ISLAMIC SCHOOL
Статистика✍ ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..! ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤ የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡ 🎖For any comment t.me/AnuSeu 💠Another channal @IslamisUniverstiy_public_group
- Последний пост
- 11 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 37
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 363
- 1/48двое суток
- 415
- 1/72трое суток
- 448
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
🎖🎖✋ #ሰላምታህ_የሰላም_ይሁን✋🎖🎖 ✍🏼አሚር ሰይድ ወዳጄ ሆይ! አሁንም ወደፊትም ልብህን አፅዳ፡፡ ደስተኛ ሕይወት ትኖራለህ፡፡ ቀለል ብሎህ ውለህ ታድራለህ፡፡ እፎይ ብለህ ትተኛለህ። አዎን ውስጥህን አፅዳ፡፡ ☞ በውስጥህ እየተራገምክ በአንደበትህ አትመርቅ። ☞ በልብህ እያጉረመረምክ በንግግር አታታልል፡፡ ሠላምታህ የሠላም ይሁን፡፡ ቃልህ የፍቅር ይሁን፡፡ ከአሽሙርና ከማሽሟጠጥ ተጠንቀቅ። ☞ ወዳጄ ሆይ በነገር እየወጋህ አትሸንግል፡፡ የጎሪጥ እያወራህ አታስመስል፡፡ የቱን ያህል ብትበደልም በወንድምህ ላይ የጥላቻ ክስ አትመስርት፣ በባልንጀራህ ላይ የውሸት ፋይል አትክፈት፤ በጓደኛህ ላይ የግፍ ጦር አታንሳ፡፡ ☞ ጠላትን የመጠንቀቁ ነገር እንዳለ ሆኖ ስለሰው መልካም ነገር እንጂ አታስብ፡፡ ጥሩ በማሰብህ ትክክል ከሆንክ ጥሩ ምንዳ ታገኛለህ።መጥፎ አስበህ ከሆነ ደግሞ በመጥፎ ጥርጣሬ ወንጀል ላይ ትወድቃለህ። ⚡️⚡️ከሰዎች መካከል እንዲሁ ከመሬት ተነስተው በውስጣቸው ለያንዳንዱ የሰው ልጅ የመገምገሚያ ኬላዎችንና የፍተሻ ጣቢያዎችን የሚያቋቁሙ አሉ፡፡ ይህች አጭር እድሜያችን ለዚህ ሁሉ የምትበቃ አይደለችም። በመሆኑም እጅግ ውድ የሆነው እድሜህን፣ እጅግ አጭር የሆነችውን ጊዜህን ውድ ለሆነው ፍቅር እንጂ ርካሽ ለሆነው ጠላትነት መስጠት የለብህም ሐቢቢ…፡፡ ☞ ወዳጄ ሆይ! ውስጥህ የጥላቻና የተንኮል ወደብ የሆነ እንደሆነ፣ በምድር ላይ ቆይታህ ሴራ ብቻ የምትጎነጉን ከሆነ በገዛ እጅህ መርዝ እየተጋትክ መሆነን እወቅ፡፡ ይቅር ባይነትና ትእግስት ጠላትን ለመጋፈጥ ትልቁ መሳሪያ ሆኖ ሣለ ቸኩለህ በደል የምትፈፅም ከሆነ ሽንፈትን እንጂ ድልን እትጎናፀፍም፡፡ ውድቀት እንጂ ስኬት አታገኝም፡፡ ሀቢቢ በጉልበትህ፣ በገንዘብህና በወገኖችህ ከምትተማመነውና ከምትታገዘው በላይ በይቅርታና ትእግስት በማድረግህ አላህ (ሱ.ወ) የበለጠ ያግዝሃል። ✏️ህልም አለኝ ከሚለዉ ሙሀመድ ሰይድ መፅሀፍ የተዘጋጀ Join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group t.me/IslamisUniverstiy_public_group
📕📕 ሐሰነ ልአ-በስሪ አላህ አዛኝ ነዉ ብለዉ ለሚዘነጉ ሰዎች ይሄን ምክር ጀባ ብለዉ አልፈዋል፡- “ምህረት እናገኛለን በሚል አጉል ምኞት ተሞልተው አንዳች በጎ ስራ ሳይኖራቸው ከዱንያ ዓለም የወጡ ሰዎች አሉ። እንዲህም ሲሉ ራሳቸውን ያታልላሉ፡-በታላቁ ጌታዬ ላይ በጎ ጥርጣሬ አለኝ። በጎ ስራዬ በዛም አነሰም ግድ የለኝም። በግርጥም እንዲህ የሚል ሰው ዋሽቷል። ምክንያቱም በጌታው ላይ በጎ ጥርጣሬ በርግጥ ቢኖረው ኖሮ ስራውን ያሳምር ነበርና። አላህ (ሱ ወ) እንዲህ ይላል። { وَذَ ٰلِكُمۡ ظَنُّكُمُ ٱلَّذِی ظَنَنتُم بِرَبِّكُمۡ أَرۡدَىٰكُمۡ فَأَصۡبَحۡتُم مِّنَ ٱلۡخَـٰسِرِینَ } “ይህም ያ በጌታችሁ የጠረጠራችሁት ጥርጣሪያችሁ አጠፋችሁ። ከከሳሪዎቹም ኾናችሁ ( ይባላሉ) ። (ፉሲለት23) 📒📒 በተጨማሪ ደግሞ የሕያ ኢብን ሙዓዝ እንዲህ ይላሉ፡- ☞ከሽንገላ ሁሉ ትልቁ ሽንገላ ራስን መሸንገል ነው፤ ይቅርታን ተስፋ በማድረግ ያለ ምንም ፀፀት በወንጀል ላይ ለረጅም ጊዜ መቆየት ነው፤ ☞አላህን ያለመታዘዝ ወደ አላህ መቃረብን መመኘት ነው፤ ☞የጀሀነም ዘርን ዘርቶ የጀነትን አዝርዕት መጠባበቅ ነው፤ ☞ወንጀል ላይ ተዘፍቆ አላህን የታዘዙ የአላህ ባሮች የሚገቡበትን ጀነት መመኘት ነው፤ ☞ስራ ሳይሰሩ ደመወዝን መጠበቅ ነው፤ በአጠቃላይ ከኸይር ስራ ሙሉ ለሙሉ ርቆ በአላህ ላይ ከንቱ ምኞት መመኘት ነው።” 📗📗አቡ ሓሚድ አል-ገዛሊ በመደጋገም ይሄን ዱዓ ያደርጉ ነበር፦ “ጌታዬ ሆይ! የማይሰሩትን ከሚናገሩ ሰዎች አታድርገን፤ ከሚሰሙ ግን ከማይቀበሉ ሰዎች አትደምረን፤ይሉ ነበር ❤️❤️❤️ ዛሬ የጁምአ ለይል ነዉ ዱንያዉም እንዲሰምር አኼራዉም እንዲያምር ነገ የቀብሩ ጥበት እንዲሰፋ የቀብሩ ጨለማ እንዲበራ... ነፍስያችንን ለመግራት ከቆሻሻ ነፍስያ ለመንጣት ...ነፍስያ ለመግራት ምክንያት እንዲሆነን... የዛ ቀን ጥም በሚበረታበት ሀዉድ በእጃቸዉ ከምንጠጣዉ እንዲያደርገን አላህ እሱን ወዶ ሁሉን ያስወደደዉ ለከዉኑ አይነታ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ሶለዋት እናዉርድ { إِنَّ ٱللَّهَ وَمَلَـٰۤىِٕكَتَهُۥ یُصَلُّونَ عَلَى ٱلنَّبِیِّۚ یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ صَلُّوا۟ عَلَیۡهِ وَسَلِّمُوا۟ تَسۡلِیمًا } አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡(አል አህዛብ 56) ሶሉ አለል ሀቢብ ሰይዲና ሙሀመድﷺﷺ💚💚💚 🌙✨መልካም ኸሚስ ምሽት 🌙✨ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ وَبَارِكْ عَلَى سَيِّدِنَا مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِهِ وَصَحْبِهِ أَجْمَعِينَ 💚💚💚💚💚 ®Amir seid Join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group t.me/IslamisUniverstiy_public_group
🔥🔥 #ያቺ_የምትንቀለቀል_እሳት🔥🔥 ✍🏼 አሚር ሰይድ ዐሊይ አቡጧሊብ ከዕለታት አንድ ቀን ኩመይል ከሚባል ሰዉ ጋር ወደ መቃብር ቦታ አመሩ፤ እዚያ እንደ ደረሱም እንዲህ አሉ፡- "...እናንተ የመቃብር ነዋሪዎች ሆይ! እናንተ አካላችሁ ወደ ብናኝ የተቀየረ ሰዎች ሆይ እናንተ የብቸኝነት ባለቤቶች ሆይ! ..እናንተ ዘንድ ያለው ዜና ምን ይሆን? እኛ ዘንድ ያለዉ ዜና ☞ ንብረታችሁ ለወራሾች ተከፋፍሏል ☞ ልጆቻችሁ የቲሞች ሆነዋል፤ ☞አሳዳጊ አልባ ሆነው ቀርተዋል፤ ☞ሚስቶቻችሁን ሌሎች ሰዎች አግብተዋል። ይህ እኛ ጋ ያለው ዜና ነው፤ እናንተ ጋ ያለው ዜና ምን ይሆ?!" ይህንን ካሉ በኋላ ወደ እኔ ዘወር ብለው፦ “አንተ ኩመይል ሆይ .... ሙታኑ መልስ እንዲሰጡ ቢፈቀድላቸው ኖሮ ' #ከስንቅ_ሁሉ_በላጩ_አላህን_መፍራት_ነው!' የሚል ምላሽ ይሰጡን ነበር።” አሉኝ። ዐሊይ ይህንን ተናግረው ተንሰቅስቀው አለቀሱ😢። አስከተሉና እንዲህ ሲሉ ምክራቸውን ለገሱኝ፦ “ኩመይል ሆይ! መቃብር የስራ ሳንዱቅ ነው፤ ውስጡ ያለውን ዜና የምታውቀው የሞትክ ዕለት ነው።” (ሐያቱ ሶሐባ፤ ካንደህለዊይ) ⚡️⚡️⚡️ ከቀብር ቡሀላ ያለዉ ህይወት እና የጀሀነም እሳት ያሳሰባቸዉ ዑመር ኢብን ዐብደል አዚዝ ..ከዕለታት በአንድ ሌሊት ሰዎች በተሰበሰቡበት የአል-ለይል ምዕራፍን አነበቡ:- { وَٱلَّیۡلِ إِذَا یَغۡشَىٰ (1 ) وَٱلنَّهَارِ إِذَا تَجَلَّىٰ (2) وَمَا خَلَقَ ٱلذَّكَرَ وَٱلۡأُنثَىٰۤ (3) إِنَّ سَعۡیَكُمۡ لَشَتَّىٰ (4) فَأَمَّا مَنۡ أَعۡطَىٰ وَٱتَّقَىٰ (5) وَصَدَّقَ بِٱلۡحُسۡنَىٰ (6) فَسَنُیَسِّرُهُۥ لِلۡیُسۡرَىٰ (7) وَأَمَّا مَنۢ بَخِلَ وَٱسۡتَغۡنَىٰ (8) وَكَذَّبَ بِٱلۡحُسۡنَىٰ (9) فَسَنُیَسِّرُهُۥ لِلۡعُسۡرَىٰ (10) وَمَا یُغۡنِی عَنۡهُ مَالُهُۥۤ إِذَا تَرَدَّىٰۤ (11) إِنَّ عَلَیۡنَا لَلۡهُدَىٰ (12) وَإِنَّ لَنَا لَلۡـَٔاخِرَةَ وَٱلۡأُولَىٰ (13) فَأَنذَرۡتُكُمۡ نَارࣰا تَلَظَّىٰ (14) } “በሌሊቱ እምላለሁ፤ በፅልመቱ ፍጡራንን በሚሸፍን ጊዜ፣ በቀኑም በገተለፀ ጊዜ፣.......... የምትንቀለቀልንም እሳት አስጠነቀቅኳችሁ በላቸው) (አል ለይል፡ 1-14) ዑመር “የምትንቀለቀልንም እሳት አስጠነቀቅኳችሁ በላቸው)::" የሚለውን የምዕራፉን ክፍል ሲያነቡ እንባ ተናነቃቸው። አንቀፁን ማጠናቀቅ አልቻሉም። ድጋሚ ወደ ምዕራፉ መጀመሪያ ክፍል ተመለሱ። ማንበባቸውንም ቀጥለው “የምትንቀለቀልንም እሳት አስጠነቀቅኳችሁ በላቸው ።" የሚለው አንቀፅ ላይ ሲደርሱ አሁንም ይንሰቀሰቁ ጀመር😢። ይህችን አንቀፅ ማለፍ አልቻሉም። በመጨረሻም ምዕራፉን ትተው ሌላ ምዕራፍ ማንበብ ጀመሩ። ✏️ነገ ወይ ዛሬ ሞት እያለና ...ያቺ የምትንቀለቀል እሳት እኛን ምን ያህል አሳስቦን ለይለ ተነስተን አልቅሰናል??ምን ያህል ሰደቃ ሰጥተናል??ምን ያህል የሰዉ ሀቅ ላይ ጠንቃቃ ሁነናል?? ግን እኛ የምንኖረዉ አኗኗር ቆም ብለን አስበንዋል?? ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺሁላችሁም እንዳኗኗራችሁ ትሞታላችሁ እንዳሟሟታችሁ ትቀሰቀሳላችሁ ያሉንን ሀዲስ ምን ያህል አስተንትነንዋል?? 🎖🎖 ወሀብ ኢብኑ ሙነበህ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- ብልህ የሆነ ሰው ከአራት ጊዜያቶች መዘናጋት የለበትም:: ➊ ከአላህ ጋርተገልሎ ጉዳዩን ለሱ የሚነግርበት ጊዜ፣ ➋ስለ አጠቃላይ ሁኔታው ራሱን የሚመረምርበት ጊዜ፣ ➌ስለ እውነት ብለው ጥፋቱንና እንከኑን ከሚነግሩት ጓደኞቹ ጋር የሚገለልበት ጊዜ እና ➍ከራሱ ነፍስ ጋር ብቻውን ተገልሎ የሚያምራት እና የምትፈልገውን ነገር ከሷ የሚያቅበበት ጊዜ፡፡ እነኚህ ሰዓታት ለነዚያ የትንሳኤ ቀን ሰዓታት ያግዙታል፡፡ ቀልቡንም ያበሩለታል፡፡ ብልህ ሰው በሶስት ነገሮች ላይየዘወትር ትኩረቱን ያደርጋል፡- ▶️ ለነፍሱ የሚሰንቅበት ጊዜያት፣ ▶️ ለምድር ላይ ኑሮው የሚሰራበት ጊዜያት እና ▶️ ሐራም ባልሆነ ነገር ላይ የሚዝናናበት ጊዜያት፡፡ ብልህ የሆነ ሰው ያለበትን ዘመን ሁኔታ የሚያውቅ፤ ምላሱን የሚጠብቅ፣ አጠቃላይ ሁኔታውን የሚመረምር መሆን ይኖርበታል፡፡ ብለዋል Join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group t.me/IslamisUniverstiy_public_group
👐 #አለይከ_ረበና_ቢሁስኒል_ሂታሚ ✍ አሚር ሰይድ “ግብፅ ውስጥ አንድ ሰው ነበር ይባላል። ይህ ሰው የመስጂድ ሙአዚን በመሆኑና ከጀመዓ ሶላት ባለመጥፋቱ ይታወቃል። ከዕለታት በአንዱ ቀን እንደተለመደው አዛን ለማለት ወደ ሚናራ ይወጣል። ከሚናራው ስር የሚኖር የአንድ ክርስቲያን ግለሰብ ቤት ይገኛል። ይህ ሙአዚን ዓይኑን ወደ ቤቱ ሲወረወር የባለቤቱን ሴት ልጅ ይመለከታል። በውበቷ በእጅጉ በመፈተኑ አዛን ማለቱን ትቶ ከሚናራው ወረደ። ወደ ቤቷም አመራ። በሩን አንኳኳ። ምን ፈልገህ ነው?' ስትል ጠየቀችው። 'የፈለግኩት አንቺን ነው' ሲል መለሰ። ልጅቱም: 'ለምን ፈለግከኝ?' ስትል ጠየቀችው። እርሱም: "ልቤን ተቆጣጥረሽዋል፤ ልቦናዬን ሰልበሽዋል' ሲል መለሰ። ልጅቱም 'ለዝሙት ፈቃደኛ አይደለሁም' አለችው። ሰውዬውም:-ላገባሽ ዝግጁ ነኝ” አላት። "አንተ ሙስሊም ነህ፤ እኔ ደግሞ ክርስቲያን:: አባቴ አንተን እንዳገባ ፈቃደኛ አይሆንም”አለችዉ "ክርስቲያን እሆናለሁ” የሚል ነበር የሰውዬው መልስ። እርሷም፡- "ይህንን ማድረግ ከቻልክ እኔም ሚስትህ እሆናለሁ” ስትል ፈቃደኝነቷን ገለፀች። ከዚያም ሰውዬው እርሷን ለማግኘት ባለው ከፍተኛ ጉጉት ምክኒያት እምነቱን ቀየረ። ከቤተሰቦቿ ጋርም መኖር ጀመረ። ጋብቻውን በፈፀመበት ሰሞን ወደ ጣሪያ ላይ ወጣ። ከጣሪያዉም ድንገት ወደቀና ህይወቱ አለፈች😔። ይህ ሰው ዲኑን አጣ። እርሷንም አላገኘ። ከአጨራረስ ክፋት ደጋግመን በአላህ እንጠበቃለን!!። ለዚህም ነው የአላህ መልዕክተኛ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ የሚከተለውን ምክር ጀባ ብለዉናል፦ “አጨራረሱን ሳትመለክቱ በአንድ ሰው ስራ አትደነቁ።' ( አጥ-ጦበራኒ) Join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group t.me/IslamisUniverstiy_public_group
🏅🏅#የጀመአና_ሶላትና_እኛስ??🏅🏅 ✍🏽 አሚር ሰይድ ዓይነ ስውር የነበረው ኢብኑ ኡሙ መክቱም ሰይዲና ሙሀመድ ﷺን በቤቱ እንዲሰግድ ፈቃድ ጠየቀ። ..ነቢዩ ﷺ እንዲህ አሉት፦ هَلْ تَسْمَعُ النِّدَاءَ بِالصَّلَاةِ؟ "የሶላትን ጥሪ (አዛን) ትሰማለህ?" "አዎ" ባለ ጊዜ "እንግዲያ ጥሪውን ተቀበል ወደ መስጊድ መጥተህ ስገድ አሉት 🟢🟢.....ዛሬ ላይ ከኔ ጀምሮ ጀመአ ሶላት ለመስገድ አይናችን እያየ ግን ልባችን ጨልሟል፡፡ ለአይነ ስዉሩ ኢብኑ መክቱም እቤቱ እንዲሰግድ ፍቃድ ያላገኘዉ የእኛ እቤት ለመስገድ ማን ፍቃድ እንደሰጠንና ለፍረዱ ቀን ምን አይነት ኡዙር እንደምንሰጥ ግራ ያጋባል ወገን፡፡ ታዳ የበፊት ምርጥ ትዉልዶች ለጀመአ ሶላት ያላቸዉ ክብር የተወሰኑትን በዱንያ ያሳለፉትን ሀል ስናወሳ ✏️ ታዋቂው የሐዲሥ ሊቅ ቢሽር ኢብን አል-ሐሰን “አሱ ሶፍፊይ” - የሚል ቅፅል ስም ነበራቸው። ለሀምሳ ዓመታት ያህል የመጀመሪያው ሶፍ አምልጧቸው አያውቅም ነበር። ✏️ በተመሳሳይ መልኩ ኢብራሂይም ኢብን መይሙን ይወሳሉ። የአንጥረኝነት ባለሙያ ነበሩ። መዶሻቸውን አንስተው እያለ አዛን ከሰሙ ባለበት ያቆሙት ነበር። ✏️ የሶሪያው ዋነኛ ዳኛ ሱለይማን ኢብን ሀምዘተል መቅዲሲይ እንዲህ ይላሉ፦ "የግዴታ ሶላቶችን ብቻዬን የሰገድኩት ሁለት ጊዜ ብቻ ነው። እነርሱን ሶላቶች በርግጥ እንዳልሰገድኳቸው ይሰማኛል።” ይህንን ሲሉ እድሜያቸው ወደ ዘጠና ተቃርቦ ነበር። ✏️✏️ የቡኻሪና የሙስሊም መምህር የነበሩት ዑበይደላህ ኢብን ዑመር አልቀዋሪይሪ እንዲህ ይተርኩልናል፦ “የዒሻእ ሶላት ጀመዓ አምልጦኝ አያውቅም ነበር፡፡ አንዲት ሌሊት እንግዳ ቤቴ አረፈ። እርሱን በማስተናገድ ተጠመድኩ፡፡ የዒሻ ጀማዓ ሶላት አለፈኝ። በስራ ከተማ ውስጥ ያሉ መስጅዶችን እየዞርኩ ጀመዓ ፍለጋ ማሰንኩ። ሁሉም መስጅዶች ጀመዓ ተሰግዶ መስጅዶቹም ተዘግተዋል። ወደ ቤቴ ተመለስኩ። ለራሴ እንዲህ እልኩ። ሶላተል ጀመዓ በተናጠል ከሚሰገድ ሶላት በሃያ ሰባት ደረጃ እንደሚበልጥ በሐዲስ ተነግሯል።' የዒሻእ ሶላትን ሀያ ሰባት ጊዜ ሰገድኩ። ከዚያም ተኛሁ። በህልሜ ሰዎች ጋር የፈረስ ውድድር እያደረግኩ ተመለከትኩ። ፈረሴን በፍጥነት እጋልባለሁ፤ ግን ልደርስባቸው አልቻልኩም ከነርሱ መካከል አንዱ ወደኔ ዘወር አለና፦ 'ፈረስህን አታድክመው፤ ልትደርስብን አትችልም።' አለኝ። 'ለምን?' እልኩት። 'እኛ ዒሻእን በጀመዓ ሰግደናል፤ አንተ ግን ብቻህን ነው የሰገድከው' አለኝ። በከፍተኛ ሃዘንና ጭንቀት ላይ ስሆን ከእንቅልፌ ነቃሁ።" ብለዉ ጀመአ ሶላት ያለፈባቸዉን ይቆጫሉ... እኛስ የጀመአ ሶላት ጋር ያለን ቁርኝነት ምን ያህል እንደሆነ ራሳችንን ብንፈትለሽ መልካም ነዉ Join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group t.me/IslamisUniverstiy_public_group
🎖🎖🎖 #ከሞኝ_ሰዉ_ራቅ🎖🎖🎖 አንድ ሰው ነቢዩ ዒሳን በከፍተኛ ፍጥነት ሲሮጡ ያያቸውና የአምላክ መልዕክተኛ ሆይ! ከአንበሳ ወይም ከጠላት እየሸሹ አይደለም፤ ለምን እንዲህ ይሮጣሉ? ብሎ ይጠይቃቸዋል። ነቢዩ ዒሳም፦ከሞኝ ሰው እሸሻለሁ! ብለው መለሱለት። ሰውየውም በመገረም፦እርስዎ ዕውሮችን የሚያበሩ፣ ሙታንን በአላህ ፈቃድ የሚያስነሱ አይደሉምን? ታዲያ የሞኝን ሰው ልብ ማከም አይችሉምን? አላቸው። ነቢዩ ዒሳ እንዲህ አሉት ፦ በአምላክ ስም እምላለሁ፤ በሙታን ላይ የጸለይኩትን ጸሎት በሞኝ ሰው ላይ ደጋገምኩት፤ ነገር ግን ምንም ለውጥ አላመጣም። ምክንያቱም የሞኝነት በሽታ የአምላክ ቁጣ(ቅጣት) ነው፤ ዕውርነት ግን ፈተና ብቻ ነው። ፈተና እረፍት እና እውቀትን ያመጣል፤ ሞኝነት ግን ሌሎችንም ያቆስላል። መልእክቱ ከሞኝ ሰው መራቅ ራስን ከመመረዝ መጠበቅ ነው። የሞኝ ሰው ጓደኝነት ቀስ በቀስ የአንተንም አእምሮ ያደነዝዘዋል። ®Amir seid Join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group t.me/IslamisUniverstiy_public_group
✋ አሰላሙ አለይኩም እንዴት ናችሁ አንድ አመት ወንጀልን የሚያብሰዉ የአላህ እዝነት ወር የሆነዉ የአሹራ ፆም አደረሰን፡፡ ፁመዉ ከሚጠቀሙት ባርያዎቹ ያድርገን :: የዘንድሮው የዐሹራ ፆም የሙሐረም 10ኛው ቀን ሐሙስ ሰኔ 18 ነዉ፡፡ ✏️ አሹራ ፆሙን ከፆምን አይቀር ይሄን ሱና ብንከተል አትራፊ ነን... 10 ቀን ብቻ ከመፆም ከአስረኛዉ ቀን በፊት ያለዉን አንድ ቀን መጨመር ወይም ከአስራኛዉ ቀን ተከታይ ያለዉን አስከትለን መፆሙ በላጭ ነዉ ፡፡ አስረኛዉን ብቻ ፁመን ባንተዉ ጥሩ ነዉ፡፡ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺአይሁዶችን ለመለየት ዘጠነኛውንም ቀን አብሮ ለመፆም አስበው ስለነበር፣ በላጩ መንገድ ረቡዕ ሰኔ 17 እና ሐሙስን ሰኔ 18 አከታትሎ መፆም ነው። 🟢 #በተጨማሪ አሹራ ፆም ፍጥሪያ ሰአት ላይ የዘነጋነዉ ነገር አለ:: እነዚህን የአለም እዝነት ራህመት የሆኑትን የነብዩ ﷺ ንግግር ላስታዉሳችሁ:- - عن أبي سعيد الخدري قال: قال رسول الله ﷺ: «من وسع على أهله في يوم عاشوراء وسع الله عليه سائر سنته كلها». >>>>> አቢ ሰኢድ አልሁድሪ እንደዘገበዉ ሀቢቡና ሙሀመድ እንዲህ ብለዋል፡- "በዓሹራ ቀን በቤተሰቡ ላይ ሰፊ (ለጋስ) የሆነ ሰው፣ አላህ ቀሪውን ዓመቱን በሰፊ ሲሳይ ያኖረዋል።" በሌላ ዘገባ ደግሞ >>>>> አብደሏህ ኢብኑ መስኡድ ረዐ እንዳስተላለፈዉ ነብዩ ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ብሎ አስተላልፏል مَن وَسَّعَ عَلَى عِيَالِهِ يَوْمَ عَاشُورَاءَ لَمْ يَزَلْ فِي سَعَةٍ سَائِرَ سَنَتِهِ. በዐሹራ ቀን በቤተሰቡ ላይ ለጋስ የሆነ ሰው፣ አላህ በቀሪው ዓመት ሁሉ ለእርሱ ስፋትና በረከት ያደርግለታል።" ብለዋል እነዚህ ሀዲሶች እንደሚጠቁሙን በዓሹራ ቀን በቤተሰቡ ላይ ሰፊ (ለጋስ) የሆነ ሰው፣ አላህ ዓመቱን ሙሉ በሰፊ ሲሳይ በረከት ያደርግልታል...በሲሳይ ያኖረዋል ማለት፦ 🏅🏅 በዓሹራ ቀን ማለትም ሙሐረም 10 ቀን ላይ ፍጥሪያ ሰአት ላይ ፁመህ ዉለህ እቤትህ ስትግባ ለቤተሰብህ ከወትሮዉ በተለየ ✔ #በምግብ ለምሳሌ ፍራፍሬ ነገሮችን ሙዝ ቡርትካን ማንጎ ወዘተ መግዛት..ከተቻለ እቤት ካለ ስጋ መስራት ወይም ከእስከዛሬ ከሚጠቀሙት ምግብ የተለየ ማዘጋጀት፡ የምግብ ሱፍዉን በሩዙ በተለያየ ነገር አሳምሮ ለፍጥሪያ ማቅረብ ✔ #በመጠጥ፣ ለምሳሌ ከዉሀ ዉጭ ያሉ ነገሮችን ማዘጋጀት ሁሉም እንደ አቅሙ ማር ያለዉ ብርዝ የሌለዉ እስታር ወይም ሌላ የሚጠጣ በአቅም ማዘጋጀት እንደማለት ነዉ ✔ #ልብስ ልብስ ማለት ለሚስትህ ቀለል ያለች ክሪም ወይ ቢጃማ ሊሆን ይችላል፡፡ ለልጆችህ ሴት ከሆነች የቅናሽ ክሪም..ለወንድ ልጅህ ዋጋዉ ቀላል ሽቶ ወይ ጥምጣም ...ለእናት ለአባትህም ስጦታ ማዘጋጀት ነዉ፡፡ ይህ ማለት አንተን በሚጎዳ ሳይሆን በቻልከዉ ነገር ወይም በሚችልህ መጠን ተጨማሪ ደስታ እንድታደርግላቸው ያበረታታል። ልትነገዘብ የሚገባዉ በብድር ገብቶ ወይም ከአቅሙ በላይ ወጪ እንዲያደርግ አይደለም። ዋናው መልዕክት ቤተሰብን ማስደሰት፣ ልግስናን ማሳየት እና በአላህ በረከት መተማመን ነው። አላህ ለእንዲህ ያለ ሰው በሪዝቁ (ሲሳይ) ውስጥ በረከት እንደሚያደርግለት ይጠቁማል። በሙሐረም 10 (አሹራ) ቀን አንድ ሰው ለቤተሰቡ የተሻለ ምግብ፣ ልብስ፣ ስጦታ ወይም ሌላ የሚችለውን በመስጠት ደስ ቢያሰኛቸው፣ አላህም በዚያ በረከት ምክንያት በዓመቱ ውስጥ በሪዝቁና በበረከት እንደሚያሰፋለት እርግጥ ነዉ ። 😎 #ላጤ_ሆይ!!! እስኪ ይሄን ቀን ፁመህ ዉለህ ለእናትህ ለአባትህ ስጦታ ይዘህ ሂደህ ዱአ አርጉልኝ እርዚቄ በረከቴ እንዲሰፋ...ዱንያ አኼራ ማሳመሪዬ ሀላሌን ብለህ ዱአ አስደርግ እርግጥ ነዉ ታተርፋለህ 🫣 #ላጢት_ሆይ በአሹራዉ ቀን ማታ እንደ ኢድና አረፋ በአል ማታ ላይ ቤቱን ፏ ሽብርቅ አርገሽ የደስታ ቤት አስመስይዉና እናት አባትሽን የጀነት መንገዴን ወገቡ ያልታሸ ኪሱ ያልተመታ ትዳር አምጣ ብለሽ ዱአ አስደርጊ፡፡😊 ዑለማዎች በዓሹራ ቀን ቤተሰብን ማስደሰትና ለጋስ መሆን የሚመከር ተግባር መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ትላልቅ መሻኢኾች ይህንን ሀዲስ በተግባር ላይ አዉለዉት እንደተጠቀሙበት ትርፉን የሀዲሱን በረከት ሲሳይ እንደአገኙበት ተናግረዋል፡፡ እኛም ኢንሻ አላህ የአሁኑ አሹራ ላይ እንሞክረዋለን ሼር አድርጋችሁ ለወዳጅ ዘመድ ያድርሱ ___ ®Amir seid Join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group t.me/IslamisUniverstiy_public_group
🎖🎖 #ባንዲራዉን_በድል_ማዉለብለብ🎖🎖 ✍🏼 አሚር ሰይድ አላህ በተከበረ ቅዱስ ቃሉ እንዲህ ብሎ ከሸይጧን ተንኮል እንድንጠበቅ አዞናል፡- { یَـٰبَنِیۤ ءَادَمَ لَا یَفۡتِنَنَّكُمُ ٱلشَّیۡطَـٰنُ كَمَاۤ أَخۡرَجَ أَبَوَیۡكُم مِّنَ ٱلۡجَنَّةِ یَنزِعُ عَنۡهُمَا لِبَاسَهُمَا لِیُرِیَهُمَا سَوۡءَ ٰ تِهِمَاۤۚ إِنَّهُۥ یَرَىٰكُمۡ هُوَ وَقَبِیلُهُۥ مِنۡ حَیۡثُ لَا تَرَوۡنَهُمۡۗ إِنَّا جَعَلۡنَا ٱلشَّیَـٰطِینَ أَوۡلِیَاۤءَ لِلَّذِینَ لَا یُؤۡمِنُونَ } የአዳም ልጆች ሆይ! ሰይጣን አባትና እናታችሁን ኀፍረተ ገላቸውን ሊያሳያቸው ልብሶቻቸውን ከነሱ የገፈፋቸው ሲኾን ከገነት እንዳወጣቸው ሁሉ እናንተን አይሞክራችሁ፡፡ እነሆ እርሱ ከነሰራዊቱ ከማታዩዋቸው ስፍራ ያዩዋችኋልና፡፡ እኛ ሰይጣናትን ለእነዚያ ለማያምኑት ወዳጆች አድርገናል፡፡ (አል-አዕራፍ ፡ 27) ⚡️⚡️ አላህን የመገዛት ፍቅር በልብ ላይ ኃይል ሲያገኝ መላኢካ ፊት ለፊት መጥቶ መነቃቃትን ይፈጥራል። በአንድ ሰው ልብ ውስጥ በመላኢካና በሸይጧን መካከል ያለው ውድድር ሁሌም ይኖራል፤ አንዱ የሌላኛውን ቦታ እስከሚቆጣጠርና ባንዲራውን በድል እስኪያውለበልብ ድረስ።ታዳ የኛን ልብ መላኢካ ነዉ ወይስ ሸይጧን ነዉ የተቆጣጠረን ብለን አስበን አስተዉለን ኢማናችንን ፈትሸን እናቃለን ወይ?? ይህንን አስመልክተው ሀቢቡና ሰይዲና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ “አንድ ሰው ከቤቱ አይወጣም ቤቱ በር ላይ ሁለት ባንዲራዎች ቢኖሩ እንጂ። አንዱ ባንዲራ በመላኢካ እጅ የተያዘ ሲሆን ሌላው ባንዲራ ደግሞ በሸይጧን እጅ የተያዘ ነው። አንድ ሰው ከቤቱ የወጣው ኃያልና የተላቀ የሆነው አላህ ለሚወደው ተግባር ከሆነ መላኢካው ባንዲራውን ይዞ ይከተለዋል፤ ቤቱ እስኪመለስ ድረስ። የወጣው አላህ ለሚጠላው ተግባር ከሆነ ደግሞ ሸይጧን ባንዲራውን ይዞ ይከተለዋል፤ ቤቱ እስኪመለስ ድረስ።” ብለዋል (ኢማም አሕመድና ጦበራኒ ዘግበውታል) 🟢 የሸይጧን ጉትጎታ ዉስወሳ ነገ የአኼራዉን ነገር የቀብር ቅጣት፡ ተቀጣጣዩ የጀሀነም እሳት ስላሳሰባቸዉ ዑመር ኢብን ዓብዱልዓዚዝ በብዛት ይህን ዱአ ያደርጉ ነበር ፡- "ጌታዬ ሆይ!... ልቤ ውስጥ እንዲኖር ያደረግከውን ጠላት ሹመህብኛል፤ በደሜ ውስጥ እንዳሻው ይዘዋወራል፤ ፀያፍ ተግባርን ካሰብኩ ያበረታታኛል፤ ለመልካም ስራ ስነሳ ያሳንፈኛል፤ እኔ ችላ ብል እሱ አይዘናጋም፤ እኔ ብረሳ እሱ አይረሳኝም፤ የክፉ ስሜት ወጥመድ ይጠምድብኛል፤ በብዠታ ያደናቅፈኛል። ተንኮሉን አንተ ካልመለስክልኝ አዳልጦ ይጥለኛል። ጌታዬ ሆይ! በኔ ላይ ያለውን ስልጣን በርሱ ላይ ባለህ ስልጣን ድል ንሳ፤ አንተን በማስታወስ ብዛት ከኔ ይጠፋ ዘንድና እኔም በአንተ የመጠበቅ እድልን እጎናፀፍ ዘንድ እያሉ በተደጋጋሚ ዱአ ያደርጉ ነበር ⚠️ ታዳ እኛስ ሸይጧን ልባችንን እንዳይቆጣጠር ከዚክሩ ከቁርአኑ ከኸይር ስራዉ ላይ እየሰራን ነዉ ወይ?? ወይስ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ እንዳሉን በሸይጧን እጅ የኛ ባንዲና ተይዞ ከሆነ ከዛ ባንዲራ ለመላቀቅ ወደ አላህ የሚያቃርበን መንገድ ላይ ለመትጋት የጀነት መንገዳችን ለማስተካከል ወደ አላህ መስመር በእርምጃ እየሄድን ነዉ ወይ?? قُلۡ یَـٰعِبَادِیَ ٱلَّذِینَ أَسۡرَفُوا۟ عَلَىٰۤ أَنفُسِهِمۡ لَا تَقۡنَطُوا۟ مِن رَّحۡمَةِ ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ یَغۡفِرُ ٱلذُّنُوبَ جَمِیعًاۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلۡغَفُورُ ٱلرَّحِیمُ እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ሀጥያቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሀሪም አዛኝ ነውና፡፡ (አል-ዙመር 53) ❤️❤️❤️ ዛሬ ጁምአ ነዉ ዱንያዉም እንዲሰምር አኼራዉም እንዲያምር ነገ የቀብሩ ጥበት እንዲሰፋ የቀብሩ ጨለማ እንዲበራ... ነፍስያችንን ለመግራት ከቆሻሻ ነፍስያ ለመንጣት ...ነፍስያ ለመግራት ምክንያት እንዲሆነን... የዛ ቀን ጥም በሚበረታበት ሀዉድ በእጃቸዉ ከምንጠጣዉ እንዲያደርገን አላህ እሱን ወዶ ሁሉን ያስወደደዉ ለከዉኑ አይነታ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ሶለዋት እናዉርድ { إِنَّ ٱللَّهَ وَمَلَـٰۤىِٕكَتَهُۥ یُصَلُّونَ عَلَى ٱلنَّبِیِّۚ یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ صَلُّوا۟ عَلَیۡهِ وَسَلِّمُوا۟ تَسۡلِیمًا } አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡(አል አህዛብ 56) ሶሉ አለል ሀቢብ ሰይዲና ሙሀመድﷺﷺ💚💚💚 Join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group t.me/IslamisUniverstiy_public_group
በጥንታዊቷ የቲክሪት መንደር በጢግሪስ ወንዝ አቅራቢያ በቀድሞ የፐርሺያ ነገስታት በተገነባው ቤተ መንግስት ውስጥ ተደላድሏል። ስኬት እና ብቃቱ ከስነምግባሩ ጋር ተዋህደው ለስልጣን አብቅተውታል። እንደ ኸሊፋ ላቅ ያለ ከበሬታና ተሰሚነትን ቢቸርም እንደ ሀገር መሪ ሁሉ ቢታዘዘውም በላጤነት ህይወቱ ዘመናትን መሻገሩ ወንድሙን ከንክኖታል። ተቀምጠው የሆድ ሆዳቸውን እያወጉ "ለምን አታገባም?!" እያለ በተደደጋጋሚ ሲጠይቀው "ተስማሚ ሴት አላገኘሁም" በማለት ይመልሳል። የሰልጁቁ ሱልጣን የሙሐመድ ቢን መሊክ ሻህ ልጅን ለምን አታጭም ይለዋል። "መልኳ ውብ ቁመናዋ የተስተካከለ ቢሆንም ለኔ ግን በፍፁም አትሆነኝም። እኔ የምፈልገው እጄን ይዛ ወደ ጀነት የምትራመድ ሷሊህ፣ ከማህፀኗ ወንድ ልጅን በአላህ ፈቃድ ወልዳ በመልካም ስብዕናዋ ከጉያዋ አድጎ መስጂደል አቅሳን ለሙስሊሞች የሚያስመልስ ጀግና ሴት ነው" በማለት ተናገረ። "እንዲህ አይነቷ ከየት ትገኝና?!" አለው ንግግሩን በተመስጦ አዳምጦ እንዳበቃ። "ኒያውን ለአላህ ያጠራ ሀሳቡን አላህ ያሰምርለታል" ሲል መለሰ። ቀናት ቀናቶችን ወልደው ከእለታት በአንዱ ነጅሙዲን በትክሪት መስጂድ ውስጥ ከሸይኾች ሸይኽ ጋር ተቀምጦ በማውጋት ላይ ሳለ ከመጋረጃው በስተጀርባ አንዲት እንስት ተጣራች። ሸይኹ ነጅሙዲንን ፍቃድ ጠይቀው ሰላምታ ተለዋወጡ "ለትዳር የላኩልሽን ልጅ ለምን መለሽው?!" ሲሉ ጠየቁ። ልጅቷም "በእርግጥ መልከመልካም ቆንጆ ነው። ይህ ግን እኔን አይስበኝም። የሰውየው ማንነትም አይመጥነኝም እርሱ ወንድ እንጂ ባል አይሆነኝም" አለች። "እንዴት" አሉ በንግግሯ እየተገረሙ ስለሰውየው ከመዘርዘር ይልቅ ስለ ፍላጎቷ መናገር ጀመረች "ወንድ ልጅ ተሰጥቼ እየሩሳሌምን ለሙስሊሞች የሚያስመልስ ጀግናን የምወልድበትን ባል ነው የምፈልገው" አለች። ነጅሙዲን ለወንድሙ አሰዱዲን የተናገረውን ተመሳሳይ ቃል የሱልጣኑን ሴት ልጅ ቁመናና ውበት ከቁብ ያልቆጠረበት ተመሳሳይ መልስ ከሴቲቱ አንደበት ተደመጠ ነጅሙዲን ለሸይኹ "ይህችን ልጅ ማግባት እፈልጋለሁ" አለ። "በአካባቢው ካሉ ድሆች ግንባር ቀደም ተሰላፊ ናት የሚላስ የሚቀመስ በቤቷ የሌለ ብዙ ቦታ በክር የተጣፈን ልብስ የምታዘወትር እንስት ናት" አሉ። "እኔም የምፈልገው ይህን ነው አቋሟን ጠብቃ ህልሟን የምትኖር፣ ድህነቷና ችግሯ ከዓላማዋ የማያዛንፋትን ይህቺን ሴት ነው የምፈልገው" አለ። ነጅሙዲንና አል-መሊክ ኻቱን በትዳር ተጣመሩ ወንድ ልጅም ወለዱ። ስሙን ሰላሐዲን አሉት። ሰላሐዲን ከዕለታት በአንዱ በለጋ የልጅነት ዕድሜው ከሰፈር ጓደኞቹ ጋር ተሰብስቦ ይጫወት ይዟል። ከወዲያ ወዲህ እየተሯሯጠ ይቦርቃል። በስራ ተወጥሮ ጎኑን ለማሳረፍ የፈለገው አባት በድንገት ከቅርብ ርቀት መንገድ ዳር በሚጫወተው ልጁ ላይ ዓይኑ አረፈ። እየተንደረደረም ወደርሱ አቀና። "የወለድኩህ ለጨዋታ ሳይሆን አቅሳን ለሙስሊሞች እንድታስመልስ ነው" ብሎ ጆሮና ጆሮውን በሁለት እጆቹ አንጠልጥሎ ወደላይ ከፍ አድርጎ ሲጥለው በአፍጢሙ ተፈጠፈጠ። እልህና ንዴት በተቀላቀለበት መንፈስ ብድግ ብሎ አቧራ የነካውን ልብሱን ማራገፍ ጀመረ። አለማልቀሱ የገረመው አባት ምነው ዕንባ ከዓይንህ አልፈሰሰምሳ?! አላመመህም ማለት ነው? ሲል ጠየቀው ሰላሐዲን እንዲህ ሲል በለጋ አንደበቱ መለሰ:- "መስጂደል አቅሳን ከጠላቶች ነፃ የሚያወጣ ልጅ እንባ ከዓይኖቹ ሊፈስ አይገባም። ቁድስን ነፃ ያወጣው ጀግና ሰላሐዲን አል አዩቢ የተገኘው ከእነዚህ ትዳርን በዓላማ ከመሠረቱ ጥንዶች ነው። ይህ ነው ቅርሳችን ለልጆቻችን ማስተማር ያለብን። ወጣቶቻችን ሊኮርጁት የሚገባቸው እውነተኛ ጀግኖች እኚህ ናቸው... ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ጌታዬ ሆይ! ብዕሬን እንደ ኻሊድ ኢብኑል ወሊድ ሠይፍ የሰላ አድርግልኝ Mahi mahisho ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
🎖🎖 #አመጋገባችን_እንዴት_ይሁን?🎖🎖 ✍🏼 አሚር ሰይድ ዐሊይ (ረ.ዐ.) እንዲህ ማለታቸው ተነግሯል ☞ ምግቡን በጨው የጀመረ ሰባ ዓይነት መከራዎች ይወገዱለታል። ☞ በቀን ውስጥ ሰባት የዐጅዋ ተምር የበላ ማንኛውም ሕይወት ያለው ነገር ሁሉ በሆዱ ውስጥ ይሞታል። ☞በየቀኑ ሀያ አንድ ቀይ ዘቢብ የበላ በሰውነቱ ውስጥ አንዳች የሚጠላው ነገር አያገኝም። ☞ሥጋ ሥጋን ይተካል (ሥጋ ሆኖ ይበቅላል)፣ ☞ ሠሪድ የዐረቦች ምግብ ነው። ☞ የላም ሥጋ በሽታ ነው፣ ወተቷ ፈውስ ነው፣ ስቧ መድሃኒት ነው። ሞራው የሱ ዓይነት በሽታን ያስወግዳል፣ ☞ወላድ ሴት ከትኩስ ተምር የበለጠ የምትድንበት ነገር የለም። ☞ ዓሳ ሰውነትን ያቀልጣል፤ ☞ በሕይወት መቆየት የፈለገ (መቆየት እይታሰብም) ጠዋት ቶሎ ይብላ። እራት ይደጋግም። ጫማ ይጫማ። ሰዎች ከሚታከሙበት ነገር ሁሉ ቅቤን የመሰለ ነገር የለም። የግብረ ሥጋ ግንኙነት ይቀንስ፣ ዕዳንም ይቀንስ። 📕📕 አል-ሐጃጅ ለአንድ ሐኪሙ ዘወትር ማድረግ ያለብኝን ነገር ንገረኝ አለው። ሐኪሙም >> “ወጣት ሴት እንጂ እታግባ፣ >> ጠቦት ሥጋ እንጂ አትብላ፣ >> የሚጠበስን ነገር በደንብ እስኪበስል እንጂ አትብላ፣ >> ሳትታመም መድሃኒት አትጠጣ፣ >> ከፍራፍሬና አትክልት የበሰለውን ብላ፣ >> የምትበላውን ምግብ በሚገባ አድቅቅ፣ >> የምትወደውን ምግብ ብላ፣ >> በምግብ ላይ አትጠጣ፣ የጠጣህ እንደሆነም አትብላበት፣ >> ሰገራና ሽንትን ይዘህ እትቆይ፣ >> ቀን ከበላህ ተኛ፤ ማታ ከበላህ በኋላ ከመተኛትህ በፊት መቶ እርምጃም ቢሆን ተንቀሳቀስበት።* 🟢 ኢማም አሽ-ሻፊዒይ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል - ምግብ መመገብ በአራት ሁኔታዎች ሊሆን ይችላል። በአንድ ጣት መብላት አስቀያሚ ነው። በሁለት ጣቶች መብላት ኩራት ነው። በሦስት ጣቶች መብላት ሱንና ነው። በአራት እና አምስት ጣቶች መብላት መጥፎ ነው:: ✏️ አራት ነገሮች ሰውነትን ያጠነከራሉ፦ ➊ ሥጋ መብላት፣ ➋ ቆንጆ ሽታ ያለው ነገር ማሽተት፣ ➌ ግንኙነት ሳይፈፅሙም ቢሆን ገላን መታጠብ ማብዛት ፣ ➍ ጥሩ መልበስ። ✏️ አራት ነገሮች ሰውነትን ያደክማሉ፡- ➊ግንኙነት መፈፀም ማብዛት፣ ➋ ሐሳብ ማብዛት፣ ➌ ማለዳ ላይ በባዶ ሆድ ውሃ መጠጣት ማብዛት፣ ➍ ወተትና ፍራፍሬን መመገብ ማብዛት። ✏️አራት ነገሮች እይታን ያጠነክራሉ፡- ➊ ወደ ቂብላ ዞሮ መቀመጥ፣ ➋ በእንቅልፍ ጊዜ መኳል፣ ➌ አረንጓዴ ነገሮችን መመልከት፣ ➍ ልብስን በንፅህና መያዝ። ብለዋል Join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group t.me/IslamisUniverstiy_public_group
🎖#ከበርህ_ብታባርረኝ_ከአንተ_ተስፋ_አልቆርጥም ✍🏽አሚር ሰይድ ያለፉት ምርጥ ታብዕዮች አላህ(ሱወ)ን በሚያምር ልመና ነበር የሚፈልጉትን የሚጠይቁት፡፡ የተወሰኑትን አጠያየቅ እስኪ እንመልከት 🟢 #ሐቢባ አል-ዐደዊያ የዒሻእ ሶላት ከሰገደች በኋላ ቀሚሷና ጉፍታዋን በሚገባ ተሸፋፍና ከለበሰች በኋላ ትቆምና፣ “አምላኬ ሆይ ከዋከብት ጠለቁ፣ ዓይኖች አንቀላፉ፤ ነገስታት ደጆቻቸውን ዘጉ፤ ሁሉም ወዳጅ ከወዳጁ ጋር ተነጠለ፤ ይኸው እንግዲህ ፊትለፊትህ ቆሜያለሁ" ትላለች። ከዚያም ወደ ሶላቷ ትገባለች። ሊነጋጋ አካባቢም፣ 🤲 “ #አምላኬ_ሆይ ሌሊትህ መልሶ ሄደ፤ ቀንህም ፊቱን አዙሮ መጣ፤ የሌሊቱን ዒባዳዬን ተቀብለኸኝ እንደሆነ ባወቅኩና እንዴት ደስ ባለኝ! ወይም ደግሞ አምልኮዬን ዱአየን መልሰህብኝ መሆኑን አውቄ ሀዘኔን ባበዛሁ። በኃያልነትህ እምላለሁ! በሕይወት እስካለሁ ድረስ እከተልሀለሁ፤ ከበርህ ብታባርረኝ እንኳ ልግስናህን እና ቸርነትህን አውቃለሁና ካንተ ተስፋ አልቆርጥም” ትላለች። 🟢 #ከዑጅረህ እንደተወሳዉ፣ ሌሊቱን ሙሉ በዒባዳ አሳለፈች። ሊነጋጋ አካባቢ ደከም ባለ ድምፅ ተጣራች። እንዲህም አለች፣ “አምላኪዎችህ ወዳንተ አስበው የሌሊቱን ጨለማ አቋረጡ። ያንተን ርህራሄና የምህረትህን ችሮታ ሽተው ተሽቀዳደሙ። አንተኑ እማፀናለሁ። 🤲#አምላኬ_ሆይ_ካንተ_ውጪ_ሌላ_አልለምንም። ከቀዳሚዎቹ አድርገኝ። ከፍ ያለውን ማዕረግ ከሚቀዳጁት እና ወዳንተ ከቀረቡት አድርገኝ። በደጋግ ባሮችህ አስጠጋኝ። አንተ የአዛኞች ሁሉ አዛኝ፣ የታላቆች ሁሉ ታላቅ፣ የቸሮች ሁሉ ቸር ነህና።" 🟢 #ሸዕዋነህ በዱዓዋ እንዲህ ትል ነበር፡- “አምላኬ ሆይ! አንተን ለመገናኘት ጉጉቴ በዛ። ባንተ ላይ ያለኝ ተስፋም አየለ። አንተ ተስፈኞች ተስፋ ያደረጉበትን ነገር የማያጡብህ ቸር ነህ። የከጃዮች ጉጉትም አንተ ዘንድ መከኖ አይቀርም። #አምላኬ_ሆይ! ዕለተ ሞቱ ቀርቦ ከሆነና ሥራዬ ወዳንተ የማያቀርበኝ እንደሆን፡ አንተኑ በማመን ወዳንተ አቃረባለሁ። 🤲 #አምላኬ_ሆይ፡ ነፍሴ ወደራሷ እንድትመለከት አደረግኩኝ፣ ያንተን መልካም ዕይታ ብቻ ተስፋ አደረግኩኝ። በርግጥ ካልተሳካላት እንጃላት!፡፡ 🤲 #አምላኬ_ሆይ! የሕይወት ዘመኔን በሙሉ ለኔ መልካም ውለሀል። ከሞትኩ በኋላም ደግነትህ አይለየኝ፡፡ በሕይወት ዘመኔ ሁሉ መልካም የዋለልኝን በሞት ጊዜም በምሕረቱ እንዲደርስልኝ ተስፋ አደርጋለሁ። 🤲 #አምላኬ_ሆይ! በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ካንተ ያየሁት በጎ ብቻ ነውና ከሞት በኋላ ያንተ መልካም ችሮታ አይደርሰኝም ብዬ እንዴት ተስፋ እቆርጣለሁ?! 🤲 #አምላኬ_ሆይ! የወንጀሎቼ ጉዳይ የሚያስፈራኝ ቢሆንም፣ ላንተ ያለኝ ፍቅር ወዳንተ እንድቀርብ አደረገኝ። ባለቤቱ ነህና ጉዳዬን ሁሉ አንተው ያዝልኝ፡፡ አላዋቂነቱ የሸነገለውን ችሮታህን ለግሠው። 🤲 #አምላኬ_ሆይ! ልታሳንሰኝ ሽተህ ቢሆን ኖሮ፣ ወዳንተ መመራትን ባላደልከኝ ነበር። ልታዋርደኝ ብትፈልግ ኖሮ አትሰትረኝም ነበር። ወደርሱ ባቀናኸኝ ነገር አጣቅመኝ በሰተርከኝ ነገር ደግሞ ዘላቂ አድርግልኝ። 🤲 #አምላኬ_ሆይ! እሷን ጀነትን ፍለጋ ዕድሜዬን የፈጀሁባትን ጉዳይ ትነፍገኛለህ ብዬ ፈፅሞ አላስብም። 🤲 #አምላኬ_ሆይ! ወንጀሎችን ባልሠራ ኖሮ ቅጣትህን ባልፈራሁ ነበር። ቸርነትህን ባላውቅ ኖሮ ምንዳህን ተስፋ ባላደረግኩ ነበር። 🎖🎖ወቅቱ የዱአ ወቅት ነዉ ለሚመጣዉ ሀጅ ትኬት የሚቆረጠዉ ዛሬ በሚደረግ ዱአ ነዉ፡፡ ዛሬ ላይ አላህን እንጠይቅ ለሚመጣዉ አመት ቤቱ ሂደን ለበይክ ከሚሉት ባረመዎቹ ያደርገን ዘንዳ፡፡ join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group t.me/IslamisUniverstiy_public_group
📒📒📒 #ነፍስን_መፋለም📔📔📔 ✍🏼 አሚር ሰይድ ነቢያችን ﷺ ባልደረቦቻቸው ከጠላት ፍልሚያ ሜዳ ሲመለሱ፣ “ከትንሹ ፍልሚያ ወደ ትልቁ ፍልሚያ እንኳን ደህና መጣችሁ" አሏቸው:: ....."የአላህ መልእከተኛ ሆይ ትልቁ ፍልሚያ ምንድነው?” ብለው ሲጠይቋቸው፣ ነፍስን መፋለም ነው' አሏቸው። (በይሁቅይ ዘግበውታል) በዚህ ሀዲስ እንደምንረዳዉ ከጀሀድ ፍልሚያ በላይ ነፍስያን የማሸነፍ ፍልሚያ ከባድ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ በሌላ ዘገባ ደግሞ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ “ታጋይ ማስት ነፍሱን በኃያሉና የተከበረው አላህ ትዕዛዝ ሥር አንድትውል የሚታገል ነው'' ብለዋል። (ቲርሚዚይ ዘግበውታል) ☞ ሱፍያን አሥ ሠውሪይ -አላህ ይዘንላቸው "ከነፍሴ በላይ ለማከም የጠናኝ ነገር የለም! አንዴ አሸንፋታለሁ፣ ሌላ ጊዜ ታሸንፈኛለች˚ ብለዋል። ☞ አቡል ዐባስ አል-ሙሲሊ ለነፍሱ እንዲህ ይል ነበር፣ “ አንቼ ነፍሴ ሆይ አንድም በዱንያ ውስጥ ከንጉሳን ልጆች ጋር አልተንደላቀቅሽ ወይም ደግሞ አኺራን ፍለጋ ከአላህ ባሮች ጋር አልተጋሽ ምንድነሽ ግን አንቺ!?። አንቺን ይዤ በጀነት እና በእሳት መካከል የታሠርኩ ይመስለኛል። ለምንድነው የማታፍሪው?እያለ የራሱን ነፍስ ይገስፃት ነበር ☞ አል-ሐሰን፣ ደግሞ “ካልተገራ አስቸጋሪ ፈረስ በላይ፥ ነፍስህ ናት መለጎም ያለባት” ይሉ ነበር። ☞ የሕያ ኢብኑ ሙዓዝ አር-ራዚይ እንዲህ ይላሉ፣ ነፍስህን በተለያዩ የስልጠና ሰይፎች ታገል፣ በዋናነት በአራት ዘርፎች። እነሱም ➊ ምግብ በመቀነስ፣ ➋ እንቅልፍ በመቀነስ፣ ➌ ንግግር በመቀነስ፣ ➍ ሰዎችን ከመጉዳት በመተቃብ። ምግብን መቀነስ ስሜትን ይገድላል፣ እንቅልፍን መቀነስ ፍላጎትን ያጠራል፤ ንግግርን መቀነስ ከመቅሰፍት ያስጥላል፤ ሰውን አለማስቸገር ካሰቡበት ያደርሳል። አንድ የአላህ ባርያ ሲጎዱት መቻል፣ ሲያስቸግሩት መታገስ ያቅተዋል።… 🌟🌟 የህያ ኢብኑ ሙዐዝ በተጨማሪ እንዲህም ብለዋል፡- የሰው ልጅ ጠላቶች ሶስት ናቸው፤ እነሱም ➊ ዱንያ፣ ➋ ሸይጣን እና ➌ ነፍሱ። >>>>> ከዱንያ በመታቀብ፣ ሸይጣንን በመቃረን፣ ነፍስን ስሜትን በመተው ራስህን ጠብቅ፡፡” ✏️✏️ አንድ ጠቢብ ሲናገሩ፣ “ነፍሱ ያሸነፈችው ስሜቷን በመውደድ ለሷ ምርኮኛ ይሆናል፤ በፍላጎቷ እስር ቤት ውስጥ ተጨቁኖ ይኖራል፣ ሰንሰለቷ በአጇ ውስጥ ሆኖ ወዳሰኛት ትወስደዋች፤ ቀልቡ መልካም ነገር እንዳይጠቀም ታደርጋለች" ብለዋል። ጀዕፈር ኢብኑ ሐሙይድ፣ “ከተድላ የሚደረሰው፣ ተድላን በመተው ብቻ እንደሆነ ዓሊሞችና አዋቂዎች ሁሉ ተስማምተዋል” ብሏል። ✏️✏️ አቡ የሕያ አል-ወራቅ፣ የሰውነቱን ከፍሎቹን ለስሜቶቹ ባርያ ያደረገ ሰው፣ በቀልቡ ውስጥ የፀፀትን ዛፍ ተከለ” ብለዋል። አንድ ሰው ለዑመር ኢብኑ ዐብዱልዐዚዝ -አላህ ይዘንላቸው- “ሙቼ ልናገር?” ባላቸው ጊዜ "ዝምታ ባሰኘህ ጊዜ" አሉት። "መቼ ዝም ልበል?” ሲላቸው ደግሞ፣ “መናገር ባሰኘህ ጊዜ አሉት። እናም በጥቅሉ፣ ዓሊሞችና አዋቂዎች የመጨረሻው ዓለም ሐሴትና ስኬት የሚገኘው ነፍስን ከእኩይ ፍላጎቷ በመከልከል እና ስሜቷን በመቃረን ነው። በዚህ ማመን ደግሞ ግዴታ ነው።ብለዋል 💐💐 ዛሬ ጁምአ ለይል ነዉ ዱንያዉም እንዲሰምር አኼራዉም እንዲያምር ነገ የቀብሩ ጥበት እንዲሰፋ የቀብሩ ጨለማ እንዲበራ... ነፍስያችንን ለመግራት ከቆሻሻ ነፍስያ ለመንጣት ...ነፍስያ ለመግራት ምክንያት እንዲሆነን... የዛ ቀን ጥም በሚበረታበት ሀዉድ በእጃቸዉ ከምንጠጣዉ እንዲያደርገን አላህ እሱን ወዶ ሁሉን ያስወደደዉ ለከዉኑ አይነታ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ሶለዋት እናዉርድ { إِنَّ ٱللَّهَ وَمَلَـٰۤىِٕكَتَهُۥ یُصَلُّونَ عَلَى ٱلنَّبِیِّۚ یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ صَلُّوا۟ عَلَیۡهِ وَسَلِّمُوا۟ تَسۡلِیمًا } አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡(አል አህዛብ 56) ሶሉ አለል ሀቢብ ሰይዲና ሙሀመድﷺﷺ💚💚💚 Join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group t.me/IslamisUniverstiy_public_group
ሰዉ ላዩ እንጂ አይታይ ሆዱ👍 t.me/IslamisUniverstiy_public_group t.me/IslamisUniverstiy_public_group
🎖🎖 #በማይመለከትህ_አትግባ🎖🎖 ✍ አሚር ሰይድ የአንድ ሙስሊም ትልቁ ሀብቱ ጊዜው ነው። በማይመለከተው ነገር ያጠፋ እንደሆነና በጊዜው ስንቁን ለአኼራ ካላስቀደመ ዋና ጥሪቱን አባከነ፡ ለዚህም ነው ሀቢቡና ሰይዲና ሙሀመድ ﷺ የአንድ ሰው እስልምና ስምረት የማይመለከተውን ነገር መተዉ ነው"ያሉት። አቢ ዘር (ረ.ዐ.) የአላህ መልእክተኛ ﷺ “ለአንደበት ላይ ቀላል በሚዛን ላይ ግን ከባድ የሆነ ሥራ ሳስተምርህን?'' አሉኝ፡፡ “እንዴታ የአላህ መልእክተኛ ሆይ አልኳቸው። እሳቸዉም ዝምታ/መልካም ሥነምግባር እና የማይመለከትህን ነገር መተዉ ነዉ አሉኝ ✏️ ሙጃሂድ ዐብዱላህ ኢብኑ ዐባስ (ረ.ዐ.) እንዲህ ማለታቸውን ሰምቻቸዋለሁ ብሏል፡፡ “እጅግ ከበረከቱ ምርጥ ግመሎች በላይ አምስት ነገሮች ወደኔ ተወዳጅ ናቸው፡ ➊የማይመለከትህን ነገር አትናገር፤ ትርፍ ነውና ወንጀል ላይ እንዳትወድቅ ያስፈራል። ➋ በሚመለከትህ ነገርም አትናገር፤ በተገቢው ቦታ ላይ ቢሆን እንጂ። የሚመለከተውን ነገር በማይመለከተው ቦታ ላይ ተናግሮ የሚነወር ስንት አለ?) ➌ ከታጋሽም ሆነ ከጅል ጋር አትቀልድ፣ ታጋሽ ይንቅሀል፣ ጅል ደግሞ ያውከሀል። ➍ ወንድምህ በራቀ ጊዜ አንተ ልትወሳ በምትፈልገው ነገር አውሳው፣ አንተ ሲከራከሩልህ በምትወደው ነገር እሱንም ስለ ጨዋነቱ ሞግትለት። ➎ አንተን እንዲያደርጉልህ የምትፈልገውን ነገር ለሌሎች አድርግ። 📕📕 #ሉቅማን እል-ሐኪም፣ "ጥበብህ ምንድነው?” ተብሎ በተጠየቀ ጊዜ "ስላለኝ ነገር አልጠይቅም፡ ስለማይመለከተኝ ነገር አልጨናነቅም።” ብሏል። ⚡️⚡️⚡️ መውሪቅ አል-ዐጅሊ፣ ከሀያ ዓመት አንስቶ የከጀልኩት ጉዳይ አለ፤ ዛሬም ድረስ አላገኘሁትም፤ ከመፈለግም አልቦዘንኩም አለ። “ምንድነው እሱም ቢሉት። በማይመለከተኝ ነገር #ዝም_ማለት አለ። ✏️ዑመር ኢብነል ከጧብ ረዐ እንዲህ ብለዋል ☞ በማይመለከትህ ነገር አትግባ፤ ☞ ከጠላትህ በማንኛዉም ጊዜ አንተዉ ራቅ! ☞ መጥፎ ጓደኛህን ተጠንቀቅ፤ ታማኝ የሚባለው ታላቁን አላህን የሚፈራው ነው። መናጢን ጓደኛ አድርገህ አትያዝ፤ መናጢነቱን ያጋባብሃል። ምስጢርህንም አትንገረው፡፡ ጉዳይህን ታላቁን አላህን የሚፈሩትን ሰዎች አማከር ብለዋል። ✍🏼ለማንኛዉም በእኛም ሀይማኖታችን በሰዎችም ሀይማኖት በማይመለከተን አንግባ >> የሰዉ ችግር እንፈታለን ብለን የሰዉ ሚስጥር ለማዳመጥ በማይመለከተን አንግባ እንደዉ ጠቅለል ሲል አንተም እኔም ሁሉም የየራሱ ቢዚ የሚያደርግ ሀሳብ ችግር ስላለዉ የሰዉ ችግር እንፈታለን ከአላህ በታች አለን እያልን በማይመለከተን አንግባ!!! ⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️ ዛሬ ጁምአ ለይል ነዉ ዱንያዉም እንዲሰምር አኼራዉም እንዲያምር ነገ የቀብሩ ጥበት እንዲሰፋ የቀብሩ ጨለማ እንዲበራ... የዛ ቀን ጥም በሚበረታበት ሀዉድ በእጃቸዉ ከምንጠጣዉ እንዲያደርገን አላህ እሱን ወዶ ሁሉን ያስወደደዉ ለከዉኑ አይነታ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ሶለዋት እናዉርድ { إِنَّ ٱللَّهَ وَمَلَـٰۤىِٕكَتَهُۥ یُصَلُّونَ عَلَى ٱلنَّبِیِّۚ یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ صَلُّوا۟ عَلَیۡهِ وَسَلِّمُوا۟ تَسۡلِیمًا } አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡(አል አህዛብ 56) ሶሉ አለል ሀቢብ ሰይዲና ሙሀመድﷺﷺ💚💚💚 Join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group t.me/IslamisUniverstiy_public_group
አስቸጋሪው እና ከባዱ የሴት ልጅ ውሳኔ በአንዳንድ ማህበረሰቦች ውስጥ አንዲት ሴት ከምታልፍባቸው እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታዎች አንዱ በሁለት መራራ ምርጫዎች መካከል ራሷን በድንገት ማግኘት ነው ። በአንድ በኩል—ክብሯን በሚያዋርድ፣ በየቀኑ በሚያቆስላት፣ በደልና ግፍ በሚፈጽምባት ባል ስር ሆኖ መታገስ፤ በሌላ በኩል ደግሞ—መዳኛ ሳይሆን የፍርሃትና የጭንቀት መንገድ ወደ ሚመስለው የፍቺ ውሳኔ መቃረብ ። እሷ የምትኖረው ለራሷ ብቻ አይደለም፤ በየቀኑ በእሷ አይን ውስጥ ሰላምን፣ ፍቅርንና ጥንካሬን የሚፈልግ ህጻን ልጅ አለ ። ከትዳር አጋሯ ጋር የመቆየት ፍርሃት፦ ልጇ በዚህ በስቃይ፣ በውጥረትና በጭካኔ ድባብ ውስጥ እንዲያድግ አትፈልግም የመሄድ ፍርሃት፦ ከቧሏ ተነጥላ ልጇ ያለ እናት ወይም ያለ አባት እንዲበተንባት ትሰጋለች ። በልቧና በአእምሮዋ መካከል ለውሳኔ ተቸግራ ትዋዥቃለች ፤ ልቧ "በቃኝ" ይላል፣ አእምሮዋ ግን "ወዴት?" ብሎ ይጠይቃታል። መረጋጋት በሌለበት፣ ነፍሷ በዛለበት ቤት ውስጥ ብትሆንም ቢያንስ መጠለያ አላት ። ቤተሰቦቿ ደግሞ የህመሟን ዝርዝር አይረዱም፤ የሚያዩት የሚወሰነውን ውሳኔ ብቻ ነው፣ እንደፈለጉም ይፈርዱባታል ። ሁሉን ችላ በትዳር ውስጥ ብትቆይ ቀኖቿ በስቃይ ያልቃሉ፤ ትዳሯን ትታ ብትሄድ ደግሞ ደካማ ጎኗን ለማይራራላት ጨካኝ ዓለም አሳልፋ ትሰጣለቸ ። ፍቅር በማታገኝበት ባል እና በማይረዷት ቤተሰቦች መካከል፣ እንዲሁም በአሁኑ ስቃይና ባልታወቀ መጻኢ እድል መካክል ተንጠልጥላ ትቀራለች ። የመቆየትም ይሁን የመሄድ ፍርሃት እኩል ይጫኗታል። ስለዚህ የእሷ ውሳኔ በቀላሉ የሚለካ አይደለም፤ ስቃይዋም ከውጭ ሆኖ አይታይም ። እዚህ ፈተና ላይ ራሷን ያገኘች ሴት የምትፈልገው ምቾትን ሳይሆን ከሁለቱ ጉዳቶች ትንሹን ነው ራሷንና ምንም ጥፋት የሌለባቸውን ልጆቿ ለማደን ትታገላለች ። እንዲህ ያሉ ማህበረሰቦች ለመረዳት እድል አይሰጡም፤ ከመረዳት ይልቅ ለመፍረድ ይቸኩላሉ ለደህንነቷ ሳይሆን "ሰዎች ምን ይላሉ?" ለሚለው ጭንቀት ቅድሚያ ይሰጣሉ ። "የተፈታች" የሚለው ስም እንዳይሰጥባት ብቻ እንድትታገስ ይጠይቋታል። የሚጨነቁት ለስማቸው እንጂ ለእሷ ሰላም አይደለም ውሳኔዋ ከባድና መራራ ነው፤ ምክንያቱም እሷ በሁለት መንገዶች መካከል እየመረጠች ሳይሆን፣ በሁለት ጠባብና አስጨናቂ ሁኔታዎች መካከል እየተገፋች በትንሹ ጉዳት ለመትረፍ እየሞከረች ነውና ። copy Join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group t.me/IslamisUniverstiy_public_group
ሴት ልጅ መቼም የማትረሳው ነገር ቢኖር ድጋፍህን፣ እርዳታህን፣ ማበረታታትህን፣ አለሁልሽ መባልን በፈለገችበት በዛች ሰዓት እንዴት እንደሆንክ ... እንዴት እንዴት እንደሆንክላት ወይም እንዴት እንዴት እንደሆንክባት ነው ፨ ይኼንን ይዘን ነገሩን በዝርዝር ወደማየት እንግባ ፨ ከፀብ በኋላ ገዝተህ የሰጠሀትን አበቦች አይደለም ነገሮች ብልሽትሽታቸው ከወጣ በኋላ የላከውን "ይቅርታ" የሚል የፅሁፍ መልዕክት አይደለም ነገሮች ጥሩ ሲሆኑ የምታሳየውን ፈገግታ አይደለም የሆነ ነገር ስትፈልግ የሚኖርህን መቅለስለስ አይደለም አብሯት የሚቆየው .... ከአይምሮዋ የማይወጣው ... ነገሮች በከበዷት ወቅት ያሳየሀት ነገርህ ነው በተጨነቀችበት ወቅት፣ በፈራችበት ወቅት፣ በተሳቀቀችበት ወቅት፣ በደነገጠችበት ወቅት፣ አለቀልኝ በቃ ባለችበት ወቅት፣ ተስፋ በቆረጠችበት ወቅት ..... በነበረህ ማንነትህ ነው ፍቅር የሚፈተሸው ያኔ ነው እውነተኛ ፍቅር የሚመዘነው ያኔ ነው እሆንልሻለሁ ያልካት ነገር ሁሉ የሚለካው ያኔ ነው ታማኝነትህ የሚታየው ያኔ ነው የምትመካብህ መሆን አለመሆንህ የሚታየው ያኔ ነው የእሷ መሆንህ የሚታየው ያኔ ነው ፀንተህ ትደግፋታለህ ወይስ እሮጠህ ሄደህ ነገሮች ሲስተካከሉ "ይቅርታን" አዝለህ ትመጣለህ የሚለው የሚታየው ያኔ ነው ቆንጆ በነበረችበት ወቅትማ ሁሉም ይወዳታል በፈገግታዋ ጊዜማ ሁሉም ይፈልጋታል በደመቀችበት ወቅትማ ሁሉም ይከተላታል ዘንጣ በምትወጣበት ጊዜማ ሁሉም ካልሸኘሁሽ ይላታል እውነተኛው ወንድ .... የእኔ የምትለው ወንድ .... የሚታወቀው እራሷን ባልሆነችበት ወቅት ነው እብደቷ በመጣ ጊዜ ነው ጭንቀት ቤቱን በሰራባት ጊዜ ነው ፀጉሯን መሰራት ባስጠላት ጊዜ ነው ከአልጋ መውጣት ባልፈለገችበት ጊዜ ነው እንባዋን መደበቅ በተሳናት ጊዜ ነው አካሏን ሳይሆን ስሜቷን የሚደግፋት ሰው በፈለገች ጊዜ ነው በዚህ ጊዜ .... ለብቻዋ ከተውካት ከስሜቷ ጋር ከተውካት ከአይምሮ ጋር ከተውካት ከመንፈሷ ጋር ከተውካት ከረሳሀት .... ከራቅካት .... "እንዳበዛችው" እንዲሰማት ካደረካት አንድ ነገር እርግጠኛ ሁን .... ምንም ላትልህ ትችላለች .... ይቅርታም ልታደርግልህ ትችላለች .... መቼም መቼም ግን ይሄንን ማንነትህን አትረሳልህም ከህይወት እኩል ያንተም ዝምታ እና መሸሽ እንደከበዳት አትረሳልህም ጥንካሬህ በፈለገች ጊዜ ቸልታህን እንዳቀበልካት አትረሳልህም እወድሻለሁ ያላት ሰው አብሯት መሆን እንኳን እንዳልፈለገ አትረሳልህም ላንተ .... ትልቅ ነገር ላይሆንብህ ይችላል ትረሳዋለች ወይም ረስታዋለች ብለህ ልታስብ ትችላለህ ችግሩ ግን ሴት ልጅ ህመምን አትረሳም ሴት ልጅ በችግሯ ጊዜ ከአይንህ ላይ ያነበበችውን ስሜት አትረሳም አብራህ ብትቆይም .... እርሳው በቃ ብትልህም .... ያለፈው አልፏል በቃ ብትልህም .... የሆነ ነገሯ ይቀየራል ምክንያቱም በፈለገችህ ጊዜ እንደማትተማመንብህ አንዴ ከተሰማት .... ከዛ በኋላ ለራሷ ያለቻት ራሷ ብቻ እንደሆነች ትቀበላለች ከዚህ በኋላ አንተ እያለህም የለህም © Abby Junior Join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group t.me/IslamisUniverstiy_public_group
ለፈገግታ ይሁን በል ይሁን የደሴዉ የሰርግ ሙሸራ ዉበት ድምቀት ረሚል፡፡ ሙሸራ ላይ ከሚያደርገዉ ዱአ አንዱን ጀባ ልበላችሁ፡፡ እኔ ከምነግራችሁ እናንተ አዳምጡት ዘና ፈታ ያደርጋል😊 Join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group t.me/IslamisUniverstiy_public_group
⚠️ አቡ ጧሊብ አል-መኪይ፣ “ትላልቅ ወንጀሎች አስራ ሰባት ናቸው ብለዋል.... ከተለያዩ ነቢያዊ መልዕክቶችና ከነ ኢብኑ ዐባስ፣ ኢብኑ መስዑድ፣ ኢብኑ ዑመር እና ሌሎችም የሰበሰብኳቸው ናቸው” ብለዋል። #ከነዚህም_መካከል 🟢 #አራቱ በቀልብ የሚሠሩ ናቸው: እነርሱም ➊ በአላህ ማጋራት፣ ➋ ኃጢአት ላይ መዘውተር (አለመቶበት)፣ ➌ ከአላህ እዝነት ተስፋ መቁረጥ እና ➍ አላህ አይቀጣኝም ብሎ ፍፁም በሆነ መልኩ መተማመን ናቸው። 🟡 #አራቱ_ደግሞ በምላስ የሚፈፀሙ ሲሆኑ ➎ የሐሰት ምስከርነት፣ ➏ ንፁሕ አማኝን በዝሙት መወንጀል፣ ➐ ቅልጥ ያለ (አስማጭ) መሐላ፣ ➑ ሲሕር (መተት) ነው፡፡ 🔴 #ሶስቱ ደግሞ በሆድ የሚፈፀሙ ናቸው። እነርሱም፡- ➒ አስካሪ መጠጥ መጠጣት፣ ➓ የየቲምን ገንዘብ በግፍ መበላት እና ➊➊ እያወቁ ወለድ መብላት ናቸው:: 🟠 #ሁለቱ ደግሞ በፈቃደ ሥጋ (ብልት) የሚፈፀሙ ናቸው ➊➋ ዝሙት እና ➊➌ ግብረሰዶም። 🔵 #ሁለቱ በእጅ የሚፈፀሙ ናቸው ➊➍ ግድያ እና ➊➎ ስርቆት፡፡ 🟣 #አንዱ ደግሞ በሁለት እግሮች የሚሠራ ነው። እሱም ➊➏ በጭንቅ ጊዜ ከፍርሃት የተነሳ ከጦር ዐውድማ ላይ ወገንን ለጠላት አጋፍጦ መሸሽ ነው። 🟡 ሌላው በሁለመና የሚሠራ ሲሆን፡- ➊➐ ወላጆችን አለመታዘዝ በነርሱ ማመፅ ነው። ሰዉ ግን እነዚህን ወደ ጀሀነም የሚያስገቡ ወንጀሎችን እንኳን መስራታቸዉን ሊተዉ ወንጀል ናቸዉ የሚለዉን ከልባችን ፍቀናን አቡ ሰዒድ አል-ኹድሪይ እና ሌሎችም ሱሐቦች እንዲህ ብለዋል፡- "እናንተ ዓይኖቻችሁ ላይ ከፀጉር የቀጠኑ ናቸው ብላችሁ የምታስቧቸው ስራዎች (ወንጀሎች) ትሰራላችሁ። በአላህ መልእከተኛ ﷺ ዘመን ግን ከትላልቅ ወንጀሎች ነበር የምንቆጥራቸው:: ብለዋል (አሕመድ እና በዛር የዘገቡት) ከላይ የተጠቀሱት 17 ከባድ ወደ ጀሀነም የሚያስገቡ ወንጀሎች ምን ያህሎቻችን ርቀናል⁉️ ©Amir seid Join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group t.me/IslamisUniverstiy_public_group
ያነበበ ሰዉ ግለሰብ ይሆናል ያላነበበ ደግሞ መንጋ ይሆናል:: ሙሉዉን ያዳምጡ ሙሀመድ አሊ ቡርሀን Join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group t.me/IslamisUniverstiy_public_group
♦በሌላም ሐዲስ “ምርጣችሁ ለቤተሰቡ ምርጥ የሆነው ነው፡፡ እኔ ለቤተሰቤ ምርጥ ነኝ። ብለዋል። ወንድ ምርጥ ሆነ የተሟላ ኢማን ያለዉ ነዉ ስንል ግን ሚስትህ የጠየቀችህን ሁሉ እሺ በል ማለት አይደለም...ሴት ልጅ እሺ እሺ ከተባለች እንደ ቢጫ ወባ አናት ላይ መዉጣቷ ስለማይቀር ነገሮች እየጠኑ ሲሄድ ፍች እንዳይመጣ ሁሉ ነገር እሺ አይባልም የሚስት ባሪያ አይኮንም፡፡ አል-ሐሰን እንዲህ ብለዋል፡- “አንድ ሰው ሚስቱን በሁሉ ነገሯ የሚታዘዝ ከሆነ ይህ አድራጎቱ እሳት ላይ ይጥለዋል።” ብለዋል። የአላህ መልዕከተኛ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል #የሚስት_ባሪያ_የሆነ_ጠፋ” ማለታቸው ተነግሯል። (ቡኻሪ ዘግበውታል) ይህ ሲባል ፍፁም በሆነ መልኩ የሚታዘዛት ማለት ነው:: 🎖🎖 #ወንድ_ልጅ_መቼ_እቤቱ_ይግባ??🎖🎖 ወንድ ልጅ ከመንገድ ወይ ከሄደበት ሲመለስ ለሊት ከሆነ እቤቱ ባይገባ ይመረጣል የአላህ መልዕከተኛ ﷺ ከመንገድ ጉዞ ሲመለሱ ወደ መዲና ከመግባታቸው በፊት ለባልደረቦቻቸው "በሌሊት ሰዓት ወደ ቤታችሁ አትግቡ።” ብለዋል። (አሕመድ ዘግበውታል) ሁለት ሰዎች ቀድመዋቸው ትዕዛዛቸውን ጥሰው ሲሄዱ ቤታቸው ሲገቡ ጥሩ ነገር እንዳላዩ ተነግሯል። 🎖🎖🎖 #ጥርጣሬ_ማብዛት🎖🎖🎖 የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- "አላህ ከሚጠላቸው ቅናቶች መካከል አንድ ባል ሚስቱን በጥርጣሬ የሚጠላበት ሁኔታ ነው” ብለዋል። (አቡ ዳዉድ፣ ነሳኢና ኢብኑ ሒባን ዘግበዉታል) ይህ ሊሆን የቻለው በክፉ መጠራጠር የተከለከለ በመሆኑ ነው። መጥፎ ጥርጣሬ ብዙን ጊዜ ወንጀል ላይ ይጥላል። ዐሊይ (ረ.ዐ.) “በሚስትህ ላይ ቅናት አታብዛ፤ ባንተ የተነሳ ወንጀል ላይ ልትወድቅ ትችላለችና።" ብለዋል። 🎖🎖#የተወለደዉ_ሴት_ነዉ_ወይስ_ወንድ?🎖🎖 ብዙዎቻችን ቤት ያለ ችግር ወንድ ልጅ ተወለደልኝ ብሎ ከልክ በላይ መደሠት፣ ሴት ሲወለድ ደግሞ መደንገጥና ማዘን። ይህ በጃሂልያዉ ጊዜ የነበረ በሀል ነዉ ዛሬም ላይ በብዙ ቤቶች ያለ አስተሳሰብ ነዉ የትኛው ልጅ በጎ እንደሆነ አያውቅም ከዚያ ይልቅ ሰላማዊና ሙሉ አካል ሆነው መወለዳቸው ነው ተፈላጊው ነገር። ከሴት ልጅ ትሩፋት መካከል ኢብኑ ዐባስ (ረ.ዐ.) እንዳወሩት የአላህ መልዕክተኛ ﷺ “አንድ ሰው ሁለት ሴት ልጆችን ተንከባከቦ አያሳድግም ይዘውት ጀነት ያስገቡት ቢሆን እንጂ” ብለዋል። (ኢብኑ ማጀህ እና ሐኪም ዘግበዉታል) በሌላ ሀዲሰ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-ሶስት ሴት ልጆች ያሉት፤ በነርሱ ላይ ወጭ ያደረገ ፣ መልካም የዋለላቸውና ራሳቸውን እስኪችሉ ድረስ የረዳቸው አላህ ጀነትን ቁርጥ ባለ መልኩ አፅንቶለታል። አላህ የማይምረው የሆነ ስራ እስካልሰራ ድረስ።"ብለዋል ኢብኑ ዐባስ ስለዚህ ሀዲስ ሲያወሩ “የሚገርም እና አጓጊ የሆነ ሐዲስ ነው::" ይሉ ነበር ተብሏል። ሌላም ሀዲስ አይቻለሁ ሀዲሱ ደካማ ነዉ እንጂ አንድ ሴትም የሚል አይቻለሁ፡፡ ሴት ልጅን በዲን ማሳደግ የጀነት መግቢያ ሰበብ ናት ወዳጄ #በትዳር_መሀል_አላህ_የሰጠህ_ልጅ_ቢወስድብህስ? ባለትዳሮች ሆይ ልጅ ሙቶ ከሶበራችሁ እነዚህን ጥቅም ታገኛላችሁ >> ልጅ ከወላጅ በፊት የሞተ እንደሆነ ለወላጅ አማላጅ የሚሆን በመሆኑ። ከአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንደተወራው “ህፃን ልጅ አባቱን ወደ ጀነት ይጎትተዋል ብለዋል >> በሌላ ዘገባም "እኔ ልብስህን እንደያዝኩት ሁሉ እሱም በዚህ መልኩ ይይዝና ይጎትትሃል” ብለዋል። (ሙስሊም ዘግበውታል) >> በሌላ ዘገባም ልጅ ጀነት ግባ ሲባል ያኮረፈ ሆኖ ጀነት በር ላይ ይቆማል፣ ወላጆቼ ከኔ ጋር ጀነት ካልገቡ አልገባም። ይላል። በመጨረሻም ወላጆቹ ከርሱ ጋር ጀነት እንዲገቡ ይደረጋሉ።” ተብሏል። (ኢብኑ ሒባን እንደዘገቡት) >> በሌላም ሐዲሥ “ሁለት ልጆች የሞቱበት ሰው በርግጥ ከእሳት በትልቅ ነገር ተጋረደ፡፡" ብለዋል። (በዛር እና ጦበራኒ እንደዘገቡት) >> በሌላም ሐዲሥ “ሶስት ለአካለመጠን ያልደረሱ ልጆች የሞቱበት ሰው አላህ ለእነርሱ በሚያደርገው ችሮታ ምክንያት ጀነት ያስገባዋል።” ያሉ ሲሆን “ሁለትስ?” ተብለው አዎን ሁለትም” ብለዋል። (ቡኻሪና ሙስሊም እንደዘገቡት) ⚠️⚠️ #ዛሬ ዘመን ላይ የተዘነጋዉ ከኒካህ በፊት የተረገዘ...ልጅ ሲረገዝ አይተዉ ኒካህ ያደረጉ ልጁ ቢወለድም ያዉ ዲቃላ የዝሙት ልጅ ነዉ፡፡ኒካሁን ያሰረዉ ቢያስረዉ ኒካሁ ባጢል ነዉ አብረዉ ቢኖሩም ዚና ነዉ፡፡የዚናዉ ልጅ ከተወለደ ቡሀላ እንደገና ኒካሁ መታሰር አለበት፡፡ ብዙ ወጣት ሲሸወድ እያየን ብቻ ዲን በመሰለኝ አይሆንም ከዝሙት እንጠንቀቅ፡፡ Join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group t.me/IslamisUniverstiy_public_group