tgindex
አፍላው ብዕሬ ✏✏

አፍላው ብዕሬ ✏✏

Статистика

አዳዲስ ያልተሰሙና ያልተደረሱ ልብ አንጠልጣይ ኢስላማዊ የሕይወት ታሪኮችን እዚህ ቻናል ላይ ታገኛላችሁ ለወዳጅ ዘመድ እንዲሁም ጓደኞቻችሁ ሁሉ share አድርጉ ስራችንን ከልብ እንሰራለን አታፍሩብንም ab love

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
5
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 526
−3 за 4 дн.
Сутки
−4
−0,26%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
105
22 постов
Вовлечённость
6,9%
к подписчикам
Постов в день
0,7
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
54
1/48двое суток
61
1/72трое суток
66

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗             "አሒል እና ፈራህ"        ✎...ፀሃፊ:-ሠምሐን ╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝       ።።።።።።•✿• ።።።።።።                 ክፍል  18       ።።።።።።•✿• ።።።።።። Ahil•••ከመስጂድ ተመለስኩ እና ወደ ቤት ስገባ ብዥ ይልብኝ ጀመር ለሊት ፈራህ ጋር ስናወራ አድረን አልተኛንም ድክምክም እያለኝ መኝታ ክፍል ገባሁ ፈራህን ነቅታ አገኛታለሁ ብዬ ነበር እንቅልፍ ወስዷታል ቆይ ምን አይነት ምቀኛ ቢሆን ነው ገና ያንን አንደበቷን ሰምቼ አልጨረስኩም እኮ ልቀሰቅሳት ፈለግኩ ግን አሳዘነቺኝ እና ተውኩት ከአንሶላው እግሯ ወጥቶ ስለነበር ሳለብሳት <<ሙሽራው መጣህ እንዴ?>> አለቺኝ በትንሹ ነቅታ ሳቅ እያለች <<አዎ መጣሁ ማነው ?…መጥቻለሁ>> አልኳት አሁንም በእንቅልፏ እንዳዘንኩ ነኝ ምን ብትለኝ ጥሩ ነው? <<በቃ ና>> <<ማለት?>> አልኳት ባልገባው ኮስተር ብላ <<ና ተኛ ትንሽ ሲነጋ እንነሳለን ኡሚ ቁርስ እኛ ጋር ናችሁ ብላን የለ?>> <<እ……እሺ>> አልኳት ሃሳቧን እንዳትቀይር ፈርቼ ሳልዋሽ የምነግራችሁ ነገር ቢኖር "ና" ስትለኝ እኔን አልመሰለኝም ነበር ከዛማ አላንገራገርኩም (የኔ የዋህ) ለማንኛውም መለስ ብዬ እንቅልፏን አመሰገንኩት ደግሞ……በቃ ይህን ያህል ሰፍ አትበሉ ቀጣዩ የባል እና የሚስት ወሬ ነበር 😄😄 ከ2 ሳምንታት በኋላ እንደአጋጣሚ የአንሃንን እና የአያንን የኒካህ ፕሮግራም ነበር እነሱን መብሩክ አልን ጀሚልም ከሃሲነት ጋር ሰርጓል ከ6 ወራት በኋላ ባባ ደግሞ ወደ ኮሎምቢያ ሄዷል ሁለተኛ ድርጅት አቃቁሟል አንዳንድ ስብሰባ እየበዛበት ስለሆነ እዛው ለመቀጠል አስቧል የእኛ ድርጅት ደግሞ አላህ ከፈቀደ የጋዜጣ ህትመቱ ባለበት ሆኖ ወደ ቲቪ እና ወደ ራዲዮ የዜና ስርጭት ለመቀየር መንገድ ላይ ነን ግን በዚህ መሃል እያመመኝ ተቸግሬያለሁ ለመኖር ይቀርሃል ከተባልኩት ጊዜ የቀረኝ ከ7 ወራት እያነሰ ነው በፊት ጊዜ(ፈራህን ሳላውቃት በፊት) መሞትን አልፈራም ነበር ብቻ የፈጠረኝን በመልካም ነገር ለመገናኘት የመሞቻዬን እለት የሚጠባበቅ ሰው ነበርኩ አሁን ግን ፈራሁ ፈራህን መለየት ምናለ የሆነ ከሞት ጋር የሚቀርብ ምርጫ ቢኖር? ከምሞት እና ፈራህን ከምለይ ያንን ስቃይ የተሞላበትም ህይወት ቢሆን እመርጥ ነበር ግን ምንድነው የማወራው እላለሁ እየደጋገምኩ በዚህ ሰዓት ከፈጠረኝ ጋር ላለመጣላት ትግል ውስጥ ነኝ መኪና እያሽከረከርኩ ስለነበር እጠነቀቃለሁ የእጅ ስልኬ ድንገት ጠርቶ ከሃሳቤ አባነነኝ እራሷ ናት የዋኋ ፍቅሬ ፈራህ air paduን ጆሮዬ ላይ ሰካሁት <<ሄሎ Nezik(የዋህ ፍቅር ማለት ነው ) አሰላሙ አለይኪ>> አልኳት <<ወአለይከ ሰላም የኔ ፍቅር በጣም አመሸህ እኮ ኡሚ እና አቢ ሲጠብቁህ ሲጠብቁህ ሰልችቷቸው ……>> ሳላስጨርሳት <<ወላህ በይ ሄዱ?>> አልኳት እያዘንኩ <<አይ ስትዘገይ ጊዜ እራት አቀረብኩላቸው እኔ ግን አልበላሁም አንተን እየጠበቅኩ ነው>> አለቺኝ <<አፍወን ሃቢብቲ መጣሁ>> አልኳት እና ተሰነባብተን ስልኩ ተዘጋ ያመሸሁት መስጂድ ውስጥ ነበር ሰሞኑን የተዋወኳቸውን ሁለት ሰለምቴዎችን እያስቀራሁ ገና ከቢሮ ስወጣ ያስጠነቀቀቺኝ ቢሆንም አረፈድኩባት ግን ይህን እያሰብኩ ወዲያው ደርሼ ነበር ሙሉ ቤተሰቡ ተገኝቷል ይቅርታ እየጠየቅኩ ገባሁ የምቀይረውን ልብስ ፈራህ አስቀምጣ ጠበቀቺኝ ታውቃላችሁ ከተጋባን ጊዜ ጀምሮ የልዑል ወይም የንጉሥ ህይወት ነው የምኖረው ማለት እችላለሁ ከቁም ሳጥን ልብስ መርጬም ሆነ አውጥቼ አላውቅም ፈራህ ይኸው ብላ ከተፍ ትላለች ምን ላምጣ? ምን ልውሰድ? ምን ጠፋህ ምን ሆንክ? ኧረ ሌላም ሌላም ያ!አላህ ገና እኮ ከእሷ ጋር የጀመርኩትን ህይወት በቅጡ አላጣጣምኩትም አትውሰደኝ እያልኩ እንዳለ <<ዛሬ ምን ነክቶሃል? አንተን በመጠበቅ ተማረሩ እኮ ኧረ ወጣ በል>> አለቺኝ ከሳሎኑ ተመልሳ መጥታ አሁንስ ልክ ናት በጣም ዘገየሁባቸው ግን ለእኔም ምን እንደሆነ አልገባኝም ፈራህ ሳታስፈቅደኝ ድንገት ተነስታ ዛሬ እራት ይኖረናል በጊዜ ና አለቺኝ መጣሁ ምንድነው ነገሩ አልገባኝም ብቻ ሁሉም ወደ ተሰበሰበበት ሳሎን ሄድኩ እና ከአዝራን እና ከአያን መሃል ተቀመጥኩ <<መጀመሪያ እራትህን ብላ>> አለቺኝ እጇ ላይ የታሸገ ወረቀት ይታየኛል ስጨርስ <<አሂል……>> አለቺኝ ሁሉም እያዳመጠ ነው ቀና ብዬ በስስት ቃኘኋት <<የይያዝኩት ወረቀት ምን ይመስልሃል? እስኪ ገምት>> አለቺኝ በዚህ ሰዓት ምንም ነገር ለማወቅ ጉጉት ውስጥ አይደለሁም እንዳታዝንብኝ ብዬ እንጂ <<ምንም ልገምት አልቻልኩም አንቺ ንገሪኝ>> አልኳት የመጀመሪያው ፈገግታዋ ትንሽ ዳመነ እንድታዝን ሳላደርጋት አልቀረሁም ምን አይነት ሰው ነኝ? የራሴን ስሜት ለመጠበቅ የእሷን ጎዳሁት የታሸገ ፖስታ ነበር ከፈተችው እና እየሰጠቺኝ <<ወረቀቱ የያዘውን መገመት ቢያቅትህም አባት መሆን ግን አይከብድህም አይደል?የኔ ፍቅር>> ╬╬═════════════╬╬                ᡣ𐭩 ይቀጥላል  ╬╬═════════════╬╬

  • ╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗             "አሒል እና ፈራህ"        ✎...ፀሃፊ:-ሠምሐን ╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝       ።።።።።።•✿• ።።።።።።                 ክፍል  17       ።።።።።።•✿• ።።።።።። Ferah•••<<ቁርስ እንብላ እርቦኛል>> ያላልኩት የለም ግን ዝም አንድ ሰው እንኳን እሺ ሊለኝ ሊያዳምጠኝ ፈቃደኛ አይደለም ለእኔ ግን ራበኝ ሆዴ ጮኸ ተንጫጫ ማለት እችላለሁ <<ኡሚ ቁርስ እንብላ?>> <<ቆይ አንድ ጊዜ ይህንን እንስራ>> <<ኡዚ እራበኝ እንብላ?>> <<ትንሽ ሷብር አድርጊ እንበላለን>> እየቀለዱብኝ ነው እንዴ? አናደዱኝ እና ወደ ማዕዱ ክፍል ራሴ ብቻዬን ሄድኩ አብሳዮቹ ሰርተው ሄደዋል ቀንሼ መብላት ጀመርኩ እየበላሁ እንዳለ የሆነ የመኪናዎች ድምፅ ከውጪ ይሰማኛል ግን ትኩረት አልሰጠሁትም መብላት ቀጠልኩ ስለምግቡ ባልነግራችሁ ይሻላል በጣም ነው የሚጣፍጠው እሱን እያጣጣምኩ እንዳለ ኑር ወዳለሁበት መጣች <<አ…እህቴ ሰዎቹ መጥተዋል እኮ አንቺ ትበያለሽ?>> <<እነማን ናቸው?>> <<ከሆስፒታል መውጣትሽን አስበው ነው የመጡት>> <<እንደዛ ከሆነ ተያቸው ትንሽ ልብላ>> እሺም እምቢም ሳትለኝ ሄደች ኡዘይማ መጣች <<ፈራህ በቃሽ ነይ እንግዳዎቹ ከመጡ እኮ ቆዩ ንቀትም ይመስላል>> <<ኡዚ አሁን ደህና ነኝ ተሽሎኛል ማጋነን አያስፈልግም እናንተ አስተናግዷችው እኔ ትንሽ በልቼ እመጣለሁ>> እሷም ሄደች የአላህ ምግቡ እንዴት ነው የሚጥመው የጥጋብ እንዲሁ ስበላ ስበላ አቢ መጣ ፈራሁ በጣም ነው የፈራሁት ቆይ ኑር እና ኡዚ ግን ምን ነክቷቸዋል? ያልኳቸውን በሙሉ ለአቢ ነገሩት እንዴ? እንባዬ መጣ <<አቢ አፍወን ላናድድህ ፈልጌ አልነበረም ስለራበኝ እኮ ነው ወላህ አሁን እመጣለሁ ስል ነው የመጣኸው>> አልኩት እየፈራሁ <<እንደዛ አይመስለኝም እንግዳው እዚህ ኪችን እንዲመጣ ፈልገሽ ነው>> <<ወላህ እርቦኝ እኮ ነው ላናድድህ ብዬ አልነበረም>> <<እንግዳው ግን አልመጣም ስትዪ እንግድነቱን አዋርዶ መጥቷል አንቺን ለማግኘት>> ሲለኝ የሚያወራው ቀልድ ይሁን እውነት አልገለፅ አለኝ በደንብ ሳየው ግን ከጀርባው አንድ ሰው አለ አቢን ተከልሎ የመጣ ድምፄን ዝቅ አድርጌ <<አቢ ከጀርባህ ያለው ሰው ማነው?>> አልኩት በሹክሹክታ <<እኔ ነኝ>> <<ሱብሃን>> ብዬ ጮህኩ ስደነግጥ የሚመጣልኝ ቃል ነው ከተከለለበት የአቢ ጀርባ ወጥቶ ሳየው ደንግጬ ፊቴን ወደ መስኮቱ አዞርኩ ጀርባዬን ሰጥቻቸው መለፍለፍ ጀመርኩ ያየሁት አሂልን ነው? አይ…አይደለም ግን አሂል ነበር የኔው አሂል ነበር <<አይ እሱ አይደለም france ሄዷል እሱ አይደለም>> ተመልሼ ዞርኩ እራሱ ነው <<አሽሃዱ አላኢላሃ ኢለሏህ……>> እስከ መጨረሻው ጀርባዬን ሰጥቻቸው ማልቀስ ጀመርኩ <<ፈራህ አላህን ፍሪ በቃ አታልቅሺ>> አቢ ነው ያለኝ ፊቴን ታጥቤ ከተረጋጋሁ በኋላ አሂል <<ብቻሽን አስችሎሽ ትበያለሽ?>> አለኝ ፈገግ እያለ ዛሬ ገና ፈገግ ሲል አየሁት እኔም ፈገግ ስል አቢ <<አላህን ፍሩ መጀመሪያ ኒካህ ይደረግ የዛኔ ታሽኮረምማታለህ አሁን ግን አይቻልም>> አለን እየተሳሳቅን ውደ ሳሎን ሄድን እና ሁላችንም አውፍ ተባብለን የቀረበውን ምግብ ተመገብን ሳልነግራችሁ የረሳሁት ደግሞ ኒካህ ከመታሰሩ በፊት ሁለት የአቢ ጓዶች መጥተው ነበር ዱዓ ተደርጎልን ኒካህ ታሰረ በሁለተኛው ሳምንት ደግሞ ሰርጋችን እንዲሆን ተቆርጦ ተለያየን አቤት የቀኑ መርዘም አቤት የለሊቱ መርዘም አያልቅም ወደ ድርጅቱ ተመልሷል ግን ከመጋባታችን በፊት አልጀመረም እያለ እያለ ቀኑ ለማለቅ ሶስት ቀናት ሲቀሩት የሰርግ ቀሚስ ለመግዛት ወጣን ኡሚ አብራን ስለነበረች ምንም ማውራት አልቻልንም እንዲሁ ተያይተን ተለያየን አሁን ያለሁት በሰርጌ እለት ላይ ነው ዙሁር ሷላት ከሰገድን በኋላ መሽራው አሂል መጣ በጥሩ ሁኔታ ተዘጋጅቶ አበቃ እና እንደ ሴት ወግ አቢኧና ኡሚን ኑርን እና ኡዚን እንዲሁም ለእኔ ሁለተኛ አባቴ የሆነውን አዝራን ስለይ ተለቃቀስን ግን የምፅናናው በምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? አሁንም እየሄድኩ ያለሁት እንደዚህ አይነት ቤተሰብ ከአላህ ጋር ወደ ምፈጥርበት ቦታ ነው ይህ ቤተሰብ ዳግም በእኔ እና በአሂል ቤት ውስጥ ለመፈጠር የሚያግደው ምንም ነገር የለም የሰርጉን ምሽት ልብሶቻችንን ቀይረን ለሊቱኑ ሙሉ ማለት እችላለሁ ስናወራ ስናወራ አነጋን የባጡን የቆጡን ኮሎምቢያ ስላሳለፋቸው ህይወት እናቱን በትንሹ እንዴት እንደሚያስታውሳት ስናለቅስ ስንስቅ ፈጅር አዛን አለ ሁለታችንም ሰክረናል ማለት ይቀላል አይኖቻችን የጋለ እና ሲበራ የኖረ አምፑል ታውቃላችሁ የዛን ያህል ሲቅበዘበዙ ነበር እንደምንም መስጂድ ስገድ ብዬ አሂልን ከአዲሱ መኖሪያ ቤታችን አስወጣሁት እኔም ሱና ሳልጨምር የሞት ሞቴን ሰግጄ ተነጥፎ ባልተበላሸው አልጋ ላይ ሄጄ ተኛሁ ቀጣዩ ተግባር የእንቅልፍ ነበር ╬╬═════════════╬╬                ᡣ𐭩 ይቀጥላል  ╬╬═════════════╬╬

  • ╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗             "አሒል እና ፈራህ"        ✎...ፀሃፊ:-ሠምሐን ╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝       ።።።።።።•✿• ።።።።።።                 ክፍል  16       ።።።።።።•✿• ።።።።።። Ferah•••ዛሬ ከሆስፒታል የምወጣበት ቀን ነው አቢ ያመጣልኝን ልብስ ቀይሬ አብረን ወጣን ስለአሂል ምንም አላለኝም አልተቆጣኝም በቃ እኔም በአሂል መሄድ ባዝንም በሚሄድበት ሁሉ ስኬታማ እንዲሆን በሰገድኩ ቁጥር ዱዓ ማድረጉን አልረሳሁም ከአቢ ውጪ ሊወስደኝ ማንም አልመጣም ወደ ቤት ከደረስኩ በኋላ ግን ተመለሰልኝ ኡዘይማ እና ኑር ከአንሃን ጋር ኡሚንም ጨምሮ ቤቱን ማስዋብ ተያይዘዋል <<ምንድነው የምታካብዱት?>> አልኳቸው በእውነቱ ሶስት ቀን ሆስፒታል ለገባ ሰው ይህ ሁሉ አይገባም እየመጡ ሳሙኝ እና በቃ እንዲሁ ደስ ስላለን ነው አሉኝ እሺ ብዬ በጣም ስለናፈቀኝ ኢልሃንን ከአዝራን ተቀበልኩት እና እሱን ማጫወት ጀመርኩ ኪችን ውስጥ ከዚህ በፊት የማላውቃቸው ሁለት ሴቶች ምግብ ያበስላሉ <<ኧረ ነገሩን እንዲህ አታግዝፉት ደህና ነኝ ለምንድነው ይሄ ሁሉ ድግስ>> <<እስቲ ዛሬን እንደሰት ሰሞኑን በአንቺ ምክንያት ቤተሰቡ ተረባብሿል>> አለኝ አያን አያንም ከእኛ ጋር መኖር ጀምሯል ብዙ አዲስ ነገር እያየሁ ነው ገረመኝ ከጠዋቱ 02:10 ላይ ፀጉሬን የምትሰራኝ ሴት መጣች እንዳልጠራኋት ልቤ ያውቃል ስጠይቃት ኡዘይማ እንደጠራቻት ነገረቺኝ ግራ እየገባኝ ወደ መኝታ ክፍሌ ወሰድኳት ተሰራሁ ስጦታ ነው ብሎ አቢ የሆነ ነጭ ቀሚስ ሰጠኝ <<ኢላሂ ምንድነው ይሄ?>> <<ስጦታ ነው>> <<ከሞት የተነሳሁ ይመስል አቢ በጣም አገዘፋችሁት ነገሩን>> <<ድርጅቱ 2million እንዳተረፈ አውቀሻል?>> አለኝ <<ወይ ጉድ! ታዲያ እንዲህ የምናደርገው ለድርጅቱ ነው አትሉኝም? ግራ አጋባችሁኝ እኮ………>> ጭራሽ ፀጉራችንን እየተሰራን እንዳለ ኑር አያን እና አንሃን ኒካህ እንደሚያደርጉ ምናምን ነገረቺኝ ደስ አለኝ እንዳልኳችሁ በሶስት ቀን ውስጥ መአት ነገር ነው ያመለጠኝ 🍂 🍂 🍂 Ahil•••ከቁሙ መልበሻ መስታወት ፊት ለፊት እየለበስኩ ነው ባባ እና ጀሚል ግን ከጨረሱ ቆይተዋል እኔን ነው እየጠበቁ ያሉት በእነዚህ ቀናት ውስጥ የሆነውን ሁሉ መናገር አልችልም ፍፁም ህልም ነበር የሚመስለው የመጀመሪያው ነገር የጀሚል እጮኛ ሃሲነት ልትመረቅ ነው ለሰርግ ሲጠብቁ የነበረው የእሷን ትምህርት ነበር በዚህ ጀሚል ተደስቷል ዛሬም ወደ ምንሄድበት ቦታ አብራን ለመሄድ ፈልጋለች አልከለከልናትም ስለጨረስኩ ሁላችንም ተያይዘን ወጣን ጀሚል እና ሃሲነት በአንድ መኪና እኔ እና ባባ ደግሞ በሌላ መኪና ከቀናት በፊት ስለተፈጠረው ነገር ስነግራችሁ ከሆስፒታሉ ወጥቼ አግዳሚ ወንበር ላይ እንደተቀመጥኩ ሃጂ ሱለይማን መጥተው ከአጠገቤ አረፍ አሉ <<ወደ france ልትሄድ ነው አይደል?>> አሉኝ በዝምታ የተኛውን የNeeraj ሃይቅ በጥልቀት እየተመለከቱ <<አዎ ልሄድ ነው የመጣሁት የድርጅቱን ድርሻዬን ለመሸጥ የፈራህ ፊርማ ያስፈልግ ነበር>> አልኳቸው በረጅሙ እየተነፈስኩ <<ለምንድነው ድርሻህን ለመሸጥ የወሰንከው?>> በልቤ"ለምንድነው? እንዳልገባው ሰው የሚጠይቁኝ (በሚል ዘወር ብዬ አየኋቸው) ትላንት ማታ ልጄን አልፈቅድልህም ማለታቸውን ረስተውት ነው?"አልኩኝ ይበልጥ ከፋኝ <<ምነው? ለመልስ ዘገየህ?>> አሉኝ ፈገግ ብለው እያዩኝ ፈገግታቸው ከፈራህ ፈገግታ ጋር ይመሳሰላል አሁን ይህን የማስተውልበት ሰዓት አይደለም አልኩ ለራሴ <<ከአሁን በድርጅቱ ውስጥ መቀጠል ስለማልችል>> <<ለምንድነው? መቀጠል የማትችለው?>> አላህ ሆይ¡! ምንድነው የላክብኝ ለምን እዚህ ተቀመጥኩ እስከማለት ደረስኩ እሳቸው ጋር ግን አይደለም መበሳጨት ከፈገግታ ውጪ ፊታቸው ላይ አይነበብም ውስጤ ያለውን እንድናገር መንገድ እየሰጡኝ ስለመሰለኝ ለማስረዳት መሞከር ጀመርኩ ነገሮች ይቀየራሉ ብዬ ሳይሆን አለመናገሬ ህመም እንዳይሆን ብዬ ነው ስናገር ፊታቸውን ላለማስተዋል ወደ ሃይቁ ዞርኩ <<……ከዚህ በላይ እዚህ የመቆየት ሃሳብ የሌለኝ ከአሁን በኋላ ጊዜው የሸይጧን ነው ሃራም እንዲገባብን አልፈልግም ምክንያቱም ሁለታችንም መፈላለግ ከጀመርን ጥሩ አይመጣም የሸይጧን ጥሪ ተፈፃሚ ይሆናል>> ዘወር ብዬ ፊታቸውን ለመረዳት ሞከርኩ ከቀድሞው እርጋታቸው ሳይወጡ <<ገባኝ>> አሉኝ <<አልገባዎትም>> ስላቸው ዞረው አዩኝ እና ፈገግ አሉ እኔ ግን መናገር ቀጠልኩ <<ያልገባዎት ነገር አለ ባየኋት ቁጥር ምን ያህል ለራሴ ራሴን ጥፋተኛ እንደማደርገው አያውቁም እና ምን ያህል ጊዜ በእሷ ጉዳይ ጌታዬን እንዳስቸገርኩት አልገባዎትም አላህ በመካከላችን ከሌለ ፍቅር ለእኔ የሙዚቃ ግጥም አይደለም በቃላት የሚዋብ እና የሚሽሞነሞን ስለዚህ ልሂድ ለእኔም ለእሷም መሄዱ ጥሩ ነው የጥላቻ ሽሽት ሳይሆን የፍቅር ሽሽት ነው>> ከዚህ በላይ መቀጠል ስላልቻልኩ ለመሄድ ተነሳሁ ዝም አሉኝ ጥቂት ከተራመድኩ በኋላ ግን <<ከዚህ በኋላ ፈራህ ታገባለች የራሷም ቤተሰብ ይኖራታል>> አሉኝ ጮክ ብለው ሊያናድዱኝ ነው እንዴ የሚፈልጉት ወንድነቴን ሲፈታተኑት ታወቀኝ እርር አልኩ ቀጥለው <<ያገባች እንደሆነ አንተን ብቻ ነው የምታገባው>> አሉኝ አይ ጆሮዬ አቃጭሎብኝ ነው ብዬ ንግግራቸውን ችላ በማለት ወደ መኪናዬ መራመድ ቀጠልኩ <<አንተ ግን አትፈልጋትም መሰለኝ>> አሉኝ በድጋሚ አሁን አልቻልኩም ዘወር አልኩና <<ለምንድነው በእኔ ላይ የሚጫወቱት ሃጂ ወደ ኋላ ላለመመለስ ወስኛለሁ እኮ>> አልኳቸው <<አሂል አንተ እርግጠኛ አልመሰልከኝም ፈራህን ታገባታለህ? ወይስ አታገባትም>> አይኖቻቸውን እያየሁ ፀጥ መልሰው <<ፍቅር እምነት ይፈልጋል ካልሆነ አላህ እንዴት ይኖርበታል? አላህ ወደዳቸው እነዛን በእሱ ያመኑትን በአላህ የምታምን ከሆነ ፈራህ የአንተ ናት ካልሆነ ሽሽትህ ትክክለኛ ውሳኔ ነው>> ግራ አጋቡኝ የፕሮፌሰር ቃል ነው የሚጠቀሙት <<ምን እንድሎት ነው የሚፈልጉት?>> <<አጂብ አንቱ አትበለኝ አንተ በለኝ አማችህ ልሆን እኮ ነው>> አሉኝ ከወንበሩ እየተነሱ ከሩጫ ባልተናነሰ ተራምጄ አቀፍኳቸው እቅፋቸው ውስጥ ገብቼ አለቀስኩ አረጋጉኝ እና ተቀምጠን ብዙ አወራን ግን ስለዚህ ነገር ፈራህ ልታውቅ እንደማይገባ ነገሩኝ ሙፋጃዓ(surprise) ነው በቀጣዩ ቀን ከባባ ጋር ተነጋገሩ እና ይህን ይመስላል እየሄድን ያለነው ከፈራህ ጋር ኒካህ ለማሰር ነው እሱን ደግሞ አታውቅም የኔ የዋህ ለጥርጣሬ አልተፈጠረችም ይሄኔ ምን ብለው አሳምነዋት ይሁን ?????? 💍 💍 💍 ╬╬═════════════╬╬                ᡣ𐭩 ይቀጥላል  ╬╬═════════════╬╬

  • ╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗             "አሒል እና ፈራህ"        ✎...ፀሃፊ:-ሠምሐን ╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝       ።።።።።።•✿• ።።።።።።                 ክፍል  15       ።።።።።።•✿• ።።።።።። <<ፈራህ ብቻሽን ከአጂ ነብይ ጋር……>> ተናግረው ሳይጨርሱ ፈራህ<<አቢ ነርሷ አለች ብቻዬን አይደለሁም>> አለቻቸው አንቱ እያልኩ የምነግራችሁ ከእውቀታቸው…

  • ╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗             "አሒል እና ፈራህ"        ✎...ፀሃፊ:-ሠምሐን ╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝       ።።።።።።•✿• ።።።።።።                 ክፍል  15       ።።።።።።•✿• ።።።።።። <<ፈራህ ብቻሽን ከአጂ ነብይ ጋር……>> ተናግረው ሳይጨርሱ ፈራህ<<አቢ ነርሷ አለች ብቻዬን አይደለሁም>> አለቻቸው አንቱ እያልኩ የምነግራችሁ ከእውቀታቸው አንፃር ነው እንጂ ሸምግለው ወይም አርጅተው አይደለም አብሯቸው የመጣውን ወጣት <<ግባ አያን አረፍ በል>>አሉት ማንነቱን ባላውቀውም ሳየው ቅናት ቢጤ አደረብኝ Ferah•••አሂል ሲመጣ ብደናገጥም ደስ አለኝ ፍላጎቴ የነበረው በየትኛውም አጋጣሚ አቢ አሂልን እንዲያየው ነበር በጣም የሚያሳዝን ባህርይ ነው ያለው ስለዚህ አቢ ይስማማበታል ብዬ ለራሴ ራሴን አታልላለሁ ነርሷ ወንበር ሰጥታቸው ሁሉም ተቀምጠዋል ኡሚ መድሃኒቶቹን ይዛ ተመለሰች አሂል ስልኩ ሲጠራ ለማናገር ይቅርታ እየጠየቀ ወጣ ኡሚ ማን እንደሆነ ስትጠይቀኝ ነገርኳት <<አይኑን ምን ሆኖ ነው?>> አለቺኝ <<ማታ አቢ አናገረው አልቅሶ ይመስለኛል>> አልኳት አሳዘናት <<እሱ ነው ማታ በ3 አመቱ እናቱን አጥቷል የተባለው>> ስትለኝ <<አዎ>> <<እንግዲህ አላህ አላለም እንጂ ወድጄዋለሁ ብታገቢው ቅር አይለኝም>> <<አውቃለሁ ኡሚ ለአቢ አግባቢው ነው እሱ ካልፈቀደ ምን ትርጉም አለው?>> <<እሺ>> አለቺኝ አቢ <<ምንድነው በግላችሁ የምትንሾካሾኩት ረሳችሁን መሰለኝ>> አለ በትላንትናው እለት አያን ወደ አቢ ቢሮ ስላልመጣ የማየት እድሉን አላገኘሁም አሁን ግን አቢ ሲጠራው ማንነቱን አወቅኩ የሚያስፈሩ እና ሰማያዊ የአይን ብሌኖች አሉት ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ አሁን የምገኝበትን ሁኔታ ጠየቀኝ ነገርኩት ወደ አቢ ዞሮ የሆነ ነገር አለ ትንሽ እኛ ከምንጠቀመው አረብኛ ለየት ይላል ምን መሰላችሁ ያለው <<ሃጂ ቆይ ስንት ሴት ልጅ ነው ያሎት?(የአቢን መልስ ሳይጠብቅ) ወደድኳት ያልኩት ይህቺን አልነበረም>> ብሎ አለው አቢ ግራ ገባው መቼም ኑርን ወደድኩ ብሎ እንደማይል ተስፋ አለኝ ሌላ እኛ ቤት ሴት ልጅ የለም ማንን አይቶ ይሁን? እያልኩ እንዳለ አቢ መለሰለት <<አያን እኔኮ ከእሷ ውጪ ለትዳር የደረሰች ልጅ የለኝም ማንን አይተህ ነው?>> አለው ለማስረዳት እየሞከረ እንዳለ በሩ ተንኳኳ እና ተከፈተ አንሃን ነበረች <<አሰላሙ አለይኩም>> <<ወአለይኪ ሰላም>> አልናት ግን የኔ ልብ ወደ ቀድሞው ወደ አያን ጉዳይ ተወስዶ ነበር መጥታ ኡሚን ቀጥላ እኔን ሳመቺኝ ከተኛሁበት አልጋ ጫፍ ላይ ስትቀመጥ <<ሃጂ ያልኮት እሷን ነው እሷ ልጆት አይደለችም እንዴ?>> አንሃን ዘወር ብላ አያንን አይታው ወደእኔ እየዞረች <<ማነው?>> አለቺኝ ሲጀመር እኔ አለመሆኔን ከተናገረ በኋላ ፊቴ ፈገግታ ብቻ ሆኗል አሂልም ስልኩን አናግሮ ተመለሰ ቆይ ምን ልበላችሁ በአላህ ላይ የዛን ያህል እርግጠኛ ሆኜ አላውቅም ነበር ግን በዛች ቅፅበት አሂል የኔ መሆኑን በአላህ ላይ አረጋግገጥኩ አንሃን ታናሽ ወንድሟን አቢ ወደ ሚሰራበት መርከዝ ትወስደውና አቢን ለማናገር ወደ ቢሮው ትገባለች አናግራው ስትወጣም ቢሆን አቢ የልጁን ያህል ስለሚወዳት የግቢውን አንዳንድ ነገሮች አስጎበኛት ሲያስጎበኛት አያን አያት ወደዳት በዛ ሰሞን እኔም ለአቢ ምግብ ለማድረስ እመላለስ ስለነበር አያን እኔን እንደወደደ እርግጠኛ ለመሆን በቃ አሁን ግን አንሃን መሆኗን ሲነግረን በቃ አላህን እንዴት ላመሰግነው እንደምችል ግራ ገባኝ የደስታ እንባ አነባሁ ግን በዚህ መሃል አሂል ከዱባይ ሊወጣ እንደሆነ ነግሮኝ ድጋሚ አዘንኩ አቢ ፊት አትሂድ ብዬ እስከመለመን ድረስ አቢ ተናደደብኝ እኔን ለመናገር የአሂልን መሄድ እንደሚጠብቅ ያስታውቅ ነበር የእኔም አሂልን መለማመጥ የመጣው ይምጣ ያልኩ ይመስላል ድምፄን ዝቅ አደረግኩት አሂል ከአልጋው ስላራቀ ይሰማዋል <<አሂል ለምንድነው? የምትሄደው? እ?……አሂል በዚህ ሰዓት ልነግርህ የማልችቸው ብዙ ነገሮች ተፈጥረዋል አሁን ተሰናብቶን የሄደው ልጅ ሳይቀር ብቻ ብዙ ብዙ ለማን ትተኸኝ ነው የምትሄደው?>> <<በቃ ሁሉንም ነገር እረስቼዋለሁ አንቺም እርሽው በአላህ እንዳታዝኚብኝ ግን እኔ እና አንቺ አብረን የምንሆን አይመስለኝም>> <<ማለት? ምን ማለት ነው? በቃ እንዲህ ነው የሚሆነው?>> <<እንዳትናደጂ ግን በዚህ ሰዓት ሃጂ ቢፈቅዱ እንኳን ባባ አይፈቅድልኝም ሳልፈልግሽ ቀርቼ ሳይሆን አላህ አላለውም በቃ>> በተኛሁበት እንባዬ ፈሰሰ አንሃን እና ኡሚ ከውደ ጥግ ያወራሉ አቢ አያንን ለመሸኘት ወጥቷል <<ለምንድነው አቶ ዘይድ የእኔን እና የአንተን ዘዋጅ የማይፈልገው?>> <<እሱን ልነግርሽ አልችልም ባህሪሽ መጥፎ ነው ብሎ ሳይሆን ለአንቺ ስላዘነ ነው ወላህ በጣም ይወድሻል ግን…>> እንባው አቀረረ እኔ ቀድሞውንም እያለቀስኩ ነው <<ግን ምን?>> አልኩት <<ግን ብንጋባ በራሱ በሃያት ለመቆየት ከሁለት አመት የዘለለ ጊዜ የለኝም አንቺ ደግሞ መኖር ያለብሽ ጤነኛ እና አንቺን ሊያስደስትሽ ከሚችለው ጋር ነው ባባ ለአንቺ አስቦ ነው እንዳላገባሽ የከለከለኝ ለእኔም ብሆን እንድትጎጂ አልፈልግም የመጣሁት ይህንንም ልነግርሽ ነው>> <<እኔ ካልፈለግኩስ? ከአንተ ውጪ ማንንም ካልፈለግኩስ አሂል?>> <<እሱን አላውቅም ፈራህ>> <<እኔም አላውቅም ህይወት ምን እንደሚሆን የትኛው ሰው ነው ደግሞ አትሞትም ተብሎ የምስክር ወረቀት የተሰጠው? አንተ ልታገባኝ ፈቃድህ ካልሆነ እሺ ግን አስበኸው አታውቅም? ዛሬ ልሞት ከፈለገ የሚያግደው አለ? አላህን የሚከለክለው አለ? አላውቅም ግን ካልወደድከኝ ይሁን መሄድ ትችላለህ እና እንዳትመለስ በየትኛውም አጋጣሚ ላይህ አልፈልግም>> አልኩት እና ፊቴን ከእሱ በተቃራኒ አዞርኩት <<ፈራህ>> <<በቃ ሂድ አልፈልግም የዞርኩት ስትሄድ ላለማየት ነው ሂድ በቃ ሂድ>> ቀስ ብሎ ከተቀመጠበት ተነስቶ ከክፍሉ ሲወጣ ኡሚ ምን እንደተፈጠረ ጠየቀቺኝ <<ወደ france ሊሄድ ነው ሊሰናበተኝ ነበር የመጣው >> ብዬ መናገር አቃተኝ ማልቀስ ብቻ ለምን እንዲህ እየሆነ እንዳለ እየጠየቅኳት ማማረር ጀመርኩ ምንም ሊያባብሉኝ ቢሞክሩ አልቻሉም አንዱን አለፍኩ አልሃምዱሊላህ ብዬ ሳልጨርስ አንዱ ይተካል ጭራሽ አሁን አሂል አረጋግጦ እንደማያገባኝ ነገረኝ በሽተኛ ነው የሆንኩት ፍቅርን ጠላሁ እንደውም የሆነ አባባል ላስታውሳችሁ ፍቅር ጎጂ ሆኖ ሳይሆን ሃራም ነገሮች ሁሉ የተፈጠሩት ለጉዳት ነው እንደዛ አስቡት የዛን እለት በጣም አልቅሼ ስለነበር በድጋሚ እዛው ሆስፒታል እንድተኛ ተደረገ 🍂 🍂 🍂 Ahil•••ከሆስፒታሉ ከወጣሁ በኋላ መረጋጋት አቃተኝ ጥቂት ተራምጄ ካገኘሁት ወንበር ላይ አረፍ ብዬ ነገሮቹን እየመላለስኩ ማሰብ ጀመርኩ በሃዘን ውስጥ ያለ ሰው ከቆመ ይቀመጥ ከተቀመጠ ደግሞ ይነሳ ያሉትን የነብያችንን ቃል አስታውሼ ነው (በእሳቸው ላይ ፍፁም ሰላም ይውረድና) ምክንያቱም በጂን ለመጠቃት በሃዘን ውስጥ ያለ ሰው ቅርብ ነው በረጅሙ ስተነፍስ አያን የተባለውን ወጣት ለመሸኘት ወጥተው የነበሩት ሃጂ ተመልሰው ነበርና ሲያዩኝ ወደእኔ መጥተው ከጎኔ በነበረው ጥቂት ቦታ ላይ አረፍ አሉ ╬╬═════════════╬╬                ᡣ𐭩 ይቀጥላል  ╬╬═════════════╬╬

  • ╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗             "አሒል እና ፈራህ"        ✎...ፀሃፊ:-ሠምሐን ╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝       ።።።።።።•✿• ።።።።።።                 ክፍል  14       ።።።።።።•✿• ።።።።።። Ferah•••ፈጅርን ሰግጄ ወደ ነበርኩበት አልጋ ተመለስኩ እና ለነርሷ <<አሁን እንደነቃሁ መናገር ትችያለሽ>> አልኳት ነገረቻቸው ገቡ ኡዘይማ እና ኑር ወደ…

  • ╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗             "አሒል እና ፈራህ"        ✎...ፀሃፊ:-ሠምሐን ╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝       ።።።።።።•✿• ።።።።።።                 ክፍል  14       ።።።።።።•✿• ።።።።።። Ferah•••ፈጅርን ሰግጄ ወደ ነበርኩበት አልጋ ተመለስኩ እና ለነርሷ <<አሁን እንደነቃሁ መናገር ትችያለሽ>> አልኳት ነገረቻቸው ገቡ ኡዘይማ እና ኑር ወደ ቤት ሄደዋል የቀሩት ኡሚ ፣አቢ እና አዝራን ናቸው አቢን ሳየው "ምን ሆንሽ?" ብሎ እንዲጠይቀኝ ተመኘሁ ምክንያቱም ሳልደብቅ ፍቅር ውስጥ እንደሆንኩ እነግረዋለሁ ብዬ ወስኛለሁ ግን <<አይዞሽ ሁሉም ነገር ይገባኛል እንደዛ የሆንሽው የአሂልን ትክክለኛ ማንነት ስለነገርኩሽ ነው አይደል?>> ውስጤ እርር አለ አቢ ሰውን በመጥፎ ሲያነሳ የሰማሁት ዛሬ ቢሆን እንጂ በጭራሽ አላውቅም የእኔ አባት አልመስልሽ አለኝ እንባ ብቻ አዝራንም ከፍቶታል ኡሚ እና አቢ የክፍሉን ጥግ ይዘው ሲያወሩ እኔ እና አዝራንም መነጋገር ጀመርን አዝራን <<አሁን ምን እናድርግ እሺ ብያቸዋለሁ ደግሜ እንዴት አይሆንም ልበላቸው?>> <<አንተ ያሳሰበህ እሱ ነው? ይገርማል እኔ ግን ያሳሰበኝ በህይወቴ ውስጥ አሂልን እስከ መጨረሻው ማጣቴ ነው>> <<እሽሽሽ… በቃ እርሽው ድጋሚ እንዳታለቅሺ አላህ ያለው ይሆናል በቃ ግን አያን የተባለው ሰው ማነው?>> <<አላውቅም ስለእሱ አታንሳ እሱ ነው አሂልን ያሳጣኝ ቆይ ማታ አናገረው? አቢ ለአሂል ደወለለት?>> <<አይ አንቺ ራስሽን ስለሳትሽ በግርግር ሳይረሳው አይቀርም>> <<እሺ ስልክህ የት ነው?>> ስጠይቀው አይኑ ፈጠጠ <<አናግሮት እንዳይሆን እሱ ጋር ነበር (አለኝ እና ወደ አቢ ዞሮ) አቢ ዛሬ አሂልን እናገኘዋለን አይደል?>> አለው አቢም <<አይ ከእኔ ጋር ማታ ተገናኝተናል ድጋሚ መገናኘት አያስፈልገንም>> ብሎ መለሰለት የተናገረውን መገመት ቀላል ነው ቆይ ሲከፋችሁ በጣም ሲከፋችሁ ከማልቀስ በላይ ስሜት መግለጫ ካለ ንገሩኝ አልቻልኩም እኮ አቃተኝ አቢ ምን እያደረገ ነው ቆይ ምን ልሁን? በዚህ ሁኔታ ለሊቱ ወደ ንጋት ተቀየረ አቢም ወደ ስራ ሄዷል ኡሚ ድክም ብሏታል እንደ ሴት ልጆች እናቴን ማማከር አለመድኩም ይህ ደግሞ በዚህ ሰዓት በጣም ጎዳኝ ትላንት ያልነበረኝን ባህርይ ከየት ላምጣው እሷም እንደማልነግራት ስለምታውቅ አይኖቼን እያየች <<አላህ እንዳሰብሽው ያድርግልሽ በምንም ነገር አንቺን ደስተኛ እንዲያደርግሽ ነው ምኞቴ>> <<ግን ኡሚ ምን እንደሆንኩ ገብቶሻል?>>አልኳት የሞት ሞት ዛሬ ላማክራት ወሰንኩ <<አንቺ ካልነገርሽኝ በምን አውቃለሁ? መጥፎው ነገር ከእኔ ጋር መነጋገር አለመድንም>> አለቺኝ በዚህ ታዝቦኝ ይሁን አላህ እንዲህ እይደረገኝ ያለው? አምላኬ ሆይ ይቅር በለኝ <<ፍቅር ይዞኛል>> ኮስተር አለችብኝ ፊቷን ሳጤነው ባልናገር ባልናገር አስባለኝ ሞትን መረጥኩ ብላችሁ ይቀላል እንባዬ ወደ ተኛሁበት ትራስ እየተንሸራተተ ነው ኡሚ ድምፁአን ቀነስ አድርጋ <<አስተግፊሩሏህ የምዕራባውያንን ፊልም ማየት ጀመርሽ እንዴ?>> <<ምን አገናኘው? ኡሚ ትረጂኛለሽ ብዬ እኮ ነው የማስበውን እየነገርኩሽ ያለሁት>> <<ምኑን ነው የምረዳሽ? ሃራም ነው እኮ>> <<…ግን ሃላል ማድረግ ይቻላል>> <<ፈራህ ምላስሽን አታርዝሚ አባትሽ ቢሰማሽስ ምን እንደሚፈጠር አውቀሻል?>> <<አላውቅም……አውቃለሁ ያዝንብኛል ግን አግዢኝ ፍቅሬን ሃላል ላድርገው>> ፊቷ ጥያቄ ምልክት እስከ መስራት ደረሰ ግን ስታየኝ አሳዘንኳት በረጅሙ እየተነፈሰች <<እሺ ግን ለእኔ ያልሺኝን ለአባትሽ ብትነግሪው በጣም ይበሳጫል ምንም እንዳትዪው …… አንቺ አረፍ በይ እኔ አናግረዋለሁ ብቻ እሺ እንዲል ዱዓ አድርጊ>> አለቺኝ እንደ ተኮሳተረች አሁን ደስ አለኝ ምክንያቱም ኡሚ ባለችው ነገር አቢ አይሆንም ሲል ማናችንም አይተን አናውቅም ብቸኛ ያለችኝ ተስፋ እሷ ነበረች <<አሁን ተኚ የታዘዙልሽን መድሃኒቶች ገዝቼ ልምጣ>> ብላኝ ወጣች ለሊት ስላልተኛሁ እንደ ቀልድ እንቅልፍ ሸለብ አደረገኝ 🍂 🍂 Ahil•••ወደ france ለመሄድ የonline ትኬት ቆርጫለሁ ከዛ በፊት ግን በድርጅቱ ውስጥ ያለኝን ድርሻ ለመሸጥ ወሰንኩ ምን አልባት የስህተቶቼ ቦታ ቢሆንም ድጋሚ ላልመለስበት እያሰብኩ ነው ከማሰብም በላይ እተገብረዋለሁ አይኖቼን ስለታመምኩ ጥቁር መነፀር አድርጌ ነው ወደ አዝራን ቢሮ ያመራሁት ሲያየኝ እንደማዘን አለ መደበኛ ሰላምታችንን ከተለዋወጥን በኋላ ቁጭ እንድል ነገረኝ <<አልቀመጥም የመጣሁት ከድርጅቱ ላይ ያለኝን ድርሻ ለመሸጥ ነው ከሌላ ሰው ጋር የድርጅቱ ሁኔታ ሳይረበሽ እንድትቀጥል ነው የምፈልገው>> አልኩት ሊያስቆመኝ አልፈለገም እያዘነም ቢሆን "እሺ" ብሎ የእሱ ፊርማ በሚያስፈልግባቸው ቦታዎች ሁሉ ፈረመልኝ <<አላህ መልካሙን ሁሉ እንዲመራህ እመኝልሃለሁ>> ሲል ምኞቱንም ገልፆልኝ ተቃቅፈን ተለያየን ግን ድርሻዬን ለመሸጥ አሁንም አልችልም የአንድ ሰው ፊርማ ያስፈልጋል የፈራህ ቢንት ሃጂ ሱለይማን <<ዛሬ ፈራህ ትመጣለች? የእሷም ፊርማ ያስፈልጋል>> አልኩት ፈገግ ብሎ <<አይ አትመጣም ማስፈረም ከተገባ ያለችበት ሄደህ አስፈርማት>> አለኝ ላላገኛት ወስኛለሁ ግን <<የት ነው ያለችው?>> <<…ሆስፒታል ናት የክፍሉ ቁጥር 324 ነው>> ብሎ ነገረኝ እና ወደ እዛው ሄድኩ በግምት የፈጀብኝን ሰዓት ባላውቀውም ብቻ ደረስኩ ወደ ውስጥ ገባሁ አሳንሰሩን ተጠቅሜ ከወጣሁ በኋላ የክፍሉን ቁጥር በክፍሎቹ አናት ላይ ለፍለጋ አማተርኩ አገኘሁት እና ስገባ እንቅልፍ ወስዷታል በክፍሉ ውስጥ ማንም የለም አንዲት ነርስ አልፋኝ ስትገባ <<ነርስ አሁን ደህና ናት?>> አልኳት <<አዎ ደህና ናት>> እሷን ሳናግር ፈራህ ከእንቅልፏ ነቅታ ነበር አየቺኝ አየኋት <<ነርሷ ለ10min ብቻ ማናገር ትችላለህ>> ስትለኝ ገባሁ ነርሷም ትንሽ አየቻት እና <<እናንተ አውሩ እመለሳለሁ>> ስትል <<አትሂጂ>> ነርሷ ግራ ገባት ሙስሊም አልመሰለችኝም ለዛ ነው ግራ የተጋባችው ይበልጥ ግልፅ እንዲሆንላት <<በሌላ መንገድ እንዳትረጅው ልሳሳት ስለምችል አናግሬያት እስከምሄድ አብረሽን ሁኚ>> <<እሺ የምረብሻችሁ ስለመሰለኝ ነው በቃ አውሩ>> መነፀሩን እንዳወለቅኩት አይኖቿን ማየት አቃተኝ የእሷም አይኖች ተጎድተዋል እንደምንም ብዬ <<የመጣሁት ከድርጅቱ የቦርድ አባላት ውስጥ በብቸኝነት ራሴን ወክዬ እንደወጣሁ ልነግርሽ ነው ድርሻዬን እሸጠዋለሁ ለዛ ደግሞ ያንቺ ፊርማ ያስፈልጋል ልትፈርሚልኝ ትችያለሽ???>> መልሷን ስጠብቅ የክፍሉ በር በዝግታ ሲከፈት በእርግጠኝነት ሃጂ ሱለይማን ይመስሉኛል ከአንድ ወጣት ጋር ሲገቡ እኔ ወደ በሩ ስዞር ተገጣጠምን አስተያየታቸውን አልወደድኩትም አሁን ምን ሊሉኝ ይሁን? ብቻዋን እንደሆነች አውቆ ልጄን ሊያገኛት መጣ አላውቅም አላህ ሆይ ምነው? እንዲህ ባታደርገኝ እባክህ ልቋቋመው የማልችልበት ነገር ውስጥ አትክተተኝ እንደፈራሁትም ╬╬═════════════╬╬                ᡣ𐭩 ይቀጥላል  ╬╬═════════════╬╬

  • ╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗             "አሒል እና ፈራህ"        ✎...ፀሃፊ:-ሠምሐን ╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝       ።።።።።።•✿• ።።።።።።                 ክፍል  13       ።።።።።።•✿• ።።።።።። Ahil•••ከመስጂዱ ወጥቼ ወደ መኪናዬ ስሄድ በጣም መሽቷል ለጀሚልም ሆነ ለባባ እዚህ ነኝ እዛ ነኝ ብዬ ያለሁበትን እንዳልነገርኳቸው ትዝ አለኝ እና ዝግ የነበረውን ስልኬን ስከፍተው ከአዝራን 3 ያልተሳኩ ጥሪዎች መኖራቸውን አየሁ አላህ መልካሙን እንዲያሰማኝ እየተመኘሁ ደወልኩለት እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ አልተነሳም መኪናውን ሳላስነሳ ቀበቶውን እየታጠቅኩ ሞከርኩ ተስፋ ለመቁረጥ መንገድ ስጀምር ተነሳ ያነሳው ግን አዝራን ሳይሆን አባቱ ነው ሀጂ ሱለይማን እንደ መተዋወቅ ከተነጋገርን በኋላ <<በቃ አዝራን ደውሎ ስለነበረ ነው የደወልኩት ደውዬ እንደነበር ይንገሩልኝ>> ብዬ ልዘጋው ስል <<አትዝጋው ላናግርህ የፈለግኩት እኔ ነኝ አዝራን አልነበረም(ትንሽ እንደ መደንገጥ አልኩ ምክንያቱ ባይገለፅልኝም)ባልሳሳት ፈራህን ለኒካህ አዝራንን ጠይቀኸው ነበር>> <<አዎ ሀጂ አልተሳሳቱም>> <<መርከዝ ስንት አመት ተምረዋል?>> <<13 አመት>> <<እንግዲያውስ ሸሪዓችንን ከማንም በላይ ታውቀዋለህ የፈራህ አባት እኔ እንጂ አዝራን አይደለም እኔ በሃያት እያለሁ ወንድሟን መጠየቅ ተገቢ ይመስልሃል?……ምን አይነት ጨዋታ ነው?(ልቤ ስንጥቅ ነው ያለው ማስተባበል አቃተኝ) ንገረኝ እንጂ አሂል ይህ ጨዋታ ነው? ትዳር ፍቅር ነው? ወይስ ተራ ፍላጎት መልኳን አይተህ ነው? ወይስ የዋህነቷን ልትጠቀምበት ፈለግክ? ልጄ የምታገባው በአባቷ እንጂ በወንድሟ ፈቃድ አይደለም ይህን የምልህ ለወደፊቱ ላንተ ብዬ ነው ትንሽ የመሰረት ስህተቶች ናቸው ትልቁን ህንፃ የሚያበላሹት ሀቁን ስነግርህ ፈራህን ላንተ አልፈቀድኩልህም………>> ስልኩን ለቀቅኩት ከዛ በኋላ ንግግራቸውም ከጆሮዬ እየራቀ መጣ ምንም ማለት አልቻልኩም ስልኩም ተዘጋ እጆቼ የመኪናውን መሪ መያዝ ስላቃታቸው እዛው ተውኩት እና ወደ ቤት እንዲወስደኝ Taxi አስቆምኩ ለሹፌሩ ከጠየቀኝ በላይ ነበር ገንዘብ የሰጠሁት ከራሴ ጋር አልነበርኩም ወደ ቤት ስገባ ባባ ምን እንደሆንኩ ጠየቀኝ ጀሚልም በተመሳሳይ ግን ለጠየቁኝ ሁሉ ምላሽ ሳልሰጣቸው ተቀመጥኩ ያበድኩም ሳይመስላቸው አልቀረም ዝም አለ ሳሎኑ ፀጥ ለእኔ ግን ብዙ ጫጫታዎች ይሰሙኛል እንደምንም አንደበቴን <<ባባ የድርጅቱ ድርሻህን ሽጠው እና እንሂድ ዱባይ አይሁን እንጂ የፈለግክበት ቦታ እንሂድ…………እዚህ መቆየት አልችልም ከቆየሁ ግን ከፈጠረኝ ጋር መጣላቴ ነው ባባ ምንም እንዳትለኝ እሺ ብቻ በለኝ ባባ እሺ በለኝ ገብቼ ልብሶቼን አዘጋጃለሁ ከዚህ እንሂድ>> ሁለቱም አፍጥጠው ተመለከቱኝ እውነት እንደ እብድ ነበር ሲያደርገኝ የነበረው እነሳለሁ እቀመጣለሁ መልሼ <<ባባ ወላህ ከአሁን በኋላ እንደዚህ አይነት ስህተት አልሰራም ቃል እገባልሃለው ባባ ብቻ እሺ በለኝ ድርሻህን ሽጠው እና እንሂድ>> <<ለምን?>> አለኝ ረጋ ባለ አንደበት ጀሚል ሁኔታዬን ሲመለከት ቅንድቦቹን ስብር አደረጋቸው <<እንድረሳት…ፈራህን እንድረሳት>> አልደነገጠም አሁንም ረጋ ብሎ <<ለምን ትረሳታለህ?>> <<ስለማላገባት ልርሳት የኔ ስላልሆነች ልርሳት ባባ አልተፈቀደችልኝም በቃ ልረሳት ይገባል >> ባባም በድጋሚ <<ለምን?>> ሲለኝ እያሾፈብኝ እንደሆነ ተሰማኝ <<ባባ ቀልድ አልያዝኩም እኮ መቶ ጊዜ ለምን? እያልክ ታሾፍብኛለህ እንዴ? እንሂድ እናንተ የማትሄዱ ከሆነ እኔ እሄዳለሁ እናንተ ለእኔ አታስቡም የራሳችሁን ምቾት ብቻ ነው የምትፈልጉት>> አሁንም ዝም አሉኝ ለምን አልተገረሙም እያልኩ ራሴን መጠየቅ ማቆም አልቻልኩም ባባ አንድ ነገር ብሎ ገላገለኝ <<አሂል ታዲያ እውነት በፈራህ ብንስማማ አባቷን እንጂ ወንድሟን የምጠይቀው ይመስልሃል? ስላልፈለግን ነው አዝራንን ያናገርነው በዚህ ሰዓት ማሰብ የነበረብህ ስለህመምህ እንጂ ስለትዳር አልነበረም በእኛ ላይ ስህተት ሲገኝ ሀጂ ሱለይማን አንተን እንደሚከለክልህ እርግጠኞች ነበርን አባቷ እያለ ወንድሟን መጠየቅ ስህተት ነውና አንተ ግን በፍቅር ስለታወርክ ያንን ማገናዘብ አልቻልክም>> <<ባባ እየዋሸሁ ነው በለኝ በአላህ ይዤሃለው ባባ ያንን ስታስብ ስለእኔ አታስብም ባባ አንተ ጨካኝ እኮ በእኔ ላይ አልነበርክም>> መፍትሄ ሳጣ ወደ መኝታ ክፍሌ ገባሁ አዞረኝ ፊቱን ወደማያዞርብኝ አላህ ዞርኩ ለመስገድ ቆሜ እግሮቼ መቆም አቃታቸው ጉልበቴ እስከሚክደኝ ድረስ 💔 💔 💔 Ferah•••ከነበርኩበት ሰመመን ስነቃ ራሴን አንድ የሆስፒታል ክፍል ውስጥ አገኘሁት በክፍሉ ውስጥ ማንም የለም ቀና ስል አንድ ግሉኮስ ተንጠልጥሏል ሊያልቅ ነው ከግራ ወደ ቀኝ ሳማትር አንዲት ነርስ ገባች <<ማሻአላህ ነቃሽ?>> <<ለምንድነው? እዚህ የመጣሁት?>> <<ራስሽን ስተሽ ነበር በደምሽ ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ወርዶ ስለነበር ነው>> <<ስንት ሰዓት ነው?>> <<ከለሊቱ 08:00 ሆኗል ቤተሰቦችሽ በጣም ተጨንቀው ነበር ቆይ መንቃትሽን ልንገራቸው>> <<አይ… አይ አትንገሪያቸው ማንንም ለማግኘት እርግጠኛ አይደለሁም አትንገሪያቸው መስገጃ ይኖርሻል?… መስገድ እፈልጋለሁ>> <<ግንኮ ዶክተሩ እረፍት እንድታደርጊ ብሏል>> <<ልብ ካላረፈ ሰውነት አያርፍም>> <<እሺ በቃ ግን ዶክተሩ እንዳያዝንብኝ እዛ ጋር ስገጂ>> ብላ የተጋረደ ቦታ ሰጠቺኝ መስገጃው ላይ ለይል ሰግጄ ብዛው ላይ እያለቀስኩ እንደተደፋሁ ፈጅር ሷላት አዛን አለ ╬╬═════════════╬╬                ᡣ𐭩 ይቀጥላል  ╬╬═════════════╬╬

  • 2 авг.96из alhudaqur

    ቁርኣን ኦንላይን መቅራት የምትፈልጉ @Susunur ላይ ተመዝገቡ

  • አላህዪ! ወዴት ልሂድ? የማንንስ በር ላንኳኳ? ከአንተ ውጪ ማን አለኝ? መጠጊያዬም፣ መሸሸጊያዬም አንተ ብቻ ነህ። የሁሉ ነገር ባለቤት ሆነህ ሳለ እንዴት ከበርህ እመለሳለሁ? የአዛኞች ሁሉ አዛኝ ሆነህ ሳለ እንዴት ተስፋ እቆርጣለሁ?

  • ╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗             "አሒል እና ፈራህ"        ✎...ፀሃፊ:-ሠምሐን ╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝       ።።።።።።•✿• ።።።።።።                 ክፍል  12       ።።።።።።•✿• ።።።።።። Ahil•••ከጀሚል ጋር ከቢሮ ወጥተን አንድ ካፍቴሪያ ውስጥ ሻይ እየጠጣን ነው ጀሚል <<…አሂል በጣም እንዳለቀስክ ታውቆሃል ስታለቅስ አይቼህ ባለማወቄ ገርሞኛል ግን ለምን አለቀስክ?>> አለኝ የያዝነው ቦታ ከካፍቴሪያው cornor አካባቢ ነው <<አስብህ ነበር አለቺኝ በተመሳሳይ አጋጣሚ ነው ራሳችንን ፍቅር ውስጥ ያገኘነው…ታዲያ ይህ ነው ያስለቀሰኝ >> <<ማሻአላህ ስታስቀኑ ታውቃለህ በጣም ነው ደስ የሚለው ……ደግሞ የዛሬ ሳምንት ሄደን አይተሃል ግን ታያታለህ ከአዝራን ጋር አውርተንበታል>> <<እሺ ጀዛኩሙላህ>> <<ምንም አይደል የኔ ውድ አሁን ሻዩ ሳይቀዘቅዝ ጠጥተን ወደ ስራ እንመለስ አዝራንም ሳይመለስ አይቀርም>> አለኝ አይኖቼ ደፍርሰዋል ወደ ውስጥ ገብተን ወደየ ቢሮዎቻችን ስንለያይ የፈራህን ቢሮ ቃኘሁት መብራቶቹ ጠፍተዋል በምናብ ስትፅፍ እና ብዙ ሰዓት አቀርቅራ አንገቷን ሲያማት ፊቷ ላይ የሚታየው መልክ ትዝ አለኝ ፈራህ እንዳለች ነበር የታየኝ የምትፅፈው እንደፍላጎቷ ካልመጣ ወረቀቱን የምትቀዳድድበት መንገድ ስትናደድ ቢሮዋ ውስጥ ስትንጎራደድ እንደምትውል በራሱ አውቃለሁ አንድ እጅ በትከሻዬ ላይ ሲያርፍ ከገባሁበት አለም ባነንኩ እና ስዞር የባባ ፀሐፊ የሆነው ሃምዛ ነው <<እዚህ ምን ታደርጋለህ?(ሲጠይቀኝ ወደ እሱ ዞርኩ) እያለቀስክ ነው እንዴ?>> አለኝ ምንም እንዳልሆንኩ ሃረካት ሰራሁ የሆነ ነገር እየተሰማኝ ነው ፈራህን የማጣት አይነት ስሜት በእያንዳንዱ አጋጣሚ ሆድ ይብሰኛል ደህና ነኝ ከሚለው ቃል ጀርባ ብዙ አይደለሁም የሚሉህ አካላት አሉ በቃ ቶሎ ቶሎ እየከፋኝ ነው የመውጫ ሰዓት ደርሶ ስለነበር ነው ሃምዛ የጠራኝ አሱር ሷላት አዛን ብሎ ስለነበር በመንገዴ ላይ ወዳገኘሁት መስጂድ ገባሁ ከ4min በኋላ ኢማሙ ሃርመው መስገድ ጀመርን ምንም እንኳን ደስተኛ ብሆን አላህን ለማመስገን ብቸኩል አይኖቼን ከማልቀስ ማስቆም አልቻልኩም ሃሳቤን የቱንም ያህል ብሰበስበው ፍርሃቱ ሊለቀኝ ፈቃደኛ አልነበረም ወደ ቤት ሳልገባ በዛው መስጂድ ውስጥ አመሸሁ 🍂 🍂 🍂 Ferah•••እራት መብላት ጀምረናል ምግቡን እየዋጥኩ ያለሁት በግድ ነው ብላችሁ ውሸት አይሆንብኝም ሊመጣ የሚቃትተውን እንባ ውሃ እየጠጣሁ እመልሰዋለሁ ለምን እንደማለቅስ ሲጠይቁኝ ወንድሜ ጋዜጣ ህትመት ላይ አስከፊ በህፃናት ላይ ስለተፈፀመው ግድያዎች አንብቤ እንደሆነ ነግሯቸው ጥያቄያቸው ጋብ ብሏል ግን ያፈንኩትን ህመም ማን ባወቀልኝ አላህ አሳይቶ ይነሳል? ሰጥቶ ይቀበላል? ብዬ ለራሴ ጥያቄ እፈጥራለሁ ከዛ ምህረቱን እማፀናለሁ ይህ ሁሉ የሚሆነው በልቤ ውስጥ ነው አዝራን ለመናገር ያሰበው ነገር እንዳለ ቢሚያሳብቅ መልኩ ጉሮሮውን ጠራረገ ሁላችንም እኔንም ጨምሮ ለመስማት ጆሮዎቻችንን አቆምን <<እናቱን ያጣው በ3 አመቱ ነው አባቱ አሁንም ድረስ በህይወት አለ አንድ ወንድም ነው ያለው እናቱን ካጣ ጊዜ ጀምሮ በጣም ተጎድቶ ስለነበር እንዲረሳት 10 አመት ሲሆነው ወደ ኮሎምቢያ አባቱ ላከው የአባቱ ወላጆች እና ዘመዶች ያሉት ወደ እዛ ነው ኮሎምቢያ አለማዊም ኢስላማዊም ትምህርት ያስተምር ወደነበረ መርከዝ ነው የገባው እና በጣም ስኬታማ ኢማን ያለው ዝምተኛ ልጅ ነው አሂል ኢብኑ ዘይድ የ24 አመቱ ልጅ እህቴን ጠየቀኝ አቢ እኔም እሺ አልኩት……ሳልነግርህ መወሰን ፈልጌ ሳይሆን አንተም ብትሆን እንደምትስማማበት እርግጠኛ ስለነበርኩ ነው>> ሲል ኡሚ እልልታዋን አዘነበችው ኡዘይማም እንዲሁ ፈገግ ትላለች ኑር "እውነት አንቺ ልታገቢ ነው? የሰርግሽን ቀሚስ የምመርጠው እኔ ነኝ እሺ?" አለቺኝ አዝራንም በተመሳሳይ ተደስቶ ነበር አቢ ግን የማንንም ግርግር ከቁብ አልቆጠረውም ዝም አለ አዝራን የአቢን ዝምታ ሲመለከት እየፈራ እና እየቸረ <<አቢ እ… እንዳልኩህ እንደምትወደው እርግጠኛ ስለነበርኩ ቀጣይ ሳምንት መጥተው እህቴን ያዩዋታል ልጁን ማየት ከፈለግክ ግን ነገ ወደ ድርጅቱ እወስድህና ታየዋለህ…………እና ምን አሰብክ?>> ሲለው አቢ የሚለውን ለመስማት የልቤ ምት ጨመረ በዛም መሃል ስለሚናገረው ነገር እየፈራሁ ነው <<…ወላጆቹን በ16 አመቱ ስላጣው ወጣት ደግሞ ልንገርህ(ስለ አያን መሆኑን አላጣሁትም የራሴው ትንፋሽ ስተነፍሰው ለራሴ ያቃጥለኝ ጀመር)ሊባኖስ ነበር የሚኖሩት እነሱን ካጣ ወዲህ ግን ስደተኛ ሆኖ ወደ ሃገሩ አልተመለሰም የቀለም ትምህርቱን ያለፈው አመት ጨርሷል እድሜውም ሩቅ ከፈራህ እድሜ ሩቅ አይደለም 25 አመቱ ነው እኛ ቤተሰቦቹ መሆን እንችላለን አልኩ ፈራህንም ስለወደዳት እሱ እንዲያገባት ወስኛለሁ ስለዚህ ሃሳብህን ሰርዘው>> ሲል አዝራን በአንክሮ አየኝ እኔም አየሁት ተያየን አሁን የማለቅስበት ጉዳይ እንደተገለፀለት ተረዳሁ እንደምንም የአቢን ሃሳብ ለማስቀየር <<አቢ እሺ ብያቸዋለሁ ላስብበት አላልኳቸውም ደግሞ ቀድመዋል እመነኝ አባቴ አሂልን ትወደዋለህ>> <<አታስብ አዝራን ነገ እንዳልከው ከእኔ ጋር ወደ ድርጅቱ እንሄዳለን እኔ አናግረዋለሁ>> ሲል ከነበርኩበት ምንጭቅ ብዬ ተነሳሁ የሁሉም ዓይን በእኔ ላይ ነበር ትቻቸው እየተመናቀርኩ ወደ መኝታ ክፍሌ ገባሁ አዝራን እየጠራኝም ሆነ እየተከተለኝ መሆኑን አላስተዋልኩም አልጋው ላይ በደረቴ ተዘርሬ ማልቀስ ጀመርኩ አዝራን በሩን ከፍቶ ገባ እና <<ፈራህ ተረጋጊ ፈራህ በቃ ተረጋጊ ሁሉንም ለአላህ ስጪው አንቺ ሰበቡን ካደረስሽ…>> ሲለኝ ተነሳሁ መናገር የፈለገውን ሳላስጨርሰው ከልክ ያለፈ ንግግር መናገር ጀመርኩ <<እውነት በል እስኪ ለአላህ ሰጥቼውማ ኢሻራውን አሳየኝ እኮ ሰጥቶ ነፈገኝ ለየትኛው አላህ? ንገረኝ እስኪ? ሰበቡን ማድረስ ስትል? ምን አይነት ሰበብ አባቴን ብድግ ብዬ ማስቀየም ነበረብኝ? ንገረኝ እስኪ ወንድሜ ለአሂል እሺ ማለቴን አትርሳ እሺ ስለው ምን እንዳለኝ ልንገርህ? "ቀልድ ከሆነ በጣም እንደምጎዳ እያሰብሽ ከልብሽ ነው አይደለም?" አዝራን ከዚህ በላይ ምንም ልሆን አልችልም>> ወደራሱ አስጠግቶ አቀፈኝ <<በቃ በቃ……አቢን ለማናገር እሞክራለሁ>> ሲለኝ አቢ የመኝታ ክፍሌ በር ላይ ደርሶ ነበር <<ቆይ እንዲህ እርግጠኛ የሆንክበትን ልጅ የት ነው ያወቅከው?>> አለ አዝራን እየለቀቀኝ <<የድርጅታችን ሸሪክ የሆነው ሰው ዘይድ ልጅ ነው>> <<ታዲያ እናንተ ምንድነው የሆናችሁት?>> ሲል ግራ ተጋብተን አየነው ቀጠለና <<በል እስከሚነጋና እና በአካል እስከማገኘው አልጠብቅም ስልኩን ስጠኝ ላናግረው>> አለ በእውነቱ ምን እንዳሰበ አቢ አላወቅንም አዝራን ስልኩን ሰጠው እየጠራ እንዳለ <<ለትዳር ሳይሆን የፈለገሽ ለድርጅቱ ድርሻ እና ገንዘብ ነው እንዲህ አይነቱን ሰው ደግሞ መታገስ አያስፈልግም>> ሲል አቢን ማግባባትም ሆነ ማሳመን ከባድ ነበር ሁሉም ነገር መንታ ሆኖ ይታየኝ ጀመር የወንድሜም ሆነ የአባቴ መልክ ሳይቀር ከዛ የሆነውን አላስታውስም ግን አቢ አሂልን የተረዳበት መንገድ ልክ ይመስላችኋል??????? ®ፈራህ ነቃ በይ ፈራህ ኡሚ ውሃ ውሃ ፈራህ ራሷን ሳተች© የሚል ድምፅ በጥቂቱ ይሰማኛል

  • . ልቀቂ ሚልም የለም 🤔 .

  • "የማጣት ፍርሃት..." አንዳንዴ ሰዎችን ወይም ነገሮችን ከማጣታችን በፊት፣ «እናጣቸዋለሁ» የሚለው ስጋት ቀድሞ ይገድለናል። በህይወታችን ውስጥ ብዙ ነገር ባጣን ቁጥር፣ ልባችን አዳዲስ ነገሮችን ከመቀበል ይልቅ መጠራጠርን ይለምዳል። አንድ መልካም ነገር፣ አንድ እውነተኛ እረፍት ወይም አዲስ ተስፋ ሲመጣልን... ደስ ከማለታችን ይልቅ ፍርሃታችን ይበልጣል «ይህስ እስከመቼ ይቆያል?» «ይህስ መቼ ይሆን የሚሄደው?» ያለፉት ስብራቶቻችን ያመጡብን ጠጠሮች ናቸው። እንደገና ላለመጎዳት ስንል እጃችን ላይ ያለውን ነገር አጥብቀን እንይዛለን፤ ግን ያው ፍርሃት አየር ያጣብናል። አጠገባችን ያለው ነገር ሳይሄድ፣ በውበቱን ከመደሰት ይልቅ መሄዱን አስበን አስቀድመን እናቀረቅራለን።    የከፋው ማጣት፣ ገና ያልተከሰተውን ማጣት እየፈሩ መኖር ነው። እጅ ላይ ያለውን ደስታ በሙሉ በፍርሃት ጭጋግ የሚጋርደው፣ የወደፊቱ ስጋታችን ብቻ ነው። ያጣነው ነገር ትምህርት ቢሆንም፣ ዳግም ማጣትን መፍራት ግን አሁናችንን ይሰርቀናል።    ✍   Susu

  • አብዱል ቃዲር አል ጂላኒ ለመጀመሪያ ጊዜ እውቀትን ፍለጋ ሲጓዝ እናቱ አርባ ዲናር ሰጠችውና ፈጽሞ እንዳይዋሽ አዘዘችው። አንዳንድ ሌቦች ወደ እሱ ቀርበው “ከአንተ ጋር ምንም ነገር አለህ?” ሲሉ ጠየቁት። እሱም “አዎ፣ አርባ ዲናር” ሲል መለሰ። እየቀለደ እንደሆነ በማሰብ ወደ መሪያቸው ወሰዱት፤ እርሱም “እውነቱን እንድትናገር ያደረገህ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። እንዲህ አለ፡- “ለእናቴ ቃል ገብቼላት ነበር” «ቃል ኪዳኗን እከዳለሁ ብዬ እፈራለሁና ልዋሽ አይገባኝምን?» ሌባውም አለቀሰና.. «የእናትህን ቃል ኪዳን ክህደት ትፈራለህ፤ የአላህን ቃል ኪዳን ግን ክህደት አንፈራም» አለ። ሌቦቹም ሁሉ በእጁ ንስሐ ገቡ። @melkamgets

  • ╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗             "አሒል እና ፈራህ"        ✎...ፀሃፊ:-ሠምሐን ╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝       ።።።።።።•✿• ።።።።።።                 ክፍል  11       ።።።።።።•✿• ።።።።።። Ferah•••በህይወትህ ውስጥ በጣም የሚያስደስተው ነገር  በወደድከው እንደተወደድክ ስታውቅ ነው አዝራን የኔን መልስ እየጠበቀ ቢሆንም እንባዬን መግታት ተሳነኝ <<መልስሽ ምንድነው? በቃ አታልቅሺብኝ አንቺ የማትፈልጊው ከሆነ አታስቢ እንደማትፈልጊው እነግረዋለሁ>> አለኝ እንባዬን እየጠረገ እኔም ሳግ እየተናነቀኝ <<ወንድሜ ምን እንዳስለቀሰኝ ታውቃለህ?>> <<ምን አልባት አልፈለግሽውም ለዛ ነው>> <<እንደዛ አይደለም ቆይ እሺ ማለት ይህን ያህል ይከብዳል? ለእኔ ግን ከበደኝ ሳልፈልገው ቀርቼ ሳይሆን ምን ማለት እንዳለብኝ አላወኩም>> <<መብሩክ ቆይ ዛሬ እንደምን ያለ ቀን ነው?…እቀፊኝ ደስ ብሎኛል አልሃምዱሊላህ ያረብ>> ሳይዘገይ የእጅ ስልኩን አውጥቶ ደወለ ለማን እንደሆነ አላውቅም <<ጥሪው ሲነሳ እሺ በይው ሁሉንም ካንቺ መስማት ይፈልጋል>> ብሎ ሰጠኝ የደወለው ለአሂል ነው <<ሄሎ ወንድሜ አዝራን>> ድምፁን ስሰማ በፈራና በተጣደፈ ድምፅ <<አሰላሙ አለይክ ፈራህ ነኝ እሺ>> አልኩት ስልክ የያዝኩበት እጄ ይንቀጠቀጣል ዝም አለ ዝም፣ ዝምታ ብቻ ምንም መልስ አልሰጠኝም እሱም እንደእኔ ሆኖ ይሁን? <<ሄሎ አሂል>> <<ወአለይኪ ሰላም>> <<ወንድሜ የሆነ ነገር ጠየቀኝ……የእኔም መልስ እሺ ሆነ>> <<እንደዚህ አይነት ውሸት በእድሜዬ አልሰማሁም>> <<እየዋሸሁ አይደለም በኒካህ አብረን እንድንሆን እፈልጋለሁ>>       ከተወሰነ ዝምታ በኋላ አቅም ባጣ ድምፅ <<ቀልድ ከሆነ በጣም እንደምጎዳ እያሰብሽ ከልብሽ ነው አይደለም?>> <<እንደዛ ካሰብክ አፍወን ግን ቀልድ አንተን ሳይሆን ቀድሞ ለእኔ ነው ህመም የሚሆነው>> <<ፈራህ እኔ ላስጨንቅሽ አልፈልግም ጊዜ ሰጥተሽ አስቢበት እና ንገሪኝ አትቸኩዪ>> <<አሂል ያልገባህ ነገር አለ 5 ወር ሙሉ አሰብኩበት አሰብኩህ አይበቃም ከዚህ በላይ ላስብበት አልፈልግም>> ምንም አላለኝም ግን የለቅሶ ድምፅ ተሰማኝ እያለቀሰ መሆኑ ሲገባኝ እኔም አለቀስኩ ይህ የመጀመሪያ ንግግራችን ነው ተነጋግረን አናውቅም ሁሉም የልብ ቋንቋ ነበር ስልኩን ጀሚል ተቀብሎ <<አውፍ በይን ትንሽ ስሜታዊ ሆኗል እያለቀሰ ነው እሺ እንዳልሽውም አውቄያለሁ ደስ ብሎናል ሁልጊዜም  የአላህ ተግባር ይደንቃል የነዛ ሱጁዶች ተዓምር ነሽ አሂል በአይኑ ሳይሆን በሱጁዱ ውስጥ ነው ሲፈልግሽ የሰነበተው ላንቺ አላህ ፊት ለይል ቆመ ፈራህ እውነት እሺ ካልሽው ደስ ብሎኛል አሁን ከቻልሽ ስልኩን ለወንድምሽ ትሰጪልኛለሽ?ከእሱ ጋር የምንነጋገረው ነገር አለ በተረፈ መብሩክ የወንድሜ ሚስት እንደምትሆኚ ሳስበው በጣም ደስ ይለኛል አላህ ሁለታችሁንም ይጠብቅልኝ>> አለኝ "አሚን" ብዬው እንዲያወሩ ስልኩን ለአዝራን ሰጠሁት እና እነሱ እያወሩ እኔ ወደ ውስጥ ገባሁ ወደ ኪችን ተመልሼ የአቢን የምሳ እቃ ሳየው አዝራን በወሰደኝ ሰዓት ኡሚ አስተካክላው ጨርሳ ነበር ግን ሲያዩኝ ደነገጡ "አዝራን ምን ብሎሽ ነው? ምነው የተፈጠረ ነገር አለ?" አሉኝ ምንም እንዳልሆነ ነገርኳቸው ባይዋጥላቸውም "ለአባትሽ ምግቡን አድርሺለት እና እናወራለን" አለቺኝ ኡሚ ወደ አቢ መርከዝ የደረስኩት እያለቀስኩ ነበር መኪና ሳሽከረክር እንባዬ አይኖቼን እየጋረደ ተቸግሬ ነበር እንደምንም እንደማንም ብዬ ደረስኩ ወንዶችን ብቻ የሚያስተምር አዳሪ መርከዝ ነው አንድ መርሃ ግብር ሳይኖራቸው አይቀርም እና ከአንዱ አዳራሽ በጣም የሚያምር የቃሪዕ ድምፅ ይሰማል ልጁ እየቀራ ያለው ሱረቱል አል_አህዛብን ነው ወደ አቢ ቢሮ ገባሁ ምስጥ ብሎ ሲያዳምጠው አየሁት እና እኔም ምንም ሳልለው ከሶፋው ላይ ተቀመጥኩ ከ10min በኋላ ልጁም ቀርቶ ጨረሰ <<ማሻአላህ የሚገርም ድምፅ ነው አላህ ይጨምርለት>> አልኩኝ አቢም ራሱን በአወንታ እያንቀሳቀሰ <<በቅርቡ ነው ያገኘሁት ኡስታዝ አያን ይባላል የሊባኖስ ስደተኛ ነው በጦርነቱ እናት እና አባቱን አጥቷል የመርከዙም ልጆች ወደውታል አያንን የሚጠላ የለም ቆይ አስተዋውቅሻለሁ>> አለኝ አቢ በዚህ ደረጃ ሰውን ሲያደንቅ አይቼው ባለማወቄ ተገረምኩ <<አቢ ምግብ ይዤልህ መጥቻለሁ>> አልኩት እና ከፊት ለፊቱ በነበረው ጠረጴዛ ላይ አቀርብለት ጀመር አብረን መብላት ጀመርን ወደ ድርጅቱ መሄድ ካቆምኩ በኋላ ምሳ የምበላው ከአቢ ጋር እዚህ መጥቼ ነው <<አልቅሰሻል እንዴዓይኖችሽ ደፍርሰዋል>> አለኝ <<ኧረ አላለቀስኩም ወዳንተ ስመጣ አቧራ ገብቶብኝ ነው አላለቀስኩም>> <<ደግሞ የሆነ ነገር ላማክርሽ እፈልጋለሁ>> <<ንገረኝ አቢ ምንድነው?>> <<ኡስታዝ አያን በጣም ጥሩ ሰው ነው ወላጆች የሉትም እኛ ቤተሰቦቹ ብንሆንለት አልኩ አላህ ይዘንለት እና ስለቀድሞው ህይወቱ የሚያወራው ከእኔ ጋር ብቻ ነው ቆይ አሁን አስተምሮ ከጨረሰ ይመጣል ታይዋለሽ>> ሲል የአቢ የንግግር ሂደት አላማረኝም ቀጠለ <<ማታ ልታገቢ እንደምትፈልጊ ነግረሽኛል ለእኔ ደግሞ ቅርብ የሆነልኝ አያን ነው ኢማን አለው አላህ ይጨምርለት አስተዋይም ነው እና በትዳር እንድትተሳሰሩ እፈልጋለሁ እሱም እሺ አለኝ ባለፈው ጊዜ ምግብ ስታመጪልኝ አይቶሽ ወዶሻል እንደምትወጂው ሙሉ እምነት አለኝ ከአላህ ጋር>> ከዚህ በፊት አቢን በምንም ነገር ተፃርሬው አላውቅም አሁን ግን እያለ ባለው ነገር እሺ ልለው አልችልም  ስለአሂል ልነግረው እና ልቀድመው አሰብኩ በወንድሜም ለማመሃኘት ፈጠን ብዬ <<ግን አቢ ከአንተ በላይ እኔ አላውቅም አዝራን ቅድም ፈልጎህ ነበር እሱን የጠየቁት ሰዎች እኮ አሉ አዝራን በጣም ወዷቸዋል አንተም ትወዳቸዋለህ ለእነሱ መልስ ሳንሰጣቸው እንዲህ ማድረጉ ተገቢ ነው አልልም>> አልኩት አይሆንም እንዳይለኝ በልቤ ዱዓ እያደረግኩ እንደፈራሁትም <<የለም ልጄ እኔ ከአያን ውጪ ማንም ያንቺ ባል እንዲሆን አልፈቅድም>> እንባዬ ለመውረድ አንድ ሁለት አለ                         💔   💔   ╬╬═════════════╬╬                ᡣ𐭩 ይቀጥላል  ╬╬═════════════╬╬

  • ╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗             "አሒል እና ፈራህ"        ✎...ፀሃፊ:-ሠምሐን ╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝       ።።።።።።•✿• ።።።።።።                 ክፍል  1⃣0⃣       ።።።።።።•✿• ።።።።።። Ahil•••ከተወሰነ የስራ ቆይታ በኋላ ወደ አዝራን ቢሮ ከባባ ጋር ገሰገስን ገና ከአሁኑ እጆቼ መንቀጥቀጥ ጀምረዋል ባባ አይዞህ እያለ እያበረታታኝ ከቢሮው ስንደርስ በወትሮው ትህትና ተቀበለን ከደቂቃዎች በኋላ ወይ ላስብበት ወይ አይሆንም ሊል ነው እያልኩ በልቤ በሶፋው ላይ ከባባ ጎን አረፍ አልኩ ከባባ ጋር ስለስራ ስለህይወት ስለብዙ ነገር ሲያወሩ ከቆዩ በኋላ ባባ <<ፈራህን ግን አይቼያት አላውቅም ምነው? ደህና ነች አይደል?>> አለ መግቢያ መሆኑ ነው አዝራንም <<ትንሽ ደበራት ምን እንደሆነችም ጠየቅኳት ብዙም መልስ አላገኘሁም ግን አልሃምዱሊላህ ደህና ናት>> ምን እንዳሰበ ባላውቅም አዝራን አይቶኝ በጣም ፈገግ አለ እንደምንም ሳቁን ዋጠው እንጂ ሲመስለኝ በትውስታ ነው ፈገግ እያለ ያለው ጁምአ ቀን ስራ አላልቅ ብሎኝ አርፍጄ ነበር ለአዝራን የእለቱን ዘገባ አስረክቤ ስወጣ እሷም መጣች አሳንሰሩ ጋር ተገናኘን አፌን ምን እንደያዘኝ አላውቅም አይኖቿን እያየሁ ፀጥ አንድም ቀን በቅርበት ባያት እንደዛ እደነግጣለሁ ብዬ አስቤአላውቅም ፈራሁ እሷም እይታዬ እንዳናደዳት ግልፅ ነው ሰላም ይውረድብህ እንኳን አላለቺኝም ተኮሳትራብኝ አለፈች እኔም ከፊት ለፊቴ ላለው አዝራን በጥቂቱ ፈገግ አልኩ የተግባባን መሰለኝ ባባ ስለፈራህ መቅረት አብዝቶ መጠየቅ ስላላቆመ ጥያቄውን ለማምለጥም ይሁን ሆን ብሎ በጋራ የመጣልንን ትውስታ ለባባ ለማጋራት ብቻ አላውቅም አዝራን <<ከእህቴ ጋር ተጋጭታችሁአል እንዴ?>> ብሎ የሁለትዮሹን ወሬ ወደእኔ አመጣው እንዳልኳችሁ ያንን እያስታወሰ ነበር <<ኧረ ለምን እንጋጫለን?>> የእኔ መልስ ነው ፈገግ ማለቱን ሳያቆም <<አትነጋገሩም ብዬ ነው…>> ባባ ዞሮ አየኝ እኔም አየሁት ግራ እየገባኝ ባባ ቀጠለ <<ፈራህ ስለትዳር ታስባለች?…ወይስ ትቆያለች?>> በቃ ቀጥታ አዝራን ግራ ገብቶት ሁለታችንንም እያፈራረቀ እያየን <<እኔም ያወኩት ትላንት ነው እንደዚህ አይነት ነገር አውርተን አናውቅም>> አለን <<ምንድነው ያወቅከው?>> ባባ ነበር አዝራንም አይን አይኔን እያየ <<እሷ ማግባት ትፈልጋለች ግን በቅርበት የማታውቀውን ሰው አትፈልግም እኔም ቢሆን ለእሷ ሰው እመርጣለሁ በዛ ሰው ደስተኛ ስለመሆኗ ያሳስበኛል>> አለን ትክክለኛ ወንድም ነው ግን በዚህ ሰዓት ከሚመርጣቸው ሰዎች መካከል መሆኔን አላውቅም ብቻ አላህ ይወቅ ባባ ቀጠለና <<ሳትዋሽ ንገረኝ አዝራን አሂል በአንተ አይን ምን ያህል ያመዝናል የእህትህ ባል ለመሆን>> አዝራን ግራ ገባው በጣም አየኝ <<የፈራህ ባል ለመሆን?>> <<አዎ የፈራህ ባል ለመሆን>> <<ምንም………ምንም(ከነበረበት ወንበር እየተነሳ)እቀፈኝ ተነስተህ እቀፈኝ>> አለኝ ተነሳሁ ተቃቀፍን <<ለእህቴ ሁልጊዜ እመኝሃለሁ የእሷን እና ያንተን ባላውቅም ከመጣህ እና ድርጅታችንን ከተቀላቀልክ ጊዜ ጀምሮ… አላውቅም ምን ማለት እንዳለብኝ>> ጭራሽ ግራ ገባኝ ምን ልበል ምን አልበል ጠፋብኝ <<እውነትህን ነው ግን…? ፈራህን ሚስትህ ማድረግ ትፈልጋለህ?(አለኝ መልሶ መልሴን ሳይጠብቅ)አጥብቆ አቀፈኝ>> ባባም; <<እርግጠኛ ነህ አይደል አዝራን? >> <<በሚገባ አሁን ለፈራህ ልንገራት (የእጅ ስልኩን አወጣ እና መልሶ ከተተው) ይህ በስልክ አይነገርም እንደውም ወደ ቤት ልመለስ>> ይለን ጀመር ከመቼውም ጊዜ በላይ ፈገግ እያለ ያየኛል እኔ ድርቅ ብያለሁ ከትላንት ማታ ጀምሮ እየሆነ ያለው ህልም ነው እየሆነብኝ ያለው አሁንም ምንም ለማመን ተቸግሬያለሁ አሁን የመጨረሻ ፈራህ ተቀብላሃለች ከተባልኩ አላውቅም ምን እንደምሆን አዝራን ቢሮው ውስጥ ትቶን ከሄደ ቆየ ባባም ግራ ገባው ለካ ከአይሆንም በላይ እሺ የምትለው ቃል ይህን ያህል ከባድ ናት ሰዎች አይሆንም ሲሉህ ራስህ ላይ ይበልጥ ትሰራለህ እሺ ሲሉህ ደግሞ ለዛ ሰው በቂ ነኝ አይደለሁም ይበልጥ ላንተ የቤት ስራ ይተውልሃል ከባባ ጋር ተፋጠጥን እና መልሰን ተሳሳቅን ለጀሚል ለመናገር ቸኮልን 🍂 🍂 🍂 Ferah•••የማዕድ ክፍል ውስጥ ለአቢ የምወስድለትን ምግብ እያበሰልኩ አዘይማ እና ኡሚ ደግሞ እያወሩ ነው እኔም የሰራሁትን ምግብ በምሳ እቃ እየገለበጥኩ እንዳለ ያለ ወትሮው አዝራን በማይጠበቅ ሰዓት መጣ ከመግቢያው ጀምሮ እየጠራኝ ነበር አዘይማ <<ዛሬ ሁቢን ምን ነክቶታል?…ና ፈራህ እዚህ ናት>> አለችው እንደመጣ <<ነይ የሆነ ነገር ላናግርሽ?>> አለኝ <<ምንድነው ለእኛም ንገረን እንጂ እህትህ ብቻ ናት መስማት ያለባት?>> አለችው ኡሚ ግን ሳይሰማት እጄን እየጎተተ ወሰደኝ እና በረንዳ ላይ <<በጣም ደስ ብሎኛል ታውቂያለሽ? በምድር ላይ እንደሱ አይነት ወንዶችን አላህ ጥቂት ነው የፈጠረው>> <<እ!?…ምንድነው የምታወራው?>> <<የሰማሁትን ወላህ ማመን አልቻልኩም ታስታውሻለሽ እንደሱ ሁኚ እይው የምልሽ እኮ እሱን ልብሽ ውስጥ ለማስቀረት ነበር አላውቅም አሁን ላይ ምን እንደምታስቢ ግን……>> ዞረብኝ ብላችሁ ይቀላል ምንድነው የሚያወራው? ይላል አንዱ ልቤ <<አሂል ይፈልግሻል>> ድንግጥ አልኩ መረጋጋት የማይችል ድንጋጤ ነበር እግሮቼን ማዘዝ እስከማልችል ድረስ <<ውሸት ስታወራ አያምርብህም እኮ አንተ አትዋሽ>> አልኩት እንባዬ ለመፍሰስ እየቃተተ ነው አዝራን ጉንጮቼን እየነካካ <<አልዋሸሁም ወላህ ሚስቱ እንድትሆኚ ይፈልጋል ዛሬ ቢሮ መጥቶ ጠየቀኝ አባቱ ሲነግረኝ እነዛን ቀናት ከድርጅቱ የቀረው በፍቅር አይን ያይሽ ስለነበር አላህ በዚና እንዲይዝበት አልፈለገም አሁን ግን ሚስቱ እንድትሆኚ ይፈልጋል አንቺስ??>> ** ╬╬═════════════╬╬                ᡣ𐭩 ይቀጥላል  ╬╬═════════════╬╬

  • ' ትዝም ባይላቹ ልልቀቅላቹ እንጂ 😢🫤 ...

  • ✨️ሀያዕ(አይናፋርነት)አንገት ደፊነት ወይም መሽኮርመም ሳይሆን አላህ በከለከለዉ ቦታ አለመገኘት ነዉ:: .©09¥

  • ╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗             "አሒል እና ፈራህ"        ✎...ፀሃፊ:-ሠምሐን ╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝       ።።።።።።•✿• ።።።።።።                 ክፍል  9⃣       ።።።።።።•✿• ።።።።።። Ahil••• ዛሬ በጣም ደክሞኛል ከእሱም በላይ ጀሚል መኝታ ከልክሎኛል ከባለፈው ጊዜ ጀምሮ ሁለታችንም ከልብ አልነበረም የምንነጋገረው አሁን ከኢሻ በኋላ መጥቶ አውፍ በለኝ ይለኛል <<በቃ ተወው አውፍ ብዬሃለው እኮ አሁን መተኛት እፈልጋለሁ አትረብሸኝ>> ይህን ስለው በደንብ አልነቃሁም ነበር እሱም መናገር አላቆመም <<…ከባባ ጋር ተነጋግረናል ፈራህ ከፈቀደች እና በአንተ ከተስማማች ልታገባት ትችላለህ……ግን ልቧ አንተን እንዲቀበል ዱዓ አድርግ>> ሲለኝ ብንን አልኩ ህልምም መሰለኝ ግን ከልቡ ነበር አክሎ ለአዝራን እንደሚነግረው እና እንደሚያግባባልኝ ነገረኝ ከክፍሌ እየገፈተርኩ አስወጣሁት <<ምን እያደረግክ ነው? ቆይ ላዋራህ እንጂ…አሂል በሩን ክፈትልኝ ፈራህ እኮ እሺ ካላለች ሁሉም ነገር ይቀራል>> ሲል እንዲሰማኝ ወደ በሩ ተጠግቼ <<ለእሱ አታስብ ለይል ስሰግድ አድራለሁ አንተን እሺ ያስባለ ጌታ ፈራህን ይከለክለኛል?>> <<አይከለክልህም ግን እናውራ…አውፍ እንዳልከኝ በምን እርግጠኛ እሆናለሁ ቢያንስ ልቀፍህ እስኪ>> በሩን ከፈትኩት እና ተቃቀፍን <<አሁን ከአንተ ጋር ሳይሆን ከአላህ ጋር ነው የማወራው ደህና እደር>> ፈገግ ብዬ በሩን በድጋሚ ዘጋሁበት [[[[[]]]]] 🍂 🍂 🍂 Ferah•••ኡዘይማ ኢሻን ስትሰግድ ኢልሃን ያለቅስና አቅፌ ሳባብለው ፀጥ አለ ይህን ስታይ ኡሚ <<ልጅ ቢኖርሽ ማባበል አይከብድሽም እኔ አዝራንን የወለድኩ ሰዓት ልጅ ስለነበኩ ማቀፍ አልችልም ነበር እሱ ራሱ እንደዛሬው እንዳይመስልሽ ኢላሂ በጣም አስቸጋሪ ነበር>> እያለችን ስንሳሳቅ ኡዘይማም ሰግዳ ተመለሰች ሁላችንም ተሰብስበን ነበር ኡዘይማ <<ይሄ በጥባጭ አስቸገረሽ አይደል? ስጪኝ ልቀበልሽ>> አለቺኝ <<ትንሽ ልቀፈው በጣም ደስ ይላልኮ ካልበጠበጠ ልጅ እንዴት ያድጋል?>> አልኳት እና ተወችው እንዲህ እንዲህ እየተባለ አቢ <<አንቺም የራስሽን አቅፈሽ እንይ ግን ወላህ የመጀመሪያ ልጅሽ ምን ቢሆን ደስ ይልሻል?>> አለኝ <<እኔ አላህ ከሰጠኝ መንትዮች እንዲሰጠኝ ነው የምፈልገው ወንድም ሆነ ሴት>> <<ስላልጠየቅኩሽ ነው እንጂ ብታገቢ ደስ ይለኛል>> <<አቢ እኔም ደስተኛ ነኝ ግን…>> <<ግን ምን?>> <<ግን ሳገባ በቅርበት የማላውቀውን ሰው ማግባት አልፈልግም ነው ለማለት የፈለግኩት>> <<ለእሱ አታስቢ አላህ ካንቺ ጋር ነው>> አለኝ ይህን ንግግር ስንት ጊዜ እንደጠበቅኩት አሂልን ከተመኘሁት ጊዜ አንስቶ ከአቢ ይህን ቃል ስጠብቅ ነበር ብላችሁ አታምኑም ምክንያቱም አሂልን በ1 እርምጃ የቀረብኩ ያህል ተሰማኝ የሆነ ሰው አለ ብዬ መናገር እችላለሁ ኢልሃንን ለኡዘይማ ሰጥቻት ወደ መኝታ ክፍል አመራሁ <<ፈራህ የት ነሽ?>> መባሉ አልቀረም << በጊዜ ማረፍ እፈልጋለሁ>> <<ታዲያ እራት እንብላ እንጂ>> <<አይ ጠገብኩ>> ለዊትር ሷላት መስገጃዬን አነጠፍኩ ከዚህ በላይ አላህ ምንም ሊያደርግልኝ እንደማይችል ተሰማኝ ምን አይነት ጌታ ነው ግን ያለኝ? ብዬ በፈጠረኝ ከወርትሮው በበለጠ እስከምኩራራበት ድረስ የሚገርም ውለታ ነው አላህ የዋለልኝ እንቅልፌ ጠፋ ሱጁዶቹን አስረዘምኩ ለአላህ የሚያንስበትም ቢሆን ከመቼውም በላይ በዛች ለሊት እንዳመሰገንኩት አመስግኜው አላውቅም 🌸አልሃምዱሊላህ🌸 ፈጅር ሙሉ ቤተሰቡን እየዞርኩ ቀሰቀስኩ አቢ እና አዝራን መስጂድ ሲሄዱ እኛ እዛው ሰገድን ቁርስ የሰራሁትም እኔ ነበርኩ ደስታዬ የዚህን ያህል ይነበብ ነበር ለማለት ነው ወደ ድርጅቱ አልሄድኩም እንደተለመደው ከኡሚ እና ከእህቴ ጋር ቀኑን ማሳለፍ ጀምረናል ╬╬═════════════╬╬                ᡣ𐭩 ይቀጥላል  ╬╬═════════════╬╬

  • ╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗             "አሒል እና ፈራህ"        ✎...ፀሃፊ:-ሠምሐን ╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝       ።።።።።።•✿• ።።።።።።                 ክፍል  8⃣       ።።።።።።•✿• ።።።።።። Ferah•••#ወላ ቱኽዚና የውሙል ቂያማ ኢነከ ላቱፍሊሁል ሚዓድ#(በመጨረሻው እና በትንሳኤው ቀን አታዋርደን እናም ከመዋረድ ጠብቀን)🌸አሚን ዛሬ የሶስተኛው ዒዳችን ቀን ነው ጁሙዓ የተከበረው የሳምንቱ እለት ዛሬ ስራ ለመግባት አልወሰንኩም እና ቁርስ እስከሚደርስ የበረንዳችንን አበባዎች ውሃ እያጠጣሁ እለቱን ጀመርኩት ጊዜያት እየሄዱ ነው እኔም ፍቅር በተባለው ጨለማ እየታወርኩ ነው ዛሬን ብቻ አይደለም ከድርጅቱ እየቀረሁ ያለሁት ብዙ ጊዜያትን የማሳልፈው መኖሪያ ቤት ውስጥ ነው ከኡሚ ፣ከኡዘይማ እና ከትንሹ ኢልሃን ጋር <<ፈራህ ቁርስ ደርሷል ነይ>> አለቺኝ ኡዘይማ ኡዘይማ ስላት ያራቅኳት ይመስለኛል እህቴ ልበላችሁ ብቻ ሄድኩ ••• እየበላን እንዳለ አዝራን <<እህቴ ቀሪዎችሽ እየበዙ ነው ለምን ትቀሪያለሽ?…አንቺ እየቀረሽ ካሳየሻቸው የድርጅቱ ሌሎች ሰራተኞች በስራቸው ላይ ዝንጉ ይሆናሉ ያንቺ መቅረት ብዙ ነገር ያጎድላል ያንቺን ቦታ እየሸፈንን ያለነው እኔ እና አቶ ዘይድ ነን>> አለኝ በአይኔ ቃኝቼው ፀጥ አልኩ አልመለስኩለትም እሱ ግን መልስ እየጠበቀ ነበር በዚህ መሃል ስልኩ ጠርቶ ገላገለኝ መብላት ቀጠልን እሱ ደግሞ ማናገር <<ሄሎ አሂል አሰላሙ አለይክ?>> ክው ነው ያልኩት አፈጠጥኩበት ምንም እኮ የተፈጠረ ነገር የለም loud ስለሆነ ይሰማል <<ወአለይከ ሰላም እንዴት አደርክ ረበሽኩህ አይደል?>> አለው ረጋ ባለ አንደበት መመገብ አቋርጬ እያዳመጥኩ ነው << አብሽር አረበሽከኝም ምነው?>> <<እሺ እ… የእኔ copy machine ተበላሽቶብኝ ነው ከፈቀድክልኝ ያንተን መጠቀም እችላለሁ?>> <<ኧረ ተው ወንድሜ አሁን ይህ መጠየቅ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው?>> <<ምንም ቢሆን ላስፈቅድህ ይገባል>> <<አንተ እንዳልክ በቃ ቁልፉን ከሰዓት ተቆጣጣሪው ውሰድ እንዲሰጥህ ደውዬ አሳውቀዋለሁ>> <<ሽኩረን እለክ>> <<ምንም አይደል?>> ተለያዩ ሲሰነባበቱ መመገብ ጀመርኩ አዝራንም ስልኩን እየዘጋ <<እንደ እኔ አይነት ግን እህት ያለው የለም>> አለ ደነገጥኩ ድንጋጤዬን በፈገግታ እየደበቅኩ <<እንዴት?>> <<ስልክ ሳናግር ሁሉም ትቶኝ ይበላል አንቺ ብቻ ነሽ ሳትበዪ የጠበቅሺኝ>> ኡፍፍፍፍ አልኩ በውስጤ ሌላ ነገር ያወራል ብዬ ነበር በዚህ ሁኔታ ቁርስ አለፈ ●●● 🎀 🎀 ♧አቢ መምህር ነው የአለማዊ ትምህርት ሳይሆን አንድ ትልቅ መርከዝ ውስጥ ርዕሰ መምህር ሆኖ ያገለግላል ኡሚ የቤት እመቤት ናት ኡዘይማ ከአዝራን ጋር ነበር የምትሰራው በእርግዝናዋ ምክንያት አቋረጠችው አቢን ፣ አዝራን እና ኑርን ሸኝተን ለጁምዓ እየተዘጋጀን ነበር አዝራን የደወለልኝ <<አቤት ወንድሜ:>> <<ምን እየሰራሽ ነው?>> <<ጁምዓም አይደል? መስጂድ ለመሄድ እየተዘጋጀሁ ነው?>> <<እሺ አውፍ በዪኝ ግን ቅር ካላለሽ የሆነ ፅሁፍ ረስቼ መጣሁ ሁቢ ትሰጥሻለች አታመጪልኝም?>> ወንድሜን ያለምክንያት አይደለም የምወደው በጣም ትህትና አለው በሃሳቡ ባልስማማ እንኳን እሺ ለማለት እገደዳለሁ የእጅ ሰዓቴን አየሁት 04:57 ይላል ጁማዓ ከሆነ በዚህ ሰዓት አሂል አይኖርም እሱ እንደማይኖር እርግጠኛ ነበርኩ ስለዚህ ላመጣለት ተስማማሁ ከመሄዴ በፊት ኡዘይማ የሆነ ጫማ ገዝታልኝ እንደነበረ ነገረቺኝ ጥቂት ከፍታ ቢኖረውም በጣም ወደድኩት የጁምዓ ስጦታ ይሁንልኝ አለቺኝ ስጦታን ማን ይጠላል? ከምትወዱት ሰው ሲሆን ደግሞ በጣም ደስ ይላል 🎀 🎀 መኪናዬን አቁሜ ወደ ድርጅቱ ስገባ "ምነው ፈራህ? ጠፋሽ ሰሞኑን? ፈራህ አለሽ ግን? የሚለኝ በዝቶ ነበር አንሃን ግን ትላንት ማታ ቤት አብረን ስላመሸን ምንም አላለቺኝም ጁምአ ስለሆነ እሷም ለመውጣት እየተዘጋጀች ነበር አሳንሰር(ሊፍት)ውስጥ ገባሁ 5ተኛ ፎቅ እንዲወስደኝ በተኑን ተጫንኩት እና ወደ ላይ ተምዘገዘገ አሁን ጉድ የፈላው እዚህ ጋር ነው አሂል ዛሬ እንዴት ከመውጫ ሰዓቱ እንደዘገየ ባላውቅም አሳንሰሩ ሲከፈት እኔ ልወጣ እሱ ደግሞ ሊገባ ሲል ተገናኘን ደነገጥኩ ለመኮሳተር እየሞከርኩ ከአጠገቡ አለፍኩ እሱም ወደ አሳንሰሩ ገባ አዝራን ቆሞ እያየን ስለነበር ገና የላከኝን ወረቀት እንደሰጠሁት <<ምንድነው?>> አለኝ ቢገባኝም ባልገባው <<ምኑ?>> <<አሰላሙ አለይኩም ማንን ገደለ? እንዲህ የምትዘጋጉት?>> <<እ… እ… ያው ቶሎ እንዳመጣልህ ስለነገርከኝ ስጣደፍ ማለት እንዳለብኝ ረሳሁት … እንደዛ ነው አሁን ቻው በቃ በኋላ እንገናኛለን>> ብዬው ሄድኩ አሂልን በቅርበት ያየሁት ዛሬ ብቻ ነው ፈገግ እያልኩ ወደ መኪናዬ ገባሁ ምክንያቱም እኔ ፈልጌው አልሄድኩም የአላህ ቀድር ነው ያገናኘን ግን ማየት አልነበረብኝም ለሱ ጥፋተኛ ነኝ ደግሞ ሌላ ጥያቄ "እኔ ዝም አልኩት እሺ ምክንያት አለኝ እሱ ግን ለምን ዝም አለኝ?" ╬╬═════════════╬╬                ᡣ𐭩 ይቀጥላል  ╬╬═════════════╬╬