Voice of Amhara የአማራ ድምጽ ®
СтатистикаVoice of Amhara Ethiopian በኢትዮጵያ ወቅታዊ ፓለቲካዊ ማህበራዊ ዘርፎችን የሚያነሳ የቴሌግራም ቻናል። ፈጣና ተአማኒ ነት ያላትቸውን መረጃዎች በፍጥነት ያግኙ!!
- Последний пост
- 16 янв.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 96
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ተወዳጁ የኪነጥበብ ባለሙያ ነጻነት ወርቅነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡ በቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢነት፣ በተዋናይነትና በሌሎች የጥበብ ስራዎች ውስጥ ስመጥር እና ተወዳጅ ከሆኑ የጥበብ ሰዎች አንዱ የሆነው ነጻነት ወርቅነህ ባደረበት ህመም በድንገት ከዚህ ዓለም ተለይቷል፡፡ ለበርካታ ዓመታት በኢቢኤስ ቴሌቪዥን የሚተላለፈው የቤተሰብ ጨዋታ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ የሆነው ነጻነት ወርቅነህ ባለትዳርና የ3 ልጆች አባት ነበር፡፡ የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ማኔጅመንትና ሰራተኞች ለቤተሰቦቹ፣ ለሙያ ባልደረቦቹ እንዲሁም አድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል በማለት መግለጫ አውጥቷል። ለነፃነት ወዳጅ ቤተሰቦች መፅናቱ እንመኛለን።
🔥#የድሮን_ጥቃት_ወግዲ_ቀጠና‼️ ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ የድሮን ጥቃት ፈፅሟል:: ፀረ-አማራው የአብይ አህመዱ አገዛዝ ዛሬ ህዳር 14/2018 ዓ.ም ደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ አብዩ ጎርባ የተባለች ታዳጊ ከተማ ላይ ባይራክታር ቲቢ2 (Bayraktar TB2) በተባለ ቱርክ ሰራሽ ድሮን ጥቃት የፈፀመ ሲሆን ጥቃቱ የተፈፀመው በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ላይ ነው:: የድሮን ጥቃቱ ከቀኑ 8:10 አካባቢ የተፈፀመ ሲሆን ጥቃቱ የተፈፀመበት ግለሰብ ሁኔታውን ሲገልፅ፦ ወትሮ እኔም ሆነ ባለቤቴ ቤታችንን አለቅም ነበር ዛሬ ማለዳ ግን አላህ በምክንያት ትረፍ ሲለኝ ባለቤቴ አባታቸው ስለታመሙ ጠይቀሻቸው ነይ አልኳትና ሄደች:: እኔም ለአጨዳ የደረሰ ጤፍ ስላለኝ እሱን ለማየት ወደ እርሻየ ሄድኩኝ ይላል በሁኔታው እየተገረመ:: በጥቃቱ ቤትና ንብረቱ ወድሟል:: ስለሆነም ድሮን በጣም የረቀቀ ቴክኖዎሎጂና ማጥቃት ያለበትን ለይቶ የሚያውቅ ቢሆንም የብልፅግናው አገዛዝ ግን በዚህ መልኩ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት በመፈፀም የታጠቀውን ፋኖን ሳይሆን የአማራን ህዝብ እንደ ህዝብ እየጨፈጨፈ ይገኛል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
#ሰበር_የድል_ዜና..‼️‼️ አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝና አፋህድ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በአገዛዙ ሰራዊት ላይ ድል ተቀዳጁ። የጡት ቆራጩ የአብይ አህመድ መከላከያ ሰራዊት ከአጣዬ(ኤፌሶን) ከተማ ወጣ ብላ በምትገኘው በርግቢ ቀበሌ ካንፕ አድርጎ በመቀመጥ ወንዶችን እየደበደበና አስሮ ገንዘብ እየጠየቀ ሴቶችን ደግሞ አስገድዶ እየደፈር እንደሆን በቅርቡ በዜና እወጃችን መግለፃችን ይታወቃል። ሆኖም በርግቢ መሸጎ ለወራት ህዝብን ሲዘርፍና ሲያሰቃይ የቆየው 103ኛ አየር ወለድ ክፍለጦር ላይ ጀግናው የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ እና ሽዋ ጠቅላይ ዕዝ ጥምር ሰራዊት በተቀናጀ የጋራ ተጋድሎ በርካታ የአገዛዙ ሰራዊት ድባቅ ተመታ! በመሆኑም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር ዓፄ ይኩኖ አምላክ ክፍለጦር እና የ7ለ70 ክፍለጦር እንዲሁም የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ከአፄ አምደ ጽዮን ኮር ራምቦ ክፍለጦር እና ሰባት ለሰባ ክፍለጦር በተውጣጡ ሻለቆች ዛሬ ህዳር 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከንጋቱ 11:00 ጀምሮ በወረዳው ላይ በአይነቱ ለየት ያለ በአራት አቅጣጫ በተካሔደው የተቀናጀ ኦፕሪሽን አውደ ውጊያ የአገዛዙ ሰራዊት ክፉኛ ተመታ። እልህ አስጨራሽ በሆነው አውደ ውጊያ ፣በአመጃ ገብርኤል፣ በበርግቢ ውሃ ታንከር እና በቴሌ ታወር አካባቢዎችን የሸፈነ ታላቅ ተጋድሎ የተደረገ ሲሆን ሰራዊታችን በተቀናጀ አንድነት የጠላትን አከርካሪ መስበር ተችሏል። በአውደ ውጊያው የአማራ ፋኖ ትግል የአንድነት ሃይል የታየበት የአፄ ዘረ ያዕቆብ ፩ ኮር የ7ለ70 ክፍለጦር ደመላሽ ሻለቃ በሳራምባ ቴሌ ታወር፣ በካራ ለጎማ ፤ በተረተር አካባቢዎች እንዲሁም የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር ዓፄ ይኩኑአምላክ ክፍለ ጦር ለማ ሻለቃና አይሻ ሻለቃ በአርብ ገብያና አጨብጭብ ተራራን በመያዝ የተቀናጀ አውደ ውጊያ ሽዋ ጠቅላይ ዕዝ አፄ አምደ ጽዮን ኮር የራንቦ ክፍለጦር ሞገሴ 1ኛ ሻለቃ እና ማንበግር 3ኛ ሻለቃ፤የሰባት ለሰባ የናሁሰናይ የሲኖ ሻለቃና አስማረ ዳኜ ሻለቃ ባደረጉት ትንቅንቅ በርካታ የ103ኛ የአገዛዙ አየር ወለድ ክፍለ ጦር አባላት ላይ የሰራዊት እና ቁሳዊ ጉዳት የደረሱበት ሲሆን፣ በቀጠናው የሚገኘው የጦር ወንጀለኛው የብልፅግናው ሰራዊት የየአሳምነው ክንድ ነበልባል ልጆች መቋቋም ሲያቅተው ከከሚሴ ከተማ ተጨማሪ ሃይል ቢያስገባም ከደረሰበት ከፍተኛ ኪሳራ ሊታደገው አልቻለም። በከሰያት አመጃ ገብርኤል ተራራው ላይ በሰፈረው የወራሪው ሰራዊት ላይ የራንቦ ክፍለጦር ሞገሴ 1ኛ ሻለቃ ታላቅ ተጋድሎ በማድረግ በርካታ የጠላት ሃይልን በመረፍረፍ የክብር መስዋዕትነት የተከፈለበት በተናበበ የሻለቆች አንድነት ስኬታማ ውጤት ተጎናፅፈዋል። ከወትሮው ለያት ባለ መልኩ የአንድነት ድባብ የታየበት በፋኖ ሰራዊት በተናበበ የጥምር ሃይል በአገዛዙ ወታደሮች ላይ የጋራ ኦፕሬሽን ጠላት በሶስት አምቡ ሙትና ቁስለኛውን በመያዝ ወደ አጣዬ ከተማ እንዲመለስ የተደረገም ሲሆን ፣ የአጣዬ እና የከሚሴ ሆስፒታሎች ከቀላል እስከ ከባድ የ103ኛ የአየር ወለድ ክፍለጦር ቁስለኞች አባላቱ መሙሏታቸው ተረጋግጧል። መረጃውን ያደረሰነ አርበኛ አማረ ታዘዘ የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነው። " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ©አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል።
ማርበርግ ቫይረስ አርሲ እና ምዕራብ ሀረርጌ ኦርቶዶክሳውያን ስቃይ የተባባሰባቸው ቦታዎች ከማርበርግ ጋር ስማቸው እየተነሳ ነው፡፡ ባሳለፍነው ወር ምዕራብ ሃረርጌ አሰቦት አካባቢ ሁለት ልጆች ከመታገታቸው በተጨማሪ የገዳሙ ስራ በተግባር ቤት ስራ የሚያግዙ በገዳሙ ዙሪያ የሚኖር ንብ በማነብ ላይ እያሉ ተኩስ ከፈቱባቸው፡፡ በዚህ የተኩስ እሩምታ ምክንያት አንደኛው አረጋዊ መነኩሴ ወዲያው ሲሞቱ ሌላኛው መነኩሴ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው እስካሁን በህክምና ላይ መሆናቸው የተዘገበው በቅርቡ ነበር፡፡ በምዕራብ ሐረርጌ በጉባ ጉቱ እና አው ጉዲና ወረዳዎች እንዲሁም በጭሮ ወረዳ በረብሱ አካባቢ ደግሞ የስድስት ኦርቶዶክሳዊያን ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ተቀጥፏል የሚለው መረጃም የዚህ ሳምንት መረጃ ነበር። እንደ ምዕራብ ሐረርጌ ፣ምስራቅ ሐረርጌ እና አርሲ ባሉ ቦታዎች ላይ ኦርቶዶክሳዊያን እየኖሩ ያሉት በስጋት ሲሆን ሌሎች ደግሞ በስደት ላይ ናቸው። በሌላ በኩል ማርበርግ ቫይረስ ምዕራብ ሀረርጌ እና ምስራቅ አርሲ እንደተከሰተ ሚዲያዎች እየዘገቡ ቢሆንም በክርስቲያኖች ግድያ እንደለመዱት ክህደት የአካባቢው ባለስልጣናት ውሸት ነው ብለው እያሉ ነው፡፡ ለማንኛውም ለክርስቲያኑም ለሙስሊሙም ለእናንተም ጭምር በሽታው አስከፊ ስለሆነ ግዴላችሁም ትኩረት ስጡት፡፡ በዛው ሰው በማፈናቀል በመግደል የዛለው እጅና አዕምሮ ፋታ ያግኝ፡፡ እኛ ግን አጀንዳችንን አንቀይርም የኦርቶዶክሳውያን ሞት ይቁም፡፡ #በሃገራችን_ኢትዮጵያ_እየተፈጸመ_ያለው_የኦርቶዶክሳውያን_እልቂት_የመንግሥት_መዋቅር_የሚያውቀው_የሚደግፈው_ሽፋን_እየሰጠ_የሚያበረታታው_እንጂ_ባልታወቁ_ኃይሎች_የሚፈጸም_ወንጀል_አይደለም ©ስምዓ ተዋሕዶ
ግፈኛው የዓብይ ሰራዊት በደፈጣ ተመታ!! አፋብኃ በላይ ዕዝ ደጃዝማች ፬ኛ ኮር አርበኞች ክ/ጦር ማዕ/አርማጭሆ ወረዳ ልዩ ስሙ እንዝልሽ ቀበሌ ጋብላ ከተማ አቅራቢያ ቻሌ መታኩስ የተሰኜ ልዩ ቦታ ዛሬ ህዳር 11/2018 ዓ.ም ጠዋት 12:00 ሰዓት የዓብይ ፋሽስት ሰራዊት በደፈጣ ሙትና ቁስለኛ ሁኗል። በርካታ ጠላት በረገፈበት የእንዝልሽ የደፈጣ ኦፕሬሽን የበላይ ዕዝ ደጃዝማች ፬ኛ ኮር አርበኞች ክ/ጦር ከአራት ብርጌዶች የተወጣጣ ሰራዊት የድሉ ባለቤት ሲሆን ለጊዜው ቁጥሩ ያልተረጋገጠ በርካታ ጠላት ሙትና ቁስለኛ ሁኗል።ከፊሉ በድንጋጤ ጥልቅ ገደል ተንከባሎ ስለገባ የሟቹ እና የቁስለኛው መጠን በቁጥር ለማስቀመጥ ለጊዜው አዳጋች አድርጎታል። በእንዝልሽ ግንባር የተመታው ጠላት ተልዕኮው የከሸፈ ቢሆንም በአምስት አቅጣጫ ተጨማሪ ሰራዊት ገፍቶ በማስገባት ሞራሉን ለማካካስ ሙከራ እያደረገ ይገኛል። በማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ከማሰሮ ደንብ ከተማ ውጭ በደጃዝማች ኮር ተጠርጎ ሸሽቶ የቆየ መሆኑ የሚታወስ ነው። ህልውናችን በተባበረ ክንድ!! አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ህዳር 11/2018 ዓ.ም ህ/ግንኙነት መምሪያ
ብልፅግናው መራሽ መንግሥት በተለያዩ ክልሎች ወጣቶችን እያፈነ በግዳጅ እያፈሰ እንደሆነ ታወቀ‼️ አገዛዙ በእርግጥም ለአመታት ወጣቶችን ፥ እድሚያቸው ለውትድርና ያልደረሱ ህፃናትን ጭምር ከተለያዩ የሀገሪቷ ክፍል በግዳጅ እያፈሰ ወደ ጦርነት እሳት እየማገደ፤ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ዕልፍ የድሃ ልጆችን አስጨርሷል ። ወላጅ እናቶችና ቤተሰቦች "ልጆቻችን የት ናቸው ?..." ብለው የመጠየቅ መብት እንኳን አይፈቀድላቸውም ። የአገዛዙ ፖሊስ እና ደምብ አሰከባሪ ተቀጣሪዎች የድሃ ልጆችን አፍነው ከወሰዱ በኋላ ቤተሰቦቻቸው፤ "ልጄ ለአቅመ-ውትድርና አልደረሰም ፥ በዚያ ላይ ያለፍላጎቱ ነው ተገዶ የተወሰደው...ወዘተ..." ለሚለው ጥያቄ፤ ምላሻቸው "ልጆቻችሁ እንዲለቀቁ ከፈላጋችሁ ከ50 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር ካልከፈላችሁ አንለቅም...." በማለት የታፋሽ ቤተሰቦችን በማጎሳቆል ያባርሯቸዋል ። እናት የልጆቿ ህይወት በአጭር እንደቀረ አስባ ተስፋ ከመቁረጥ ውጪ ምንም አይነት መፍትሄ እንደማታመጣ አውቃ እያነባች ትኖራለች ። ይህ መፍትሄ የታጣለት የአገዛዙ የአፈሳ ጉዳይ ዛሬም በእጅጉን ተባብሶ መቀጠሉ ከተለያዩ ክልሎች መረጃዎች እየወጡ ይገኛል ። በቢንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ላይ በቀን 05/03/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ከፍተኛ የሆነ አፈሳ በአገዛዙ ፖሊስ እና ደምብ አስከባሪ ቅጥረኞች ወጣቶች፣ ሴቶች፣ በእድሜ የገፉ እንዲሁም እድሚያቸው ለውትድርና ያልደረሱ ህፃናትን ጭምር በግዳጅ አስገድደው እያፈሱ ወደ ወታደር ካምፕ እያስገቡ እንደሆነ ስማቸውን እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአከባቢው ነዋሪዎች ለከሰም ሚዲያ መረጃውን አድርሰዋል ። ነዋሪዎች በቆይታቸውም፤ "በብልፅግናው አገዛዝ የግዳጅ አፈሳ ምክንያት በነፃነት መንቀሳቀስና ማህበራዊ ኑሮዋችን መኖር አልቻልንም ፥ ከቤት እንኳን ወጥተን ወደ ሱቅ መሄድ ፥ የተለያዩ የባልትና ግብዓቶችን አለማግኘታችን ለከፍተኛ ችግር ዳርጎናል..." ሲሉ ለጣቢያችን ቅሬታቸውን ያቀርባሉ ። የብልፅግናው መንግሥት በበኩሉ፤ በተለያዩ የፕሮፖጋንዳ የሚዲያ መሣሪያው "ምንም አይነት አፈሳ አላደረግንም፤ ወደው እና ፈቅደው ነው 'የሀገር መከላከያ ሰራዊት'ን የሚቀላቀሉት ። ይህ ሁሉ የጠላት እና የአሸባሪዎች የሀሰት ወሬ ነው..." በማለት፤ ውሃ የማያነሳ ማስተባበያ እየሰጠ ይገኛል ። ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ በኦሮሚያ ክልል፡ በመርቲ ወረዳ አቦምሳ ከተማ፣ በናዝሪት እና በሀረርጌ በተለያዩ አከባቢ እንዲሁም በሁሉም ክልል በሚባል ደረጃ በዚህ ወራት ብቻ ቁጥራቸው በውል የማይገመት እድሚያቸው ለውትድርና ያልደረሱ ህፃናትን ፥ በእድሚያቸው የገፉ ዜጎችን በግዳጅ ታፍሰው በብልፅግናው መንግሥት ተወስደዋል ። በአርሲ ዞን መርቲ ወረዳ፡ አቦምሳ ከተማ ዛሬ ማለትም፤ በቀን 11/03/2018 ዓ.ም "በአገዛዙ በፖሊስ እና በደምብ አስከባሪ አባላት በየመንገዱ የሚንቀሳቀሱትን ዜጎች በግዳጅ እያፈኑ እያፈሱ ወደ ወታደር ካምፕ (ማጎሪያ መጋዘን) እየወሰዱ እንደሚገኙ..." አንድ የከተማው ነዋሪ የሆኑ ግለሰብ አቤቱታቸውን ለከሰም ሚዲያ ተናግረዋል ። በአርሲ ዞን አከባቢ በተለያዩ ወረዳዎች በዚህ ወራት ብቻ በሺህ የሚቆጠሩ አማራ ኦርቶዶክሳውያን በግፈኞች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን መዘገባችን ይታወሳል ። በተለያዩ መዓዘናት በጦርነት ውጥረት ሲገጥመው፤ ምስኪን የድሃ ልጆችን ዛሬም በግዳጅ እያፈሰ ትውልዱን ለእሳት እራት እየዳረገው ይገኛል ። © በአበባየሁ ሰይፈ
የአርበኛ ዋሴ ከበደ የህይወት እና የትግል ታሪክ! "ጀግና ይሰዋል ትግል ይቀጥላል!" አርበኛ ዋሴ ከበደ የትውልድ ቦታው የራያ ቆቦ አርበት ልዩ ስሙ ቀጋይ አቦ የተባለ ቦታ ነው:: የ1ኛ ደረጃ ትምህርቱን እዛው ተወልዶ ባደገበት አገሩ የተማረ ሲሆን የ2ኛ ደረጃ ትምህርቱንም ቆቦ ሃይስኩል ጨርሶ በኋላም በመምህርነት ተመርቋል:: አርበኛ ዋሴ ከበደ ከሰሜኑ ጦርነት በፊት በመምህርነት ሞያ ሃገሩንና ወገኑን ያገለገለ የነበረ ሲሆን 2013 ዓ.ም በጀመረው የሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በነበረው ጥሪ ወደ ማሰልጠኛ ገብቶ ተመርቆ የአማራ ልዩ ሃይልን ተቀላቅሎ ታግሏል:: አርበኛ ዋሴ ከበደ በሰሜኑ ጦርነት የአማራ ልዩ ሃይል የቴዎድሮስ ክፍለጦር አር ፒ ጅ እና ብሬን ተኳሽ ሆኖ የታገለ ሲሆን በወቅቱ በነበረው ከፍተኛ ሴራና አሻጥር በመማረር ነፃ ሆኖ ህዝቡን ለማገልገልና ለመታገል ሲል ከልዩ ሃይሉ በመውጣት በትውልድ አካባቢው ወጣቶችን በማደራጀትና በማስታጠቅ ወደ ሽምቅ ውጊያ በመግባት በርካታ ጀብዶችን ፈፅሟል:: ከጥር 2013 ዓ.ም ድል በኋላም በይፋ ምስራቅ አማራ ፋኖን ተቀላቅሎ የቀድሞው የዞብል አምባ ብርጌድ አባል ሆኖ ሲታገልና ሲያታግል ቆይቷል:: በታሪካዊው የበላጎ ድልም የቀድሞው የዞብል አምባ ብርጌድ አባል ሆኖ ታሪክ ሰርቶ አልፏል:: አርበኛ ዋሴ ከበደ ከሰሜኑ ጦርነት በደቡብ አፍሪካው የፕሪቶሪያ ስምምነትና ድራማ መጠናቀቅ በኋላ ምስራቅ አማራ ፋኖ የአማራን ህዝብ ህልውና በትጥቅ ትግል ለማረጋገጥ ሚያዚያ 1/2015 ዓ.ም በረሃ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ሰራዊቱን እንደ አዲስ በማሰባሰብ በማደራጀትና በማስታጠቅ ጉልህ ሚና ተጫውቷል:: አርበኛ ዋሴ ከበደ ሰራዊት ከማሰባሰብ ከማደራጀትና ከማስታጠቅ ባሻገር ዞብል አምባ ክፍለጦር 2ኛ ሻለቃ ሻምበል መሪ ዘመቻ እና የሻለቃዋ አመራር ሆኖ በበርካታ ግንባሮች በርካታ ጀብዶችን በመፈፀም ብሎም ቆቦ ከተማ ድረስ ዘልቆ እየገባ ባንዳ ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድና በማፅዳትም የሚስተካከለው አልነበረም:: በመቀጠልም አርበኛ ዋሴ ከበደ የዞብል አምባ ክፍለጦር 2ኛ ሻለቃን እየመራ በራያ በየጁ በአምባሰልና በተለያዩ የቤተ-አማራ ግንባሮች በርካታ ድሎችን የተጎናፀፈ ሲሆን መስከረም 26/2016 ዓ.ም ቆቦ ከተማ ሆርማት እና መጋቢት 3/2016 ዓ.ም አምባሰል አካባቢ ሁለት ጊዜ የቆሰለና በፅናት የታገለ ጀግና ነበር:: አርበኛ ዋሴ ከበደ በዞብል አምባ ክፍለጦር ሻለቃ እየመራ ባስመዘገበው ድልና ከፍተኛ አፈፃፃም ምክንያት ወደ ዞብል አምባ ክፍለጦር አመራርነት በኋላም ባለው ከፍተኛ ውጊያን የማንበብና የማዋጋት አቅም የክፍለጦር ዘመቻ ሆኖ የመራ ሲሆን በቅርብ ጊዜም የምስራቅ አማራ ኮር 2 ምክትል ዘመቻ መሪ ሆኖ እስከመመረጥ የደረሰ ጀግና አርበኛ ነበር:: በመጨረሻም አርበኛ ዋሴ ከበደ ምኒልክ ዕዝ ባወጀውና ከመስከረም 14-30/2018 ዓ.ም በቆየው በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) የምስራቅ አማራ ኮር ሁለት ምክትል ዘመቻ አመራር ሆኖ በርካታ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ብሎም ዲፕሎማሲያዊ ድሎችን ተጎናፅፎ ከዘመቻው መገባደድ ማግስት የጠላትን ከባድ የማጥቃት ዘመቻ በመመከት ተኩለሽ ግንባር ከቆቦ ከተማ ቅርብ ርቀት ልዩ ስሙ ጠበለት የተባለ ቦታ ላይ ጥቅምት 7/2018 ዓ.ም በክብር መስዋዕትነትን ተቀብሏል:: በመጨረሻም እኛ የትግል ጓዶቹ አርበኛው ጓዳችን መስዋዕትነት የከፈለበትን አላማ ከግብ እናደርሳለን የህዝባችንን ህልውና እናረጋግጣለን! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የትግል ጓዶቹ ከትግሉ ሜዳ! አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ህዳር 7/2018 ዓ.ም
без подписи
без подписи
🔥#የደፈጣ_ጥቃት_ዜና‼️ አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ነበልባል ክፍለ ጦር ወሳኝ የተባለ የደፈጣ ጥቃት ሰነዘረ። ህዳር 6/03/2018 ዓ.ም የብልፅግውን ወንበር አስጠባቂ አራዊት ሰራዊት የመቶ አራተኛ ክፍለ ጦር ቀይ ቦኔት ለባሽ ኮማንዶ አባል #ከምንጃር ሸንኮራ ወደ በረኸት ወረዳ እሬሽን አድርሶ ሲመለስ በነበልባል ክፍለ ጦር በጀነራል ተፈራ ማሞ ብርጌድ በሸማቂው ናደው ሻለቃ ፋኖ አባላቶች አሮጌው ምንጃር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደፈጣ በወሰዱበት መብረቃዊ ጥቃት ከፍተኛ የሆነ የሰውና የንብረት ኪሳራ አድርሰውበታል። በዚህ ጥቃት የተደናገጠው የብልፅግና ጉጂሌ በእጁ ላይ የሚገኘውን ከቀላል እስከ ከባድ መሳሪያ ቢጠቀምም ሸማቂዎቹ በብርሃን ፍጥነት ከተሳፈረበት ከአስሩ መኪና #ሁለቱን ከነሰራዊቱ ከጥቅም ውጪ በማረግ በሰላም ወደ ቀጣናቸው ተመልሰዋል። መረጃውን አጠናቅሮ ያደረሰን የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ነበልባል ክፍለጦ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው። " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን" ©አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል #VOAamhara
🔥#የድል_ዜና‼️ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር የበፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር ድልን ተቀናጀ! በትላንትናው ዕለት በቀን 05/03/2018 የአብይ አህመድ አገዛዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር በፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር አናብስቶች አሉበት ወደ ተባለው ቀጠና የጠላት ኃይል ዘልቆ በመግባት ከበባ ለማድረግ ቢሞክርም በክንደ ነበልባሎች ሙትና ቁስለኛ ሆኗል። በመሆኑም ጠላት በሰፊው ከጉንዶ መስቀል በመነሳት ከግራኝ ሙቀጫ እስከ ሀንቁ ባለው ቀጠና ከስድስት ሰዓት በላይ የወሰደ ውጊያ በማድርግ የጡት ቆራጩ ኃይል ሶስት መኪና አስከሬን በመያዝ አይቀጡ ቅጣት በመቀጣት እንዲሁም የበፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር ትግስት ይርሳው ብርጌድ በማከፍታ ቀጭኔ ቀጠና በአደረጉት ውጊያ በጠላት ላይ ከፍታኛ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል። በመሆኑም የአብይ አህመድ ተላላኪ ባንዳና ወራዳ መከላከያ በዚህ አካባቢ ፋኖን አጠፋለሁ በማለት በዘጠኝ ሪጅመት በሜካናይዝድ የታገዘ ውጊያ ቢያደርግም በአሳምነው አናብስቶች ከጥዋቱ አስራ አንድ ስዓት እስከ ቀኑ ሰባት ሰዓት በመደበኛ ውጊያ ሲዋጉት ውለዋል። እንደለመደው አሁን የማህበረሰብ የሰብል መሰብሰቢያ ወቅት በመሆኑ አማራን ከምድረ ገፅ እንዲጠፋ ስልጣን ከያዘበት ቀን ጀምሮ በደራ አማራ ያላደረገው ያልሰራው ስራ የለም ነገር ግን ጀግኖች የአማራ እናት የወለደቻቸው የበፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር በአስደማሚ ሁኔታ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ድልን ተቀናጅተዋል። አማራ በታሪክ ጀምሮ ያልጨረሰው የትግል ምዕራፍ የለም አባቶቻችን ብዙ ጥበብን፣ ፅናትን፣ አይበገሬነትን አስተምረውን አልፈዋል። እኛም የአባቶቻችን ፈለግ ተከትለን በጥበብ፣ በፅናትና በአሸናፊነት መንገድ የጀመርነውን የአማራን ህዝብ ከመጥፋት የህልውና አዳጋ የማዳንን ሂደት በማይታመን ፍጥነት ወደ ፊት እየገሰገሰ በጠላት ላይ የበላይነት በመውሰድ ዳር ለማድረስ ጠንክረን እየሰራን እንገኛለን ። መረጃውን ያደረሰን የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ኛ ኮር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ ነው። " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን" © አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል #VOAamhara
በቅርብ ቀን የተዋቀረው የጊዜያዊ መንግስት የህዝብ ውይይቱ እያካሄደ ይገኛል። ህዳር 05/2018 ዓ.ም በእነማይ ወረዳ 3 ቀበሌወችጊዜያዊ መንግስት አስተዳደር ህዝባዊ ውይይት በማካሄድ ከውጊያው ጎን ለጎን የስርአተ መንግስት ተከላ ስራ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ደብር፣ ደንሳ እነቆራ እና አዲስ አለም ቀበሌዎች ላይ ህዝባዊ ውይይቶች ተካሂደዋል። የእነማይ ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት አመራሮች በሶስቱም ቀበሌዎች ህዝብ ያመነባቸውን የቀበሌ አስዳደር፣ ም/አስተዳደሪ፣ ፀሀፊ፣ ፀጥታ ዘርፍ፣ የፍትህ አካላት፣ ገቢና ሀብት አሰባሰብ፣ ወጣት ተጠሪ እና በሶስቱም ቀበሌዎች የህዝብን ችግር ለመፍታት ህዝብ ያመነባቸው ችግር ፈች ሽማግሌዎችን አዋቅሯል። አፋብኃ ቴወድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ አስተሳሰብ! ህዳር 05/2018 ዓ.ም
፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ!!! ችጓሊ እና አዲስ ቅዳም በጠላት ዋይታ ተሞልተዋል። ዛሬ ህዳር 5/2018 ዓ/ም አመለኛዋ ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ባደረገችዉ የሁለት ከተሞች ልዩ ኦፕሬሽን ጠላትን ስትረፈርፈዉ አርፍዳለች። በዚህ ከለሊቱ 12:00 ጀምሮ አዲስ ቅዳም ከተማ እና ችጓሊ ታዳጊ ከተማ ላይ በተደረገ ልዩ የማፅዳት ኦፕሬሽን አዲስ ቅዳም ከተማ የተከማቸዉ የብልፅግና ታጣቂ ከምሽጉ ሳይወጣ በአለበት የተረፈረፈ ሲሆን ችጓሊ ከተማ ዉስጥ በመግባትም ጠላት ይዘርፍባቸዉ በነበሩ ችጓሊ እና ችጓሊ አቅራቢያ የሚገኙ ቦታዎች ላይ መጠነ ሰፊ ማጥቃት በማድረግ ጠላትን ወደ አፈርነት ቀይራዋለች። በዚህም መሰረት ችጓሊ ላይ 6 የብልፅግና ታጣቂ ተወግዶ 13 ቁስለኛ ብዛት ካለዉ ቁሳቁስ ጋር ጋር በዉጤት አስመዝግቦ መዉጣት የተቻለ ሲሆን በአዲስ ቅዳሙ ኦፕሬሽንም 9 የተደምሰሰ ከ10 ቁስለኛ ጋር እስካሁን ባለዉ ማረጋገጥ ተችሏል። አጠቃላይ በዛሬዉ የሁለት ከተሞች ልዩ ኦፕሬሽን _ጥላየ እንየዉ _ምንችል ክንዴ _ ደሴ አብዬ የተባሉ የከተማ ወሻ |ፖሊሶችን| ጨምሮ 15 ጠላት ተደምስሶ፣ 23 በላዩ ቁስለኛ በመሆን የነገ ሞቱን ቀብድ ሲቀበል ፣ 8 ሰልጣኝ | ግልገል | የብልፅግና ታጣቂ ምርኮኛ፣ 3 ክላሽንኮቭ ፣ 2 የቃታ መሳሪያ 1የብሬን ሸንሸል 71 የብሬን ተተኳሽ ፣ 8 የክላሽ ካዝና ከ176 ተተኳሹ፣ 5 ኩንታል የተፈጨ እህል 20 ሊትር ዘይት፣ 150 ኪ/ግ ምስር 9 ኩንታል ድንች ከተለያዩ የማብሰያ ቁሳቁሶች ጋር ገቢ ተደርጓል ። አዲስ ትዉልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!!! ህዳር 5/2018 ዓ/ም
🔥#የማስጠንቀቂያ_መልዕክት‼️ #ህገወጥ_ደላሎች_ከድርጊታችሁ_ታቀቡ‼️ #ለደብረማርቆስ ከተማ ለሚገኙ #ደላሎች (አሰሪና ሰራተኛ አገናኝ አጄንቶች ) የሚመለከት ማስጠንቀቂያ ሲሆን ደብረ ማርቆስ ከተማና አካባቢው የሚገኙ ወጣቶች ሰርቼ ራሴንም ቤተሰብንም እለውጣለሁ ብለው ተስፋ በማድረግ ወደ ደላሎች ጋር የሚሄዱ ቢሆንም #እነዚህ_በወጣቶች_ህይዎት የሚነግዱ #የደም_ነጋዴ_ደላሎች ከአገዛዙ ሰዎች ጋር በመነጋገር( በመጣመር) ለአብይ ወምበር ጠባቂነት ወጣቶችን በስራ ስምሪት ስም ካንቀሳቀሱ በኋላ ወደ #ወታደራዊ_ማሰልጠኛ ጣቢያ አሳፍነው እንደሚወስዷቸው ንስር አማራ ተጨባጭ ማስረጃ ደርሷታል። ስለሆነም በዚህ ህገወጥ ተግባር የተሳተፋችሁ፣ የድሀን ልጅ ከአገዛዙ ሰዎች ጋር በመሆን ወደ ጦርነት እየማገዳችሁ ኑሯችሁን የምታደላድሉ ደላሎች ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እያሳሰብን ከድርጊታችሁ የማትቆጠቡ ከሆነ ስም ዝርዝራችሁን ሚዲያ ላይ የምናወጣና ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወሰድ እንደምናደርግ ከወዲሁ እናሳስባለን‼️ ደብረማርቆስ ከተማ ይሁን በሌሎች ከተማዎች ይህንን መሰል ድርጊት የሚፈፅሙ ግለሰብ ወይንም ተቋም ካለ ለንስር አማራ ትቆማ ትሰጡ ዘንድ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን‼️ ©ንስር አማራ #VOAamhara
አራት የቪአይፒ (VIP) ጥበቃወች ፋኖን ተቀላቀሉ። የአፋብኃ ቴድሮስ እዝ የ102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለ ጦርን በዛሬው እለት ከወገናችን ጋር አንዋጋም በማለት ከአድማ ብተና ተቋም በመውጣት ፋኖን የተቀላቀሉት፦ 1 መልካሙ አድኛው 2 አሸናፊ ጥጋቡ 3 እንዳለው አበበ 4 እሱባለው አቅነው የተባሉ ሲሆኑ ፦ ➢ 04 ክላሽ ➢06 ቦንብ ➢03 የወገብ ትጥቅ ➢06 ካዝና ➢270 የክላሽ ተተኳሽ መሉ ትጥቃቸውን በመያዝ ወደ ወገኖቻቸው የተቀላቀሉ ሲሆን በአመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ። ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ ህዳር 03/2018 ዓ.ም
ከመብረቅ ክ/ጦር የተሰጠ የሃዘን መግለጫ "በጓዳችን ድንገተኛ ሞት ልባችን ተሰብሯል ፤ ትከሻችንም ቀሏል !!" ህዳር 02/2018 ዓ.ም የመብረቅ ክ/ጦር ልዩ ተወርዋሪ ብርጌድ አርኖ ጋርኖ በተባለችው ከተማ ላይ የፀጥታ ተግባርን በማከናወን ላይ በነበረበት ወቅት የጠላትን የእጅ አዙር ተልእኮ ሳያነግብ እንዳልቀረ በተጠረጠረ ግለሰብ በተተኮሰ ጥይት የመብረቅ ክ/ጦር ልዩ ተወርዋሪ ብርጌድ ዋና አዛዥ የሆነው አርበኛ መልካሙ ሞላ መስዋእትነት ከፍሏል። ጀግናው ጓዳችን አርበኛ መልካሙ ሞላ ከመሪዎቹ የሚሰጠውን ማንኛውንም ግዳጅ በቀናኢትና በታዛዥነት መስዋእትነት እስከከፈለበት ጊዜ ድረስ ሲፈጽምና ሲያስፈጽም ነበር። ጓዳችን ትግሉ ከተጀመረ አንስቶ ከመብረቅ ክ/ጦር አመራሮችና አባላት ጋር በመሆን ሚካኤል ደብር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በጎንደር ሰማይ ስር የመጀመሪያውን ድሽቃ መማረክ የቻለ ክንዳችን ነበር። የክ/ጦራችን ብልህና ጠንካራ አርበኛ መልካሙ ሞላ መስዋእትነት የተሰማንን ሃዘን እየገለጽን አርበኛ መልካሙ ሞላና ሌሎች እልፍ ጀግኖች አርበኞቻችን የከፈሉለትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ከመቸውም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት እንተጋለን። ➢ለወዳጅ ፣ ለቤተ ዘመዱ እንዲሁም ለትግል አጋሩ በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን። አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ህዳር 4/2018 ዓ.ም
የአብይ አሕመድ ድሮን ተመትቶ ወደቀ! በትላንትናው ዕለት ማለትም ሕዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም በአፋር በረሀሌ ላይ ጥቃት ለመፈፀም እንደሔደ በተፈፀመበት ጥቃት ተመትቶ እንደወደቀ የኢትዮ 251 ሚዲያ ምንጮች ከአፋር ገልፀዋል። ምንጮች አክለውም ባለፉት ቀናት አካባቢው ላይ ከፍተኛ የድሮን አሰሳና ጥቃት ጭምር እንደነበር የገለፁ ሲሆን በትላንትናው ዕለት ግን ድሮኑ ተመትቶ እንደወደቀ ገልፀዋል። "ድሮኑ ተመትቶ ከወደቀ በኋላ ለአሰሳም ይሁን ለጥቃት ተጨማሪ ድሮን በሰማይ ላይ አላየንም።" ሲሉ የአካባቢው ምንጮች ለ251 ሚዲያ ገልፀዋል። አብይ አሕመድ 11 ድሮኖችን እንደታጠቀና ከትላንቱ ጥቃት በኋላ 10 እንደቀሩት የታወቀ ሲሆን፤ ባለፉት ወራት ብቻ ከ60 እስከ 70 የሚደርሱ የድሮን ጥቃቶችን እንዳደረገ የታወቀ ሲሆን የራሱን ዜጎች ለማጥቃት ከፍተኛ የሀገሪቱን ሀብት እያባከነ እንደሆነ ተገልጿል። በአየር ኃይልና በቤተመንግስት ከፍተኛ ትርምስ እንደተፈጠረ ለማወቅ ችለናል።
⚫️#አሳዛኝ_ዜና‼️ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ወገራ ወረዳ የደረሰ ሰብል በመሰብሰብ ላይ የነበሩ ከ10 በላይ ንፁሀን አርሶ አደሮች በጡት ቆራጩ የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ሀይል ስራ ላይ እንዳሉ በወጡበት ተገድለዋል ። አርሶ አደሮቹ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር አካል የሆነው ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር የሚንቀሳቀስበት ቀጠና ነዋሪ ሲሆኑ በዚህ አካባቢ የጀግኖች ፋኖዎቻችን ምትና ሀይል በተደጋጋሚ መቋቋም ያቃተው ሆድ አደሩ የብልፅግና ሰራዊት ዛሬም የበቀል በትሩን እንደተለመደው ንፁሀን ላይ በማሳረፍ የደረሰ ሰብልላቸውን በመሰብሰብ ላይ የነበሩ አርሶአደሮችን በጥይት ገድሏቸዋል ። ይህ አማራ ጠል የሆነው የብልፅግና መንግስት ተብየው በቀጠናው ምንም ጦርነት ባልነበረበት ሰዓት ሆን ብሎ አልሞና አቅዶ አርሶአደሮችን በመግደል ዛሬም አማራን ከምድረ ገፅ የማጥፋት ስራውን ቀጥሎበታል። ከተገደሉት ንፁሀን አርሶ አደሮች መካከል ጥቂቶቹ 1; አቶ ሞላ ደርብ ዕድሜ 56 ቀበሌ ሚጦ 2; አቶ ይርዳው ዘመነ ዕድሜ 28 ቀበሌ ሚጦ 3; ወጣት እያያለም ውዱ ዕድሜ 16 ቀበሌ ሚጦ 4; አስማረ በላይ ዕድሜ 38 ቀበሌ ጭልፋ ወንዝ 5; አለምነህ ቀኔ ዕድሜ 60 ቀበሌ ጭልፋ ወንዝ 6; ድረስ ፀሐይ ዕድሜ 62 ቀበሌ ጭልፋ ወንዝ 7; መልካሙ አለሙ ቁስለኛ ጭልፋ ወንዝ 8; ታደሰ ይግዛው ቁስለኛ ቀበሌ ሚጦ 9; አዋጅ በላይ ቁስለኛ ቀበሌ ሚጦ ሲሆኑ እንዲሁም ወ/ሮ ካሳየ ያለው የተባለች እናታችን ሳንቃ ጥቅም ቀበሌ የፋኖ አገርነው እናት ሰባት ልጆችን ያለ አባት ስታሳድግበት የነበረው ቤቷ ሙሉ በሙሉ በእሳት እንዲወድም በማድረግ ከእነ ልጆቿ ሜዳ ላይ እንድትወድቅ አድርገዋል። በአጠቃላይ በዚህ ጭፍጨፋ በርካታ የቁም እንስሳትን በመግደል እና ንብረታቸውን ሽጠው የገዙትን የጦር መሳሪያ ጭምር በመቀማት አርሶአሮችን ለከፍተኛ የሆነ ሰባዊ፣ ቁሳዊና ስነ- ልቦናዊ ጉዳት አድርሶባቸዋል ። ስለሆነም የሰባዊ መብት ተሟጋች ቦታው ድረስ በአካል በመገኘት ጉዳዩን አጣርተው ለአለማቀፋ ማህበረሰብና መንግስታት ይህ አምባገነን የሆነው የአገዛዙ ስርዓት በእየ ጊዜው ምን ያህል የገዛ ዜጎቹን እየፈጀ እንደሆነ እንዲያውቁልንና እንዲያሳውቁልን ጥሪ እናቀርባለን። ለሟቾች ነብሳቸውን በአፀደ ገነት እንዲያሳርፍልን ቤተሰቦች ደግሞ መጽናናትን እንመኛለን ። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!!! ©አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ #VOAamhara
የአርበኛ ጌትነት መሳፍንትን መስዋዕትነት አስመልክቶ ከዋርካው ምሬ ወዳጆ የተላለፈ መልዕክት! ዘመናትን ተሻግሮ የመጣውን የአማራ ህዝብ ግፍና በደል ለማስቆም ህዝቡንና መላ ቤተሰቡን አስተባብሮ ሲታገል የኖረው የትግል አባታችን አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ዛሬም የዘመናት ግፉ ወደ ዘር ማጥፋት አድጎ የህልውና አደጋ ውስጥ የገባውን የአማራ ህዝብ ለመታደግ እየተደረገ ባለው ተጋድሎ ከባድ ዋጋ እየከፈለ ይገኛል:: በዚህ መራር ዋጋ እየተከፈለበት ባለ ትግል ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ አጅሬ የተሰኘች ታዳጊ ከተማ የሰሜን አምባራስ ክፍለጦር አዛዥና የራስ አሞራው 3ኛ ኮር አስተዳደር ሃላፊ የሆነው አርበኛ ጌትነት መሳፍንት ተስፉ መስዋዕትነት የከፈለ ሲሆን በዚህም ከባድ ሃዘን እንደተሰማኝ ለመግለፅ እወዳለሁ:: ትግላችን እስከቀራኒዮና አባታችን አርበኛ መሳፍንት ተስፉ እስከ ቤተሰብዎ ለአማራ ሕዝብ በደማቅ የደም ቀለም እየተጻፈ ነውና ትውልድ በጀግንነትና ለአማራ ሕዝብ የተከፈለ እውነተኛ አማራነት ነውና ለእሱ በግሌ አመሰግናለሁ ማለት እወዳለሁ። ይህ መስዋዕትነት የአንድ ጀግና መስዋዕትነት ብቻ ሳይሆን ለአማራነት ዋጋ መክፈል ምን ማለት እንደሆነ በሕይወት እያሉ ህያው ምስክር ነዎት! የአማራ ፋኖ የጀመረውን የህልውና ትግል አጠናክሮ ይቀጥላል፣ የወንድማችን አርበኛ ጌትነት መሳፍንት ተስፉና በአውደ ውጊያ በወደቁ ጀግኖቻችን ዘመቻ አውጀን የአብይ አህመድን አገዛዝ ድባቅ እንደምንመታው ወደ ድልና ነጻነትም እንደምንሸጋገር ከምስራቅ አማራ ቀጠና ሁኜ ይሄን መልዕክት ሳስተላልፍ በታላቅ ቁርጠኝነትና ቁጭት ሁኜ መሆኔን መግለጽ እፈልጋለሁ። በመጨረሻም ለአርበኛ መሳፍንት ተስፉ፣ ቤተሰቦቹ፣ እና መላው የትግል ጓዶቹ ልባዊ መጽናናትን እመኛለሁ። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባል እና የምኒልክ ዕዝ ሰብሳቢ ዋርካው ምሬ ወዳጆ ህዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም
без подписи