ጥዑም አጭር ልቦለድ እና ግጥም 📚 📚
Статистикаከተለያዩ ደራሲያን የግጥም ወግ እና አጫጭር ልቦለድ በአጠቃላይ የተለያዩ ህይወት ያላቸው የጥበብ ስራዎች ይቀርብበታል ። በተጨማሪ አዲስ የተከፈቱ Channel እና Group ያላቸው በነፃ ሼር አደርጋለሁ For any promotion please contact +251995158041 @GetemeBot
- Последний пост
- 8 дек.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ተደገፊኝ ልደገፍ የዚህ ዓለም ትርክሚክ የሚያልፍ በመደጋገፍ ብሎኝ እንዳበቃ ሃሳቤን ብጥል ሽምበቆ ሆነና ስሩ ውሃ ቀረው በእንጥልጥል https://t.me/Teaumeachirlbwalde
ለምን ትመጫለሽ? ወና መሆን ለምዷል ባይተዋር ነው ሆዴ ትራስ አቅፎ ማደር ለምዶበታል ክንዴ። ገላዬ ቀዝቅዟል ልቤ ተሰቅዟል እንስት ላለማመን ዜሮ ነኝ ስተመን ብትመጭም ከንቱ ነው መመለስሽ ምንም ስታወሪ አልስቅም በእንባሽ አልቆዝምም በድን ነኝ አልድንም ። ለምን ትመጫለሽ? የለሁም በድሮ ሌላ ነኝ ዘንድሮ ግዴ አይደለም ነገ አትገርመኝም ጀንበር ብራና ክረምቱ … ቢዛወር ዓመቱ ጨፍሬ አልደክርም አልመታም አታሞ ዓመት አንድ ቀን ነው ለከሸፈ ታሞ ። ለምን ትመጫለሽ ? መምጣትሽ እንደ ቧልት መመለስሽ ምንም ... ፡ ይህንን እያልኩኝ ብናገር ብገጥምም ስትመጪ ስዳበስ በጣት በመዳፍሽ ያልኩትን ዘንግቼ አዲስ ሰው ሆንኩልሽ። አትሄጂም አይደለ ?🙄 (ሚካኤል አ) ✍️ ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ https://t.me/Teaumeachirlbwalde
ተናገሪ ይሉኛል ለማይሰማው ጆሮችው የውሰጥሸን ይሉኛል ሆዴ ላይቀለው በአንዲት ክብሪት ለኩሰው እሳት ሰውነቴም ለመደው ብርዱም አሰፍራው በእሳቱ የሞቀው ልቤ ቢናገር አላርፍ አለኝ ወገቤ አውሪ ተናገሪ አሉኝ እህ ብለው ላያዳምጡኝ ችግሬን ከቁብ ላይቆጥሩት ብሷቴን አውጥቼ ለሌሊት በንጋት አሸከሙኝ ሁለት ፀፀት አንድም ዝምታ ሌላው ማውራት https://t.me/Teaumeachirlbwalde
እሽሩሩ ፍቅር እሽሩሩ መውደድ እሽሩሩ ፍቅር ሙዚቃው በስሱ በጆሮዬ በኩል ይንቁረቋራል በጀርባዬ ፍራሼ ላይ ተጋድሜ ከማየው ከቤቴ ጣሪያ በላይ አስባለሁ ይሄ ዘፈን ለማን ይሆን ?? ለአንተ ይሆን ሳሚ ?? ከትከሻዬ አልፎ ጡቶቼ ድረስ የደረሰውን በፓይስትራ የተሰራውን ፀጉሬን አንዴ እየፈታሁ መልሼ እየተጐነጐንኩ እንዲሁ በሙዚቃው ስመስጥ አንዴ ደግሞ በራሴው ትዝታ ስዋኝ ቆየው እኔ እሻልሃለሁ አንተ ልጅ አንተ ልጅ አንተ ልጅ አንተ ልጅ ሳሚ እኔ እኳ እሻልህ ነበር በድንገት ከአጠገቤ ያለ ይመስላል ድምፅ አውጥቼ ተናገርሁ በራሴ አፍርኩኝ ከትራሴ አጠገብ የተቀመጠውን ስልኬን አንስቼ ሙዚቃውን ዘጋሁ ይሄ መጃጃል ነው ቆፍጠን በይ እንጂ እያልኩኝ እራሴው በራሴ ለማበረታታት ጣርኩኝ በተኛሁበት ፍራሽ ላይ በለበስኩት አንሷላ ውስጥ የሳሚ ጠረን እንደ ማህተብ ታትሞል ክፍሉ ውስጥ ትዝታው ይገኛል ከሁለት ዓመት በፊት ይሄ ቤት ኦና ነበር ከሁለት ዓመትም በኋላ ኦና ሆኖል ሰው መላመድ መጥፎ ነው ምክንያቱም በትንሿ ጎጇዬ ውስጥ ትዝታ ብቻ ቀርቷል የማይጨበጥ የማይዳሰስ እንደ ጉም የሚተን ትዝታ እኔ እሻልሃለሁ አንተ ልጅ አንተ ልጅ አንተ ልጅ አንተ ልጅ ሙዚቃውን በሆዴ አዜምኩ ሆዴ ውስጥ የበቀለ የትዝታ አዝመራ ነውና https://t.me/Teaumeachirlbwalde ህይወት ይቀጥላል !!!!
👆👆👆👆👆👆👆 ☑️Anycast HDMI Dongle Wifi Display Receiver ⚫️ቲቪዎት ላይ በመሰካት ከስልክዎ፣ ከታብሌትዎና ከኮምፒውተሮ የተለያዩ ቪዲዮዎችን፣ ጌሞችን፣ Presentations እንዱሁም ያሻዎትን ነገር በቲቪዎት ላይ ለማየት የሚረዳ አዲስ ቴክኖሎጂ Product Description: ➡️This wifi display dongle receiver applies to LCD/TV/Projector with HDMI interface sharing picture/video/music of Apple devices, Android smartphones, tablet PCs etc. ⚫️Enjoy your video on the big screen! ⚫️Packaging 1 x AnyCast WiFi Display Dongle 1 x USB Cable 1 x User Manual 🟢ዋጋ: 1900 ብር ስልክ: 📞0995158041 ቀድሞው ይዘዙን free delivery
без подписи
ለማላውቅሽ ለአንቺ . . . የፍቅር ደብዳቤ ከወደዱት ለፍቅረኛዎ ያጋሩ 😊😊 https://t.me/Teaumeachirlbwalde ህይወት ይቀጥላል !!!
"ሞት ሰራቂው ሞተ" በአንድ ወቅት አንድ ሰው የፈጣሪን ተአምር ለመመስከር እሩቅ አገር ለመሔድ ከተሳፋሪዎች ጋር በአውቶብስ ጉዞ ይጀምራል። ጉዞ ከተጀመረ በኋላ ግን መንገድ ላይ አንድ ከተማ ውስጥ ተሳፋሪው በሙሉ ምሳ ለመብላት ይወርዳል። ...ይህም ሰው ወደ አንድ ምግብ ቤት ይሔድና ምሳውን ከበላ በኋላ ለመክፈል ቦርሳውን ሲፈልግ ያጣዋል። መሰረቁንም ከተረዳ በኋላ ለምግብ ቤት ባለቤቱ የደረሰበትን ስርቆት አስረድቶ በነበረበት ከተማ የሚያውቀው ዘመድ ስለነበር ገንዘብ አምጥቶ እንደሚከፍል ተናግሮ ገንዘብ ይዞ መጥቶ ይከፍልና ወደ አውቶብሱ ሲሔድ አውቶብሱ ለካ ጠብቆ ጠብቆ የደረሰበትን ነገር ስላላወቀ ትቶት ሔዷል። "#ይሄ_ፈተና_ነው!_ሰይጣን_እፈር! እኔ እንደሆነ ከአገልግሎት አልቀርም" ብሎ በሌላ አውቶብስ ተሳፍሮ ጉዞ ይጀምራል። በመንገድ ላይም አንድ ትልቅ ገደል ውስጥ የገባ አውቶብስ ያያል። ከተሳፋሪዎቹም የተረፈ ሰው አለመኖሩ ይመለከታል። ደነገጠ። እሱም ተሳፍሮበት የነበረው መሆኑን አዬ። ...በጣም ገርሞት ለካ አውቶብሱ ጥሎኝ የሔደው #ለበጎ_ነው በሚል ፈጣሪውን እያመሠገነ ጉዞ ይጀምራል። ከሚያገለግልበት ቦታም ደርሶ ስለተደረገለት ነገር ለአንድ ሣምንት እዛው ፈጣሪውን ሲያመሰግን ሰንብቶ ወደ ቤቱ ሲመለስ መኖሪያ ቤቱ ድንኳን ተተክሎ ያያል። ደንግጦ "ማን ነው የሞተው?' ብሎ ይጠይቃል። እነርሱም "አንተ" ይሉታል። እርሱም እንዴት እኔማ ይሄው አለሁ አይደል። ይላል። የእርሱን በሕይወት መምጣት የሰሙ ቤተሰቦቹም ማመን አቅቷቸው እየመጡ ይጠመጠሙበታል። ሐዘኑም ወደ ደስታ ይለወጣል። ...ለካ አውቶብሱ ሲገለበጥ አደጋው የከፋ ስለነበር የሰዎቹ ማንነት በመልክ መለየት ስላልተቻለ የሟቾች ኪስ ፓሊስ እየበረበረ ማንነታቸውን መለየት ሲጀምር የሰውየውም የጠፋው ቦርሳ አንዱ የሰረቀውና አንዱ ሟች ክስ ውስጥ ይገኛል። …ፓሊስም በመታወቂያው መሠረት ለሰውየው ቤተሰቦች መርዶ ይነገራል። ለቤተሰቡም በቤ/ክን በተዘጋጀ አዲስ የመቃብር ቦታ ይቀብሩታል። ለካ ሠውየው ነው ተብሎ የተቀበረው #ሌባው ነው። ሁሉም ሠው ይህን ሲሰማ ይገረማል። ከሰወችም መካከል አንዷ ልጁ "የአንተ አዲሱ መቃብር የተቀበረው ሌባው ነው። አንተ መቃብር ላይ ሌባ አይቀበርም። #ይውጣ! "ስትል። ሠውየው አንድ አስገራሚ ነገር ተናገረ " አይሆንም ሌባውን #እወደዋለሁ ሞቴን የወሰደልኝ ሞቴን የሰረቀኝ ባለውለታየ ነው..." ነበር ያለው። ፈጣሪ ሲፈቅድ ለካ ሞትም ይሰረቃል። አይገርምም? "ነገር ሁሉ ለበጎ ነው።'' ሁሌም በመንገዱ ፈጣሪውን ያስቀደመ አያፍርም! ከንባብ ዓለም የቴሌግራም ቻይናል የተወሰደ፦ ሁሌም ማንበብ!📚📚 Share and join us @yenbabalem1 @yenbabalem1
"ከቁራ ጋር ጊዜ ማባከን አያስፈልግም" ንስር የሚደፈረው በቁራ ብቻ ነው ምክንያቱም ቁራ ልኩን አያውቅም ቁራ ከንስሩ ጀርባ ላይ ተቀምጦ ሲያበቃ የንስሩን አንገት ይነክሳል ለማሸነፍ አንገት ለማስደፋት እኔ እበልጣለሁ ለማለት ይሞክራል ነገር ግን ንስሩ ለዚህ ተንኮለኛ መልስ አይሰጥም ከቁራ ጋር አይጣላም ጊዜውን እና ጉልበቱን አያባክንም ነከስኝ ብሎ አይበሳጭም ያሸንፋኛል ብሎ ከቁብ አይቆጥረውም ንስር ይልቁንም በተረጋጋ ትዕግሥት ታጅቦ ክንፎቹን ዘርግቶ በሰማይ ላይ ከፍ ብሎ ከፍ ወዳለው ስፍራ መውጣት ይጀምራል በረራውንም ወደ ከፍታው ቦታ ያደርጋል ቀስ በቀስ ወደ አስበበት ከፍታ ይደርሳል ታዲያ በረራውን በጨመረ ቁጥር ቁራው ለመተንፈስ ይከብደዋል ንስሩ ከፍታውን በጨመረ ቁጥር ያ ተንኮለኛ ቁራም ከንስሩ ጀርባ ላይ ተነጥሎ ይወድቃል ተንኮሉንም እንደ ያዘ ወደ 👇ታች ይወድቃል ከቁራ ጋር ጊዜ ማባከን አያስፈልግም የራሳቸውን የቅዥት አውሎ ንፋስ በአንተ ላይ ለማንዛበብ ይሞክራሉ ዝም ብለህ ወደ ከፍታ ብረር እንጂ ተንኮለኛዎች የሰውን ውድቀት የሚሹ በራሳቸው ጊዜ ቦታ ቦታቸውን ይይዛሉ አዎ እንደ ቁራ እና በቀቀን ሳይሆን እንደ ንስር እንሁን ። ከ ጠዋት መልእክት ከተባለ ከ ቴሌግራም ፔጅ የተገኝ https://t.me/yetewat/28 ያማረ የስራ ቀን ተመኘሁ ጥዑም አጭር ልቦለድ እና ግጥም ቻይናል https://t.me/Teaumeachirlbwalde
ሉሊት ክፍል አንድ ጥዑም አጭር ልቦለድ እና ግጥም ቻይናል https://t.me/Teaumeachirlbwalde ከጥበብ አፍታ ጋር በመተባበር @Artofmub2 ከወደዳችሁት Like and Share አርግሉን
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ውድ የቻይናላችን ተከታዮች እናንተን ያስደስታል ብለን ባሳብነው መልኩ ሉሊት የተሰኝ ተከታታይ አጭር ልቦለድ ከብዙ ድካም ጋር በትረካ ወይም በድምፅ ለማቅረብ ዝግጅታችንን አጠናቀናል ዛሬ ማታ ይጀምራል like and share በማድረግ አብሮነታችሁን አሳዩን ከጥዑም አጭር ልቦለድ እና ግጥም ቻይናል https://t.me/Teaumeachirlbwalde ከጥበብ አፍታ ጋር በመተባበር @Artofmub2 ህይወት ይቀጥላል !!! መልካም እለተ ሰንበት
" ከለሊቱ ስድስት ስዓት ከምናምን የፃፍኩልሽ ግጥም " ገጣሚ ዝምተኛው ፀሃፊ @belay_HI አንባቢ ሙባ @Artofmub2 ከ ጥዑመ አጭር ልቦለድ እና ግጥም ቻይናል https://t.me/Teaumeachirlbwalde መልካም የደመራ በዓል ከወደዱት ለወዳጇ ያጋሩ
ከሌሊቱ ስድስት ሰአት ከምናምን የፃፍሁልሽ ግጥም አንች የኔ ኮከብ አንች የእኔ ጨረቃ ሌሊት ስድስት ሰአት ከ45 ደቂቃ ድንገት ገድ ቀንቶኝ ከእንቅልፌ ስነቃ ከበ'ሬ ደጃፍ ላይ ሰማሁኝ ሙዚቃ ምን ይላል መሰለሽ "መሄዱንስ ሂጂ አልከለክልሽም በሴቱም ሴት አለ እናቴ አይደለሽም እህቴ አይደለሽም" ይህ ገራሚ ሀሳብ ይህ ጥዑም ሙዚቃ በደረቀው ሌሊት ቤቴን እና ልቤን ደጋግሞ ሲደቃ ላዜምልሽ ሳስብ ድምፅህ ውሻንም አይጠራ ብለሽኛል ለካ ያኔ ቃልሽን ባከብርም ከቤቴ ሳትወጭ ዛሬ አብረሽኝ የለሽ ይኧው አዜምሁልሽ ምናባሽ ታመጭ መሄዱንስ ሂጂ አልከለክልሽም በሴቱም ሴት አለ እናቴ አይደለሽም እህቴ አይደለሽም" (በዜማ ነው) ይህ ጥዑም ሙዚቃ ወደውስጤ ገብቶ ቀርጥፎ ሲበላኝ የት እንደሰማሁት ብዙም ትዝ የማይለኝ "ገደል ግቢ" የሚል ግጥም አስታወሰኝ ይህንን ቃል ስልሽ ገደል ግቢ ይላል ብለሽ አታስቢ ክፋሽን አልስማ ገደልስ አትግቢ ግን በዚህ ድቅድቅ ምሽት በጥቁሩ ጨለማ የጉዳቴ መጠን ለእግዜር እንዲሰማ ሳጥናኤል በጆሮሽ ነግቶልሻል ተነሽ በሚል ሹክ ብሎሽ ቀውሶ ሰአትሽ የነጋልሽ መስሎሽ በፍጥነት ሩጭ ከቤትሽ እርቀሽ ከዛ ከአውላላ ሜዳ ላይ አስር ጅብ ይክበብሽ መኖር ግራ ይግባሽ ጭንቀትን ተጎንጭ መሄጃው ጠፍቶብሽ በቆምሽበት ቦታ ደጋግመሽ እርገጭ የእንባ ሳግ ይነቅሽ በለቅሶ ፍረጭ የሲኦልን ፍዳ ከሰማይ ሳትሄጅ ከዚህ ምድር ጠጭ እንዲህ ከሆንሽ ሗላ የእግዜር ምህረት ደርሶ ከዚህ ጭንቀት ውጭ እንዲህም የምልሽ የአንችን ክፉ ማየት ስለማልውድ እንጅ እንደስራሽማ ገደል መግባት ቀርቶ አስር ጅብ ቢበላሽ ያንስብሻል ላንች ✍ ዝምተኛው ፀሀፊ @belay_HI
# ኪነ ጥበባችን ያሳመመው ፍቅር # ዋንኞቹ ስለ ፍቅር የሚሰብኩን ሙዚቃ ፣ ልቦለድ ፣ ፊልም ድራማ የመሳሰሉት ናቸዉ እነዚህ የኪነ ጥበብ ዘርፎች ፍቅርን እንዴት ነው የገለፁት ? " እኔ እወድሃለሁ የአንተ ፍቅር የታለ ...? አንዳንድ ቀንማ ይሻላል ውሽማ .... ብትበድለኝም አፈቅርሃለሁ .... አንቺ ባትታመኝም እኔ እታመንሻለሁ .... ለፍቅር ተጓዳሁ ..... በፍቅርሽ ተቃጠልኩ አይነት ሙዚቃዎች ምንድነው ስለ ፍቅር የሚነግሩን አሁን 13 ወይም 14 ዓመት የሆነው ልጅ መጀመሪያ ስለ ተቃራኒ ፆታ ፍቅር ማን ነገረው ? ማንነቱን ማን ስጠው ፊልም ፣ ዘፈን፣ ግጥም ፣ ድራማ ፣ የቴሌቪዥን ማስታወቂያ ፣ ልቦለድ ድርሰቶች እነዚህ ናችው እነዚህን እያየ አድጎ ነው ፍቅር ማለት ይሄ ነው ለማለት የቻለው ፍቅርን በትምህርት ቤት አይማረውም ወላጆችም ብዙዉን ጊዜ ( በዚህ እድሜው ስለ ወንድ እና ሴት ፍቅር ሊወራለት አይገባም ስለሚሉ ሊሆን ይችላል ) አይነግሩትም ። ፍቅር አፍ አውጥቶ ሲናገር የምናየው ኪነ ጥበቡ ላይ ነው ግን እንዴት ነው የሚናገረው? እንዴት ነው እንዲናገር የተፈለገው ? ሰለ ምን አይነቱ ፍቅር ነው እንዲናገር የተፈለገው ? " ከአንቺ ጋር አድሬ ሲነጋ ልሙት " የሚል ዘፈን ምንድነው ለአድማጭ በተለይም ለታዳጊው አድማጭ የሚያስተላልፈው መልእክት ? ከእሷ ጋር አድሮ ሲነጋ መሞትን ምን አመጣው ገጣሚው የሀሳቡን መነሻ እና ሊያስተላልፈው የፈለገው መልእክት ምንድን ይሁን ፍቅር የአንድ ለሊት አብሮ የማደር ጉዳይ ነው ? አይደለም ሊሆንም አይገባም በሃይማኖት ፍቅር ዘላለማዊ እንደሆነ ነው እየነገረን ያደግነው ሙዚቃው ደግሞ ከዘላለማዊነት አውጥቶ የአንድ ለሊት ጉዳይ ሲያደርገው ይታያሉ ። የአንድ ለሊት ጉዳይስ ፍቅር ነው ወሲብ ? ወሲብን ነው ፍቅር ያልነው እንዲህ ያሉ የተተረማመሱ አገላለጾች ( ከያኒያኑ ምንም አስበው ይስሩት ) ተደራሲው ጋር መንገዳቸውን ስተው ይደርሳሉ ። ከዛ ፍቅር ማለት ይሄ ነው የሚል ትርጉም ይስጣሉ ። " ኪነ ጥበብ የገሃዱ ዓለም ነፀብራቅ ነው ። "ይባላል እኔ በዚህ ሀሳብ አልስማማም ገሃዱ ዓለም አስሱም ገስሱም ነው ። ኪነጥበብ ግን ከአስሱም ከገሰሱም የተመረጠ እና የተጠነፈፈ ታሪክ ነው ብዬ አምናለሁ ። ምን ሆኛለሁ ከሚለው ከትዕግስት ዋልተንጉስ እና ከ ዶ/ር ቴዎ ድሮስ ተ/ አረጋይ የተወስደ ... ከገፅ 35 - 36 https://t.me/Teaumeachirlbwalde
አሁን online ላላቹ የ 200 ብር ካርድ ሊለቀቅ ነው
ተው ግድየለህም ተው ቆንጆ ማሬ እናቱ ከአፍ አይውጣ ቃላቱ ተው ፀዳልን አታጎናፀፈኝሳቄን አትለካው ጨረቃ ወርዝታ በላያት ከቶ በአንተ አፍ ሰትነገር እጥፍ ድርብ ትሆናለች ውበቷ ተባዝቶ ተው ግድየለም ተው ቆንጆ ማሬ እናቱ ከአፍ አይውጣ ቃላቱ ትዝ ይልክ እንደሆነ ታሰታውስ ከሆነ የሆነ ቀን ላይ የቦዘዙ አይኖችህን ከአልጋ ውሰጥ አሳርፈክ ማር እኳ ነሸ ብትለኝ የገዛ ገላዬ ማር ማር አለኝ ተው ግድየለህም ተው ቆንጆ ማሬ እናቱ ከአፍ አይውጣ ቃላቱ ደግሞም በተዋበ ቀን አንተን እያሰበኩ አንተን እያለምኩ ሰግፈው መንገዱን ድንጋይ እያሞቀ ጫቱን ከጉያው እየሽሽገ "እናቱ" ቢለኝ በግልምጫ ባነሰው እሱም ተሽሸገ አንተ ግን ግና አ ያልክ እንደሆን ከልቤ ሰር ታፍልቃለህ ደስታን ትዘራለህ ሀሴትን ተው ግድ የለህም ተው ቆንጆ ማሬ እናቱ ከአፍ አይውጣ ቃላቱ አቤት ፊደላቱ አቤት ቀለማቱ በአንተ አፍ ሲጠራ ማማሩ ምንድነው አንደበትምን ይሆን ሚስጥሩ ፍቅር ነው ካባው ሞገሰክ ከአንተ ምደርበው ተው ግድየለህም ተው ቆንጆ ማሬ እናቱ ከአፍ አይውጣ ቃላቱ ..... https://t.me/Teaumeachirlbwalde
ከተስማኝ ማህደር ✍ አንዳንዴ .... ስውን በጥቅም ሳይሆን እንዲሁ የወደድንበት ጊዜ ይናፍቃል ። አንዳንዴ ...... መብራት ሲጠፋ የሚነግረን የአባታችን የድሮ ታሪክ ትዝ ይላል ። አንዳንዴ ..... እንደአሁኑ በስማርት ስልክ ሳይሆን በሳምንት የተወሰነ ቀን የምናያቸው ገመና እና ሰውለሰው ድራማ ለማየት የነበረን ጉጉት እርሱም ትዝታ ነውይሄም እኳ ይናፍቃል አዎ ለድብርት ሳይሆን ጊዜ ማሳለፊያ እውቀት ማግኛ ብለን ያነበብናችው ልቦለዶች በልባችን አሉ ከምንም ነገር በላይ የእናት ድምጽ ይናፍቃል ከዉጪ ወጥታችሁ ስትገቡ የምትሰሙት ስላም እረፍት ያለው ድምጽ የእናት ድምፅ ይናፍቃል ። እረጅም እድሜ ለእናቶች 🙏🙏
ቤተስብ ጀማሪ ነች አበረታቱ 👇👇👇
አሜን በል ልመርቅህ ከፍ ከፍ በል ወደ ላይ ደመወዝ ይጨመር እላይ በላይ እግርህ በገባህበት cv ይቀበሉ ጓረቤትህ ሁሉ እልል ይበሉ አሜን በይ ልመርቅሽ ያስበስሽው ተሳክቶ ሁሉ ስምሮልሽ ይጭስ ይናደድ የድሮ ባልሽ ደግሞም ልመርቅሽ በትምህርቱ በስራ የተትረፈረፈ ይሁን ህይወትሽ ለሌላው የተረፈ አሜን በሉ ልመርቃችሁ ፍቅረኛ ያጣችሁ ፍቅረኛ አግኝታችሁ ስራተኞቹ በስራው ተደስታችሁ የተጣላ ተታርቆ የታመመ ድኖ ሀዘን ርቆ ሁሉም ተደስቶ ገበሬው በእህሉ መሬቱ በጠል እረክቶ እድሜ ለፍቅር ለለውጥ ሆኖልን ለዛሬው ዓመት በስላም ያድርስን መልካም አዲስ ዓመት ጥዑም አጭር ልቦለድ እና ግጥም ቻይናል ቻይናላችን ዛሬ ሶስተኛ ዓመቱን🧭 ይዟል እንኳን ደስ አለን 😋🙏🙏 ቤተስብ እንደ ሁሌም በ 2018 'ም ህይወት ይቀጥላል !!! https://t.me/Teaumeachirlbwalde
መልካም አዲስ ዓመት ቤተስብ በዓሉን የፍቅር ያድርግልን 🙏🙏