ሐበሻ ኢስላሚክ ሚድያ
Статистикаقال الله تعالى ( وَلَا تَلْبِسُوا الْحَقَّ بِالْبَاطِلِ وَتَكْتُمُوا الْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ )البقرة (42) አሏህ በእርግጥም አለ፦[እውነትን በውሸት አትሸፍኑ እናንተ እውነታውን እያወቃቹህ] ምንጭ፦«ሱረቱ አል–በቀራህ አንቀፅ /42/ በኡስታዝ ሐምዛ [አሰዱሏህ]
- Последний пост
- 7 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 117
- 1/48двое суток
- 1 280
- 1/72трое суток
- 1 380
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
https://www.tiktok.com/@hamzamudsir0/photo/7671289861847944468?_r=1&u_code=f0je30fl7kadi0&preview_pb=0&sharer_language=en&_d=f0je295m7eh0ad&share_item_id=7671289861847944468&source=h5_m×tamp=1786111371&user_id=7579234243294266389&sec_user_id=MS4wLjABAAAAtGHHZTFTO78xUgWMrSSJWUb3UzQImBp1vUtuuc62QoHu7EHXsbpWewqK8XFIaQU-&aweme_type=150&pic_cnt=2&social_share_type=14&ug_photo_idx=1&utm_source=more&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7666499547074529032&share_link_id=95b11cfb-5cd4-4f87-9faa-f6a1c37d255d&share_app_id=1233&ugbiz_name=UNKNOWN&ug_btm=b2863&sp_root_share_link_id=95b11cfb-5cd4-4f87-9faa-f6a1c37d255d&link_reflow_popup_iteration_sharer=%7B%22click_empty_to_play%22%3A1%2C%22dynamic_cover%22%3A1%2C%22follow_to_play_duration%22%3A-1.0%2C%22profile_clickable%22%3A1%7D&panel_source_v2=share_panel&share_enter_from=homepage_friends&item_author_type=1&enable_checksum=1&sp_level=1&sp_root_u=f0je30fl7kadi0&sp_root_d=f0je295m7eh0ad
https://vt.tiktok.com/ZS4B26quX/
Check out HAMZA ASEDULLAH's video! #TikTok https://vm.tiktok.com/ZSXwgrJHL/ This post is shared via TikTok Lite. Download TikTok Lite to enjoy more posts: https://www.tiktok.com/tiktoklite
Check out HAMZA ASEDULLAH's video! #TikTok https://vm.tiktok.com/ZSX3bSFjc/ This post is shared via TikTok Lite. Download TikTok Lite to enjoy more posts: https://www.tiktok.com/tiktoklite
ከባድ ጥያቄ፦ يقال للمجسم ومن داهنه: ¤ ለሙጀሲማዎች ጥብቅና የቆሙ አካላት እራሳቸውን ምታሳምማቸው አንድ ጥያቄ አለች፦ الله هو الجسم أم غير الجسم ؟ ✧ አሏህ አካል ነው ወይስ አካል አይደለም? الجواب: الله غير الجسم، الله ليس جسما. ✧ መልሱ ፦አሏህ አካል አይደለም። فمن عبد الجسم فقد عبد غير الله ومن عبد غير الله لا يكون مسلما ✧ ስለዚህ አሏህ አካል ካልሆነ: አካልን ያመለከ ሰው ከአሏህ ሌላ አምልኮ ማይገባውን ነገር ነው የተገዛው።ከአሏህ ውጪ ያለን የተገዛ ደግሞ ሙስሊም አይሆንም። ✧ ታድያ እንዴቱን ብሎ ነው ዑለማዎች በመክፈሩ ላይ ልዩነት አሳይተዋል የሚባለው?። ABU ...AYSEL
видео или голосовое, без подписи
^ በዛሬው ዕለት ከሙሐመድ አያሌው ጋር በሙሓመድ ረመዷን አል ቡጢይ አሏህን ዒላህ ብሎ በመሰየሙ ዙርያ የተደረገ ውይይት::
عَن أَنَسٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنهُ قَالَ: «مَا شَمَمتُ عَنبَرًا قَطُّ وَلَا مِسكًا وَلَا شَيئًا أَطيَبَ مِن رِيحِ رَسُولِ اللَّهِ ﷺ»، رَوَاهُ البُخَارِيُّ. 📌 ከ'ኣነስ ረዲየሏሁ ዓንሁ እንደተያዘው እርሳቸው እንዲህ ይላሉ፦「"ዐንበርንም¹ ሆነ ሚስክን እንዲሁ ሌላ ሽታው ሚማርክን ነገር አላሸተትኩም የነብዩን ሽታ የመሰለ"」። ምንጭ፦『ሶሒሑል ቡኻርይ』። ① መሃዛቸው ከሚያውዱ የሽቶ አይነት ነው።አይነት ያለው ሲሆን ከእርሱ ውስጥ በማጨስ ሽታው እንዲወጣ ሚደረግ አለ። ② ማራኪ እንዲሁ ልዩ ከሚባሉ ሽታ ካላቸው ነገሮች የሚመደብ ሲሆን ከሚዳቆ ሰውነት የሚቀሰም ልዩ የሽቶ አይነት ነው። FROM .......ABU AYSEL
♦ ثبت لدينا بالوجه الشرعي رؤية هلال 🌙شهر *المحرم* 1448 للهجرة بعد غروب شمس يوم الإثنين. ๏ በሂጅርያህ አቆጣጠር የ 1448 ኣመተ ሂጅርያህ የሙሐረም ወር ጨረቃ በሸሪዓዊህ መንገድ በተደረገ ክትትል መታየቷ ተረጋግጧል::
✧ እገሌን ተሳስተዋል ልትል ነው?! እነ ሸይኽ ፉላንን ጠመዋል ልትል ነው? እነ ምናምን እነ… ለምትሉ፤መመዘኛቹ ሸሪዓው ቀርቶ የሰዎች ማንነት የሆናችሁ ግለሰቦች ሰከን ብላችሁ አንብቡት። قال الشيخ العلامة الزاهد الكوثري في مقالاته ما نصه "[ الكُفْر كُفْرٌ كَائِنًا مَنْ كَانَ النَّاطِق بِهِ، وَالزَّيْغ زَيْغٌ كَائِنًا مَا كَانَ مَصْدَرهُ، وَلَيْسَ فِي الإِسْلاَمِ دِينٌ يَخْتَلِفُ بِاخْتِلاَفِ الأَشْخَاصِ، فَالإِيمَان إِيمَانٌ مُطْلَقًا، وَالكُفْر كُفْرٌ مُطْلَقً"]انتهى ¤ ኣ'ሸይኹ ኣል-ዐላመቱ ሙሐመድ ኣ'ዛሂዱ ኣል-ከውሰርይ እንዲህ ይላሉ፦ [“የተናገረበት ማንም ይሁን ማን ኩፍር ኩፍር ነው።ጥመትም ጠንሳሹ ማን ሆነ ማን ጥመትነቱ አይቀሬ ነው።በእስልምና ውስጥ በሰዎች መለያየት የሚለወጥ ሕግጋት የለውም።ኢማን ማንም እስካመነበት ድረስ ኢማን ነው።ክህደትም ማንም እስከካደበት ድረስ ክህደት ነው”]። ምንጭ፦[መቃላቱ ኣል-ከውሰርያህ]። HAMZA ....ASEDULLAH
قَالَ سَحنُونُ: «مَن اشتَرَى كُتُبَ العِلمِ أَو وَرِثَهَا ثُمَّ أَفتَى بِهَا وَلَم يَعرِضهَا عَلَى الفُقَهَاءِ أُدِّبَ أَدَبًا شَدِيدًا»، [ፉቀሃኦች ዘንዳ አቅርቦ ሳይቀራ የእውቀት ኪታቦችን በመግዛት አልያ በመውረስ (ብቻ)ፈትዋ ሚሰጥ ከፍተኛ በሆነ መልኩ አደብ እንዲይዝ ይደረጋል]።
መረጃ ይዳኘን ክፍል ①② [ሑጀቱል ኢስላም አል-ገዛልይ] ስማቸው ከቀደምት ግዜያት ጀምሮ እስካለንበት ዘመን ድረስ ሳይጠለሽ በክፉም ሳይደበዝዝ በበጎ ከሚታወሱ አኢማዎች መሀከል ሑጀቱል-ኢስላም የሚሰኙት ስመ ገናናው ኣቡ-ሓሚድ አል-ገዛልይ ረዲየሏሁ ዐንሁ ይገኙበታል።እኚህ ታላቅ ሰው የሰለፍን ዘመን አልፈው ኸለፍ ከሚሰኙት የእውቀት ሊሂቃን የሚመደቡ ሲሆን፤በመዝሃብ ደረጃ የሻፊዒይን፣ በዒልም ደረጃ አል-ሙጅተሂድ ፊል መዝሀብ የተሰኙ በዓቂዳ መንገድ አ'ሽዓርይነትን የተላበሱ ታላቅ የኢስላማዊ እውቀት ምሁር ናቸው። አል-ኢማሙ ኣል-ገዛልይ 450-505 አመተ ሂጅራ የቆዩ ሲሆን ከመሻይኾቻቸው መሀከል አቡል-መዓሊይ አል-ጁወይንይ አንዱ ሲሆኑ ከተማሪያቸው ውስጥ ደግም ታላቁ ወልይ ኣቡበክር ብኑል ዓረብይ ይገኙበታል። እኚህ ታላቅ የእውቀት ሰው ከዓቂዳ ዘርፍ አንስቶ እስከ ፊቅሂ የተዋጣላቸው የኢልም ባልተቤት መሆናቸው እብለት የሌለው ፍንትው ያለ እውነት ነው።ከሰነዷቸው ኪታቦች መሀከልም ኢልጃሙል ዓዋም ፊይ ዒልሚል ከላም፣ አል-ሙስተስፋ፣ ኢ'ሕያእ ሌሎችም ጥቂት ማይባሉ እውቀታቸውን በይፋ የሚያስተጋቡ መፅሀፎችን ለኡማው አበርክተዋል። እንዲህ ያሉ ታዋቂ ሊሂቃን ምእመኑ ኮርቶ ወደነርሱ በመጠጋት ንግግራቸውን በማስረጃነት ቀን ከሌት መፅሀፍቶቻቸውን በመያዝ እንደሚደጋግመው ሁሉ፤ በተቃራኒው የእስልምና ጠላት የሆኑ ሰዎች የነዚህ ሊሂቃን እውቅናን በመጠቀም ጥለው በሄዱት በጎ አሻራዎች ላይ የራሳቸውን መርዝ ቀስ በቀስ በቀለሙ እንዲሁ በአይነቱ አመሳስለው ለኡማው በመስጠት ለምእመኑ የእፍረት ካባ ለማከናነብ መጣር ከጀመሩም ዋል አደር ያሉም አልጠፉም። በዛሬው ርዕሴ ኣቡ-ሐሚድ አል-ገዛልይ (ሑጀቱል ኢስላም) በአህሉል ቢድዓዎች ላይ ከነርሱ ውስጥም ሙጀሲማ የሚሰኙት አንጃዎች ላይ ያላቸው ፅኑ አቋም ምን ይመስል ነበር የሚለውን ኪታቦቻቸውን እያስደገፍኩ አጠር ባለ መልኩ በማስረጃ የማቀርብ ይሆናል። ¤ በመጀመርያ ሑጀቱል-ኢስላም ኣቡ'ሓሚድ አል-ገዛልይ ኢ'ልጃሙል ዓዋም ፊይ ዒልሚል ከላም በተሰኘ ኪታባቸው ላይ ገፅ 96 ላይ እንዲህ ሲሉ ያሰፈሩትን እንመልከት፦ * قال في إلجام العوام 〔وأن من عبد جسماً فقد عبد صنماً سواء كان الجسم صغيراً أو كبيراً، قبيحاً أو جميلاً، سافلاً أو عالياً على الأرض أو على العرش، فكان نفي الجسمية ونفي لوازمها معلوماً لكافتهم على الضرورة بإعلام رسول الله صلى الله عليه وسلم والمبالغة على التنزيه لقوله: لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ ) سورة الشورى: (۱۱〕 ① [“ፈጣሪ ብሎ ያሰበው "አካል" ትንሽ አልያ ትልቅ፣አስጠሊታ አልያ ቆንጆ፣ከላይ ያለ ወይም ከታች ፣በምድር አልያ ከዓርሽ በላይ ብሎ ብያስበውም፤ አካልን የተገዛ #ጣኦትን እንደተገዛ ነው። አካልን ሆነ አካልን የሚያሲዙ ነገራቶች ከአሏህ የራቁ እንደሆኑ ሁሉ በሚጋራው መልኩ በነብዩ አድራሺነት እንዲሁ አሏህን በሚያጠሩ አናቅፅቶች የተሰራጨ ሲሆን ይህም <እርሱን ሚመስል የለም፤እርሱም ሰሚም ተመልካች ነው> የሚለውን የመሰለ አንቀፅን ይገኝበታል።”] ๏ አል-ገዛልይ ፈጣሪውን ጅስም አድርጎ የሳለ አልያ ያሰበ ሰው ከጣኦት አምላኪ ጋር ማመሳሰላቸው ጎልቶ የሚታይ ሐቅ ሲሆን ያን አካልም አቆሞ አልያ አስቀምጦ፣ ጭራቅ አልያ የውበት ሞዴል ቢያደርገውም አንዳች ልዩነት እንደማይፈጥር አስፍረዋል። ¤ ሑጀቱል-ኢስላም ኣል-ሙስተስፋ የተሰኘው ኪታባቸው ላይ በገፅ 332 በተመሳሳይ የሙጀሲም ዕምነት ከሚያከፍሩ የእምነት አይነቶች የሚመደብ መሆኑን ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ፦ *وقال الغزالي في المستصفى ”أما إذا كفر ببدعته، فعند ذلك لا يعتبر خلافه، وإن كان يصلي إلى القبلة ويعتقد نفسه مسلماً.لأن الأمة ليست عبارة عن المصلين إلى القبلة، بل عن المؤمنين، وهو كافر، وإن كان لا يدري أنه كافر“ ② [«በቢድዓው የከፈረ እንደሆነ በዛ ግዜ ልዩነቱ ቦታ አይሰጠውም።ወደ ቂብላ ዞሮ በመስገድ እራሱን ሙስሊም አድርጎ ቢያስብም፤ ምክነያቱም ኡማህ ሲባል ወደ ቂብላ ዞረው የሚሰግዱ ሰዎች ገለፃ ሳትሆን ይልቅንስ የትክክለኛ አማኞች ናት።ይህ ደግሞ ካ*ፊር ነው።መክፈሩን ባያውቅም»]። ¤ በተመሳሳይ መልኩ ከመሞታቸው ከሶስት ቀን በፊት በፃፉበት የመጨረሻ ኪታባቸው ከሚሰኘው ውስጥ አንዱ የሆነው በኢልጃሙል ዓዋም ገፅ 5 ላይ ፍንትዋ አድርገው ሽምያ፣ማሽሟጠጥ ሆነ ማጣመም በማይቀመስበት ቃላት የሙጀሲምን ከሃዲነት በኢጅማዕ መሆኑን ያሰፍራሉ፦ وقال أبو حَامِدٍ الغَزَالِيُّ في كتابِهِ المسمَّى إِلْجَامَ العَوَامِّ عَنْ عِلْمِ الكَلَامِ ما نَصُّهُ: «فَإِنْ خَطَرَ ببالِهِ أَنَّ اللهَ جسمٌ مُرَكَّبٌ مِنْ أعضاءٍ فهو عابدُ صَنَمٍ؛ فَإِنَّ كُلَّ جسمٍ هو مخلوقٌ، وعبادةُ المخلوقِ كفرٌ، وعبادةُ الصنمِ كفرٌ لأَنَّهُ مخلوقٌ، وكان مخلوقًا لأَنَّهُ جسمٌ، فَمَنْ عَبَدَ جسمًا فهو كافرٌ بإجماعِ الأُمَّةِ السَّلَفُ منهم والخَلَفُ».اهـ ③[“በአዕምሮ ላይ አሏህን ከክፍለ አካላት የተገጣጠመ ነው ብሎ ካመነ ይህ ሰው #ጣዎትን አምላኪ ነው። ሁሉም አካሎች ፍጡሮች ናቸው። ፍጡርን መገዛት ደግሞ ኩፍር ነው።ጧኦትን ማምለክ ኩፍር ነው ምክነያቱም ፍጡር ስለሆነ። ፍጡር የሆነውም አካል ስለሆነ ነው።አካልን የተገዛ ደግሞ #በዑለማዎች የጋራ አቋም ከሀዲ ነው”]። ¤ ይህም ብቻ ሳይሆን በሙጀሲምና በፀሀይ አምላኪ መሀል ልዩነት እንደሌለም በኣሊቅቲሷድ ፊል ዒቲቃድ ገፅ 34 ላይ ሲጠቅሱ ይህን ይላሉ፦ فإن القائل بأن الله سبحانه جسم وعابد الوثن والشمس واحد〕 [“አሏህን አካል ነው ብሎ የሚል እንዲሁ ጣኦትና ፀሀይ የሚገዙ ሰዎች #አንድ ናቸው”] ∅ አንተ እውነትን ፈላጊ ሆይ ሐቅን ከመናገር ምኑ ነው ሚያስፈራህ?! ኣቡ ሐሚድ መጨረሻ ከእርሱ ቡሀሏ ሌላን ለመፃፍ ብእራቸውን አላነሱም በተባለበት ኢልጃሙል ዐዋም ኪታብ ላይ ሙጀሲማዎች ካፊር ናቸው። ይህም ኢጅማዕን በመመርኮዝ ነው ሲሉህ በግልፅ ፈንትው አድርገው ገልፀውልሀል።ከዚህ ሁሉ ማስረጃ ቡሀሏ ተጨምሮባቸው ነው የሚለው ቢያደናግርህ እውን ከአሏህ ውጪ ያለን በአሏህ ስያሜ አድርጎ ሚገዛን ሙስሊም አድርጎ ሚያስብ ኢማም አለን? እንዲሁ ኺላፍም ተነቅሏል ለማለት ምን ነክቶህ በምንስ ታውረህ ነው?! አሏህን በዲናችን ላይ ከሚመጣ አደጋ ሰላምን እንጠይቀዋለን። ሸይኽ ዓብዱሏህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦ سلامةُ الدينِ لا يعادلُها شيءٌ [የዲን ሰላም መሆን ምትክ የለውም]። ↘ በስተመጨረሻም ወንድማዊ ምክሬ የሚሆነው ኪታብን በማንበብ ብቻ እውቀት አይያዝም። ማንበብን ብቻ ተመርኩዞ እውቀት ለመሰብሰብ ሲደከርት የከረመ ሸይኩ ሸይጧኑ ሆኖ እንጂ አልታየም።ለዚህም ታላቁ የሰለፍ ዓሊም ሰሕኑን አል-ማሊክይ ኪታብን (ከመርካቶ) እየሸመቱ ፈትዋ ሚሰጡ ሰዎችን እንዲህ በማለት ይገስፃሉ፦
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
«ባንቱ በመቅራቴ ልቅና ይሰማኛል» "እኛ የአሏህ ነን ወደ አሏህም ተመላሾች ነን" የአስ-ሱናህ ቲቪ ኸሚስን በአስ-ሱናህ ባልደረባ የነበሩትና በበርካታ የዲን ማዕከላት እንዲሁም የሚዲያ አማራጮች ዲንን በማስተማር ላይ የነበሩት ኡስታዝ ሙሐመድ ሰዒድ ባጋጠማቸው ድንገተኛ የመኪና አደጋ ሕይዎታቸው አልፏል።በኡስታዛችን ሙሐመድ ሰዒድ ሕይዎት ማለፍ የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅኩ ለቤተሰቦቻቸው ፤ ለተማሪዎቻቸው…
๏ ሸይኹና ሸይኽ ዑመር ኢማም አሏህ ይጠብቃቸውና በቂርአት መሀል ሳለን ወደ አንድ እጅግ አስተውሎት ስለሚሻ፡ እጃችንም ላይ ስላለ ትልቅ ጀውሃር እንዲህ ሲሉ አስታወሱን፦[“ሸይኽ ዓብዱሏህ¹ ረሒመሁሏህ በኣ'ሲራጥ ኪታባቸው ላይ አንድ ፀሀይን የሚገዛ ሰው ከነዛህ ሙሸቢሃዎች መሀከል አንዱን በአዕምሮ ማስረጃ ብቻ ለውይይት ቢፈልገው ፀሀይ ሚገዛው ያሸንፈዋል ሲሉ መናገራቸው በነ እፎይ ይገለጥልሀል” አሉ]። ¹ هو الشيخُ الحافظُ معلمُ التوحيدِ مجددُ زمانِه خادم علم الحديث عبد الله بن محمد بن يوسف الهرري الحبشي. መልካም ጁሙዓህ።
በስተመጨረሻ፦በነዚህ ርዕሶች ላይ #አደም ሙሐመድ ለውይይት እጠራሀለው።በፈለከው ግዜና ሰኣትም እንዲሆን ይደረጋል።ለዚህም ጥሪ ዝግጁ ከሆንክ በግዜ በማሳወቅ ለውይይቱ መንገድ ልታቀል ዘንዳ እጠይቃለው።
በማለት ኢብን ተ'ይሚያን ነፃ ለማድረግ ሐዲሱን በደንብ ባለመረዳት እመት ዐኢሻህን ረዲየሏሁ ዓንሃ በፈጣሪዋ ላይ ባላት እምነት ጎዶሎ ማድረግ ውጤቱ ሆኗል። ለዚህም በቅርቡ በአዲስ ዝግጅት እመለስበታለው። ሌላው በተእዊል ከሆነ ብሎ ኢብን ተ'ይሚያን ላለማክፈር ያነሳቸው ደዋቢጦች ኢብን ተ'ይሚያህ ሚያህል ሓፊዝ በየትኛውም በተጠቀሱ የስድ ደዋቢጦች ዓቂል፣ባሊግ ሆኖ ያለ ምላስ ወለምታ እስከተናገረው ድረስ ተእዊል የሚለው በዚህ ቀጥዕይ ጉዳይ ላይ ላለመክፈር ዑዝር ሊያሰጠው የሚችል ምንም ነገር ፈፅሞን አይኖርም።ለዚህም ረምልይ ባዘጋጁዋት በሚንሃጅ ሸርሓቸው ላይ አሕመድ ብኑ ዓብዲረዛቅ አል-መግሪቢይ አ'ረሺድይ በመባል ሚታቁት 1096 አመተ ሂጅራ የሞቱት እንዲህ ሲሉ የተእዊል ጉዳይ በስድ ለሁሉ ነጥብ ድርሻን ይዞ እንደ ዓቂል መሆን የሚጠየቅበት እንዳልሆነ በዚህ መልኩ ያስረዳሉ፦ قَالَ الْمُحَشِّي عَلَى الرَّمْلِيِّ أَحْمَدُ بنُ عَبْدِ الرَّزَّاقِ الْمَعْرُوفُ بِالْمَغْرِبِيِّ الرَّشِيدِيِّ الْمُتَوَفَّى سَنَةَ أَلْفٍ وَسِتٍّ وَتِسْعِينَ «قَوْلُهُ «وَاجْتِهَادٍ» أَيْ فِيمَا لَمْ يَقُمِ الدَّلِيلُ الْقَاطِعُ عَلَى خِلافِهِ بِدَلِيلِ كُفْرِ نَحْوِ الْقَائِلِينَ بِقِدَمِ الْعَالَمِ مَعَ أَنَّهُ بِالِاجْتِهَادِ» اهـ [“(ኢጅቲሃድ አልያ በተእዊል) ማለታቸው ከእርሱ በተቃራኒ ማስረጃ ባልቆመበት ላይ ነው።ለዚህም ዐለምን ጅምር የላትም በማለት የከፈሩ ሰዎችን የመሰለ: ይህም ከነርሱ በኢጅቲሃድ (ተእዊል) ከመሆኑም ጋር ነው”] በማለት ተእዊል ማድረግ ሁሌ ኩፍር ላይ ከመውደቅ እንደማይከለክልና በነዚህ ባሉ ቦታዎች ደግሞ ፈፅሞን እንደ ቅድመ ሁኔታ እንደማይታይ ያስቀምጣሉ።ዓለምን ጅምር የላትም ያሉ ሰዎች በተእዊል ቢሆንም ነገር ግን ተእዊል ሁሌ ተክፊርን አይከለክልምና፤ ይህን ያለ ሰው ይከፍራል ሲሉ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ማለት ይህ ነው። አንደኛው ተእዊል ሁሉ ቦታ ኩፍር እንደማይከለክልና። ሁለተኛ ኢብን ተ'ይሚያህ በዚህ ንግግሩ ካፊር እንደሆነ እየገለፁ ነው።ኢብን ተ'ይሚያህ በዚህ ዓለምን ጅማሬ የላትም ባለበት ንግግሩ የቁርኣንና የሓዲስን ህግጋቶች ከመተላለፉ አልፎ በዚህም አቋሙ ላይ እርሱን የማክፈር ብያኔ ከምስራቅ እስከ ምዕራቡ ዳርቻ ያሉት ምእመናን እንደሰጡ በጥቂቱ እንገልፃለን ከነርሱ መሀከልም፦ وقال الحافظ اللغوي محمد مرتضى الزبيدي في شرح الإحياء عند الكلام على تكفير الفلاسفة ما نصه (21) "ومن ذلك قولهم بقدم العالم وأزليته، فلم يذهب أحد من المسلمين إلى شىء من ذلك" اهـ، ① አል-ሓፊዙ አ'ሉገውዩ ሙሐመድ ሙርተዶ ኣ'ዘቢድይ "ኢትሓፉ ሳዳቲል ሙተቂይን"ብለው በሰየሙት ኪታብ ላይ ስለ ፋላስፋዎች መክፈር ሲጠቅሱ ይህን ይላሉ፦[“ከንግግራቸው መሀከል ዓለም ጅምር የላትም የሚለው ይገኝበታል። አንድም ሙስሊም እነርሱ ባሉበት የተጓዘ የለም”]። ይህ ከሳቸው የተሰጠ የተክፊር ፍርድ እንደሆነ ልብ ሊባል ይገባል። ምክነያቱም በዚህ መንገድ የተጓዘ እንደሆነ ሙስሊም የለም፤ ሲሉ በዛ መንገድ የተጓዘ ኢማኑ የተነጠቀ እንደሚሆን አስምረውበታል። وقال الحافظ ابن حجر العسقلاني في فتح الباري (20) ما نصه "قال شيخنا- يعني العراقي- في شرح الترمذي: الصحيح في تكفير منكر الإجماع تقييده بإنكار ما يعلم وجوبه من الدين بالضرورة كالصلوات الخمس، ومنهم من عبر بإنكار ما علم وجوبه بالتواتر، ومنه القول بحدوث العالم، وقد حكى القاضي عياض وغيره الإجماع على تكفير من يقول بقدم العالم، ② አል-ሓፊዙ ኢብኑ ሓጀር አል-ዓስቀላንይ "ፈትሑል ባሪይ" በተሰኘው የሶሒሑል ቡኽርይ ሸርሓቸው ላይ ይህን ሲሉ ያስቀምጣሉ፦[“ሸይኻችን (ኣል-ዒራቅይ ማለታቸው ነው)በሸርሑ ኣ'ቲርሚዝይ ላይ"ኢጅማዕን የጣሰ ይከፍራል" የሚለው ንግግር ትክክሉ "ኢጅማዕ የተደረሰበት ነጥብ ግዴታነቱ ሁሉ ዘንዳ የተሰራጨ በሆነ ጉዳይ መሆን አለበት" ተብሎ መለየት ያስፈልገዋል። ለምሳሌ እንደ አምስት ግዜያት ሶለዋቶችን ያለ ይመስል።ከነኚህ ዑለማዎችም መሀከል ስለዚህ ገለፃ ሲያደርግ "ግዴታነቱ በተዋቱር የመጣን ነገር መቃወም በማለት ያስቀምጣሉ"። ከዚህ ጉዳይ መሀከልም የዓለም ጅማሬ መኖር ይገኝበታል።አልቃዲይ ዒያድ እንዲሁ ሌሎችም “ዓለምን ጅማሬ የላትም ብሎ በተናገረ ላይ #ካፊር እንደሆነ የጋራ አቋም አስቀምጠዋል”]። وقال في موضعءاخر منه ما نصه (22) "وقال السبكي في شرح عقيدة ابن الحاجب: اعلم أن حكم الجواهر والأعراض كلها الحدوث،ا فإذًا العالم كله حادث، وعلى هذا إجماع المسلمين بل وكل الملل، ومن خالف في ذلك فهو كافر لمخالفة الإجماع القطعي" ا.هـ.ا በሌላ ቦታ ላይ በዛው ፈትሑል ባሪይ ኪታባቸው ኣ'ሱብክይ "ሸርሑ ኢብኒል ሓጂብ" ላይ እንዲህ ብለዋል ይላሉ፦[“የመጠን እንዲሁ የመጠን ባህሪያቶች ሁሏም ፍጥረት ናቸው።ስለዚህም ዓለም በጠቅላላው ፍጡር ነው። በዚህም ላይ የሙስሊሞች የጋራ አቋም #ታስሯል። ይልቅንስ ከእስልምና ውጪም ያሉ እምነቶች በዚህ ላይ ያፀናሉ። በዚህ ላይ የተቃረነ #ካፊር ነው። ምክነያቱም በቁርጥ የታወቀን የሆነ የኢጅማዕ አቋም ተላልፏልና”]። قال القاضي عياض في الشفا (19) "وكذلك نقطع على كفر من قال بقدم العالـم أو بقائه أو شك في ذلك على مذهب بعض الفلاسفة والدهرية" اهـ.ا ③ አል-ቃዲይ ዒያድ "ኣ'ሺፋ" በተሰኘው ኪታባቸው ላይ እንዲህ ይላሉ፦[“እንዲሁ እንደ ከፊል ፈላስፋዎች እንዲሁ ደህሪያዎች ዓለምን ጅማሬ የላትም አልያ ዘውታሪ ናት፤ብሎ በተናገረ አልያ በተጠራጠረ ሰው በኩፍሩ ላይ በቁርጥ #እንወስናለን”]። نقل المحدّث الأصولي بدر الدين الزركشي في تشنيف المسامع (18) اتفاق المسلمين على كفر من يقول بأزلية نوع العالم فقال بعد أن ذكر أن الفلاسفة قالوا: إن العالم قديم بمادته وصورته، وبعضهم قال: قديم المادة محدث الصورة، ما نصه "وضلَّلهم المسلمون في ذلك وكفروهم" اهـ. ④ አል-ሙሐዲሱ አል-ኡሱልዩ በድሩ ዲን አ‘ዘርከሽይ የዐለምን መሰረት ጅማሬ የለውም ያሉትን ፈላስፋዎች ንግግራቸውን በ "ተሽኒፉል መሳሚዕ" ብለው በሰየሙት ኪታብ ከጠቀሱ ቡሀሏ በዚህም በመክፈራቸው ላይ የዑለማእን የጋራ አቋም ሲያስተላልፉ እንዲህ ይላሉ፦[“በእርግጥም ሙስሊሞች በዚህ ላይ አጥምመዋቸዋል ብሎም አክፍረዋቸዋል”]። ከዚህ ሁሉ የዑለማእ የጋራ አቋም ቡሀሏ የተለመደው ኺላፍ አለበት ምትለው ማታለያቹህ የምትሰራ አትሆንም።አልያ አሏህን ፈጣሪ አይደለም ያለ ሙስሊም ነው ትላላችሁ አልያ ካፊር ነው በማለት ኢብን ተ'ይሚያን በመተው የዑለማኡል ኣዕላምን መንገድ ትይዛላችሁ።
መረጃ ይዳኘን ❿ قال الله تعالى"يُضِلُّ بِهِ كَثِيرًا وَيَهْدِي بِهِ كَثِيرًا ۚ وَمَا يُضِلُّ بِهِ إِلَّا الْفَاسِقِينَ" سورةُ البقرة ٢٦ [“ በርሱ (በምሳሌው) ብዙዎችን ያጠማል።በርሱም ብዙዎችን ያቀናል፡፡በርሱም አመፀኞችን እንጅ ሌላን አያጠምም”] "ሱረቱል በቀራህ 26" ፍትሓዊው ጌታ አሏህ ሁሉ የእርሱ ንብረት ነው። በችሮታው ያሻውን ገነት ቢያስገባ ቀሪውን በፍትሑ ቢቀጣ ውዳሴ እንዲሁ ልቅና እንጂ ፈፅሞን ውሳኔው ላይ ውግዘት አይታሰብም።ሁሉ የእርሱ ሁሉም ወደርሱ፣ ሁሉ ለእርሱ ተገዢ: ጉዳዩም ሁሉ ወደ እርሱ ተመላሽ ነውና። መሃሪው ጌታ አሏህ ነብያትን ያወጣበት ሰው የተባለን ዘር ከሁሉ ዘሮች በጥቅሉ አብልጦታል። ብሎም ይህ ዘር ከእርሱ ውስጥ ለፈጠረው ሀያል ጌታ ተገዢ እና ተዋዳቂ በትዕዛዙ በነብያቱ በኪታቡም ተመሪ ቢኖርም፤በተቃራኒው ደግሞ ሊመራበት ዘንዳ በተሰጠው መፅሀፍ አስተባባይ ሊመራው ሰበብ በመሆን በተላከለት ነብይ ክዶና አምፆ እሚገኝ ዘመን የተረከለን እልፈ አላፍ ለቁጥር ሚያዳግት ሆኖ ይገኛል። ነብዩና ሙሐመድ ﷺ በብዙ ትውፊቶቻቸው እንዲሁ ለእርሳቸው በተላከው ቁርኣን ላይ ጥቂት በማይባሉ አናቅፅቶች ውስጥ የአሏህን ፈጣሪነት የሌሎችን ፍጡርነት የአሏህን ጅማሬ አለመኖር የሌሎችን ግኝነት በዝርዝር አስፍረውና እንዲሁ ሰፍሮ ምናገኘው ከኢማን መሰረታዊ ነጥብ ከሆኑት ውስጥ የሚመደብ ችላ ማይሰኝ ትልቅ ጉዳይ ነው። አሏሁ ጀለ ጀላሉሁ በሱረቱል ኣ'ዙመር አንቀፅ 62 ላይ እንዲህም ይላል፦ قالَ اللهُ تعالى" اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ" الزمر آية 62 [“አሏህ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው”] አንድ ግለሰብ ይህን ሶሪሕ የሆነ አንቀፅ እተርጉማለው በማለት የያዘውን ፍቺ ማጣመም አይበቃለትም።በዚህም አንቀፅ አሏህ የራሱን ፈጣሪነት የሌሎችን ደግሞ ፍጡርነት አፅድቋል። ይህም ሲፈታ አሏህ ጅማሬ የለውም ሌላው ደግሞ ጅምር አለው የተገኘ ነው ሚለውን ያለ ምንም ጥርጥር የሚያስረዳ ነው። የአሏህን ኪታብም ከሁሉ በላይ ተገንዛቢ የሆኑት ትልቁ ሰው ነብዩ ሙሐመድﷺ"አልቡኻርይ" በዘገቡት ሓዲሳቸው ከየመን በሕቡእ ሆነው በመምጣት ስለ መጀመርያው ፍጡር ምንነት ለጠየቋቸው ሰዎች እንዲህ ሲሉ መልሰዋል፦ قالَ عليه الصَّلاةُ السَّلامُ "كانَ اللهُ ولَم يَكُنْ شَيءٌ غَيرُه" رواهُ البخاريُّ [“አሏህ ነበር ምንም ነገር ከመኖሩ በፊት”]። ይህ ሓዲስ ብዙ ቁም ነገሮችን ይዟል።ነገር ግን የማስረጃ ቦታውን በመጥቀስ ሲታጠር ነብዩ ﷺ ለነኚህ ሰዎች በመጀመርያ የአሏህን ጅማሬ አለመኖር አፅድቀውላቸዋል።ምክነያቱም ከእውቀቶች ሁሉ ሊቀደም የሚገባው አሏህን ማወቅ እንደሆነ እኚህ ትልቁ ሰው በመንገዳቸው ምልክት እየሰጡን ነው።ቀጥሎም ከእርሱ ውጪ ያለ በጠቅላላ ከእርሱ ጋር እንዳልነበርና አሏህ እንደፈጠረው ገለፃ አድርገዋል።ሐዲሱም ይቀጥላል… ብሎም አንድ ሰው ነብዩﷺያሉት ከእርሱ ውጪ ምንም አልነበረም ቢሆንም ነገር ግን "ምንም" የሚለው ቃል በራሱ ጥቅላዊ ውጤት እንዴት ያሲዛል ካለ እኛም በምላሹ ዑለማዎች ዘንዳም ምትታወቅ አንድ መመርያ አለች እርሷም "ነኪራህ የሆነች ቃል በነፍይ የንግግር ዘይቤ ላይ ከመጣች ጥቅላዊ ትርጉምን ትሰጣለች" ይህም ማለት ነብዩﷺሓዲሳቸው ላይ "شيء" የሚልን ቃል ተጠቅመዋል ይህች "ነኪራህ" ትሰኛለች። "ነፍይ" ደግሞ "لَمْ" የምትሰኘዋ ናት። ሁለቱ በአንድ ዐ.ነገር ሲጣመሩ ትርጉማቸው ጥቅልን የሚያሲዝ በዚህ ሓዲስ ደግሞ ከአሏህ ውጪ ያለን የሁሉንም ጅማሬ አለመኖር የሚያስክድ፤ፍጥሩነቱን ደግሞ የሚያፀና ነው።በዚህም ጅማሬ አለመኖርን ለአሏህ ብቻ የሚያረጋግጥ ይሆናል በማለት ገለፃ እናደርግለታለን”]። በዚህ ርዕስ በዒልማቸው ከጠመሙ ሰዎች መሀከል ኢብን ተ'ይሚያህ አል-ሓራንይ አንዱ ሲሆን በዚህም የፈላስፋዎችን መንገድ በመከተል ዓለም ጅምር የላትም(አሏህ አልፈጠረውም) በማለት "መጅሙዑ'ል ፈተዋ" በተሰኘው ኪታቡ ላይ ሙጀለድ 10 ገፅ 142 ላይ እንዲህ ሲል ያሰፍራል፦ ففي كتابه المسمى مجموع الفتاوى، المجلد العاشر، صحيفة 142، يقول ابن تيمية(وإن قدر أن نوعها لم يزل مع الله فهذه المعية لم ينفها شرع ولا عقل) وهذا من أشنع الكفر. [“የዓለም መሰረቱ ጅማሬ የለውም የሚለው ታሳቢ ተደርጎ ከሆነ "የዓለምን መሰረት ጅማሬ አለመኖር ሸሪዓም ሆነ አዕምሮ አይክደውም”]። በማለት ሽምጥጥ አድርጎ እረ ሸሪዓ እራሱ የዓለምን ጅማሬ አለመኖር አይክድም፤ አዕምሮ ሊክደው ይቅርና!? በማለት እጅ በአፍ በሉት እጅ በእግር የሚያሲዝ ዓቂል ሊያምንበት ቀርቶ እብድ ሊናገረው ሚከብድ ሃሳብ ሲያንተርስ ይታያል። ይህን የመሳሰሉ ጥመቶቹን በይፋ ለተመለከተ ዘይኑዲን አል-ዒራቅይ ስለ ኢብን ተ'ይሚያህ "ኣል-አጅዊበቱል-መርዲያህ" ብለው በሰየሙት ኪታብ ላይ እንዲህ በማለት መሳለቃቸው እውን ነው ያስብላል፦ عِلْمُهُ أكبرُ من عقلِهِ [“እውቀቱ ከጭንቅላቱ የበለጠ ነው”] ውዳሴ መስሎህ እንዳትሞኝ ይልቅንስ ጆሮ ሚያሲዝ ውግዘት እንጂ።የሆነው ሆኖ ነብይ የተላከለትና ተኣምራትን ከሙሳ ዓለይሂ ሰላም የተመለከተም ፊርዓውን ፈጣሪ ነኝ ከማለት አልተመለሰምና፤ ነገርዪው በእውቀት ብቻ ምንከላከለው ሳይሆን ቁልፉ ያማረ አሟሟት መሆኑን መዘንጋት የፊርዓውንና የኢብን ተ'ይሚያህን መጨረሻ ላየ ሚደበቅ አይሆንም።ለዛም ነው የገትይ ደረሳ የሆኑት አ'ሸይኽ ጀውሃር ብኑ ሓይደር፦ يَا ربّنَا بِحُسنِ الختامِ [“ጌታችን ሆይ መልካም አሟሟትን”] በማለት ቀን ከሌት ሲማፀኑ የመዋላቸው ሚስጥር፤ በመሆኑም ከቅርብ ግዜ ወዲህ ለኢብን ተ'ይሚያህ የተለያዩ ማዕረጎችን በመለጠፍ ለዚህ ግልፅ ለሆነው የኩ*ፍ*ር ንግግሩ ለመከላከል ሲጋጋጥ ያገኘሁት #አደም ሙሐመድ ይህን ንግግር ባልሰማ ጆሮ ዳባ በማለት ኢብን ተ'ይሚያህን ሸይኽል ኢስላም ብሎ እስከመሰየም የመዳፈሩን ጉዳይ ስንመለከት ይህ ከናዳ ማውረድ ዑለማእን ኮርስ የመስጠት የዳና መውረድ አጀንዳ በነርሱ ላይ የተያዘ ስላቅ እንጂ ለፍሬ የታጨ ጉዳይ አለመሆኑ ልብ ያስብለናል። በነገራችን ላይ ከኮርሱ ስላቅ በፊት በብዙ ጉዳዮች ላይ ከጅምሩ የውድቀትን መንገድ እያስተናገደ የመጣው አደም ሙሐመድ በቅርቡ "ዶዋቢጡ ተክፊር" ብላ በተሰየመችው ሪሳላህ ስለ መክፈርያ ነጥቦቹ ሲዘረዝር ለሰማው ጉድ ለካ ጅህልናም እንዲህ ይሰፍራልን በማለት ማስተዛዘቡ አይቀሪ ነው። እንዲሁ አንዱ ከሌላው ሚጣረስና ከተሕቂቅ በፀዱ ንግግሮች መመርኮዙን ላስተዋለ የዒልም ሰው ሳይሆን የህልም ሰው መሆኑን ያውጃል። በመሆኑም የዓለምን ጅማሬ አለመኖር የሚያምነው ኢብን ተ'ይሚያህ ከራሱ አልፎ እነ ተቂዩዲን ኣ'ሱብክይም ይህን ንግግሩን በምስክርነት አኑረውታል።ይህንንም መካድ የነኚህን ታላላቅ ዑለማእ አመኔታ ማራቆት ተደርጎ ያስወነጅላል። ኢብን ተ'ይሚያን በዚህ ንግግሩ ላለማክፈር ዑዝር ለመፈለግ አደም ሙሐመድ ያነሳቸውን ማስረጃ ለተመለከተ በግዜ አቁሙሉን የሚል ጠያቂም ከተመልካች አይጠፋም። ከዛ ውስጥ አንዱ የእናታችን ዓኢሻህን (አሏህ በሰዎች የውስጥ ሚስጥር) ምንም ነገር ከእርሱ እንደማይደበቅበት አታውቅም ነበር በማለት ነብዩም "አሏህ ያውቃልን" በሚለው በዚህ ጥያቄዋ "አዎ ያውቃል" የሚል መልስ እንጂ አላከፈሯትምና: አንዳንድ በጅህልና ዑዝር ሚሰጡባቸው ባህሪዎች አሉ
видео или голосовое, без подписи