዛሬ የተከልነዉ ችግኝ ነገ ጥላ እንደሚሆን ሁሉ፤ ዛሬ የምንገነባው የጋራ እሳቤም ነገ የሀገር ጽናት ይሆናል! እኛ ኢትዮጵያውያን በኅብረት ስንቆም የሚያስቆመን ምድራዊ ሀይል አለመኖሩን የቀደመዉ ታሪካችን ይመሰክራል፡፡ አድዋ ላይ በልዩነቶቻችን ሳንከፋፈል፣ በአንድ ልብና በአንድ ዓላማ ተሰልፈን የቅኝ ግዛት ሥርዓት ካባ ሊያላብሰን ድንበር ተሻግሮ የመጣዉን ወራሪ ድል ነስተናል። ይህ ታሪካችን ትልቅ ትምህርት ነው፤ የጋራ ዓላማችንን ከግለሰባዊና ከቡድናዊ ልዩነቶቻችን በላይ ስናደርግ ትላልቅ ድሎችን እንደምናስመዘግብ ህያዉ ምስክር ነዉ፡፡ የዛሬውም ትውልድ ይህንኑ የቀደምቶቹን ታሪካዊ መንፈስ በአዲስ መልክ መድገሙን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኅብረትና የሀገራዊ ቁርጠኝነት ምልክት ሆኖ በመቆም አረጋግጧል፡፡ የአረንጓዴ አሻራም በተመሳሳይ መንፈስ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን በአንድ ዓላማ አሰባስቦ ሀገራዊ ለውጥን በተግባር እያሳየ ይገኛል። በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) የተጀመረዉ የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር በስምንት ዓመት ጉዞዉ 48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች እንዲተከሉ አድርጓል፡፡ በዚህም ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር የመተው ኃላፊነት፣ የምግብ ዋስትናን የማጠናከር ጥረት፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በዚህ ዓመት “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን መትከላችን በኅብረት ስንንቀሳቀስ ምን ያህል ታላቅ ግብ ማሳካት እንደምንችል ያሳየን የአንድነት ድል ነው። በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ባህል እየሆነ የመጣዉ የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር የደን ሽፋን ወደ 23.4 በመቶ እንዲያድግ ምክንያት ሆኗል፡፡ የጋራ ዓላማን ለማሳካት ከሚደረግ ጥረት ጎን ለጎን አብሮነትን፣ ወንድማማችነትን/ እህትማማችነትን በማጎልበት ለሀገራዊ አንድነት መጠናከር የአንበሳዉን ሚና እየተወጣ ይገኛል፡፡ በብልጽግና ፓርቲ የሚመራዉ የመደመር መንግሥት አረንጓዴ ኢኮኖሚን፣ የአካባቢ ጥበቃንና የተፈጥሮ ኃብት መንከባከብን ትልቅ ትኩረት በመስጠት ከ2011 የክረምት ወቅት ጀምሮ በየዓመቱ ‘አረንጓዴ አሻራ’ ገቢራዊ እያደረገ ይገኛል። በመላ አገሪቱ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች እያሳተፈ መርሃ-ግብሩ እንደቀጠለ ነው። ይህ መርሀግብር ኢትዮጵያን በአፍሪካና በዓለም አቀፍ መድረክ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ተምሳሌት ያደረገ ተግባር ነው። አሁን ላይ ደግሞ የችግኝ መትከል ባህል ከመንግሥት ቅስቀሳና ከግለሰቦች ጥረት ባለፈ ሀገራዊ ቅርፅ የያዘ ሲሆን ባለፉት ስምንት ዓመታት የተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ትልቁ ማሳያ ነው። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን አለም አቀፍ ገፅታና ተጽዕኖ ፈጣሪነት በማጠናከሩ ሀገራችን ኢትዮጵያ የCOP32 አስተናጋጅ እንድትሆን አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡ በመሆኑም በተፈጥሮ እንክብካቤ መሪ መሆኗን አሻራዋን በማኖር እያረጋገጠች ከፊት ወደሚጠብቃት የCOP32 አስተናጋጅነት ታሪካዊ ኃላፊነት ታቀናለች፡፡ በአንድ ጀምበር የተከልናቸዉ ሚሊዮን ችግኞች ተከታታይ ክትትልና እንክብካቤ ይፈልጋሉ፡፡ በመሆኑም የተከልነውን ማሳደግ፣ ያስጀመርነውን ማስቀጠል እና የጋራ ጉዳዮቻችንን በኅብረት ማሳካት ይጠበቅብናል። እንዲሁም ዘላቂ ልማትና ሰላም፣ የኢኮኖሚ እድገት፣ ሀገራዊ አንድነትና ሌሎች የጋራ ጉዳዮቻችን ላይ በህብረት መረባረብ ይገባናል፡፡ ዛሬ የተከልነዉ ችግኝ ነገ ጥላ ይሆናል፤ ዛሬ የምንገነባው የጋራ እሳቤም ነገ የሀገር ጽናት ይሆናል። ስለዚህ ችግኝ መትከል ለአካባቢ ጥበቃ ብቻ የሚደረግ ተግባር አይደለም፤ ለልጆቻችንና ለልጅ ልጆቻችን የምናስረክበውን ሀገር ዛሬ የመገንባት ሀገራዊ ኃላፊነትም ጭምር ነው።
видео или голосовое, без подписи
"ሌብነት ላይ ጠንከር ያለ ርምጃ እንወስዳለን፤ ማን ላይ እንደሚያርፍ አላውቅም፤ ማንም ላይ ቢያርፍም ግን ጠንከር ያሉ ሥራዎችን እንሰራለን" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግሥት በአረንጓዴ አሻራ ያስመዘገባቸውን ስኬቶች በሁሉም ዘርፎች ለመድገም በቁርጠኝነት ይሰራል - አደም ፋራህ በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግሥት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ያስመዘገባቸውን ስኬቶች በሁሉም የልማት ዘርፎች ለመድገም፣ ሕዝቡን በሰፊው በማሳተፍና የልማት ተጠቃሚነቱን በማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና የዋና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ገለጹ። አቶ አደም ፋራህ፣ የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፣ ሚኒስትሮች፣ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የፀጥታ ኃይሎችና የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ህዳሴ ፓርክ በመገኘት አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል። በዚሁ ወቅት "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል የተካሄደውን የአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል መርሃ ግብር በይፋ ያስጀመሩት አቶ አደም፣ ይህ ቀን ያለ ልዩነት በአንድነት የምንንቀሳቀስበትና የሀገራችንን ታሪክ በጋራ የምንጽፍበት የሀገራዊ አንድነት ቀን መሆኑን ገልጸዋል። "ባለፈው ዓመት 714 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድነት ተክለናል፤ ዘንድሮ 800 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል ትልቅ ሀገራዊ አደራ ነው" ያሉት አቶ አደም፣ ሁሉም ዜጎች አሻራቸውን በማሳረፍ የዚህን ሀገራዊ ግብ እንዲያሳኩ ጥሪ አቅርበዋል። አቶ አደም ፋራህ እንደገለጹት፣ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በ2011 ዓ.ም ያስጀመሩት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተራቆተውን ሥነ ምህዳር ከመመለስ ባለፈ የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ የታለመ ሀገራዊ እንቅስቃሴ ነው። አክለውም የምግብ ዋስትናና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እንቅፋት ሆኖ ከቆዩ ዋነኛ ምክንያቶች መካከል የደን መመናመንና በቂ የዛፍ ተከላ አለመኖሩ ይጠቀሳሉ። ይህንን ችግር ለመቅረፍ በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ እንቅስቃሴ ዘርፈ ብዙ ውጤቶች መመዝገባቸውንም ገልጸዋል። በተለይም መርሃ ግብሩ የምግብ ዋስትናን በማጠናከር፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትንና የሀገሪቱን ሁለንተናዊ እድገት በማፋጠን፣ የሕዝብን አብሮነትና ወንድማማችነት በማጠናከር እንዲሁም ሀገራዊ አንድነትን በማጎልበት ለሀገር ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አስረድተዋል። እንዲሁም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን አለም አቀፍ ገፅታና ተጽዕኖ ፈጣሪነት በማጠናከሩ ሀገሪቱ የCOP32 አስተናጋጅ እንድትሆን አስተዋጽኦ እንዳበረከተ ጠቁመዋል። በመጨረሻም በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮችን በማንሳት፣ የችግኝ ተከላን ከብዛት ወደ ጥራት ማሸጋገር፣ የተተከሉ ችግኞችን በአግባቡ መንከባከብና ለታለመላቸው የኢኮኖሚና የአካባቢ ልማት ዓላማዎች በብቃት መጠቀም እንደሚገባ አሳስበዋል። "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል የተካሄደው የአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል መርሃ ግብር በመላው ኢትዮጵያ በሰፊ የሕዝብ ተሳትፎ እየተካሄደ ነው።
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02GaDGbzwemPPSj2ima3DQyxsTfHby34G8ao5Y4fMCTgoYZdwpv5CRLuFvJN2F3myFl&id=100044231869241&mibextid=ZbWKwL
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи