tgindex
አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ Pope Shenouda III

አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ Pope Shenouda III

Статистика

ይኽ መንፈሳዊ ፅሁፎችን፣ መፅሐፍቶችንና ትምህርቶችን የምናጋራበት ቻናል ነው። ሊንኩን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ! የክርስቶስ ሰላም ይብዛላችሁ!

Последний пост
22 июл.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
32
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 643
0 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 669
32 постов
Вовлечённость
101,6%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 32
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
667
1/48двое суток
764
1/72трое суток
824

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 22 июл.7522131

    👉አንተ አልችልም ስትል ~ እግዚአብሔር በሰው ዘንድ የማይቻል በኔ ዘንድ ይቻላል ይልሃል። “እርሱ ግን፦ በሰው ዘንድ የማይቻል በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል አለ።” ሉቃስ 18፥27 👉አንተ ደክሞኛል ስትል ~እግዚአብሔር አሳርፍሃለሁ ይልሃል። "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።" (ማቴ. 11 ፡28-30) 👉አንተ ማንም አይወደኝም ስትል ~ እግዚአብሔር እወድሃለሁ ይልሃል። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” (ዮሐንስ 3፥16) 👉አንተ አቅቶኛል መቀጠል አልችልም ስትል ~እግዚአብሔር ጸጋዬ ይበቃሃል ይልሃል። “እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ።” (2ኛ ቆሮ 12፥9) 👉አንተ መንገድ መለየት ከብዶኛል ስትል ~ እግዚአብሔር አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ ይልሃል።” "አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፤ ዓይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ።” (መዝሙር 32፥8) 👉አንተ ማድረግ አልችልም ስትል ~ እግዚአብሔር ኃይልን በምሰጥህ በእኔ ሁሉን ትችላለህ ይልሃል ። "ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። " (ፊልጵስዩስ 4፥13) 👉አንተ ብቃት የለኝም ስትል ~ እግዚአብሔር ብቃት አለህ ይልሃል። “በተነ፥ ለምስኪኖች ሰጠ፥ ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔር፥ ሁልጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ፥ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።” (2ኛ ቆሮ 9፥8-9) 👉አንተ ይህ ለኔ አይገባኝም ነበር፣ ለምን እኔ ላይ ሆነ ስትል ~ እግዚአብሔር ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ይልሃል። “እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።” (ሮሜ 8፥28) 👉አንተ ራሴን ይቅር ማለት አልችልም ስትል ~ እግዚአብሔር ይቅር እልሃለሁ ይልሃል። “በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።” (1ኛ ዮሐንስ 1፥9) 👉አንተ ኑሮ ከብዶኛል ስትል ~እግዚአብሔር የሚያስፈልግህን ሁሉ እሞላልሃለሁ ይልሃል ። “አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል።” (ፊልጵስዩስ 4፥19) 👉አንተ ፈርቻለሁ ስትል ~ እግዚአብሔር የፍርሃት መንፈስ አልሰጠሁህም ይልሃል። “እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና።” (2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥7) 👉አንተ እጨነቃለሁ ስትል ~ እግዚአብሔር የሚያስጨንቅህን ሁሉ በኔ ላይ ጣል ይልሃል። “እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።” 1ኛ ጴጥሮስ 5፥7 👉አንተ ብልሃት የለኝም ስትል ~እግዚአብሔር ጥበብን እሰጥሃለሁ ይልሃል። “ነገር ግን፦ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው።”1ኛ ቆሮንቶስ 1፥30-31 👉አንተ ማንም የለኝም ብቻዬን ነኝ ስትል ~ እግዚአብሔር አለቅህም ከቶም አልተውህም ይልሃል። “ አልለቅህም ከቶም አልተውህም።" (ዕብ. 13፥5)         #እግዚአብሔር_ይክበር_ይመስገን!

  • 31 мая1 1212010

    "ኢየሱስም እንዲህ አለ፦ “..ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራምም።" የዮሐንስ ወንጌል ምእራፍ - 14 1: ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። 2: በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤ 3: ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ። 4: ወደምሄድበትም ታውቃላችሁ፥ መንገዱንም ታውቃላችሁ። 5: ቶማስም፦ “ጌታ ሆይ፥ ወደምትሄድበት አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን እናውቃለን?” አለው። 6: ኢየሱስም አለው፦ “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። 7: እኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር። ከአሁንም ጀምራችሁ ታውቁታላችሁ አይታችሁትማል።” 8: ፊልጶስ፦ “ጌታ ሆይ፥ አብን አሳየንና ይበቃናል፡” አለው። 9: ኢየሱስም አለው፦ “አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ፦ ‘አብን አሳየን፡’ ትላለህ? 10: እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም፤ ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል። 11: እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ ስለ ራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ። 12: እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል፥ 13: እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ። 14: ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።” 15-16: “ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ* ይሰጣችኋል፤ (* አጽናኝ ማለት በግሪክ ቋንቋ ጰራቅሊጦስ ማለት ነው) 17: እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ። 18: ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። 19: ገና ጥቂት ዘመን አለ ከዚህም በኋላ ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና እናንተ ደግሞ ሕያዋን ትሆናላችሁ። 20: እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ። 21: ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ።” 22: የአስቆሮቱ ያይደለ ይሁዳ፦ “ጌታ ሆይ፥ ለዓለም ሳይሆን ራስህን ለእኛ ልትገልጥ ያለህ እንዴት ነው?” አለው። 23: ኢየሱስም መለሰ፡ አለውም፦ “የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል፡ ወደ እርሱም እንመጣለን፡ በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን። 24: የማይወደኝ ቃሌን አይጠብቅም፤ የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም። 25: ከእናንተ ዘንድ ስኖር ይህን ነግሬአችኋለሁ፤ 26: አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል። 27: ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም። 28: እኔ እሄዳለሁ ወደ እናንተም እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ። የምትወዱኝስ ብትሆኑ ከእኔ አብ ይበልጣልና ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር። 29: ከሆነም በኋላ ታምኑ ዘንድ አሁን አስቀድሞ ሳይሆን፥ ነግሬአችኋለሁ። 30: ከእንግዲህ ወዲህ ከእናንተ ጋር ብዙ አልናገርም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ይመጣልና፤ በእኔ ላይም አንዳች የለውም፤ 31: ነገር ግን አብን እንድወድ ዓለም ሊያውቅ፥ አብም እንዳዘዘኝ፥ እንዲሁ አደርጋለሁ። ተነሡ፤ ከዚህ እንሂድ።”

  • 21 мая1 349814

    #ዕርገት #በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ የዛሬው በዓል ምን ይደንቅ! እነሆ ነገደ መላእክት ኹሉ ሲዘምሩ፣ አንዳንዶቹ ከኋላው ተከትለዉት፣ አንዳንዶቹ ከፊቱ ቀድመዉት፣ አንዳንዶቹ በዙሪያው ከብበዉት፣ ሌሎቹ ከሐዋርያት ጋር ኾነው፡- “እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ! ወደ ሰማይ እያያችሁ ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል” ሲሏቸው እናያቸዋለንና፡፡ ብዙ ድንቅ ምልክቶችን ያደረገው ይህ ኢየሱስ ነው፡፡ በዚህ የጌታችን በዓል፣ በዚህ በዕለተ ዕርገት ቀድመን እንደ ተናገርን ዲያብሎስ አለቀሰ (አዘነ)፤ ምእመናን ግን ተድላ ደስታ አደረጉ፡፡ እነሆ አሁን ደስ የሚያሰኘው ምንጭ ፈለቀ፤ እነሆ አሁን አበቦች ፈኩ፡፡ የወይን ቅርንጫፎች ደረሱ፤ የወይራ ዛፎችም ጥዑም መዓዛቸውን ሰጡ፡፡ በለሶችም እሸት ፍሬያቸውን ለገሱ፡፡ ነፋሱም ሐመልማላትን እንደ ባሕር ጨዋታ እያወዛወዘ ነፈሰ፡፡ ኹሉም ከእኛ ጋራ በጌታችን ዕርገት ተድላ ደስታ አደረጉ፡፡ ስለዚህ፡- “አሕዛብ ኹላችሁ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፤ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር ዕልል በሉ፡፡ እግዚአብሔር በዕልልታ፣ ጌታችንም በመለከት ድምፅ ዓረገ” እያልን ወደ ላይ ወደ ሰማያት ላረገው ለጌታችን እንዘምር ዘንድ ከእኛ ጋር የክቡር ዳዊትን ቃለ መዝሙር አምጡ፡፡     እነሆ ጌታችን ወደ ሰማያት ዓረገ፤ ነገር ግን ከእኛ አልተለየም፡፡ የወደቀውን አዳም ያነሣው ዘንድ የወረደው እርሱ እነሆ ዛሬ ከሰማየ ሰማያት በላይ ዓረገ፡፡ 👉ነቢያት በትንቢት መነጽር ያዩት እርሱን እንጂ ሌላ አይደለም፤ 👉ሐዋርያትም የበሉት ከእርሱ ጋር እንጂ ከሌላ ጋር አይደለም፡፡ 👉በአባቱ ዕቅፍ የነበረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ 👉በጲላጦስ የተፈረደበትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም። 👉በመስቀል ላይ በሚስማር የተቸነከረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ 👉በዘባነ ኪሩብ ላይ የነበረውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ 👉ጻድቁ ዮሴፍ በጨርቅ የጠቀለለው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ 👉በእጁ መዳፍ ፍጥረታትን የያዘውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ 👉በመቃብር ያደረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ 👉ሱራፌል ያመሰገኑትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም። 👉በአባቱ ቀኝ የተቀመጠው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ 👉ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ነስቶ ሰው የኾነውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ #እግዚአብሔር_በዕልልታ_ዓረገ፡፡ #አምላክ_በመለከት_ድምፅ_ዓረገ፡፡ #ከዘለዓለም አንሥቶ ፈጣሪ የኾነው፣ #ኹሉንም ነገር ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጣው፣ አዳምን የሠራው፣ #የሰው ልጆችን የፈጠረው፣ #ደስ ያሰኘውን ሄኖክን ወደ ሕይወት ያሸጋገረው፣ ኖኅን ከዓለም ጋር  የጠበቀው፣ #አብርሃምን ከከለዳውያን ምድር የጠራው፣ #ይስሐቅን የነገረ መስቀል ምሥጢር ምልክት እንዲኾን ያደረገው፣ #ያዕቆብን የዐሥራ ኹለቱ አዕማድ ሥር እንዲኾን ያደረገው፣ #ለኢዮብ ትዕግሥትን የሰጠው፣ #ሙሴን የሕዝቡ መሪ እንዲኾን አድርጎ የሾመው፣ #ሳሙኤልን ከእናቱ ማኅፀን አንሥቶ በትንቢት የሞላው፣ #ከነቢያት መካከል ዳዊትን ንጉሥ አድርጎ የቀባው፣ #ለሰሎሞን ጥበብን የሰጠው፣ #ኤልያስን በእሳት ሰረገላ የወሰደው፣ #ነቢያት መጻእያትን እንዲያዩ ያደረጋቸው፣ #ለሐዋሪያት ሀብተ ፈውስን የሰጣቸው፥ “አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ” ብሎም አሰምቶ የነገራቸው #እርሱ ዛሬ በዕልልታና በመለከት ድምፅ #ዐረገ፡፡ #ወደ ሰማያት በዕልልታ ያረገው፣ #በአባቱም_ቀኝ_የተቀመጠው #የክብር_ጌታ ይህ ነው፡፡ #መላእክትና አለቆች ኃይላትም #ይገዙለታል፡፡ #ልመናችንን የሚቀበል፣ #ወደረኞቻችንን ድል እንድንነሣቸው ኃይልን የሚሰጠንም #እርሱ ነው፡፡ “እባቡን ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ እነሆ ሥልጣን ሰጠኋችሁ” እንዳለ በክፉ መናፍስት ኹሉ ሥልጣን ያለው እርሱ ነው፡፡ #ነውር ነቀፋ #የሌለብህ ንጹሃ ባሕርይ ሆይ! በነፍስ፣ በሥጋና በመንፈስ ጠብቀን፡፡ ይህን በዓል እናከብረው ዘንድ #የሰበሰብከን_የኹሉም_አምላክ የኾንህ #ጌታችን ሆይ ! በጽድቅ ፍሬ የተሞላን አድርገን፡፡ #ለአንተም ከባሕርይ አባትህ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወትህ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ክብር፣ ኃይልና ስግደት ኹሉ ዛሬም ዘወትርም እስከ ዘለዓለሙ ድረስ ይገባል፥ አሜን፡፡ 🙏🙏🙏 (ገብረ እግዚአብሔር ኪደ)

  • 17 мая1 027236

    ወንድሞች ሆይ ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፦ ፨አባቶቻችን ሁሉ ከደመና በታች ነበሩ፥ ፨ሁሉም በባህር መካከል ተሻገሩ፥ ፨ሁሉም ሙሴን ይተባበሩ ዘንድ በደመናና በባህር ተጠመቁ፨ ፨ሁሉም ያን መንፈሳዊ መብል በሉ፥ ፨ሁሉም ያን መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፣ ፨ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ አለት ጠጥተዋልና፥ ያም አለት ክርስቶስ ነበረ። 🙏 (1ኛ ቆረንቶስ ምዕ.10)

  • 30 апр.1 43724

    видео или голосовое, без подписи

  • 30 апр.1 430726

    видео или голосовое, без подписи

  • 19 февр.2 239399

    "አሁንስ፥ ይላል እግዚአብሔር፦ በፍጹም ልባችሁ፥ በጾምም፥ በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ። ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ፥ ቍጣው የዘገየ፥ ምሕረቱም የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ። የሚመለስና የሚጸጸት እንደ ሆነ፥ ለአምላካችሁም ለእግዚአብሔር የእህልና የመጠጥ ቍርባን የሚሆነውን በረከት የሚያተርፍ እንደ ሆነ ማን ያውቃል? ( ኢዮኤል 2÷ 12-14)

  • 25 янв.2 8622831

    የስጋ ስራም የተገለጠ ነው እርሱም :- 1.ዝሙት 2.ርኩሰት 3.መዳራት 4.ጣኦትን ማምለክ 5.ምዋርት 6.ጥል 7.ክርክር 8.ቅንአት 9.ቁጣ 10.አድመኝነት 11.መለያየት 12.መናፍቅነት 13.ምቀኝነት 14.መግደል 15.ስካር 16.ዘፍኝነት ይህንም የሚሠስል ነው። አስቀድሜ እንዳልሁ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርሱም። #የመንፈስ_ፍሬ ግን:- 1.ፍቅር 2.ደስታ 3.ሰላም 4.ትዕግሥት 5.ቸርነት 6.በጎነት 7.እምነት 8.የውሃት 9.ራስን መግዛት ነው። እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም። የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ። በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ። እርስ በርሳችን እየተነሣሣንና እየተቀናናን በከንቱ አንመካ። (ገላ.5÷19-26) ✝️✝️✝️ ...ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ:- #በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፥ #በበጎነትም እውቀትን፥ #በእውቀትም ራስን መግዛት፥ #ራስንም_በመግዛት መፅናትን፥ #በመፅናትም እግዚአብሔርን መምሰል፥ #እግዚአብሔርንም_በመምሰል የወንድማማችን መዋደድ፥ #በወንድማማችም_መዋደድ #ፍቅርን ጨምሩ። (2ኛ ጴጥሮስ) ... • ትጋትን • እምነታችሁ • በጎነት • እውቀትን • ራስን መግዛት • መፅናት • እግዚአብሔርን መምሰል • የወንድማማች መዋደድ • #ፍቅርን ጨምሩ።

  • 7 янв.2 3601710

    "በመመሳሰሉ ሳበን፣ ልዩ በመሆኑ ማረከን። መሪ እኛን ካልመሰለ መሪዬ ብሎ መቀበል ከባድ ነው፣ መሪ እኛን ከመሰለ ደግሞ ለምን መሪያችን ይሆናል? ከኛ ከልወጣ እኛን እንዴት ያውቀናል፣ ከኛ ከወጣ ደግሞ እኛን ከዚህ እንዴት ያወጣናል? አብሮን ካልበላ፣ አብሮን ካልጠጣ፣ አብሮን ካልተቸገረ፣ አብሮን ካልዘመረ፣ አብሮን ካልጸለየ የኛ ነገር እንዴት ይገባዋል ብለን እንመን? በሁሉ ነገር ከኛ ካልተለየ ከምንም ነገር እኛን ሊለየን አይችልም! የምናውቀው ነገር ብቻ ነው የሚስበን ፥ ልዩ የሆነ ነገር ብቻ ነው የሚማርከን። የምናውቀው ልዩ ካልሆነ፣ ልዩ የሆነው የምናውቀው ካልሆነ ዓይናችንን አይስበውም፣ አዕምሮአችንን አይማርከውም። ራሱን ድኋ ካደረገ ሀብታም ነው ማለት ነው፣ እረኞች ከሰገዱለት የበጎቹ ጌታ እርሱ ነው ማለት ነው፣ ጥበበኞች ከተንበረከኩለት ጥበብ እርሱ ነው ማለት ነው፣ ካህናት ካልሄዱ ራሱ ካህን ነው ማለት ነው፣ በእንግዶች ማደሪያ ስፍራ ከሌለው እርሱ እንግዳ አይደለም ማለት ነው። ስላላወቅነው እርሱ እንደሆነ አወቅነው፣ ስላሳደድነው እውነት እንደሆነ ገባን፣ ወደ ግብጽ በመውረዱ የአባቶቻችን ዘመድ እንደሆነ ተገለጠልን። ወደ ግብጽ ስላልጠራን፣ በግብጽ ስላላገኘነው ከአባቶቻችን የተለየ እንደሆነ አወቅን። በመመሳሰሉ ሳበን፣ ልዩ በመሆኑ ማረከን። ሕጻን ተወልዶልና ግን የዘላለም አባት ነው፣ የሰላም አለቃ ነው ግን የኛን ሰላም ያናጋዋል፣ ንጉስ ነው ግን እግራችንን ነው የሚያጥበው፣ አምላክ ነው ግን አምላኬ ለምን ተውከኝ ይላል። ወንድ ልጆች ሲገደሉ አባታችን ሙሴ ወደ ገዳዩ ቤት ገባ፣ ወንድ ልጆች ሲገደሉ ወንዱን ልጅ በመጠቅለያ ይዛ ወደ ግብጽ ወረደች። አካላዊ ቃል ፥ ቃል አልባ ሕጻን ሆነ፤ ቤት ያልተገኘለት ልደት በሁሉ ቤት የሚከበር ልደት ሆነ። ያለእናት የተወለደው ልጅ፣ ያለ አባት ደግሞ ተወለደ። የሰውን ልጅ በኃጢአቱ ምክንያት ከገነት ያሳደደው አምላክ፣ በሰው ልጅ በንጽህናው ምክንያት ከቤተልሄም ተሳደደ። ለካህናት እና ለጠቢባን ረቂቅ የሆነው ልደት ለእረኞች እና ለበጎቹ ግልጽ ሆነላቸው። ቅርብ ለነበሩት የራቀው ልደቱ ለሩቅ ምስራቆቹ ቅርብ ሆነላቸው። ምድራውያን ከልደቱ ሲሸሹ ሰማያዊያን በቤተልሄም ቆሙ። የሚሰግዱት በሄሮድስ ሲያልፉ የሰገዱት ከሄሮድስ ራቁ። አዋቂዎች ሊሰይፉት ሲነሱ ሕጻናት ስለእሱ ተሰየፉ። ምኞታችንን ሕይወት እንድንነሳው ፥ ሕይወት ያለስጋ ምኞት ተወለደ። መንግስቱ የማይታየው ንጉስ፣ አሳዳጃችንን ያሳደደልንን ተሳዳጅ፣ ልብስ አልባው አልባሽ፣ በቤት ያኖረን ቤት ያልተገኘለት። ያን ነው ታናሿ ቤተልሄም የሰጠችኝ ታላቁ ጌታ። ከሁሉ አንሶ የተገለጠውን ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሺም የተባለችው ከተማ ሰጠችን።  ከሁሉ ለመብለጥ ከሁሉ ታናሽ ሁኑ፣ ለመቅለል ቀንበሬን ተሸከሙ ፣ ዓለምን ለመውረስ ዓለምን ካዱ ፣ ራሳችሁን ለማዳን ራሳችሁን እጡ፣ ፊተኞች ለመሆን ኋለኞች ሁኑ፣ አለቃ ለመሆን ሠራተኞች ሁኑ የሚለን ሕጻኑ አባት፣ ማረፊያ አልባው አሳራፊ፣ ሰላም የነሳነው የሰላም አለቃ፣ ሄሮድስን የሚሸሽ የዘላለም ንጉስ፣ የራሱ የሆኑት ያላወቁት ከርሱ ያልሆኑት ያወቁት በዳዊት ከተማ ተወለደ። መልካም ገና!!! (Mulualme's View)

  • አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ Pope Shenouda III pinned «#ሀሜት “…እንዲሁም ሴቶች ጭምቶች፥ የማያሙ፥ ልከኞች፥ በነገር ሁሉ የታመኑ ሊሆኑ ይገባቸዋል።” (1ኛ ጢሞ. 3፣11) ሀሜት ምንድን ነው? 👉"ሀሜት"ማለት :- ሰዎች ቢኖሩ ልንለው የማንችለውን ነገር በሌሉበት ስለሰዎች መጥፎ የሆነውን ማውራት። 👉ለበጣ (አስመሳይነት): -ሰዎች ባይኖሩ ልንለው የማንችለውን ነገር ሲኖሩ የምንክበው የውሸት ካብ (የውሸት ሙገሳ ወይም አስመሳይነት)። ሀሜት ባለበት ሁሉ ለበጣ…»

  • 28 нояб.2 6042319

    #ሀሜት “…እንዲሁም ሴቶች ጭምቶች፥ የማያሙ፥ ልከኞች፥ በነገር ሁሉ የታመኑ ሊሆኑ ይገባቸዋል።” (1ኛ ጢሞ. 3፣11) ሀሜት ምንድን ነው? 👉"ሀሜት"ማለት :- ሰዎች ቢኖሩ ልንለው የማንችለውን ነገር በሌሉበት ስለሰዎች መጥፎ የሆነውን ማውራት። 👉ለበጣ (አስመሳይነት): -ሰዎች ባይኖሩ ልንለው የማንችለውን ነገር ሲኖሩ የምንክበው የውሸት ካብ (የውሸት ሙገሳ ወይም አስመሳይነት)። ሀሜት ባለበት ሁሉ ለበጣ አለ። 👉አሽሙር: - ስለሰዎች በቀጥታ መናገር የሚገባንን ነገር በተዘዋዋሪ መናገር (ሀሜት ነው፡፡) ✍️አንድ ወሬ ሲመጣ ስለ ሰው ወሬ ከመስማታችን በፊት እንዲሁም ሰምተን ወሬውን ከማስተላለፋችን በፊት የምናጣራበተ ወንፊት ሊኖረን ይገባል፡፡ በ3 ነገሮች - ነገሩ (የምንሰማው/ ለሌሎችየምናስተላልፈው)፡- 1. እውነት ነው ወይ:- ስለዚህ ሰው የምትነግረኝ እውነት መሆኑን አረጋግጠሃል ወይ? 2. መልካም ነገር ነው ወይ? 3. ጠቃሚ ነው ወይ? … ጌታችን በወንጌል የነገረንን እናስተውል 👉 “…እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤” (ማቴ. 12፣36)

  • Channel photo updated

  • 26 нояб.2 04651

    https://t.me/yaregalabegaz/2255

  • " በሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አስተምህሮ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ አባወራው(ባል) የቤተሰቡ ሊቀ ጳጳስ ነው፡፡ የአንድ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዋናነት ቃለ እግዚአብሔርን ማስተማር፤ ሥርዓተ ቅዳሴንና ሌሎች ጸሎቶችን መምራት እንዲሁም ለምእመናን አርአያ ሊኾን እንደሚገባው ሁሎ የአንድ ቤተሰብ አባወራም ዕለት ዕለት ቃለ እግዚአብሔርን በማስተማር በቤተሰብ ውስጥ ምንም ዓይነት ምንፍቅና እንዳይኖር እረኝቱን በአግባቡ መወጣት አለበት፡፡ የቤተሰብ ጸሎት ከመምራትም ባሻገር ጸሎቱ እንዳይታጎል መትጋት አለበት፤ ለቤተሰቡ የሚያስተምረውን ቃለ እግዚአብሔር በተግባር በመፈጸም አርአያ ሊኾን ይገባል፡፡ ምእመናን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ምንም ዓይነት ኃላፊነትና ድርሻ የላቸውም እንደማይባለው ኹሉ የቤተሰብ አባላት ማለትም ሚስት፣ ልጆችና የቤት ውስጥ ሠራተኞችም ሊቀ ጳጳሳቸውን - ማለትም አባወራውን - ሊታዘዙትና ሊራዱት ይገባል፡፡" (ኦሪት ዘፍጥረት- ቅዱስ ዮሐንስ እንዳስተማረው- ትርጉም ገ/እግዚአብሔር ኪደ)

  • "እናንተ የምድር ጨው ናችሁ! ርካሽ ልትሆኑ ትችላላችሁ ግን እናንተ ለአለም አስፈላጊ ናችሁ።" (አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ) ...

  • 10 окт. 2025 г.2 254911из shenouda27

    "ፈተና ሲገጥመን ውስጣችን ሊረበሽ ወይም በቀቢጸ ተስፋ ሊያዝ አይገባውም፡፡ ወርቅን የሚያነጥር ሰው በእሳት ውስጥ የጨመራትን የወርቅ ቅንጣት እዚያ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ መቆየት እንዳለባት ያውቃል፤ መቼ ከእሳቱ ሊያወጣት እንደሚገባውም ያውቃል፡፡ እንዲሁ እስከ መጨረሻው በእሳቱ ውስጥ ተጥላ እንድትቀርና በዚያ እንድትቃጠል አይፈቅድም፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ከወርቅ አንጣሪው በላይ ያውቃል፡፡ መቼ ከርኩሰታችን እንደምንነጻ ያውቃል፡፡ በመኾኑም ራሳችንን በመጣልና ተስፋ በመቁረጥ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመርን እንዳንኼድ ሽቶ መቼ ከዚያ ፈተና እንደሚያወጣን ያውቃል፡፡ ስለዚህ ድንገት ያላሰብነው ነገር ቢገጥመን በፍጹም የምናማርር፣ ወይም ተስፋ የምንቆርጥ ልንኾን አይገባንም፡፡ ከዚህ ይልቅ የእነዚህ ነገሮች ምንነትን የሚያውቅ እግዚአብሔርን መጠበቅ፣ እርሱ እስከ ፈቀደው ጊዜ ድረስም ልቡናችንን በእሳት እንዲፈተን ማድረግ ይገባናል። ምክንያቱም ይህ ነገር በእኛ ላይ እንዲኾን (እንዲመጣ) የፈቀደው ለእኛ ጥቅምና በዚያ ውስጥ ኾነን በምናሳየው ጥረት ይበልጥ ሊያከብረን ስለሚወድ ነው፡፡" #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ወደ ኦሎምፒያስ መጽሐፍ በ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ

  • ተባብረው ፥ ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ለመተባበር የመርህ ውሳኔ አድርገዋል። በስም ሳይሆን በተግባር ክርስቶስን ለመምሰል መጣር የእነዚህ ራስን እና ሰውን የመረዳት ጉዞ እና ከዛ ተፈጥሮአችን በተቃራኒ የመጓዝ ውሳኔ ነው።"

  • "ከተፈጥሮአችን በተቃራኒ የመጓዝ ውሳኔ" (በሙሉአለም ጌታቸው) . "አላን ዋትስ ስለ ካርል ዩንግ በጻፈው መጣጥፍ ላይ ከራሱ ጋር የታረቀ ሰው በዚህ ዓለም ላይ ካርል ዩንግ ነበረ ይላል። ዩንግ ራሱ ላይ ያሉትን ሕጸጾች እና ድካሞች በይሁንታ ያለማፈር የተቀበለ ሰው ነበር። በተለይ በ1950ዎቹ ሲዊዘርላንድ ላይ ለቀሳውስት ያደረገው ንግግሩ ዩንግ የሰውን ተፈጥሮ በጥልቀት መረዳቱን የሚያሳይ ነበር። ሰዎች ለራሳቸው ጥቅም እንደሆነ እስካወቁ ድረስ ምንም ክፋትን በሰዎች ላይ የማድረግ አቅም አላቸው። የሰው ልጆች በጎ ላደረገላቸው እና መልካሙን ነገር ለሰጣቸው ሳይቀር የእነሱ ሕይወት የሚሰምር ከመሰላቸው ወይም በጣም የሚፈልጉት ነገር እንዲሆንላቸው የወደዱ እንደሆነ ክፋትን ለማድረግ ፈቃደኛ ናቸው። ለዚህ ነው ለክርስቲያኖች የክርስቶስ ሕይወት አስገራሚ የሆነው። ምክንያቱም በበርባን ምትክ ንጹሁ ክርስቶስ ለመሞት ፈቅዷልና። ... ...የሰው ልጅ ጠባዩ እንስሳዊነት ሲሆን፤ ተፈጥሮውም እስካልተገራ ድረስ ከበጎነት ይልቅ ለክፋት የተመቸ መሆኑን ነው። ለዚህ ነው ሰው የራሱን ጥቅም ከሚያጣ፤ ሰዎችን አሳልፎ መስጠት እና መጉዳት ምርጫው የሚሆነው። ይሄን ለክፋት የተመቸን ማንነታችንን እውቅና ካልሰጠነው እና በፍጹም ሰብአዊ አስተሳሰቦች እና ክርስትናዊ ፍቅር ካልገራነው በቀር ሰው አውሬ ነው። ክርስቶስን የተለየ የሚያደርገውም ይሄ ነው። ተፈጥሮ ለመልካም ነገሮች ያደላ ነው። ፍጹም ስለራሱ ሕመም ብቻ ማሰብ በሚገባው የመስቀል ሰዓት ያሰበው ከራሱ ይልቅ ስለ ሰቀሉት ምህረትን ነበር። ከዛም ለሚወዳት እናቱ ልጅ እና ተንከባካቢን መስጠት ነበር። ከዛም በዛ መራራ ሰዓት አንተም እንደኛው ወንጀለኛ ነህ እያለ በሚከሰው አላዋቂ ከመናደድ እና ከመራገም ይልቅ በሌላኛው ጎኑ ሆኖ አንተ ልዩ ነህ ያለውን ያን ሰው የገነት ቁልፍን መስጠት ነበር ሥራው ያደረገው። ለክፋት ፈጽሞ አልመለሰም። ከክፋት ጋር ድርድር ውስጥ አልገባም። ፍርድን ሊሰጥ ከማይችል ከጲላጦስ ፊት አለፈለፈም። ሦስቴ የከሰሰውን ሰው ከሰስከኝ ብሎ አላወራውም። ይሄ ሁሉ ክፋት ምንም አላስደነቀውም። የበሰሉ ሰዎች የሚደርሱበት ደረጃ ያ ይመስለኛል። በሰው ክፋት አለመደነቅ። ከሰው ልጆች ሞራል እና ከፍታን አለመጠበቅ። የሰው ልጅ ተፈጥሮ በሆኑ ጉዳዮች ጉድ አለማለት። ያ ብቻ ሳይሆን እነርሱም ለዛ ክፋት ብቁ መሆናቸውን ማወቅ። ለጴጥሮስ መመለስ ትልቁ አስተዋጽኦ ክርስቶስ በርሱ መክዳት አለመደነቁ ነው። የሰው ልጅ የሚድን ከመሰለው ሁሉን ትቶ የተከተለውን መልሶ ይክደዋል። ተመልከቱ አሜሪካ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ጉድ። በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ክርስትናን የሚያራምድ ነው። አሜሪካ ውስጥ በባለፉት ሃምሳ ዓመታት ውስጥ እንደዚህ ጊዜ ስደተኞች ባይተዋርነት ተሰምቷቸው አያውቅም። ጥቁር እና ስደተኛ ፍጹም ወደ ሆነ ባይተዋርነት እየተገፉ ያለበት ዘመን ላይ ነን። አንገታቸው ላይ መስቀል ያደረጉ እና የቻርሊ ከርክን መገደል አስመልክቶ ወደ ቤተክርስቲያን እየጎረፈ ያለ የትረምፕ ደጋፊዎች ናቸው ስልጣን ላይ ያሉት። ከክርስትና በላይ ለስደተኞች መጨነቅ ያለበት ሃይማኖት መኖር ያለበት አይመስለኝም። ምክንያቱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰደደ ነበር። ለስደተኞች ፍጹም ርህራሄ እንድናሳይ የተጋበዝንበት ሃይማኖት ነበር። ክርስትና መሠረቱ፣ ምሰሶው፣ ጣሪያው ሁሉ ምስኪኖችን እና መሄጃ የሌላቸውን በመቀበል ላይ የተመሰረተ ነው። ቤተክርስቲያን ለዚህ ነው የስደተኞች ቤት የምትባለው። ተሰደው የመጡ ሰዎች የሚጠለዩት የክርስቶስ ቤት ውስጥ ነው። አሁን ግን ክርስትና የሰው ክፋትን ሊገራው ይቅርና የመጨቆኛ መሳሪያ ሆኖ መጥቷል። ኃጢያተኞች ቤት እየሄደ በአመንዝራዋ እንባ እግሮቹ የታጠበ፣ በቀራጩ ቤት እራት የበላ፣ ከወንበዴው ጋር ንግግር ያደረገ፣ ባል እየቀያየረ ከኖረች ሴት ጋር ለማውራት በጠራራ ፀሐይ ወንዝ ዳር ቁጭ ብሎ የጠበቀን አምላክ የምናመልክ እና የምንከተል ሰዎች ፈጽሞ ልንሆን አንችልም፤ አሁን የምናደርገውን እያደረግን። ይሄ የክርስትና ተቃራኒ ነው። ይሄ ፖለቲካ እንጂ ክርስትና፣ ሃይማኖት ሊሆን አይችልም። ለባህሪያችን የሚስማማ ነገር እያደረግን ክርስቲያን ተብለን ልንጠራ አንችልም። ለዚህ ነው ዩንግ በዚህ ስብከቱ ለእነዛ ቀሳውስት የክርስትና መሠረቱ በራሳችን ውስጥ ያለውን በርባንን፣ ያን ወንበዴ፣ ያን ዘረኛ የሆነውን እና ቡድነኝነት የሚስማማውን ተፈጥሮአችንን መቀበል ነው ያለው። በርሱ ማፈር ሳይሆን መቀበል፣ በውስጣችን እንደሚኖር ማወቅ ነው ያለብን። ምክንያቱም ሰዎች እንደዛ ነን። ያንን በውስጣችን ያለው የክፋት ጥግ ስናውቅ ሌላው ላይ የመፍረድ አቅም አይኖረንም። ሌሎችንም ከፍ ወዳለ ስብዕና እና እርከን ማውጣት እንችላለን። ያኔ ብቻ ራሳችንን ወደ ማወቅ እና ክርስቶሳዊ ፍቅርን ወደ መላበስ ማደግ እንችላለን። አሁን ግን ክርስትና የሰው ክፋትን ሊገራው ይቅርና የመጨቆኛ መሳሪያ ሆኖ መጥቷል። ኃጢያተኞች ቤት እየሄደ በአመንዝራዋ እንባ እግሮቹ የታጠበ፣ በቀራጩ ቤት እራት የበላ፣ ከወንበዴው ጋር ንግግር ያደረገ፣ ባል እየቀያየረ ከኖረች ሴት ጋር ለማውራት በጠራራ ፀሐይ ወንዝ ዳር ቁጭ ብሎ የጠበቀን አምላክ የምናመልክ እና የምንከተል ሰዎች ፈጽሞ ልንሆን አንችልም፤ አሁን የምናደርገውን እያደረግን። ይሄ የክርስትና ተቃራኒ ነው። ይሄ ፖለቲካ እንጂ ክርስትና፣ ሃይማኖት ሊሆን አይችልም። ለባህሪያችን የሚስማማ ነገር እያደረግን ክርስቲያን ተብለን ልንጠራ አንችልም። ለዚህ ነው ዩንግ በዚህ ስብከቱ ለእነዛ ቀሳውስት የክርስትና መሠረቱ በራሳችን ውስጥ ያለውን በርባንን፣ ያን ወንበዴ፣ ያን ዘረኛ የሆነውን እና ቡድነኝነት የሚስማማውን ተፈጥሮአችንን መቀበል ነው ያለው። በርሱ ማፈር ሳይሆን መቀበል፣ በውስጣችን እንደሚኖር ማወቅ ነው ያለብን። ምክንያቱም ሰዎች እንደዛi ነን። ያንን በውስጣችን ያለው የክፋት ጥግ ስናውቅ ሌላው ላይ የመፍረድ አቅም አይኖረንም። ሌሎችንም ከፍ ወዳለ ስብዕና እና እርከን ማውጣት እንችላለን። ያኔ ብቻ ራሳችንን ወደ ማወቅ እና ክርስቶሳዊ ፍቅርን ወደ መላበስ ማደግ እንችላለን። አረመኔያዊ ነገሮች ሊደርሱብን የፈቀድን ካልሆንን የክርስቶስን ፍቅር መሸከም የምንችል አይመስለኝም። ምክንያቱም መልካም ካልሆንን የሰዎች ክፋትን መቋቋም እንችላለን። የሰዎች ክፋትን ስናውቅ ነው ደግሞ እውነተኛ መልካም መሆን የምንችለው። ምክንያቱም በጎ እንደሚሰጠን እያመንን መልካም ካደረግን’ማ ከተፈጥሮአችን ተቃራኒ የሆነን እምነት አልተከተልም። ክፋት እና መከዳት እንደሚጠብቀን አምነን መልካምነትን የመረጥን ከሆንን ብቻ ነው በመርህ እየተጓዝን ያለነው። በሰው ልጆች እንደምንጎዳ አውቀን ነው ፍቅርን የመረጥነው። ባጎረስን እንደምንነከስ በፍጹም ጠብቀን ነው እጃችንን በክፋት አፍ ውስጥ የከተትነው። ለምን? ይሄi ምርጫ ነው። ምርጫችን በጨለማው ዓለም ውስጥ ጨለማ ላለመሆን ነው። በጨለማው ዓለም ውስጥ ላለመታየት የፈለገ ሰው እርሱም ጨለማ ነው መሆን ያለበት። ከጨለማው ጋር የተባበረ በጨለማው አይጎዳም። የጨለማውን ጨለማነት በመልካም ባህሪ እና በፍቅር ለመለወጥ የፈለጉ ሰዎች ብቻ በዚህ ዓለም ክርስቲያን ተብለው ይጠራሉ። ከዓለም እና ከተፈጥሮአችን ግብዣ ውጪ ክፋትን በክፋት ላለመመለስ ወስነዋልና። እንደሚጠቁ እና እንደሚከሰሱ እያወቁ ራሳቸውን ለሚበልጠው የስብዕና ማማ አሳልፈው ሰጥተዋል። ከርሱ የመከዳት የውስጥ ሕመም እና የሀሰት ክስ ስቅላት ቁስል ጋር አሁን

  • 1 окт. 2025 г.1 7401433из shenouda27

    #ተግባራዊ_ክርስትና #የስሜት_ሕዋሳትን_መቆጣጠር ባሕታዊው ቴዎፋን የሰውን ነፍስ በንጉሥ የሚመስለው ሲሆን ሥጋውን ደግሞ በንጉሡ ቤተ መንግሥት ይመስለዋል፡፡ ይህ ቤተ መንግሥት አምስት መስኮቶችና አንድ በር አለው፡፡ እነዚህ አምስት መስኮቶች አምስቱ የስሜት ሕዋሳት ናቸው፡፡ በሩ ደግሞ አእምሮ ነው፡፡ ጠላት በመስኮትና በበር ካልሆነ በየትም ሊገባ አይችልም፡፡ እነዚህ ከተዘጉ ጠላት ለመግባት አይችልም፡፡ በእነዚህ መስኮቶች (የስሜት ሕዋሳት) የኃጢአት ነጋዴ ዲያቢሎስ ልዩ ልዩ ልምምዶችንና ነፍስን የሚያስደስቱ ስሜቶችን ያመጣል፡፡ በዚህም የተነሣ ነፍስ እርካታን ጠቅልላ ትይዛለች፡፡ ከዚያም ይህንን እርካታ እንደ ዋና መልካም ነገርና እንደ ግብ መቁጠር ትጀምራለች፡፡ በዚህ መንገድ ነገሩ ይገለበጥና ነፍስ እግዚአብሔርን መፈለግ ትታ ደስታን መሻት ትጀምራለች፡፡ መንፈሳዊውን ፍጹምነት መንገድ ለመጀመር የሚፈልግ ሰው ትክክለኛውን የሕይወት ቅደም ተከተል ዳግም ሊመሠርት ይገባዋል፡፡ ይህም በደስታ ከመዋጥ ይልቅ እረፍትን ከአምላክ መፈለግ ነው፡፡ ትግሉ ረዥምና አስቸጋሪ ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ ይህን ውሳኔ እንወስናለን፡፡ (#ተግባራዊ ክርስትና አቡነ አትናስዮስ እስክንድር እንደፃፉት) ሙሉ መፅሐፉን ያንብቡ👆👆

  • (ትንቢተ ሚክያስ 7 ÷ 7-10) 7: እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር እመለከታለሁ፥ የመድኃኒቴንም አምላክ ተስፋ አደርጋለሁ፤ አምላኬም ይሰማኛል። 8: ጠላቴ ሆይ፥ ብወድቅ እነሣለሁና፥ በጨለማም ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛልና በእኔ ላይ ደስ አይበልሽ። 9: በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና እስኪምዋገትልኝ ድረስ፥ ፍርድን ለእኔ እስኪያደርግ ድረስ ቍጣውን እታገሣለሁ። ወደ ብርሃን ያወጣኛል፥ ጽድቅንም አያለሁ። 10: ጠላቴም ታያለች፥ እኔንም፦ “አምላክህ እግዚአብሔር ወዴት ነው?” ያለች በእፍረት ትከደናለች።

አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ Pope Shenouda III — tgindex