tgindex
ባሕራን ሚዲያ አ/ኅ/ደ/ም/ቅዱስ ሚካኤል ካ/ሰ/ት/ቤት

ባሕራን ሚዲያ አ/ኅ/ደ/ም/ቅዱስ ሚካኤል ካ/ሰ/ት/ቤት

Статистика

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ሰንበት ት/ቤት ዩቱዩብ https://youtube.com/channel/UCfs9sQ51kB6zs4hgWZueEFQ ቲክቶክ @bahranmedia12 Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=61562025038863&mibextid=ZbWKwL Instagram @Bahran_Media_Official

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
2
Всего постов
29
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 471
+5 за 4 дн.
Сутки
−1
−0,04%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
631
29 постов
Вовлечённость
25,5%
к подписчикам
Постов в день
0,3
всего 29
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
327
1/48двое суток
374
1/72трое суток
404

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ዲጂታል ስብከት የዲጂታሉ ዓለምን እንዴት ለወንጌል እንደምንጠቀምበት የምንማርበት ልዩ መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል፤ መጥተው ይሳተፉ! አዘጋጅ፦ የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ሰንበት ት/ቤት 🗓 ቀን፦ እሑድ፣ ነሃሴ 10 / 2018 ዓ.ም ⏰ ሰዓት፦ ረፋድ 4፡30 📍 ቦታ፦ በሰንበት ት/ቤቷ አዳራሽ 🌟 #በነጻ_ይሳተፉ – መግቢያው በነጻ ሲሆን ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!   Digital Evangelism Join us for a special program on how to utilize the digital world for Gospel ministry. Organizer: African Union Debre Mihret St. Michael Cathedral Sunday School 🗓 Date: August 16, 2026 ⏰ Time: 10:30 AM (4:30 AM Local Time) 📍 Venue: Sunday School Hall #FreeAdmission #ሰንበትትምህርትቤት #ቅዱስሚካኤል #አፍሪካኅብረት #ባሕራንሚዲያ #ኢትዮጵያ #DigitalPreaching #DigitalEvangelism #Tewahedo #OrthodoxEvangelism #DigitalMinistry #FaithInTheDigitalAge #StMichael #AfricanUnion #BahranMedia #EthiopianOrthodox #AddisAbaba #EOTC #FreeEvent Follow Bahran Media on social media and become part of our family! የባሕራን ሚዲያ የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! 👉 ዩቲዩብ / Youtube 👉 ፌስቡክ / Facebook 👉 ቲክቶክ / Tiktok 👉 ኢንስታግራም / Instagram 👉 ቴሌግራም / Telegram

  • #የፍልሰታ_ጾምን ምክንያት በማድረግ ቤተ መጽሐፍታችን ለአንባቢያን ከምሽት 12፡00 ሰዓት እስከ ማታ 4፡15 ድረስ ክፍት መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን። እስከ ነሃሴ 15 ብቻ In observance of the #Filseta_Fast, we are pleased to announce that our library will be open for readers in the evening from 6:00 PM to 10:15 PM. Notice: Valid until Nehase 15 (August 21) only. Follow Bahran Media on social media and become part of our family! የባሕራን ሚዲያ የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! 👉 ዩቲዩብ / Youtube 👉 ፌስቡክ / Facebook 👉 ቲክቶክ / Tiktok 👉 ኢንስታግራም / Instagram 👉 ቴሌግራም / Telegram

  • ነገ ነሃሴ 03 / 2018 ዓ.ም ረፋድ 4፡30 ጀምሮ 🛡 የዲጂታሉ ዓለም ምስጢራዊ ፈተናዎች በዲጂታሉ ዓለም ውስጥ ያሉትን ተፅዕኖዎች፣ ስውር አደጋዎች እና ሊኖረን የሚገባውን ጥንቃቄ የምንማርበት ልዩ መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል፤ መጥተው ይሳተፉ! አዘጋጅ፦ የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ሰንበት ት/ቤት 🗓 ቀን፦ እሑድ፣ ነሃሴ 03 / 2018 ዓ.ም ⏰ ሰዓት፦ ረፋድ 4፡30 📍 ቦታ፦ በሰንበት ት/ቤቷ አዳራሽ 🌟 #በነጻ_ይሳተፉ – መግቢያው በነጻ ሲሆን ሁሉም ተጋብዘዋል!   🛡 The Dark Side of the Digital World Organizer: African Union Debre Mihret St. Michael Cathedral Sunday School 🗓 Date: August 9, 2026 (Nehase 03, 2018 E.C.) ⏰ Time: 10:30 AM (4:30 AM Local Time) 📍 Venue: Sunday School Hall #FreeAdmission #የዲጂታልዓለም #ሰንበትትምህርትቤት #ቅዱስሚካኤል #አፍሪካኅብረት #ባሕራንሚዲያ #ኢትዮጵያ #DigitalWorld #YouthMinistry #StMichael #AfricanUnion #BahranMedia #EthiopianOrthodox #AddisAbaba #EOTC #FreeEvent Follow Bahran Media on social media and become part of our family! የባሕራን ሚዲያ የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! 👉 ዩቲዩብ / Youtube 👉 ፌስቡክ / Facebook 👉 ቲክቶክ / Tiktok 👉 ኢንስታግራም / Instagram 👉 ቴሌግራም / Telegram

  • ጾመ ፍልሰታ/ጾመ ማርያም/ #ፍልሰታ ማለት ፈለሰ፤ተሰደደ፤ተጓዘ፤ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሄደ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ «ፈለሰት ማርያም እምዘይበሊ ኀበኢይበሊ፤ ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም፣ ከምድር ሕይወት ወደ ሰማያዊ ሕይወት፣ ተሻገረች» በማለት ፍልሰታ የሚለውን ቃል ትርጓሜ አመሥጥሮ ገልጾታል፡፡ ጾመ ፍልሰታ ከእመቤታችን ድንግል ማርያም የዕረፍት ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ እመቤታችን በዚህ ዓለም ፷፬ ዓመታትን በሕይወተ ሥጋ ከቆየች በኋላ ጌታችን የእናቱን ተድላ ነፍሷን እንጂ ተድላ ሥጋዋን አይወድምና ጥር ፳፩ ቀን ፵፱ ዓመተ ምሕርት አረፈች፡፡ ዕረፍቷም እንደሌላው ሰው በሕማምና በድካም አይደለም፡፡ በገነት ዕፀዋት መዓዛ ተመስጣ ቅድስት ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይታለች፡፡ ታሪኩ በነገረ ማርያም እንደተጻፈው ሐዋርያት እመቤታችንን በአጎበር አድርገው አክብረው ወደጌቴሴማኒ መካነ መቃብር ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉም ነበርና ቀድሞ ልጇን ተነሣ ዐረገ እያሉ ሲያውኩ ኖረዋል፤  እርሷን ደግሞ ተነሣች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን ነውና «ኑ የማርያምን ሥጋ በእሳት እናቃጥለው» ብለው በምቀኝነት ተነሱ፡፡ ከመካከላቸው አንድ ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ከሐዋርያት እጅ ለመንጠቅ ዘሎ ሄዶ የአልጋውን ሸንኮር ሲይዝ የታዘዘ መልአክ በረቂቅ ሰይፉ እጆቹን ቆረጠው፡፡ እጆቹም በአልጋው ሸንኮር ላይ ተንጠልጥለው ቀሩ፡፡ የምሕረት እናት የሆነችው ድንግል ማርያም ቅዱስ ጴጥሮስ ጸልዮ እጆቹን እንዲመልስለት ነግራው እንደነበረ አድርጎለታል፡፡ የእመቤታችን ሥጋዋን መላእክት ከዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር ወስደው አስቀምጠውታል፡፡ ሥጋዋ ያለበትን ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ አይቶ እነርሱ ባለማየታቸው እመቤታችን ባረፈች በ፮ኛው ወር ከነሐሴ ፩ ቀን እስከ ፲፬ ቀን ድረስ ከጾሙ በኋላ በ፲፬ኛው ቀን ሥጋዋን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በጌቴሴማኒ ባለው መቃብር ቀብረውታል፡፡ ከዚህ በኋላ እንደ ልጇ በ፫ኛው ቀን ተነሥታ መላእክት እየዘመሩላት ወደሰማያት ስታርግ፤ ሐዋርያው ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሰ ዕርገቷን በማየቱ መላእክት «እመቤትህ እርሷ ናት፤ስገድላት» አሉት፤ እርሱም «ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ ይላል፤ከደመናው ሊወድቅ ወደደ» ምክንያቱም ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ፤ዛሬ ደግሞ የእርሷን ትንሣኤ ለማየት ብሎ ነው፡፡ እመቤታችንም «ትንሣኤየን ያየህ አንተ ነህ ሌሎቹ አላዩም» ብላ ሐዋርያት ገንዘው የቀበሩበትን የሐር ግምጃ ሰጥታ አጽናንታ ሰደደችው፡፡ ቅዱስ ቶማስ ኢየሩሳሌም ሲደርስ የእመቤታችን ነገር እንዴት ሆነ ብሎ ጠየቃቸው፤እነርሱም አግኝተው እንደቀበሯት ነገሩት፤ እርሱም ያየውን ምሥጢር በልቡ ይዞ «ሞት በጥር፤ በነሐሴ መቃብር፤ ለሰሚውም አያምር፤ይህ እንዴት ይሆናል?»፤ ቢላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ «ድሮም አንተ ተጠራጣሪ ነህ፤ማን ያርዳ የቀበረ፤ ማን ይናገር የነበረ እንዲሉ፤ ገንዘን የቀበረን እኛ እያለን እንዴት ትጠራጠራለህ» ብለው ወደ መቃብሯ ሄደው መቃብሯን ቢከፍቱት ባዶ ሆኖ አገኙት፡፡ በዚህ ተደናግጠው ተያዩ፤ በዚህ ጊዜ ቅዱስ ቶማስ «አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችን ተነሣች፤ዐረገች፤ ይኸው ምልክቱ» ብሎ ገንዘው የቀበሩበትን ሰበን አሳያቸው፤እነርሱም አምነው ሰበኗን ለበረከት ተካፈሉት፡፡ በዓመቱ ነሐሴ ፩ ቀን ሐዋርያት በመንፈሰዊ ቅናት ተነሳስተው «ቶማስ ትንሣኤዋን አይቶ እኛ ሳናይ እንዴት ይቀርብናል» በማለት ነሐሴ ፩ ቀን ሱባኤ ጀምረው በ፲፮ኛው ቀን የሐዋርያትን ሱባኤ ተቀብሎ እመቤታችንን መንበር ጴጥሮስን ተራዳኢ፣ ካህን እስጢፋኖስን ሠራዔ ዲያቆን አድርጉ ቀድሶ አቅርቧቸዋል፡፡ ከዚያ ጊዜ በኋላም ከነሐሴ ፩ እስከ ፲፭ ቀን  ጾመ ፍልሰታ ተብሎ ሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ ይጾመዋል፡፡ የጾሙና የትንሣኤዋ በረከት ተካፋይ ያድረገን፤አሜን ©ማኅበረ ቅዱሳን #ፍልሰታ #ጾም #የማርያምጾም #ማርያም #FastOfFilseta #Filseta #VirginMary #EthiopianOrthodox #EOTC #BlessedFast #Filseta2026 #BahranMedia Follow Bahran Media on social media and become part of our family! የባሕራን ሚዲያ የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! 👉 ዩቲዩብ / Youtube 👉 ፌስቡክ / Facebook 👉 ቲክቶክ / Tiktok 👉 ኢንስታግራም / Instagram 👉 ቴሌግራም / Telegram

  • 7 авг.508122

    ጾመ ፍልሰታ / ጾመ ማርያም እንኳን ለፍልሰታ ጾም (ጾመ ማርያም) በሰላም አደረሳችሁ! ጾሙን በሰላም አስጀምሮ በሰላም ያስፈጽመን የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በረከት በሁላችን ላይ ይደር Blessed Fast of Filseta (Fast of Saint Mary)! May Almighty God allow us to begin and complete this holy season in peace. May the blessings of Our Lady, the Holy Virgin Mary, be upon us all! #ፍልሰታ #ጾም #የማርያምጾም #ማርያም #FastOfFilseta #Filseta #VirginMary #EthiopianOrthodox #EOTC #BlessedFast #Filseta2026 #BahranMedia Follow Bahran Media on social media and become part of our family! የባሕራን ሚዲያ የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! 👉 ዩቲዩብ / Youtube 👉 ፌስቡክ / Facebook 👉 ቲክቶክ / Tiktok 👉 ኢንስታግራም / Instagram 👉 ቴሌግራም / Telegram

  • 6 авг.508102

    🛡 የዲጂታሉ ዓለም ምስጢራዊ ፈተናዎች በዲጂታሉ ዓለም ውስጥ ያሉትን ተፅዕኖዎች፣ ስውር አደጋዎች እና ሊኖረን የሚገባውን ጥንቃቄ የምንማርበት ልዩ መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል፤ መጥተው ይሳተፉ! አዘጋጅ፦ የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ሰንበት ት/ቤት 🗓 ቀን፦ እሑድ፣ ነሃሴ 03 / 2018 ዓ.ም ⏰ ሰዓት፦ ረፋድ 4፡30 📍 ቦታ፦ በሰንበት ት/ቤቷ አዳራሽ 🌟 #በነጻ_ይሳተፉ – መግቢያው በነጻ ሲሆን ሁሉም ተጋብዘዋል!   🛡 The Dark Side of the Digital World Organizer: African Union Debre Mihret St. Michael Cathedral Sunday School 🗓 Date: August 9, 2026 (Nehase 03, 2018 E.C.) ⏰ Time: 10:30 AM (4:30 AM Local Time) 📍 Venue: Sunday School Hall #FreeAdmission #የዲጂታልዓለም #ሰንበትትምህርትቤት #ቅዱስሚካኤል #አፍሪካኅብረት #ባሕራንሚዲያ #ኢትዮጵያ #DigitalWorld #YouthMinistry #StMichael #AfricanUnion #BahranMedia #EthiopianOrthodox #AddisAbaba #EOTC #FreeEvent Follow Bahran Media on social media and become part of our family! የባሕራን ሚዲያ የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! 👉 ዩቲዩብ / Youtube 👉 ፌስቡክ / Facebook 👉 ቲክቶክ / Tiktok 👉 ኢንስታግራም / Instagram 👉 ቴሌግራም / Telegram

  • 6 авг.454102

    ከዚህ ኣኳያ ጌታን መውደድ ማለት ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ግዙፍ ነገር እንጂ ምናባዊና የማይታይ ድብብቆሽ ነገር ኣይደለም ማለት ነው፣ ጌታችንን የመውደድ ነገር ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ከሆነ ትእዛዙ ምንድን ነው? የሚለውን ማየት ኣስፈላጊ ይሆናል፤ ትእዛዙን በጥቅል ስናይ እግዚአብሔርንና ባልንጀራን በመውደድ እንደሚጠቃለል ራሱ ጌታችን ኣስገንዝቦናል፣ በተለይም በባልንጀራችን ላይ የምንከተለው መውደድ ከላይ እንደተገለጸው “እንደራስህ ኣድርገህ ውደድ" ተብለ በግልጽ ተቀምጦኣል፤ የሰው ባልንጀራ እነማን ናቸው? በሕይወት ያሉት ናቸው? ወይስ የሞቱት? ወገን ዘመድ? ወይስ የሰው ወገን በሙሉ የሚለውንም ማወቅ ኣስፈላጊ ነው፡፡ ጌታችን ነገሩን በዚህ ደረጃ ለያይቶ ኣላስቀመጠም፣ ለምን? ቢባል ባልንጀራ ማለት የተወሰነን የማኅበረ ሰብ ወገን የሚያሳይ ሳይሆን መላውን የሰው ወገን የሚገልጽ በመሆኑ፤ እንደዚሁም የሞቱም ሆኑ ያለነው ሁላችን በእሱ ፊት ሕያዋንና እርስ በእርሳችን ባልንጀሮች በመሆናችን ነው፤ በመሆኑም መዋደዳችንም ሆነ መከባበራችን በሕይወተ ሥጋ ሳለን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ እስከ በሌለው ዕድሜ በመሆኑ ጌታችን በጊዜ በቦታና በከፊል ለይቶ ኣላስቀመጠም፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት ! ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምሮ ለ፲፭ ቀናት የምንጾመው የጾመ ማርያም መነሻ ምክንያቱ የእግዚአብሔርትእዛዝና ፍቅር ነው፣ እግዚአብሔር ሰውን በኣጠቃላይ በተለይም ደግሞ እንደፈቃዱ የኖሩ ቅዱሳንን እንድናከብርኣዞናል ክቅዱሳን ፍጥረታት መካክል ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች፤ ይህም በመሆኑ ከፍጥረት ወገን ከሏ ክብር የሚደርስ ባለመኖሩ ከሁሉም ኣብልጠን እናክብራታለን፤ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ደረጃ የድንግል ማርያምን ክብር ስትገልጽ ክእግዚአብሔርና ለባስያነ እግዚአብሔር ክሆኑ ቀደምት ኣበው ተምራ ነው! በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ዕውቁ ቅዱስና ዓለም ዓቀፋዊው አባት ቅዱስ ኤፍሬም የድንግል ማርያምን ክብር! ቅድስና እና ልዕልና ሲናገር “ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል፡ ወትፈደፍድ እምሱራፌል፣ እስመ ኮነት ታቦተ ለአሓዱ ዘእምቅድስት ሥላሴ- እሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች! ከሱራፌልም ትልቃለች፣ ከቅድስት ሥላሴ ኣንዱ ለሆነው ታቦት ወይም ማደሪያ ሆናለችና" በማለት አስተምሮናል፡፡ በመሆኑም ለስሟ መታሰቢያ በሆነው በዚህ ጾም ድንግል ማርያምን በዚህ ደረጃ ስናክብርትእዛዙን እንጠብቃለን፤ ትእዛዙን በመጠበቃችን ደግሞ እሱን መውደዳችንን እናረጋግጣለን ! እኛ ድንግል ማርያምን እንድንወዳት "እናታችሁ'' ብሎ እንዳዘዘ፣ እሷም ልትወደን “ልጆችዅ ተብላ ታዛለችና ስለኛ ትጸልያለች፡፡ በጸሎቷም ከመከራ ትታደገናለች፤ በኣጠቃላይ በእግዚአብሔር' በቅዱሳንና በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት በዚህ ትእዛዝና ፍቅር በትዕይንተ ዓለም ባለች ቤተ ክርስቲያን ዘንድ የተሳሰረ ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ የጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሱባዔ የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሎትን በማስታረቅ፤ የታመሙትንና የታስሩትን በመጠየቅ፤ ቅዱስ ቍርባንን በመቀበልና ለኃጢኣታችን የንሥሐ ሥርየትን በመለመን ሱባዔውን ልናሳልፍ ይገባል፡፡ በመጨረሻም በሀገራችንም ሆነ በዓለም ዙሪያ ከባድ ስጋት የሆነው የፍጥረት ኣውዳሚ ጦርነትን በመለኮታዊ ጥበቡና ሥልጣኑ እንዲያስቆምልን በቅን ልቡና፤ በትሑት ሰብእና ሆነን እግዚአብሔርን በዚህ ሱባዔ እንድንጠይቀው ኣደራ ጭምር ኣባታዊ መልክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤ የተባረከና የተቀደስ ጾም ያድርግልን፤ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ! ወስብሐት ለእግዚአብሔር፣ አሜን! አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘኣኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

  • без подписи

  • “መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ" በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ፣ አሜን ! በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ! የሰውን ወገን ለማዳን የልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ ድንግል ማርያምን የመረጠ መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር ኣምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ጾመ ማርያም ኣደረሰን ኣደረሳችሁ! “ወእመሰ ታፈቅሩኒ ዕቀቡ ትእዛዝየ፡- ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ" (ዮሐ.14፥15)፤ ፍቅር የሕያዋን ኣካላት ረቂቅ መገናኛ ነው፣ ሕያዋን ኣካላት በውጫዊው ግዙፍ ኣካላቸው በተወሰኑ ጊዜያትና ቦታ ይገናኛሉ ፤ ስለ ጋራ ጉዳያቸውም በጋራ ይመክራሉ፤ ይበልጥም ይቀራረባሉ፡፡ ይሁንና የሕያዋን ኣካላት ግንኙነት በኣካል በጊዜና በቦታ ብቻ የተወሰነ ኣይደለም፣ በፍቅረ መንፈስ ተገናኝተውም ይግባባሉ፣ ከኣካላዊ ግንኙነት በላይ የበለጠም ይኸው ፍቅረ መንፈስ ነው፤ ከዚህ ኣንጻር እግዚአብሔርንም ማግኘት የምንችለው በዚሁ ፍቅረ መንፈስ ሆነን በእምነት ዓይን ነው! ይህም በመሆኑ ሓዋርያው ቅዱስ ዮሓንስ በመልእክቱ “በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔርይኖራል፣ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል" በማለት ያስተምረናል፣ (1ዮሐ. 4፥16) ይህም ማለት ከሱ ጋር በፍቅር ስንገናኝ፤ እሱም በኛ፣ እኛም በእሱ የመኖሩ ኩነት ይፈጠራል ማለት ነው፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! ጌታችን “አፍቅሮ ለእግዚአብሔር ኣምላክከ፤- አምላክህን እግዚአብሔርን ውደደው" በማለት በፍጹም ልባችን እንድንወደው፣ እንደዚሁም ራሳችንን በምንወድበት መጠን እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ ማዘዙን እናውቃለን፤ የመውደዳችን መለኪያ ሚዛንና መገለጫ ምልክትም ትእዛዙን ማክበርና መጠበቅ እንደሆነ “ብትወዱኝስ ትእዛዜን ጠብቁ” በማለት ኣስተምሮናል

  • без подписи

  • без подписи

  • 4 авг.634201

    በጌታ የሚሞቱ ብፁዓን ናቸው ። ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ ሥራቸው ይከተላቸዋልና ። ራዕ ፲፫ ÷ ፲፬ #በጻድቃኔ_ማርያም_የመሬት_መንሸራተት_አደጋ_ተከሰተ። በሰሜን ሸዋ ጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም በተከሰተ ርዕደ መሬትና የመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ሰው ሕይወት ሲያልፍ በ5 ሰው ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ። ከክረምቱ መግባት ጋር ተያይዞ በተከሰተው ከፍተኛ የዝናብ መዝነብና የመባርቅት ድምፅ በታላቋ ገዳማችን በጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም ርዕደ መሬትና የመሬት መንሸራተት አደጋ በድንገት በመከሰቱ ለጸበል ፣ ለሱባኤና ለመሳለም ከአራቱም አቅጣጫ በተሰበሰቡ በጻድቃኔ ማርያም ልጆችና ወዳጆች ላይ እጅግ አስደንጋጭና ልብ ሰባሪ ኀዘን በመድረሱ ከፍተኛ ኀዘን ተሰምቶናል ። በዚህ አስደንጋጭና ልብ ሰባሪ ድንገተኛ አደጋም የ14 ወገኖቻችን ሕይወት ሲያልፍ በ5 ወገኖቻችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶብን በከፍተኛ የመርዶ ኀዘን ውስጥ እንገኛለን ። በዚህ ሰኣት የሀገረ ስብከታችን ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቀሌምንጦስ በስፍራው በመገኘት ለሞቱ ወገኖቻችን ጸሎተ ፍትሐት ለተጎዱት ጸሎት ላዘኑ ወገኖቻችን የማጽናኛ ትምህርተ ወንጌልና አባታዊ ቃለ በረከት በመስጠት ላይ ይገኛሉ ። በዚህ አስደንጋጭና ልብ ሰባሪ መርዶ ሀገረ ስብከታችን የተሰማውን ጥልቅና መሪር ኀዘን እየገለጽን እግዚአብሔር አምላክ ለሞቱ ወገኖቻችን ዕረፍተ ነፍስን ለተጎዱት ፈውስን ላዘኑት መጽናናትን ይሰጥልን ዘንድ ከዕንባ ጭምር ጋር ከልባችን እንመኛለን አባ ቀሌምንጦስ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ምንጭ የአቡቀለምሲስ ሚዲያ 👉 ዩቲዩብ / Youtube 👉 ፌስቡክ / Facebook 👉 ቲክቶክ / Tiktok 👉 ኢንስታግራም / Instagram 👉 ቴሌግራም / Telegram

  • የእህቶች ጉባኤ በአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ሰንበት ት/ቤት 🗓 ቀን፦ ሐምሌ 27 / 2018 ዓ.ም ⏰ ሰዓት፦ ምሽት 12፡00 📍 ቦታ፦ በሰንበት ት/ቤቷ አዳራሽ እህትሽን ይዘሽ ነይ! Sisters' Conference Organized by: African Union Debre Mihret St. Michael Cathedral Sunday School 🗓 Date: August 3, 2026 (Hamle 27, 2018 E.C.) ⏰ Time: 6:00 PM (12:00 Local Time) 📍 Venue: Sunday School Hall Bring your sister! Follow Bahran Media on social media and become part of our family! የባሕራን ሚዲያ የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! 👉 ዩቲዩብ / Youtube 👉 ፌስቡክ / Facebook 👉 ቲክቶክ / Tiktok 👉 ኢንስታግራም / Instagram 👉 ቴሌግራም / Telegram

  • 🚨 ልዩ የወጣቶች የክረምት ስልጠና 🚨 አዘጋጅ የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ሰንበት ት/ቤት 🗓 ቀን፦ ሐምሌ 26 / 2018 ዓ.ም ⏰ ሰዓት፦ ረፋድ 4፡30 📍 ቦታ፦ በሰንበት ት/ቤቷ አዳራሽ ይጀምራል። 💸 ክፍያ፦ በስልጠናው ላይ #በነጻ ይሳተፉ 🚨 Special Youth Winter Training! 🚨 Organized by the African Union Debre Mihret Saint Michael Cathedral Sunday School. 🗓 Date: Saturday, August 2, 2026 (Hamle 26, 2018 E.C.) ⏰ Time: 10:30 AM 📍 Location: Sunday School Hall 💸 Admission: FREE OF CHARGE! Don't miss out—join us and participate for #Free! የባሕራን ሚዲያ የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! 👉 ዩቲዩብ / Youtube 👉 ፌስቡክ / Facebook 👉 ቲክቶክ / Tiktok 👉 ኢንስታግራም / Instagram 👉 ቴሌግራም / Telegram

  • 🚨 ልዩ የወጣቶች የክረምት ስልጠና 🚨 አዘጋጅ የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ሰንበት ት/ቤት 🗓 ቀን፦ ሐምሌ 26 / 2018 ዓ.ም ⏰ ሰዓት፦ ረፋድ 4፡30 📍 ቦታ፦ በሰንበት ት/ቤቷ አዳራሽ ይጀምራል። 💸 ክፍያ፦ በስልጠናው ላይ #በነጻ ይሳተፉ 🚨 Special Youth Winter Training! 🚨 Organized by the African Union Debre Mihret Saint Michael Cathedral Sunday School. 🗓 Date: Saturday, August 2, 2026 (Hamle 26, 2018 E.C.) ⏰ Time: 10:30 AM 📍 Location: Sunday School Hall 💸 Admission: FREE OF CHARGE! Don't miss out—join us and participate for #Free! የባሕራን ሚዲያ የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! 👉 ዩቲዩብ / Youtube 👉 ፌስቡክ / Facebook 👉 ቲክቶክ / Tiktok 👉 ኢንስታግራም / Instagram 👉 ቴሌግራም / Telegram

  • በቅርብ ቀን ልዩ የወጣቶች የክረምት ስልጠና በአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ሰንበት ት/ቤት #በነጻ Coming Soon! Special #Free Youth Summer Training at African Union Debre Mihret Saint Michael Cathedral Sunday School. የባሕራን ሚዲያ የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! 👉 ዩቲዩብ / Youtube 👉 ፌስቡክ / Facebook 👉 ቲክቶክ / Tiktok 👉 ኢንስታግራም / Instagram 👉 ቴሌግራም / Telegram

  • መንፈሳዊ የክረምት ትምህርት #ለወጣቶች ዕድሜ ከ18 ዓመት ጀምሮ ምዝገባ ከሰኔ 12 / 2018 ዓ.ም ጀምሮ መስከረም 10 / 2019 ዓ.ም ትምህርቱ ይጀምራል ባሉበት ሆነው ለመመዝገብ ከታች የተቀመጠውን ጎግል ፎርም ይጠቀሙ 👇👇👇 https://forms.gle/3QF9HXssawbJJzKo7 .

  • እንኳን ለሊቀ መላዕክት ቅዱስ ዑራኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም እና የበረከት እንዲሆንላችሁ የቅዱስ ዑራኤል ምልጃ እና ጥበቃ እንዳይለያችሁ እንመኛለን መልካም በዓል ሐምሌ 22 Happy Annual Feast of Saint Uriel the Archangel! May the blessings, peace, and intercessions of Saint Uriel the Archangel be with you all as you celebrate this holy feast. Happy Feast Day! Hamle 22 (July 29) የባሕራን ሚዲያ የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! 👉 ዩቲዩብ / Youtube 👉 ፌስቡክ / Facebook 👉 ቲክቶክ / Tiktok 👉 ኢንስታግራም / Instagram 👉 ቴሌግራም / Telegram

  • без подписи

  • ሐምሌ 19 እንኳን አደረሳችሁ ሐምሌ 19 መልዐኩ ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ቂርቆስ እና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ከእሳት ያዳነበት መታሰቢያ በዓል ነው። Hamle 19 Happy Feast Day! On Hamle 19, we commemorate the holy Archangel St. Gabriel delivering St. Cyriacus (St. Kirkos) and his mother St. Julitta (St. Yeluta) from the fiery furnace. የባሕራን ሚዲያ የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! 👉 ዩቲዩብ / Youtube 👉 ፌስቡክ / Facebook 👉 ቲክቶክ / Tiktok 👉 ኢንስታግራም / Instagram 👉 ቴሌግራም / Telegram