tgindex
ግጥም እና ጥበብ

ግጥም እና ጥበብ

Статистика

የግጥም መፀሐፎች የግጥም ድምፆች አንዲሁም የተለያዩ የጥበብ ወጥቶች ምቀርብበት ኑ ይቀላቀሉን☺☺☺ እባካቹን ተቀላቀሉን ✋አንዴ🤚 አስተያየት ካላቹ 👇👇👇👇👇👇👇👇 Contact me @Mintesnot_suleyman

Последний пост
25 мая
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 236
+1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 736
20 постов
Вовлечённость
140,5%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • አታውቂም ልንገርሽ ======+===== አንቺ እኳን  ጨክንሽ ላትመጪ ሔደሻል በስለቱ ፍቅርሽ ልቤንም ቆርጠሽዋል። ትመጫለሽ  ብዬ ማዶ ማዶ ባይ አትመጣም ይሉኛል ለመሆን ገላጋይ እውነት ግን አትመጪም? ተስዬ ነበረ ከቤተ መቅደሱ ግዜው ነጎደ አልደረሰኝ መልሱ አንቺን ስላልሰጠኝ እግዜርን መውቀሱ በዝምታው ብዛት ለኔ መመለሱ? ዛሬ ግን ታመምኩኝ መመነን አማረኝ አንቺን መሳይ አየው እግዜር ሊፈትነኝ እመጣለሁ በይኝ መጠበቅ አልደክምም ሄደሽ ቀርተሻል እውነት ግን አመጪም? "ሺ ቢባል ዘመኑ ፍቅሬ........... ቀን፦17/09/2018 ✍ ምንተስኖት ሱሌይማን

  • አይ መክሊት ----+---------- መክሊት ወይስ ገንዘብ ብቻ መልስልኝ ሳታበዛ ሠበብ? ገንዘብ ያለም ገዢ ሁሉን ነገር ከዋኝ ብትታመም አሳክሞ አዳኝ ታድያ መክሊት ነው ምትመኝ? ከችግር በመነሳት ጥያቄዬን መልስልኝ። ነበርኩ ደራሲ እንዲሁም ገጣሚ ብታመም አጣው አሳካሚ። ሕልሞቼን እጆቼ ቢፅፉ እንጀራን ፍለጋ ስደት ሆነ ትርፉ ለምን? ማጣት ስለሆነ ክፉ። ነዋይ ተናግሮታል በሙዚቃ ግጥም እኔ ማን ሆኜ በመክሊቴ ላልም ቅዠት ቢሆንብኝ መክሊቴ ዘወትር ተሸንፊለሁ በፍራንካ ፍቅር አወየው ገንዘብ አወየው ብር። ገጣሚ፦ ምንተስኖት ሱሌይማን ቀን፦06/08/2018

  • 8 дек.1 3202

    без подписи

  • без подписи

  • 21 окт.1 52331

    без подписи

  • без подписи

  • ማረኝ ==== ሰውነኝ ስጋ ለባሽ ሀጥያት ያደለበኝ፤ ባልገድል ባልዘርፍ ሀጥያቴ ባያቀኝ፤ በአምሳልህ ተፈጥሪለው እና ማረኝ። የበደሉኝን ሁሉ ቂምን የማልሽር፤ ዳቢሎስ ተጠግቶኝ የማይገባኝ ፍቅር፤ ሰው የሚያስጠላኝ ብቻያን የምኖር፤ አንተን ለመጠጋት ሀጥያቴ ሚቀፈኝ፤ አቤቱ አማላኬ ሰው ነኝ እና ማረኝ። ✍ምንተስኖት ሡሌይማን መሐመድ ቀን፦26/01/2018

  • ጦርነት ሠለቸን ---------+__ ወጣት ተገደለ                    ከገደል ከዱር እርስ በእርስ እልቂት                  በዚች ቅድስት ሀገር ማንስ ነው ያልሞተ                 በሀሳብ፤በባሩድ የሠው ልጅ ረከሰ                 ኑሮ እንኳን ሲወደድ። ✍ምንተስኖት ሱሌይማን

  • ወይ ፍቅር ==+=== ፀሀይ ገባቸች ብርሀን ተባረረ ይነጋል ይመሻል እየተቀያየረ ልቤ ከእኔ ወጥቶ ከሷ ቤት አደረ። ወይ ፍቅር አምላከ ዓብ ልቤን አይቶ አንቺን ሠጠኝ ጌታ ፀሎቴም ሠምቶ። አለም በጥበብ ቃል ፍቅሬን ብትገለጠው አካሌ በምድር አንቺን ነው ሚመስለው። ወይ ፍቅር በቅዠት ያስዋኛል ሠፊውን ውቂኖስ የጎሠቆለ ጎጆዬን በፍቅሯ ስታድስ ምድር ጨልማብኝ የሚታየኝ ጠፍቶ በፈገግታሽ ብርሀን ታቶኛልና ነግቶ። አዎ ሳቂልኝ ሳቅሽ የኔ ገዳይ ግን ፀለይኩኝ ሌላው እንደኔ አንዳያይ። ዓይኖትሽ ክብል ክብልል ሲሉ ሲስተዋሉ አፍዝዘው ከመንገድ አድርቀው ያስቀራሉ። እምወድሽ የጎደለው ጎኔ ፍቅርሽ በርቶቶብኝ ታምሚለሁ እኔ በቶሎ ነይልኝ አትራቂ ከጎኔ። ✍ምንተስኖት ሡሌየይማን መሀመድ ቀን፦14/10/2017 ዕኩለ ለሊት 6:56

  • ስለ ውበቷ ላድንቅ ----__---------- ዓይና ሲንከባለል ልብን ይነጥቃል ሀር መሳ ፀጉራ የሠው ቀልብ ይስባል የጥርሷ ፈገግታ አይኖችን ያጠፋል የከንፈሯ ውበት ብሉኝ ብሉኝ ይላል። እንኳን የአዳም ዘር በውበት ሚል ዕልም ውበቷ ሴቱንም ሚስደምም ስለውበቷ ላወራ ቃላት ቢያጥርብኝ የጠዋት ፀሀዬ ለኔ ብሪልኝ። ✍ምንተስኖት ሡሌይማን መሐመድ ቀን፦23/10/2017 ከ ምሽቱ 5:20

  • አበደ ተባልኩኝ ------++___ ወፊቷ ባትበርም መልክቴን ልታደርስ አንቺን በመናፈቅ እንዲው ብመላለስ አበደ ተባልኩኝ በፍቅርሽ ከነፈ አንቺን ባያገኝሽ ፎቶሽን ታቀፈ። የኔ እሠይ ልበድ ሰውን ዝም በይ ግና ናፈቀሽኛል ብቅ በይ ከርቀትም ቢሆን አይንሽን እዳይ ሰዎች አፌዙብኝ ብዙ ወሬ አወሩ አንቺን በማፍቀሬ ተቃጥለው አደሩ። አው አብጃለው በፍቅርሽ ወድቄ ሚሰበስብ ጠፍቶ ጨርቄና ሜቄ አው ናፍቀሽኛል በጣም በክፉኛ አንቺን አልማለው እንቅልፍም አልተኛ። አው ወድሻለው ከልብ ካንጀቴ አብጃለው እና ነይ መዳኒቴ። ✍ምንተስኖት ሱሌይማን መሐመድ ቀን፦23/10/2017 ከ ምሽቱ 1:25

  • አንቺ ነሽ ----+---- ፈጣሪ ከሰጠኝ ከሴቶች ለይቶ ከጎደለው ጎኔ አንቺን አበጅቶ የኔ ጠይም የኔ ቸኮሌት ከምንም ከምንም መውደዴን ወደድኩት። አው ተማረኩ በፍቅር ከንፌ እሷ ትራመድ እኔ ተነጥፌ። የኔ አለም የአብራኬ ክፋይ የበረከት ፈለግ ሲሳይ ፈጣሪ የሠጠኝ ከጎኔ ለይ እኔ ወድሻለው ከማንም በላይ። ሰክና እደ አቦል ብና በሳቋ እኔን ስታዝናና የተፈጠርኩ መሠለኝ በዐለም እንደገና። አፍሽ ጣፋጭ ሳቅሽ ገዳይ ናፍቆትሽ ድርብ ስቃይ ማሬ አጥቷል ገላጋይ ልምጣ ወይ ነይ እንድንተያይ። የኔ አለም የኔ ውብ ሴት ዘላለም ፍኪልኝ እነደ መብራት። ✍ምንተስኖት ሱሌይማን መሐመድ ቀን፦22/10/2017 ከምሽቱ 4:35

  • ግዜ አደለም የዋዛ +_+__ የወየበ ከንፈር በጢስ የገረጣ ጎስቋላ አካሉ የመሠለ ቋንጣ ጠረኑን የቀየረ በጣም ሚከረፋ ዘመደ ብዙ ሆኖ ሚደግፈ ጠፋ። በነበረው ሠዓት ቸር ለጋሽ ነበረ ቀን ጣለው እና ይኸው ተሠበረ የከበበው ሁሉ ይርቀው ጀመረ። የሣቀልን ሁሉ ወዳጃችን መስሎን እሱ ሲቸገር ከሌለን ለይ ሠጥተን ባዶ በሆንን ሠአት እሱ ገፈተረን። አይ ግዜ እውነት በደለችው በደግነቱ ለይ ጓዳና አውጥታው ውለታው ነው ነፍጋ ገፍትራ ጣለችው። በዚህ ምስኪ ጫማው የነተበ የኔ እንዳልቸረ ዛሬ ግን ተራበ። እውነት በጨለማ ዘመን ብርሀን ሆኖ ማብራት ግዜው ተቀይሮ ሆኗል መሰለኝ ሀጥያት። እኔንጃ ፈራው ውስጤም ተረበሸ ሀሰት ነገሰና እውነት ተበላሸ። ከዚ ምስኪን ሠው አካሉ ሲያወራ ሞት አይቀርም ነው ሚለው የሠው ልጅ አትፍራ። ሁለት አምላክ አታምልክ ለገንዘብ አትገዛ አተርፋለው ብለሕ ገነዘብ ታጣዋለሕ በዋዛ ከአለማዊ ኑሮ ለፈጠረክ ተገዛ ግዜ አደለም ዋዛ አትሁን ፈዛዛ። ✍ምንተስኖት ሡሌይማን መሐመድ ቀን፦22/10/2017 ከቀኑ 10:45

  • አውቃለው ====== አፍቅሮ ማጣት ቢሆንም ቅጣት በባዶ መጠበቅ ነገ ነዶ ለማለቅ ሀሳቤም ቢዋዥቅ አውቃለው አትንገሪኝ ይሕን መስማት ነው የሠለቸኝ። ተወኝ፣አትተወኝ በይ ተናገሪ አውቃለው ነኝ ያንቺ አፍቃሪ ቢሆንም ፈልጋለው ቁርጥ መልስ ወይ ላፅና ወይ ልሒድ ላልመለስ። አውቃለው ስግብግብነኝ ግን በሌላ አደለም ባንቺ ከመጡብኝ። አውቃለው ደክሞኛል በጫዋታ መሀል ስምሽ ይቀድመኛል። አውቃለው ደሀ ነኝ የደሀ ደሀ አቅሜን ያጣው በፍቅርሽ ማዕበል ስምሽን ተነቅሼ እራሴንም ምጥል። ፍቅርሽ በርትቶ በብዕር መንጎሌ ተተፍቶ አውቃለው አንቺን አንቺን ባለ ተጎድቶ። ከበር ሲመታ ይላል ድው እልልም ልቤ ሲመታ ያወጣል ያንቺን ስም። አውቃለው እወቂ እንዲው ሁሉን ነገር መጠበቅ ማልታክት ያበድኩ ባንቺ ፍቅር። እንዴት በምን ልርሳ በምን ልዳን ከፍቅርሽ አበሳ። አውቃለው ቁርጡን መልሺልኝ ልስማ በይ ተናገሪው አንደበትሽ ልቤን ያድማ። ቀን፦12/07/2017 ✍ምንተስኖት ሡሌይማን መሀመድ

  • ይኸውልሽ ስሚኝ ======+==== የሞት ሞቴን ልፅፍ ከነጩ ሜዳ ለይ ቃላትን ላነጥፍ እየተሽቀዳደምኩ ሀሳበን ሳጣርስ ሁሉም ፈለሱብኝ አጣው የልብ የሚደርስ። በቀለም በብዕር በልኬት በምትር በዘር በክልል በርስት በመንደር አንቺን የሚመስል አጣሁኝ ሚታጠር። አቤት ግዜ አቤት ቃላት፤ መጥበቤ ታወሰኝ እራሴን ታዘብኩት። አቅልሜ ለክቼ ብቆይም ለፍቼ አንቺን እረሳውሽ ከሰፈር ገብቼ። አልገርምም ነጩን አጨክይቼ ነገርን በቁና ስሰፍር ቆይቼ አነሳሴ ቢምር እንደ መቶ ሜትር አቦ ተሸነፍኩ እሩጫ ሳልጀምር። በተቀበዣዠረ በማይሆን ስሜት እፅፋለሁ ብዬ ፁፌንም አጣሁት። አቤት ዳሌ አቤት ደረት አቤት ቁመት አቤት ሠውነት ጀመረኩኝ ጫወታ ከአካል ከጠጉርሽ ኤጭ እንደመንግስት መግለጫ ሁሉን ሸፋፍነሽ አርቴፊሻል በሬ ወለደ ሆንሽ። ዳሌሻን እያልኩኝ ለምርጫ ቦርድ ሪፍረንደም ጣፍኩኝ ፀጉርሽን እያልኩኝ በሠላም ሚኒስተር ሠላሜን አጣሁኝ ከንፈርሽን ብዬ እንደተጠጋሁኝ በሁዳዴ በአብይ ፀም ረከስኩኝ። በጠራራ ፀሀይ እንዲያው ባደባባይ መቀመጫ ኖሮ ብቀመጥ ከላይ ሰው ሲቸገር አሿፊ አታላይ ምሆን ይመስለኛል ሳስበው አንዳንዴ ልክ እንዳልኩሽ ስገልጠው መውደዴ መበልፀግ ነው ብዬ መዛለው ጎራዴ። ✍ምንተስኖት ሱሌይማን መሀመድ ቀን፦12/04/2017

  • https://user281448.psee.ly/6r53qx

  • ወይ ዘንድሮ ና ኑሮ ------------------------- ኑሮ ግን እንዴት ነው? አያኖረን ነው? ወይንስ እያኖርነው ነው። ሁሉም ሠው ተርቧል? ሁሉም ሠውስ ጠግቧል? ሚበላውን አጥቶ ወንድ ልጅ ቢለምን፤ ውስጣችን ጨክኖ ስንቱን አለፍን፤ እኛም ቸግሮን ሰስተን ከልክለን፤ ከተዘጋ ደጅ ማንኳኳት ከቻልን፤ የሁሉን ሠቆቃ መስማት እንችላለን። ✍ምንተስኖት ሡሌይማን ቀን፦09/01/2017 ከምሽቱ 4:45

  • https://youtu.be/q6uMa-JQPVY?si=YoBsD-hTXeXpFabW like Subscribe🙏

  • https://youtu.be/snlDlfwiplg?feature=shared

  • https://youtu.be/q6uMa-JQPVY?si=hFrqlOA_GP7yCvVV