Artios Media
СтатистикаWe Are Artios! We are complete! #Artios spiritual journey towards #completeness ! "So that the man of God may be complete and equipped for every good work." 2 Tim 3:17 Join the complete journey @artios_media
- Последний пост
- 10 апр.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
https://youtu.be/39LKYYnoa00
без подписи
We are pleased to introduce our new staff member; Selome Solomon, a Law graduate from Haramaya University. She has joined us as Registrar, Finance and Administration Officer. She can be reached at: Phone: 0940143053 Telegram: @bekael69 Email: solomesolomon436@gmail.com Welcome to the team, Selome!
Faye - Praying for the students 🔥🔥
Baye - OT Survey Lecture 🔥🔥
✨እነሆ ሰውየው✨ የኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰው መሆንና በዚያም ያስገኘልን ትሩፋቶች። ድንቅ ትምህርት በየአምላክ ቸርነት🎧
You can suggest your friends now !!! ATC Lebu campus is officially started. Equipping Saints for every good work.
без подписи
ስለዚህ የሰው ልጅም ባላሰባችሁት ሰዓት ይመጣል፤ እናንተም እንደዚሁ ዝግጁ ሁኑ። ማቴ 24፥44 2018 ዓ.ም የንጥቀታችን ዓመት ቢሆንስ? በምድር ላይ የሚኖረን ዘመን ሁሉ ሙሽራችንን ኢየሱስን ለመቀበል የምንዘጋጅበትና እንደ ታማኝ ሚዜዎች ደግሞ ሙሽሪትን አስውበን ለባሏ ለማቅረብ የምንተጋበት ዘመን ያድርግልን። @artios_media @artios_media @artios_media
ማጠቃለያ - የተገራ ሕይወት የአካል ብቃት ልምምድ ለጥቂት ነገር ይጠቅማልና፤ ለእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ራስን ማሠልጠን ግን ለአሁኑም ሆነ ለሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው ለሁለቱም ይጠቅማል። 1ኛ ጢሞ 4: 8 ላለፉት 52 ሳምንታት ስናጠና የነበረውን አንኳር የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮት ልንቋጭ ነው። በትጋት እየተከታተላችሁ የነበራችሁ ሁሉ እግዚአብሔር ይባርካችሁ እላለሁ። በቅርቡ ከወዳጆቼ ጋር በምን አይነት ሁኔታ እንደምናገለግላችሁ ተማክረን እንመለሳለን። እናንተም በምክርና በፀሎት ብትረዱን ብዬ እጠይቃለሁ። ወዳጆቼ! የተያያዝነው የመንፈሳዊ ሕይወት ጉዞ ቀላል ስላለሆነ የተገራ ልምምድ እንደሚያስፈልገን በአጽንኦት ላሳስባችሁ እሻለሁ። ከራሴ ጀምሮ ለአንድ ቀን እንኳ እራሳችንን ሸብበን፣ ስሜታችንን ጨቁነን በፀሎት መሰዊያችን ላይ መሆን፣ ቃሉን በደስታ የማጥናት ልምምድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ለመሞላት የሚናፈቅ ጉጉት ከአማኞች ሕይወት እየሳሳ መምጣቱ አሳሳቢ ጊዜ ላይ መሆናችንን ያመላክታል። በዚያ ፈንታ ሰሞነኞች፣ ፕሮግራም ወዳዶች፣ በዝግጅቶች የተሰላቸን፣ በግርግር ሕይወት የታከትን፣ ስለ ክርሰቶስ ሳይሆን ስለ ፕሮግራምና ግለሰብ ችሎታ ማውራት የሚቀናን ሆነን መገኘታችን ያሳዝናል። ያለንበት ዘመን ክፋት፣ አጋንንት ትውልዱን ወደ ሞት እየነዳ ያለበት ፍጥነትና የእኛ ዘመኑን የመዋጀት ብቃትና መንፈሳዊ ዝግጅት በጭራሽ የሚመጣጠን እንዳልሆነ በብዙ መልኩ እያየን ነው። አሁንም ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ እግዚአብሔር እድል ከሰጠን ወደ ቀድሞ የሐዋርያት ቤተክርስቲያን ልምምድ መመለስ አለብን። ከምንጊዜውም በላይ የተገራ ሕይወት ያስፈልገናል። የተገራ ማለት የሠለጠነ፣ የተማረ፣ የተቀጣ፣ ያልተለቀቀ፣ የተሸበበ፣ መስመሩን የሚያውቅ፣ የታሸ፣ የተለማመደ የሚሉትን ቃላት ያቀፈ ነው። የተገራ ሕይወት በምኞትና በናፍቆት አይገነባም ብቸኛው መንገድ መለማመድ ብቻ ነው። ጢሞቴዎስ የተመከረው እራስህ አስለምድ ተብሎ ነው። የመጨረሻውን መከር እንድንሰበስብ የታደልን ቅዱሳን በግላችንና በምድራችን እውነተኛና ዘላቂ የሆነ መንፈሳዊ ተሃድሶ እንዲመጣ ከተፈለገ ያታከተንን ፍሬ አልባ ልምምድ አቁመን እራሳችንን እየገራን ወደ ፀሎት መሰዊያችን እንመለስ። ዕለት ዕለት መስቀላችንን ተሸክመን፣ በክርስቶስ ላይ ያየነውን የሕይወት ምሳሌ ፈለግ ተከትለን ለመኖር እንወስን። ቆርጠን ወስነን ስንጀምር ፀጋው ያግዘናል መንፈሱም ይረዳናል። ዛሬ የማሰላስለው እውነት፦ የተገራ ሕይወት መገንባት ለመንፈሳዊ ዕድገት የማይተካ ሚና አለው። የዛሬው ፀሎት፦ "እግዚአብሔር ሆይ በቁርጥራጭ ፕሮግራሞች ያልተገደበ፣ የተገራና የሰለጠነ ሕይወት እንዲኖረኝ፣ ቋሚ የፀሎትና የቃልህ ማጥኛ መሠዊያ እንዲኖረኝ እርዳኝ"
የዘላለም ፍሰሐ 52ኛ ሳምንት 7ኛ ቀን ከእንግዲህ ወዲህ ሌሊት አይኖርም፤ ጌታ አምላክ ስለሚያበራላቸው የመብራት ወይም የፀሓይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ። ራእይ 22:5 የእግዚአብሔር የትድግና ፕሮግራም መቋጫ ተራኪ የሆነው የዮሐንስ ራዕይ መጽሐፍ በመጨረሻዎቹ ሁለቱ ምዕራፎች ቅዱስ በመንግስተ ሰማያት ውስጥ የሚኖራቸውን አኗኗር ይነግረናል። በዘፍጥረት ላይ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ሲፈጥራቸው መልካም፣ ውብና ለሰው ልጆች ተስማሚ እንድትሆን አድርጎ ነው። ነገር ግን በኀጢአታችን ምክንያት ምድር ተረገመች። የተፈጥሮ ስርዓቶች ተዛቡ። እግዚአብሔር የጠፋውን የሰውን ዘር ለመታደግ የመጨረሻ የፍቅሩ መገለጫ የሆነውን ልጁን ኢየሱስን ልኩ የዘላለምን ሕይወት ግብዣ አደረገልን። በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን እድል ያገኘን ሁሉ ክርስቶስ በክብሩ ዳግም ሲመለስ እራሱ ወዳዘጋጀልን አዲስ ከተማ ወስዶ እዚያ ያኖረናል። የአዲሱ ሀገራችን ስፋት፣ ውበት፣ ነዋሪዎች፣ የኑሮ ሥርዓትና የመሳሰሉ ነገሮች በራዕ 21ና 22 እጅግ በሚያጓጓ መልኩ በዝርዝር ተነግሮናል። የተጻፈው ነገር ሁሉ እውነት መሆኑን የሚያምን ሁሉ አንድ ቀን እንኳን በዚህ ዓለም ውስጥ ለማደር የሚፈልግ አይመስለኝም። ወገኖቼ!! የአዲሲቷ ኢየሩሳሌም ውበት ልብን የሚጠፋ፣ ነፍስን የሚማርክ፣ ሁለንተናችንን በአግራሞት የሚሞላ ነው። የተዘጋጀልን ሀገር ብቻ ሳይሆን አዲስ የትንሣኤ አካል የሚባል የከበረ ሥጋ ነው። በምድር ላይ በብዙ ስደትና ስቃይ ከምንኖርበት ሥርዓተ ወጥተን ከክርስቶስ ጋር ለዘለዓለም የምነግስበት አዲስ የንግስና ማዕረግ ተዘጋጅቶ ይጠብቀናል። ከተጣልንበት ከሞት መንደር በፍቅሩ ጠርቶን የዘላለምን ሕይወት ሰጥቶ፣ አገር አዘጋጅቶ፣ አብረነው እንድነግስ ተመልሶ በቅርቡ ለሚመጣ ለጌታችንና ለንጉሣችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር፣ ምስጋና፣ ውዳሴ፣ አምልኮ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁንለት። አሜን!! ዛሬ የማሰላስለው እውነት የዘላለም ፍሰሐ መደምደሚያው የዘላለም ንግሥናን ተጎናፎ መኖር ነው። የዛሬው ፀሎት እግዚአብሔር ሆይ ካንተ ጋር ለዘላለም ነግሼ የመግዛትን እድል ስለሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ። አሜን!!! መልካም ቀን!! @artios_media @artios_media @artios_media
የዘላለም ፍሰሐ 52ኛ ሳምንት 6ኛ ቀን ድል የሚነሣ ይህን ሁሉ ይወርሳል፤ እኔም አምላክ እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል። ራእይ 21:7 በዮሐንስ ራዕይ ውስጥ የክርስቲያኖች ምድራዊ ሕይወት በብዛት በውጊያ ስለ ተመሰለ ለክርስቶስ ታማኝ በመሆን የሚደርስባቸውን ስደት እስከ መጨረሻው ጸንተው የሚጓዙት ድል ነሺዎች በመባል ተጠርተዋል። እግዚአብሔር ደግሞ ለእዚህ ድል ነሺዎች የዘላለም ሕይወት አክሊል አዘጋጅቶ ይጠብቃቸዋል። በተጨማሪም ከራዕ 19፥ 1-6 ባሉት ክፍሎች እነዚህ የእምነት አርበኞች ብዙ ትሩፋቶች እንደሚጠብቋቸው ይናገራል። ከእነዚያም በረከቶች በመጀመሪያው ከእግዚአብሔር ጋር በአንድ ከተማ ውስጥ አብሮ የመኖር በረከት ነው። የነገር ሁሉ ምንጭ ከሆነው ከእግዚአብሔር ጋር ከመኖር የሚበልጥ ፍሰሐ የለም። በሁለተኛው በእግዚአብሔር እንባቸው ሁሉ ከዐይናቸው እንደሚታበስ ያበስራል። ይህም ከምድራዊ ፍልሚያ በኋላ ወደ አዲስቷ ኢየሩሳሌም ሲገቡ በእግዚአብሔር የሚያገኙትን የመጀመሪያ መጽናናት የሚያመለክት ነው። ቀጥሎም ከእንግዲህ ወዲህ ሞት ወይም ሐዘን ወይም ልቅሶ ወይም ሥቃይ አይኖርም በማለት የቀድሞው ሥርዐት ማለፉን ያበስራል። ይህም ምድራዊውን ስደትና መከራ በጌታው ፀጋ ተቋቁሞ ወደ አዲስቷ ኢየሩሳሌም የገባ አማኝ ከእንግዲህ ሌላ የመከራ የሕይወት ስርዓት እንደማይገጥማቸው የሚያሳይ አስተማማኝ ተስፋ ነው። በመጨረሻም የዘላለም ፍሰሐ መደምደሚያው "እኔም አምላክ እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል" የሚል የኪዳን ቃል ነው። የእግዚአብሔር ልጅ ከመሆን የሚበልጥ ክብርና ደስታ የለም። በአጠቃላይ በእግዚአብሔር ከተማ ውስጥ የመኖር መብት የሚያገኙት ቅዱሳን በሙሉ በምንም መንገድ የማይወሰድባቸውን ዘላለማዊ ደስታ ተጎናጽፈው የታረደውን በግ ጌታቸው ኢየሱስ ክርስቶስን እያመለኩት ይኖራሉ። ዛሬ የማሰላስለው እውነት የመጨረሻው የዘላለም ደስታ ጥጉ የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ መኖር ነው። የዛሬው ፀሎት እግዚአብሔር ሆይ በዘላለም ኪዳናህ አባት ልትሆኝ ስለጠራኸኝ አመሰግንሃለሁ። አሜን!!! መልካም ቀን!! @artios_media @artios_media @artios_media
የዘላለም ፍሰሐ 52ኛ ሳምንት 5ኛ ቀን “ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፥ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት፥ ስማቸው በሰማይ ወደ ተጻፈው ወደ በኵራት ማኅበር ቀርባችኋል።" ዕብ 12፥22-23 የብሉይ ኪዳን አማኞች፣ ማለትም ከግብፅ የወጡት እስራኤላውያን፣ የመጨረሻ የክብር ጥግ ያዩት በሲና ተራራ ላይ የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ክብር ነበር። የአዲስ ኪዳን አማኞች ደግሞ የደረሱበት የክብር ጥግ ከላይ ባለው ክፍል ላይ ተብራርቷል። በምድር ላይ ተቀምጠን እዚህ ደርሰናል ወይ በሚያስብል ሁኔታ ወደ እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል ይላል። በተጨማሪም በዚያ ከተማ ውስጥ ያለውን ክብር ይጠቁማል። በዚያ የእግዚአብሔር ከተማ ውስጥ ካሉት ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ በደስታ የተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት መኖራቸው ነው። እነዚህ መላእክት በዘላለም ፍሰሐ ውስጥ ሆነው ለንጉሣቸው የሚቀኙ ናቸው። የእግዚአብሔር ከተማ የላይኛዋ የጽዮን ሀገር ከምትታወቅባቸው አንደኛው መገለጫዋ የደስታ ጅረት ሳያቋርጥ ከበጉ ዙፋን ስር እየፈሰሰ የነዋሪዎቿን ሕይወት በማረስረሱ ነው። አሁን በሥጋ በምድር ላይ እየኖርን ያለን አማኞች ደርሳችኋል የተባልነው ቦታ ሙሉ በሙሉ ጠቅልለን እዚያ ባንገኝም ሕጋዊ ስፍራቸው ከክርስቶስ ጋር ሕይወታችን ተሰውሮ ያለው በመንግተ ሰማይ ነው። መንግስተ ሰማይ በዘላለማዊ ፍሰሐ የተሞላች አገር ነች። አሁን ሙሉ በሙሉ ያንን ደስታ ማጣጣም ባንችልም በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት መረዳት ግን እንችላለን። ከምድራዊ ድንኳን ተለይተን ስንሄድ ደግሞ ባለ ማቋረጥ በደስታ እንሞላለን። ወዳጆቼ!! በምድር ላይ ስንኖር ልባችንን በሐዘን በሚሰብሩ በብዙ ሁኔታዎች ውስጥ ብናልፍም ፍጹም የሆነ ደስታና የፍሰሐ ሕይወት በመንግስተ ሰማያት ተዘጋጅቶልን ስላለ እርሱን ተስፋ እያደረግን ሩጫችንን በጽናት በመሮጥ እንድንጨርስ ጌታ ይርዳን። ዛሬ የማሰላስለው እውነት ወደ እግዚአብሔር ከተማ ደርሰናል የዛሬው ፀሎት እግዚአብሔር ሆይ በደስታ ወደ ተሞላችው ወደ አዲስቱ እየሩሳሌም ስለ ተጋበዝኩ እጅግ አርጌ አመሰግንሃለሁ። አሜን!!! መልካም ቀን!! @artios_media @artios_media @artios_media
የዘላለም ፍሰሐ 52ኛ ሳምንት 4ኛ ቀን እኔ ድል ነሥቼ ከአባቴ ጋር በእርሱ ዙፋን ላይ እንደ ተቀመጥሁ፣ ድል የሚነሣውንም ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ እንዲቀመጥ አደርገዋለሁ። ራእይ 3:21 በእስያ አውራጃ ያሉ ሰባቱ አብያተክርስቲያናት በትግል ውስጥ ናቸው። የሮም ገዢዎች ቤተክርስቲያንን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ታጥቀው ተነስተዋል። ሐዋርያው ዮሐንስ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር ስለ ክርስቶስ ምስክርነት መከራን በመቀል ላይ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ለእርሱ ታማኝ በመሆን በብዙ ስቃይ ውስጥ እያለፈች ያለችውን ቤተክርስቲያን በሚገባ እየተመለከታት ነው። በባሪያው ሐዋርያው ዮሐንስ አማካኝነት ያሉበትን አጠቃላይ መንፈሳዊ ደረጃ ግምገማ ግልጽ በማድረግ ድካማቸውን፣ ብርታታቸውን፣ ማስተካከያ የሚገባውንና በመረሻ ድል ከነሱ የሚጠብቃቸውን ሽልማት ይነግራቸዋል። በዚሁ መሰረት በመጨረሻ ለተጠቀሰችው የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ድል የነሱት የሚጠብቃቸውን ከፍ ያለ ሽልማት ይነግራቸዋል። ምናልባትም ለአንድ ሰው የዘላለምን ሕይወት ከማግኘት ከጥሎ የመጨረሻ የክብር ጥግ ሊሆን ይችላል። እርሱም በክርስቶስ ዙፋን ላይ የመቀመጥ ዕድል ማግኘት ነው። ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ እራሱ ነው በዙፋኔ ላይ እንዲቀመጥ አደርገዋለሁ ያለው። ለሰባቱ አብያተክርስቲያናት በተላከላቸው ደብዳቤ መጨረሻ ላይ ድል ስለሚነሱ የተገባላቸው ሽልማቶች እጅግ አጓጊ ቢሆኑም ለሎዶቅያ ቤተክርስቲያን የተገባላት ግን ከሁሉ የሚበልጥ ነው። አንድ ንጉሥ ዙፋኑን አጋራ ማለት በመንግሥቱ ውስጥ ባሉት ጉዳዮች ላይ ከንጉሡ ጋር የማስተዳደርና ኃላፊነትን መስጠቱንና በግዛቱ ውስጥ ባሉት ማንኛውም ሃብቶች ደግሞ የመጠቀምን ዕድል ማጋራቱን የሚያመለክት ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በሎዶቅያ ላሉት ታማኝ አገልጋዮች እንደዚሁም በየዘመናቱ ለነበሩት ቅዱሳን በመንግስቱ ውስጥ የገባላቸው ተስፋ ከእርሱ ጋር የመንገስን ነው። በትያጥሮን ላሉት አማኞችም "ድል ለሚነሣና ሥራዬንም እስከ መጨረሻው ለሚፈጽም በአሕዛብ ላይ ሥልጣን እሰጠዋለሁ፤ እርሱም፦ ‘በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እንደ ሸክላ ዕቃም ይፈጫቸዋል፤’ ይህም ልክ እኔ ከአባቴ ዘንድ ሥልጣንን እንደ ተቀበልሁ ነው"። (ራእይ 2፥26-27) በማለት ይናገራል። ወዳጆቼ ከክርስቶስ ጋር በዙፋኑ ላይ መቀመጥ ማለት ምን እንደሆነ ሙሉ በሙሉ ባይገባንም እጅግ አጓጊ ክብር እንደሆነ ግን እናምናለን። ስለዚህ የገባንበትን የእምነት ገድል በሚገባ ታግለን ድል በመንሳት የተዘጋጀለንን አክሊል እንድንቀበል ጌታ ይርዳን። ዛሬ የማሰላስለው እውነት ከክርስቶስ ጋር ለዘላለም መንገስ ትልቅ ክብር ነው። የዛሬው ፀሎት እግዚአብሔር ሆይ አንድያ ልጅህ ኢየሱስ ክርስቶስ ድል ነስቶ ካንተ ጋር ነግሶ ለዘለዓለም እንደሚኖር እኔም ትግሌን በድል ደምድሜ ከኢየሱስ ጋር እንድነግስ እርዳኝ። አሜን!!! መልካም ቀን!! @artios_media @artios_media @artios_media
የዘላለም ፍሰሐ 52ኛ ሳምንት 3ኛ ቀን ጌታውም፣ ‘ደግ አድርገሃል፤ አንተ መልካም ታማኝ አገልጋይ፤ በትንሽ ነገር ላይ ታማኝ ስለ ሆንህ በብዙ ነገር ላይ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ’ አለው። ማቴ 25:21 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጀመሪያው መምጣትና በዳግም መመለሱ መካከል ባሉት የምህረትና የፀጋ ዘመናት ውስጥ ቤተክርስቲያን የተሰጣትን አደራ እንዴት መወጣት እንዳለባት በምሳሌ ያስረዳበት ክፍል ነው። ቤተክርስቲያን ግልጽ የሆነ ተልዕኮ ተሰቷታል። የተቀበለችው ኃላፊነትና መክሊት ስላለ ከተጠያቂነት ውጪ ልትሆን አትችልም። እኔ ተመልሸ እስከመጣ ድረስ እየሰራሽ ጠብቂኝ የተባለችው ሥራ አለ። ይህንንም አደራ ብድር ተቀብለው በንግድ ሥራ ላይ ከተሰማሩት ነጋዴዎች ጋር በማመሳሰል ይገልጸዋል። የተወሰኑት ነጋዴዎች በተበደሩት ገንዘብ በሚገባ ነግደው ከነወለዱ ለጌታቸው ሲመልሱ አንዱ ግን የተቀበለውን መክሊት በመቅበር ተጠያቂ ላለ መሆን ጠያቂውን በመካድ ምክንያት ደረደረ። በዚህ ጊዜ ሃኬተኛና ሰነፍ የሆነውን ባሪያ ዘላለማዊ ቅጣት ወደሚቀበልበት ቦታ ተጣለ። ታማኞች ለነበሩት አገልጋዮች ግን ጌታቸው በሰሩት ሥራ ስለ ተደሰተ ተጨማሪ ኃላፊነት ሰጣቸው። ከምንም በላይ የተሰጣቸው ሽልማት ወደ ደስታ መግባትን ነው። ደስታው የጌታ ደስታ ብሎታል። የጌታ ደስታ ዘላለማዊ ደስታ ነው። በሁኔታ የማይገደብ፣ ዘመን የማይሽረው፣ ከሌሎች ታማኝ አገልጋዮች ጋር የምንጋራው ነው። ጊዜያዊ አደራቸውን በሚገባ የተወጡና የተሰጣቸውን ማንኛውንም መክሊት በአግባቡ የነገዱበት ታማኝ አገልጋዮች ያለ ገደብ ወደሚዋኙበት ዘላለማዊ ደስታ ውስጥ ይገባሉ። ስለዚህ ዛሬ አገልግሎታችንን ለመፈጸም በብዙ የምንደክም፣ እግዚአብሔር የሰጠንን አደራ ለመወጣት የምንታገል ደስ ይበላችሁ! የእረኞች አለቃ በቅርቡ ተገልጦ እንባችንን ያብሳል። ወደ ጌታችን ደስታ ገብተን ለዘላለም እንደ እምቦሳ እየፈነደቅን እንኖራለን። አሜን! ዛሬ የማሰላስለው እውነት በመክሊታቸው ታምነው ለነገዱት ዘላለማዊ ደስታ ተጠብቆላቸዋል። የዛሬው ፀሎት እግዚአብሔር ሆይ የዛሬውን መከራ ሳይሆን ዘላለማዊውን ደስታ እያየው በርትቼ በመክሊቴ እንድነግድ እርዳኝ። አሜን!!! መልካም ቀን!! @artios_media @artios_media @artios_media
የዘላለም ፍሰሐ 52ኛ ሳምንት 2ኛ ቀን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም፤ በእኔም የሚያምን ፈጽሞ አይጠማም።”ዮሐ 6:35 ዓለም በሕይወት እጦት ረሃብ ውስጥ ገብታለች። የሚያረካት የነፍስ ውሃ ተሟጦባት በጊዜያዊ ማስታገሻ ታክታለች። የሰው ልጅ የዘላለም ሕይወት ተስፋ ሰንቆ ሳይሆን ስለ ተወለደ ብቻ ለመኖር በመታተር ላይ ነው። በዚያ የጭለማ ዘመን ውስጥ ነው ኢየሱስ የዓለም ብርሃን የሕይወት ተስፋ ሆኖ የመጣው። የዘላለም ሕይወት ጉዞ ጅማሬው የሕይወት እንጀራ ሆኖ የመጣውን እርሱን በማመን ብቻ እንደሆነ አስረግጦ ነገራቸው። ይህ ውሃ ልክ በክረምት ወቅት ፈሶ በበጋ ጊዜ የሚቋረጥ ሰሞነኛ ምንጭ አይደለም። ወደ እርሱ የሚመጡትን ሁሉ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚያረካ ወራጅ ወንዝ ነው እንጂ። ጌታ ኢየሱስ የሚሰጠው እርካታ በሞት የሚገታ አይደለም። የትኛው ምድራዊ ሲሳይ የሚጠቅሙን እስከ ሞት ነው። ከመቃብር በኋላ አብሮን የሚዘልቀው ዘላለማዊ ፍሳሃ ጌታ ኢየሱስ የሚሰጠን ሕይወት ብቻ ነው። የሆነ ወቅት ላይ ሃሳቡን ቀይሮ ይተወኛል ተብሎ የማይሰጋበት አስተማማኝ ሕይወት ነው የተሰጠን። ጠርተነው ሳይሆን እራሱ በፍቅር ፈልጎን ስለሆነ የመጣው ሃሳቡን ቀይሮ ይተወናል ብለን የማንሰጋበት ነው። የዘላለም እንጀራና የሚያረካ የሕይወት ምንጭ በመሆን ለተገለጠው ጌታችንና መድኀኒታችንን ኢየሱስ ክርስትስ ክብርና ምስጋና ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁንለት። ዛሬ የማሰላስለው እውነት ኢየሱስ የዘላለም ፍሰሃችን ብቸኛው ምክንያት ነው። የዛሬው ፀሎት ጌታ ኢየሱስ ሆይ ዳግም ላልራብ የሕይወት እንጀራ ሆነህ ደግሞም እንዳልጠማ የሕይወት ውሃ ሆነህ ስለጠራኸኝ አመሰግንሃለሁ። አሜን!!! መልካም ቀን!! @artios_media @artios_media @artios_media
የዘላለም ፍሰሐ 52ኛ ሳምንት 1ኛ ቀን ❝እንባን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት ወይም ሐዘን ወይም ልቅሶ ወይም ሥቃይ አይኖርም፤ የቀድሞው ሥርዐት ዐልፎአልና።❞ - ራእይ 21: 4 እግዚአብሔር ምድራችንን ሲፈጥራት መልካም ነበረች። በኃጢአት እስከ ተበከለችበት ጊዜ ድረስም እጅግ ዉብና ምቹ ነበረች። ነገር ግን እንደዚያው አልዘለቀችም። በሰማይ ችግር ፈጥሮ የተወረወረው ዲያብሎስ ምድራችንንም ማወኩን ተያያዘው። ባደረገውም የማሳት ዘመቻ ኃጢአት፣ መርገም፣ እንባ፣ ሞት የሚባሉ አስከፊ ዘሮችን በመልካሚቷ መሬት ላይ በመዝራት በብዙ እጥፍ እንዲበቅሉና እንዲሰራፉ አደረገ። እግዚአብሔር በዚህ ምድር ላይ የወጠነው እቅድ በሰው አለመታዘዝ ሲዛነፍ ወደ ሁለተኛው እቅድ በማለፍ አዲስ ሰማይና ምድር የማዘጋጀቱን ዓላማ ይፋ አደረገ። ❝ከዚህ በኋላ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር አየሁ፤ የመጀመሪያው ሰማይና የመጀመሪያዪቱ ምድር ዐልፈዋልና፤ ባሕርም ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።❞ - ራእይ 21: 1 ምድር በክፋቷ እየፀናች በመሄዷ የደም አውድማ እሆነች መጣች። የመጨረሻ የክፋቷ ጥግ የታየው የፈጠራትንና ሊያድናት የመጣውን ጌታ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ የተገደለባት ዕለት ነበር። ይህ ከእግዚአብሔር እቅድ ውጪ ሆና በራሷ ክፋት እየጋለበች ለመኖር መወሰኗን የሚያመለክት ነው። ምድር እስከማትጠገን ድረስ ስለ ተበላሸች እግዚአብሔር አዲስ መኖሪያ ሊሰራልን ወሰነ። ይህችም ኃጢአትና መከራ የሌለባት ፍጹም ደስታ፣ ሰላም፣ አምልኮ፣ እርካታ የሰፈነባት ውብ ሀገር ነች። ጆሴፍ ካምቤነሎ የተባለ ሰው "በምድር የመጨረሻ ትንፋሼን እንደ ጨረስኩ በሰማይ ኑሮዬን እጀምራለሁ ብሎ ለሚያምን ለእርሱ ሕይወት ማብቂያ የለውም።" ብሎ እንደ ተናገራው፤ በክርስቶስ የምናምን ሁላችንም "የሥጋ ሞት" በሚባል ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት ወደዚያችው ውብ አገር እንገባለን። ወገኖቼ! እግዚአብሔር አባታችን ወደ አዲስቱ ኢየሩሳሌም እንደሚወስደን በእርሱ ላመነው ልጆቹ አስተማማኝ ተስፋ ሰጥቶናል። የተስፋው መያዣ ይሆን ዘንድ መንፈሱን በውስጣችን አፈሰሰው። በዚህም ለዘላለም ፍሰሃ መታጨታችንን እርግጠኞች ሆነናል። ክብር ሁሉ ለመረጠን፣ ላዳነን፣ ላፀናን፣ በፀጋው ለሚያበረታን፣ እስከ መጨረሻው ስለሚረዳን ይሁን!!! ዛሬ የማሰላስለው እውነት ከሞት በኋላ ከሚወደኝ ጌታ ጋር የዘላለም ፍስሃ በሞላበት ለመኖር የታጨሁ ሰው ነኝ!! የዛሬው ፀሎት አባቴ ሆይ! በመከራ የተሞላውን ምድራዊ ጉዙ ስጨርስ ዘላለሜን ካንተ ጋር በደስታ እንደምኖር አስተማማኝ ተስፋን ስለ ሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ። በዚህ ተስፋ ፀንቼ እንድቆም እንዲሁም ሃሳቤን በሰማያዊው ጉዳይ ላይ እንዳደርግ እርዳኝ። አሜን!! መልካም ቀን!! @artios_media @artios_media @artios_media
ለንጥቀት መዘጋጀት 51ኛ ሳምንት 7ኛ ቀን ዘመኑ ቀርቧል፤ እንግዲህ ይህን የትንቢት ቃል የሚያነብብ ብፁዕ ነው፤ የሚሰሙትና የተጻፈውንም የሚጠብቁ ብፁዓን ናቸው። ራእ 1፥3 ሐዋርያው ዮሐንስ በፊጥሞ ደሴት ላይ ስለ ክርስቶስ ወንጌል መከራን እየተቀበለ ስለ ዓለም ፍጻሜና የታሪክ መቋጫ የሆነውን ታላቅ ራዕይ አየ። የመጽሐፍ ቅዱስ መደምደሚያ የሆነውን የራዕይን መጽሐፍ ሊቀበል ሰማያት ተከፍተው በአስጎብኚ መልአክ አማካኝነት የነገሮች ፍጻሜን በመመልከት ላይ ነው። ዓለማችን በኃጢአት ምክንያት ከወደቀችበት የመርገም ማጥ ውስጥ ወጥታ እፎይ ልትል። ለሰው ልጅ የውድቀት ምክንያት የሆነው ዲያብሎስ የመጨረሻ ፍርዱን ተቀብሎ በእሳት ባህር ውስጥ ሊጣል ዘመኑ ቀርቧል። ሁሉ ነገር በአዲስ ስርዐት ሊተካ ነው። ዘመኑ ቀርቧል የሚለው ንግግር የክርስቶስ ዳግም ምጻትና የመጨረሻው ዘመን ክስትቶች በፍጥነት ሊፈጸሙ መሆኑን የሚያመለክት ነው። ትንቢቱን የማንበብና የመፈጸም እድል የሚያገኙት አማኞች በእርግጥም የታደሉ ናቸው። ምክንያቱም የሚያደርጉትን በሙሉ ከእግዚአብሔርን ዕቅድ አንጻር የመስራት ዕድል ስለሚኖራቸው። የእግዚአብሔር የትድግና ፕሮግራም መደምደሚያው የክርስቶስ ዳግም ምጻት ነው። ቤተክርስቲያን በትልቅ ጉጉት የምትናፍቀው የመጨረሻው የእፎይታ ሰዓት በንጥቀት ከዚያ ምድር ላይ ተወስዳ ንጉሷን ኢየሱስን በአየር ላይ ለመቀበል የምትሄድበትን ጊዜ ነው። ወንድሞቼና እህቶቼ! የክርስቶስ ዳግም ምጻት በጣም ቅርብ ነው። የመጨረሻው መለከት ሊነፋ ተቃርቧል። ስለዚህ እንንቃ!! ቤተክርስቲያን ለሁለት ሺህ አመታት መብራቷን አብርታ ስትጠብቀው የኖረችው አዳኟ ኢየሱስ በቅርቡ ይመጣል። ስለዚህ ይህንን ታላቅ የደስታ ቀን በንቃትና በጉጉት እንድንጠብቅ መንፈስ ቅዱስ ያንቃን!! ዛሬ የማሰላስለው እውነት ንጥቀት በእኔ ዘመን ሊሆን ይችላል ብሎ ማሰብ ብልህነት ነው። የዛሬው ፀሎት ጌታ ኢየሱስ ሆይ በምትገለጥበት ቀን በደስታ እንድቀበልህና ለሽልማት በፊትህ እንድቆም እርዳኝ። አሜን!!! መልካም ቀን!! @artios_media @artios_media @artios_media
ለንጥቀት መዘጋጀት 51ኛ ሳምንት 6ኛ ቀን ደግሞም የእግዚአብሔርን ቀን እየተጠባበቃችሁ መምጫውን ልታፋጥኑ ይገባል። በዚያን ቀን ሰማያት በእሳት ተቃጥለው ይጠፋሉ፤ የሰማይም ፍጥረት በታላቅ ትኵሳት ይቀልጣል። 2ጴጥ 3፥12 የሐዋርያው ጴጥሮስ መልዕክት ተደራሲያን እግዚአብሔር የተስፋ ቃሉን መፈጸም የማይችል አይነት አድርገው በሚዘብቱበት ማህበረሰብ ውስጥ ነው ያሉት። በተለይ የክርስቶስ ዳግም ምጻት ጉዳይ ሲነሣ የት አለ ያላችሁት በማለት ያሾፉባቸው ነበር። እነርሱም፣ ‘እመጣለሁ’ ያለው ታዲያ የት አለ? አባቶች ከሞቱበት ከፍጥረት መጀመሪያ አንሥቶ እስካሁን ድረስ ሁሉም ነገር እንዳለ ይኖራል' በማለት ያላግጣሉ። ሆኖም ግን ከክርስቶስ ዳግም ምጻት በኋላ ሌላ ተጨማሪ እድል ስለማይኖር ማንም እንዳይጠፋ ፈልጎ፣ ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃ እየታገሰ መሆኑን አያስተውሉም። እኛ ግን የክርስቶስ መምጣትና ንጥቀት በፍጥነት እንዲሆን ከፈለግን ወንጌልን እየሰበክን ብዙዎችን ወደ ንሳሃ በማምጣት መምጫውን ማፋጠን ይኖርብናል። በተጨማሪም የዕለት ተዕለት ተግባራችን ትርጉም ያለውና ዉጤታማ እንዲሆን ለክርስቶስ ዳግም ምጻት የተዘጋጀ የሕይወት ምልልስ ሊኖረን ይገባል። ሐዋርያው ጴጥሮስ በዘመኑ ሲያገለግላቸው ለነበረው ቅዱሳን ለክርስቶስ ዳግም መመለስ እንዴት መዘጋጀት እንዳለባቸው ሁለት ዋና ዋና ምክሮችን ይሰጣቸዋል። ይህም፦ በቅድስናና በእውነተኛ መንፈሳዊነት በመኖር ነው። ❝እንግዲህ ሁሉም ነገር በዚህ ሁኔታ የሚጠፋ ከሆነ፣ እናንተ እንዴት ዐይነት ሰዎች ልትሆኑ ይገባችኋል? አዎን፣ በቅድስናና በእውነተኛ መንፈሳዊነት ልትኖሩ ይገባችኋል፤❞ - 2ጴጥ 3:11 የክርስቶስን መገለጥ የሚያስብ አእምሮ ኃጢአትን ለማድረግ እቅድ የሚነድፍበት ጊዜ የለውም። ማራናታዊ የሆነ ሰው ግብዝነት በእርሱ ላይ አይሰለጥንም እውነተኛ እንደሆነ ይፀናል እንጂ። ከአለም ጋር ለመሰንበት ቆርጦ የተነሣ ሰው እንኳንስ መምጫውን ማፋጠን ይቅርና ቢቻለው የክርስቶስን መምጫ የሚያዘገይበትን መንገድ ነው የሚፈልገው። እኛ ግን እዳችንን ኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ለፊት በማየት የምንጓጓ ቅዱሳን በሙሉ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ላልዳኑት እየሰበክን የዳኑትን እያዘጋጀን እንድንቆይ ጌታ ይርዳን። ዛሬ የማሰላስለው እውነት ያለንበት ዘመን ኢየሱስ ከመምጣት የዘገየበት ጊዜ ሳይሆን ብዙዎች በንሰሐ እንዲመለሱ የተሰጠ የምህረት ዘመን ነው። የዛሬው ፀሎት እግዚአብሔር ሆይ የተከፈተው የምህረት በር ከመዘጋቱ በፊት ቶሎ ቶሎ ብዬ ወንጌልን እንድመሰክር አንቃኝ። አሜን!!! መልካም ቀን!! @artios_media @artios_media @artios_media