- Последний пост
- 9 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 25
- Тип
- открытый
- Язык
- eo
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 111
- 1/48двое суток
- 127
- 1/72трое суток
- 137
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የጭንቅ በሮች መክፈቻ፣ የሪዝቅ ማዝነቢያና የልብ ሰላም ማግኛ ከፈለግክ ምስጢሩ አንድ ነው—#ኢስቲግፋር 📿 እርሱ ከአላህ ዘንድ ይቅርታን የመጠየቂያ መንገድ ብቻ ሳይሆን፣ ከማንኛውም መከራ የምታመልጥበት ታላቅ መከላከያህ ነው። وَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيُعَذِّبَهُمۡ وَأَنتَ فِيهِمۡۚ وَمَا كَانَ ٱللَّهُ مُعَذِّبَهُمۡ وَهُمۡ يَسۡتَغۡفِرُونَ "እነርሱም ምሕረትን የሚለምኑ (እስቲግፋር የሚያደርጉ) ሲኾኑ አላህ የሚቀጣቸው (የሚያጠፋቸው) አይደለም፡፡" (ሱረቱ አል-አንፋል 8:33) ህይወት ፊቷን አዙራብህ ነገሮች የተዘጋጉ ሲመስሉህ፣ የውስጥህ ጭንቀት አቅም ሲያሳጣህ፣ ወይም የመንገዱ መውጫ ጠፍቶ ግራ ሲገባህ... ወደ ጌታህ ተመለስ። በአንደበትህና በልብህ «አስተግፊሩሏህ» ማለትን አብዛ። ባሪያው ተጸጽቶ ምህረቱን ሲጠይቅ አላህ በፍጹም አይጥለውም፤ ይልቁንም በደሉን በሙሉ አብሶ፣ በምትኩ ማለቂያ የሌለው እፎይታንና በረካን በህይወቱ ላይ ያዘንብበታል። Ke quran ayah
አላህ የሰጠህን ሪዝቅ ጀሊሎ ያን ሲሳይ በመከልከል ከሚፈትነው ወንድምህ መደበቅ እስከምትችል ድረስ በሚስጥር መያዝህ፣ አንድም የወንድምህን ስሜት መጠበቅ ነው ሲቀጥልም ሳያውቅ በዓይኑ ጉዳት እንዳያደርስብህ ማድረግህ ነው። አላህ ለሁላችንም የምናስበውን እና የምናቅደውን ነገር ከቀደር ጋር ያጋጣጥምልን
"መን ለም የፍሐም ቢልኢሻራ ፈሁወደንጋራ" ይሉ ነበር ኡስታዛችን
без подписи
ልባችሁ ውስጥ የዩሱፍ ታሪክ ያለ አይመስላችሁም? ሩ…ቅ ህልሞች፣ አጥር የተሻገሩ ምኞቶች… እና ደግሞ "ዩሱፍ ሊመለስ አይችልም" ብለው የሚምሉ የመንደሩ ሰዎች .. የያዕቁብን የለቅሶ ዓለም እንደ ንጭንጭ የሚቆጥሩ ዘላኖች አሉ። በህይወት ኖረም አልኖረም ለሩቅ ሰዎች በባርነት እንደሸጡት እርግጠኛ የሆኑ ወንድሞቹም አሉ። አንዳንዴ… እዚህ መሀል የአላህ ፍላጎት ጣልቃ ይገባል። "የማይሆን" ብለው የማሉለት ጉዳይ መሀል "የፈለኩትን አድራጊ ነኝ" ሊል ይመጣል። ሊቀየር የማይችል የሚመስለን ሁሉ ይቀየራል። ተበትነው የነበሩ ምኞቶች ይሰበሰባሉ። ህልም የነበረው በገሀዱ ዓለም ይታያል። አጠገብህ ላሉት ሰዎችም “አላህ እንደሚቀበለኝ በእርግጠኝነት ምዬ አልነገርኳችሁም ወይ?" ትላቸዋለህ። ዓጂብ🖤 ɢℓσσм
አንድ ቀን ህልሜ ይሳካና ደስተኛ እሆናለሁ፣አንድ ቀን ከልቤ አላህን አመሰግነዋለሁ ፣አንድ ቀን አላህ የጠየቅኩትን ሁሉ ይሰጠኝ እና እደሰታለሁ እውነተኛ አመስጋኝ ሁኜም እኖራለሁ ፣ለሰወች ችግርም እደርሳለሁ አትበሉ! አላህን ዛሬ አመስግኑት፣በፈተናወቹ ውሰጥ ደስተኛ ሁኑ ፣ወደ ፊት ብር ሲሰጣችሁ ስለምትረዱት ደሀ አታልሙ ዛሬ አንዱን ፌርማታ ወክ አድርጉና የታክሲ ብራችሁን መፅውቱ፣ አላህ ሀብታም ሲያረጋችሁ አዲስ ልብስ ገዝታችሁ ለየቲሞች ለማልበስ አትመኙ ዛሬ ከልብሳችሁ መሀል አንዱን የአላህን ውዴታ ሽታችሁ መፅውቱ፣ ምኞታችሁ ሁሉ ሰምሮ አላህዬ እውን ይሄ ለኔ ተደረገልኝ ብላችሁ በምስጋና ስለማልቀስ ማሰብ አቁሙና ዛሬ ስላላችሁ የብናኝ ያክል ፀጋ እንኳን አላህን በእምባ ተሞልታችሁ አመስግኑ ፣ዛሬ ለበላችሁት ሽሮ እና ደረቅ ዳቦ አመስግኑ፣ የታክሲ አጥታችሁ በፀሀይ ተንከራታችሁ ይሆናል ስለእግሮቻችሁ ግን አመስግኑ፣ ለአይን የሚማርክ ሰፊና ውብ ቤት አትኖሩ ይሆናል ለደሳሳ ጎጇችሁ አመስግኑ ፣ለተሰተረላችሁ አይብ አመስግኑ። ዛሬ ካላመሰገናችሁ መቸም አታመሰግኑም! የምታመሰግኑት ከናንተ በታች ያነሰ ሂወት የሚኖር ስላለ አልያም እናንተ ያላችሁን ነገር የሚመኝ ሚስኪን ሰው ስላለ ከእሱ እሻለለሁ በሚል ሊሆን አይገባም ! ይህ በጣም ደባሪው አላህን የማመስገን መንገድ ነው። ይህ አይነቱ ማመስገን የመጨረሻ ውድቀት ላይ ያለ ሰው ብትሆን እንደማታመሰግን በግልፅ አረጋጋጭ ነው። ስለእግሮችህ የምታመሰግነው እግር የሌለው ስታይ፣ሰለ ደሳሳ ጎጆህ የምታመሰግነው ጎዳና የሚያድርን ስታይ፣ስለ ኑሮ ሁኔታህ የምታመሰግነው ምግብ አጥቶ የሚለምን ስታይ ብቻ ከሆነ አንተ ደካማው አመስጋኝ እና አማኝ ነህ። እግርህ ቢቆረጥ፣ጎዳና ብትወድቅ፣ ቢርብህ እንኳን አመስጋኝ መሆን እችላለሁ ወይ ብለህ እራስህን ጠይቅ። የአማኞች እና የአመስጋኞች እውነተኝነት ማረጋገጫ በሁሉም ፈተናወች ውስጥ ማመስገናቸው ነው። አንድ ነገር እርግጠኛ ሁኜ ልንገርህ በችግር ውስጥ ያላመሰገነ በማግኘት ውስጥም አያመሰግንም! ምስጋና ከማግኘት እና ከማጣት ጋር የተያያዘ አይደለም!! ምስጋና አላህን እጅጉን በመውደድ እና በማመን ውስጥ የሚገኝ ፀጋ ነው። ዛሬ ያላመሰገንከውን ጌታ ነገ የእውነት ማመስገንን ልታመሰግነው ከቶ አይቻልህም !ብታመሰግነው እንኳን ከምላስ የማያልፍ ምስጋና ነው ፀጋው በጠፋ ቅፅበት የሚበን ምስጋና። አመስጋኝነትን መለማመድ እና ከልብ መተግበር የተረጋጋ ሂወት ባለቤት እና ደስተኛ ማንነትን ይገነባልሀል። እውን አላህን የምትወድ፣በእርሱ የምትተማመን እና የምትመካ ከሆንክ አመስጋኝ ሁን። በሁሉም የሂወት ከፍታህና ዝቅታህ ውስጥ ከልብ የመነጨ ምስጋና እና ሪዷ ይኑርህ። ያኔ አለም ላይ ሁሉም የሚያሳድደው እውነተኛ ደስታ ባለቤት ትሆናለህ ። በጣም በደስታ አመስግን! (ረሂማ ሁሴን) @rehimahu
"አዱ ሀቢባ ተሳትፏቸውን አድንቃ ሀሳቡን ወደተነሳችበት የቁርዓን አንቀፅ መለሰች። <<ቁርዐን ላይ አላህ ወሀደይናሁ ነጅደይን ይላል። ልብ ብላችሁ ካስተነተናችሁ የሰው ልጅ አወላለድ አላህ ለመኖሩ የሚታይ ማስረጃ ሆኖ ታገኙታላችሁ። ህፃን ልጅ ልክ እንደተወለደ አይኖቹን ሳይገልጥ .... ጠት ፈልጎ ሲቅበዘበዝ ታዩታላችሁ። አሁን ነጥቡ ጠት የሚባል ነገር መኖሩን አንዴት አወቀ የሚለው ነው፡፡ አላህ ሞላሹን ሲሰጥ…
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ ⏰#ሰብት 1⃣8⃣ #ሰፈር 1⃣4⃣4⃣8⃣ ሂ
ዑምራ የሄዱ ሰዎች ስለመዲና የሚያወሩት ነገር ለየት ይላል ። ሁሉም በሚባል ደረጃ ከዚህ በፊት ተሰምቷቸው የማያውቅ እጅግ የተለየ ስሜት እንደተሰማቸው ፣ የሚገርም ሰኪና እንዳገኙና ይህ ነው ተብሎ የማይገለፅ ነገር ከተማው እንዳለው ይናገራሉ ። {ሰሞኑን ተመሳሳይ ስሜት እዛ ያሉ ሰዎች አጋርተውኛል} እርግጥ ይሄ ሁሉ አያስደንቅም : አላወቁም እንዴ ? ከተማውኮ ለሰማይና ለምድር የከበዱት ፣ ከአዋቂና ጥበበኛው ጌታ ቁርዐንን የተሰጡት ፣ የፍጡራን ሁሉ አማላጅ የሆኑት አሽረፉ ኸልቂላህ ክቡር ገላ ያረፈበትኮ ነው ። እንዴት ነው ታዲያ ሰኪና ማያገኙት ? እንዴት ነው በደስታ የማይሰክሩት ? እንዴት ነው አይናቸው ማያነባው ? እንዴት ነው Emotional ማይሆኑት ? إنها مدينة رسول الله ﷺ 💚 አብዱ ሰመድ
ሳያጣሩ መረጃን ማሠራጨት፣ የሰሙትን ነገር ሁሉ ለማውራት መቸኮል፣ በማያገባ ነገር ገብቶ መፈትፈት፣ እዚህም እዚያም ሄዶ መከራከር፣ አዋቂ መስሎ ለማስረዳት መሞከርና … ሌላው የጊዜው ማላ የዕኒ ነው፡፡ ዛሬ ላይ ማንን መስማት እስኪያቅተን ድረስ ሁሉም ተንታኝ፣ ሁሉም መካሪ፣ ሆኗል፡፡ የሚችለውም የማይችለውም፣ የሚያገባውም፣ የማያገባውም ይናገራል፡፡ የዚህ ዓይነቱ ባህሪ የጥሩ ሙስሊም መገለጫ አይደለም፡፡ የአንድ ሰው እስልምና ማማርን ከሚያመለክቱ ነገሮች መካከል አንዱ የማይመለከተውን ነገር መተዉ ነው፡፡ አንዳንድ ዝምታና ከሰው መገለል ጥሩ ነው፡፡ ትኩረትህን ይሰበስብላህል፡፡ ጊዜህን ሙጥጥ አድርገህ ለዉጤታማ ሥራ እንድትጠቀምበት ያግዝሃል፡፡ እናም ወዳጆቼ … ለጊዜያችን በትልቁ እንጨነቅ፡፡ እያንዳንዷን ሰከንድ በምን ላይ እንዳዋልናት መለስ ብለን እንቃኝ፡፡ ምድር ላይ የምናሳልፋትን ይህችን አጭር የሀምሳ እና ስልሳ ዓመት ዕድሜ ከተራ ብዙ ነገሮች ይልቅ ጥቂት ቋሚና ጠቃሚ ቅርሦችን እንለፍ፡፡ መዝናናት መቀለዳችንም በልክ ይሁን፡፡ መልካም ሥራችን ይብዛ ይክበድም፡፡ የነገ ሥራችን ይመዘናል እንጂ አይቆጠርም፡፡ ከመልካም ሥራ በላይም ምንም ዋስትና የለንም፡፡ አምላኬ ሆይ ! አንተን በማውሳት፣ በማመስገንና አምልኮህን በማሳመሩ ላይ እርዳኝ፡፡ አቡሱፍያን
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ ⏰ #ጁምዓ 1⃣0⃣ #ሰፈር 1⃣4⃣4⃣8⃣ ሂ
አያልፉም ያልናቸው እጅግ በጣም ብዙ ፈታኝ ጊዜያት አልፈዋል ። ዛሬ ላይ ስናስባቸው ይቀሉን ይሆናል እንጂ በወቅቱ ቀናችንን በልተው ሌሊት እንቅልፍ ነስተውናል ፣ እንይዘው እንጨብጠው አጥተናል ። ያም ሆነ ይህ ግን ፈተናው ታልፏል ፣ ጭንቀቱ ተረስቷል ። ይህ ሊሆን ግን ስንቱን አሰብን ?! ዛሬም እየተፈተንን እየተጨነቅን አለን ። እነዚህ ጊዜያትም ግን እንዳለፉት ጊዜያት ሁሉ ያልፋሉ ። ወቅትና ጊዜውን ጠብቆ መሳካቱ ላይቀር ዛሬያችንን አናበላሽ እንዲሉ አበው ከትናንት እንማር ፣ ዛሬን እንኑር ፣ ለነገ እናስምር 😉 አላህ ልባችን የሚያረጋጋበትን እርካታ ይወፍቀን ዘንዳ ሰለዋት ላይ ሙጥኝ 🤎 ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ ዓለይክ 💚 ©አብዱ ረዛቅ
ዓይኖችህን ያለ ገደብ በዘረጋህ ቁጥር ልብህ መጨነቁ የማይቀር ቋሚ ሕግ ነው ። ያየኸውን ሁሉ እየተመኘህ ካየኸው ነገር ሁሉ ጋር ራስህን እያነጻጸርክ ላየኸው ምስል፣ ፊት እና ሰዎች ለሚያሳዩት እያንዳንዱ (የውሸትም ይሁን የእውነት) ሕይወት ዓይንህን ትከፍታለህ፤ ከዚያም "ለምን እርካታ አጣሁ? ለምን ልቤ ተጨነቀ?" ብለህ ትጠይቃለህ። ልብ እኮ ብረት አይደለም ልብ ይሞላል፣ ይበከላል፣ ይደክማል፣ ይለምዳልም። የዕይታህን በር ባሰፋህ ቁጥር በእጅህ ያለው ጸጋ ባንተ ላይ እየጠበበ እና እየቀለለ ይመጣል በዚህ ጊዜ ሚስትህ አታረካህም፣ ባልሽ አይበቃሽም፣ ቤትህ አይሞላልህም፣ መልክህ አይማርክህም፣ ሕይወትህም አያስደስትህም ። ለምን መሰለህ? ምክንያቱም ዓይኖችህ በንጽጽር ውስጥ መሮጥን፣ መቅበዝበዝን እና ሁልጊዜ "ተጨማሪ" መፈለግን ስለለመዱ ነው ። ሰው ያለ ምንም ገደብ ዓይኑን ከዘረጋ ዓለምን እንኳ ቢገዛ አይጠግብም አንዳንዶችን ተመልከት መልካም፣ ሐቅን የምትጠብቅና ቆንጆ ሚስት አለው ቤት፣ ሰላምና እረፍትም አለው ነገር ግን ዓይኑ ያለገደብ ስለሚዘረጋ አይጠግብም ባለው ነገር አይረካም ጸጋው እያለው እርካታውን በገዛ እጁ ያጣል ። ሴቶችም በተመሳሳይ በራሳቸው ላይ የንጽጽርን በር ሲከፍቱ ታያለህ፦ "እገሌ ከእኔ ትበልጣለች፣ እገሌ ሕይወቷ የተደላደለ ነው፣ የእገሌ ባል የተሻለ ነው" እያሉ ሰላም የነበረውን ቤታቸውንና ሕይወታቸውን ወደ ጭንቀት፣ ወደ ማማረርና ወደ መቆጨት ይቀይሩታል ። ወንዶችም ዓይኖቻቸውን ለሁሉም ሴቶች፣ ለሁሉም ቪዲዮዎችና ለሁሉም የተከለከሉ ግንኙነቶች ይከፍታሉ ከዚያ በኋላ በሚስታቸው ላይ ውበትን፣ በሐላል (በተፈቀደው) ውስጥ እረፍትን፣ በምንም ነገር ላይ ደግሞ እርካታን ማየት ያቅታቸዋል። ለዚህ እኮ ነው ዓይንን መስበር (በኢስላም) በከንቱ ያልታዘዘው አላህ ጀለ ጀላሉሁ ዓይን በልብ ላይ ምን አደጋ እንደምታደርስ ጠንቅቆ ያውቃል አንዲት ትንሽ እይታ እንዴት ወደ ጭንቀት፣ ከዚያም ወደ ባዶነት፣ ቀጥሎ ወደ ማማረር እና በመጨረሻም ወደ ግንኙነቶች መፈራረስ እንደምትቀየር ያውቃል እውነተኛ እርካታ የሚመጣው የምታየውን ነገር መቆጣጠር ስትችል ብቻ ነው ። ለዚህም ነው አይናችንን እንድንሰብር ያዘዘው አላህ ጀለ ጀላሉሁ እንዲህ ይላል "ለምእመናን ንገራቸው፦ ዓይኖቻቸውን (ያልተፈቀደን ከማየት) ይከልክሉ፤ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፤ ይህ ለነሱ ይበልጥ ንጹህ ነው። ለምእመናትም ንገራቸው፦ ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፤ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ።" (አል-ኑር: 30-31) ©Ramzi
አስቸኳይ አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላህ አዲስ አበባ እና ለአዲስ አበባ ቀርብ በሆኑ 30 መስጂዶች ወስዶ መልዕክት የሚያደርስልን ሰው እንፈልጋለን። ያደረሰውን መልዕክት በቪድዮ እና በፎቶ ማቅረብ የሚችል 0996887867 0983828579 ኑረይን ህትመት እና ማስታወቂያ
ክፍት የስራ ማስታወቂያ የስራ መደብ፦ የግራፊክስ ዲዛይን ሙያ ያላትና እና ማንኛውም የማተሚያ ቤት ስራ ለመስራት ዝግጁ የሆነች ※ ልምድ፦ 0 አመት(ከዚህ በፊት ማተሚያ ቤት የሰራች ቢሆን ይመረጣል) ※ አድራሻ፦ አየርጤና አደባባይ ※ የስራ ሰዐት:- ከጠዋቱ 2:00 እስከ የመጝሪብ ሰላት ተሰግዶ እስከሚያልቅበት ሰዐት ※ ደመወዝ፦ በስምምነት ※ ፆታ፦ ሴት ※ መኖርያዋ ለስራ ቦታዋ ቅርብ የሆነች ኢንቦክስ…
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ ⏰ #አልስነይን 0⃣1⃣ #ዙልሒጃ 1⃣4⃣4⃣7⃣ ሂ
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ ⏰#ሰብት 1⃣5⃣ #ዙልቀዓዳ 1⃣4⃣4⃣7⃣ ሂ
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ ⏰ #አልስነይን 1⃣0⃣ #ዙልቀዓዳ 1⃣4⃣4⃣7⃣ ሂ
без подписи
без подписи