tgindex
የሱና ኡስታዞች ትምህርት ብቻ የምላክበት

የሱና ኡስታዞች ትምህርት ብቻ የምላክበት

Статистика
@Twehid12арабский

فاعلم أن العبادة لا تسمى عبادة إلا مع التوحيد، كما أن الصلاة لا تسمى صلاة إلا مع الطهارة. فإذا دخل الشرك في العبادة فسدت، كالحدث إذا دخل في الطهارة. ( القواعد الأربع: ٧) ✍️ ابو رسلان حسين بن محمد

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
8
Всего постов
24
Тип
открытый
Язык
арабский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 391
+1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
88
24 постов
Вовлечённость
6,3%
к подписчикам
Постов в день
1,1
всего 24
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
29
1/48двое суток
33
1/72трое суток
35

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 13 авг.32из IbnuMunewor

    السلام عليكم ورحمة الله وبركاتة ታላቅ የሙሀደራና የኒያ (የገቢ ማሰባሰቢያ) ፕሮግራም! ​እነሆ የፊታችን ጁመዓ ምሽት 3:00 በወለኔ ወረዳ ቤደር ከተማ ለሚገነባው የአል-ሂዳያ መርከዝ ደማቅ የሙሀደራ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል። እርሶም ባሉበት ሆነው በኦንላይን በመከታተል የዚህ ታላቅ ኸይር ሥራ ተሳታፊ እንዲሆኑ በታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋል። ​🎤 የእለቱ ተጋባዥ ኡስታዞች፦ 🎙 ኡስታዝ አቡ ሱፍያን 🎙 ኡስታዝ አብድረዛቅ ባጂ 🎙 ኡስታዝ አብዱል መሊክ ​🎤 የፕሮግራሙ መሪዎች፦ 🎙 አቡ ሂበቲላህ እና አቡ ሁዘይፋ ​📌 ማሳሰቢያ፦ ፕሮግራሙ በቀጥታ በመርከዙ የቴሌግራም ቻናል የሚተላለፍ በመሆኑ፣ ከወዲሁ ቻናሉን በመቀላቀል ሰዓቱን አክብረው ይጠብቁን። ​📲 የቀጥታ ስርጭቱን ለመከታተል የቴሌግራም ሊንክ፦ https://t.me/+h5YVkNAk55hkYWI8 ​💳 የበኩሎን አስተዋፅኦ ለማድረግ (የባንክ ሒሳብ)፦ ​የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)፦ 1000675591664 ​የሒሳብ ስም፦ ሱፉያን ሱልጣን እና ቀድሪያ ኸድር ​መልዕክቱን ላልሰሙ ወንድምና እህቶች በማጋራት (Share) የኸይሩ ተካፋይ እንሁን!

  • አውነትነቱን አይተው ከሚከተሉት ሀሰትን ሀሰትነቱን አይተው ከሚርቁት ያድርገን፡፡ ኣሚን፡፡ ©IbnuMunewor 👉https://t.me/IbnTaymiyyahrahimahullah 👉https://t.me/Twehid12

  • “ተነቃብሽ ምስር በለጠችሽ ቀይስር” ጌታዬ እሱ ከዐርሹ በላይ እንደሆነ ነገረኝ፡፡ “መካሪዎች” “ዟሂሩን እንዳትወስድ መልእክቱ ሌላ ነው” አሉኝ፡፡ እኔ ግን “ከናንተ ይልቅ ግልፅ በሆነ ዐረብኛ የነገረኝን ጌታዬን አምናለሁ፣ እንዳለኝም እርሱ ከዐርሹ በላይ ነው” አልኩኝ፡፡ “አንተ ወሃቢ” ተባልኩኝ፡፡ ይሁን ብዬ ተቀበልኩኝ፡፡ “ከአላህ ጋር ማንንም አትጣሩ” የሚል ቁርኣናዊ ጥሪ ሰማሁኝ፡፡ ተከትየም አስተጋባሁኝ፡- “ነብዮችም ሷሊሖችም አክብሮት እንጂ አምልኮት አይገባቸውም” አልኩኝ፡፡ “አንተ የነቢ ጠላት ወሃቢ!” ተባልኩኝ፡፡ የነቢዩን ዐለይሂሠላም ትእዛዝ ስላከበርኩኝ፡፡ ይሁን ምን አደርጋለሁኝ፡፡ “ቢድዐ ሁሉ ጥመት ነው” የሚል ሐዲሥ አገኘሁኝ፡፡ ነብዩን ዐለይሂሠላም አምኜ እውነት ብየ ተቀበልኩኝ፡፡ ከማንም ፍጡር በላይ ነብዬን አስቀደምኩኝ፡፡ “ሁሉም ቢድዐ ጥመት ነው” አልኩኝ፡፡ ነብዩን ዐለይሂሠላም እንወዳለን በሚሉ ሰዎች ቅፅል ስም ተወጣልኝ፡፡ “ወሃቢው” ተብየ ተጠራሁኝ፡፡ ትእዛዝ ስላከበርኩኝ፡፡ ለወንዶች ልብስ “ማስረዘምን ተጠንቀቁ፣ ማስረዘም በራሱ ኩራት ነውና” የሚል ሐዲሥ ሰማሁኝ፡፡ ትእዛዙን አክብሬ ልብሴን አሳጠርኩኝ፡፡ ይህን በሚቃወሙት “ምልክቱ ታይቶብሃል አንተ ወሃቢ” ተባልኩኝ፡፡ የነብዩን ዐለይሂሠላም ትእዛዝ ስለፈፀምኩኝ፡፡ “ፂማችሁን አሳድጉ” የሚል ሐዲሥ አገኘሁኝ፡፡ የምወደውን ነብይ ትእዛዝ አከበርኩኝ፡፡ ፂሜንም አሳደግኩኝ፡፡ ስላሳደግኩ “ከኛ ወዲያ ነብዩን ወዳጅ ላሳር” በሚሉ ጀሌዎች ተወነጀልኩኝ፡፡ “ወሃቢ” ተባልኩኝ፡፡ ትእዛዝ ስለፈፀምኩኝ፡፡ . . . ቆምኩኝ አሰላሰልኩኝ፡፡ ሂሳብ አወራረድኩኝ፡፡ ሰዎቹ ዘንድ “ወሃቢ” ማለት እንዲህ ሆኖ አገኘሁኝ፡፡ ወደተውሒድና ሱና የሚጣራ፤ ከሺርክና ከቢድዐ የሚጠነቀቅና የሚያስጠነቅቅ፤ ሱናን በላዩ ላይ ለማንፀባረቅ የሚታትር፤ ለእኛንዳንዱ እምነታዊ ጉዳይ መረጃ የሚጠይቅ፡፡ በቃ ይሄው ነው “ወሃቢ” ያስባለው፡፡ “አይ..” የሚል ካለ I am ዝግጁ for any የተረጋጋ ውይይት፡፡ ለመሆኑ “ወሃቢያ” የሚለው ስያሜ ከየት መጣ ጠላቶቹ እንዲህ ሲሉ ይመልሳሉ፡ “ስያሜው የተወሰደው ከመስራቹ ነው” ማነው መስራቹ “ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዱልወሃብ” አሉ፡፡ ታዲያ “ወሃብያ” ብላችሁ ለምትጠሯቸው አካላት እንደመነሻ የተጠቀማችሁት “ወሃብ” የሚለው ቃል መስራች ነው የምትሉት ሰውየ ስም ነው በጭራሽ!!! እሺ የአባቱስ ስም ነው በፍፁም!!! እና የማን ስም ነው የአላህ!!! አላሁ አክበር!!! ለማውገዝ ወደ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዱልወሃብ ያስጠጋችሁት ስያሜ እንዳሰባችሁት ሳይሆን ወደ አላህ ነው የተጠጋው፡፡ ለመሆኑ ዐረብኛ የማይችል ነው እንዴ ስሙን ያወጣላችሁ አይ የናንተ ነገር፡፡ ኢማሙሻፊዒን አላህ ይማራቸውና “አንድ ሰው ጧት ሱፊ ከሆነ ከሰዐት ሞኝ ሆኖ እንጂ አይመለስም” ያሉት ትዝ አለኝ፡፡ ማስታወስ መብቴ ነው፡፡ አንዳንድ “ሰፋ” “ቦርቀቅ” ያሉ ሰዎች ይችን ጥቅስ ሲሰሙ ሲቆጡ ስላየሁ ነው፡፡ ብቻ እኔ “ኢማሙሻፍዒ አሉ” ነው ያልኩት፡፡ በቃ፡፡ ለማንኛውም ሁሉም ይወቅ፡፡ “ወሃቢ” የሚለው ቃል የተወሰደው “አልወሃብ” ከሚለው የአላህ ስም እንጂ ከሙሐመድ ኢብኑ ዐብዱልወሃብ ስም አይደለም፡፡ ሰዎችን ከትክክለኛው ቁርኣናዊና ሐዲሳዊ አስተምሮ ለማስበርገግ ያወጡት ስያሜ ሳያውቁት ለሚጠሉት አካል ሙገሳ ሆኖባቸዋል፡፡ ምን እንደሚሻላቸው አላውቅም፡፡ ማናቸው “ተነቃብሽ ምስር በለጠችሽ ቀይ ስር!!!” ያሉትብቻ ተነቅቶባችኋል፡፡ ግን ለእነኚህ የሱና ጠላቶች “የወሃቢ” መገለጫ ምንድን ነው - “ወሃቢዮች ነብዮችንና ሷሊሆችን ይጠላሉ” አሉ፡፡ “ይቺ ጠጋ ጠጋ እቃ ለማንሳት ነው፡፡” እንዴት ነው ነብዮችንና ሷሊሆችን የምንጠላው “በዱዓ ላይ እነሱን አማላጅ ማድረግን ትቃወማላችሁ” አሉ፡፡ አዎ እንቃወማለን!! የገብሬ “ድንግል ማሪያም ሆኝ አማልጂኝ” ስህተት ነው እንደምንል ሁሉ፣ የኑርሁሴን “ጀይላኒ ሆይ አማልዱኝ፣ ድረሱልኝ” ማለት ስህተት ነው እንላልን፡፡ እንዴ የጥፋት ቡላና ዳለቻ አለውንዴ በቃ ከማንም ይምጣ ከማን ጥፋት ጥፋት ነው፡፡ ሺርክ ጀለብያ ስለለበሰ ተውሒድ አይሆንም!!! አይሆንማ! ለምን አይሆንም ስለማይሆን አይሆንም!!! ያለበለዚያማ የመካ ሙሽሪኮችም የሚያመልኳቸውን አካላት “አማላጆቻችን ናቸው” አላሉም እንዴ ይሄው ቁርኣን ይመስክር፡፡ ለምሳሌ ሱረቱ ዩኑስ ቁጥር፡18 እንዲህ ይላል፡- ((ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ያመልካሉ፤ እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው ይላሉ፤ አላህን በሰማያትና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ ትነግሩታላችሁን በላቸው፤ ከሚያጋሩት ሁሉ አላህ ጠራ ፤ ላቀም)) ባይሆን ከአላህ ብቻ ይጠየቅ አልን እንጂ ምልጃ የሚባል ነገር ጭራሽ የለም አልወጣንም፡፡ እንግዲህ ተመልከቱ፡፡ ሺርክን መቃወም ነው “ወሃቢ፣ የነቢዮች ጠላት፣ የሷሊሆች ጠላት” ያስባለን፡፡ ይሄ ከሆነ “ወሃቢዮች” ያስባለን በሉን ምንም አይደንቀንም፡፡ እንዳውም ስያሜው ከአላህ ስም ጋር እንደሚያያዝ እናውቃለን፡፡ - “ወሃቢዮች ነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አይወዱም” አሉ፡፡ እንዴት ሲባሉ “መውሊድ ይቃወማሉ” አሉ፡፡ ነብዩ ዐለይሂሠላም “የኔ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ስራው ውድቅ ነው” አሉ፡፡ አላሉም በሉን ደግሞ!! እሺ “መውሊድ አክብሩ” የሚል ቀጥተኛ ነብያዊ ትእዛዝ አምጡ ሲባሉ ቤሳቤስቲን የላቸውም፡፡ “እንግዲያውስ ውድቅ ነው” አልን፡፡ አሁን ማነው እውነተኛው የነቢዩ ዐለይሂሠላም ወዳጅ ትእዛዝ የሚያከብረው ወይስ ያለትእዛዝ የሚያነፍረው ለማንኛውም ይሄ ከሆነ “ወሃቢዮች” ያስባለን ይሁንላችሁ ያሻችሁን በሉን፡፡ ባይሆን አስታውሱ፡፡ ይሄን ባመት አንዴ የምትሰባሰቡበትን መውሊድ ሶሐቦቹም ፣ ታቢኦቹም፣ አትባኡታቢኦቹም፣ አራቱም የመዝሀብ መሪዎች አላከበሩትምና ከወሃቢያ መዝገባችሁ ውስጥ እንዳትረሷቸው፡፡ in your blacklist ማለቴ ነው! ኧረ ወይኔ! እናንተ አኮ አታደርጉትም አይባልም!!! ለነገሩ ብታደርጉት ባታደርጉት…:: ሲመስለኝ እዚያ ስትደርሱ ወይ ሚዛናችሁን ወይ ግራማችሁን ትቀይራላችሁ፡፡ - “ወሃቢዮች ሙስሊሞችን ያከፍራሉ” አሉ፡፡ እኛም እንዲህ እንላለን፡፡ ይሄ የሚያንፀባርቅ ነጭ ውሸት ነው!! አንዳንድ ተክፊሮችን አይታችሁ ሺርክና ቢድዐን ያወገዘን ሁሉ ይህን ካባ ለማልበስ የምትቧጭሩት ጥረት የተበላበት ንግድ ነው!! እኛን በሚያከፍሩ ሰዎች ጠቅልላችሁ “ተክፊሮች” ካላችሁን ተመሳሳይ ሂሳብ እንድንጠቀም እየጋበዛችሁን ነው፡፡ ስለሆነም ከናንተም ውስጥ “አላህ ከዐርሹ በላይ ነው” ያለን ሁሉ የሚያከፍሩ አሉና ሁላችሁንም “ተክፊሮች” እንበላችሁ ይሄ ሂሳብ ያዋጣል ለነገሩ ለማስታወስ ያክል አነሳሁት እንጂ የናንተን ሂሳብ እንጠቀማለን እያልኩ አይደለም፡፡ . . . ቢሆንም “ወሃብያ” የሚሉት እውነተኛውን የነብዩን ዐለይሂሠላም አስተምሮ ነው ብንልም፣ “ወሃብያ” የሚሉት የፀረ-ሺርክና ፀረ-ቢድዐ እንቅስቃሴን እንደሆነ ብናውቅም፣ “ወሃብያ” የሚሉት ተውሒድና ሱና ተኮር አካሄድን ነው ብንልም፣ “ወሃብያ” ማለታቸው የሚጠሉትን ደዕዋ ጭራቅ አድርጎ በመሳል ሰዎችን ከሐቅ ለማስበርገግ ነው ብንልም፣ … ይህም ከመሆኑ ጋር “ወሃብያ” ሲሉ ሳያውቁት እያሞገሱ እንደሆነ ብናውቅም በጭብጡ ውስጡ ስህተትም ነውርም እንደሌለ ለመጠቆም እንጂ ስያሜውን ተቀብለን መጠሪያችን እናደርጋለን እያልኩ አይደለም፡፡ ከሌሎችም የአላህ ስሞች እንዲሁ እየቆነጠርን ለራሳችን ስያሜ ወደማውጣት አይዳዳንም፡፡ ለምን ቢባል መልካም ቀደምቶቻችንን የበቃቸው ይበቃናል፡፡ አላህ እውነትን

  • видео или голосовое, без подписи

  • 💵 ነጋዴው ሆይ ጠንቀቅ በል!💵⚠ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡- ↘ “ነጋዴዎች አመፀኞች ናቸው❗” ሶሐቦች፡- የአላህ መልእክተኛ ሆይ “አላህ ንግድን ፈቅዶ የለ እንዴ?" ሲሉ ጠየቁ። ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ መለሱ፡- “እንዴታ! ግን እነሱ 👉 ያወራሉ፡፡ ሲያወሩ ይዋሻሉ❗ 👉 ይምላሉ፡፡ ሲምሉ ይወነጅላሉ❗" 🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴 ሸይኹል አልባኒ “ሶሒሕ” ብለውታል፡፡ (አስሶሒሓህ፡ 1/366) ℹ ©IbnuMunewor

  • 9 авг.1021из AbulBukhariSeid

    √ መውሊድ መውሊድን በተመለከተ በኡስታዝ ኢብኑ ሙነውር የተዘጋጁ ከፊል ፅሁፎችን በቀላሉ እነዚህን ሊንኮች በመጫን ማንበብ ትችላላችሁ። 1, ነብዩ ﷺ መቼ ተወለዱ? t.me/IbnuMunewor/893 2, መውሊድን ማን ጀመረው? በመረጃ ለሚያምኑ ብቻ t.me/IbnuMunewor/869 3, መውሊድ ለምን አላማ እንደተጀመረ ያውቃሉ? t.me/IbnuMunewor/876 4, መውሊድና ነባሩ እስልምና አይተዋወቁም! {ምስክር እራሳቸው!} t.me/IbnuMunewor/884 5, “በአላህ እዝነት ይደሰቱ...” - ትልቁ የመውሊድ አጋፋሪዎች ምርኩዝ t.me/IbnuMunewor/2227 6, የሰኞ ፆም እና መውሊድ t.me/IbnuMunewor/2214 7, ዐቂቃ ሌላ መውሊድ ሌላ! t.me/IbnuMunewor/2261 8, ዓሹራን ለመውሊድ? t.me/IbnuMunewor/2269 9, መውሊድ ውስጥ እነዚህ አደጋዎች አሉ! t.me/IbnuMunewor/2294 10, በመውሊድ ላይ ስለሚፈፀመው ጭፈራ ዑለማዎች ምን እንዳሉ ታውቃለህ? t.me/IbnuMunewor/882 11, መውሊድን የሚፈቅዱትም አይፈቅዱትም! t.me/IbnuMunewor/2298 12, መውሊድ የማያከብር ሰው የሙሐመድ ﷺ ጠላት ከሆነ፣ ገና የማያከብር ሰው የዒሳ ጠላት ነው! t.me/IbnuMunewor/886 13, እውን የሡወይባ ታሪክ ለመውሊድ ማስረጃ ይሆናል? t.me/IbnuMunewor/2234 14, ሸውካኒ እና መውሊድ (ወሳኝ ነጥቦች የተዳሰሱበት) t.me/IbnuMunewor/898 15, ሲዩጢ፣ የመውሊድ ደጋፊዎች ሌላኛው ምርኩዝ t.me/IbnuMunewor/2277 16, እውን ኢብኑ ተይሚያ መውሊድን ፈቅደዋል? t.me/IbnuMunewor/878 17, በሸይኹል አልባኒ እና “መውሊድ ይፈቀዳል” በሚል ሰው መካከል የተደረገ ድንቅ ቃለ-ምልልስ t.me/IbnuMunewor/34 18, ከ“ወሃብዮች” በፊት የነበሩ የመውሊድ ተቃዋሚዎች t.me/IbnuMunewor/1624 19, መውሊድ ተከሽኖ t.me/IbnuMunewor/2309 20, ለምንድን ነው የመውሊድ ተቃውሞ ኢኽዋኖችን ምቾት የሚነሳቸው? t.me/IbnuMunewor/918 21, መሷሊሐል ሙርሰላ፣ የመውሊድ አክባሪዎች የመጨረሻው ምሽግ t.me/IbnuMunewor/2302 = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

  • ይድረስ ለወይዘሪት አህባሽ በናንተ ምክኒያት ስንት ኢስላማዊ ተቋም ተዘጋ፣ ስንቱ ሞተ? ስንቱ ተደበደበ፣ ስንቱ ታሰረ፣ ስንቱ ሀገሩን ጥሎ ተሰደደ፣ ስንት የደዕዋ እንቅስቃሴ ተገታ? ስንትስ ቤተሰብ ተናጋ? ከምንም በላይ ደግሞ በኢስላም ስም ስንት የተበላሸ ዐቂዳ ደካሞች ላይ አሰረፃችሁ? ኢስላምን ስንት አመት ወደ ኋላ ለሞገተት እየተውተረተራችሁ እንደሆነ ለማንም አይሰወርም - ለካፊር እንኳን - ለናንተ ሲቀር፡፡ እናንተማ ከሰል ጠቆረ ውሃ ቀጠነ ብላችሁ የምትከራከሩ ናችሁ፡፡ እናንተ እኮ “የትኋንና የቅማል ደም ነጃሳ ነው፤ የነካውም ሰው አወቀም አላወቀም ሶላቱ ውድቅ ነው” የምትሉ ናችሁ፡፡ ሀሰት ካላችሁ ኪታባችሁ ይናገራል፡፡ (ቡግየቱ ጧሊብ፡ 87(ሁለተኛ እትም፡ 119)) በፃም ፅሩ! እንዴት ያለች “ፅድት” ያለች እምነት ነች? የዝንብ ጡሃራ አይነት እንዳትሆን ብቻ? “የዝንብ ጧሃራ ከነጃሳ እኩል ነው” ትል ነበር እህቴ፡፡ አባባሉን ከየት እንዳመጣችው አላውቅም፡፡ ብቻ ሳስታውስ አጓጉል የሆነ ንፅህና ስታይ ነበር እንዲህ የምትለው፡፡ ግን አህባሽ “ጡሃሪት” በነጃሳ ያውም በውሻ ኩስ፣ ሽንትና ልጋግ ተጨማልቆ መስገድ ይቻላል ትላለች፡፡ (ቡግየቱ ጧሊብ፡ 99-100 (አዲሱ እትም፡ 131-132))፡፡ እኔን የገረመኝ “የትኋንና የቅማል ደም ነጃሳ ነው” ማለታቸው አይደለም፡፡ ምንም እንኳን የሚገርም ቢሆንም፡፡ እኔን የገረመኝ “በውሻ ኩስ፣ ሽንትና ልጋግ ተጨማልቆ መስገድ ይቻላል” ማለታቸውም አይደለም፡፡ ምንም እንኳን የሚገርም ቢሆንም፡፡ እኔን የገረመኝ የሚገርመኝም ሁለቱ የተራራቁ ሀሳቦች ካንድ አካል መውጣታቸው ነው፡፡ እስኪ አስቡት “የውሻ ኩስ አይነጅስም” ያለ ሰው “የትኋን ደም ይነጅሳል” ይላል? ኧረ ተመስጌን በሉ “ምራቋም ይነጅሳል” ብለው የካፊር መሳለቀያ ቢያደርጉን ምን ይባል ነበር፡፡ ሞኝ ባያፍር የሞኝ ዘመድ ያፍር፡፡ ለነገሩ እንዳው ቢገርመኝ አነሳሁት እንጂ ከዚህ የከፋ ስንት የዐቂዳ ክፍተት አለባቸው አይደለም ወይ? ለምሳሌ “አላህ አለም ውስጥም የለም ከአለም ውጭም የለም፣ ከአለም ጋር ተያይዞም የለም ተነጣጥሎም የለም” የሚሉት፡፡ ሱብሐነላህ! ሰዎቹ ምን እየሆኑ ነው? ይሄ ማለት ምን ማለት ነው ይሄም ብቻ አይደለም “አላህ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ አይደለም” ይላል ሸይኻቸው አብደላህ አልሀረሪ፡፡ ምነው ስትሉ “ለምሳሌ አላህ መበደል አይችልም” ሲል ይፈላሰፍባችኋል፡፡ እናስ ሶቅራጠስ? አላህ ስላቃተው ነው እንዴ የማይበድለው? ፍትሃዊ ስለሆነ እንጂ፡፡ ይሄውና በሐዲሰል ቁድሲ ላይ፡- “ባሮቼ ሆይ እኔ በራሴ ላይ በደልን ክልክል አድርጊያለሁ፤ በናንተም መካከል እንዲሁ ክልክል አድርጌዋለሁና አትበዳደሉ” ይላል ጌታችን፡፡ ስለዚህ ስለሚችል አይደለም እንዴ በራሱ ላይ ክልክል ያደረገው፡፡ ባይችል እንዲህ ይል ነበር? ኧረ እነኚህ ሰዎች በምንኛ ነው የሚያስቡት? ይሄን ሁሉ እያደረጉ ከማንም በላይ ለኢስላም እየሰሩ እንደሆነ ይነግሩናል፡፡ ድንቄም፡፡ “ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል” ነውና ነገሩ ይሄው ለጊዜው የሚችሉትን ብቻ ሳይሆን የማይችሉትንም ጭምር እያደረሱ ነው፡፡ “ውጭ ካለ መቶ ጠላት ቤት ውስጥ ያለ አንድ ጠላት የከፋ ነው” ይላሉ ዐረቦቹ፡፡ ጥፋታችሁ ምንኛ ከፋ!!! ይሄ አቋማችሁ ድንገት አንድ ቀን ተሳስታችሁ ካሰባችሁ ያሳፍራችኋል፡፡ ምናልባት፡፡ ኧረ አላህን ፍሩ፣ ሞት አለ፣ የቀብር ጥያቄ አለ፣ ነገ አላህ ፊት መቆም አለ፣ ሲራጥ አለ፣….፡፡ ከውስጣችሁ አላህን የሚፈራ የለምንዴ? ለነገሩ ይሄ ቋንቋ መቼ ይገባችኋል ጨው ቀምሳችኋላ?! ምነው “አልገባንም” ብላችሁ ዝም ባላችሁ!!! ገልብጣችሁ መረዳታችሁ ከፋ እንጂ፡፡ ግን ቢገባችሁም ባይገባችሁም ወላሂ ወቢላሂ ወተላሂ ትሸነፋላችሁ! እርግጠኛ ሆኜ ነው የምናገረው! እየጠነቆልኩ አይደለም፡፡ በጥንቆላም በኹራፋትም አላምንም፡፡ ይቺ የናንተ ናት፡፡ እናም እላለሁ፡፡ አይወድቁ አወዳደቅ ነው የምትወድቁት፡፡ ሰማያዊ፣ መለኮታዊ መመሪያ አንብቤ ነው ይህን የምለው፡፡ ኢስላምን ሊያጠቃ የመጣ የውስጥም ይሁን የዉጭ ጠላት መቼም ቢሆን ቋሚ ድል ሊቀናው አይችልም፡፡ ይሄው አብረን እናንብብ፡ ((የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይፈልጋሉ፤ አላህ ግን ከሃዲዎቹ ቢጠሉም ብርሃኑን ይሞላል))፡፡ ታማኙና እውነተኛው ነብይም ዐለይሂሰላም እንዲህ ይላሉ “ውርደትና ክብረ ቢስነት ትእዛዜን በጣሰ ላይ ይሁን!!” በርግጥ ብዙ መስዋእትነት ታስከፍሉ ይሆናል፡፡ ቢሆንም ዲኑ ብዙ ሊከፈልለት የሚገባ ዲን ነው፡፡ በአላህ ፈቃድ ትወድቃላችሁ፡፡ እንዳውም የሮማን አወዳደቅ ነው የምትወድቁት፡፡ ታዲያ አትሰሙም እንጂ ወድቃችሁ መውደቃችሁ ላይቀር መፈራገጥ ባታበዙ መልካም ነበር፡፡ “የማይበስል ጭንቅላት መብሰሉ ላይቀር የሰው ማገዶ ያስጨርሳል” (ኢብኑ ሙነወር፣ 10/01/2005) ©IbnuMunewor 👉https://t.me/IbnTaymiyyahrahimahullah 👉https://t.me/Twehid12

  • видео или голосовое, без подписи

  • 8 авг.68из Sle_qelbachn1

    🎉 አስደሳች ዜና!! ♥️የኪታቡ ስም፡ اِنْتَبِهْ أَنْتَ مُرَاقَبْ!! (ኢንተቢህ አንተ ሙራቀብ) ✍️ የኪታቡ ፀሐፊ፡ አቡ ዐብዱረሕማን አኒስ ብኑ ሷሊሕ 🎙አቅራቢ ፡በኡስታዝ ዐብዱረዛቅ አል ባጂ 🗓 መቼ ይጀምራል? ነሐሴ 4 ፣ ሰኞ ⏰ የዘወትር ፕሮግራማችን ቀናት እና ሰዓት፡ ☑️ ቀናት፡ በየሳምንቱ ቅዳሜ እና ሰኞ ☑️ሰዓት፡ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ⚠️ሐቂቃ ይህ ኪታብ በተለይም በዚህ ዘመን በድብቅ ወንጀል ለተፈተነ፣ ስማርት ስልኮችና ኢንተርኔት ላመጡት የብቸኝነት ፈተና መፍትሔ የሚሰጥ፣ እንዲሁም ጌታችን አላህ ሁሌም እየተመለከተን መሆኑን በማስታወስ ልብን የሚያነቃቃ ድንቅ ኪታብ ነው! 🔴ትምህርቱ ቀጥታ ስርጭት የሚሰጥበት ቻናል፦🔗 ✈️⬜️ስለ ቀልባችን☑️ ➡️ Share: t.me/Sle_qelbachn1 😬የኪታቡን PDF ለማገኘት:t.me/Sle_qelbachn1/1963

  • 🚫በሆድ ተደፍቶ መተኛትን አስመልክቶ🚫 ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል "ይቺ አላህ የሚጠላት መጋደም ነች❗❗" {አልባኒ ✅ሶሒሕ✅ ብለውታል} ↘↘↘↘↘ 🍀 እባኮትን ለሌሎች ያስተላልፉ። ወደ መልካም አመላካች ከፈፃሚው ጋር ተመሳሳይ ምንዳ ያገኛልና። ℹ ©IbnuMunewor

  • ⚠ለሚያስተውሉ ብቻ⚠ ሸይኽ ኢብኑልዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ: " ሸይኽ ረቢዕ (አልመድኸሊ)ን የሚጠሉት የጥመት ቁንጮዎችን ስላጋለጠባቸው ነው❗❗" 💯 http://www.safeshare.tv/w/IOtheNAYuK ለኢኽዋኖችና ለምርከኞቻቸው እስኪ ተጠየቁ ሸይኽ ኢብኑልዑሠይሚንስ መድኸሊ ናቸው? ዐቅልን የሰጠ ጌታ ምስጋና ይድረሰው!! ©IbnuMunewor

  • ነብዩ ዐለይሂሠላም እንዲህ ይላሉ፡- “የፈለግከውን ያክል ብትኖር ትሞታለህ! የፈለግከውን ብትወድ ትለየዋለህ! የፈለግከውን ስራ ዋጋውን ታገኛለህ! እወቅ! የሙእሚን ክብሩ የሌሊት ሶላት መስገዱ፣ የበላይነቱም ከሰዎች መብቃቃቱ ነው፡፡” (ሐኪም ዘግበውታል፡፡ አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል) ©IbnuMunewor

  • 3 авг.1521из IbnTaymiyyahrahimahullah

    видео или голосовое, без подписи

  • ቀልብ የፅድቅም የጥፋትም የእዝ ማዕከል ጀነት ነፍስ በምትጠላቸው ነገሮች ተከባለች፤ ጀሀነም ደግሞ ነፍስ በምትወዳቸው ሸይጧን በሚያስውባቸው አማላይ ነገሮች፡፡ በብዙ ሁኔታዎቻችን ከአረሕማን ይልቅ ለሸይጧን የቀረብን ነን፡፡ ዐይኖቻችን፣ ጆሮዎቻችን፣ እጆቻችን፣ እግሮቻችን፣ እንዲሁም ምላሳችን ለሸይጧናዊ ተልእኮ የሰሉ ናቸው፡፡ ቀላሉን አምላካዊ ክልከላ መታገስ አቅቶን ከባባድ ሸይጧናዊ ልፋት ላይ እንተጋለን፡፡ ሁሉም የሰውነታችን ክፍሎች ለጥፋት ሲተባበሩ፣ አንዳቸው ብቻ ለሚበቁት ኸይር ግን ተባብረውም ይዝላሉ፡፡ ይሄ ሁሉ የሚሆነው እንግዲህ ማዕከሉን “ዋግ” ሲመታው ነው፡፡ ቀልብ በሺርክ፣ በቢድዐ፣ በስሜት፣ ለሙስሊሞች በምታረግዘው ክፋት፣ … ከተበከለች ታማ፣ ታውካ፣ አመርቅዛ ትሞታለች፡፡ታዲያ ቀልብ ስትሞት ሞቷ ለኸይሩ እንጂ ለሸሩማ ኢንኩቤተር ትሆናለች- ክፉ የሸር መፈልፈያ፡፡ብቻ ሂወቷ በኢማን ካልኩሌተር ሲሰላ ያለኢማን ሂወት የለምና ሞታለች - የምር ሞት! ከዚያስ? ከዚያማ ቀልብ ተበላሽታ ሌላው ሰውነት ምን ጤና ሊኖረው? የአካል እንቅስቃሴ በሙሉ ደመ-ነፍሳዊ ይሆናል- ተንቀሳቃሽ ሙት!!! ግድግዳ የተጠጋ እንጨት ሆኖ ሄወት እንዳለው ያስባል፡፡ ከዚህ በኋላ ዐይንም ዐይን ጆሮም ጆሮ አልሆነም፡፡ የሰማያትና የምድር አፈጣጠር፤ የሌሊትና የቀን መተካካት ለሱ ከታክሲዎች መተላፍ፣ ሽንት ቤት ደርሶ ከመመለስ ብዙም ልዩነት የለውም፡፡ ችግሩ ከማዕከሉ ነዋ!!! ((ለነርሱም በነርሱ የሚያውቁባቸው ልቦች ወይም በነርሱ የሚሰሙባቸው ጆሮዎች ይኖሩዋቸው ዘንድ በምድር ላይ አይሄዱምን እነሆ ዐይኖች አይታወሩም ግን እነዚያ በደረቶች ውስጥ ያሉት ልቦች ይታወራሉ፡፡)) (አልሐጅ፡ 46) በሌላ በኩል ልብ ከተስተካከለች፣ በኢማን ከተዋበች፣ በኢማን ካሸበረቀች መላ ሰውነት ጤና ይኖረዋል፡፡ ፊትም ኑር ይላበሳል፡፡ ዐይኖች በሐራም አይገግሙም፡፡ ጆሮዎች ለሙዚቃ አይቆሙም፡፡ ምላስም የሀሜት ማሽን አትሆንም፡፡ ከውጭ ሙስሊም ያልሆነ ገፅታ እየተስተዋለ ምላስ “ዋናው ልብ ነው” እያለች አታሽቃብጥም፡፡ ማዕከሉ ነቅቶባታላ!!! ልብ ስትስተካከል እውነተኛ ማንነት ይገኛል፡፡ ከውስጥም ሙስሊም፣ ከውጭም ሙስሊም! በሐያእ የለሰለሰ፣ በውጭ ገፅታው ያልተኮፈሰ፣ በልቡ የመጠቀ፣ ከእንቶ ፈንቶ የራቀ ልዩ ስብእና!!! አቡበክር አሲዲቅ ረዲየላሁ ዐንሁ ከሌሎች የመጠቀው በሶላቱና በፆሙ አልነበረም፡፡ ይልቁንስ ልቡ ላይ በፀደቀ ነገር ነበር- ኢማን!!! የቀልብ ልዩ ክብር!!! ባጭሩ ጥፋታችንም ልማታችንም ከልብ ጋር የተሳሰረ ነው ማለት ነው፡፡ ታዲያ እኔና እርሶ የቱጋ ነን? ሰገነት ወይስ ጫማ ተራ? ነው ወይስ መሀል ሰፋሪ? በሌላ አነጋገር ልባችን ጤነኛ ነው፣ በሽተኛ ነው፣ ወይስ ሙት ነው? ለካ ይህንንም ለማወቅ ልብ ያስፈልጋል፡፡ ((ባለ ልቦናዎቹ እንጂ አይገነዘቡም)) አይደል ያለው ኻሊቁ? አንተ ልቦችን ገለባባጭ የሆንከው ጌታችን ሆይ! ልቦቻችንን ወደ ትእዛዝህ ኡዙርልን፣ በዲንህም ላይ አፅናን፡፡ አላሁመ ኣሚን፡፡ ©IbnuMunewor 👉https://t.me/IbnTaymiyyahrahimahullah 👉https://t.me/Twehid12

  • видео или голосовое, без подписи

  • አሕባሽ ለሀገር ልማት - በርግጥ ይለምናሉ፡፡ ግን በብዛት በህይወት ያለ ሰው አያስቸግሩም! ከሞተ ሰው ነው የሚለምኑት!(ቡግየቱጧሊብ፡ 8፤ ሶሪሑልበያን፡ 57-58፤ አደሊሉል ቀዊም፡ 173) ወይም ከድንጋይ ነው በረካ የሚፈልጉት!!(ሶሪሑልበያን፡ 58፤ ኢዝሃሩል ዐቂደቲሱኒያህ፡ 244) - በስራ ቦታዎች ላይሆንላቸው ተፍ ተፍ በማለት የስራ ቦታዎችን አያጨናንቁም፡፡ ይልቅ ጫት ነው የሚቅሙት፡፡ እስኪ ዐስር ሶላት ላይ የማይገኙ የሱፍያ ኢማሞችን ቁጠሩ፡፡ እንግዲህ በየቀኑ ለሀገር ኢኮኖሚ የሚያስገቡትን አስቡት? - አሕባሽ ለውበት፡- ዐብደላህ አልሀረሪ፡ ሒጃብ የሰውነትን ቀለምና ፀጉርን ከሸፈነ ይበቃል ብሏል(ቡግየቱ ጧሊብ፡ 104(አዲሱ እትም፡137))፤ ተማሪው ኒዛር ሐለቢ፡ ሴቶች ወጣቶቻችን በጂንስ ይዋባሉ፤ ምክኒያቱም እኛ ሰውነትን መሸፈንም ፋሺን መከተልም በተመሳሳይ ጌዜ እናስገኛለን ብሏል(አልሙስሊሙን ጋዜጣ ቁጥር፡407፣ 1992)፤ ሴት ሽቶ ተቀብታ መውጣቷን ፈቅዷል(ቡግየቱ ጧሊብ፡ 351(አዲሱ እትም፡446)) አሕባሽ ሙድ የገባው፡- ከአጅነቢይ ጋር በእጆቻቸው መካከል የሚለይ ነገር አድርጎ መጨባበጥን ፈቅዷል(ሶሪሑል በያን፡ 144)፤ የሴቶችና የወንዶችን መቀላቀል ፈቅዷል(ሶሪሑል በያን፡ 178-179)፤ በስሜት ካልሆነ ሴትን ለረጅም ጊዜም ቢሆን መመልከት ይቻላል(ቡግየቱ ጧሊብ፡224፣287፣288(አዲሱ እትም፡280፣266፣267))፤ ቤተሰብ ከሆነች ደግሞ ከእንብርት እስከ ጉልበት ካለው ውጭ መመልከት ይቻላል(ቡግየቱ ጧሊብ፡290(አዲሱ እትም ላይ ግን አውጥቶታል)፤ ወንድ ወይም ሴት መሆኑ ከማይለይ ፍናፍንት ጋር በረመዷን ግንኙነት ማድረግ ፆም አያበላሽም(ቡግየቱ ጧሊብ፡ 192(አዲሱ እትም፡243))፤ ብልት ከተሸፈነ በፓንት ሶላት መስገድ ይቻላል(ቡግየቱ ጧሊብ፡ 139) - አሕባሽ የቴክኖሎጂው ትውልድ፡- የአለም ቅርፅ ላይ አዲስ ግኝት አግኝተው ቂብላ ሊቀይሩ ተውተርትረዋል፡፡ - አሕባሽ ዘመኑን የቀደመ የህክምና ግኝት ባለቤት፡ አንድ በርሜል ውሃ ውስጥ አንዲት ፀጉር ብቻ በመክተትና በመርጨት ለበርካቶች ፈውስ ይሰጣሉ፡፡ ቂቂቂ.. በዚህም ለህክምና የሚወጡ አላስፈላጊ ወጪዎችን በማስወገድ ለሀገር ኢኮኖሚ የበኩላቸውን ያበረክታሉ፡፡ - አህባሽ ለአእምሮ ንቃት፡- በነጃሳ ያውም በውሻ ኩስ፣ ሽንትና ልጋግ ተጨማልቆ መስገድ ይቻላል(ቡግየቱ ጧሊብ፡ 99-100(አዲሱ እትም፡131-132))፡፡ የትኋንና የቅማል ደም ግን ነጃሳ ነው፤ የነካውም ሰው አወቀም አላወቀም ሶላቱ ውድቅ ነው ይላል(ቡግየቱ ጧሊብ፡ 87(ሁለተኛ እትም፡ 119))፣ ኢስቲንጃን ከውዱእ በኋላ ማድረግ ይቻላል(ቡግየቱ ጧሊብ፡134) ታጥቦ ጭቃ አሉ እማማ እንትና፡፡ - አሕባሽ ለድህነት ቅነሳ፡ ከወረቀት የብር ኖት ዘካ የለም(ቡግየቱ ጧሊብ፡160፣ 169(አዲሱ እትም፡207)) አሕባሽ ለዘላቂ ሰላምና መረጋጋት - የካፊርን ገንዘብ መስረቅ ይቻላል(ካሴት ቁጥር፡2)፣ በቁማር መብላት ይቻላል(ሶሪሑል በያን፡133-134)፡፡ ቢሆንም ችግር በማይፈጥር መልኩ ስለሚሰራ ብዙም የሀገርን ሰላም አያናጋም (እዚጋ ትእምርተ-ስላቅ ጨምራችሁ አንብቡ፡፡ የት እንዳለች ስለማላውቅ ነው) አሁን ይሄ ነባሩ እስልምና ነው? የት የነበረው? ©IbnuMunewor 👉https://t.me/IbnTaymiyyahrahimahullah 👉https://t.me/Twehid12

  • видео или голосовое, без подписи

የሱና ኡስታዞች ትምህርት ብቻ የምላክበት — tgindex