tgindex
Tikvah-Education

📚 ይህ የቲክቫህ ኢዱኬሽን ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም ትምህርታዊ መረጃዎች የሚያገኙበት መድረክ ነው ። በዚህ ቻናል ትክክለኛ የትምህርት መረጃዎች እና ወቅታዊ ክስተቶች ይዳሰሱበታል ።

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
9
Всего постов
75
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 780
+1 Са 4 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
—
 
Месяц
—
 
Просмотров на пост
280
40 постов
Вовлечённость
15,7%
к подписчикам
Постов в день
1,3
всогО 75
УпОПинаниК
0
канаНОв
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
180
1/48двое суток
206
1/72трое суток
222

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • йоС пОдписи

  • йоС пОдписи

  • йоС пОдписи

  • йоС пОдписи

  • #ተጨማሪ   ከነሐሴ 13-15/2018 ዓ.ም በሚሰጠው የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ወቅት ተፈታኞች የብሔራዊ መታወቂያ (National ID) እንዲሁም ሲስተሙ የሚሰጠውን QR Code ያለው የፈተና መግቢያ (ስሊፕ) ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡ ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች፣ ምንም አይነት ማጣቀሻዎች እንዲሁም ባዶ ወረቀቶች፣ ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ወደ መፈተኛ ክፍል ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡ በፈተናው ወቅት ተመዛኞች በሁለቱም ክፍለ-ጊዜ (ጠዋት እና ከሰዓት) የፈተና ክፍሉን ለቀው ከመውጣታቸው በፊት አቴንዳንስ ላይ መፈረም ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተመዛኞች የመረጣችሁትን የፈተና ማዕከል ለማየት፦ https://t.me/M0H_EThiopia/3191 ተመዛኞች ስማችሁ ከተጠቀሰበት የመፈተኛ ጣቢያ (ተቋም) ውጪ በፍጹም ፈተናውን መውሰድ እንደማይፈቀድላችሁ ተገልጿል፡፡   @tikvah_edu

  • йоС пОдписи

  • #AREB የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2019 የትምህርት ዘመን በክልሉ በሚገኙ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ለሚገቡ ተማሪዎች የምዝገባ ጥሪ አድርጓል፡፡ የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ አዳሪ ትምህርት ቤት - ደሴ፣ የክቡር ዶ/ር ሐዲስ አለማየሁ - ደብረማርቆስ፣ እንዲሁም አዲስ የተገነቡ የደብረ ታቦር እና የሰቆጣ አዳሪ ትምህርት ቤቶች አዲስ ተማሪዎችን ተቀብለው ለማስተማር ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በመሆኑም በ2018 ዓ.ም በክልሉ ከሚገኙ የመንግሥት እንዲሁም የግል ትምህርት ቤቶች ተምራችሁ፣ ክልላዊ ፈተና የወሰዳችሁና የተቀመጡ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተማሪዎች በትምህርት ቤቶቹ ምዝገባ እንድታደርጉ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ጥሪ አስተላልፏል፡፡ መሰፈርቶች ● የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና አማካይ ውጤት ለሴቶች 80% እና ለወንዶች 82% ● የ7ኛ እና የ8ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት አማካይ ውጤት ለሴቶች 83% እና ለወንዶች 85% የምዝገባ ጊዜ 👇 ከነሐሴ 06-15/2018 ዓ.ም የምዝገባ ቦታ 👇 በአማራ ክልል በሚገኙ በሁሉም የወረዳ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤቶች የመግቢያ ፈተና በዞን ዋና ከተሞች ነሐሴ 25/ 2018 ዓ.ም ይሰጣል ተብሏል፡፡ (ተጨማሪ መረጃ ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ፡፡) @tikvah_edu

  • ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ባለሙያዎችን ሙያዊ አቅም ለማሳደግ የሚረዱ ተንቀሳቃሽ የአይሲቲ ቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን ለሚመለከታቸው ተቋማት ማስረከቡን ገልጿል። ሚኒስቴሩ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚሠሩ መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎችን ሙያዊ አቅም ለማሳደግ የሚረዳ የአይሲቲ ቴክኖሎጂ ፕሮጀክትን ወደ ተግባር ለማስገባት እየሠራ መሆኑን በሚኒስቴሩ በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት ተ/መሪ ሼል አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሎ አሰግድ ምሬሳ ገልፀዋል። ፕሮጀክቱ ከተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (UNESCO) እና ከጃፓን መንግሥት ጋር በመተባበር የሚተገበር ነው፡፡ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች 35 የሚደርሱ የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች እና በመምህራን ትምህርት ላይ ትኩረት አድርገው እየሠሩ ያሉ አምስት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች መሆናቸው ተጠቁሟል። @tikvah_edu

  • ትምህርት ሚኒስቴር በፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ9ኛ እና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ በነፃ ማስተማር ይፈልጋል። 🔔 ሙሉ የትምህርት ክፍያ ሽፋን እንዲሁም ነፃ የመኝታ እና የምግብ አገልግሎት በነፃ ትምህርት ዕድሉ ይሰጣል፡፡ 9ኛ ክፍል ብቻ የሚቀበሉ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ● አርባ ምንጭ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ● ድሬዳዋ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ● አሶሳ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ● ባህር ዳር ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት 9ኛ እና 10ኛ ክፍል የሚቀበሉ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ● ቡኢ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ● ጅግጅጋ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ● ጋምቤላ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ● ወሊሶ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ● ቦንጋ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ለ9ኛ ክፍል የመመዝገቢያ መስፈርቶች ● በ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና 85 እና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች ● በሂሳብ እና እንግሊዝኛ የትምህርት ዓይነቶች 80 እና በላይያመጣ/ያመጣች ● ጥሩ ስነ-ምግባር ያለው/ያላት ለ10ኛ ክፍል የመመዝገቢያ መስፈርቶች ● በ2017 ዓ.ም በ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና 70 እና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች ● በ9ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት 95 እና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች ● በሂሳብ እና እንግሊዝኛ የትምህርት ዓይነት 80 እና በላይ ያመጣ/ያመጣች ● ጥሩ ስነ-ምግባር ያለው/ያላት ኦንላይን ይመዝገቡ 👇 https://sbs.moe.gov.et/apply የመመዝገቢያ ጊዜ 👇 እስከ ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም ለፈተና የሚቀርቡ ተማሪዎች ዝርዝር እና የፈተና ጊዜ ወደፊት ይገለፃል፡፡ የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ ተማሪዎች በሚደቡበት ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ለመማር ፈቃደኛ የሆኑ መሆን አለባቸው ተብሏል፡፡ @tikvah_edu

  • #ጥቆማ #EthiopianAirlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ ብቁ የሆኑ ተለማማጅ የበረራ አስተናጋጅ (Trainee Cabin Crew) አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡ ➤ የሥራ መደብ፦ ET SPONSORED Trainee Cabin Crew ➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ሰርተፊኬት ቢያንስ 200 ውጤት ያለው/ያላት ➤ ዕድሜ፦ ከ 21-30 ➤ ቁመት፦ 1.58ሜ እና በላይ ለሴት (የክንድ ርዝማኔ 212ሴ.ሜ. ፤ 1.70ሜ እና በላይ ለወንድ ➤ ክብደት፦ ከቁመት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ➤ ቋንቋ፦ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ደረጃ III (ሌሎች ቋንቋዎች መቻልም ጥሩ ነው)   የምዝገባ ቀናት፦ ከነሐሴ 04-08/2018 ዓ.ም የምዝገባ ቦታዎች፦ ➫ አዲስ አበባ፦ በኦንላይን (የማመልከቻ ሊንክ በምዝገባ ቀናት አክቲቭ ይሆናል) ➫ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ አዳማ ➫ አምቦ ዩኒቨርሲቲ፣ አምቦ ➫ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ አርባ ምንጭ ➫ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ፣ አሶሳ ➫ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ባህር ዳር ➫ ወሎ ዩኒቨርሲቲ፣ ደሴ ➫ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ፣ ድሬዳዋ ➫ ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ፣ ጋምቤላ ➫ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ ጎንደር ➫ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ፣ ሐረር ካምፓስ፣ ሐረር ➫ ሀዋሳ ኤርፖርት፣ ሀዋሳ ➫ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅግጅጋ ➫ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅማ ➫ መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ፣ ሮቤ ➫ መቐለ ዩኒቨርሲቲ፣ መቐለ ➫ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ፣ ነቀምቴ ➫ ሰመል ዩኒቨርሲቲ፣ ሰመል ➫ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፣ ወልቂጤ ➫ ቦረና ዩኒቨርሲቲ፣ ያቤሎ ➫ ነገሌ ቦረና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣ ነገሌ 🔔 ምዝገባ ሲያደርጉ የአስፈላጊ ሰነዶችዎንና የትምህርት ማስረጃዎችዎን (የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ካርድ፣ የልደት ሰርተፊኬት፣ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት፣ የቀበሌ መታወቂያ) ዋናውንና ኮፒውን መያዝ ይጠበቅብዎታል፡፡ ከላይ የተገለፁ መስፈርቶችን ማሟላትዎን ያረጋግጡ፡፡ በሐሰተኛ መረጃ ለመመዝገብ ከሞከሩ ወዲያውኑ ከቅጥር ሂደቱ የሚወገዱ ይሆናል፡፡ @tikvah_edu

  • #ጥቆማ እንግሊዝኛ ቋንቋን ያለምንም ክፍያ በማንኛውም ጊዜ እና በየትኛውም ቦታ ሆነው ይማሩ! ትምህርት ሚኒስቴር ያዘጋጀውን የመምህራን እና የተማሪዎችን እንግሊዘኛ ቋንቋ ለማሻሻል የሚያግዝ ፖርታል ይጠቀሙ፡፡ ፖርታሉ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ ለሁሉም የክፍል ደረጃዎች የተዘጋጀ ነው። በቀላሉ ለመረዳት በሚቻሉ በድምፅ፣ በፅሁፍ እና በምስል በተቀናበሩ ማስተማሪያዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋን ለማሻሻል የሚያስችል ትምህርት ያገኛሉ። ወደ ፖርታሉ ለመግባት👇 http://learn-english.moe.gov.et ፖርታሉን ለመጠቀም ኢንተርኔት የሚያስፈልግ ቢሆንም ገንዘብ የማይቆርጥ ሲሆን፤ በስማርት ስልክ፣ ስማርት ቴሌቪዥን፣ በታብሌት እና በኮምፒውተር በማንኛውም የዌብ መፈለጊያ ላይ ይሰራል፡፡ @tikvah_edu

  • #NGAT   አገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ እስከ ረቡዕ ሐምሌ 29/2018 ዓ.ም መከናወኑ ይታወቃል፡፡     የፈተና ጣቢያ ምርጫችሁን Update እያደረጋችሁ ያላችሁ ተፈታኞች፣ በፈተና ሲስተሙ ላይ የሚገኝ የትኛውንም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ በፈተና ማዕከልነት መምረጥ እንደምትችሉ ተገልጿል፡፡   🔔 የተመዝጋቢዎች Username፣ Password እና Entrance Ticket የ GAT ፈተና ከሚሰጥበት ሁለት ወይም ሦስት ቀናት ቀደም ብሎ በእያንዳንዳችሁ Dashboard ላይ የሚመጣላችሁ ይሆናል፡፡ በመሆኑም ዳሽቦርዳችሁን ቶሎቶሎ ቼክ እንድታደርጉ ተብሏል፡፡ @tikvah_edu

  • #ጥቆማ   በ2019 የትምህርት ዘመን ወደ ሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (SIT) ለመግባት ያመልክቱ!   የማመልከቻ ጊዜው እስከ ነሐሴ 24/2018 ዓ.ም መራዘሙን ኢንስቲትዩቱ ገልጿል።   የትምህርት መስኮች ● Electrical Engineering ● Biotechnology ● Space Science ● Mechanical Engineering ● AI ● Nuclear engineering ያመልክቱ 👇 https://sitedu.info/admission/application መስፈርቶች ● የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል አማካኝ ውጤት 90% ● የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት 95 ፐርሰንታይል ● ከ500-700 ቃላት የግል መግለጫ መጻፍ ይኖርብዎታል ● የድጋፍ ደብዳቤ ከ2ኛ ደረጃ መምህርዎ/ሜንተርዎ ማጻፍ ● የማኅበረሰብ በጎ አገልግሎት የሰጡት ካለ ቢያይዙ ጥሩ ነው   @tikvah_edu

  • йоС пОдписи

  • йоС пОдписи

  • йоС пОдписи

  • #ጾመ_ማርያም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘኣኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በኦርቶዶክሳውያን ልዩ ትኩረት ከሚሰጠው አፅዋማት አንዱ ጾመ ፍልሰታ መግባቱን ተከትሎ ያስተላለፉት መልዕክት : ፦ " በዚህ የጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሱባዔ የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሉትን በማስታረቅ፣ የታመሙትንና የታሰሩትን በመጠየቅ፣ ቅዱስ ቊርባንን በመቀበልና ለኃጢኣታችን የንሥሐ ሥርየትን በመለመን ሱባዔውን ልናሳልፍ ይገባል፡፡ ... በሀገራችንም ሆነ በዓለም ዙሪያ ከባድ ስጋት የሆነው የፍጥረት ኣውዳሚ ጦርነትን በመለኮታዊ ጥበቡና ሥልጣኑ እንዲያስቆምልን በቅን ልቡና፣ በትሑት ሰብእና ሆነን እግዚአብሔርን በዚህ ሱባዔ እንድንጠይቀው ኣደራ ጭምር ኣባታዊ መልክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን። " (የቅዱስነታቸው ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል) ©️ Tikvah ethiopia @tikvah_edu

  • የፈተና ጣቢያ መረጣ ዛሬ ይጠናቀቃል! ከነሐሴ 13-15/2018 ዓ.ም ለሚሰጠው የጤና ሙያ ተመራቂዎች የብቃት ምዘና ፈተና፣ የተመዛኞች የፈተና ጣቢያ ምርጫ ማድረጊያ ጊዜ ዛሬ ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡ በመሆኑም ስማችሁን ከፋይዳ ቁጥር ጋር አያይዛችሁ በመጠባበቅ ላይ የምትገኙ የጤና ሙያ ተመራቂ ተመዛኞች https://hple.moh.gov.et/ ላይ በመግባት Fayda and Password በማስገባት በቀሩት ሰዓታት የፈተና ጣቢያ ምርጫ አድርጉ፡፡ @tikvah_edu

  • йоС пОдписи

  • የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 ዓ.ም የ8ኛ እና የ6ኛ ክፍል ውጤቶች ይፋ ተደርገዋል፡፡ በክልሉ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን፤ ድጋፍ ለሚሹ ደግሞ 48 የማለፊያ ነጥብ እንደሆነ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አብዮት ደምሴ ገልፀዋል፡፡ በዚህም በክልሉ የ8ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ 78,203 ተማሪዎች መካከል 47,307 ተማሪዎች (60.4%) የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል፡፡   540 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ማሳፍ ሲችሉ፤ 155 ትምህርቶች ደግሞ ምንም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ኃላፊው ጠቁመዋል። በተመሳሳይ በክልሉ የ6ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ 126,224 ተማሪዎች መካከል 110,566 ተማሪዎች (63.8%) የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል፡፡   የ6ኛ ክፍል ፈተና ያስፈተኑ 476 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ሲያሳልፉ፤ 81 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ አላሳለፉም ብለዋል። የ8ኛ ክፍል ውጤት ለማየት 👇 https://se.ministry.et/#/result የ6ኛ ክፍል ውጤት ለማየት 👇 https://se6.ministry.et/#/result    @tikvah_edu