- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 8
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 225
- 1/48двое суток
- 257
- 1/72трое суток
- 278
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
በቀጣይ የትምሕርት ዓመታት በተመራጩና በተዋበው የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤታችን ለመማር ወስናችሁ የመጣችሁ ተማሪዎቻችን እንኳንም የትምሕርት ተቋማችን ቤተሰብ ሆናችሁ ለማለት እንወዳለን ። በቀጣይ ቀናትም በተቀሩት ቦታዎችና ክፍሎች ማለትም 10ኛ እና 11ኛ ክፍል ምዝገባ እናከናውናለን። ወላጆችና አሳዳጊዎች የምዝገባ ቀነ-ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት በተቀመጠው ጊዜ እንድትጠቀሙ እንጋብዛለን ።
I am one of the former students who is happy to see that Biruk Academy is stepping up to another level by opening a secondary school. For me, learning at Biruk Academy was a great experience. I watched my teachers put in every effort they had to help me and my friends shine and take responsibility for our academic and behavioral development. It felt like having a family that deeply cared about me and my fellow students and our future. I truly believe that Biruk Academy will reach even greater heights beyond this. (FORMER STUDENT YEAMLAK TESHALE)
без подписи
без подписи
አርሶ አደሩ በበረቱ ውስጥ ያሉት ከብቶች ሌሊቱን ሙሉ ሲረባበሹ እና ሲታመሱ በማደራቸው ምክንያት እንቅልፍ አጣ። ችግሩ ምን እነደሆነ ስላላወቀ፣ መላ እንዲፈልግለት ወደ አንድ አዛውንት ጠቢብ ጎረቤቱ ዘንድ ሄደ። ... ጠቢቡም "ነገ ከብቶችህን ለሁለት በረት ከፍለህ አሳድር" አለው። ባለቤቱም እንደተባለው አደረገ። በነጋታው ሂዶ ሲያይ አንደኛው በረት ሲረበሽ አድሮ፣ ሌላኛው ግን ሙሉ በሙሉ ሰላም ሆኖ አገኘው። .... ጠቢቡ አሁንም "ያንን የረበሸውን በረት መልሰህ ለሁለት ክፈለው" አለው። ባለቤቱም በተመሳሳይ መንገድ ከፈለ ... በመጨረሻም የመጨረሻው ክፋይ አስር ከብቶች ብቻ ሲቀሩ፣ አዛውንቱ "አሁን ሌሊቱን የሚሆነውን ተከታተል፤ ምናልባት ሶስት ወይም አራት ወይፈኖች ይሆናሉ የሚረብሹ አለው።" አሉት። ባለቤቱ ሌሊቱን በጥንቃቄ ሲከታተል፣ ሙሉውን መንጋ ሲያሸብር እና ሲረብሽ የነበረው አንድ ወይፈን ብቻ መሆኑን አወቀ! ወይፈኑ ደንዳና እና ወፍራም ስለነበር ወዲያውኑ ለእርድ ሸጠው፤ መንጋውም ሙሉ በሙሉ ሰላም ሆነ። .... የሚፈጠሩት ትልልቅ ምስቅልቅሎችና ረብሻዎች የብዙ ሰዎች ውጤት ሳይሆኑ፣ ከጀርባ ሆነው ሰላም የሚነሱ ጥቂት አካላት ውጤቶች ናቸው፤ ሰላማችን ሲታወክ አጠቃላይ መንጋውን ወይም ሁነቱን ከመወቀስ ይልቅ፣ ችግሩን በብልሃት እና በትዕግስት ደረጃ በደረጃ በመተንተን ዋናውን የችግር ምንጭ ለይቶ ማወቅና ከህይወታችን ማስወገድ ዘላቂ እረፍትን ያጎናጽፈናል። ማዕደ ጥበብ https://t.me/meadetibeb76
በሰፈርከው ይሰፈርልሃል ----- ቀበሮው እና ሽመላ ማህበርተኞች ነበሩና ለምሳ ቤቱ ይጋብዘዋል። ቀበሮው ምግቡን (soup) በሰፊ እና ዝርግ ሳህን ያቀርበዋል። ቀበሮው በምላሱ እየላሰ በቀላሉ ሲበላ፣ ሽመላው ግን ረጅም መንቆሩ ሳህኑ ስር ስለማይደርስ ምንም ሳይበላ ቀረ። ቀበሮውም ሽመላውን እያፌዘበትና እየሳቀበት ምሳውን ብቻውን ይጨርሳል። ከጥቂት ቀናት በኋላ ሽመላው ቀበሮውን ለምግብ ቤቱ ይጋብዘዋል። ሽመላው ምግቡን ያቀረበው ረጅም እና ጠባብ አንገት ባለው እቃ (ማሰሮ) ውስጥ ነበር። ሽመላው ረጅም አፉን እቃው ውስጥ አስገብቶ በቀላሉ ሲበላ፣ ቀበሮው ግን አፉ እቃው ውስጥ ሊገባ ስላልቻለ ውጭውን እየላሰ በርሃብ ተመለሰ። 🖊 ለሰው የምታደርገው መልካምም ሆነ ክፉ ነገር ተመልሶ ወደ አንተ ይመጣል። ሰዎችን ስንረዳ ወይም ስናስተናግድ እንደነሱ ፍላጎት እና ሁኔታ እንጂ እንደራሳችን ብቻ ማሰብ የለብንም። በሰፈርከው ልክ ይሰፈርልሃል። Tit for tat! ማዕደ ጥበብ
без подписи
" በወጣትነቱ በተገቢው መንገድ የሕይወት ዝግጅቶቹን የፈፀመ ሰው ስልጠናውን አጠናቆ ፣ ሰይፍና ጋሻውን ታጥቆ ወራሪ ጠላቱን በተጠንቀቅ ከሚጠብቅ ወታደር ጋር ይመሳሰላል ። ሁሉቱም በቀላሉ በማይሸነፉበትና በማይወድቁበት ግብአቶች ተሞልተዋልና ። " ከ"የልጅነቴ ወግ -እኔና አባቴ"
ማራኪ ሐሳብ ፦ ▸ በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል። ሰምቶ ማመን፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል። ▸ ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው። በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው። ብልህ ከሆንህ በሰው ከደረሰው ትማራለህ፣ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ። ▸ ዓይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ። ነገ ላይ እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ። ▸ የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ። ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን። ሌሎች መሆን ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው። ▸ ክፋት አይሙቅህ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ። ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት። ▸ በዓላማ ኑር፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ። ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ። ▸ የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን፤ የትላንቱንም አስብ፤ አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና። ▸ ዓለም ዋዣቂ ናት። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም። ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ! (Social Midia)
እኛ ብሩክ አካዳሚዎች በተሰማራንበት የትምሕርት ዘርፍ ሰፊ ተሞክሮ አበልፅገናል ። ትውልድን በጠራና በተሻለ የትምሕርት አስተሳሰብ እንዲሁም ስነ-ምግባር መቅረፅም የኖርልነትና የምንኖርለት ተልዕኳችን ሆኗል ። ስለትምሕርት አንዳችም የምንቆጥበውና የምንሰስተው አቅም አይኖረንም ። በዚህም በአለፉት ዓመታት ያስመዘገብናቸው ውጤቶቻችን ምስክሮቻችን ናቸው ። በቀጣይ ዓመትም ብሩክ ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት በተዋበ ምድረ- ግቢና በላቀ አደረጃጀት ለአቃቂ ቃሊቲና አካባቢው የትምሕርት ማሕበረሰብ አማራጭ ሆኖ መጥቷል ። ወላጆችና አሳዳጊዎች ኑና ውብ የሆነውን አዲሱን የልጆቻችሁ ማደጊያና መበልፀጊያን በመጎብኘት ሐሳባችሁን አጋሩ ። ቦታ አቃቂ ቃሊቲ ማረሚያ ፊት ለፊት ከክራውን ሆቴል ጎን ። (ብሩክ አካዳሚ)
የኢትዮጵያ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ሊሻሻል ነው የትምህርት ሚኒስቴር ከብሪቲሽ ካውንስል ጋር በመተባበር የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ጥራትን ለማሻሻልና የመምህራንን ሙያዊ ብቃት ለማጎልበት የተዘጋጀውን የ5 ሚሊዮን ፓውንድ የፕሮጀክት ስምምነት ወደ ተግባር ለማስገባት ቴክኒካል ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን ገለጸ። በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ዳረን ዌልች ---- ፤ ትምህርት ከማንኛውም ኢንቨስትመንት በላይ ዘላቂ ለውጥ የሚያመጣ ቁልፍ ዘርፍ መሆኑን ገልጸው፣ የእንግሊዝ መንግሥት በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፍ የሚደረጉ ማሻሻያዎችን በቀጣይነት እንደሚደግፍ አረጋግጠዋል። አምባሳደሩ በተለይም ተማሪዎች ከአንደኛ ደረጃ ወደ ሁለተኛ ደረጃ በሚሸጋገሩበት ወቅት የትምህርት ቋንቋ መቀየሩ የሚፈጥረውን ጫና ለመቀነስ የቋንቋ ክህሎትን ማጠናከር በልዩ ትኩረት ሊከናወን እንደሚገባ አሳስበዋል። ት/ሚኒስቴር
без подписи
без подписи
የተማሪዎች አለባበስ (ዩኒፎርም) በተማሪዎች አስተሳሰብና ስነልቦና ላይ ትልቅ ተፅዕኖ እንዳለው የዘርፉ ሙያተኞች ይስማሙበታል ። ተማሪዎች የሚወዱትና የወደዱት ፣ ወላጆችም የፈቀዱት ፣ ማራኪ ፣ ዘመናዊና ምቹ የተማሪዎች ዩኒፎርም ማዘጋጀት ለአንድ የትምሕርት ተቋም አንደኛው ተግባር ነው ። በመጨማደድና በመነጫጨት ተማሪዎችን የማያሸማቅቅ ፣ በሚለዋወጥ የአየር ፀባይም ምቾት የማይነሳ ፣ በከለርና በዲዛይንም አብዛኛው ባለድርሻ አካል የፈቀደው እንዲሁም ከትክክለኛነትና ከልከኝነት አኳያም በጥንቃቄ የሚዘጋጅ ዩኑፎርም የተማሪውን ሞራል ይጠብቃል ። የመማር ማስተማሩን ሒደቱፈትንም በመደገፍ ረገድ ሚናው ቀላል አይደለም ። ከዚህ በመነሳት አዲሱ ብሩክ ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት የተማሪዎችን ዩኑፎርም በምረጥና በማስምረጥ ላይ ይገኛል ። ወላጆች ፣ ተማሪዎች ፣ መምሕራንና የተቋሙ ማሕበረሰብ በዚህ ጉዳይ ተሳትፎ እንድታረጉ ይጠበቃል ። " ኑ ! የትምሕርትን ፀሐይ ሙቁ ፤ በቀለም ብርሐኑም ድመቁ ! የብሩክ አካዳሚዎች
እንቅፋት የስራ ፣ የሕይወት የኑሮና የዚህ ዓለም አንደኛው ገፅ ነው ። እንቅፋቱን ፈርተህ ብትቆም --- ለዘላለሙ ቆመህ ትቀራለህ ። መቆም ያፈርሳል ፤ መቆም ሕልውናን ያሳጣል ። እናም ቆመህ እንዳትቀር እንቅፋቱን ነቅለህ ለመጣል ቁረጥ ። ምንአልባት ልትነቅለው ባትችል እንኳ እሱ በማይገኝበት አቅጣጫ ተጓዝ ። አቅጣጫ መቀየርህ ችግር አይደለም ። ዋናው ቁም ነገር አለመቆምህ እንዲሁም ካሰብክበት መድረስህ ነው ። ደግሞም አዲስ አቅጣጫ የአዲስ አስተሳሰብና የአዲስ ጥበብ ውጤት ነው ። (ተመነ)
መልካም ምክር .... " ልጄ ፦ ..... ሁሌም ንቁ መሆንሽን የተረዳ ባላንጣ ድንገት በሚከሰት ለውጥ መሐል ሊጥልሽ ያደባልና .... ለውጥ ሲመጣ የለውጡን አዎንታዊና አሉታዊ ገፅታ በፍጥነት ለመገምገም ሞክሪ ። በሚፈጠሩ ለውጦችም የማትሸበሪ ፣ ከለውጦቹም ጋር በፍጥነት መለዋወጥ የምትችይ ፣ ለውጦቹንም ለበጎ የሕይወት እርምጃ የምትጠቀሚ ንቁና አስተዋይ ሁኚ ። አንዳንዴ ለውጥ ደራሽ ጎርፍ ነው ። ጎርፍ ደግሞ የሚወስደውን አይመርጥም ። የጎርፉ ዱካ ፣ በየት አቅጣጫ መሆኑን ፈጥኖ መተንበይ የቻለ ተጠርጎ ከመወሰድ ይድናል ። የገበያ ግርግር ለሌባ ያመቻልና በጠላትሽ ተገፍትረሽ እንዳትገቢ ከጎርፉ ፍሰት ርቀሽ ቁሚ ። ባልሸፈንሺው ቀዳዳ ፣ ባልጠበቅሺው ሁኔታ ጠላትሽ ቢጥልሽ አትሸበሪ ፤ ብትወድቂም የምትነሺ ፣ ብትሸነፊም ተመልሰሽ የምታሸንፊ ፅኑ ሆነሽ የተሰራሽ ፍጡር መሆንሽን ሳትጠራጠሪ እመኚ ። በአንድ ወቅት በሰሩት ስሕተት የተሸነፉ ፣ ስብራታቸውን ጠግነው ዳግም አሸንፈው ለክብር የበቁ ጀግኖችም እንዳሉ አትርሺ ። .... " (ተመነ)