Sharp Swords | ስለታማ ሰይፎች
Статистика🖋️ ስለታማ ሰይፎች የእይታ አድማስን የሚያሰፋ የነፍስ መስታወት! ✨ ♦️በአላህ ፍቃድ የቆሰሉ ልቦችን የሚጠግን፣ በውድቀት ውስጥ ያለን ጥንካሬ የሚዘክርና ተስፋን የሚያድስ። ህይወት በአንድ መጥፎ ምዕራፍ አታበቃም፤ መፅሐፉን አትዝጉት! ከመከራ መስመር ስር የድል ፊርማ ተቀምጧል። 📖🚩 ✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል http://tiktok.com/@sharpswords1
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 20
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 13
- 1/48двое суток
- 14
- 1/72трое суток
- 16
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
🌿🌿🌿🍃ጥቆማ🍃🌿🌿🌿 መውሊድን በተመለከተ በኡስታዝ ኢብኑ ሙነውር የተዘጋጁ ከፊል ፅሁፎችን በቀላሉ እነዚህን ሊንኮች በመጫን ማንበብ ትችላላችሁ። 1, ነብዩ ﷺ መቼ ተወለዱ? t.me/IbnuMunewor/893 2, መውሊድን ማን ጀመረው? በመረጃ ለሚያምኑ ብቻ t.me/IbnuMunewor/869 3, መውሊድ ለምን አላማ እንደተጀመረ ያውቃሉ? t.me/IbnuMunewor/876 4, መውሊድና ነባሩ እስልምና አይተዋወቁም! {ምስክር እራሳቸው!} t.me/IbnuMunewor/884 5, “በአላህ እዝነት ይደሰቱ...” - ትልቁ የመውሊድ አጋፋሪዎች ምርኩዝ t.me/IbnuMunewor/2227 6, የሰኞ ፆም እና መውሊድ t.me/IbnuMunewor/2214 7, ዐቂቃ ሌላ መውሊድ ሌላ! t.me/IbnuMunewor/2261 8, ዓሹራን ለመውሊድ? t.me/IbnuMunewor/2269 9, መውሊድ ውስጥ እነዚህ አደጋዎች አሉ! t.me/IbnuMunewor/2294 10, በመውሊድ ላይ ስለሚፈፀመው ጭፈራ ዑለማዎች ምን እንዳሉ ታውቃለህ? t.me/IbnuMunewor/882 11, መውሊድን የሚፈቅዱትም አይፈቅዱትም! t.me/IbnuMunewor/2298 12, መውሊድ የማያከብር ሰው የሙሐመድ ﷺ ጠላት ከሆነ፣ ገና የማያከብር ሰው የዒሳ ጠላት ነው! t.me/IbnuMunewor/886 13, እውን የሡወይባ ታሪክ ለመውሊድ ማስረጃ ይሆናል? t.me/IbnuMunewor/2234 14, ሸውካኒ እና መውሊድ (ወሳኝ ነጥቦች የተዳሰሱበት) t.me/IbnuMunewor/898 15, ሲዩጢ፣ የመውሊድ ደጋፊዎች ሌላኛው ምርኩዝ t.me/IbnuMunewor/2277 16, እውን ኢብኑ ተይሚያ መውሊድን ፈቅደዋል? t.me/IbnuMunewor/878 17, በሸይኹል አልባኒ እና “መውሊድ ይፈቀዳል” በሚል ሰው መካከል የተደረገ ድንቅ ቃለ-ምልልስ t.me/IbnuMunewor/34 18, ከ“ወሃብዮች” በፊት የነበሩ የመውሊድ ተቃዋሚዎች t.me/IbnuMunewor/1624 19, መውሊድ ተከሽኖ t.me/IbnuMunewor/2309 20, ለምንድን ነው የመውሊድ ተቃውሞ ኢኽዋኖችን ምቾት የሚነሳቸው? t.me/IbnuMunewor/918 21, መሷሊሐል ሙርሰላ፣ የመውሊድ አክባሪዎች የመጨረሻው ምሽግ t.me/IbnuMunewor/2302
የማለዳ መልእክት (46) ~ ከአቡ ሁረ ይረህ - ረዲየላሁ ዐንሁ - ተይዞ ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ أكْملُ المؤمنينَ إيمانًا أحسنُهُم خلقًا . وخيارُكُم خيارُكُم لنسائِهِم "ከምእመናን መካከል ኢማኑ ሙሉ የሆነው ሥነ-ምግባሩ ያማረው ነው። ከእናንተ መካከል በላጮቹ ለሴቶቻቸው (ለባለቤቶቻቸው) መልካም የሆኑት ናቸው።" [አቡ ዳውድ (4682)፣ ቲርሚዚይ (1162) እና አሕመድ (2/ 472) የዘገቡት ሲሆን ሸይኹል አልባኒይ "ሐሰኑን ሶሒሕ" ብለውታል። (ሶሒሑ ቲርሚዚይ፡ 1162) ] የራሳችንን ሁኔታ እናጢን፤ የተሻለ ለመሆንም እንጣር። (ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል አወል 01/1448)
━━━━━━━━━━━━━━━ Telegram: 👇👇 https://t.me/SharpSwords1 ቲክቶክ: 👇👇👇 ➊ tiktok.com/@sharpswords1 ➋ tiktok.com/@sharpswords2 https://www.tiktok.com/@sharpswords1?_r=1&_t=ZS-98s5u3iScxm
اللهم صلي وسلم وزد وبارك على نبينا محمد https://www.tiktok.com/@sharpswords1?_r=1&_t=ZS-98s5u3iScxm
14. በመውሊድ በዓላት የተከበሩ የአላህ ቤቶች በጭብጨባ፣ በውዝዋዜና በጭፈራ ክብራቸው ይረከሳል። ይሄ ደግሞ አላህ ከሃዲዎችን እንዲህ ሲል ከወቀሰባቸው ነገሮች ውስጥ ነው፡- (وَمَا كَانَ صَلَاتُهُمۡ عِندَ ٱلۡبَيۡتِ إِلَّا مُكَآءٗ وَتَصۡدِيَةٗۚ) {በቤቱ ዘንድም ስግደታቸው ማፏጨትና ማጨብጨብ እንጂ ሌላ አልነበረም።} [አል-አንፋል፡ 35] ሃያሉ ጌታ እንዲከበሩና ስሙ እንዲወሳባቸው ባዘዘባቸው መስጂዶች ውስጥ ድቤ መደብደብ፣ ማጨብጨብና መጨፈር በአራቱም መዝሀብ የተወገዘ እጅግ አስነዋሪ ተግባር ነው። ይህን ቆሻሻ ተግባር መቃረቢያ አድርጎ ማሰብ ደግሞ የለየለት ጥመት ነው። ኢብኑል ጀውዚይ፡ “ዳንስን ወደ ላቀው አላህ መቃረቢያ ነው ብሎ የሞገተ ሰው ከኢስላም እንደሚወጣ የዑለማዎች ኢጅማዕ ተቋጭቷል” ብሏል። [ሶይዱል ኻጢር፡ 168] 15. ብዙ የመውሊድ ዝግጅቶች የሴትና የወንድ ቅልቅል በብዛት አለባቸው። የብል -ግና መናሃሪያ እየሆኑም ነው። በእለቱ እቃ እያዞሩ የሚሸጡ ሰዎች ሲጋራ፣ ኮንዶምና መሰል ነገሮችን እንደሚይዙ ተጨባጭ መረጃ አለ። በአንዳንድ አካባቢዎች ሴተኛ አዳሪዎች መውሊድ በሚከበርበት አካባቢ የተለያዩ ነገሮችን ለመሸጥ በሚል ሽፋን ጊዜያዊ ዳስ በመቀለስ ለጥፋት እንደሚሰማሩ ከሰበሰብኳቸው መረጃዎች አረጋግጫለሁ። አል-መቅሪዚይ በ790 ሂጅሪያ በዒማዱል አንባኒይ በተዘጋጀው መውሊድ ላይ የታዘበውን እንዲህ ሲል ይገልፀዋል፡- “ሜዳው በዓሊሞች እስከሚጨናነቅ ህዝብ ጎረፈ። በዚያች ሌሊት ሴቶችና ወጣቶች ከባለጌዎች ጋር በመቀላቀላቸው ምክንያት ብዙ አይነት ብልግናዎች ተፈፀሙ። ማለዳ ላይ ሌሊቱን የተጠጡ ከሃምሳ በላይ የአስካሪ መጠጥ እንስራዎች በዛውያው ዙሪያ በነበሩ እርሻዎች ውስጥ ተጥለው እንደተገኙ፣ በርካታ ደናግላንም ክብረ-ንፅህናቸው እንደተገሰሰ፣ በጣም ብዙ ገንዘብ የወጣባቸው ሻማዎችም እንደተለኮሱ እጅግ በርካታ መረጃ ወጥቷል። በማግስቱ ጧት አላህ የንፋስ ጥቃት ላከባቸውና ከቦታው የነበሩ ሰዎችን ፊታቸውን አፈር አለበሳቸው። ድንኳኖቹንም ቆራረጣቸው። አንድም ሰው ባህር መሳፈር አልቻለም። ከዚያን ጊዜ በኋላ መውሊድ አልተዘጋጀም።” [ዱረሩል ዑቁዲል ፈሪዳህ፡ 2/501] 16. የመውሊድ ጨፋሪዎች በውዝውዛኔና መሰል ነገሮች ሰውነታቸው ዝሎ ሌሊቱን ገፍተው ስለሚተኙ አብዛኞቹ የፈጅር ሶላትን የተወሰኑት ደግሞ ዙህርንም ጭምር አይሰግዱም። ለነገሩ ክፍለ - ሃገር ላይ አብዛኛው ታዳሚ ከነጭራሹ ሶላት ሰጋጅ አይደለም። 17. መውሊድ ለማክበር አገር አቋርጠው ረጃጅም ርቀቶችን የሚጓዙ ሰዎች ሞልተዋል። ነብዩ ﷺ ግን ለቢድዐ ቀርቶ ለአላህ ታስቦ ለሚፈፀመው አምልኮት እንኳን ከሶስቱ መስጂዶች (መስጂደል ሐራም፣ መዲና የነብዩ መስጂድ እና አቅሷ) ውጭ አገር አቋርጦ መጓዝ እንደማይገባ አሳስበዋል። [ቡኻሪ፡ 1189] [ሙስሊም፡ 3450] አገር አቋርጠው ያለ መሕረም የሚጓዙ ሴቶችም ቀላል አይደሉም። ነብዩ ﷺ ግን “ማንኛዋም ሴት ከቅርብ ወንድ ቤተሰቧ ጋር እንጂ እንዳትጓዝ” ብለዋል። [ቡኻሪ፡ 1862] 18. መውሊድ የልዩነት መንሰኤ ነው። ለዚህም መውሊድ በተቃረበ ቁጥር የሚነሳውን ውዝግብ መስማቱ ብቻ በቂ ነው። በመውሊድ ላይ ስላልተጋሯቸው ብቻ “ወሃ ~ ቢ”፣ “የነቢ ጠ ^ላት”፣ “ከአይ ^ ሁድ በከፋ ዲን ያበላሹ” እያሉ ሙስሊሞችን መወንጀል የተለመደ ዘመቻ ነው። ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንደሚሉት “ቢድዐ ከልዩነት ጋር የተቆራኘ ነው።” ስለዚህ ቢድዐው እስካለ ድረስ መለያየቱ አይቀርም። ሸውካኒይ እንዲህ ይላሉ፡- “ደግሞም ይሄ መውሊድ ከተከሰተ በኋላ ውዝግቡ ተጧጡፏል። በዚህም ላይ የሚፃፉት ኪታቦች ከከልካዩም ከፈቃጁም በዝተዋል። … ከነሱ ውስጥ እንደማይፈቀድ ቁርጥ አድርጎ የተናገረ ሲኖር ከነሱ ቢድዐነቱን አምኖ መጥፎ ነገር ካልተቆራኘው በሚል መስፈርት የፈቀደው አለ፣ ምንም ማስረጃ ግን አላመጣም።” [አልፈትሑ ረባኒይ፡ 2/1091 - 1095] ጥፋቶቹ እነዚህ ብቻ አይደሉም። ይህን ሁሉ ጉድ አጭቆ የያዘ ቢድዐ ከጥቃቅን ነገሮች ነውን? ህሊና ያለው ይፍረድ። በርግጥ ከነዚህ ጥፋቶች ውስጥ ከፊሎቹን የሚርቁ አሉ። ግና አንደኛ ጥቂት ናቸው። ሁለትኛ እነዚህ እራሱ ድግሳቸውን በሺርክ የተቀላቀለ መንዙማ ባዮችን ይጋብዙበታል። ከሺርኩ ቢጠራም ድርጊቱ በራሱ መረጃ የለውምና ከቢድዐነት አይዘልም። ሶስተኛ በጥፋት የተወረረውን መውሊድ ሊያወግዙ ቀርቶ የሚያወግዙትን የሚነቅፉ ናቸው። ስለሆነም ጥፋታቸው ከነዚያኞቹ ጥፋት ብዙም የራቀ አይደለም። = ኢብኑ ሙነወር ©️ IbnuMunewor
የመውሊድ አደጋዎች ~ ከመውሊድ ቢድዐ የምናስጠነቅቀው መነዛነዝ ስለሚያምረን፣ በአጉል ቡድንተኝነት ተነሳስተን ወይም በሌላ ምክንያት ሳይሆን እነዚህ አደጋዎች ስላሉበት ወገናችን እንዲነቃ በማሰብ ነው። 1. መውሊድን ማክበር የነብዩን ﷺ እና የምርጥ ትውልዶቻቸውን ፈለግ መጣስ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡- (وَمَن يُشَاقِقِ ٱلرَّسُولَ مِنۢ بَعۡدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ ٱلۡهُدَىٰ وَيَتَّبِعۡ غَيۡرَ سَبِيلِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ نُوَلِّهِۦ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصۡلِهِۦ جَهَنَّمَۖ وَسَآءَتۡ مَصِيرًا) {ቅኑም መንገድ ከተገለፀለት በኋላ መልእክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከአማኞቹም መንገድ ሌላ የሆነን የሚከተል ሰው በተሾመበት ላይ እንሾመዋለን። ጀሀነምንም እንከተዋለን። መጨረሻይቱም ከፋች።} [አን-ኒሳእ፡ 115] 2. መውሊድ “ዒባዳ ነው” ብሎ የሚያስብ ሰው “ዲኑ ሙሉእ ነው” የሚለውን ጌታ እያስተባበለ፣ ነብዩ ﷺ አደራቸውን አልተወጡም እያለ እየሞገተ ነው። ኢማሙ ማሊክ እንዲህ ይላሉ፡- “በኢስላም ውስጥ መልካም ናት ብሎ የሚያስባትን ቢድዐ የፈጠረ ሰው ሙሐመድ ﷺ ተልእኳቸው ላይ ሸፍጥ ሰርተዋል ብሎ እየሞገተ ነው። ምክንያቱም አላህ {ዛሬ ለናንተ ሃይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ} ብሏልና።” [ሱነኑ ዳሪሚይ፡ 141] ነብዩ ﷺ በመሰናበቻው ሐጅ ላይ “አጥብቃችሁ ከያዛችሁት ከሱ በኋላ የማትጠሙበትን ነገር በርግጥም ትቼላችኋለሁ፣ የአላህን ኪታብ። እናንተ ስለኔ ትጠየቃላችሁና ምንድን ነው የምትሉት?” ሲሉ ሶሐቦችም “አንተ በርግጥም እንዳደረስክ፣ አደራህን እንደተወጣህና እንደመከርክ ነው የምንመሰክረው” አሉ። ይህኔ አመልካች ጣታቸውን ወደ ሰማይ እያነሱ ከዚያም ወደ ሰዎቹ እየጠቆሙ “ጌታዬ ሆይ! መስክር” አሉ ሶስት ጊዜ በመደጋገም። [ሙስሊም፡ 3009] 3. የመውሊድ ቢድዐን የሚፈፅም ሰው የማይመነዳበትን ከንቱ ልፋት እየለፋ ነው ያለው። ነብዩ ﷺ “የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ እሱ (ስራው) ተመላሽ (ውድቅ) ነው” ብለዋል። [ቡኻሪ፡ 3/69] [ሙስሊም፡ 4590] 4. ይህን ቢድዐ የሚፈፅም ሰው ጥመት ላይ ነው። ነብዩ ﷺ “መጤ የሆኑ ነገሮችን ተጠንቀቁ። መጤ ፈሊጥ ሁሉ ፈጠራ ነው። ፈጠራ ሁሉ ጥመት ነው። ጥመት ሁሉ ወደ እሳት ነው” ብለዋል። [ኢርዋኡል ገሊል፡ 608] 5. መውሊድ የሚያከብርና እንዲከበር የሚሟገት ሰው ከሸሪዐ ክፍሎች ውስጥ አንዱ የሆነውን ነብዩን ﷺ የመውደድ ፅንሰ-ሀሳብን እያዛባ ነው። እሳቸውን ስለመውደድ፣ ስለማክበርና ስለመከተል የሚያትቱ ብዙ የቁርኣን አያዎችን፣ ሐዲሦችንና የሰለፎች ንግግሮችን ቀደምቶቻችን ባልተረዱት መልኩ በመተንተን እነሱ ላልፈፀሙት ቢድዐ ማስረጃ በማድረግ ነብዩን ﷺ መውደድ ማለት መውሊድን ማክበር፣ በሶለዋት ስም መጨፈር ተደርጎ እንዲሳል ተደርጓል። ይህ እሳቸውን የመውደድን ሸሪዐዊ ትእዛዝ ማዛባት ነው። 6. መውሊድን ማክበር በአንድምታ ቀደምቶቻችንን በነገር መውጋት አለበት። ሶሐቦችና ተከታዮቻቸው ከኛ በበለጠ ነብዩን ﷺ የሚወዱ ከመሆናቸው ጋር መውሊድን አላከበሩም። ዛሬ መውሊድን የሚያከብረው የነብዩ ﷺ ወዳጅ፣ የሚቃወመው ደግሞ የሳቸው ጠላት ተደርጎ እየተሳለ ነው። በነዚህ ሰዎች አረዳድ መሰረት ቀደምት ሰለፎችም ነብዩን ﷺ “አይወዱም ነበር” ማለት ነው። ይሄ አደገኛ ጥፋት ነው። እነዚያ ለነብዩ ﷺ ሲሉ አጥንታቸውን የከሰከሱ፣ ደማቸውን ያፈሰሱ፣ ቤታቸውን ያፈረሱ፣ ገንዘባቸውን የለገሱ ሶሐቦች መውሊድን ስላላከበሩ እሳቸውን “አይወዱም” ቢባል ማን ያምናል?! 7. መውሊድ በአብዛኛው ከባባድ የሆኑ ሺርኮች ይፈፀሙበታል። ለቀብር ሱጁድ የሚወርዱ፣ ለቀብር የሚሳሉ፣ ቀብር ጦዋፍ የሚያደርጉ፣ የቀብር አፈር ለበረካና ለፈውስ የሚወስዱ፣ በጥብጠው የሚጠጡ፣ ስለታቸውን የሚያደርሱ፣... አሉ። መንዙማዎቹ እራሳቸው በሺርክ የታጨቁ ናቸው። {አላህ በርሱ ማጋራትን በፍፁም አይምርም።} [አን-ኒሳእ፡ 48] 8. መውሊድ ከክርስቲያኖች ጋር መመሳሰል አለበት። የነብይን ልደት በዓል አድርጎ መያዝ ክርስቲያናዊ ሱና ነው። ክርስቲያኖች ገናን የሚያከብሩት የዒሳ ልደት ነው በሚል እንደሆነ የሚታወቅ ነው። ነብዩ ﷺ “ከሆኑ ሰዎች ጋር የተመሳሰለ ከነሱው ነው” ብለዋል። [ኢርዋኡል ገሊል፡ 1269] 9. መውሊድ ውስጥ ብዙ አይነት ድንበር ማለፍ አለ። በነብዩ ﷺ ላይ፣ በሌሎችም ሙታኖች ላይ ድንበር ማለፍ ይፈፀማል። ይሄ በእለቱ በሚነበቡ ግጥሞች፣ መንዙማዎችና ዶሪሖች ላይ በሰፊው የሚንፀባረቅ ነው። ነብዩ ﷺ ግን “ክርስቲያኖች የመርየምን ልጅ ዒሳን ድንበር አልፈው እንዳወደሱት አታወድሱኝ” ብለዋል። [ጋየቱል መራም፡ 123] አንዳንዶች በድፍረት የመውሊድ ሌሊት ከለይለተል ቀድር የበለጠ ነው ብለው እስከሚሞግቱ ደርሰዋል። [አልመዋሂቡ ለዱንያህ፡ 1/135] ሱብሓነላህ! ይህ ሁሉ የሚባለው እንግዲህ የተወለዱበት ቀን አወዛጋቢ ከመሆኑ ጋር ነው። ይህ ሁሉ የሚሆነው የተወለዱት በሌሊት እንደሆነ የሚጠቁም መረጃ በሌለበት ነው። በዚያ ላይ የተወለዱበት ጊዜ ከ 14 ከፍለ-ዘመናት በፊት ያለፈ እንጂ እንደ ለይለተል ቀድር በያመቱ የሚመላለስ አይደለም። ዐልዩል ቃሪ (1014 ዓ. ሂ.) “(የለይለተል ቀድር) በላጭነት ዒባዳ በሷ ውስጥ በላጭ ስለሆነ እንጂ በሌላ ምክንያት አይደለም። ይህም {መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺህ ወር በላጭ ናት} በሚለው ቁርኣናዊ ምስክርነት ነው። ለመውሊዳቸው ግን ይህቺ ብልጫ ከቁርኣንም፣ ከሱናም፣ ከሙስሊሙ ህዝብ ዑለማዎች ከአንድም አትታወቅም!” ይላሉ። [አልመውሪዱ ረዊይ፡ 97] 10. መውሊድን ከኢስላማዊ በዓላት ውስጥ ማካተት ሁለት አመታዊ በዓል ያደረጉልንን ነብይ ትእዛዝ መጣስ ነው። ነብዩ ﷺ መዲና ሲገቡ ነዋሪዎቿ የሚጫወቱባቸው ሁለት ቀናት ነበሯቸው። “ምንድን ናቸው እነዚህ ሁለት ቀናት?” ሲሉ ጠየቁ። “በጃሂሊያው ጊዜ እንጫወትባቸው ነበርን” አሉ። ይህኔ “የላቀው አላህ ከነሱ በላጭ በሆኑ ሁለት ቀናት ተክቶላችኋል። እነሱም የአድሓ ቀን እና የፊጥር ቀን ናቸው” አሉ። [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 1039] 11. የመውሊድ በዓልን ማክበር ለሌሎች የቢድዐ በዓላት በር መክፈት ነው። የወሊዮች ልደት እያሉ በመቃብር ዙሪያ ለሚልከሰከሱ፣ የልጆች አመታዊ ልደት ለሚያከብሩ ሰዎችና ለሌሎችም ምርኩዝ ማቀበል ነው። 12. የመውሊድ ኪታቦችና የመውሊድ ድግሶች በነብዩ ﷺ ስም በሚነገሩ የውሸት ቂሷዎች የታጨቁ ናቸው። “አብዛኛው በመውሊድ ደስኳሪዎች እጅ ያለው ውሸትና ቅጥፈት ነው” ይላሉ መውሊድ ደጋፊ የሆኑት ሰኻዊ። [አልመውሊዱ ረዊይ፡ 32] መልእክተኛው ﷺ ግን “በኔ ላይ ሆን ብሎ የዋሸ ሰው መቀመጫውን ከእሳት ያዘጋጅ” ይላሉ። [ቡኻሪ፡ 1291] [ሙስሊም፡ 5] 13. በመውሊድ የቢድዐ ድግስ ላይ ነብዩ ﷺ “ከጭፈራው ይታደማሉ” የሚል ሰቅጣጭ እምነት አለ። የቅጥፈታቸው ቅጥፈት የመውሊዱ ሌሊት ላይ “ነብዩ መጡ” እያሉ ከተቀመጡበት መነሳታቸው ነው። በነገራችን ላይ ነብዩ ﷺ ከሞቱ በኋላ ቀርቶ በህይወት እያሉ እንኳን ሲመጡ ሶሐቦች አይነሱላቸውም ነበር። [አስ-ሶሒሐ፡ 358] ሀይተሚ እንዲህ ይላል፡- “የዚህ አምሳያው ብዙዎች የነብዩ ﷺ ልደትና እናታቸው እሳቸውን መውለዷ ሲወሳ የሚያደርጉት መቆም ሲሆን ይህም ምንም አይነት መረጃ ያልመጣበት ቢድዐ ነው።” [አልፈታወል ሐዲሢያህ፡ 58]
видео или голосовое, без подписи
የማለዳ መልእክት (45) ለኸጢቦች እና ለዱዓቶች ~ የደዕዋ እና የኹጥባ መድረክ የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መድረክ ነው። የማህበረሰብን ንቃተ ህሊና ለመቀየር፣ ዲኑን ለማስተማር፣ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለማንቃት እጅግ የላቀ ቦታ ነው። ግን እንደሚገባ እየተጠቀምነው ነው ወይ? መድረኩ ነብያዊ አማና ነውና አማናውን እየተወጣን ነው ወይ? ለመድረኩ የሚመጥን አቅምና ዝግጅትስ አለን ወይ? ሐቅን ለመናገር፣ ማህበረሰብን ለመጠበቅ የሰዎችን ስሜትና ፍላጎታቸውን ተከትለን ነው የምንፈሰው ወይስ አላህን በማሰብ፣ ለሐቅ በመቆርቆር፣ ዘላቂ ጥቅምን በማስቀደም በጀግንነት እንጓዛለን? ኃላፊነትን ባለመወጣት ከመጠየቃችን በፊት ከራሳችን ጋር ሂሳብ እንስራ። 1. ወደ ህዝብ ከመቅረባችን በፊት በቂ ዝግጅት እናድርግ፣ አቅማችንን እናዳብር። ሳይዘጋጁ መቅረብ ታዳሚን መናቅ ነው። ቦታውንም ክብር ማሳጣት ነው። 2. መሰረታዊ የኢስላም ርእሶችን ቅድሚያ እንስጥ። አርካኑል ኢማን፣ አርካኑል ኢስላም፣ ተውሒድና ሺርክ፣ ሱናና ቢድዐ፣ ከባኢረ ዙኑብ፣ ስነ ምግባር፣ ኢስላማዊ ቤተሰብ፣ እንደ ኡማ ሊኖረን የሚገባ መተዛዘንና መደጋገፍ፣ ዘረኝነት፣ እንደ ጫትና ሲጋራ ያሉ ጎጂ ሱሶች፣ ወዘተ. የህዝብን ቁጣና ኩርፊያ ሳንፈራ ግን ደግሞ ባማረና በማያስበረግግ መልኩ ደጋግመን እናስተምር። 3. ርእስ መረጣ ላይ የሰዎችን ስሜትና ፍላጎት እየተከተልን አንፍሰስ። ትኩረታችን የሚጠቅማቸውን መስጠት ይሁን። ደዕዋ ሰው መለወጫ እንጂ መዝናኛ መድረክ አይደለም። የሰዎችን ስሜትና ፍላጎት እየተከተለ የሚፈስ አስተማሪ ፈሪና አስመሳይ እንጂ እውነተኛ ተቆርቋሪ አይደለም። 4. እንደ ዘመን በህዝብ ላይ የተጋረጡ አደጋዎች እና ወቅታዊ ክስተቶች ሲኖሩ አቅጣጫ መስጠት ያስፈልጋል። ለዚህ ደግሞ በቂ ንቃትና ዝግጅት ይፈልጋል። ንቃትና ዝግጅት ማለት እንግሊዝኛ መቀላቀል አይደለም። በሚዲያ የሰማነውን ዜና ማስተጋባትም አይደለም። የዳዒ ኃላፊነት እንደ ጋዜጠኛ ክስተቶችን ማንልበልና መተንተን አይደለም። መድረኮችን የፖለቲካ መደስኮሪያ እያደረጉ ማርከስ ንቃት አይደለም። ከዳዒ የሚጠበቀው ነገሮችን በኢስላም መነፅር በመመልከት ህዝብን ማረጋጋት፣ ሰዎችን ወደ አላህ መመለስ፣ በወቅታዊ ክስተቶች ከአቅማቸው በላይ በመግባት እንዳይዋጡ ማሳሰብ ነው። እንዳጠቃላይ ለመድረኩ የሚመጥን ትኩረት እንስጥ፤ አቅም እናዳብር፤ ዝግጅት እናድርግ፤ ጀግንነትን እንላበስ፤ ሐቀኛ ተቆርቋሪነትን ሁሌም እናስብ። ሰላም። (ኢብኑ ሙነወር፣ ሶፈር 30/1448) ©️ IbnuMunewor
видео или голосовое, без подписи
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: ③②⑥∅]👌 #ቁርኣን
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ❤️ #ቁርኣን #Qur'an
የማለዳ መልእክት (44) ~ ስለ ሌሎች ጥፋት መናገር የሚፈልግ ሰው የመጀመሪያው የሚጠበቅበት ነጥብ ማስረገጥ ነው። የተነገረን ነገር የእውነት በተወራው መልኩ ነው ወይ? ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ማስረገጥ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው፣ ዋጂብ። አሉባልታ ላይ ተመስርቶ ማማት፣ ፍረጃ ውስጥ መግባት፣ ነገር ማራገብ፣ ለመልስ መቸኮል፣ ... አንደኛ ከተቅዋ ጋር የሚሄድ አይደለም። ሁለተኛ ከማንም በላይ የሚጎዳው እኛኑ ነው። ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ كَفى بالمَرءِ كَذِبًا أن يُحَدِّثَ بكُلِّ ما سَمِعَ "አንድ ሰው የሰማውን ሁሉ ማውራቱ ከውሸት በኩል (ውሸታም ለመባል) በቂው ነው።" [ሙስሊም፡ 5] ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ “በሰው ላይ መዋሸት ሰውየው ሙስሊምም ሆነ ካ^ፊር፣ መልካምም ሆነ አመፀኛ ሙሉ ለሙሉ ክልክል ነው። በሙእሚን ላይ መቅጠፍ ግን የከፋ ነው፡፡” [መጀመዑል ፈታዋ፡ 28/ 223] ውሸቱ ሰላም የሚያደፈርስ፣ ሰዎችን የሚያቆራርጥ፣ ደዕዋን የሚያሰናክል ከሆነ ደግሞ በሚደርሰው ጥፋት ሁሉ ተጠያቂነት ስለሚኖር በጣም መጠንቀቅ ያስፈልጋል። (ኢብኑ ሙነወር፣ ሶፈር 29 /1448) = ©️ IbnuMunewor
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: ③②⑤⑧]👌 #ቁርኣን
*حين تشرق شمس الصباح، تذكّر أن الله أعاد إليك يومًا جديدًا، فلا تستقبله بمعصيةٍ كنت بالأمس تتمنى أن تتوب منها.* When the sun rises in the morning, remember that Allah has blessed you with a new day. Do not welcome it with a sin that you wanted to repent from yesterday. — Your new day is a new test. 📚 የማለዳ ፀሐይ ስትፈነጥቅ፣ አላህ አዲስ ቀን እንደለገሰህ አስታውስ። ትናንት ተውበት ለማድረግ (ንስሀ ለመግባት) በተመኘኸው ወንጀል አዲሱን ቀን አትቀበለው። 🔴 — አዲሱ ቀንህ አዲስ ፈተና ነው።
ከፊሉ ልጅ የለኝም ብሎ ያለቅሳል። ሌላውን ልጁ ያስለቅሰዋል። ከፊሉ እህት ወንድም የለኝም ብሎ ይከፋዋል። ሌላው በእህት በወንድሞቹ ውስጡ ቆስሏል። ዱንያ አጃዒቧ አያልቅም። ግማሹ በመከራ፣ ሌላው በጥጋብ ያለቅሳል። "እናቱ የሞተችበትና፣ ገበያ የሄደችበት እኩል ያለቅሳል" በሚለው አገርኛ ብሂል ውስጥ ህመም አለ። መከራ ሁሉ አንድ አይደለም። ከባሰም በላይ ብዙ የባሰ እንዳለ በማስተዋል "አልሐምዱ ሊላህ" እንበል። = ©️ IbnuMunewor
видео или голосовое, без подписи
🎙️ የአዛን ታላቅነትና የቢላል (ረ.ዐ) ልዩ ቦታ የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ «ያ ቢላል! ተነሳና በሶላት አሳርፈን (እፎይ አብለን)።» (ሱነን አቡ ዳዉድ፡ 4985፣ ሶሂህ) ✨ ትምህርት፦ ነብዩ (ﷺ) የእኛ አርአያ ናቸውና፣ ሶላት ለእሳቸው የልባቸው ማረፊያ እንደነበረች ሁሉ ለያንዳንዳችንም ሙስሊሞች የልባችን ማረፊያና የእፎይታችን ምንጭ ልትሆን ይገባል። #አዛን #ቢላል #ሐዲስ #እስልምና #ሶላት
ወንጀል ማቆም አቃተኝ 🎤 መልስ: በሸይኽ ኢብኑ ባዝ
Sharp Swords | ስለታማ ሰይፎች pinned «የዓላማ ፅናት 📩 አንዳንዴ የህይወት አድማስ ሲጠብ፣ መንገዶች ሁሉ በጭጋግ ሲሸፈኑ፣ እንዲሁም በዙሪያችን ያሉ ማነቆዎች ሲበራከቱ፤ ብዙዎቻችን አቅም በማጣት አንገታችንን ደፍተን መሬት መሬቱን ማየት እንመርጣለን። ነገር ግን እውነተኛው መፍትሄ ያለው እይታችንን ከፍ በማድረግ ውስጥ ነው። የሰው ልጅ አስተሳሰቡ የደረሰበትን ያህል ይጓዛል፤ ልቡናው ያለመውን ያህል ይተጋል። ዛሬም ቢሆን ከጠባቡ የሰዎች አለም…»