BIRUK ACADEMY SCHOOL SYSTEM
Статистика- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 11
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 633
- 1/48двое суток
- 725
- 1/72трое суток
- 782
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
በቀጣይ የትምሕርት ዓመታት በተመራጩና በተዋበው የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤታችን ለመማር ወስናችሁ የመጣችሁ ተማሪዎቻችን እንኳንም የትምሕርት ተቋማችን ቤተሰብ ሆናችሁ ለማለት እንወዳለን ። በቀጣይ ቀናትም በተቀሩት ቦታዎችና ክፍሎች ማለትም 10ኛ እና 11ኛ ክፍል ምዝገባ እናከናውናለን። ወላጆችና አሳዳጊዎች የምዝገባ ቀነ-ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት በተቀመጠው ጊዜ እንድትጠቀሙ እንጋብዛለን ።
I am one of the former students who is happy to see that Biruk Academy is stepping up to another level by opening a secondary school. For me, learning at Biruk Academy was a great experience. I watched my teachers put in every effort they had to help me and my friends shine and take responsibility for our academic and behavioral development. It felt like having a family that deeply cared about me and my fellow students and our future. I truly believe that Biruk Academy will reach even greater heights beyond this. (FORMER STUDENT YEAMLAK TESHALE)
без подписи
без подписи
ዉድ የብሩክ አካዳሚ የተማሪ ወላጆች የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን የመፅሀፍ ክፍያ የከፈላቹ ወላጆችን በቅድሚያ እያመሰገንን ያልከፈላቹ ወላጆች ክፍያ ለከፈሉ ተማሪዎች ብቻ መፅሐፍ የሚመጣ መሆኑን አዉቃቹ እስከ ዕሮብ 6/12/2018 ድረስ ብቻ በአካል መጥታችሁ ክፍያ እንድትፈፅሙ ስንል በአክብሮት ለማሳሰብ እንወዳለን። የት/ቤቱ አስተዳደሮች
ውድ የብሩክ አካዳሚ 2ኛ ደረጃ ት/"ቤት ወላጆች የከበረ ሰላምታችን ይድረሳችሁ እያል የተማሪዎች የት/ቤት የደንብ ልብስ ዩኒፎርም ነገ ሰኞ መለካት ስለሚጀመር ከ3:00 ጀምሮ የሚከናወን ይሆናል:: ስለሆነም ወላጆች በሰዓቱ ተማሪዎች እንዲገኙ አድርጉ። እናመሠግናለን የት/ቤቱ ኃላፊዎች
አርሶ አደሩ በበረቱ ውስጥ ያሉት ከብቶች ሌሊቱን ሙሉ ሲረባበሹ እና ሲታመሱ በማደራቸው ምክንያት እንቅልፍ አጣ። ችግሩ ምን እነደሆነ ስላላወቀ፣ መላ እንዲፈልግለት ወደ አንድ አዛውንት ጠቢብ ጎረቤቱ ዘንድ ሄደ። ... ጠቢቡም "ነገ ከብቶችህን ለሁለት በረት ከፍለህ አሳድር" አለው። ባለቤቱም እንደተባለው አደረገ። በነጋታው ሂዶ ሲያይ አንደኛው በረት ሲረበሽ አድሮ፣ ሌላኛው ግን ሙሉ በሙሉ ሰላም ሆኖ አገኘው። .... ጠቢቡ አሁንም "ያንን የረበሸውን በረት መልሰህ ለሁለት ክፈለው" አለው። ባለቤቱም በተመሳሳይ መንገድ ከፈለ ... በመጨረሻም የመጨረሻው ክፋይ አስር ከብቶች ብቻ ሲቀሩ፣ አዛውንቱ "አሁን ሌሊቱን የሚሆነውን ተከታተል፤ ምናልባት ሶስት ወይም አራት ወይፈኖች ይሆናሉ የሚረብሹ አለው።" አሉት። ባለቤቱ ሌሊቱን በጥንቃቄ ሲከታተል፣ ሙሉውን መንጋ ሲያሸብር እና ሲረብሽ የነበረው አንድ ወይፈን ብቻ መሆኑን አወቀ! ወይፈኑ ደንዳና እና ወፍራም ስለነበር ወዲያውኑ ለእርድ ሸጠው፤ መንጋውም ሙሉ በሙሉ ሰላም ሆነ። .... የሚፈጠሩት ትልልቅ ምስቅልቅሎችና ረብሻዎች የብዙ ሰዎች ውጤት ሳይሆኑ፣ ከጀርባ ሆነው ሰላም የሚነሱ ጥቂት አካላት ውጤቶች ናቸው፤ ሰላማችን ሲታወክ አጠቃላይ መንጋውን ወይም ሁነቱን ከመወቀስ ይልቅ፣ ችግሩን በብልሃት እና በትዕግስት ደረጃ በደረጃ በመተንተን ዋናውን የችግር ምንጭ ለይቶ ማወቅና ከህይወታችን ማስወገድ ዘላቂ እረፍትን ያጎናጽፈናል። ማዕደ ጥበብ https://t.me/meadetibeb76
без подписи
без подписи
በሰፈርከው ይሰፈርልሃል ----- ቀበሮው እና ሽመላ ማህበርተኞች ነበሩና ለምሳ ቤቱ ይጋብዘዋል። ቀበሮው ምግቡን (soup) በሰፊ እና ዝርግ ሳህን ያቀርበዋል። ቀበሮው በምላሱ እየላሰ በቀላሉ ሲበላ፣ ሽመላው ግን ረጅም መንቆሩ ሳህኑ ስር ስለማይደርስ ምንም ሳይበላ ቀረ። ቀበሮውም ሽመላውን እያፌዘበትና እየሳቀበት ምሳውን ብቻውን ይጨርሳል። ከጥቂት ቀናት በኋላ ሽመላው ቀበሮውን ለምግብ ቤቱ ይጋብዘዋል። ሽመላው ምግቡን ያቀረበው ረጅም እና ጠባብ አንገት ባለው እቃ (ማሰሮ) ውስጥ ነበር። ሽመላው ረጅም አፉን እቃው ውስጥ አስገብቶ በቀላሉ ሲበላ፣ ቀበሮው ግን አፉ እቃው ውስጥ ሊገባ ስላልቻለ ውጭውን እየላሰ በርሃብ ተመለሰ። 🖊 ለሰው የምታደርገው መልካምም ሆነ ክፉ ነገር ተመልሶ ወደ አንተ ይመጣል። ሰዎችን ስንረዳ ወይም ስናስተናግድ እንደነሱ ፍላጎት እና ሁኔታ እንጂ እንደራሳችን ብቻ ማሰብ የለብንም። በሰፈርከው ልክ ይሰፈርልሃል። Tit for tat! ማዕደ ጥበብ
без подписи
" በወጣትነቱ በተገቢው መንገድ የሕይወት ዝግጅቶቹን የፈፀመ ሰው ስልጠናውን አጠናቆ ፣ ሰይፍና ጋሻውን ታጥቆ ወራሪ ጠላቱን በተጠንቀቅ ከሚጠብቅ ንቁ ወታደር ጋር ይመሳሰላል ። ሁሉቱም በቀላሉ በማይሸነፉበትና በማይወድቁበት ግብአቶች ተሞልተዋልና ። " ከ"የልጅነቴ ወግ -እኔና አባቴ"
ማራኪ ሐሳብ ፦ ▸ በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል። ሰምቶ ማመን፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል። ▸ ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው። በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው። ብልህ ከሆንህ በሰው ከደረሰው ትማራለህ፣ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ። ▸ ዓይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ። ነገ ላይ እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ። ▸ የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ። ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን። ሌሎች መሆን ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው። ▸ ክፋት አይሙቅህ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ። ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት። ▸ በዓላማ ኑር፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ። ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ። ▸ የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን፤ የትላንቱንም አስብ፤ አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና። ▸ ዓለም ዋዣቂ ናት። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም። ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ! (Social Midia)