ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
Статистика❝...ስሙን ያያውቅ ሃገሩን ያያጠይቅ «ኤፍሬም ሶርያዊ ኤፍሬም ለብሐዊ ብላችሁ ጥሩልኝ ከመዓዝነ ቤተ ክርስቲያን ባንዱ ቆሞ ይጸልይላችኋል» ብሎ አስጠርቶ.... ሲጨዋወቱም አድረው ኤፍሬም «አባ ባርከኝና ልሒድ» አለው። ባስልዮስም መች ልትሔድ እግዚአብሔር አምጥቶሃል ልትኖር እንጂ ብሎ ሕዝባዊ ነው ቢሉ ዲቁናን፥ ዲያቆን ነው ቢሉ ቅስናን ሹሞ ከሃገረ ሰብከቱ ከፍሎ እንዲአስተምር ሰጥቶታል።❞
- Последний пост
- 22 июл.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 442
- 1/48двое суток
- 506
- 1/72трое суток
- 546
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
🕯በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ሐምሌ ፲፭ ይኽች ቀን ክቡር ቅዱስ አባታችን ማር ኤፍሬም ሶርያዊ የዕረፍቱ መታሰቢያ የሚደረግባት ናት።🕯 በረከተ ጸሎቱ ሃብተ ረድኤቱ ከእኛ አትለይ🤲 #ሐምሌ_15 #ቅዱስ_ኤፍሬም @St_Ephrem_Syrian @st_ephrem_group
አዳም በኀጢአት ምክንያት የሞትን እንቅልፍ ወደ ዓለም አመጣ፥ ሕያው የሆነው እርሱ ግን ከወደቅንበት ጥልቅ የኃጢአት እንቅልፍ ሊያነሳን መጣ። እንግዲህ ባለ መተኛታችን ምክንያት ገንዘባቸውንና ወለዱን እያሰቡ በስግብግብነታቸው መተኛት እንዳልቻሉ እንደ አራጣ አበዳሪዎች አትመልከቱን፡፡ ወይም ደግሞ ንቁ ሆኖ እያደባ እንደሚሔድ፣ የሰረቀውንም ገንዘብ መሬት ውስጥ ቀብሮ እንቅልፉን አጥቶ እንደሚጠብቅ እንደ ሌባ የሚያየን ማን ነው? የዚህ ሌባ ንቃት እስከዚህ ድረስ ብቻ ነው። መተኛት ለሚገባው ነገር ከሚገባው በላይ ነቅቶ ይጠብቃልና፡፡ የእነዚህ ሰዎች ንቃት ከሚገባው በላይ በልቶ በቁንጣን ምክንያት ዕረፍትና እንቅልፍ እንዳጣ ገብጋባ ሰው ነው፡፡ የዚህ ሰው ንቃቱ ሥቃዩ ነው፤ በስስቱ ምክንያት ሰላሙን ያጣ ሰው ነው። የዚህ ሰው ንቃት በመሥራቱ ንዋይን እንደሚሰበስብና ከሁሉ በላይ እንደሚሆን እያሰበ እጆቹን ያለ ዕረፍት ሌሊቱን ሁሉ እንደሚያሠራ ነጋዴ ነው። በመሥራቱም ገንዘቡ በሁለት እና በሦስት እጥፍ እንደሚያድግ ያስባልና። የእነዚህ ሰዎች ንቃት ገንዘቡ እንቅልፉን እንዳራቀበት ባዕለ ጸጋ ነው። እርሱ ንብረቱን ከሌቦች ለመጠበቅ ቆሞ ያድራል፤ ውሾቹ ግን ሲተኙ ያድራሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ለጥንቃቄ ብሎ ሳይተኛ የሚያድር ሰውን ይመስላሉ፤ ጥንቃቄው እንቅልፉን ውጦታልና። ምንም እንኳ የመጨረሻ ሕቅታው በትራሱ ላይ ቢሆንም ለዓመታት ንብረቱን ሲጠብቅ ቆሞ ያድራል። ወንድሞች ሆይ ሰይጣን የሚያስተምረውን እንግዲህ አስተውሉ! መጠበቅ ያለብንን አስትቶ መጠበቅ የሌለብንን እንድንጠብቅ ያተጋናል፡፡ መልካም ሥራ በመሥራት ፈንታ እንተኛለን፤ ክፉ ሥራ ለመሥራት ግን እንነቃለን፤ በትጋትም እንፈጽመዋለን፡፡ የአስቆሮቱ ይሁዳ ሌሊቱን ሁሉ አልተኛም ነበረ። በትጋት ጠብቆ ንጹሕ የሆነውን ስሞ ሸጠ፤ እርሱ ዓለሙን ሁሉ የሚገዛውን ደም አሳልፎ ሰጠ። የጨለማ ልጅ የሆነው ይሁዳ ከብርሃን ተራቁቶ ጨለማን ለበሰ። የብር ፈጣሪ የሆነውን አምላክ ሌባ በብር ሸጠው። የጨለማ ልጆች የሆኑ ፈሪሳውያን ሌሊቱን ሁሉ ሳይተኙ ነቅተው ቆዩ፡፡ እነዚህ የጨለማ ልጆች ማንም ሊገድበው የማይችለውን ብርሃን ይከልሉ ዘንድ ተጉ፡፡ ነገር ግን በዚህ ሌሊት የነበረው ብርሃን መንግሥተ ሰማያት ውስጥ የሚኖር ብርሃን ነው፡፡ በከዋክብት ብርሃን የደመቀ ሌሊት ነው፡፡ ምንም እንኳ መልኩ ጨለማ ቢመስልም፣ ጊዜውም ሌሊት ቢሆን ነገር ግን ንጹሕና ብርሃናማ ነበር። እንግዲህ እንደዚህ ንጹሕ እና ብሩህ የሆነው ሌሊት ለጸሎት የሚነሣ በሌሊቱ ጨለማ ውስጥ ሆኖ በጸሎት የሚተጋ ሰው ሌሎች ሰዎች ሊያዩ የማይችሉትን ብርሃን ያያል። ክፉ ሰው ግን በቀን ብርሃን ውስጥ ሆኖ ጨለማ ውስጥ እንዳለ ሰውይሆናል፡፡ ምንም እንኳ ውጭው ብርሃን ቢሆንም ውስጡ ግን ጨለማ የለበሰ ነው፡፡ *ድርሳነ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ በጸሎት የምንተጋበት ምሽት ያድርግልን!🌓 ለወዳጆችዎም ያጋሩ🙏 #ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ #ጸሎት #ድርሳነ_ኤፍሬም @St_Ephrem_Syrian⌲
“እግዚአብሔር አምላክህን ፣ በፍጹም ልብህ ፣ በፍጹም ነፍስህ ፣ በፍጹም ኃይልህ (እንደችሎታህ መጠን) ውደድ” (ዘዳግ.6፥4-6)የሚለው ሕግ እርሱ የመጀመሪያው ሕግ ነው ፡፡ እግዚአብሔርንም ስለማፍቀርህ ምልክቱ ባልንጀራህን እንደራስህ መውደድህ ነው፡፡ ነገር ግን ባልንጀራህን የምትጠላው ከሆነ የአንተ ጥላቻ በእግዚአብሔር ላይይሆናል፡፡ ከባልንጀራህ ጋር በጠብ እየኖርህ በእግዚአብሔር ፊት ለጸሎት የምትቆም ከሆነ፣ እርሱን እንደ መሳደብ ይቆጠርብሃል፡፡ በከንቱ ቃላትን እያበዛህ እንደሆነ የገዛ ሕሊናህ ይመሰክርብሃል፡፡ ሕሊናህም ከጸሎትህ አንዳች ፍሬ እንደማታገኝ ያስታውቅሃል ፡፡ አምላክህ ክርስቶስ ስለ ገዳዮቹ በመስቀሉ ላይ ሳለ ይቅርታን ለመነ፤ እንዴት አንተ ፍጥረትህ ከትቢያ የሆነ ቁጣን በፈቃድህ በራስህ ላይ ታቀጣጥላለህ? በወንድምህ ላይቂምን ይዘህ ሳለ ጸሎትህ በእግዚአብሔር ዘንድ ተወዳጅ የሚሆን ይመስልሃልን ? በአንተ ምክንያት ከአንተ ጋር ያለ ፣ ነገር ግን በኃጢአትህ ተባባሪ ያልሆነው ሰው ድንኳን መተላለፍህ ያገኘዋል፤ በአንተ ምክንያትም ጸሎቱ አይሰማለትም። መራርነትን ከሰውነትህ አርቅ ከዛም ጸሎትህን አቅርብ ፡፡ ባልንጀራህ በቁጣ ውስጥ ከሆነ ፣ ምንም ቁጣው በአንተ ላይ ባይሆን ፣ ቁጣን ከሰውነቱ ያርቀው ዘንድ እርዳው ፤ ምክንያቱም በሰውነቱ ርኩሰት ይነግሥበታልና ፡፡ አንተ መንፈሳዊ ተፈጥሮ አለህ፡፡ ነፍስህም የእግዚአብሔር አርዓያና አምሳል ናት፡፡ እናም ከሰው ሁሉ ጋር በፍቅር በመኖር የእግዚአብሔር አርዓያ የሆነችውን ነፍስህን አክብራት፡፡ በምትኖርባቸው ዘመኖችህ ሁሉ በተቻለህ መጠን ሰውነትህን ከቁጣ ጠብቅ፡፡ ያለበለዚያ አንተን ወደ ሲኦል ታወርድሃለች ፤ ጎዳናዎቿም ወደ ገሃነም የሚያመሩ ናቸው፡፡ እናም ቁጣን በልብህ አታኑራት፡፡ መራርነትንም በነፍስህ አታሳድር፡፡ በነፍሰህ ላይ አንዳች ሥልጣን የለህምና ነፍስህን መልካም በማድረግ ጠብቃት፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ እንደተናገረው ©️ ⌲⌲⌲⌲⌲⌲⌲⌲⌲⌲⌲⌲⌲⌲⌲⌲⌲⌲⌲⌲⌲⌲⌲⌲ #ተግሳጽ 🕊️ @St_Ephrem_Syrian @St_Ephrem_group
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ቅዱስ ኤፍሬም በክርስቶስ ትንሳኤ ስላገኘነው አዲስ ተፈጥሮ እንዲህ ብሎ በድርሳኑ ጻፈ... ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ጌታችን የተከፈነበትን የመግነዝ ጨርቅ ከመቃብር ጥሎ መውጣቱ አዳም በኃጢአት ምክንያት የለበሰው ልብስ ሳያስፈልገው ወደ ገነት ስለመግባቱ ምሳሌ ነው። አዳም ከልብሱ ተራቁቶ ወደ ገነት ከመግባቱ በፊት ጌታችን ከመግነዙ ጨርቅ ተራቁቶ ወደ መንግሥቱ ገብቶአልና፡፡ አንድም ጌታችን የእርሱ ትንሣኤ ምሳሌያት የሆኑትን ትቶ ያለ ልብስ በክብር ወደ አባቱ እንደተመለሰ እንዲሁ እኛም ያለ ልብስ ከሥራችን ጋር እንነሣለን። የአይሁድ ካህናት መቃብሩን የሚጠብቁ ወታደሮችን በገንዘብ አባበሏቸው፡- “እኛ ተኝተን ሳለን ደቀ መዛሙርቱ በሌሊት መጥተው ሰረቁት”™ እንዲሉ አደረጓቸው። እንዲህ ማድረጋቸው ጌታችን በሲኦል ያሉትን ነፍሳት መርቶ እንደሚያወጣቸው ከቃሉ ተረድተው ስለ ነበር ነው። እንዲሁም ትንሣኤውን በተመለከተ ምስክርነት ከወንበዴዎች (ከወታደሮቹ) እንዳይሻ ያሳየበት ነው። ጌታችን የአጋንንት አፍ ዘጋ ምክንያቱም እውነት እንኳ በሐሰተኞች ቢነገር የማይታመን ነውና፡፡ አዳም ባይስት ኖሮ የሰው ልጅ አኗኗሩ ምን እንደሆነ አይሁድ እስቲ ያስረዱን፡፡ መሲሑ ክርስቶስን ባይገድሉት እንኳ እግዚአብሔር በሌላ መንገድ ለሕዝቡና ለአሕዛብ ሕይወትን ሊሰጥ ይችል እንደነበር ይረዱ። እንዲህም ብለን እንመን፡- አዳም የሞተው ኃጢአትን በመሥራቱ በመሆኑ ኃጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱ የግድ ሊሞት አስፈለገው፡፡ በአዳም ላይ እንዲህ ተብሎ ተፈርዶአልና፡- “ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና” ነገርግን እንደ በላ ወዲያው የሞተ አይደለም፤ ነገር ግን የልጅነት ጸጋው ከእርሱ ላይተወሰደ፣ ከገነትም ተባረረ፣ ሞትን እየፈራ ኖረ። ከጌታችን ከመድኀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን ሕይወት ለማግኘት ስንል ከሕይወት ዛፍ ይልቅ ሥጋውን እንበላ ዘንድ ተሰጠን፤ በገነት አጸድ ሥፍራ ምትክመስቀሉን ሰጠን፤ ንጹሕ በሆነው ደሙ ርግማናችን ታጠበ፤ ትንሣኤን ተስፋ አድረገን የሚመጣውን ሕይወት እንጠባበቃለን፡፡ በአጠቃላይ አሁን በአዲስ ሕይወት እየተመላለስን ነው፤ ለዚህ መስቀሉና የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም እንደ ማኅተም ሆኖልናል። ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ©️ #ትንሳኤ @St_Ephrem_Syrian @St_Ephrem_Group
«ሁሉን የፈጠረው ጌታ ዛሬ በቀያፋ ቤት እንደ ክፉ ወንጀለኛ እየተመረመረ ነው። ከባርያዎቹ አንዱም በጥፊ መታው። ጌታ ቆሞ ባርያው ሊፈርድበት ተቀመጠ፤ በክፋት የተሞላው ቁጭ ብሎ በንጹሑ ላይ ፈረደበት! እነዚህን ባሰብሁኝ ጊዜ ልቤ በፍርሐት ይንቀጠቀጣል፤ ሰማያትም ይንቀጠቀጣሉ፤ የምድርም መሠረት ይነዋወጻል። መላእክትና ሊቃነ መላእክት በፍርሐት ይጨነቃሉ። ሚካኤልና ገብርኤል ፊታቸውን ይሸፍናሉ! ባርያ ጌታውን በጽፊ ሲመታው ባዩ ጊዜ ኪሩቤል ከዙፋኑ ሥር ይሸሸጋሉ፤ ሱራፌልም ክንፎቻቸውን ያማታሉ!» ቅዱስ ኤፍሬም ©️ #ሕማማት @St_Ephrem_Syrian @St_Ephrem_group
✞ መድኃኔ ዓለም ✞ ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ «አብርሃም አባታችን ብዙ አገልጋዮች ነበሩት። ስለምን እግዚአብሔር ከእነዚህ ከአገልጋዮቹ አንዱን እንዲሠዋለት አልጠየቀውም? ምክንያቱም አብርሃም ለእግዚአብሔር ያለው ፍቅር በባሪያው በኩል ስለማይገለጥ ነው። ስለዚህም አብርሃም ለእግዚአብሔር ያለው ፍቅር እንዲገለጥ ልጁን እንዲሠዋ ጠየቀው። እንዲሁ እግዚአብሔር በአንዱ አገልጋዩ በኩል ለሰው ልጅ ያለውን ፍቅር ሊገልጥ አልፈለገም፡፡ ነገር ግን በልጁ ለእኛ ያለውን ፍቅር ገለጠልን፡፡ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” (ዮሐ 3፥16) ተብሎ እንደተጻፈልን፡፡ » ቅዱስ ኤፍሬም ©️ #ወንጌል_ዘዮሐንስ #ሕማማት @St_Ephrem_Syrian @St_Ephrem_Group
_ 💫ጥበብ💫 _ ጥበብ ባለጠጋን ሰው በባለጠግነት ከሚመጡ ሐዘናት ትጠብቀዋለች። ድሃን መሠረታዊ ነገሮችን ማጣቱ ከሚያመጠበት ሐዘን ታጽናናዋለች። ለአረጋዊው ብርታትን ትሰጠዋለች፤ ሕፃናትን ጥበበኞች ታደርጋለች፤ ታዳጊዎችን ንጽሕናቸውን እንዲጠብቁ ታጸናቸዋለች። የመከራ ማዕበላት ምንም ያህል ቢጸኑ በትንሽ እንጨት ማዳን ታውቅበታለች። በእርግጥ በሁሉ ነገር ላይ ድልን መቀዳጀት ታላቅ ጸጋ ነው። ጥበብም ለዚህ ታበቃለች እርሷም ማስተዋል ናት፡፡ ©️ ✎ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ *ጥበብ ምንድር ነው?👇👇 @St_Ephrem_Syrian @St_Ephrem_Group
●▬▬▬▬▬▬▬๑✟✟✟๑▬▬▬▬▬▬▬▬● 💔የተረሳው መጻጕዕ🤕👨🦽🛌 🛏🛏🛏🛏🛏🛏🛏🛏🛏🛏🛏🛏🛏🛏🛏🛏🛏 እነሆም፥ በአልጋ የተኛ ሽባ ወደ እርሱ አመጡ፡፡ ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባው አንተ ልጅ፥ አይዞህ፥ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ አለው።” የአንዳችን እምነት ለሌላው ወዳጃችን ምን እንደሚሠራ ተመለከታችሁን? ጌታችን የሽባውን እምነት አልተመለከተም። ይህ ሰው በመፍረስ ላይ ያለን ሕንጻ ይመስላል፥ ከልጁ ሳይሆን ከአባቱ እምነት እንደጠበቀ ሰው(ሉቃ 9፥38 ማር 9፥23) ጌታችንም እምነትን ከዚህ ሰው አልጠበቀም ነበር። እንዲሁም ጌታችን “አዎን ጌታ ሆይ! ቡችሎችም እኮ ከጌቶቻቸው ማዕድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ”(ማቴ 15፥27) እንዳለችው እናት እምነትን ከእርሷ እንጂ ከዚያች ታናሽ ብላቴና አልጠበቀም ነበር። ስለዚህ በእምነታችን እንጽና ይህ ለእኛ የምንቀደስበት ነው፡፡ እንደዚህ ሽባ ሰው እኛ በኃጢአት ሽባ የሆንን አይደለንም፡፡ በሁሉ ላይ የሰለጠነው ቃል ይህን ሽባ አጸናው፣ አነጻው ፈወሰው፡፡ በስውር ከነበረው ኃጢአቱ አነፃው በሥጋው በግልጥ ከሚታየው ሕመሙም ፈወሰው፡፡ ጌታችንም በኅቡዕ ያለውን ማንነቱን በሚታየው አካሉ በኩል የምናየው ጌታ ነው። እርሱ በማይታየው ባሕርዩ እግዚአብሔር ነው በሚታየው ሰውነቱ ደግሞ ሰው ነው። እርሱ በሚታየው ሰውነቱ የሰው ልጅ መሆኑን ስናረጋግጥ በኅቡዕ ባለው ባሕርዩ ደግሞ እርሱ ኃያል አምላክ መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡ “እነሆም፥ በአልጋ የተኛ ሽባ ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን፤ አንተ ልጅ፥ አይዞህ፥ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ አለው።”(ማቴ 9፥2) በዙሪያው ያለው ሕዝብ ግን ኃጢአትህ ተሰረየችልህ ማለት ማንም ይለው ዘንድ ቀላል ነው። ነገርግን ከሕመሙ ቢፈውሰው ግን ድንቅ ይባልለታል በማለት በጌታችን ላይ ተቀጣጠቡ። የእነርሱን ሐሳብ ሲረዳ “ኢየሱስም አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አለ፦ ስለ ምን በልባችሁ ክፉ ታስባላችሁ?” አላቸው፡፡ ጌታችን ይህን ልጅ፡- “አይዞህ፥ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ አለው” የትኞቹ ኃጢአቶቹ ናቸው የተሰረዩለት? በክርስቶስ ፊት የፈጸማቸው ኃጢአቶቹ ናቸው። እንዴት ታዲያ ጌታችን የሕጉ ተቃዋሚ ሊሆን ይችላል? ስለምን በጌታችን ሥራ ይደነቃሉ? እርሱም ሆነ አባቱ ሕዝቡ የማይቀበለውን፣ ተፈጥሮን ወይም ሕግን የሚቃረን ተግባርን ፈጸሙን? ነገር ግን መርቅያውያን ትክክል ከሆኑ ኃጢአትን የሚፈጽም ሰው እግዚአብሔርን የሚበድል ከሆነና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሕጉ ባለቤት (ከእግዚአብሔር አብ) ጋር ምንም ዓይነት ሕብረት ከሌለው ኃጢአትን እንዴት ይቅር ማለት ቻለ? ይህ በራሱ እርሱ የሕጉ ባለቤት ልጅ ስለመሆኑ ማረጋገጫ አይሆንልንምን? ምክንያቱም ሽባው ኃጢአትን በሥጋው ፈጽሞ ስለተገኘ በሥጋው ተቀጣ፡፡ ይህ ለመርቅያውያን የሚሠራ የጌታ ትምህርት ነው፡፡ ወይስ ሽባ የሆነው ሰው በእርሱ ፊት ኃጢአት ካልፈጸመ እንዴት ኃጢአትህ ተሰረየልህ ይለዋል? ወይም ኃጢአትን ሳይፈጽም ኃጢአትህ ተሰረየችልህ መባሉ ምን ጥቅም አለው? እነርሱ (ልጅና አባት) የኃጢአት ሥርየትን የማድረግ ሥልጣን ባይኖራቸው ኖሮ እርሱን ሽባ የማድረግም ሥልጣን ባልነበራቸው ነበር። ነገር ግን ጌታችን ከርኅራኄው የተነሣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይህን ሰው ኃጢአቱ ካመጣበት ደዌ ፈወሰው። ©️ ✎ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ትክክለኛውን የቅዱስ ኤፍሬምን ቤት ይቀላቀሉ ♡ ለወዳጆችዎም ያጋሩ ⌲ @St_Ephrem_Syrian @St_Ephrem_Group
ተግሳጽ ዘቅዱስ ኤፍሬም ━━━━━━━━━━━━━━━━ የትኛውንም ኃጢአት በፈጸምኽ ቁጥር በስውር ጣዖትን እያመለክ እንደሆነ እወቅ ፡፡ መተላለፍንም በወደድክ ቁጥር በነፍስህ አጋንንትን እያገለገልኽ መሆንህን ተረዳ፡፡ በወንድምህ ላይ በጠብ በተነሣሣህ ቁጥር ደግሞ ሰይጣን በእርጋታ እንዲቀመጥ እየረዳኸው ነው፡፡ ባልንጀራህ ላይ በቀናህ ቁጥር ለዲያብሎስ ሰላምን ሰጠኸው፡፡ አጠገብህ ስለሌለው ሰው ድክመት በተናገርክ ቁጥር፣ ሰይጣን ይዘፍንበት ዘንድ ምላስህን በገና አድርገህ እንደሰጠህ ይቆጠራል ጥላቻ በልቡናህ ነግሦ ከሆነ የዲያብሎስ እርዳታ እጅግ ታላቅ ይሆናል፡፡ ደስ የማያሰኝ ከንቱ የሆነ ንግግርን የምትወድ ከሆነ ለአጋንንት ድግስ እየደገስክላቸው መሆኑን ተረዳ። ስለዚህም ነው የሥጋ ሥራዎች መፈጸም ጣዖትን እንደማምለክ ነው መባሉ፡፡ ምጽዋትን ስታደርግ በትዕቢት ተሞልተህ ከሆነ ምጽዋትህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንዳማይደርስ ታወቀ፡፡ በራስህ እውቀት ታምነህ ራስህን ከፍ ከፍ ያደረግኽ ከሆነ የእግዚአብሔርን ጸጋ እየካድኽ ነው፡፡ ድሃ ሆነህ ትዕቢተኛ ከሆንኽ ፍጻሜህ እሳት ነውና ወዮልህ! ትዕቢተኛና ደሃ ከሆንኽ ፈቃድህ ሁሉ ወደ ጥፋት ይመራሃልና ወዮልህ፡፡ ሕመምተኛ ሆነህ ተሳዳቢ ከሆንኽ፣ መከራህ ሁሉ በጥፋት የተሞላ ነውና ወዮልህ፡፡ የምትበላው ሳይኖርህ ነገርግን ሕሊናህ ብልጽግናን የሚመኝ ከሆነ ስቃይህ እንደ ድሃ፥ ቅጣትህ ግን እንደ ባለጠጎች ይሆንብሃለና ወዮልህ። ©️ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ #ዐቢይ_ጾም #ጾም @St_Ephrem_Syrian @St_Ephrem_group
ድንግልን ለምን ኪዳነ ምሕረት እንላታለን? ክብር ለእርሱ ለወደደን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይሁንና ብዙዎች ድንግል እናቱን ኪዳነ ምሕረት ስንላት ግራ ሲጋቡ እናስተውላለን። በእርግጥም ግራ ቢጋቡ አይደንቅም፤ ምክንያቱም ይህን መረዳት መጽሐፍ ቅዱስን ጠንቅቆ ማወቅና የመንፈስ ቅዱስን ድጋፍ ይፈልጋልና። ጌታችን ራሱን መሥዋዕት አድርጎ በመስቀል ላይ ከማቅረቡ አስቀድሞ በብሉይ ኪዳን የቃል ኪዳኑ ታቦት ላይኛው ክፍል “የሥርየት መክደኛ/የምሕረት ዙፋን” ከሚባለው አንጻር ከነሐስ በተሠራ መሠዊያ ላይ መሥዋዕት ይቀርብ ነበር።(ዘጸ 25፥17) በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ቃል ኪዳን ያደረገው በዚሁ በታቦቱ ራስ በሥርየት መክደኛው ላይ በደመና ዓምድ በመገለጥ ነበር። ከሙሴ ጋር የተነጋገረውና ከካህናቱም እጅ መሥዋዕቱን ይቀበል የነበረው በዚህ ሥርየት መክደኛ ላይ በመገለጥ ነበር፡፡ ይህ መገለጥ ግን ከሰዎች ልጆች ጋር ፍጹም እርቅ መፈጸሙን የሚያሳይ አልነበረም። ነገር ግን በእርሱ በክርስቶስ የሚፈጸመውን ማዳን በምሳሌ የሚያሳይ ነበር። እግዚአብሔር ለአባታቸው ለአብርሃም የገባውን ቃል ኪዳንም እንደማያጥፍ ማሳያም ነበር፡፡ ምሳሌውም እውን የሆነውና በሰውና በእግዚአብሔር መካከል እርቅ የወረደው የእግዚአብሔር ቃል ድንግል እናቱን የቃል ኪዳን ታቦት በማድረግ ከእርሷ ሥጋና ነፍስን ነሥቶ ሰው ከሆነ በኋላ ነበር። ያኔ በሰውና በእግዚአብሔር፣ በሰውና በቅዱሳን መላእክት፣ በሰውና በሰው መካከል የነበረው የጠብ ግድግዳ ፈረሰ፡፡ 🏘የቅዱስ ኤፍሬምን ቻናል ይቀላቀሉ 🏘 #ድንግል_ማርያም❤️ @St_Ephrem_Syrian @St_Ephrem_Group
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✞ ጥር ፲፰ በዚኽች ቀን የሰማዕታት አለቃ የቅዱስ ጊዮርጊስ ዐጽሙ ተቃጥሎ ተደቁሶ የተበተነበት (ውዕየተ ዐጽሙ፣ ዝርወተ ዐጽሙ) ነው። ዳግመኛም በዚኽች ቀን በገድል የተጠመደ የከበረ አባት፥ ይኸውም ለቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ መምህሩ የሆነ የንጽቢን ሊቀጳጳሳት ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን ዐረፈ። ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ምንም እንኳ ወደበረሃ እየወረደ…
በእንተ ልደቱ ለእግዚእነ “ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኰከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።"ማቴ ፪፥፩ ኰከብ ቆጣሪዎች ሆይ! ታስተውላላችሁን? እናንተ ኰከቡ የጌታን ልደት ገለጠ ብላችሁ የምትመኩ ናችሁና፡፡ ነገር ግን እንደ ንግግራቸው ኰከቡ የጌታን ልደት…
«ነፍስ ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናል» መዝ 150፥6 ━━━━━━━━━━━━━━━━ በአንደበታችን ቃልህን በማኖር በፊትህ ልመናችንን ለማቅረብ ስላበቃኸን ጌታችን ሆይ! እናመሰግንሃለን፡፡ አዳም የአንተን መልክና ምሳሌ ስለያዘ ሰላምህን ስለሰጠኸው በዚህም ምክንያት ሁሉም ከጸጋህ ተካፋዮች ስለሆኑ ያመሰግኑሃል። ነፋሳት ውኃውን በማነዋወጥ ያመሰግኑሃል፡፡ ምድር የአንተ ቸርነት ስላልተቋረጠባት ዕጸዋት በወቅታቸው ፍሬ እንዲሰጡ ሆነዋልና ታመሰግንሃለች፡፡ ባሕር በመነዋወጥ ለአንተ ትዘምራለች፤ በአንደበት እንደሚነገር ቃል ማዕበላት እርስ በእርስ እየተማቱ ለጌትነትህ አዋጅ ነጋሪዎች ሆነዋል። ዛፎች ነፋስ ነፍሶ ባወዛወዛቸው ቍጥር እያሸበሸቡ አንተን ያመሰግናሉ። በዚህም ምክንያት ዕፅዋት በአበቦቻቸው ያለውን ዘራቸውን አንዱን ወደሌላው አበባ በመውሰድ እንዲዳቀሉ በማድረግ ዘርን እንዲሰጡ ታደርጋቸዋለህ። የምድር ሳር በየዝርያቸው አበቦቻቸውም በየቀለማቸው በዝናብህ ስለምታረሰርሳቸውና በጠልህ ስለምታረካቸው ያመሰግኑሃል። ፍጥረት ሁሉ በአንድነት አንድ በመሆን ብልህ ሐናጺ እንደሠራው ሕንጻ ያንተ የሆነውን ምስጋናቸውን ያቀርባሉ። ስለዚህ በሙሉ ፈቃዳችን ከአንተ ጋር ሆነን ለጽድቅ መድከም የእኛ ተግባር ሆኖአል። አንተም ከበዛው ጸጋህ ጥቂቱን ታድለን ዘንድ ፈቃድህ ይሁን። እኛን ከኃጢአት ምልልስ በምታወጣን በአንተ በጌታችን እውነትን ገንዘብ ልናድርግ እንችላለን፡፡ አንተም ኃጢአታችንን ልታርቅልንና ልታጠፋልን ትችላለህ። ጌታችን ሆይ! አንተ ለሚያስፈልጉን ጸጋዎች ሁሉ ጌታ ነህና ከአንተ ጸጋ በቀር ወደ አንተ ከቶ ልንቀርብ አይቻለንም፡፡ መዝሙር ዘቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ©️ ተቀላቀሉ🏘ለወዳጆቻችሁም አካፍሉና ቤተሰብ እንሁን⌲❤️ @St_Ephrem_Syrian @St_Ephrem_group
ድንግል ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ግብር መጽነሷን ለዮሴፍ ለማስረዳት አሰበች። ነገርግን በእርሷ የተፈጸመው ከመረዳት በላይ ስለሆነ እርሷን እንደማይቀበላት ተረዳች። ምንም እንኳ የድንግል ሆዷ ቢገፋም በእርሷ ገጽታ ላይ የሚነበበውን ፍጹም የሆነ እርጋታና ሰላም ዮሴፍ ባየ ጊዜ “ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ።” ነገር ግን ከሌላ ጸንሳ ይሆናል የሚል ሐሳብም በሕሊናው ስለገባ እርሷን እንደ እጮኛው አድርጎ ሊቀበላት አመነታ። እንደ ጻድቅነቱ ወደርሱ ሊመውሰዳት አልፈቀደም፤ እርሱዋንም ለሌሎች አጋልጦ ሊሰጣትም አልወደደም። በዚህ ግራ መጋባት ውስጥ ሳለ መልአኩ በሕልም ተገልጦ “የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ!”(ማቴ 1፥20) ብሎ ጠራው። ዮሴፍ ከዳዊት ወገን እንደሆነ ለማስታወስ ሲል መልአኩ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ! ብሎ መጥራቱ የተገባ ነበር። ምክንያቱም ለአያቶቹ ራስ ለሆነው ዳዊት እግዚአብሔር ከወገቡ መሢሕን እንደሚያስነሣለት ቃል ኪዳን ገብቶለት ነበርና፡፡ ስለዚህም መልአኩ “ከእርሷ የተጸነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ለመውሰድ አትፍራ” አለው። ከእርሷ የተጸነሰው ከመንፈስ ቅዱስ መሆኑን ተጠራጥረህ ከሆነ ኢሳይያስ ስለ እርሷ የተናገረውን ስማ እርሱ፡- “እነሆ ድንግል ትጸንሳለች”(ኢሳ 7፥14 ማቴ 1፥22) ብሎ አስቀድሞ ተናግሮአል፡፡ ዳንኤል ደግሞ “እጅ ሳይነካው የተፈነቀለው ድንጋይ”(ዳን 2፥34-45) ብሎ በምሳሌ መስሎ ተናግሮለታል፡፡ የዚህ ቃል ትርጕም፡- “ከእርሱ የተቆረጣችሁበትን ድንጋይ ከእርሱም የተቆፈራችሁበት ጉድጓድ ተመልከቱ”(ኢሳ 51፥1)ከሚለው ጋር አንድ አይደለም፡፡ ይህ ለባልና ለሚስት ተሰጥቶ የሚተረጎም ነውና፡፡ በዳንኤል የተነገረው ግን “እጅ ሳይነካው የተፈነቀለ ድንጋይ” ድንግል ማርያም ያለ ወንድ ዘር ጌታን መጽነሷን የሚያረገግጥ ነው። የቀድሞው አዳም ለሔዋን የአባትነትንና የእናትነትን ድርሻ ተወጣ፤ ድንግል ማርያም ደግሞ ለጌታ የእናትነትንና የአባትነትን ድርሻ ተወጣች፡፡ አንድም ወንጌላዊው፡- “እጮኛዋ ዮሴፍም ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ” ሲል የዮሴፍ ጽድቅ ከኦሪቱ ሕግ ጋር ተቃራኒ መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ ሕጉ በስውር እንዲተዋት ሳይሆን ወደ ውጪ አውጥቶ በድንጋይ እንዲወግሯት ሊተዋት እንዲገባ የሚያዝዝ ነው። ቢሆንም ዮሴፍ የድንግል መጽነስ ያልተለመደ፣ ተፈጥሮዊ ከሆነውም ከሴቶች ሥርዓት የተለየ፣ ካገቡትም ሴቶች የማይመሳሰል እንደሆነ አስተዋለ፤ ወዲያውም ይህ ነገር ከእግዚአብሔር እንደሆነ ተረዳ፡፡ እርሱም አንድም ጊዜ በእርሷ ላይ ነውር አይቶባት አያውቅም። በእርግጥ እርሷ እንዲህ እንዳልሆነች ብዙ ብዙ ምስክሮች አሉና ዮሴፍ ድንግል ማርያምን በምንዝር ይጠረጥራት ዘንድ አንዳች ምክንያት አልነበረውም። የካህኑ ዘካርያስ ድዳ መሆን፣ የኤልሳቤጥ በእርጅና መጽነስ፣ የመልአኩ የምሥራች ቃል፣ በማኅፀን ሳለ የዮሐንስ በደስታ መዝለል፣ የካህኑ ዘካርያስ የትንቢት ቃል ሁሉ ስለድንግል ማርያም በድንግልና መጽነስ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይመሰክራሉ፡፡ ©️ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ #ወንጌል_ዘማቴዎስ@St_Ephrem_Syrian @St_Ephrem_Syrian @St_Ephrem_Group
በእንተ በዓታ ለእግዝእትነ ቅድስት ድንግል በክልዔ ማርያም ወላዲተ አምላክ ውስተ ቤተ መቅደስ ━━━━━━━━━━━━━━━━━ «የእግዚአብሔር ዔደን ገነት ድንግል ማርያም ናት። በእርሷ ውስጥ የሚጐዳው እባብ የለም፥ የሕይወት ዛፍ ይበቅልባታል እንጂ፥ ይኸውም ግዞተኞቹን ነጻ የሚያወጣው ነው። እነሆ ዛሬ በዚኽች ዕለት በዛሬው በዓል የነቢያት ትንቢት ፍጻሜ የሆነችው፣ እርስዋ ራስዋ ማንም በውስጥዋ ሊገባባት የማይችልና የሰው እጅ ያልተጠበበባት መቅደስ ስትሆን፥ የሰው እጆች ወደ ተጠበቡበት የቤተ መቅደስ ደረጃዎች በእግሮቿ ስትወጣ ታናሺቱን ብላቴና ድንግል ማርያምን ተመለከትናት።» ©️ቅዱስ ኤፍሬም @St_Ephrem_Syrian @St_Ephrem_group
መድኃኔ ዓለም ━━━━━━━━━━━━━━━━ «ሙታን ሕያው የሆነውን መግደላቸው የሚደንቅ ነው፥ ሆኖም በፈቃዱ የሞተው እርሱ ለሙታን በሞቱ ሕይወትን ሰጣቸው። ቁጣቸውን እስከ ሰማይ ድረስ ከፍ ከፍ አደረጉ፤ እርሱ ግን በምድር ልብ እስከመውረድ ደርሶ ትሕትናውን አሳያቸው። የሞተውን ጌታ በመቃብር ያኖረው ሞት በጌታችን ድል ተነሥቶ የሞትን ምርኮ ን በዘበዘ። ጌታችን አንቀላፍቶ ሳለ ሞት ሰርቆ ከመቃብር አኖረው፥ ነገር ግን ከእንቅልፉ በመነቃ ጊዜ በሞት የተማረኩትን ከሞት እጅ ነጥቆ አዳናቸው። ለምርኮ ተላልፈው ሊሰጡ የሚገባቸው በእነርሱ ተላልፎ የተሰጠ እርሱ ነው፡፡ ጌታችን ሆይ! በአንተ ምክንያት መስቀል ለሙታን የሕይወት መገኛ ምንጭ ሆነ! ከእርሱ የሕይወትን ውኃ የሚጠጡ ከእርሱ እንደተገኘው የሕይወት ውኃ ሕይወትን አፈሩ። ሞት ሳያውቀውና ሳይረዳው በጌታችን ሰውነት በኅቡዕ ያለውን ሕይወት ተስገብግቦ ዋጠው፡፡ ራቡ ጸንቶበት ከራቡ ፈጥኖ ለመውጣት ሲል ፈጥኖ ዋጠው፡፡ ሞት በሔዋን ጆሮ በኩል ወደ ዓለም ገባ፥ ሕይወትም በድንግል ማርያም ጆሮ በኩል ወደ ዓለም ገባ። የሰው ልጅ በእንጨት ምክንያት ባለዕዳ ሆኖ ነበር፥ በእንጨት ምክንያት ከዕዳ ነፃ ወጣ፡፡» ©️ኤፍሬም ሶርያዊ (Commentary on Diatessaron) “መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በቀራንዮ ስቁል በለኒ መሐርኩከ በእንተ ማርያም ድንግል እስመ ኄር አልቦ እንበሌከ ቃል🤲” share⌲ join🈴 @St_Ephrem_Syrian @St_Ephrem_group
በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል ━━━━━━━━━━━━━━ ስምዖን ቅድስት ድንግል ማርያምን፡- “በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል” (ሉቃ 2፥35)አላት። ይህ ሰይፍ ክርስቶስ ስለሚቀበለው መከራና በእርሱ ምክንያት የድንግልን ሰቆቃ የሚያስረዳ ነው። ሰይፍ በሔዋን ምክንያት ወደ ገነት ከመግባት ከልክሎን ነበር፤ በድንግል ማርያም ግን በእኛ ላይ የተመዘዘው ሰይፍ ተወገደልን፡፡ ግሪካውያን “በልብ በቁጥር የበዛው ሐሳብ መገለጡ አይቀርም” ይላሉ፡፡ እንዲሁ በልባቸው ጥርጣሬ የነገሠባቸው ሰዎች ምንፍቅናቸው መገለጡ አልቀርም። ስለ ድንግል ማርያምም “በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል” ተባለላት። መግደላዊት ማርያም ክርስቶስ ማን እንደሆነ ስላልተረዳችው የአትክልት ጠባቂው መስሏት ነበር፡፡ ድንግል ማርያም ደግሞ እርሱን የምወልደው እንዴት ነው ብላ ተጨንቃ ነበር፡፡ ጌታን እንዴት እንደጸነሰችውም ለሌሎች ስትናገር የሚሰሟት ሁሉ በንግግሩዋ ይደነቁና ይገረሙ ነበር፡፡ ©️ቅዱስ ኤፍሬም በዲያቴሳሮን እንደተረጐመው ይቀላቀሉ🈴 ያጋሩ⌲ የቅዱሱ ወዳጅ ይሁኑ❤️ #ወንጌል_ዘሉቃስ @St_Ephrem_Syrian @St_Ephrem_group
🐬 ዓሣ ማጥመድ🐠 «ስምዖን ለጌታ “አቤቱ ሌሊቱን ሁሉ አድረን ስንደክም ምንም አልያዝንም😔”(ሉቃ 5፥5) ብሎ ተናገረ። ይኽም ምሳሌው ለነቢያት ነው። የእርሱ ትምህርት ከላይ ከሰማይ ወደዚኽ ምድር በመምጣት በባህር ላይ በምሳሌ ቆመ። ሁለቱ ጀልባዎች በግዙራንና በኢ-ግዙራን ይመሰላሉ። ሐዋርያት በሌላ ጀልባ የነበሩ ወዳጆቻቸው መጥተው እንዲአግዙአቸው መጥቀሳቸው ምሳሌነቱ ለሰባሁለቱ አርድእት ሲሆን መከሩ ብዙኅ ስለሆኾነ ሠራተኛዎቹ ሐዋርያት ጥቂቶች ስለኾኑ የተጠሩ ናቸው።» ቅዱስ ኤፍሬም ©️ #ወንጌል_ዘሉቃስ @St_Ephrem_Syrian @St_Ephrem_group