- Последний пост
- 24 дек. 2024 г.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ውድ #የድህረ_ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኛችን ወርሃዊ የቆጣሪ ንባብ እየተወሰደ መሆኑን ያረጋግጡ! የቆጣሪ ንባብ ካልተወሰደ ለተጨማሪ ውዝፍ እዳ የሚዳርግ በመሆኑ ወቅቱን የጠበቀ ንባብ መወሰዱን ያረጋግጡ፤ አለመነበቡን እርግጠኛ ከሆኑ በአቅራቢዎ ለሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል በመሄድ ያሳውቁ፡፡ የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳብ ከዚህ በፊት በሚከፍሉበት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ተቋሙ በዘረጋቸው ዘመናዊ የክፍያ አማራጮች ይፈፅሙ! #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ለክቡራን ደንበኞቻችን ======= ዛሬ ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በሲስተም አለመረጋጋት ምክንያት ኤሌክትሪክ በሀገር አቀፍ ደረጃ መቋረጡን ይታወቃል። በመሆኑም የተቋረጠውን ኤሌክትሪክ መልሶ የማገናኘት ሥራ እየተሰራ ሲሆን ችግሩን በመቅረፍ ዳግም ሲስተሙን ተመልሶ እስከሚናገናኝ ድረስ ክቡራን ደንበኞቻችን በትዕግስት እንድትጠብቁ በአክብሮት እንጠይቃለን። የአፋር ኤሌክትሪክ አገልግሎት ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡- ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/100068806796522/ ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia ቴሌግራም፡ https://t.me/afeeu ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtilit
ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ሀይል ወደ አገልግሎቱ ተመልሷል። ዛሬ እሑድ ህዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም 12:00 ጀምሮ በሠመራ ሠብስቴሽን ላይ በሚደረግ ጥገና ምክንያት ዋና ከተማ፣ ሎግያ፣ ሚሌ፣ ኤሊውሃ፣ ዱብቲ፣ አይሳኢታ፣ ዲጂኦቶ፣ ጋላፊ፣ ሰርዶ፣ ኤሊዳር፣ አፍዴራ ዋና ዋና ከተሞች እና አካባቢዎቻቸው ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ከተያዘለት ጊዜ በፊት ስራውን በማጠናቀቅ ወደ አገልግሎቱ ተመልሷል፡፡ የጥገና ስራው ተጠናቆ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት ለጠበቃችሁ ደንበኞቻችን ከልብ እናመሰግናለን፡፡ #የአፋርክልልኤሌክትሪክአገልግሎት
የጥገና ሥራ ለማከናወን ሲባል የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት ***** እሑድ ህዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 12፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሰመራ ሰብሰቴሽን ላይ በሚያደርገው ጥገና ስራ ምክንያት በሠመራ ዋና ከተማ፣ ሎግያ፣ ሚሌ፣ ኤሊውሃ፣ ዱብቲ፣ አይሳኢታ፣ ዲጂኦቶ፣ ጋላፊ፣ ሰርዶ፣ ኤሊዳር፣ አፍዴራ ዋና ዋና ከተሞች እና አካባቢዎቻቸው የኃይል አቅርቦቱ ተቋርጦ ይቆያል፡፡ ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንን ተገንዝባችሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ ተቋማችንን የሚመለከቱ ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡ ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/ ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
ነፋስ ቀላቅሎ በጣለ ከባድ ዝናብ ምክንያት የተቋረጠ የኃይል አቅርቦት ስለማሳወቅ። ==== ዛሬ ሀሙስ 30/01/2017 ዓ.ም ቀን 11:00 አካባቢ ነፋስ ቀላቅሎ በጣለ ከፍተኛ ዝናብ የ 66 ኬቪ ሀይል ተሸካሚ የኤሌክትሪክ መስመር ምሰሶዎች ላይ ጉዳት በመድረሱ ወረር አዶብተሌ፣ገዋኔ ፣ ሳቡሬ ፣ገልአሎ እና አካባቢዎች የኤሌክትሪክ የኃይል አቅርቦት ተቋርጧል፡፡ በመሆኑም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የጥገና ስራ ተጠናቆ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡ ወደ 9380 የስልክ መስመር ይደውሉ #የአፋርኤሌክትሪክአገልግሎት ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡- ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/100068806796522/ ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia ቴሌግራም፡ https://t.me/afeeu ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtilit
ነፋስ ቀላቅሎ በጣለ ከባድ ዝናብ ምክንያት የተቋረጠ የኃይል አቅርቦት ስለማሳወቅ። ==== ዛሬ ሰኞ 06/01/2017 ዓ.ም ምሽት 12:00 አካባቢ በነፋስ ቀላቅሎ በጣለ ከፍተኛ ዝናብ ሀይል ተሸካሚ የኤሌክትሪክ መስመር ምሰሶዎች ላይ ጉዳት በመድረሱ ሠመራ ፣አይሳኢታ እና አካባቢዎች የኤሌክትሪክ የኃይል አቅርቦት ተቋርጧል፡፡ በመሆኑም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የጥገና ስራ ተጠናቆ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡ ወደ 9380 የስልክ መስመር ይደውሉ #የአፋርኤሌክትሪክአገልግሎት ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡- ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/100068806796522/ ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia ቴሌግራም፡ https://t.me/afeeu ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtilit
እንኳን ለ2017 አዲሱ ዓመት በሠላም አደረሳችሁ፡፡ ==== የአፋር ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመላው ደንበኞቹ በሙሉ እንኳን ለአዲሱ 2017 ዓ.ም በሠላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡ በአዲሱ ዓመት ብልሹ አሰራሮችን ለመቅረፍ፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ከምንጊዜውም በላይ በቁርጠኝነት እንሰራለን፡፡ #የአፋርክልልኤሌክትሪክአገልግሎት
ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያን በቀላሉ፣ የትም ሳይሄዱ ባሉበት ሆነው ከዚህ በፊት በሚከፍሉበት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ካሻዎ በቴሌ ብር፣ በሲቢኢ ብር፣ በሞባይል ባንኪንግ፣ በአዋሽ ብር ፕሮ ወይም በኤም ፔሳ በኩል ይፈፅሙ፡፡ ፍጆታዎ በስልክዎ! ዘመናዊ የክፍያ አማራጭ በመምረጥ ኑሮዎን ያቅሉ! #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
አዲስ የነጠላ ፌዝ ቆጣሪ ለማስገባት የሚያስፈልጉ መሰረታዊ ቅድመ ሁኔታዎች 👉 የአመልካቹ የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ 👉 አንድ ጉርድ ፎቶግራፍ 3 በ 4 የሆነ 👉 የኪራይ ቤት ከሆነ ከባለቤቱ የተሰጠ የስምምነት ደብዳቤ 👉 ለተጨማሪ ቆጣሪ ከሆነ የኤሌክትሪክ ፍጆታ የመጨረሻ ደረሰኝ 👉 ጥያቄው ለሽርክና ማህበር ከሆነ የሽርክና ማረጋገጫ ሰነድ ኮፒ በተጨማሪም የኃይል ጥያቄውን ያቀረበው ቤቱን በመንግስት ስም የተዋዋለ ተከራይ ከሆነ በሚመለከተው የመንግስት አካል ፈቃድ ማግኘት እና ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ ሲያቀርብ አገልግሎቱ የሚፈቅድለት ሲሆን፤ ነገር ግን ማንኛውም ኃላፊነት ቤቱን የሚያስተዳድረው የመንግስት አካል ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል አመልካቹ የመንግስት/የቀበሌ ቤት ተከራይ ከሆነ የኪራይ ውል አያይዞ ሲያቀርብ አገልግሎቱን በተከራዩ ስም ሊያገኝ የሚችል ሲሆን፤ በአጠቃላይ እነዚህን እና ከላይ የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች አሟልቶ የመጣ አዲስ ቆጣሪ ፈላጊ ደንበኛ ያለምንም ውጣ ውረድ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችል እናሳውቃለን፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
በኤሌክትሪክ ማሰራጫ ጣቢያ ላይ በተፈጠረ የቴክኒክ ችግር የተቋረጠ የሀይል አቅርቦት ስለማሳወቅ ========= ዛሬ በቀን 17/12/2016 ምሽት 2:40 አካባቢ ጀምሮ በሠመራ በኤሌክትሪክ ማሰራጫ ጣቢያ ላይ በተፈጠረ ቴክኒካል ችግር ምክንያት በሠመራ ፣ሎጊያ ፣አይሳኢታ ፣ዱብቲ፣ ሚሌ፣ ኤሊውሀ፣ ዲችኦቶ፣ ኤሊዳአር፣ ጋላፊ፣አፍዴራ እና አካባቢዎች ላይ የሀይል አቅርቦት የተቋረጠ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ብልሽቱ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል በኩል ተጠግኖ አገልግሎት እስከሚሰጡ ድረስ ክቡራን ደንበኞቻችን በትዕግስት እንድትጠብቁን እንጠይቃለን። #የአፋርክልልኤሌክትሪክአገልግሎት ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡- ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/100068806796522/ ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia ቴሌግራም፡ https://t.me/afeeu ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
без подписи
без подписи
без подписи
የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር የአፋር ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰራተኞች በዱብቲ ከተማ በመገኘት አሻራቸውን አኑረዋል፡፡ = = = = = የአፋር ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች ዱብቲ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በመገኘት በአንድ ጀምበር 6 መቶ ሚሊየን ችግኞች ተከላ ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ ተሳትፈዋል:: በቦታው ላይ ተገኝተው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ያስጀመሩት የሪጅኑ ስራ አስፈፃሚ ኢ/ር ያሲን አሊ በመርሃ ግብሩ አምስት የተለያዩ ዝርያ ያላቸው ከ600 በላይ ችግኞች ተዘጋጅተው የተተከሉ መሆናቸው ገልፀዋል፡፡ እንደ ስራ አስፈፃሚው ገለፃ በተቋሙ በሶስት የተለያዩ ቦታዎች የተካሄደው የችግኝ ተከላ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እንደ ሀገር በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል የተጀመረው ንቅናቄ አካል መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ከተተከሉት ችግኞች መካከል ከ60 % በላይ የሚሆኑት የሎሚ እና ፓፓያ መሆናቸውን የገለፁት ስራ አስፈፃሚው፡፡ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ለተሳተፉት የስራ መሪዎች እና ሰራተኞች ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን እንዲፀድቁ ሁሉም ክትትል እንዲያደርግ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ በዛሬው እለት ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራን ማኖር ለቀጣይ ትውልድ ትልቅ ትሩፋት መሆኑን የገለፁት ስራ አስፈፃሚው የተቋሙ የስራ መሪዎችና ሠራተኞች ንቅናቄው ተቀላቅለው ችግኞችን በመትከል አሻራቸውን በማኖራቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ #የአፋርኤሌክትሪክአገልግሎት
без подписи
без подписи
''የምትተክል ሃገር የሚያፀና ትውልድ'' በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል አሻራችንን እናኑር! 1 ቀን ብቻ ቀረው! #አረንጓዴአሻራ #Greenlegacy #የአፋርኤሌክትሪክአገልግሎት
ዘመናዊ የክፍያ አማራጮች በመጠቀም ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳብዎን በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በቴሌብር፣ በሞባይል ባንኪንግ፣ በሲቢኢ ብር፣ በኢንተርኔት ባንኪንግ እና በአዋሽ ፕሮ ይፈፅሙ፡፡ ዘመናዊ የክፍያ አማራጮችን ሲጠቀሙ አስፈላጊ ካልሆነ ወጪና እንግልት ያድናል! ኑሮንም ያቀላሉ! ክቡራን ደንበኞቻችን የተጠቀማችሁበትን የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በኤጀንቶች በኩል ስትፈጽሙ ምንም አይነት የአገልግሎት ክፍያ የማይከፈል መሆኑን እናሳውቃለን። ወደ 9380 የስልክ መስመር ይደውሉ #የአፋርኤሌክትሪክአገልግሎት ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡- ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/100068806796522/ ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia ቴሌግራም፡ https://t.me/afeeu ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtilit
без подписи
без подписи