- Последний пост
- 7 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 42
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 41
- 1/48двое суток
- 46
- 1/72трое суток
- 50
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
#Update በ'ፊንቴክ ኢንቨስትመንት' የማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ አርቲስቶች የዋስትና መብታቸው ተነስቶ ጉዳያቸውን በእስር ላይ ሆነው እንዲከታተሉ አቃቢ ህግ አቅርቦት የነበረው አቤቱታ ውድቅ እንዲደረግ እና በከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ ብይን ተሰጠ። አቃቢ ህግ በከፍተኛ የኢንቨስትመንት ማጭበርበር ወንጀል ተከሰው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙ ተከሳሾች እና ጠበቃቸው፣ የተከሰሱበት የክስ መዝገቡ በክርክር ሂደት ላይ የሚገኝ እና በችሎት ውሳኔ ያልተሰጠበት ሆኖ እያለ በሚዲያ ላይ በመቅረብ ከክሱ አውድ ውጪ የሆነ ማብራሪያ በመስጠታቸው የፍትሕ ሂደቱን ተጽዕኖ ውስጥ ለመክተት እና ምስክሮችን ላይ ተጽዕኖ ለማድረግ ሞክረዋል በሚል የዋስትና መብታቸው ተነስቶ ከማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ የሚል አቤቱታ አቅርቦ ነበር። በተጨማሪም ዘገባው የተጫነበት ሚዲያ ይቅርታ እንዲጠይቅ እና ቪዲዮውን እንዲያወርድ ፣ በወንጀል ህግ አንቀጽ 457 ስር በቀጥታ እንዲቀጡ እንዲወሰን የሚሉ አቤቱታዎችንም አቃቢ ህግ አካቷል። ፍ/ቤቱ ድርጊቱን በቀጥታ መቅጣት የማይችል ከሆነ ደግሞ አቃቢ ህግ የወንጀል ምርመራ የማድረግ እና ክስ የማቅረብ ስልጣኑን ተጠቅሞ ምርመራ የሚጀምር እና ተከሳሾችን በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጎ ክስ የሚያቀርብ መሆኑንም አስረድቷል። ዛሬ ጠዋት በዋለው ችሎት የአቃቢ ህግ አቤቱታን እና የተከሳሾችን ምላሽ መርምሮ ምላሽ ለመስጠት ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው ችሎቱ ተከሳሾቹ የዋስትና መብታቸው እንዲነሳ የቀረበውን አቤቱታ ውድቅ አድርጎታል። ችሎቱ በዋስትና ላይ የቀረበውን አቤቱታ ውድቅ ያደረገው በጥቃቅን ስህተቶች የዋስትና መብታቸውን መከልክል አግባብነት ያለው ባለመሆኑ አልተቀበልነውም በሚል ነው። እንዲሁም አቃቢ ህግ ፍ/ቤቱ ድርጊቱን በቀጥታ መቅጣት የማይችል ከሆነ አቃቢ ህግ የወንጀል ምርመራ የማድረግ እና ክስ የማቅረብ ስልጣኑን ተጠቅሞ ምርመራ የሚጀምር እና ተከሳሾችን በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጎ ክስ የሚያቀርብ መሆኑን ያሳወቀበትን አቤቱታን በተመለከትም በመደበኛ ምርመራ ተጣርቶ የመከራከር መብታቸውም ተከብሮ የሚታይ ነው በሚል አልተቀበለውም። የተላለፈውን ዘገባ ይዘት በተመለከተ ግን ህጉን ያልተከተለ አሳሳች ዘገባ ነው ያለው ሲሆን ከተጫነነት ሚዲያ ላይ እንዲወርድ እና ሚዲያውም ይቅርታ እንዲጠይቅ ትዕዛዝ ተሰጥቷል። አርቲስቶቹን በተመለከተ በከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ ችሎቱ ብይን የሰጠ ሲሆን በመዝገቡ ላይ ለ ጥቅምት 2/2018 ዓም የተያዘው ቀጠሮ እንደተጠበቀ ነው በማለት ብይን ተሰጥቷል። #tikvahethiopia @subitime
"ወደ ሚድያ የመጣነው በሚድያ የጠፋ ስማችንን ለማደስ ነው" ተከሳሾች "የዋስትና መብታቸው ይውረድና ጉዳያቸውን በማረሚያ ሆነው ይከታተሉ " ዐቃቢ ሕግ በፊንቴክ የማጭበርበር ወንጀል የተከሰሱት አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች ፍርድቤት መደበኛ ስራውን በከፊል የዘጋ ቢሆንም በተለዋጭ ቀጠሮ ለነሐሴ አንድ እንዲቀርቡ በተባለው መሰረት ተከሳሾቹ ፍርድቤት መቅረባቸውን ተመላክቷል። ከዚህ በፊት በነበረው ችሎት አቃቤ ሕግ ላቀረበው ምላሽ ብይን ለመስጠት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት፣ አቃቤ ሕግ ያቀረበውን ምላሽ መርምሮ ብይን ለመስጠት ለሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱ የሚታወቅ ሲሆን በዚሁም መሰረት ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ቀርበው ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ ችሎቱ መርምሮ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ ማድረጉ የሚታወስ ነው ። ከቀረቡ የክስ መቃወሚያዎች መካከል 1ኛ ተከሳሽ ሰራዊት ፍቅሬ የሚያታልል ንግግር አልተናገርኩም እንዲሁም ድርጅቱ ከመንግስት እውቅና ያለው ነው ከማለት በተጨማሪ ከድርጅቱ ማግኘት የነበረባቸውን ጥቅም እንዳላገኙም በአቤቱታው ገልጸው ነበር ። ሌሎችም በተመሳሳይ የሰራነው ማስታወቂያ እንጂ የኮምፕዩተር ወንጀል ባለመሆኑ ክሳችን በዚህ መልኩ ሊታይ አይገባም ያሉ ሲሆን ሌላኛው 6ኛ ተከሳሽ ደግሞ በካሊድ በጎ አድራጎት ድርጅት ስም እርዳታ እንጂ በግል እንዳልተከፈላቸው በክስ መቃወሚያቸው ላይ ገልጸው ነበር ። እንዲሁም ደግሞ ክሳቸውን በማረሚያ ሆነው ሲከታተሉ የቆዩት እና ከቀናት በፊት ከማረሚያ ቤት የወጡት 5ኛ ተከሳሽ መንሱር ጀማል በተደራራቢ ወንጀል ልከሰስ አይገባኝም በማለት የክስ መቃወሚያ አስገብተው የነበረ ቢሆንም ችሎቱ መቃወሚያውን ውድቅ አድርጎታል። ከዚሁ ጋር በተገናኘ አቃቤ ሕግ አዲስ አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ተከሳሾቹ "እግረኛው" በተሰኘ የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ላይ ቀርበው መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ አቃቤ ህግ ባለ 5 ገጽ የክስ አቤቱታ ለችሎቱ አቅርቧል። በዚህም በፍርድ ቤት በሂደት ላይ ባለ ጉዳይ ላይ መግለጫ መስጠት በፍትሕ አሰጣጥ ሂደቱ ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳድር ፍርድ ቤቱ አቤቱታው ታይቶ ውሳኔ እንዲሰጥበት እንዲሁም ይህ ድርጊት ወንጀል በመሆኑ ፍርድ ቤቶች በተዘጉበት ወቅትም ቢሆን ችሎቱ አስቸኳይ ብሎ በሚያያቸው ጉዳዮች ውስጥ ተካቶ እንዲታይለት ጠይቋል። በተጨማሪ አቃቢ ሕግ በፍርድ ሒደት ላይ በሚገኝ ጉዳይ ተክሳሾች እና የከፊሎቹ ጠበቃ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በመቅረብ የፍትህ ሂደቱን የሚያዛባ ተግባር መፈጸምቸውን ጠቅሶ ይህም ፍትህ ላይ ጉዳት ማድረስ በመሆኑ ጠበቃ አበባው አበበ እና የእግረኛው ሚዲያ ባለቤት ጋዜጠኛ ተክለኃይማኖት አዳነ ተይዘው እንዲቀርቡ ሲል ጠይቋል ። በዚህም ችሎቱ የማንኛውም ሰው የመናገርና ሀሳብን የመግለጽ መብት ሕገ-መንግሥታዊ ቢሆንም፣ በሕግ በተያዘ ጉዳይ ላይ አስተያየት መስጠትን በተመለከተ ዝርዝሩን ለማጣራት ጋዜጠኛ ተክለሃይማኖት አዳነ እና ጠበቃ አበባው አበበ በችሎት ተገኝተው የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ ለነሐሴ 1 2019 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ሲሆን በዚሁም መሰረት በሌላ ወንጀል ተጠርጥረው በማረሚያ የሚገኙት ጋዜጠኛ ተክለ ኃይማኖት አዳነ እና ሌሎች ተጠርጣሪዎች ችሎት ቀርበዋል። ጠበቃ አበባው አበበን ጨምሮ 5ኛ ተከሳሽ መንስሩ ጀማል እና ስድስተኛ ተከሳሽ ካሊድ በችሎት አልቀረቡም ነገር ግን የስድስተኛ ተከሳሽ ጠበቃ በህክምና ምክንያት አለመቅረባቸውን ማስረጃ አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱ በነሐሴ 1 ቀን የጠዋት ችሎቱ ከ5ኛ ተከሳሽ ውጭ እግረኛው ሚዲያ ላይ በመቅረብ የፈፀሙት የፍትህ ሂደትን ለማዛባት በተንኮል የሚፈፀም ወሬ መግለፅ ድርጊት ምክንያት ተጠያቂነት እንዲሰፍን ለማስደረግ በቀረበ አቤቱታ ምላሽ ሰጥተዋል ። በምላሻቸውም በሚዲያ የጠፋ ስማችንን ለማደስ ነው የቀረብነው በማለት የፍርድ ሒደቱን የሚያዛባ ነገር አላደረግንም በማለት ምላሽ ሰጥተዋል። 3ኛ ተከሳሽ ይገረም ደጀኔ በበኩላቸው በማህበራዊ ሚዲያ በደረሰባቸው የስም ማጥፋት ምክንያት ከ 4-5 ድርጅቶች ጋር የስራ ውላቸው እንደተቋረጠ ገልጸው በሚዲያ የጠፋ ስማቸውን ለማደስ እንዳደረጉት ተናግረዋል። ጋዜጠኛ ተክለኃይማኖት በበኩላቸው ተከሳሾች ከመያዛቸው ቀድሞ በጉዳዩ ዙሪያ እየሰሩ እንደነበር ጠቅስው የሰሩትም በተከሳሾቹ ጥያቄ መሰረት መሆኑን ገልጸው የሕግ ጉዳዩን አለመንካታቸውን ገልጸዋል። ዐቃቢ ሕግ በበኩሉ ተከሳሾች ስማችን ጠፍቷል ካሉ ይህንን ጉዳይ ሊያጣራ የሚችል አካል በመኖሩ ጉዳዩን ወደእዛ መውሰድ እንደሚችሉ ጠቅሶ ጠበቃቸውን ጨምረው መቅረባቸው ለሕጉ ግንዛቤ እንዳላቸው የሚያስረዳ በመሆኑ የመጣው ይምጣ ብለው ነው የቀረቡት ሲል ለችሎቱ አስረድቷል። ዐቃቢ ሕግ በጽሁፍ ባቀረበው አቤቱታ መሠረት 1ኛ ተከሳሾች እና አቶ ተክለሃይማኖት አዳነ ድርጊቱን ሆነ ብለዉ የፈፀሙት ስለሆነ ለችሎቱ ቀርበው ለምን ጥፋቱን እንደፈፀሙ አስተያየት ሰጥተዉ በወንጀል ህግ አንቀፅ 457 ስር በቀጥታ እንዲቀጡ እንዲወስን፣ 2ኛ ተከሳሾች ሌሎች ወንጀሎችን እንደማይፈፅሙ ታምኖ የተሰጣቸዉን ዋስትና ግዴታ እያከበሩ ስላልሆነ እንዲያዉም የዳኝነት ነፃነትን እየተጋፉ እና ምስክሮች ላይ ጫና እያሳደሩ ስለሆነ ዋስትናቸው ወርዶ ከማረሚያ ሆነው እንዲከራከሩ እንዲወሰን 3ኛ የተላለፈው ዘገባ ይቅርታ ተጠይቆበት እንዲወርድ ትዕዛዝ እንዲሰጥ ጠይቋል። ችሎቱም ጉዳዩን መርምሮ ብይን ለመስጠት ከሰአት በኋላ ለዘጠኝ ሰዓት (9:00) ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ። ምንጭ አዋሽ ኤፍ ኤም @subitime
ድምፃዊት ራሄል ዮሐንስ ከዚህ አለም በሞት ተለየች! ራሄል ዮሐንስ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ በተለይም በ1980ዎቹ እና 1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈች ታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ ድምፃዊ ናት። ለቤተሰብ ወዳጅ ዘመድ መፅናናትን እንመኛለን :: @subitime
ሐምሌ 8/2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የቀረቡ ስምንት አጀንዳዎች በዝርዝር:- አጀንዳ ቁጥር 1 1. የሀገር ግንባታ 1.1 የማንነት እና የሀገር ባለቤትነት ጉዳዮች 2. ታሪክ እና ማንነት 3. የጋራ ሀገራዊ ማንነት እና እሴቶች (እሴቶችንም የሚመለከቱ ጉዳዮች) 4. ሀገር ግንባታና ብዝሀነት አስተዳደር ጉዳዮች 5. የቋንቋ ጉዳዮች 1.6 የባህል፣ታሪክና ቅርስ ጥበቃ ጉዳዮች እንዲሁም ሌሎችም በርካታ ጉዳዮች አጀንዳ ቁጥር 2 2. የመንግስት አደረጃጀትና ቅርጽ እንዲሁም የፖለቲካ ስርአት፣የፖለቲካ ውክልና እና የምርጫ ስርአት 2.1 የመንግስት አደረጃጀትና ቅርጽ 2.1.1 የመንግስት አደረጃጀት፣አስተዳደር ስርአት አይነት 2.1.2 የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት (በቅንፍ ውስጥ ሲቲዝንሺፕ ዜግነት) ህዝባዊ...አንድ 2.1.3 የብሄር ብሄረሰቦች ትርጓሜ (አንቀጽ 39 ንኡስ አንቀጽ 5 ህገ መንግስቱ) 2.1.4 የፌደራል መንግስት እና የክልል መንግስታት መሪዎች የስልጣን ዘመን 2.1.5 የፌደራልና የክልል መንግስታት ግንኙነት። የስልጣን ክፍፍል፣የፌደራልና የክልል መንግስት። የፊሲካል ፌደራሊዝምና የሀብት ክፍፍል 2.1.6 የክልል አስተዳደር እና ወሰኖች፤ የአዳዲስ ክልሎች አመሰራረት። የክልል አስተዳደራዊ ወሰኖች 2.1.7 የህግ አውጪው አካል ወይም ፓርላማ አወቃቀርና ሚና 2.1.8 ህገ መንግስትን የመተርጎም ስልጣን 2.1.9 የህገ መንግስት ማሻሻያ ስርአት (አንቀጽ 104ና 105) 2.2 የፖለቲካ ውክልናና የምርጫ ስርአት ጉዳዮች 2.2.1 የሀገሪቱ የምርጫ ስርአት 2.2.2 የመድብለ ፓርቲ ስርአት 2.2.3 የፖለቲካ ፓርቲ አደረጃጀት 2.2.4 የመንግስትና የገዢ ፓርቲ ሚና መለያየት 2.2.5 የምርጫ ክልሎች አወቃቀር 2.2.6 የፖለቲካ ፓርቲዎች የመንግስት ሀብት አጠቃቀም አጀንዳ ቁጥር 3 3. የፌደራል ከተሞች (አዲስ አበባና ድሬዳዋ) 3.1 የአዲስ አበባ ጉዳይ 3.1.1 የአዲስ አበባ ህጋዊ አቋም። አዲስ አበባ ከኦሮሚያ ክልል ጋር ያለው ግንኙነት የአዲስ አበባ ከተማ የበጀት ድርሻ ጉዳይ 3.1.2 የፌደራል ዋና ከተማ ጉዳይ 3.1.3 የአዲስ አበባ ፖሊስና ፍ/ቤት ጉዳይ 3.1.4 የአዲስ አበባ ወሰንና የቦታዎች ስያሜዎች 3.1.5 የአዲስ አበባ የስራ ቋንቋ 3.1.6 የአዲስ አበባ ታሪካዊ ቅርሶች፣አካታችነት ጉዳይ 3.2 የድሬዳዋ ጉዳይ 3.2.1 የድሬዳዋ ህጋዊ አቋም 3.2.2 የድሬዳዋ የወደፊት አስተዳደራዊ ሁኔታ፣የህዝቦቿ ውክልናና ከኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች ጋር ያላት ግንኙነት 3.2.3 የድሬዳዋ በፌደራል መንግስት ውክልና። ድሬዳዋ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚኖራት ውክልና ጉዳይ አጀንዳ ቁጥር 4 4. የሃይማኖት ጉዳዮች፣ታሪካዊ ቅሬታዎች እና እርቅን የሚመለከቱ ጉዳዮች 4.1.1 በሴኪውላሪዝምና በሃይማኖት ነጻነት መካከል ጤናማ ሚዛን መጠበቅ 4.1.2 የሃይማኖት ነጻነትና ገደቦቹ 4.1.3 አናሳ የተከታይ ቁጥር ያላቸው ሃይማኖት ተቋማት ጥበቃ 4.1.4 ከባህል እና ከሃይማኖታዊ እሴቶች ጋር የሚጋጩ ድርጊቶች ጉዳይ 4.2 ታሪካዊ ቅሬታዎችና እርቅን የሚመለከቱ ጉዳዮች 4.2.1 ታሪካዊ መገለል እና ልዩ ተጠቃሚነት 4.2.2 የእርቅና እውቅና የመስጠት ሂደት 4.3 በሃይማኖቶች መካከል ስላለው ግንኙነት እና አብሮ መኖርን በተመለከተ 4.3.1 በሃይማኖቶች መካከል ያሉ ውጥረቶችና መፍትሄዎቻቸው 4.3.2 በሃይማኖቶች መካከል የውይይት እና ምክክር ዘዴዎችን ማጠናከር 4.4 ሃይማኖት በህዝብ ህይወት እና ማህበራዊ ግንኙነቶች ውስጥ ያለውን መስተጋብር በተመለከተ 4.4.1 በህዝብ ተቋማት ውስጥ የሃይማኖት ሚና 4.4.2 የሃይማኖት መድረኮች፣ሚዲያና ህዝባዊ ውይይቶች 4.4.3 የሃይማኖት ተቋማት የድምጽ አጠቃቀም እና የህብረተሰብ መብት አጀንዳ ቁጥር 5 5. የተቋማት ግንባታ፣ የህግ የበላይነትና ሰብአዊ መብቶች 5.1 የሰብአዊ መብቶች 5.1.1 ህገ መንግስታዊ እና ህጋዊ ማእቀፍ ለሰብአዊ መብቶች ጥበቃ 5.1.2 በሀገር ውስጥ የተፈናቀሉ ሰዎች መብቶች 5.1.3 አካል ጉዳት፣ተጋላጭና የተገለሉ ቡድኖች መብቶች 5.1.4 የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ በግጭት እና በጸጥታ ሁኔታዎች ውስጥ 5.1.5 ለሰብአዊ መብት ጥበቃ ተቋማዊ ማእቀፎች የማጠናከር ጉዳይ 5.1.6 በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ (ዳያስፖራ)። የጥምር ዜግነት መብት እውቅና እና ሌሎች ጉዳዮች 5.2 የህግ የበላይነት 5.2.1 የህግ የበላይነት (ህጋዊነት) 5.2.2 በህግ ፊት እኩልነት 5.2.3 ተጠያቂነት 5.2.4 የፍትህ ተደራሽነት 5.3 የተቋማት ግንባታ 5.3.1 የዲሞክራሲያዊ ተቋማት ገለልተኝነት፣ ነጻነትና ተደራሽነት 5.3.2 የፍትህ ተቋማት ነጻነትና ተጠያቂነት 5.3.3 የጸጥታና ደህንነት ተቋማት ነጻነት፣ ገለልተኝነትና አደረጃጀት 5.3.4 የሶስቱ የመንግስት አካላት ሚዛን፣ ነጻነት እና ተጠያቂነት 5.3.5 የመገናኛ ብዙሃን ተቋማዊ ገለልተኝነት፣ ነጻነት እና ተጠያቂነት 5.3.6 የሲቪል ማህበራት ነጻነት፣ ሚናና ተጠያቂነት አጀንዳ ቁጥር 6 6. ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ጉዳዮች 6.1 ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች 6.1.1 የሴቶች ጉዳይ እና ተያይዘው የቀረቡ ጥያቄዎች 6.1.2 የሀብት አስተዳደር እና ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል 6.1.3 የመሬት ይዞታና ባለቤትነት 6.1.4. የህዝብ ቆጠራ ውክልና እና አካታች አስተዳደር 6.1.5 ማህበራዊ አገልግሎቶች (ጤና፣ ትምህርትና የኑሮ ደረጃ) 6.1.6 የሰራተኛ መብቶች እና ፍትሀዊ የስራ ሁኔታ 6.1.7 ዘላቂ ልማትና የአካባቢ ጥበቃ። 6.1.8 የተፈጥሮ ሀብት መብቶችና ጥቅም መጋራት 6.1.9 አካታች ኢኮኖሚ፣ኢንቨስትመንት እና ምርታማነት 6.1.10 ማህበራዊ ደህንነትና የስራ እድል 6.2. የአርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ጉዳይ 6.2.1 የአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ተሳትፎና እኩልነት ተጠቃሚነትን የማሳደግ ጉዳይ 6.2.2 የግብርና ግብአቶች ወቅታዊና ፍትሀዊ ተደራሽነትን በተመለከተ። 6.2.3 የህገ መንግስቱ አንቀጽ 40 ንኡስ አንቀጽ 5ና አንቀጽ 41 ንኡስ አንቀጽ 8 ላይ የተጠቀሰውን 'ዘላን' የሚለውን ስያሜ ማስተካከል 6.2.4 ነጻ የገበያ እድልና የገበያ ትስስር መፍጠር 6.2.5 የአርሶ አደርና አርብቶ አደር ማህበረሰቦች የጋራ መልማትና ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ 6.2.6 የአርብቶ አደሮች የኑሮ ዘይቤያቸውን ያማከለ የልማት ፖሊሲ አጀንዳ ቁጥር 7 7. ሙስና እና መልካም አስተዳደር 7.1 የመልካም አስተዳደር ችግር እና የሙስና ጉዳዮች። 7.2 የጸረ-ሙስና ስርአት ግንባታ 7.3 የመልካም አስተዳደር ስርአት ግንባታ 7.4 ፍትሀዊ ፓብሊክ ሰርቪስ 7.4.1ፍትሀዊና አካታች ፓብሊክ ሰርቪስ 7.4.2 በብቃት ላይ የተመሰረተ የሰው ሀብት አመዳደብ እና ቅጥር አጀንዳ ቁጥር 8 8. ሰላም ግንባታ 8.1የግጭት መንስኤዎች እና አፈታት መንገዶች ግጭቶችንና መሳሪያ ያነሱ አካላትን በሚመለከቱ 8.3 የዘላቂ ሰላም መሰረቶች 8.4 ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎች እውቅና፣ ማጠናከር እና ዘመናዊ ውህደት 8.4.1 ባህላዊ እውቅና እና ህጋዊ ማእቀፍ 8.4.2 የእርቅና ይቅርታ ጉዳይ 8.4.3 የተኩስ አቁም እና የሰላም ስምምነቶች 8.4.4 የሽግግር ፍትህ 8.5. ሃይማኖት ተቋማት ሚና በሰላም ግንባታ ሂደት ውስጥ ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ/ም #tikvahethiopia @subitime
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
በእምነት ተቋም ውስጥ በመግባት ውድመትና ዝርፊያ የፈጸሙ 21 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ። *** አዲስ አበባ፤ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 12:00 ሠዓት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው አያት 49 ቁጥር-2 የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒም) አካባቢ ነው። በተጠቀሰው አካባቢ የሚገኝው ባዶ ቦታ በከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የመንግስተ ሰማይ እንደራሴዎች ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን የተወሰነ ሲሆን ቤተ ክርስቲያኑም ግንባታ አድርጎ አገልግሎት እየሠጠበት ይገኛል። ሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 12:00 ሠዓት ላይ ቁጥራቸው 21 የሆኑ የጋራ መኖሪያ መንደሩ ነዋሪዎች በቡድን በመደራጀትና ቦታው የእኛ ነው በማለት የቤተክርስቲያኑን ግቢ በኃይል ሰብረው በመግባት 10,132000 (አስር ሚሊዮን አንድ መቶ ሰላሳ ሁለት ሺህ) ብር የሚገመት ንብረት የመዝረፍና የማውደም ወንጀል ፈጽመዋል። የወንጀል ድርጊቱ መፈጸም መረጃ የደረሰው የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያም በወንጀሉ ተሳታፊ የሆኑ ግለሠቦች ምንም እንኳን ከአካባቢው ቢሠወሩም ከያሉበት በቁጥጥር ስር ውለው ተገቢው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል። በቀጣይ በወንጀሉ ተሳታፊ ናቸው ያላቸው ግለሠቦች ላይ ክስ እንደሚያስመሠርት የገለጸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መሠል ድርጊቶች የኃይማኖት ግጭት የሚቀሰቅስና ተከባብሮ የኖረውን ህዝብ በጥርጣሬ እንዲታይ የሚያደርግ በመሆኑ ሁሉም ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባውም አሳስቧል። * ዘገባ፦ ረ/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ #addisabeba police @subitime
ገዥው ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል‼ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የክልል ምክር ቤቶች ውጤት ዝርዝር ይፋ ሆኗል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት፣ የክልል ምክር ቤቶች የምርጫ ውጤት ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፦ 📌ኦሮሚያ ክልል፦ ከጠቅላላው 528 ወንበሮች ውስጥ ብልጽግና ፓርቲ 523 ወንበሮችን በማሸነፍ አብላጫነቱን ይዟል። ቀሪዎቹን ወንበሮች የግል ተወዳዳሪዎች (4) እና ኢዜማ (1) አግኝተዋል። (የመራጮች ተሳትፎ፦ 97%) 📌አማራ ክልል፦ከጠቅላላው 277 ወንበሮች ውስጥ ብልጽግና ፓርቲ 257 ወንበሮችን አሸንፏል። ቀሪዎቹ ወንበሮች ለአዴኃን (4)፣ ለኢዜማ (3) እና ለአብን (2) ደርሰዋል። (የመራጮች ተሳትፎ፦ 95%) 📌ሶማሌ ክልል፦ከጠቅላላው 252 ወንበሮች ውስጥ ብልጽግና ፓርቲ 214 ወንበሮችን ሲያሸንፍ፣ ኦብነግ 20 እንዲሁም ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ 13 ወንበሮችን አግኝተዋል። (የመራጮች ተሳትፎ፦ 94%) 📌ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፦ ከጠቅላላው 171 ወንበሮች ውስጥ ብልጽግና ፓርቲ 144 ወንበሮችን አግኝቷል። ሰላም ለኢትዮጵያ 12 እንዲሁም ኢዜማ 10 ወንበሮችን ማሸነፍ ችለዋል። (የመራጮች ተሳትፎ፦ 97%) 📌ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፦ ከጠቅላላው 170 ወንበሮች ውስጥ ብልጽግና ፓርቲ 143 ወንበሮችን ሲወስድ፣ ኢዜማ 12 እንዲሁም ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ 7 ወንበሮችን አሸንፈዋል። *(የመራጮች ተሳትፎ፦ 96%) 📌ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፦ከጠቅላላው 165 ወንበሮች ውስጥ ብልጽግና ፓርቲ 143 ወንበሮችን አግኝቷል። ጉህዲን 16 እንዲሁም ቤህነን 5 ወንበሮችን ይዘዋል። (የመራጮች ተሳትፎ፦ 97%) 📌አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፦ከጠቅላላው 158 ወንበሮች ውስጥ ብልጽግና ፓርቲ 134 ወንበሮችን ሲያሸንፍ፣ ኢዜማ 8 እንዲሁም አንድ ኢትዮጵያ ፓርቲ 4 ወንበሮችን አግኝተዋል። (የመራጮች ተሳትፎ፦ 96%) 📌አፋር ክልል፦ ከጠቅላላው 135 ወንበሮች ውስጥ ብልጽግና ፓርቲ 124 ወንበሮችን አሸንፏል። አኔግ 6 እንዲሁም የአፋር ህዝብ ፓርቲ 3 ወንበሮችን አግኝተዋል። (የመራጮች ተሳትፎ፦ 94%) 📌ሐረሪ ክልል፦ከጠቅላላው 36 ወንበሮች ውስጥ ብልጽግና ፓርቲ 32 ወንበሮችን ሲያሸንፍ፣ ነፃነትና እኩልነት (1) እና ሐዴድር (1) ወንበር አግኝተዋል። (የመራጮች ተሳትፎ፦ 99% @subitime
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи