- Последний пост
- 09:44
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 4
- Всего постов
- 34
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Instagram (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 155
- 1/48двое суток
- 177
- 1/72трое суток
- 191
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ተከፋይ ሙያ ባለቤት ለመሆን ዝግጁ ናችሁ? ላሊ ፊልም ስኩል (Lali Film School) በዘመናዊ የፊልም እና የዲጂታል አርትስ ሙያዎች አጠቃላይ የተግባር ስልጠና ለመስጠት ምዝገባ ጀምሯል። የሚሰጡ የትምህርት ዘርፎች 🎥 1. ቪዲዮግራፊ (Videography) 📷 2. ፎቶግራፊ (Photography) 🎬 3. ቪዲዮ ኤዲቲንግ (Video Editing) 🖼 4. ፎቶ ኤዲቲንግ (Photo Editing) 🎨 5. ግራፊክ ዲዛይን (Graphic Design) 📈 6. ዲጂታል ማርኬቲንግ (Digital Marketing) 📱 7. ኮንቴንት ክሬሽን (Content Creation) የቦታዎች ብዛት ውስን ስለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ! 📞 ስልክ፡ 0933606469 / 0996242250 የTelegram page QR ኮዱን ስካን በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ! https://t.me/lalifilmschool #LaliFilmSchool#Hawassa#LaliDigitas
ኑኃሚን ከቤተልሔም መውጣት ለቤተሰቧ የተሻለ ምርጫ እንደሆነ አስባ ወደ ሞዓብ ሄደች ነገር ግን ከዚያ በኋላ ብዙ ሀዘንና ህመም አጋጠማት፤ ባሏንና ልጆቿንም አጣች። በመጨረሻም ወደ ቤተልሔም ለመመለስ ወሰነች። ስትመለስም ሰዎች፣ “እግዚአብሔር ሕዝቡን ጎበኘ” ብለው ሰምታለች፤ እርሷም በሀዘን ብትመለስም፣ እግዚአብሔር ታሪኳን እንዳላቋረጠ በኋላ ተመለከተች። የኑኃሚን ታሪክ ከእግዚአብሔር ዕቅድ ጋር መቆየትና ወደ እርሱ መመለስ ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ያሳየናል። አንዳንድ ጊዜ የራሳችን መንገድ የተሻለ ይመስለናል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ያዘጋጀው መንገድ ከእኛ እይታ በላይ የሆነ ዓላማ አለው። ኑኃሚን እና ሩት በቤተልሔም ከተመለሱ በኋላ፣ እግዚአብሔር ከሀዘናቸው መካከል አዲስ ታሪክ ጀመረላቸው። ስለዚህ ከእግዚአብሔር ዕቅድ አትራቁ፤ መንገዱ ቢከብድም እሱን እንመነው። ዛሬ የምናየውው ሀዘን የነገው የእግዚአብሔር በረከት መጀመሪያ ሊሆን ይችላል።
ኑሃሚን 📌በመጽሐፈ ሩት ምዕራፍ 1 ላይ እንደምናየው ኑኃሚንና ቤተሰቧ በቤተልሔም ይሁዳ የእግዚአብሔር ኪዳን እና መገኘት በነበረበት ስፍራ ይኖሩ ነበር። 👉 ነገር ግን በምድሪቱ ላይ ታላቅ ራብና ፈተና በደረሰ ጊዜ መፍትሔውን ከእግዚአብሔር በመጠበቅ ፈንታ ችግሩን በራሳቸው መንገድ ለመፍታት ወስነው ወደ ባዕድ አገር ወደ ሞአብ ኮበለሉ ይህ ከእግዚአብሔር ስፍራ የመውጣት ውሳኔ ለጊዜው መሸሸጊያ ቢመስልም በባዕድ ምድር ያጋጠማት ግን ታላቅ ባዶነት ነበር ኑኃሚን በዚያ ባሏን ሁለቱን ልጆቿን በሞት በማጣት (ሩት 1:21) በሙላት ወጣሁ፤ እግዚአብሔርም ወደ ቤቴ ባዶዬን መለሰኝ ብላ እስክትል ድረስ መሪር ሐዘን እንደገጠማት እንመለከታለን ። 📌ሆኖም እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደ ጎበኘ በሰማች ጊዜ የእግዚአብሔር መገኘትና ፈቃድ ወደ ሚገኝበት ቦታ ቤተልሔም ተመለሰች እግዚአብሔርም በዚህ ስፍራ ባዶነቷን በምራቷ በሩት በኩል ሲሞላ እንዲህ ሆነ 👉የዳዊትና የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ ግንድ የሚሆን ተስፋን አገኘች! የት? ስንል🤔 የእግዚአብሔር መገኘት ባለበት ስፍራ ስትገኝ እንደሆነ እንመለከታለን 👉ታዲያ ከዚህ እኛ ምን ልንማር ይገባናል? እያንዳንዳችን በሕይወታችን ምንም ያህል ታላቅ ፈተና ቢገጥመን በፈተናው ውስጥ እግዚአብሔር ባስቀመጠን ረድኤቱ በሚገኝበት ስፍራ ላይ ጸንቶ መቆምን ነው! 👉ምክንያቱም ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጪ የሚገኝ ሙላት የለም ወደ ህልውናው ስንመለስ ግን አምላክ ያጣነውን ሁሉ የመተካትና የማደስ ኃይል አለው ነገር ግን አስቀድመን በማንኛውም ሁኔታ ስፍራችንን ልጠብቅ ጸንተንም በመቆም መታገስ እንጂ እግዚአብሔር በማይገኝበት ስፍራ ልንገኝ አይገባም:: @revealjesus
ወንጌልና የዘመኑ ክፍተቶች 👉በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ወንጌል ማለት፣ እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት፣ ሞት፣ ትንሣኤ እና ክቡር መንግሥቱ አማካኝነት ለሰው ልጆች ያደረገውን የማዳን ሥራ የሚያበስር መልእክት ነው። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ፲፭:፫-፬ ---------------------------------------------- ፫፤ እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ፦ መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ ፬፤ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥ 👉ወንጌል ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ መሆኑን፣ የእግዚአብሔር መንግሥት መቅረቡን፣ ሰዎች ንስሐ ገብተው በእርሱ እንዲያምኑ፣ ደቀ መዛሙርት ሆነው አዲስ ሕይወት እንዲኖሩ የሚጠራ የእግዚአብሔር መልእክት ነው። 👉ስለዚህ ወንጌል ማለት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት የመጣው የድነት፣ የእርቅ፣ የተስፋ እና የእግዚአብሔር መንግሥት የምሥራች ነው። 👉በዚህ ዘመን ያሉ ክፍተቶችን ስናይ ከሁሉ የሚበልጠው ክፍተት የወንጌልን የመመስከር ቴክኒክ ማጣት አይደለም። ዋነኛው ክፍተት ወንጌልን በማወቅና በሕይወት በመኖር መካከል ያለው፣ ወንጌልን በማመንና ስለ እርሱ መሥዋዕት ለመሆን ፈቃደኛ በመሆን መካከል ያለው፣ እንዲሁም ድነትን በመረዳትና የእግዚአብሔርን መንግሥት ተልዕኮ በመቀበል መካከል ያለው ክፍተት ነው። 📌ዛሬ በዋነኝነት እንደ ክፍተት የሚታዩት ትንሽ እንጥቀስና በሚቀጥሉት ቀናቶች ደግሞ የቀሩትን እንመለከታለን። 👉 የተሳሳተ አመለካከት ወንጌል የድነት መልእክት ብቻ ሳይሆን፣ የእግዚአብሔር መንግሥት መልእክት፣ የሕይወት ለውጥ ጥሪ እና የደቀ መዝሙርነት ጥሪ ነው። ስለዚህ በምድር ላይ የመቆየታችን ዋና ተልዕኮ መሆኑን መረዳት አለብን። ትክክለኛውን ወንጌልና የክርስቶስ ሞት የተረዳ ክርስቲያን አጠገቡ ያለው ወንድሙ መጥፋት የሚያሳዝነውና ግድ እንዲለው የሚያደርግ ነው።አሁን ላይ አብዛኞቻችን ትኩረት የምንሰጠው ለራሳችን መንፈሳዊ ዕድገት በቤተክርስቲያን ውስጥ ስላለን ቆይታ ነው ይህ በጣም ጥሩ ነገር ቢሆንም በዚሁ ልክ ስለሌሎችም በጨለማ ስላሉት ልናስብላቸው ያስፈልጋል። እኛ ከእግዚአብሄር ጋር ስላለን ህብረት እንደምንጨነቅ ሌሎች እንዲኖራቸው ደግሞ ልንፀልይላቸው ና ወንጌልን ልንነግራቸው ያስፈልጋል። 👉ምቾትና ቁሳዊ አስተሳሰብ (Materialism) 📌በዘመናችን ወንጌልን ለመመስከር ካሉት ትልልቅ ክፍተቶች አንዱ ምቾትንና ቁሳዊ ነገሮችን ከክርስቶስ ተልዕኮ በላይ ማስቀደም ነው። ብዙ ክርስቲያኖች የሕይወታቸው ዋና ግብ ምቹ ኑሮ፣ የገንዘብ ብዛት፣ የሥራ ስኬት፣ የማኅበራዊ ክብር ወይም የግል ደህንነት እንዲሆን ይፈልጋሉ። እነዚህ ነገሮች በራሳቸው ኃጢአት ባይሆኑም፣ የክርስቶስን ጥሪ ሲተኩ መንፈሳዊ አደጋ ይሆናሉ። 📌የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ለወንጌል ሲል ሀብትን፣ ምቾትን፣ ነፃነትን እንኳን ለመተው ዝግጁ ነበረች። ሐዋርያት መከራን፣ እስራትን፣ ረሃብን እና ሞትን ቢገጥማቸውም ወንጌልን አልተዉም። ለእነርሱ የክርስቶስ መንግሥት ከዓለማዊ ምቾት እጅግ የላቀ ዋጋ ነበረው። ዛሬ ግን በአንዳንድ ጊዜ ወንጌልን በመመስከር ምክንያት ሥራችንን፣ ዝናችንን ወይም ምቾታችንን እንዳናጣ እንፈራለን። ይህ ፍርሃት በጸጥታ እንድንኖር እንጂ ስለ ክርስቶስ በድፍረት እንዳንናገር ያደርገናል። መፅሀፍም እንዲህ ይለናል፦ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ፩:፳፯ --------------------------------------- ፳፯፤ ይሁን እንጂ፥ መጥቼ ባያችሁ ወይም ብርቅ፥ በአንድ ልብ ስለ ወንጌል ሃይማኖት አብራችሁ እየተጋደላችሁ፥ በአንድ መንፈስ እንድትቆሙ ስለ ኑሮአችሁ እሰማ ዘንድ፥ ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ። ወንጌል ከማንኛውም ቁሳዊ ሀብት፣ ስኬት ወይም ምቾት የበለጠ ዋጋ እንዳለው በሕይወታችን ልናሳይ ይገባል። ተባረኩ🙌
🕯የሕይወታችን ሦስቱ ምሰሶዎች፡ ብርታት፣ ዝማሬና መዳን 📖“ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም ሆኖአል።” ኢሳይያስ 12፥2 (አዲሱ መ.ት) ✍️ነቢዩ ኢሳይያስ ይህንን ድንቅ የድል አዋጅ የተናገረው፣ እግዚአብሔር ሕዝቡን ከከባድ መከራና ፍርድ ካወጣቸው በኋላ፣ የሰጣቸውን የተስፋና የመጽናናት ዘመን ሲያበስር ነው። በሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ፣ ጉልበታችን ሲዝል፣ ደስታችን ሲጠፋና አደጋ ሲያንዣብብብን የምንደገፍበት ጽኑ መሠረት ያስፈልገናል። ይህ አጭር ነገር ግን እጅግ ጥልቅ የሆነ ጥቅስ እግዚአብሔር በአማኙ ሕይወት ውስጥ የሚጫወተውን ሦስት ወሳኝ ሚናዎች (ብርታት፣ ዝማሬና መዳን) በማጣመር ፍጹም የሆነ የሕይወት ዋስትና ይሰጠናል። ይህ የግል ምስክርነት በእግዚአብሔር ማንነት ላይ የተመሠረቱ ሁለት ዓበይት እውነቶችን ይገልጣል፡- 1. የዕለታዊ ኑሮአችን ሞተር፡ "ብርታቴና ዝማሬዬ ነው" ይህ ለድካማችንና ለኀዘናችን የተሰጠ መፍትሔ ነው። ➺ብርታት (ኃይል)፦ ነቢዩ "እግዚአብሔር ብርታት ይሰጠኛል" አላለም፤ "እርሱ ራሱ ብርታቴ ነው" አለ እንጂ። የሰው ልጅ የራሱ ጉልበት ውስን ነው፤ ቶሎ ያልቃል፣ ይደክማል። እግዚአብሔር ግን ብርታታችን ሲሆን፣ እኛ ስንደክም እርሱ ይሸከመናል፤ እኛ አቅም ስናጣ የእርሱ ኃይል በውስጣችን ይሠራል ማለት ነው። የሚያጋጥመን ፈተና ከእኛ አቅም በላይ ሊሆን ይችላል፤ ከብርታታችን (ከእግዚአብሔር) ግን አይበልጥም። ➺ዝማሬ (ደስታ)፦ ዝማሬ የውስጣዊ ደስታ፣ የሰላምና የድል መግለጫ ነው። ኑሮ ሲከብድ፣ ችግር ሲበዛ የሰዎች "ዝማሬ" (ደስታ) ይጠፋና በለቅሶና በማጉረምረም ይተካል። ነገር ግን እግዚአብሔር ራሱ ዝማሬያችን ከሆነ፣ በኀዘንና በጨለማ መካከል ሆነንም ልባችን በምስጋና ይሞላል። እርሱ ሁኔታዎች በማይቀይሩት ደስታ አፋችንን ይሞላዋል። 2. የመጨረሻው ዋስትናችን፡ "ድነቴም ሆኖአል" ይህ ከፍርሃትና ከአደጋ ነጻ መውጣታችንን የሚያረጋግጥ ነው። ➺ሁለንተናዊ መዳን፦ መዳን ሲባል ከዘላለም ሞት (ከሲኦል) መዳን ብቻ አይደለም። በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ከሚያጋጥሙን ጠላቶች፣ ከበሽታ፣ ከጭንቀት፣ ከገንዘብ ቀውስና ከስህተት መንገድ የሚያድነን እርሱ ነው። እርሱ "ድነቴ" (My Salvation) ከሆነ፣ የትኛውም ዓይነት አደጋ የመጨረሻውን ቃል ሊናገርብኝ አይችልም ማለት ነው። ➺የግል ባለቤትነት፦ በዚህ ጥቅስ ውስጥ "የእኔ" የሚለው ባለቤትነት ጎልቶ ይታያል። እግዚአብሔር የዓለማት ፈጣሪ ቢሆንም ለእኛ ግን የቅርብ፣ የግል አዳኛችን ነው። ይህንን አዋጅ የሚያውጅ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ጥልቅና ግላዊ የሆነ ግንኙነት ያለው ሰው ነው። 📢የዕለቱ መልእክት ዛሬ የሕይወትህ ብርታት ማነው? በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ስታልፍ፣ የምትደገፈው በባንክ ሂሳብህ፣ በሰዎች፣ ወይስ በራስህ እውቀት ላይ ነው? የውስጥህን ሰላም አጥተህ "ዝማሬህ" ጠፍቶብህ ይሆን? ወይስ አደጋና ፍርሃት ከቦህ "ማን ያድነኛል?" እያልክ እየተጨነቅህ ነው? ይህ ቃል ዛሬ እኛን ያስተምረናል፦ ከእግዚአብሔር ውጪ ያለ ማንም ሆነ ምንም ነገር የውሸት ብርታት ነው። እውነተኛ ጥንካሬ፣ እውነተኛ ደስታና አስተማማኝ መዳን የሚገኘው ጌታን የሕይወትህ ሁሉ-በ-ሁሉ ስታደርገው ብቻ ነው። ስለዚህ ዛሬ በድካምህ ላይ ተደገፍበት (ብርታትህ ነውና)፤ በኀዘንህ ጊዜ አመስግነው (ዝማሬህ ነውና)፤ በፍርሃትህ ጊዜ ተማመንበት (ድነትህ ነውና)። 🙏የዕለቱ ጸሎት የሕይወቴ መሠረት የሆንክ ጌታ አምላኬ ሆይ አንተ ብርታቴ፣ ዝማሬዬና ድነቴ ስለሆንክ እጅግ አድርጌ አመሰግንሃለሁ። በገዛ ጉልበቴ መቆም በማልችልበት ጊዜ አንተ ኃይል ሁነኝ። የዓለም ችግርና ኀዘን ሲከብደኝ የውስጤን ደስታ መልሰህ አንተ ራሱ ዝማሬ ሁንልኝ። ከሚያስፈራኝና ከሚያስጨንቀኝ ነገር ሁሉ የምታድነኝ አንተ ብቻ ነህና፣ ሕይወቴን በፊትህ አደራ እሰጣለሁ። በጌታ በኢየሱስ ስም አሜን። #ጌታ_ኢየሱስ_ይመጣል!!! “ቃሉን ስበክ፤ ጊዜው ቢመችም ባይመችም ዝግጁ ሁን፤ በታላቅ ትዕግሥትና በማስተማር አቅና፤ ገሥጽ፤ አበረታታም።” — 2ኛ ጢሞቴዎስ 4፥2 @revealjesus
без подписи
🌟በህይወታችሁ ከባድ የሚባልን ህይወት እያለፋችሁ ነው? ✨ በዝህ የህይወት መስመር እየተሰራችሁ መሆኑን መገንዘብ እጅግ አስፈላጊ ነው በተለይም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የምናልፋቸዉ ከባባድ የምመስሉ ግዜያት በከባዱ የምንሰራበት መሆኑን ማወቅ ይገባናል ለምንፈልገው ትልቅነት ላቀድነዉ አሸናፊነት ለምንደርስበት ነገነት እነዛ ከባድ የብቸኝነት ዘመነናችን ወሳኝ ናቸው ። 🙌ለምን ይመስላችኋል ዮሴፍ ; ጠቅላይ ገዥ እንድሆን ታስቦ በወንድሞቹ ከመሸጥ እስከ እስር ቤት መጣል ምንም ባላጠፍዉ በከባድ ህይወት የምያልፈዉ 🙌 ለምን ይመስላችኋል ? ሙሴ ; እስራኤልን ከግብፅ እንድያወጣ ና እንድመራ የንጉሥ የልጅ ልጅ ከምባልበት ወርዶ ለ40 አመት እርኛ ሆኖ በምድርበዳና በሰዉ ቤት ዋጋን የምከፍለው 🙌 እሽ የነሱ ይሁን ለምን ይመስላችኋል ኢየሱስ ; የአለምን ሀጥያት እንድስወግድ ለዓለም ቤዛ ልሆን ወደ ምድር መቶ እንደ ሰው ከሀጢአት በቀር በነገር ሁሉ እስከ መስቀል ሞት የተፈተነው “ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም።” — ዕብራውያን 4፥15 👉የመጀመሪያው በየትኛውም ፈተና ዉስጥ ብትሆኑ ልክ እናንተ ያለፋችሁት ያለፈና የሚረዳ ሊቀ ካህናት የሆነ ንጉስ እንድሁም አባት በሰማይ አላችሁ በርሱ ተጽናኑ 👉ሁለተኛው ደግሞ ፈተና የሚበዛበት ሰዉ ካለ የሚሰራዉ ትልቅ ስራ ያለበት ሰዉ ነዉ የሆነ ከባድ ሚባል ነገር ዉስጥ እያለፍችሁ ያላችሁ ሰዎች ራእይ እዳለባችሁ ምልክት እያሳያችሁ መሆኑን ተርዱ ሌላው እናንተ ስትጨርሱ እርሱ ስለሚጀምር እስቲ ለሱ ተዉለት እርሱ ይስራበት እግዚአብሔርን በመጠበቅ ውስጥ በረከት ብቻ ሳይሆን ራሱ እግዚአብሔርም ይኖራል፡፡ ጌታን ቀድመን ከተጓዝን የምንጓዘው ብቻችንን መሆኑን ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ ( እናንተ ፈቃድ ካላችሁ እርሱ የምትቀጥሉበት ጸጋ አለው )
"ቤተ ክርስቲያን ቴአትር ቤት፣ እኛም ኮሜዲያን ሆነናል!" ብዙ አማኝ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጣው ለመዝናናት ነው። ሌላውም ሰው ጆክ ሲያምረው፣ መሳቅ ሲፈልግ የእኛን ቪዲዮዎች ነው የሚያየው። በኢየሱስ ስም፣ በልሳን፣ በጸሎት ከት ከት ብሎ ይስቃል። እኛም አብረን እንስቃለን። ምንም ስለማይመስለን ቪዲዮውን እየተቀባበልን እንስቃለን። የእግዚአብሔር ስም መቀለጃ ስለሆነ የሚያየው አይፈራው፣ የሚሰማን አይፈራው። እኛም አላከበድነው በሚገባ አላሳየነው፣ አልገለጥነው፣ አላመጣነው...። የአብዛኞቻችን አገልጋዮች ዓላማ ራሱ ሰውን ማዝናናት ነው፤ "ምን ብናገር አዝናናዋለሁ ነው።" የብዙ ምዕመናን የቤተ ክርስቲያን፣ የስብከትና የአገልግሎት ምርጫ "የት ብሄድ ያልተካበደ ነገር እሰማለሁ"፣ "መዝናናት አገኛለሁ" የሚል ነው። ቤተ ክርስቲያን ቴአትር ቤት፣ እኛም ኮሜዲያን ሆነናል። ተዉ እንጂ ብዙም ሩቅ ባልሆኑ ዓመታት፣ የዛሬ ሰልሳ ዓመት ወደ ኃላ "ሪዋይንድ" ብታደርጉ አማኞች የሚፈራ ምገስ ነበራቸው። ሰዎቹ ዛሬም በሕይወት ስላሉ ሄዳችሁ ጠይቋቸው። በቤተ ክርስቲያናቸው ደጃፍ ማለፍ እንኳ ያስፈራ ነበር። ሕይወታቸው ግርማ ነበረው። መልዕክታቸው አስደንጋጭ ነበር። ለማስደንገጥ ብለው ሳይሆን እግዚአብሔር በመካከላቸው ነበር። እዚያ ለመቀለድ አትሄድም፤ ንሰሐ እንጂ ጆክ ትዝ አይልህም። አጋንንት ይወጣል፣ ሰዎች ይፈወሳሉ። የእግዚአብሔር ቃል፣ የክርስቶስ ወንጌል ይሰበካል። ይኼ ሁሉ የሚሆነው ፐርፌክት [ፍጹማን] ክርስቲያኖች ስለሆኑ አይደለም። ግን የኢየሱስን ስም አስከባሪዎች ነበሩ። አሁን ቢያንስ ስሙ በሆነ መንገድ ይከበር ዘንድ ብንጸልይስ? ቢያስፈልግ ኮሜዲያኖቹን በጊዜ ቢወስደን፤ ይኼም እኮ አንዱ መንገድ ነው። ወይም ደግሞ ጥግ አስይዞን የሆኑ ሌሎች ሰዎች ቢያመጣ፣ እኛ ዕድሉን አልጠቀም ስላልን ሌላን ትውልድ ቢያስነሳልን፣ ስላላየናቸው እንጂ እግዚአብሔር ስሙን የሚያስከብሩለት ልጆች አሉታ!... በዚህ ዘመን ወንጌል የምንሰብክበት ብዙ መድረክ አግኝተን፣ ሚዲያ ተመቻችቶልን አልተጠቀምንበትም። በየሰዉ ቤት የጌታን ስም ተሸክመን ለመግባት እንደዚህ ዘመን ዕድል ተሰጥቶን ያውቃል እንዴ? እኛ ግን ጆካችንን ይዘን ገባንበት፤ እግዚአብሔርን መሳለቂያ አደረግነው። ስለዚህ ወገኖቼ በአሕዛብ መካከል የተነቀፈው ማንነቱ የቀለለው ስሙ መልሶ እንዲከብድ በየትኛውም መንገድ ምክንያት ለመሆን መጸለይ አለብን። ዶ/ር ማሙሻ ፈንታ @revealjesus
ሃሪየት አትዉድ በጥቅምት 30 ቀን 1786 ዓ.ም በሀቨርሂል፣ ማሳቹሰትስ ተወለደች። በደስተኛ፣ በጣም ቅን እና በጥልቅ አሳቢነቷ የምትታወቅ ወጣት ነበረች። በብሩህ አእምሮዋ እና ለንባብ በነበራት ልዩ ፍቅር የተነሳ ምቹ አስተዳደግን አግኝታ አደገች። ይሁን እንጂ ሕይወቷ ትልቅ መንፈሳዊ ለውጥ ያደረገው ብራድፎርድ አካዳሚ በመማር ላይ ሳለች ነው። በአስራ ሥስት ዓመቷ ጥልቅ የሆነ የንስሐ እና የለውጥ ሕይወትን አሳለፈች፤ ከዚያም ጀምሮ እስከ ዕድሜዋ ማጠናቀቂያ ድረስ የዕለት ተዕለት መንፈሳዊ ውጣ ውረዶቿን የምትመዘግብበት ማስታወሻ መያዝ ጀመረች። በ አስራ አምስት ዓመቷ ሕዝባዊ የሃይማኖት ህብረት አባል በመሆን፣ በዙሪያዋ ያሉትን ሰዎች ያስገረመ የጸሎት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ እና የታታሪነት አርአያ አሳየች። የአካል ጤንነቷ ደካማ ቢሆንም በቤተሰቧ ታሪክ የሳንባ ነቀርሳ በሽታ የተለመደ ነው ሆኖም መንፈሳዊ ጥንካሬዋ ግን ከሥጋዊ ድክመቷ በላይ ነበር። የሚስዮናዊነት አገልግሎት ጥሪ: ሐሪየት ወደ ዓለም አቀፍ የወንጌል ተልዕኮ ዓለም የገባችው በእግዚአብሔር የዘመን ቀጠሮና በሚያስደንቅ የፍቅር ሕይወት ተደባልቆ ነበር። በ1790ዎቹ መባቻ፣ የአሜሪካ የውጭ ሀገር ሚስዮናዊነት እንቅስቃሴ ገና በጨቅላነቱ ላይ የሚገኝ ነበር። ሬቨረንድ ሳሙኤል ኒውል የተባለ ወጣት መለኮታዊ ትምህርት ቤት ተማሪ፤ እንደ አዶኒራም እና አን ጃድሰን ካሉ ቀዳሚ አገልጋዮች ጋር በመሆን ወደ ምስራቅ ያልተደረሱ አካባቢዎች እንደ ሚስዮናዊ ሆኖ ለማገልገል ራሱን ባቀረበ ጊዜ፣ ቁርጠኝነቱን የሚጋራ የትዳር አጋር ይፈልግ ነበር። እሱም ለሐሪየት የትዳር ጥያቄ አቀረበላት፤ ጥያቄውም ብዙዎች ሊያስቡት የማይችሉት ከባድ ውሳኔን የሚጠይቅ ነበር፡- የቤተሰብን፣ የዘመድን እና የባህልን ደህንነት በመተዉ ለአህጉር አቋራጭ አስቸጋሪና እርግጠኛ ባልሆነ ሕይወት ውስጥ መጓዝ የሚጠይቅ ነበር። ሐሪየት ለአፍታም አላመነታችም። በመጽሔቷ ላይ ባሰፈረችው ሐሳብ፣ "የዚህን ሀላፊ ዓለም አንጸባራቂ ከንቱ ውበት ልታስቀጥለው ይገባል ወይስ ለእግዚአብሔር ብለህ ልትተወው ይገባል ስትል እጅግ በሚያስደንቅ ሁኔታ ጠይቃለች"። ከሰማያዊው ጥሪ የተነሣ፣ የካቲት 2 ቀን 1804 ዓ.ም. ከሳሙኤል ጋር ጋብቻን ፈጸመች፤ ከጥቂት ሳምንታት በኋላም የካቲት 12 ቀን 1804 ዓ.ም. ካራቫን የተባለችውን መርከብ በመሳፈር ወደ ሕንድ በመጓዝ የአሜሪካ የመጀመሪያው የባህር ማዶ ሚስዮናዊ ማዕበል አካል ለመሆን በቃች። የአገልግሎት ፈተናዎች እና ፍሬ የሐሪየት ኒውል አገልግሎት የሚታወቀው በረጅም ዓመታት የስብከት ሥራ ወይም ተቋማትን በመገንባት ሳይሆን; በጽናት፣ በስደት እና በከባድ መከራ ነበር። በሰኔ 1804 ዓ.ም ሕንድ ካልኩታ እንደደረሱ፣ በግዛታቸው ውስጥ ክርስቲያናዊ የሚስዮናዊነት ሥራዎችን ይቃወሙ የነበሩት የብሪታንያ ምስራቅ ሕንድ ኩባንያ አሜሪካውያን ወዲያውኑ እንዲለቁ ትዕዛዝ አስተላለፈ። በእርግዝናዋ የመጨረሻ ወራት ላይ ሳለች እንዲሰደዱ በመገደዳቸው ምክንያት፣ ሐሪየት እና ሳሙኤል በሕንድ ውቅያኖስ ውስጥ ወደምትገኘው የሞሪሸስ ደሴት የሚያመራ መርከብ ተሳፈሩ። ጉዞው እጅግ አስፈሪና መራራ ነበር። የነበረው ከባድ የአየር ንብረት፣አጣብቂኝ እና አስጨናቂ ሁኔታ፣ እንዲሁም ያለማቋረጥ የነበረው ስጋት በሐሪየት ደካማ አካል ላይ ከፍተኛ ጉዳትን አደረሰ። ገና በባህር ላይ እያለች፣ ከ19ኛ ዓመት ልደቷ ሁለት ቀናት በፊት የተወለደችው ህፃን ልጅ ከአምስት ቀናት በኋላ በሞት ተለየቻት። በሐዘን የተሰበረችው፣ የደከመችው እና የአካል ብቃቷ የተሟጠጠው ሐሪየት ቲዩበርክሎሲስ በወቅቱ ኮንሰምፕሽን እየተባለ የሚጠራው የሳንባ ነቀርሳ በሽታ ባሰባት መርከቡ በመጨረሻ ወደ ወደብ ሲደርስ የሕክምና እርዳታ ማግኘት ከቶውንም አልተቻለም ነበር። ሐሪየት ኒውል ጉዞዋን ከጀመረች ከጥቂት ወራት በኋላ፣ ህዳር 21 ቀን 1805 ዓ.ም ከወደደችው ሀገር ውጭ ባዕድ ምድር ላይ ሕይወቷ አለፈ። ሐሪየት የውጭ አገር ቋንቋ አውቃም ሆነ በባዕድ ምድር ላይ በይፋ የቆመ ስብከት አድርጋ የማታውቅ ቢሆንም፣ በክርስቲያናዊ ታሪክ ላይ ያላት አሻራ ግን እጅግ ግዙፍ ነው። እሷ በውጭ አገር የሚስዮናዊነት መስክ ላይ ሕይወቷ በመጥፋቱ የመጀመሪያዋ አሜሪካዊት ሴት ሚስዮናዊ እንዲሁም በአጠቃላይ የመጀመሪያዋ አሜሪካዊ በመሆን ታሪካዊ የክብር ባለቤት ሆናለች።ከሞቷ በኋላ፣ በሐዘን የተመታው ባሏ ማስታወሻዎቿን እና ደብዳቤዎቿን በአንድ ላይ በማሰባሰብ የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ አዘጋጀ። በ1806 ዓ.ም የታተመው የሐሪየት ኒውል የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ተነባቢነትን ያገኘ ምርጥ ሽያጭ በመሆን፣ ለብዙ አሥርት ዓመታት በየዓመቱ ማለት ይቻላል ታትሞ ወጥቷል። ጽሑፎቿ ለ19ኛው ክፍለ ዘመን ክርስቲያኖች ጀግና እና አርአያ እንድትሆን አድርገዋታል። በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣት አሜሪካዊያን ሴቶች ታሪኳን በማንበብ ሕይወታቸውን ለአለም አቀፍ ተልዕኮ ለመስጠት ተነሳስተዋል፤ ብዙ ወላጆችም ለልጆቻቸው "ሐሪየት ኒውል" የሚለውን ስም በክብሯ አውጥተውላቸዋል (ለምሳሌ ታዋቂው የቻይና ሚስዮናዊ ሐሪየት ኒውል ኖየስ። ቀደም ብሎ የተከሰተው ይህ አሳዛኝ ዕለተ ሞቷ አሜሪካዊያን አማኞች ለእምነታቸው ሲሉ የመጨረሻውን መስዋዕትነት ለመክፈል ፈቃደኛ መሆናቸውን ያረጋገጠ ሲሆን፣ የዘመኑን የሚስዮናዊነት እንቅስቃሴ አካሄድ ለዘላለም የቀረጸ ክስተት ሆኗል። ምንጮች · ዊኪፔዲያ እና የአካዳሚክ ማጠቃለያዎች፡ የክርስቲያን ሚስዮናዊያን የሕይወት ታሪክ መዝገበ ቃላት (Wm. B. Eerdmans Publishing)፣ እንዲሁም ስለ ሐሪየት ኒውል ሕይወት፣ ጋብቻ እና የባህር ጉዞ የሚዳስሱ አጠቃላይ ታሪካዊ ጽሑፎች። · የወንጌል ሕብረት ማህበር (GFA) ሚስዮናዊያን፡ የግል የዕለተ መጽሔት ጽሑፎቿን፣ ስለ "አላፊ ዓለም አንጸባራቂ ከንቱ ውበት" የነበራትን አመለካከት እና በካራቫን ) መርከብ ላይ ያደረገችውን ጉዞ ቅደም ተከተል በዝርዝር የሚያሳዩ ታሪካዊ መዛግብት። · የማክክሊንቶክ እና ስትሮንግ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ኢንሳይክሎፒዲያ፡ ስላደረገችው ቲዎሎጂያዊ ተጽዕኖ እና ቀደምት መስዋዕትነቷ የአሜሪካንን ሚስዮናዊ እንቅስቃሴ እንዴት እንዳቀጣጠለው የሚገልጹ ታሪካዊ እንቅስቃሴዎች። · የቤተ መጻሕፍት መዛግብት እና የዕለት ተዕለት አምልኮ ታሪኮች፡ "የአንድ ዓመት የክርስቲያን ታሪክ ሴቶች" (The One Year Women in Christian History Devotional) መጽሐፍ እና በ1806 ዓ.ም. (1814 እ.ኤ.አ.) የታተመውን የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ ህትመትና የባህል ተጽዕኖ የሚከታተሉ ማስታወሻዎች። @revealjesus
без подписи
Battery low ሰሞኑን ስልኬን በበቂ ሁኔታ ቻርጅ ወይንም ሀይል ሳልሞላው ከቤት እየወጣሁ ባልተጠበቀ ሰአት፣ በሚያስፈልገኝ ጊዜ እየዘጋብኝ ተቸግሬ ነበር ለዚህ ችግር መፍትሄው ወደቀኑ ትግል ከመግባቴ በፊት ቻርጅ ማድረግን አለመርሳት ነው። በህይወትም እንዲሁ በድካም በዝለት የምናሳፋቸው ቀናቶች ብዙ ናቸው። መፍትሄው በበቂ ሁኔታ ቻርጅ ማድረግ ነው። ይህን ስል በጸሎት መንፈሳዊ ህይወታችንን ማጠንከር፣ በጥሞና ውስጥ ራሳችንንም አምላካችንንም በመስማት ውስጣችን ማደስ፣ አካላዊ ሰውነታችንንም እረፍት በማድረግ ማደስ ወይንም ሀይል መሙላት መዘንጋት የለብንም። ጸሀፊ:- ሳሙኤል ከበደ #photo ሰሙኑን ለደቡብ ኦሞ የልብስ ቻሌንጅ ላይ ስላለን ያንን በማስመልከት ነዉ የተጠቀሙት 🙏 @revealjesus
📢 We are collecting clothing donations for our brothers and sisters in South Omo who have been affected by flooding. 👕 We welcome all types of clean, usable clothing, with a special need for women's and children's clothes. Your donation can bring warmth, dignity, and hope to someone in need. 📍 Donation Contacts: • Hawassa – 📞 0980404779 • Shashemene – 📞 0916828046 • Nagele Arsi – 📞 0916148697 • Addis Ababa – 📞 +251912766809 "Whoever is kind to the poor lends to the Lord." — Proverbs 19:17 Thank you for your love, prayers, and generosity. 🤍 #SouthOmo #ClothingDrive #Mission #GiveHope #LoveInAction #Ethiopia@revealjesus
የደከማችሁ የመሰላችሁ የዛላችሁ የመሰላችሁ ኑ እስኪ አንድ ሰዉ ላስተዋውቃችሁ 👐 #ዛሬም ጉልበታም ነኝ የሚል ለድካሙ ምክያት የማይፈልግ ይልቁንም ለመበረታታት ምክንያት የሚፈልግ #በጎልማሳነቱ በወጣትነቱ የሰራዉን እያወራ የማይተክዝ አቅሙን በብርታቱ ብቻ የማያደርግ ከሁኔታ የማይጀምር ና የማይጨርስ ስጀምረም ስጨርስም ከላይ የሚነሳ ሰማይ አቅሙ የሆለት (ኢያሱ 14 ¹¹ ሙሴም በላከኝ ጊዜ እንደ ነበርሁ፥ ዛሬ ጕልበታም ነኝ፤ ጕልበቴም በዚያን ጊዜ እንደ ነበረ፥ እንዲሁ ዛሬ ለመዋጋት ለመውጣትም ለመግባትም ጉልበቴ ያው ነው። ¹⁴ ስለዚህም የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ፈጽሞ ስለ ተከተለ ኬብሮን እስከ ዛሬ ለቄኔዛዊው ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ርስት ሆነች።) #ታሪክ ላይ ታሪክ የሚጨምር አምላኩ አቅሙ የሆነለት መዉጣት ና መዉረስ የሚታየዉ ጀግና ሰዉ የ85 አመቱ ጉልበታም በጉብዝናዉ የተነገረለትን ሳይወረስ የማያርፍ ህልሙ እስክሳካ የማይደክም ጨረሰ ስባል የሚጀምርን ካሌብ አያችሁት ? ተማሩበት 🙏 ✍️ Genet Zewdie @revealjesus
👸"እሷ ማን ናት?" 📌በዕለት ተዕለት ሕይወቷ ውስጥ የእግዚአብሔርን መለኮታዊ ውበት የምታንጸባርቅ☀️ ሕያው ምስክር የሆነች ይህች ሴት እርስዋ ማናት? መገለጫዋስ ምንድን ነው? የሚለውን ቀጣይ ክፍል ዛሬ አብረን እንመለከታለን። እሷ👇👇👇 👉በሥነ-ሥርዓት (ዲሲፕሊን) በነገር ሁሉ የተገራች ናት እርሷ ስሜቶቿንና ምኞቶቿን በቃሉ ሥልጣን ሥር የምታስገዛ ሴት ናት። የምትናገረውን የምትመዝን፣ ጊዜዋን በንቃት የምትጠቀም እና የሕይወቷ መሪ ጌታ መሆኑን በራስ መግዛት የምታሳይ ናት። እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና። 2ኛ ጢሞቴዎስ 1:7 👉በጨዋነትና በልከኝነት የምታጌጥ (የምትለብስ)ናት እርሷ እውነተኛ ውበት ከውስጥ የሚፈልቅ መሆኑን የተረዳች ናት። አለባበሷ የውስጧን ቅድስና፣ ክብርና ራስን መግዛት የሚያንጸባርቅ እንጂ የዓለምን ግብዝነት የሚከተል አይደለም ሰውነቷ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሆኑን ስለምታውቅ ክብሯን በሚመጥን ጨዋነትና ልከኝነት ትሸፈናለች። እንዲሁም ደግሞ ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ 1ኛ ጢሞቴዎስ 2:9-10 👉ለሥራ የማትለግም ትጉ💪 ናት እርሷ ሥራን እንደ መለኮታዊ ጥሪ የምታይ ብርቱ ሴት ናት ስለሆነም ስንፍናን አትወድም እጆቿን ለሥራ ትዘረጋለች በቤቷም ሆነ በማኅበረሰቡ ውስጥ የምታበረክተው አስተዋጽኦ ሕይወቷን ፍሬያማ ያደርገዋል ። ወገቧን በኃይል ትታጠቃለች፥ ክንዶቿንም ታበረታለች። ምሳሌ 31:17 👉ለማንም መሰናክል የማትሆን ናት እርሷ የሰዎችን ድካም የምትሸከም እንጂ በሌሎች ሕይወት ላይ እንቅፋትና መውደቂያ የማትሆን ናት ማንም በእሷ ምክንያት እንዳይሰናከል በንግግሯ፣ በአካሄዷና በውሳኔዎቿ ሁሉ ትጠነቀቃለች። ሰዎችን በፍቅር ትደግፋለች በዙሪያዋ ላሉት ሁሉ የማነጽ እንጂ የውድቀት ምክንያት አትሆንም። ስለዚህ እርስ በርሳችን ከእንግዲህ ወዲህ አንፈራረድ፤ ይልቁን ግን ለወንድም እንቅፋትን ወይም መውደቂያን ማንም እንዳያኖርበት ይህን ቁረጡ። ሮሜ 14:13 👉ሁልጊዜ የምታመሰግን ነች እርሷ ሕይወት በበረከት ሲሞላ ብቻ ሳይሆን መንገዶቿ ሁሉ በፈተና ሲሸፈኑ እንኳ ምስጋናዋ አይቋረጥም። "ለምን?" ብላ ከማማረር ይልቅ እግዚአብሔር በነገሮች ሁሉ ውስጥ መልካም እንደሆነ ታምናለች። ለእያንዳንዱ ትንሽም ይሁን ትልቅ ነገር የምስጋና መሠዊያ አላት። 📌በጎ ተጽዕኖ በትውልድ መካከል እያኖርን መመላለስ እንድንችል ለሁላችንም የእግዚአብሔር የአባታችን ጸጋ ይብዛልን። 🙏 From HU Sisters Ministry @revealjesus
ዓለም ታላቅነትን በቁሳቁስ ሀብትና ምቾት በሚለካበት ዘመን፣ የአሚ ካርማይክል ሕይወት ሙሉ በሙሉ እጅን በመስጠት፣ ጽኑ እምነት እና ያለ ቅድመ ሁኔታ በሚኖር ፍቅር የሚገኘውን ታላቅ ውጤት እንደ ሕያው ምስክር ሆኖ ይታያል። አሚ ታኅሣሥ 8 ቀን በ1860 ዓ.ም ሰሜን አየርላንድ የባህር ዳርቻ መንደር ሚልስል በሚባል ቦታ ነበር የተወለደችው ፤ በጽኑ የክርስቲያን እምነት፣ ርኅራኄ እና ጠንካራ ሥነ ምግባር በታነጸ ቤተሰብ ውስጥ አደገች። ይሁን እንጂ የልጅነት ሕይወቷ ፈተናዎች ያልተለዩት ነበር፤ አሚ የ18 ዓመት ወጣት ሳለች አባቷ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው ቤተሰቡ ከፍተኛ የኢኮኖሚና የስሜት ቀውስ ገጠመው። አሚ ግን ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ እምነቷን በማጠንከር በቤልፋስት ከተማ ውስጥ "ሻውሊስ" በመባል ለሚታወቁት ድሆችና በፋብሪካ ለሚሠሩ ሴት ወጣቶች የእሁድ ጥዋት የትምህርት መርሃ ግብር ማዘጋጀት ጀመረች፤ ይህ ድርጊቷም ለተገለሉ ሰዎች የነበራትን ቀደምት ርኅራኄ በግልጽ የሚያሳይ ነበር። በዚያን ጊዜ ነበር ነፍሷ ከዓለማዊ ምቾት ይልቅ ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ብቻ ለመኖር በታላቅ ቅንዓት የተሞላችው። የሚስዮናዊነት አገልግሎት ጥሪ: የአሚ መንፈሳዊ ጉዞ ትልቅ ለውጥ ያደረገው በኬስዊክ ጉባኤ (Keswick Convention) ላይ በተገኘችበት ወቅት ሲሆን፣ ከሀገር ውጭ ባሉ ቦታዎች የሚስዮናዊነት አገልግሎት እንድትሰጥ ጠንካራ እና የማይናወጥ ጥሪ ተሰማት። ወደ ሚስዮናዊነት መስክ ያደረገችው ጉዞ ግን ፈጽሞ ቀላል የሚባል አልነበረም። ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚስዮናዊ ድርጅቶች ያቀረበችው ማመልከቻ ተቀባይነት ለማግኘት ፈታኝ ሆኖ ነበር፤ ምክንያቱም በወቅቱ የነበራት ደካማ የጤና ሁኔታ (ከፍተኛ የነርቭ ሕመምን ጨምሮ) ጥርጣሬን ፈጥሮ ነበር። በሁኔታው ሳትበገር ለአጭር ጊዜ በጃፓን አገልግላለች፤ ነገር ግን የአየር ንብረቱ ከባድነት ወደ ሀገሯ እንድትመለስ አስገደዳት። በኅዳር ወር 1888 ዓ.ም በ28 ዓመቷ ከእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን የዜናና ሚስዮናዊ ማኅበር ጋር በመሆን ደቡብ ሕንድ ደረሰች። ይህች ውብ፣ ድንቅ እና መንፈሳዊ ውስብስብነት ያላት ምድር ለሚቀጥሉት 55 ዓመታት መኖሪያ ቤት እንደምትሆንላት እርሷ ራሷ በወቅቱ አላወቀችም ነበር፤ በእነዚህ ዓመታት ውስጥም አንድ ጊዜ እንኳን ወደ አየርላንድ የትውልድ ሀገሯ አልተመለሰችም ወይም የተለመደውን የዕረፍት ጊዜ አልወሰደችም። ሕንድ እንደደረሰች አሚ የአካባቢውን ባህል ለመረዳት ራሷን አሳልፋ ሰጠች፤ የታሚል ቋንቋን አቀላጥፋ በመማር እና የአካባቢውን ልብስ በመልበስ ከህዝቡ ጋር በቅርብ ለመግባባት ችላለች። ብዙም ሳይቆይ በባህላዊው ማህበረሰብ ስር ተሸሽጎ የነበረውን አስከፊ እውነት ተረዳች፤ ይኸውም ዴቫዳሲ በመባል የሚታወቀው ሥርዓት ሲሆን፣ በዚህም ወጣት ሕፃናት በተለይም ሴት ልጆች ለቤተ መቅደስ አማልክት ይሰጡ ነበር፤ ይህ ልማድም ሕፃናቱን ወደ ሃይማኖታዊ ባርነት እና ብዝበዛ ይመራቸው ነበር። በዚህ ኢ-ፍትሃዊ ድርጊት የተሰበረው ልቧ ይህም የአሚን ተልዕኮ ከሰፊው የወንጌል ስብከት ጉዞ ወደ ሕፃናትን የማዳንና የመጠለያ ሥራ እንዲቀየር አደረገው። እ.ኤ.አ. በ1901 የመጀመሪያዋን የታደገችውን ልጅ በመቀበል የዲናቭር ፌሎሽፕ (Dohnavur Fellowship) መሠረት ጣለች። ገንዘብ ሳትጠይቅ እና ዕዳ ውስጥ ሳትገባ ሙሉ በሙሉ በእምነት እና በጸሎት ብቻ ትንቀሳቀስ የነበረው ዲናቭር፣ ከአንድ ትንሽ መጠለያነት ተነሥቶ ወደ ትልቅና ራሱን ወደ ቻለ ማህበረሰብ አደገ። በሕይወት ዘመኗ አሚ እና አብረዋት ያሉት ቡድን ከአንድ ሺህ በላይ ሕፃናትን አደገኛ ከሆኑ ሁኔታዎች አድነዋል፤ እንደ እውነተኛ ቤተሰብም አሳድጓቸዋል። ሕፃናቱ በፍቅር "አማ" (እናት) ብለው ይጠሯት ነበር። ህብረቱም ከጊዜ በኋላ መዋለ ሕፃናትን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ ሆስፒታልን እና የሙያ ማሰልጠኛዎችን በማካተት የክርስቶስን ፍቅር የሚያንጸባርቅ ብርሃን ሆነ። የአገልግሎት ፈተናዎች እና ፍሬ በ1923/24 ዓ.ም የገጠማት ከባድ ውድቀት ከባድ አርትራይተስ ወይም የመገጣጠሚያ ሕመም አስከተለባት፤ ይህም ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት በአልጋ ላይ እንድትወሰን አደረጋት። ሆኖም የአካል ውስንነት የእርሷን ሕያው መንፈስ ማሰር አልቻለም። መኝታ ቤቷን ወደ ጽሕፈት ቤት በመቀየር ግጥሞችን፣ ዕለታዊ መልእክቶች እና የሕይወት ታሪክ ማስታወሻዎችን ጨምሮ 35 የሚጠጉ መጻሕፍትን ደረሰች፤ ከእነዚህም መካከል ጎል ባይ ሙንላይት እና ኢፍ ይገኙበታል። ስለ መከራ፣ ትዕግስት እና "የካልቫሪ ፍቅር" የጻፈችባቸው መጻሕፍት ዛሬም ድረስ በዓለም ዙሪያ ያሉ አማኞችን ይፈትናሉ፣ ያጽናኑማል።አሚ ጥር 10 ቀን 1943 ዓ.ም በ83 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ስትለይ፣ በመቃብሯ ላይ ምንም ዓይነት የትዝታ ድንጋይ ወይም መታሰቢያ እንዳይደረግ ጠየቀች። ይህም የሕይወት እውነተኛ ስኬት የሚገኘው በምቾት ሳይሆን ለእግዚአብሔር ጥሪ ባለው ጽኑ ታማኝነት መሆኑን የሚያሳይ ታላቅ ትምህርት ሆኖ ቀጥሏል። ምንጮች · የዲናቭር ፌሎሽፕ ኦፊሴላዊ መዛግብት እና ታሪካዊ መረጃዎች (Dohnavur Fellowship Official Archives): ዲናቭር ማኅበር ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ያሉት ዕለታዊ የሥራ ሂደቶች፣ የአሚ ካርማይክል የሕይወት ዘመን ቆይታ በሕንድ እና የማኅበሩን መሠረታዊ መዋቅር ለማወቅ ታላቅ ግብዓት ሆኖ አገልግሏል። · የሚስዮናዊነት ታሪክ ማዕከል – ቦስተን ዩኒቨርሲቲ (History of Missiology, Boston University School of Theology): የአሚን መንፈሳዊ አስተዳደግ፣ የኬስዊክ ጉባኤ (Keswick Convention) ተሳትፎዋን እና የሚስዮናዊነት ጉዞዋን የጊዜ ሰሌዳ በትክክል ለመረዳት ተጠቅሞበታል። · የሕይወት ታሪክ መጻሕፍት (Biographical Works & Literature): ኤልሳቤጥ ኤልዮት (Elisabeth Elliot) – አን አቻንስ ቱ ዳይ፡ ዘ ላይፍ ኤንድ ሌጋሲ ኦቭ አሚ ካርማይክል (A Chance to Die: The Life and Legacy of Amy Carmichael): ለአሚ ሕይወት ጥልቅ ትንተና እና መንፈሳዊ ልዕልና ዋነኛ ማጣቀሻ። ኢያን ኤች. ሙራይ (Iain H. Murray) – አሚ ካርማይክል፡ ቢዩቲ ፎር አሼስ (Amy Carmichael: Beauty For Ashes): የታሪኩን እውነተኝነት እና የጽናት አርአያነት በሰፊው ለማሳየት የረዳ ድንቅ ሥራ። @revealjesus
без подписи
የተስፋ ወሳኝነት በአሁን ሰዓት አንድን የጀመራችሁትን ነገር ተሳክቶ ለማየት ባላችሁ ጉዞ ያላችሁ ምርጫ ሁለት ነው፡- 1) ተስፈኛነት፡- በተስፋ ቀና ብሎና ተነቃቅቶ መገንባት 2 ) ተስፋ-ቢስነት፡- በተስፋ መቁረጥ አቀርቅሮና ግድየለሽ ሆኖ መገንባት፡፡ እነዚህ ሁለቱ ዝንባሌዎች አንድ አይነት ውጤት እንደማይኖራቸው አትዘንጉ፡፡ ተስፈኛነት፡- ጉዞው ምንም ያህል ቢከብድም ተስፋን ሳይጥሉ መቀጠል በየእለቱ ከሚነሱ እንቅፋቶች ባሻገር በመመልከት ከመጨረሻው ዋና ዓላማ አንጻር እንድንገሰግስ ያደርገናል፡፡ “የተስፋን ቃል የሰጠን ታማኝ ስለ ሆነ፣ አምነን የምንናገርለትን ተስፋ አጥብቀን እንያዝ” - ዕብ. 10:23 ተስፋ-ቢስነት፡- በተቃራኒው፣ ተስፋ እንደሌለንና ሁኔታው እንደዘገየብን ስናስብ በሂደቱ በመዛል ተስፋ በመቁረጥ መጓዝ ጥራትና ውጤት-ተኮር ከመሆን ይልቅ ላይ ላዩን ሰርተን እንድናልፍ ያደርገናል፡፡ “ለነገ የሚባል ተስፋ ልብን ያሳምማል” - ምሳ. 13:12 በተስፋ እንገንባ!!! 1. በእጃችሁ ያለው ነገር ምንም ትንሽ ቢሆን፣ በተስፋ ገንቡት! “የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? ሰዎች በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን ሲያዩ ይደሰታሉ። “እነዚህ ሰባቱ በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ የእግዚአብሔር ዐይኖች ናቸው” - ዘካ. 4:10 2. የነገን ውጤት አይታችሁ ገንቡት! “ስለዚህ ዐይናችን የሚያተኵረው በሚታየው ነገር ላይ ሳይሆን በማይታየው ላይ ነው፤ የሚታየው ጊዜያዊ ነውና፤ የማይታየው ግን ዘላለማዊ ነው” - 2ቆሮ. 4:18 3. “እንደጀመርኩት እጨርሰዋለሁ” በሚል የመነሳሳት መንፈስ ገንቡት! “በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እርሱ እስከ ክርስቶስ ኢየሱስ ቀን ድረስ ከፍጻሜው እንደሚያደርሰው ርግጠኛ ነኝ” - ፊል. 1:6 4. “ለጊዜው ያለብኝ ፈተና ቢከብደኝና ብዝል እንኳን እንደምንም አጠናቅቀዋለሁ” በሚል ዝንባሌ ገንቡት! “በፈተና የሚጸና ሰው ብፁዕ ነው፤ ምክንያቱም ፈተናን ሲቋቋም እግዚአብሔር ለሚወድዱት የሰጠውን ተስፋ፣ የሕይወትን አክሊል ያገኛል” - ያዕ. 1:12 5. የዛሬ ትግል ነገ ዋጋ እንዳለው በማሰብ ገንቡት! “የአሁኑ ዘመን ሥቃያችን ወደ ፊት ሊገለጥ ካለው፣ ለእኛ ከተጠበቀልን ክብር ጋራ ሲነጻጸር ምንም እንዳይደለ እቈጥራለሁ” ሮሜ 8:18 6. በተስፋ ወደፊት ከመገስገስ ውጪ ሌላ ምርጫ እንደሌላችሁ ራሳችሁን በማሳመን ገንቡት! “ወንድሞች ሆይ፤ እኔ ገና እንደ ያዝሁት አድርጌ ራሴን አልቈጥርም፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ ከኋላዬ ያለውን እየረሳሁ ከፊቴ ወዳለው እዘረጋለሁ” - ፊል. 3:13 Dr eyob mamo @revealjesus
እግዚአብሔር የሚፈለገው ለህይወት ነዉ
እንጸልይ ለጉራጌ የሕዝብ ክፍል የጉራጌ ማህበረሰብ የሚታወቅበት የኢኮኖሚ ጥንካሬ እና ጠንካራ የማህበረሰብ ተቋማት ቢኖሩትም፣ አሁንም ድረስ በርካታ አጣዳፊ የልማት እና የመሰረተ ልማት ክፍተቶች ይፈታተኑታል። በገጠሩ አካባቢ ዘመናዊ የጤና አገልግሎት መስጫዎችን፣ ንጹህ የመጠጥ ውሃን እና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል የማግኘት ፍላጎት አሁንም በከፍተኛ ደረጃ ይገኛል። የግብርናው ማህበረሰብ ምርቱን በብቃት ወደ ክልላዊ ገበያዎች ለማቅረብ ዘመናዊ የግብርና መሣሪያዎች፣ የእንሰት ተክል በሽታዎችን የመካከላዊ እና የማከም ዘዴዎች፣ እንዲሁም የተሻሉ የትራንስፖርት እና የመንገድ መረቦች ያስፈልጉታል። በተጨማሪም፣ ወደ ከተሞች የሚደረገው ፍልሰት አዳዲስ የኢኮኖሚ እድሎችን የሚከፍት ቢሆንም፣ በገጠሩ ማህበረሰብ ላይ የራሱ የሆነ ማህበራዊ ጫና ያሳድራል። በመሆኑም በራሱ በጉራጌ ዞን ውስጥ ዘላቂ እድገትን ለማረጋገጥ የአካባቢውን ትምህርት ቤቶች፣ የሙያ ማሰልጠኛዎችን እና የሥራ እድሎችን ለወጣቶች ማስፋፋት እጅግ አስፈላጊ ሆኖ ይገኛል። የጸሎት ርዕሶች 🤲🏼 👉🏼 በጉራጌ ሕዝብ ክፍል መካከል ያለውን ያላለቀ የወንጌል ተልእኮ ስራ ለማዳረስ የሚተጉ የመኸሩ ሰራተኞች ሚሲዮናዊያን እንዲሰማሩ እንጸልይ። 👉🏼 በተለያዩ ወረዳዎች እና ዞኖች ቤተክርስቲያን ተከላ ንቅናቄዎች እንዲፋጠኑ፤ የሚባዙ አገርበቀል ቤተክርስቲያኖች እንዲተከሉ እንጸልይ። 👉🏼 የምስራቹ ወንጌል እያንዳንዱን ቤት እና ግለሰብ እያለፈ እንዲሰበክ፣ የመዳን መልእክት በዚህ ሕዝብ መካከል በሙላት እንዲታወጅ እንጸልይ። @revealjesus
без подписи