ባህረ ጥበባት
Статистика"ህዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቷል" ት. ሆሴዕ 4:6 አለማወቅ እያጠፋን ነውና እንወቅ። ለማንኛውም አስተያየትና ጥያቄ @Filoppader
- Последний пост
- 7 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 175
- 1/48двое суток
- 200
- 1/72трое суток
- 216
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
የቀን : እረኛ : የሌሊት : ጠባቂ : ቅዱስ : ሚካኤል #ሰኔ_12_ቀን ቅዱስ ሚካኤል ቅድስት አፎሚያን ከዲያብሎስ መንጋጋ ያስጣለበት እንዲሁም የባሕራንን የሞቱን ጦማር ቀዶ ሠርግ ያደረገበትን እለት ነው ። ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ልጆቿን ሰብስባ በዓልን ሰርታ በታላቅ ድምቀት ከዓመት ዓመት ታከብረዋለች ። መጋቤ ብሉይ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በተአምራቱ ዘወትር እንደሚጠብቀን ባሕረ ጥበባት ቅዱስ ያሬድ እንዲህ እያለ ይመሰክራል ፦ « የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል የቀን እረኛ የሌሊት ጠባቂ ክንፎቹ የእሳት የሆነ ዘወትር የሚጠብቀን ቅዱስ ሚካኤል የእውነት የድንኳን ከተማ ነው ። » በማለት ተናግሯል ። በዚህ መሠረት ድንኳን ከቀን ሐሩር ከሌሊት ቁር እንደሚከለሉበት ሁሉ #ቅዱስ_ሚካኤልም በቃል ኪዳኑም የሚታመኑትን ሁሉ ከምሕረት አልባው ከዲያብሎስ ደባ ከአጋንንት ድብደባ ከዚህ ዓለም ፈተና ያድነናል ይታደገናል ።
без подписи
ልደታ ለማርያም እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል አደረሰን!!! ንጽሕተ ንጹሐን፣ ቅድስተ ቅዱሳን፣ ከተለዩ የተለየች፣ ከተመረጡ የተመረጠች ክብርት እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በከበረች ቀን ግንቦት አንድ ቀን ተወለደች፡፡ የመወለዷም ነገር እንዲህ ነው፡፡ በጥሪቃና ቴክታ የተባሉ የእግዚአብሔር ሰዎች ነበሩ፤ ባለጸጎች ቢሆንም ልጅ ግን አልነበራቸውም፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ቴክታ ሕልም አለመች፡፡ ለባሏም እንዲህ ስትል ነገረችው «በራእይ ነጭ ዕንቦሳ ከማሕፀኔ ስትወጣ፤ ያችም ዕንቦሳን እየወለደች እስከ ፮ ትውልድ ስትደርስ ፮ኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃ ደግሞ ፀሐይን ስትወልድ አየሁ» አለችው፡፡ (ውዳሴ ማርያምና ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ) ባሏ በጥሪቃም «ራእዩስ ደግ ነው፤ የሚፈታልን የለም እንጂ» አላት፡፡ በማግሥቱ ለሕልም ፈቺ ሔዶ ነገረው፡፡ ሕልም ፈቺውም «እግዚአብሔር በምሕረቱ አይቷችኋል፤ በሣህሉ መግቧችኋል» ብሎ ፮ቱ እንስት ጥጆች መውለዳቸው ፯ ሴቶች ልጆች እንደሚወልዱ፤ ፯ኛይቱ በጨረቃ መመሰሏ ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ደግ ፍጥረት እንደሚወለዱ፤ የፀሐይ ነገር ግን እንደንጉሥ ያለ ይሆናል አልተገለጸልኝም ብሎ ነገረው፡፡ (ነገረ ማርያም) በጥሪቃም ለሚስቱ ሔዶ የሕልሙን ፍቺ ነገራት፡፡ በዚያም ወር የመጀመሪያዋ ሴት ልጅ ተፀነሰች፡፡ በተወለደች በ፰ኛው ቀን ሄኤሜን አሏት፤ ወላጆቿም በሥርዓት አሳደጓት፡፡ እርሷም ለአቅመ ሔዋን ስትደርስ ባል አግብታ ሴት ልጅ ወለደች፤ የሄኤሜን ልጅም ዴርዴን ትባል ነበር፡፡ ዴርዴንም እንዲሁ አድጋ ቶና የምትባል ሴት ልጅ ወለደች፡፡ ቶና ደግሞ ሲካርን ወለደች፤ሲካርም ሔርሜላን ወለደች፤ ሔርሜላም በሥርዓት አድጋ ባል ካገባች በኋላ ሐና የተባለች ልጅ ወለደች፤ሐና ማለትም በሃይማኖትና በምግባር የጸናች፤ በንጽሕና በቅድስና የኖረች ቡሩክት ክብርት ልዕልት ማለት ነው፡፡ የሐና ወላጆች ልጃቸውን በሥርዓት አሳደጓት፡፡ ለአካለ መጠን ስትደርስም ኢያቄም የተባለውን ጻድቅ ሰው አጋቧት፡፡ ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑም ኖረዋለወ። በዚያ ወራት የመካኖች መብዓ ካህናቱ አይቀበሉም ነበርና፡፡ እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኅዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር፡፡ እናም ባልና ሚስቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ፤ ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ሐሳባቸውን ተመለከተ፡፡ ክቡር ኢያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኅነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው፡፡ በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ፤ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት። ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች። ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገነች። የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርገው ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች፡፡ ከዚህም በኋላ ሐምሌ ፴ ኢያቄም ለሐና ራእይ አየ፤ ነጭ ርግብ ፯ቱን ሰማያት ሰንጥቃ ወርዳ በራሷ ስታርፍ በቀኝ ጆሮዋ ገብታ በማኅፀኗ ስታድር አየ፤ ሐናም ለኢያቄም ፀምራ ሲያስታጥቀህ መቋሚያህ አብባ አፍርታ ፍጥረት ሁሉ ሲመገባት አየሁ ብላ» ነገረቸው፡፡ ነሐሴ በባተ በሰባተኛው ቀን በዕለተ እሑድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተፀነሰች፡፡ በ፶፻፬፻፹፭ ዓመተ ዓለም በግንቦት ፩ ቀንም እመቤታችን ድንግል ማርያም ከሐና እና ከኢያቄም፡፡ በ፰ኛው ቀንም ስሟን ‹ማርያም› ብለው ሰየሟት፤ በዚህ ዓለም ካሉት ምግቦች ሁሉ ጣፋጭ «ማር» በመሆኑ እንዲሁም በገነት ካሉት ምግቦች ደግሞ «ያም»ን የሚያህል ጣፋጭ ባለመኖሩ «ማርያም» አሏት፡፡ ትርጓሜውም ‹እመቤት› ነው። ‹ደግሞም ሀብታና ስጦታ› ማለት ነው፡፡ በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነትን ያገኘንባት ናትና። የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን፤ አምላካችን እግዚአብሔር ከበዓሉ ረድኤትና በረከት ይክፈለን! (ከመጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ግንቦት) ማነው ትክክል? ወገኔ በአዘቦት ለመብላትና ለመጠጣት ያልታደለ መሆኑ ይመስለኛል ለመብላትና ለመጠጣት ሠበብ የሚፈልገው ። ከሠበቡ መካከል፤ እንደሚታወቀው ድንግል ማርያም የተወለደችው በሊባኖስ ተራራ ነውና በወቅቱ ለአራስ የሚሆን ምግብ በወቅቱ የተገኘው የእረኞች ንፍሮ ነበርና ያንን ትውፊት አስመልክቶ ክርስቲያን ወገኔ ንፍሮ ይቀቅል ነበር ። ያሁኑን ባላውቅም ድሮ ክፍለ ሀገር የግንቦት ልደታ ዕለት በየቤቱ ከውጭ ንፍሮ ይቀቀላል ፣ ማታ ደግሞ ሰብሰብ ተብሎ ንፍሮው ከቤት ውጭ ይበላል ፤ የተረፈውም እቤት አይገባም ነበር ። አሁን ግን ልደቷን አስመልክቶ በሠበቡ ለመብላት ይታረዳል ፣ ቢራ ፣ ውስኪ ፣ ጠላ ይጠጣል ፤ ይጨፈራል ፣ ይሰከራል ። ትውፊታዊውን ትተን ለመብላት ሠበብ የምናደርግበት ምክንያት እየበዛ በመሆኑ ቀጣይ ለምን ይከበራል የሚል ጥያቄ መጣ በቃ ግንቦት ልደታ ስለሆነ የሚል ይሆናል ። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ "ህዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቷል" ሆሴዕ 4፥6 @bahreTibebat @Filoppader 2018 ዓ.ም
без подписи
የአባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ታሪክ ባጭሩ 🌿 ሐዲስ ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ተክለሃይማኖት ማለት ‹‹የሃይማኖት ተክል፣ ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ›› ማለት ነው፡፡ 🌿 እግዚአብሔር አምላካችን ለኢትዮጵያ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጎ የመረጣቸው ጻድቁ አባታችን ተክለ ሃይማኖት በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኀረያ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ጻድቁ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው ‹‹አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ›› 🌿 ማለትም ‹‹አንዱ አብ ቅዱስ ነው አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው›› በማለት የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነውታል፡፡ ወላጆቻቸውም ስማቸውን ፍሥሐ ጽዮን አሏቸው፡፡ ይኸውም የጽዮን ተድላዋ ደስታዋ ማለት ነው፡፡ የወላጆቻቸው የቀድሞ ስማቸው ዘርዐ ዮሐንስና ሣራ ይባል ነበር፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከልጅነታቸው ጀምሮ በወላጅ አባታቸው በካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብ ግብረ ዲቁናን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ሲያጠኑ ቆይተው ከእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ከአቡነ ቄርሎስ (ጌርሎስ) ዲቁናንና ቅስናን ተቀብለዋል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን ቅድስት ቤተክርስቲያንን በወጣትነት ዕድሜያቸው ያገለግሉ እንደነበር በዚህ ይታወቀል፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን አባታችን ለአደን ወደ ዱር ሄደው ሳለ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦ ታያቸው፡፡ ቅዱስ አባታችንም ‹‹እንደዚህ ባለ ገናንነት የማይህ ጌታዬ ማነህ?›› ባሉት ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ‹‹ዘወትር የምጠብቅህ ካንተ የማልለይ እናትህንና አባትህንም ስላንተ ከውኃ ስጥመትና ከምርኮ ያዳንኳቸው እኔ ሚካኤል ነኝ፡፡ 🌿ከእንግዲህ አውሬ አዳኝ አትሁን፤ ሰውን ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ ሰውን በትምህርት የምታድን ሁን እንጂ ፡፡ እነሆ እግዚአብሔር ጽኑዕ ሥልጣን ሰጥቶሃልና፤ ሙት ታስነሣለህ፤ ድውያንን ትፈውሳለህ፤ አጋንንትም አንተን በመፍራት ይሸሻሉ፡፡ ስምህ ፍሥሐ ጽዮን አይሁን፤ ተክለ ሃይማኖት ይሁን እንጂ፡፡ ትርጓሜውም ተክለ አብ፥ ተክለ ወልድ፥ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው›› አላቸው፡፡ 🌿ቅዱስ ሚካኤል ይህን ሲነግራቸው ጌታችን በሥጋ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር እንደነበር ሆኖ መልከ መልካም ጎልማሳ መስሎ ታያቸው፡፡ ጌታችንም ‹‹ወዳጄ እንዴት ሰነበትክ? ቸር አለህን?›› አላቸው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ‹‹ጌታዬ ሆይ አንተ ማነህ?›› ብለው ሲጠይቁት ጌታችንም ‹‹እኔ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ነኝ፤ በእናትህ ማኅፀን ፈጥሬህ ያከበርኩህ እኔ ነኝ፡፡ በተወለድክ በሦስተኛው ቀን አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብለህ ታመሰግነኝ ዘንድ የምስጋና ሀብት ያሳደርኩብህ እኔ ነኝ፡፡ በርሃብ ዘመን በቤት የሚያሻው ምግብ ሁሉ ቅቤው፣ የስንዴው ዱቄት በእናት በአባትህ ቤት ይመላ ዘንድ በእጅህ ሀብተ በረከት ያሳደርኩብህ እኔ ነኝ፡፡ ያንን ሰው አንተን በተጣላ ጊዜ በነፋስ አውታር የሰቀለኩት በመዓት ጨንገር የገረፍኩት እኔ ነኝ፡፡ ውኃ ጠምቶህ በለመንከኝ ጊዜ ከደረቅ መሬት የጣፈጠ ውኃ ያመነጨሁልህ እኔ ነኝ፡፡ 🌿 ከልጅነትህ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ብዙ ተአምራት እያደረግሁ በአንተ እጅ የታመሙትን ያዳንኳቸው እኔ ነኝ፡፡ ወደፊትም አደርግልሃለሁ›› አላቸው፡፡ ይህንን ብሎ በእጆቹ ባረካቸውና ‹‹ንሣእ መንፈስ ቅዱስ›› ብሎ የሹመትን ሀብት አሳደረባቸው፡፡ ዳግመኛም‹‹በምድር ያሰርከው በሰማይ የታሰረ ይሁን።
без подписи
без подписи
በዕለታት ባንድ ቀን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱን በእኔ ምክንያት ካገኙሽ ኃዘኖች ማናቸው ኃዘን ይበልጣል አላት፡፡ እመቤታችንም ፈጣሪዬ ጌታዬ ሆይ በእኔ ዘንድ እኒህ አምስቱ ኃዘኖች ይበልጣሉ አለቸው። 1• ከአምስቱ አንዱ አይሁድ እንዲገድሉህ በቤተ መቅደስ ስምዖን ትንቢት በተናገረ ጊዜ ነው፡፡ 2• ሁለተኛውም ሦስት ቀን በቤተመቅደስ ፈልጌህ ባጣሁህ ጊዜ ነው፡፡ 3 • ሦስተኛውም እግርህንና እጅህን አሥረው በጲላጦስ አደባባይ የገረፉህን ግርፋት ባሰብኩ ጊዜ ነው፡፡ 4 • አራተኛውም በዕለተ ዓርብ ራቁትህን ቸንክረው በሁለት ወንበዴዎች መካከል እንደሰቀሉህ ባሰብኩ ጊዜ ነው አለችው፡፡ 5• አምስተኛውም ወደ ሐዲስ መቃብር ውስጥ እንዳወረዱ ባሰብኩ ጊዜ ነው፡፡ ጌታችንም እናቱን ድንግል ማርያምን በእኔ ምክንያት ያገኙሽን እኒህን ኃዘኖችና መከራዎች በሰላመ ገብርኤልና አቡነ ዘበሰማያትን እየደገመ ያሰበውን ኃጢአቱን እኔ አስተሰርይለታለሁ፡፡ መንግሥተ ሰማያትንም አወርሰዋለሁ አላት፡፡ እናቴ ሆይ ከሞቱ አስቀድሞ በሦስተኛው ቀን ካንቺ ጋር መጥቼ እገለጽለታለሁ፡፡ ይህን ሲናገር ቅዱስ ደቅስዮስ ሰምቶ ምእመናን ያነቧት ዘንድ በእመቤታችን ተዓምር መጽሐፍ ውስጥ ጻፈው፡፡ ††† † ልመናዋ ክብሯዋ የልጅዋ ቸርነት በእኛ ለዘለዓም በእውነት ይደርብን †
без подписи
ሚያዚያ 6 ቅድስት ግብፃዊት ማርያም እረፍቷ ነው +++++ቅድስት ማርያም ግብጻዊት~ የተወለደችው በግብጽ ሲሆን ገና የ12 አመት ልጅ እያለች ነበር ወደ እስክንድርያ በመሄድ ድንግልናዋን ያፈረሰችው:ከዚያም የዝሙት ፍቅር አድረባት:ለ17 አመት ያህል ሰዎችን በሚያቃጥል የሃጥያት እሳት ታስፈጃቸው ነበር ዝሙት እያሰራች:ብዙዎችንም ታስት ነበር። ዝሙት ከመውደድ የተነሳ ገንዝብ እንኳን ልስጥሽ ሲሉ አትቀበልም ነበር:በእግዚአብሄርም አታምንም ነበር። በዛው ፋንታ እንደፈለገች ትሆን ነበር። በልቧ ከዚህ ሲራዬ ማንም አይከለክለኝም ትል ነበር:: አንድ ቀን ሊቢያውያን እና ግብጻውያን ወደ ባህር እየተቻኮሉ ሲሄዱ አይታ ወዴት እንደሚሄዱ ብጠይቃቸው የከበረ የጌታችንን መስቀል በዓል ለማክበር ወደ እየሩሳሌም እንደሚሄዱ ሲነግሯት እና የሚሄደው ሰው ብዙ መሆኑን ሲታይ: ብዙ ዘመዶችን አገኛለው ብላ ከነሱ ጋር ለመሄድ ተነሳች:ለጉዞዋ ወይም ለምግብ የሚሆን አንድም ገንዘብ አልያዘችም ነበር። በሁኃላም በሰውነቷ ማማር ብዙዎችን በዝሙት ምክንያት አጠመደች ወደ ተቀደሰ ቦታ የሚሄዱቱን ሰዎች በማሳት ዋና የሰይጣን መረብ ሆና ነበር:በዚህም ስራዋ እየተኩራራች ለሰው ሁሉ ትናገር ነበር። የሃጥያተኛን ሞት የማይወድ እግዚአብሄር መመልሷን እየጠበቀ ይታገሳት ነበር። በመጨረሻም እየሩሳሌም ደርሰው ከበዓሉ በፊት እንደለመደችው እንደውም በከፋ መልኩ ዝሙትን አብዝታ ትሰራ እና ሰውንም ታስት ነበር። የበዓሉ ዕለት ጠዋት ብዙ ተሳላሚዎች ጌታችን መቃብር ላይ ወደ ተሰራችው ቤተ-ክርስቲያን ሊሳለሙ ሲሄዱ አየችና እዛ ሄደው ምን እንደሚያደርጉ ለማወቅ ፊላጎት አደረባት እናም ህዝቡ በሚገቡበት በር እየተጋፋች ለመግባት ትሞክር ጀመር በኃላም በሩ ጋር ስትደርስ የሆነ ሃይል ሲገፋት ይታወቃት ጀመር። ሌሎችን ሰዎች ስታይ በቀላሉ ይገባሉ እና መጀመሪያ ላይ ምንድን ነው እያለች ትስቅ ነበር?! ደጋግማ ስትሞክር አልቻለችም በኃላም ዝም ብላ በሩ ላይ ቆመች እንደገናም ደጋግማ ሞከረች በኃላም ሲደክማት ግዜ እልፍ ብላ ከበሩ አጠገብ ቆመች። በህሊናዋም በብዙ መከራ ምን እንደሆነ ታስብ ጀመር: ቅዱስ መስቀሉን ለማየት እሷ ያልቻለችበትን ምክንያት ታስብ ጀመር:የድህነት ቃል የልቦናዋን አይኖች ነካቸው እና እንዳልገባ የከለከለኝ የራሷ የግል ሃጥያት መሆኑን ተረዳች። በኃላም በማልቀስ እና ደረቷን እየደቃች ከውስጣዊ ልቧማዘን ጀመረች:"ለምን አልገባም? እንዳልገባ የከለከለኝ የኃጢአቴ ብዛት ነው?" እያለች ደጋግማ እራሷን ትጠይቅ ጀመር:ያን ግዜ የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን ስዕል (ስዕል አድኖ)ከበሩ ላይ አየችና ሄዳ ስዕሏ ፊት ቆማ የስዕሏን ግርማና ውበት ባየች ግዜ ያለፈ የራሷ ሃጥያት ወለል ብሎ ታያት እና አፈረች። በኃላም በብዙ ለቅሶ ስዕሏ ስር ወድቃ "ከእንግዲህ በኃላ ጌታየን አገለግል እና ያንቺ ባርያ እሆን ዘንድ እድል አገኝ ይሆን ?" እያለች ታለቅስ እና ትለምን ጀመር። ጌታችንንም ካለችበት ስቃይና መከራ እንዲያድናት እና በመንገዱ እንዲመራት ለመነችው:"ቅዱስ መስቀሉን ካየው በኃላም አለም እና ደስታዋን እንደምክድ ቃል ገባለው" ብላ ቃል ገባች። ከጸለየችም በኃላ የመተማመን ስሜት ተሰማትና ወደ መስቀሉ ቦታ ወደሚያስገባው ቦታ ሄደች ከዚያም ያለችግር ገባች። በኃላም መስቀሉ ጋር ደርሳ በመንቀጥቅጥ እና በብዙ እምባ ሳመች የእግዚአብሄርን ሚስጥር እና ንስሃን እንዴት እንደሚቀበል አየች:ከዚያም ወታ ቃል ወደ ገባችበት ወደ እመቤታችን ስዕል ጋር ሄዳ "የሃጥአንን ንሰሃ ባንቺ አማላጅነት የሚቀበል እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን:የከበርሽ እመቤቴ ሆይ ኃጥእት እኔ ምን እላለው?"አለችና "አለቀስች ወደ ሥዕሏም ተመልሳ አለቀሰች፡፡ ከሥዕሏም ድምፅ ወጣና ‹‹ወደ ዮርዳኖስ በረሃ ሂጂ›› አለቻት፡፡ ዮርዳኖስን ተሻግራ ሄዳ 47 ዓመት በበረሃ ብቻዋን ስትጋደል ኖረች፡፡ ሰይጣንም በዝሙት ጦር ይዋጋት ነበር፡፡ 40 ጾምን ሊፈጽም ቅዱስ ዞሲማስ ወደ በረሃው መጣ፡፡ በዚያ በረሃ ውስጥ የሚጽናናበትን ነገር እንዲሰጠው ወደ ጌታችን ጸለየና ማርያምን ገለጠለት፡፡ ሲጠጋት ሮጣ አመለጠችውና ‹‹ዞሲማስ ሆይ ጨርቅ ጣልልኝ›› ብላ በስሙ ስትጠራው እጅግ ደነገጠ፡፡ ልብሱንም ከሰጣት በኋለ ሰገደላት፡፡ ገድሏንም እንድትነግረው በብዙ ለመናትና ነገረችው፡፡ በዓመቱ ሥጋ ወደሙን አምጥቶ እንዲያቆርባት ጠየቀችው፡፡ በዓመቱ መጥቶ አቆረባት፡፡ አሁንም በዓመቱ ይመጣ ዘንድ ለመነችው፡፡ ድጋሚም ሲመጣ ዐርፋ አንበሳ አስክሬኗን ሲጠብቀው አገኛት፡፡ አንበሳውም መቃብሯን ቆፍሮ አሳየውና ገንዞ ቀበራት፡፡ ገድሏንም ለመነኮሳቱ ሁሉ ነገራቸው፡፡ አባ ዞሲማስም ከደጋግ ክርስቲያን ፍልስጤማውያን ወላጆች የተገኘ ጻድቅ ነበር፡፡ ለመምህርም ሰጥተውት በሚገባ ተምሮ ካደገ በኋላ መነኮሰ፡፡ ሲሠራም ሆነ ሲበላ እንኳን ምስጋናን ከአፉ የማያቋርጥ ደገኛ አባት ከሆነ ከ45 ዓመት በኋላ ቅስና ተቀበለ፡፡ ተጋድሎውንም ጨምሮ 13 ዓመት ከቆየ በኋላ ሰይጣን በልቡ ክፉ ሀብን አሳደረበት፡፡ በልቡም ከበጎ ሥራዎች ሁሉ እኔ ያልሠራሁት ምን ነገር አለ?›› ይል ጀመር፡፡ ጌታችንም ሊተወው አልወደደምና መልአኩን ልኮ ወደ ዮርዳኖስ አቅራቢያ ወዳለው በረሃ እንዲሄድ ነገረው፡፡ በዚያም ሌሎች ደጋግ አባቶችን አገኘና ከእነርሱ ተማረ፡፡ በዚያም ሳለ ወደ በረሃው ገብቶ የሚጽናናበት ነገር ይገልጥለት ዘንድ ወደ ጌታችን በጸለየ ጊዜ ነው ማርያምን ያገኛት፡፡ ዞሲማስ ብሔረ ብፁዓንም ድረስ ሄዶ የቅዱሳንን አኗኗራቸውንና ገድላቸውን አይቶ የጻፈልን ታላቅ አባት ነው፡፡ የቅድስት ማርያም ግብፃዊት ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን። አሜን!
без подписи
በሰሙነ ሕማማት ስለማይጸለዩ ጸሎቶች ከነ ማብራሪያው ☝️ መልካም ንባብ🙏
በዚህ ሰሞነ ሕማማት ብዙዎቻችሁ የሚጸለዩት እና የማይጸለዩት ጸሎቶች ጥያቄ እንደሚሆንባችሁ ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን ጥያቄ በተቻለን አቅም ለመመለስ እና እናንተም ተረጋግታችሁ አውቃችሁ ሕማማትን በስግደት ብቻ ሳይሆን በጸሎት እንድታሳለፉ ጥቂት ይህን እላለሉ፡፡ ወዳጆቼ በሰሞነ ሕማማት አንዳንዶች ይህ አይጸለይም ይህ ይጸለያል እያሉ ምክንያቱን ሳያስረዱና ሳያውቁ ሲጽፉ ይስተዋላል፡፡ ይህ ደግሞ ምዕምናኑን በጸሎት ዙርያ ጥያቄ እና ውዝግብ ውስጥ ይከታቸዋል፡፡ እንደሚታወቀው በሰሞነ ሕማማት የጌታችን ሕማም፣ ስቃይ፣ መከራ የሚታሰብበት እንጂ የሌሎችን የቅዱሳንን በዓላት አብረን የምናስብበት ጊዜ አይደለም፡፡ ምክንያቱም የእነሱ በዓል ከጌታ ሕማም፣ ስቃይ፣ መከራና ለሰው ልጆች ከከፈለው ውለታ አይበልጥምና፡፡ እንኳን እኛ በዚህ በሰሞነ ሕማማት በአጸደ ነፍስ ያሉትም ቅዱሳን የጌታን ሕማም የሚያስቡበት እንጂ የራሳቸውን ክብር የሚሹበት ጊዜ አይደለም፡፡ በሰሞነ ሕማማት ምዕመናኑ መጸለይ ያለበት ጸሎቶች ውስጥ፦ ውዳሴ ማርያም፣ ውዳሴ አምላክ፣ መዝሙረ ዳዊት፣ ሰይፈ ሥላሴ፣ ሰይፈ መለኮት፣ መጽሐፈ አርጋኖን፣ ሰኔ ጎልጎታ፣ ጸሎተ ባርቶስ፣ ግብረ ሕማማት፣ ትምህርተ ህቡአት፣ መልክዓ ሕማማት በዜማ፣ ድርሳነ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ድርሳነ ስምዖን ዘዓምድ፣ ድርሳነ ማሕየዊ፣ ድርሳነ መድኃኔ ዓለም ወዘተ ናቸው፡፡ አንዳንዶች ከየት እንዳገኙት ባላውቅም ውዳሴ ማርያም እና ዳዊት ብቻ ነው የሚጸለየው ይላሉ፡፡ ግን ከላይ የዘረዘርኳቸውን ጸሎቶች በሰሞነ ሕማማት ይጸለያሉ፡፡ በእርግጥ በሰሞነ ሕማማት የማይጸለዩ ጸሎቶች ተብለው ሳይሆን የሰሞነ ሕማማት ሥርዓት በዚህ ሳምንት የማያካትታቸው ጸሎቶች አሉ፡፡ እነሱም መልክዐ ማርያም፣ መልክዐ ኢየሱስ፣ ገድለ ቅዱሳን፣ ድርሳነ መላእክት፣ መልክዓ ቅዱሳን አይጸለዩም፡፡ ግን በግብረ ሕማማት ላይ አባ ጊዮርጊስ የደረሰው መልክዐ ሕማማቱ በዜማ ይጸለያል፡፡ ይህ የሚያሳየው የጌታን ሕማም በተመለከተ ለጌታ ሕማም የሚስማማ መልክዐ መጸለዩን ነው፡፡ በመልክዐ ኢየሱስ ላይ ‹‹ሰላም ለትንሣኤከ፣ ሰላም ለዕርገትክ›› የሚሉ ሰላምታዎች ወይም ምስጋናዎች አሉ፡፡ ስለዚህ እስከ አርብ የጌታን ትንሣኤና ዕርገት ሳይሆን ሕማማት ስለምናስብ ነው የማንጸልየው፡፡ እንዲህም በሰሞነ ሕማማት የመላእክት ድርሳናት እና የቅዱሳን ገድላት አይጸለይም ወይም አይነበብም፡፡ ይህም የሆነው ቢጸለይ ነውር ኖሮበት ሳይሆን በሰሞነ ሕማማት ቅዱሳን መላእክትንና ቅዱሳን አባቶች እና እናቶችን በድርሳናቸው፣ በገድላቸው፣ በመልክዐቸው የምናስብበት ጊዜ ስላልሆነ ነው፡፡ ግን በግብረ ሕማማት ድርሳነ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እና ድርሳነ ስምዖን ዘአምድን ይነበባል፡፡ እንደሚታወቀው በሰሞነ ሕማማት ላይ የግዝት በዓላት ወይም ታላላቅ በዓላት ቢውሉ ሰሞነ ሕማማቱ ስለሚሽራቸው እነሱ እንኳን አይታሰቡም፡፡ ዋና አላማው በሰሞነ ሕማማት በቤተ ክርስትያናችን ብዙ መጻሕፍት ስለሚነበቡ ከጸሎታችን ባሻገር የሚነበቡትን መጻሕፍት በነፍሳችን እያዳመጥን የጌታን ሕማም እንድናስብ ነው፡፡ ከላይ እንዳየነው መልክዐ ማርያም እና መልክዐ ኢየሱስ የማይጸለዩት እነዚህ ጸሎቶች የግል ብቻ ሳይሆኑ የማህሌት ምስጋናዎችም ናቸው፡፡ ስለዚህ በዚህ በሰሞነ ሕማማት ማህሌት፣ ቅዳሴ ከጸሎተ ሐሙስ በስተቀር ስለሌለ እነዚህ ጸሎቶች ለጊዘው አረፍ ይላሉ፡፡ ግን አርጋኖን፣ ሰይፈ ሥላሴ፣ ሰይፈ መለኮት፣ ሰኔ ጎልጎታ፣ ውዳሴ አምላክን በግል መጸለይ የሚከለክል ሥርዓት የለም፡፡ ተወዳጆች ሆይ ያ የተረገመ መናጢ በየሰዉ እያደረ አጉል የቤተ ክርስትያን የሥርዓት ጠበቃ እየመሰለ፣ ሰሞነ ሕማማትን እየታከከ ከጸሎት ሕይወት እንዳያዘናጋን እንጠንቀቅ፡፡ ቢቻል በዓብይ ጾም የተዳከምን በዚህ ሳምንት በጸሎት እና በስግደት በመበርታት ልንጋደል ይገባናል፡፡ እንኳን ጸሎት ትተን እየጸለይንም ፈተናችንንና መከራችንን እኛ ነን የምናውቀው፡፡ በተረፈ ድርሳነ ማሕየዊ የሚባለውን ስለ ጌታችን ሕማም፣ ስቃይ፣ መከራ በአስገራሚ ሁኔታ የሚነግረንን መጽሐፍ ገዝታችሁ ጸልዩት፡፡ ምንክያቱም ድርሳነ ማሕየዊን በሰሞነ ሕማማት ብቻ ሳይሆን የጌታን መከራ እና ውለታ እያሰበ አርብ አርብ ቀን የሚጸልየው ‹‹በነፍሱም በሥጋውም ይከብራል፣ በመንግሥተ ሰማያትም እድል ፈንታው ጽዋዕ ተርታው ጌታችንን ከገነዙት ከኒቆዲሞስ እና ከዮሴፍ ጋር ይሆናል›› እንዲሁም ‹‹በሰባቱ ጊዜያት የሚጸልየው ሰው ቢኖር በነፍሱም በሥጋው ፈጽሞ ይከብራል፡፡ በመንግሥተ ሰማያትም እድል ፈንታው ጽዋዕ ተርታው እስከ ሰባ ዘመን ድረስ በየቀኑ የጌታውን መከራ እያሰባ ካለቀሰ ከጌታ ባለሟል ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ይሆናል›› የሚል ታላቅ ቃል ኪዳን አለው፡፡ ተወዳጆች ሆይ አራቱ ወንጌላውያንና ጌታችን የመከራውን ነገር ያስተማራቸው ኤልሳቤጥ፣ መልቴዳ እና በርዜዳ የጻፉትን ድርሳነ ማሕየዊን በመጸለይ የጌታን ሕማም ልናስብ እና ከቃል ኪዳኑ በረከት ልንሳተፍ ይገባናል፡፡ ወዳጆቼ ድርሳነ ማሕየዊ ልክ እንደ ውዳሴ ማርያም የየእለት ወይም ከሰኞ እስከ እሑድ የተከፋፈለ በመሆኑ ለመጸለይ አይከብድም፡፡ ወዳጆቼ በዚህ በሰሞነ ሕማማት እመቤታችን በልጇ የተነሳ ብዙ መከራ ደርሶባታልና፣ ጌታም በእሷ ሥጋ ተሰቅሏልና እሷን በውዳሴ ማርያም፣ በአርጋኖን፣ በሰኔ ጎልጎታ፣ በጸሎተ ባርቶስ ልናስባት ልናመሰግናት ይገባል፡፡ ሥላሴንም በሰይፈ ሥላሴ ልናመሰግናቸው ይገባል፡፡ ጌታችንንም በሰይፈ መለኮት፣ በውዳሴ አምላክ፣ በዳዊት፣ በድርሳኑ ልናስበውና ልናመሰግነው ይገባል እንጂ በሕማማት ምክንያት ከጸሎት ልንርቅ አይገባም፡፡ መልካም ሰሞነ ሕማማት በያላችሁበት! @ቀሲስ መምህር ሔኖክ ወልደማርያም @bahreTibebat
https://youtu.be/Tl7c6eD3H0A
https://youtu.be/tvuhOCz_ENU
https://youtu.be/Uo3BbC8pSEk
https://youtu.be/3PZ3W6Lllvo
без подписи