tgindex
Afar Communication Bureau

Afar Communication Bureau

Статистика

Rakaakayak Doolat Angaarawih Biiro

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
5
Всего постов
32
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
12 авг.
Подписчики
786
+1 за 3 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
170
31 постов
Вовлечённость
21,6%
к подписчикам
Постов в день
0,7
всего 32
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
78
1/48двое суток
89
1/72трое суток
96

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ስለ #አረንጓዴዐሻራ መርሃግብር ማወቅ ያለብዎት 10 እውነታዎች፦ 🌱 ለለመለመች ኢትዮጵያ ተስፋን መትከላችንን እንቀጥል! 🇪🇹 #PMOEthiopia #አረንጓዴዐሻራ

  • "ዛሬ የምንተክላቸው ችግኞች ነገ በብዙ ጥቅም የሚሰጡ ናቸው።" አቶ መሐመድ አሊ ቢኢዶ የአፋር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ

  • “በክልሉ እየተካሄደ ያለው የአረንጓዴ አሻራ እንቅስቃሴ ለአካባቢው ስነ-ምህዳር ጥበቃ ብቻ ሳይሆን ለማህበረሰቡ የጎላ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያስገኘና የወጣቶችን ተሳትፎ በማሳደግ በኩል አዎንታዊ አስተዋጽኦ ያበረከተ ነው።” አቶ ኡመር ኑር የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የመሬት ቢሮ ኃላፊ

  • "ኢትዮጵያን ከወጣቶቿ ነጥሎ ማየት አይቻልም!" ኢትዮጵያን ከወጣቶቿ ነጥሎ ማየት እንደማይቻል የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የወጣቶች አብላጫ ዕድሜ ስብጥር ለሀገር ብልጽግና መረጋገጥና መጽናት ታላቅ ዕድል መሆኑን አሳሰቡ። የኢትዮጵያ ወጣት መልካም ዓላማን አንግቦ የሚንቀሳቀስ፣ የለውጥ ዋነኛ ሞተርና የሉዓላዊነት ጽኑ ማገር መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ወጣቱ ትውልድ የሀገሩን ታሪክ በአዲስ ብዕርና ብራና እየጻፈ እንደሚገኝ ጠቁመው፣ ሀገራችንን የኋሊት ጠፍንገው የያዟትን አጓጉል ልማዶች፣ አላስፈላጊ ንትርኮች፣ ጭቅጭቅ እና ግጭቶች በመራቅ አሁን ያለው ወጣት በልማት ላይ አተኩሮ ድህነትን እንደተጠየፈ ገልጸዋል። የመደመር መንግሥትም የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና የአመራርነት ሚና ለማጠናከር በትኩረትና በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ አስታውሰዋል። በመጨረሻም ሀገራዊ ርዕይን ዕውን ለማድረግ ሁሉም በንቃት እንዲተጋና በፍቅር እንዲመላለስ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ጥሪ አቅርበዋል።

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ

  • без подписи

  • без подписи

  • መንግሥት ሌብነትን እና ሕገወጥነትን ለመከላከል ጠንካራ እርምጃ እየወሰደ ነው ፡፡ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየተደረገ ያለውን ሰፊ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለማደናቀፍ በሚንቀሳቀሱ እና የሀገር ሀብት በሚመዘብሩ አካላት ላይ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ መሆኑን አስታወቀ። የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ወይዘሮ እናትዓለም መለሰ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ፈጣን ልማትና ዕድገት እንድታረጋግጥ በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን ጠቅሰው፣ በዚህም ሰፋፊና አስደናቂ ሀገራዊ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡ በዚህ ሂደት ግን ይህ ውጤት ጉዞው አልጋ በአልጋ እንዳልነበር አመላክተዋል ። ከተለያዩ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ተግዳሮቶች ባሻገር፣ ሕገ-ወጥነት እና የሙስና ተግባራት የልማቱ ዋነኛ ፈተና ሆነው መቆየታቸውንም ክብርት ሚኒስትሯ አብራርተዋል። እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ፣ የሕገ-ወጥነት ችግር በአንድ ወገን ብቻ የሚፈጸም ሳይሆን በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የሚያጠቃልል መሆኑን ገልጸው ከውስጥም ከውጪም ያሉ ኃይሎች በተደራጀ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ነበር፡፡ በንግዱ ማኅበረሰብ፣ በልማት ድርጅቶች፣ በመንግሥት መዋቅር፣ በግለሰቦች እና በተገልጋዮች ጭምር በተደራጀ መንገድ በስፋት የሚታይ ነው። እነዚህ አካላት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ከቁጥጥር ውጭ ለማድረግ በፋይናንስ እና በንግድ ሥርዐቱ ውስጥ ሰርገው በመግባት የኢኮኖሚ አሻጥር ሲፈጽሙ ቆይተዋል" ያሉት ወይዘሮ እናትዓለም፤ ድርጊቱ ሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ እንድታጣ፣ የዋጋ ንረትና ኮንትሮባንድ እንዲባባስ እንዲሁም በፍጆታ እቃዎች ላይ ሰው ሠራሽ እጥረት እንዲፈጠር ማድረጉን አስታውቀዋል። ይህንን የተደራጀ አሻጥር ለመግታት መንግሥት እና የሚመለከታቸው የሕግ አካላት ባከናወኑት ሰፊ ኦፕሬሽን አሻጥሩን ማክሸፍ መቻሉ ተገልጿል። በሌላ በኩል በመንግሥት አገልግሎት ሰጪ እና አስተዳደር አካላት እንዲሁም የሕዝብ ተቋማት ውስጥ የተሰገሰጉ ሌቦችን በማጽዳት ረገድ መንግሥት ቁርጠኛ እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ ያስታወቁት ወ/ሮ እናትዓለም በሕዝብ ሀብት ላይ ምዝበራ የፈጸሙ እና ተቋማዊ አሻጥር በሠሩ አመራሮች እና ሌሎች የጥቅም ትስስሮችና ድርጅቶች ላይ የማያዳግም እርምጃ መወሰዱንም አስታውቀዋል። በተለይም በሚከተሉት ቁልፍ ዘርፎች ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች ሰፊ ማጣራት ተደርጎ ተጠያቂነት ሰፍኗል ሲሉ ገልጸዋል፡ በመንግሥት አገልግሎት ሰጪ እና አስተዳደር አካላት፣ እንዲሁም ልዩ ልዩ የልማት ዘርፎች ውስጥ የተፈጸሙ ዋና ዋና የሙስና እና አሻጥር ወንጀሎችን ለማረም በተወሰዱት ሰፊ ኦፕሬሽኖች እና ሕግ የማስከበር እርምጃዎች ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር በተያያዘ ማሻሻያውን ለማደናቀፍ በማሰብ መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶችን በማከማቸት እጥረት እንዲፈጠርና ዋጋ እንዲንር ሲያደርጉ የነበሩ 13 አቅራቢ ድርጅቶች ባለቤቶች ላይ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል፤ ሕገ-ወጥ ተግባር ሲፈጽሙ በነበሩ ከ7 ሺህ በላይ የንግድ ድርጅቶችና መጋዘኖች ላይ የማሸግ እርምጃ ተወስዷል። በፋይናንስ ተቋማት እና የገንዘብ ዝውውር፡ በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በሐዋላ እና በጥቁር ገበያ ተሳታፊ የሆኑ 169 ኢትዮጵያውያንና የውጭ ሀገር ዜጎች በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርጓል። በተደራጀ መንገድ ከንግድ ባንክ ደንበኞች አካውንት ላይ በማጭበርበር ገንዘብ የወሰዱ 36 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው የባንክ ሒሳባቸው እንዲታገድ ተደርጓል። ለሕገ-ወጥ ዝውውር ሽፋን ይሰጡ የነበሩ 7 የክሪፕቶ ካረንሲ መተግበሪያዎች በሀገር ውስጥ እንዳይሠሩ ሙሉ በሙሉ ታግደዋል፤ ምርት ልከው የውጭ ምንዛሬ ተመላሽ ያላደረጉ 29 ላኪ የንግድ ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይም የህግ ተጠያቂነት ሰፍኗል። በቤቲንግ እና ፊንቴክ ቢዝነሶች፡ የደንበኞችን መረጃ በመደበቅ መንግሥትን ግብር ያጭበረበሩ፣ ገቢያቸውን የሰወሩ እና ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር በፈጸሙ 38 የቤቲንግ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወስዶ ባለቤቶቻቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል፤ የእነዚህ ሕገ-ወጥ ተቋማት የባንክ ሒሳብ ታግዷል፤ በማዕድን ዘርፍ ሕገ-ወጥ ዝውውር፡ የወርቅ ምርትን ከገበያ ውጭ በኮንትሮባንድ በማስወጣት ወንጀል የተሳተፉ የመንግሥት ኃላፊዎችን፣ የፀጥታ መዋቅር አመራሮችን፣ አምራቾችን እና የውጭ ዜጎችን ጨምሮ 183 ግለሰቦች በሕግ ተጠያቂ ተደርገዋል። በወንጀሉ የተሳተፉ የውጭ ሀገር ዜጎች ከሀገር እንዲወጡ ተደርገዋል፤ ሕገ-ወጥ ወርቅ፣ የወርቅ ሚዛንና ማቅለጫ፣ የተለያዩ የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣ እንዲሁም የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ከነዳጅ አቅርቦት እና ሎጂስቲክስ አንጻር፡ በሕገ-ወጥ መንገድ የሽፋን ደብዳቤዎችን በማዘጋጀት፣ ነዳጅ በመደበቅ እና አየር በአየር በመሸጥ ወንጀል የተሳተፉ 38 የመንግሥት አመራሮች በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርጓል። በተጨማሪም በሀገር አቀፍ ደረጃ በሕገ-ወጥ የነዳጅ ንግድ ላይ የተሰማሩ ከ650 በላይ ግለሰቦች፣ ማደያዎች እና አቅራቢ ኩባንያዎች ላይ የህግ እርምጃ ተወስዷል። በአፈር ማዳበሪያ ግዢ አሻጥር፡ በተቋሙ የጥቅም ትስስር በመፍጠር ጥራት የጎደለውና ጊዜው ያለፈበት የአፈር ማዳበሪያ ግዢ እንዲፈጸም በማድረግ ሆን ብለው ችግር በፈጠሩ የግብርና ሚኒስቴር አመራሮች ላይ የወንጀል ተጠያቂነት እርምጃ ተወስዷል። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (EEP)፡ ተገቢው መመሪያ በሌለበት ሁኔታ ከ36 የዳታ ማይኒንግ ድርጅቶች ጋር ሕገ-ወጥ የኃይል ሽያጭ ውል የፈጸሙ 4 ከፍተኛ አመራሮች ላይ እርምጃ ተወስዷል። የኤሌክትሪክ ኃይል ስርቆት የፈጸሙ ድርጅቶች እና ግለሰቦችም እንዲሁ በሕግ እንዲጠየቁ ተደርጓል። በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የሰዎች ዝውውር የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ሲስተምን በማዛባት እና ጉቦ በመቀበል ወንጀል የተሳተፉ 8 ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል። እንዲሁም በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ የተሰማሩ 44 ደላሎች እና አዘዋዋሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ሲውሉ፣ ሕገ-ወጥ ፈቃድ የነበራቸው ተቋማት ሙሉ በሙሉ ታሽገዋል። በገቢዎችና ጉምሩክ ዘርፍ፡ የግብር ውሳኔዎችን በመቀነስ፣ ሐሰተኛ ደረሰኞች በማወራረድ፣ እና በሲስተም መረጃ በማጥፋት የመንግሥት ገቢን ባሳጡ አካላት ላይ ኦፕሬሽን ተካሂዷል። በራሳቸው፣ በዘመድ እና በሹፌሮቻቸው አካውንት በመጠቀም የጥቅም ትስስር የፈጠሩ 109 ተጠርጣሪዎች ተለይተው ከእነዚህ መካከል 91 ግለሰቦች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል። መንግሥት የልማት እንቅፋት የሆኑትን ሙስና እና ሌብነት እንደማንኛውም ፈተና በጽናት እየተጋፈጣቸው መሆኑን ሚኒስትሯ አረጋግጠዋል። መንግሥት ሌብነትን ለማጥፋት ዘመናዊ አሠራሮችን በመዘርጋት እና በዲሲፕሊን የታነጸ አመራር ለመገንባት ቁርጠኛ ነው" ያሉት ወይዘሮ እናትዓለም፤ ሕዝቡ በስፋት የሚያነሣቸውን "ሌብነትን አስቁሙልን" ጥያቄዎች ለመመለስ የተጀመረዉ ጠንካራ እርምጃ ውጤታማ እንዲሆኑ ማኅበረሰቡ ሙስናን በማጋለጥ፣ ሕጋዊ መብቱን በመደለያ ባለመጠየቅ እና ከሕገወጦች ጋር ባለመተባበር ከመንግሥት ጎን በመቆም ሀገርን ከሕገወጥነትና ሙስና የመከላከል ታሪካዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

  • የትናንትና በአንድ ጀምበር ከ800 ሚሊዮን በላይ ችግኞች፤ በ26 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ማሳካት ታሪካዊ ፅናት እና የጋራ ድል ነው! ምስጋና ለሁሉም።- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) #አረንጓዴዐሻራ #GreenLegacy

  • እየሰራን ያለነው ለልጆቻችን ተስፋን ለመትከል ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

  • ዛሬ የምንተክላት ችግኝ የነገዋን ኢትዮጵያ የምታለመልም የአየር ንብረት ለውጥን የምትከላከል እና ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገርን የምታስረክብ ናት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) #ተስፋንእንትከል #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #ኢዜአ #አረንጓዴዐሻራ #በአንድጀምበር800ሚሊዮንችግኝ #GreenLegacy

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи