tgindex
ኡስታዝ በድሩ ሁሴን bedru husen

ኡስታዝ በድሩ ሁሴን bedru husen

Статистика
Последний пост
5 июл. 2025 г.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 760
−2 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
3 796
20 постов
Вовлечённость
215,7%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • "እባቡ የማይተነፍስበት ክልል ውስጥ ገብተናል" 🐸❌ በበረራ ላይ እያሉ ሆስተሷ አውሮፕላን ውስጥ እባብ አይታ በጣም ደነገጠችና እየጮኸች አብራሪው ጋር ገብታ እባብ አውሮፕላን ውስጥ ገብቷል አለችው። እሱም ችግር የለውም ተረጋጊ አለና የሚበርበትን ጫማ ከፍታ ጨመረና አሁን ሄደሽ እይ አላት። እሷም ሄዳ ስታይ እባቡ ሞቷል። ወደ አብራሪው ተመለሰችና እንዴት ሊሆን ቻለ ስትለው እባቡ የማይተነፍስበት ክልል ውስጥ ገብተናል አላት። 😇 የነገሩ ማጠንጠኛ፦ በገጠመህ ሁሉ አትደንግጥ ለሁሉም ነገር መልስ አትስጥ ዝምብለህ ጉዞህን ቀጥልና ጠላትህን የሚያስጨንቅ ከፍታ ላይ ውጣ። 💪 https://t.me/bedru511111

  • видео или голосовое, без подписи

  • አሜሪካ ጣልቃ የምትገባ ከሆነ ከፍተኛ አደጋ ሊከሰት ይችላል- አያቶላህ አሊ ሀሚኒ አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢራን እና እስራኤል ግጭት አሜሪካ ወታደራዊ ተሳትፎ ካደረገች ከፍተኛ አደጋ ሊከሰት ይችላል ሲሉ የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ሀሚኒ አስጠነቀቁ፡፡ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን በፍጥነት እጅ እንድትስጥ ማሳሰባቸውን ተከትሎ የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ሀሚኒ ሀገራቸው በቀላሉ የምትንበረከክ እንዳልሆነች ማስታወቃቸውን የሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡ ድል ለኢራን

  • видео или голосовое, без подписи

  • አ.ወ.ወ እንዴት ናቹህ addmine ሰጥቼው ይህንን ቻናል በሀላፊነት ለማስተፋደር ፍቃደኛ የሚሆን ካለ ግሩፑ ላይ እኔ ፍቃደኛ ነኝ ብሎ መልስ ይመልስልኝ

  • አንድ ትልቅ የንግድ መርከብ ተበላሽቶ ቆመ ብዙ መካኒኮች ቢሞክሩትም መጠገን አቃታቸው ፣ በኋላም አንድ የ40 ዓመት ጎልማሳ የመርከብ ኢንጅነር አግኝተው መርከቡን እንዲሰራላቸው ጠየቁት ። ኢንጅነሩም እሺ ይልና የመርከቡን የተበላሸውን ክፍል ለመለየት ሞተሩን ከታች እስከላይ ከገመገመ በኋላ፣ አነስ ያለች የእቃ ቦርሳውን ከፍቶ ትንሽዬ መዶሻ አወጣና፣ በመዶሻው አንዷን ቦታ መታ፣መታ አረገ ከዚያም ሞተሩ መስራት ጀመረ። ስራውን እንደጨረሰም የሰራበትን ዋጋ አንድ ሚሊዮን ብር ጠየቀ ። ባለቤቱ በድንጋጤ ጭንቅላቱን ይዞ "ምን"? አለ ከዚያም ለመሆኑ በዚች ሰኮንድ ውስጥ ምን ሰርተህ ነው ይሄን ያህል ብር የምትጠይቀኝ ? በል ምን እንደሰራህ ዝርዝሩን ጽፈህ ስጠኝ አለው በንዴት። ኢንጂነሩም በጠየቀው መሰረት በብጣሽ ወረቀት የሚከተለውን ፅፎ ሰጠው ፅሁፉም እንዲህ ይላል በመዶሻ የመታሁበት 200 ብር የተበላሸበትን ቦታ ላወኩበት 999800 አለው። ይሄን ስራ በሰኮንድ ውስጥ ነው የሰራውት ላለፉት 20 አመታት እንዴት በ ሰኮንድ ውስጥ እና በ ደቂቃዎች ውስጥ መስራት እንዳለብኝ ተምሬ ነው፣ ይሄን የማስከፍልህ ለተማርኩበት አመታት እንጂ ለሰራውበት ሰኮን ወይም ደቂቃ አይደለም አለው ይባላል። https://t.me/bedru511111

  • видео или голосовое, без подписи

  • ታኩር በሚል የቲክቶክ ስም የሚታወቀው ልጅ ምን እንዳለ ሰማችሁ? ካልሰማችሁ እኔ ልንገራችሁ …ከዚያ ግን ከንግግሩ ምን ቁም ነገር መውሰድ እንዳለብን ቀጥሎ እፅፍላችኋለሁ:: እናንተ ብቻ በትዕግስት ተከተሉኝ… "እዚህ ያደረሰኝ ጌታዬ ነው:: ታቃለህ:: ካድኩት በቃ በይፋ:: (ጌታየን አመፅኩት) እስካሁን ርዝቄን ያልዘጋብኝን ከለቀኩት በ )በኋላ በቃ! እስካሁን እየተፀፀትኩኝ ነው:: ብታምንም ባታምንም የተቀበልኩትን ብር እስካሁን አላጠፋሁትም…የክሊፑን ብር:: ምናልባት ሰርቼ ሃብታም ከሆንኩኝ ሰደቃ ምናምን ነው ምሰጠው:: ካልቸገረኝ አላጠፋውም አሁን::" ከታኩር ንግግሮች መውሰድ አለብን ብዬ የማስባቸው ቁም ነገሮች … ያው ባለፈውም እንዳልኳችሁ የ አላህ ውዴታ እያላቸው ፣ በልባቸው እስልምናቸውን እየወደዱ ነገር ግን ሁል ግዜም ከነፍሲያቸው ጋር የሚታገሉ ሰዎች እንዳሉ ማወቅ አለብን:: አንድ ሙስሊም ወንጀል ላይ ሲውል ወንጀሉን ወዶት ብቻ ሳይሆን ከራሱ ጋር ጂሃድ (ትግል) እያደረገ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ:: ከዚያ ራስን እንደ ፃዲቅ ቆጥሮ በየኮሜንት ቦክሱ አፀያፊ ስድቦችን ከመሳደብ እና ወንድሞቻችን ላይ ከመፍረድ መቆጠብ ያስፈልጋል:: ይልቁንስ በክብርና በፍቅር መገሰፅን እንልመድ:: በብልጠትና በዘዴ ወደ ቀጥተኛው መንገድ እንዲመለሱ መምከርን እናዳብር:: ሌላኛው ምንም ስኬታማ ብትሆኑ ምንም ፌመስ ብትሆኑ ከ እስልምና የሚበልጥ ሀብት እንደማታገኙ ከታኩር ንግግር መገንዘብ ይቻላል:: አላህ በሀላሉ ያብቃቃህ ብላችሁ ዱዓ አድርጉለት እስኪ! እዚህ ደርሳችሁ ደሞ Follow ሳታረጉኝ እንዳትሄዱ 👉https://t.me/bedru511111

  • видео или голосовое, без подписи

  • ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዓ.ወ) ተከታዮች ብቻ የተሰጠችው ከሺህ ወራት በላጯ ሌሊት ****** የኢስላም ሃይማኖት ምሁራን እንደሚሉት፥ ከነቢዩ ሙሐመድ(ሰ.ዓ.ወ) መላክ አስቀድሞ በምድር ላይ ኖረው ያለፉ ሕዝቦች ዕድሜያቸው ረጅም ነበር፤ በመቶዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ዓመታትን በሕይወት የመቆየት ዕድል ነበራቸው። በአንፃሩ የነቢዩ (ሰ.ዓ.ወ) ተከታዮች ዕድሜ በአማካይ ከ60 እና ከ70 ዓመት የማይዘልና በጣም አጭር ነው። በመሆኑም የነቢዩ ተከታዮች በአምልኮም ሆነ በበጎ አድራጎት ተግባራት በሚያስመዘግቡት ምንዳ ከቀድሞዎቹ ሕዝቦች ጋር ተወዳዳሪ ሊሆኑ የሚችሉበት ዕድል አልነበራቸውም። አላህም ይህን ሊያካክስላቸው ከረመዳን ሌሊቶች አንዷን በምርታማነቷ ከሺህ ወራት ጋር ተመጣጣኝ እንድትሆን አደረገላቸው። ይህች ሌሊት ለይለቱል ቀድር ወይም የመወሰኛዋ ሌሊት በመባል ትታወቃለች። የረመዳን ወርን ክብር ካላቁት ነገሮች አንዷም ይህችው ለይለቱል ቀድር ናት። ነቢዩ (ሰ.ዓ.ወ) ለይለቱል ቀድርን ከመጨረሻዎቹ 10 የረመዳን ቀናት በተለይ ኢ-ተጋማሽ በሆኑት ውስጥ ተጠባብቃችሁ ፈልጓት ብለዋል። ይህም በረመዳን 21፣ 23፣ 25፣ 27፣ እና 29 መሆኑ ነው። አብዛኛዎቹ የሃይማኖቱ ምሁራን ወደ 27ኛዋ ሌሊት ቢያደሉም፣ለዚህ ቁርጥ ያለ ማስረጃ ወይም ማረጋገጫ የለም። አላህ ሌሊቷ ተለይታ እንዳትታወቅ ያደረገበት የራሱ ምስጢር አለው ይላሉ የኢስላም ምሁራን። ምዕመናን ሌሊቷ የቷ እንደሆነች ለይተው ቢያውቁ ኖሮ፤ በዚያች ሌሊት ብቻ ሥርዓተ አምልኮን በመፈጸም ረመዳንን ላይጾሙ፣ ዓመቱን ሙሉ ፈጣሪያቸውን ላያመልኩ ይችሉ ነበር። ያ እንዳይሆን ለመከላከል አላህ ለይለቱል ቀድርን ድብቅ ሌሊት አደረጋት። ለይለቱል ቀድር ከሌሎቹ ሌሊቶች የምትልቀው ቁርዓን የወረደባት እና የመወሰኛ ሌሊት በመሆኗ ነው። የምዕመናን ዓመታዊ ጉዳዮች አላህ ዘንድ ቀርበው ውሳኔ የሚያገኙት በዚህች ሌሊት ነው።በመሆኑም በዚህች ሌሊት ምዕመናን የአላህን ምህረት፣ ጸጋ እና ውዴታ ለማግኘት የአምልኮ ተግባራትን ከወትሮው በበለጠ ትጋት እና ትኩረት ያከናውናሉ። በሌላ አባባል፥ በዚህች ሌሊት የሚከናወን አምልኮተ ሥርዓት ከረመዳን ዉጪ ለ1 ሺህ ወራት ወይም ለ83 ዓመት ከ3 ወር ከሚከናወነው ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ምንዳን ያስገኛል። በመሆኑም በዚህች ሌሊት ምዕመናን ሥርዓተ አምልኮን እና በጎ−ምግባራትን ከወትሮው በበለጠ መጠን እና ጥራት ያከናውናሉ፤ለአብነትም፥ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን ይከውናሉ፣ ቁርዓን ይቀራሉ፣ የሌሊት ሶላት ይሰግዳሉ፣ ዱዓ ያደርጋሉ (ፈጣሪያቸውን ይለምናሉ)። በዚህች ሌሊት ከሚደረጉ ተወዳጅ ዱዓዎች መካከልም፥ "አላህ ሆይ፥ አንተ ይቅር ባይ ነህ፤ ይቅር ማለትን ትወዳለህ፤ ይቅር በለን!" የሚለው ተጠቃሽ ነው። በሴራን ታደሰ https://t.me/bedru511111

  • ሰውየው ለዒድ በግ ገዝተው መኪና ላይ ሊጭኑት ሲል ያመልጣል ሰውየው እየሮጡ ሲከተሉት በጉ ሚስኪን ቤት ይገባል፣ሚስኪኗ እናት ሁሌም በር ቆመው በሰፈራቸው አንድ ሰው እርዳታ ካመጣ ብለው ይጠብቃሉ በጉ ሲገባ የበጉ ባለቤት አቡ ሙሀመድና እናት ይገጣጠማሉ እናት ሰውየው በጉን ለዒድ ያመጡላቸው መስሏቸው ለአቡ ሙሀመድ ዱዓ ያደርጋሉ አሏህ ኸይር ስራህን ይቀበልህ አሚን አቡ ሙሀመድ በነገታው ሌላ በግ ሊገዙ ይወጣሉ በከባድ መኪና የተጫኑ ብዙ በጎች አዩ አሪፍ ያሉትን በግ መረጡ ወደ መኪናቸው አስገብተው ሊከፍሉ ሲሉ ባለበጉ "አሏህ በዚህ አመት ብዙ በጎችን ስለሰጠኝ የመጀመሪያ ለገዛኝ ሰው በነፃ ልሰጥ ነይቼ ነበር አንተ የመጀመሪያ ነህ በጉን በነፃ ውሰድ" https://t.me/bedru511111

  • видео или голосовое, без подписи

  • ይህን ድንቅ ታሪክ በፍፁም ሳያነቡ እንዳያልፉ አላህ (ሱ.ወ) ባደረከው ነገር ይደነቃል አቡ ሁረይራህ (ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል፡- ከእለታት “አንድ ቀን አንድ ሰው ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ መጣና “ችግር ውስጥ ነኝ ርቦኛል፣ ገንዘብም ሆነ የምበላው ነገር የለኝም )” አላቸው። ከዚያም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሰውየውን ወደ እያንዳንዱ ሚስቶቻቸው ቤት አመጡትና፣ ምግብ አለን ወይ ብለው ጠየቁ። ሁሉም ሚስቶቻቸው "በእውነተ በላከህ አላህ እምላለሁ ከውሃ ውጪ ምንም የምንበላው ነገር የለንም" እያሉ ሀሉም ይህን መልስ ሰጡ ። ከዚያም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለባልደረቦቻቸው እንዲህ አሉ፡- “ይህን ሰው በቤቱ በእንግድነት ሊጋብዘው የሚችል ሰው አለ ይህን የሚያረግ ሰው ካለ እርሱ በእርግጥ አላህ ዘንድ ይባርካል አሉ ። ከዚያም ከባልደረቦቻቸው መካከ አንድ ሰው ቆሞ አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ ይህን ሰው እኔ ቤት ወስጄ በእንግድነት እጋብዘዋለው አለ። ከዚያም ሰውየውን ወደ ቤቱ አመጣውና ሚስቱን የሚበላ ነገር አለ ወይ ብሎ ጠየቀ ? እሷም “ከልጆቻችን ምግብ በስተቀር ምንም የለም” ብላ መለሰች። እርሱም፡ “ ልጆቻችንን በሥራ አስጠምጂያቸውና (ምግቡን እንዲረሱ አድርጊ)። እንግዳችን ወደ ቤታችን ሲገባ ከእርሱ ጋር እንደምንበላ እናስመስል። ከዚያም ምግቡን ልንበላ ስንል ተነስተሽ ኩራዙን። አጥፊው አለ ለሁላችንም የሚበቃ ምግብ ስለሌለ ከእርሱ ጋር እንደማንበላ አያውቅም)። እንግዳው ወደ ቤት ሲገባ፣ ሚስት ባሏ እንድታደርግ የነገራትን በትክክል አደረገች። ከሰሀባዎች እንዱ በጠዋት ወደ እነርሱ ዘንድ መጣና ፈገግ ብሎ “ትላንትና ማታ እንግዳህን የተቀበልክበትን መንገድ አላህ ተደንቋል አለው ።  የታሪኩ መልእክት የእራሱን ሃብት መስዋእት ማድረግ ቢሆንም ለተቸገሩት እንግዳ ተቀባይ እና ለጋስ መሆን ነው። ሰውየው እና ሚስቱ ውስን ምግብ ቢኖራቸውም እንግዶቻቸውን ሳይሳቀቁ ምቾት የሚያገኙበት መንገድ ስላገኙ ሌሎችን በማገልገል ላይ የፈጠራ እና የጥበብን አስፈላጊነት አጉልቶ ያሳያል ። ታሪኩ ሩህሩህ እና እንግዳ ተቀባይ እንድንሆን ያበረታታናል፣ https://t.me/bedru511111

  • ድንቅ ታሪክ ነብዩላሂ ሙሳ አላህን ያናገሩ ነብይ ናቸው፡፡ አንድ ጊዜ አላህን የጀነት ጎደኛዬን አሳየኝ ብለው ጠየቁ ፡፡ አላህም ወደ አንድ ደካማ ቤት እንዲሄድ የመንገዱን አቅጣጫ ነግራቸው ሄዱ፡፡ የተባሉት ቤት ደርሰው አንኳክተው ገቡና ቁጭ አሉ፡፡ በእድሜ የገፉ እናትና አባቱን የሚካድም አንድ ወጣት ልጅ ተመለከቱ፡፡ ልጁ ሽማግሌዎቹን በመካደም ተጠምዶዋል ያጎርሳቸዋል ያጠጣቸዋል፡፡ በዚህ የተነሳ ቤቱ ማን እንደገባ እንኳን አላወቀም፡፡ ከጨረሰ በኃላም ዞር ብሎ ሲመለከት አንተ እንግዳ ቤት በኩል ገባህ አላቸው? ነብዩላሂ ሙሳ (ዐ.ሰ) አፉ በለኝ ይሉትና ልጁም እንዲህ አላቸው እነሱን እየካደምኩ ስለነበረ በዛ ምክንያት ነው ። ስትገባም ያለየሁክ አላቸው። ነብይ መሆናቸውን አላወቃቸውም፡፡ ልጁም እንግዳዬ ነህ እሺ ምን ላድርግልህ ከነሱ የተረፈ አለ ትበላለህ አላቸው፡፡ ( ነብዩላሂ ሙሳም( ዐ.ሰ) ምንም አልፈልግም ሸኘኝ በቃ አሉት፡፡ ወጪ ከወጡ በኃላም ነብዩላሂ ሙሳም(ዐ.ሰ) ልጁን ጠየቁት እነዛ ሽማግሌዎች ምንህ ናቸው አሉት? ልጁም ወላጆቼ ናቸው አላቸው፡፡ ነብዩላሂ ሙሳም( ዐ.ሰ) ምንም ሌላ ልጆች የላቸውም ቤተሰብም የላቸውም አሉት፡፡ ልጁም አዎ እኔ ብቻ ነኝ ያለሁት አላቸው፡፡ ነብዩላሂ ሙሳም( ዐ.ሰ) ምንድን ነው የምትሰራው አሉት? ልጁም ተሸካሚ ነኝ ተሸክሜ ባገኝሁት ብር እነሱን ቁርስ፣ምሳ፣እራት ሳላሳልፍባቸው እየገዛሁ እካድማቸዋለሁ አላቸው፡፡ ነብዩላሂ ሙሳም( ዐ.ሰ) ወላጆችህ ስታስደስታቸው ምን እያሉ ነው ሚመርቁህ አሉት፡፡ ልጁም አይ እሱስ ከባድ ነው የማለገኝውን ነው የሚመርቁኝ በተለይ እናቴ አንድ ነብይ አለ ደረጃህን በጀነት ከነብዩ ሙሳ ጋር ያድርግልህ ትለኛለች፡፡ ስለምትወደው ነው እንጂ እኔ እንኳን ከነሱ እኩል መሆን አልችልም አላቸው፡፡ ነብዩላሂ ሙሳም( ዐ.ሰ) ታውቀዋለህ ግን ነብዩላሂ ሙሳን አሉት? አላውቀውም! እንዳለ እሰማለሁ እንጂ አላቸው፡፡ ነብዩላሂ ሙሳም (ዐ.ሰ) በል እንግዲህ እኔ ነብዩላሂ ሙሳ ነኝ እኔም የጀነት ጎደኛህ ነኝ አላህን የጀነት ጎደኛዬን ማን እንደሆነ አሳየኝ ብዬው ነው! ዛሬ አንተ መሆንህን ያሳየኝ አሉት። https://t.me/bedru511111

  • видео или голосовое, без подписи

  • 🚨🌙 በሳውዲ አረቢያ ጨረቃ መታየቷን ተከተሎ የታላቁ የረመዳን ፆም ነገ ይጀመራል። ረመዳን ሙባረክ 🌙 #RAMADAN1446

  • ጾም እና ምጽዋት የሰይጣንን አከርካሪ ይሰብራሉ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- እ“የሙእሚን ፆሞች የሰይጣንን ፊት ያጠቁራሉ። ኢስቲግፋር የሰይጣንን የሕይወት ሥር ይቆርጣል፣ መልካም ስራ የአላህን ውዴታ ያጎናፅፋል ።ሰደቃ ወይም በጎ አድራጎት ፣አከርካሪ ይሰብራል። መጋረጃዎቹ ከዓይኖችህ ላይ ከተነሱ፣ ስለ ፆምህ ምክንያት የሰይጣን ፊት እንደጠቆረ ታስተውላለህ። ሰይጣን ግን ደካማና የተዳከመ አይደለም በጾምህ ብቻ ፊቱን ታጠቁርና በምጽዋትም አከርካሪውን ትሰብራለህ። በሰባቱ መጋረጃዎች ውስጥ በማለፍ የሰይጣንን አከርካሪ ሰብረው እንዲያጠፉት ሁሉንም ድርጊቶች በፍጹም ቅንነት ማከናወን አለቦት። የሰይጣንን እናት አይቻለሁ።። በአንድ በአስከፊ ረሃብ ወቅት አንድ ሰባኪ በመስጊድ ውስጥ ሚንበር ላይ ቆሞ አንድ ሰው ሰዳቃን መስጠት ከፈለገ (70) ሰይጣኖች እጁ ላይ ተጣብቀው ሰደቃውን እንዳይሰጥ ሊከለክሉት ይሞክራሉ። በማለት ተናገረ ። ይህን ጊዜ ከሚንበሩ እግርጌ ተቀምጦ የነበረው አንድ ሙእሚን በመገረም ለጓደኞቹ እንዲህ አላቸው... ሰይጣንን ከሰዳቃ ከመስጠት ጋር ምን አገናኘው? ቤት ውስጥ ስንዴ አለኝ። አሁን ወደ ቤት እሄዳለሁ ከዚያም ስንዴውን መስጂድ አምጥቼ ምጽዋት እሰጣላው እስኪ። ሰይጣን ይሄን እንዳላደርገው እንዴት እንደሚከለክለኝ አያለሁ!” አለ። ከዚያም ሰውዬው ተነስቶ ወደ ቤቱ ሄደ። ቤት እንደደረሰ ሚስቱ ሃሳቡን ስታውቅ፣ “በዚህ አስከፊ ረሃብ ጊዜ ለሚስትህና ለልጆችህ ምንም ግድ የለህምን? ምናልባት የረሃቡ ሁኔታ ሊራዘም ይችላል እና ሁላችንም በስንዴ እጥረት በረሃብ ማለቃችን ነው አለች ። ይህን ጊዜ ባልየው በከባድ ጥርጣሬ በመዋጥ እና የረሀቡን አስከፊነት በመፍራት ባዶ እጁን ወደ መስጊድ ተመለሰ። ጓደኞቹም “ምን ሆነሃል? ስንዴውን ሳትይዝ ባዶ እጅህን ከቤት ተመልሰህ ነው ? ወይስ! ሰባዎቹ ሰይጣኖች በእጆችህ ላይ ተጣብቀው ሶደቃውን ከለከሉህ አሉት? ሰውየውም፣ እንዲህ ሲል መለሰ “ሰይጣንን አላየሁም፣ ነገር ግን በመልካም ስራዬ ላይ የመጣችውን እናታቸውን አይቻቸዋለሁ!” አለ። ይህ የሚያሳየው ሰው ከሰይጣን ጋር ለመታገል እንደሚሞክር ነገር ግን ብዙ ጊዜ ሚስቱ ወይም ሌሎች ከመልካም ስራ ያዘናጉታል። ።።። https://t.me/bedru511111

  • видео или голосовое, без подписи

  • ◉አንድ ሰው በሞተ ጊዜ (ነፍሱ ከስጋው በተለየች ጊዜ) ጎረቤት ፣ወዳጅ ዘመድ አዝማድ ተሰባስቦ ለሟች ይለቀሳል ፣ ለቅሶው፣ ኡኡታ፣ ሙሾው፣ ትርምሱን ይህን ሁሉ የሟች (አስክሬን) ያዳምጠዋል። ገናዦች አይኑን ባይከድኑት ኖሮ በዙርያው የሚሆነውን ሁሉ በግልፅ ይከታተል ነበር። ◉ይሁን እንጂ አንድ የሞተ ሰው መጀመሪያ ላይ መሞቱን አያውቅም።ልክ በእንቅልፍ ውስጥ ሆኖ ሞትን በህልም ውስጥ እያለመ እንደሆነ ይሰማዋል፣ መሞቱን ተከትሎ እየተለቀሰለት፣ ◉ጀናዛው ታጥቦ ፣ በጨርቅ ተገንዞ ካበቃ በኋላ በሰዎች ትከሻ ላይ ሆኖ ወደ ሙታን መንደር ወደ መቃብር ስፍራ እየተሸኘ እንደሆነ እና ወደ መቃብር ሲወርድ ያያል። ◉ወደ መቃብር ውስጥ ከገባ በኋላ እንኳ ይህ ሁሉ በህልም ያውስጥ እንዳለ አይነት ስሜት ይኖረዋል።ለቀብር የመጡ ሰዎች ቀብረውት አፈር ተመልሶ ሲያበቃ እና ሁሉም ሰው ከስፍራው ሲሄድ ◉መጮኽ ነገር ግን ጩኸቱን የሚሰማው ማንም የለም ሁሉም ሰው ተበታትኖ ብቻውን ምድር ውስጥ ሲቀር ። አላህ ነፍሱን ይመልሳል። ◉አይኑንም ገልጦ ከ"መጥፎ ህልሙ" ይነቃል።ይህ ሰው ከመጥፎ ህልሙ ሲነቃ መጀመሪያ ላይ ደስተኛ ይሆናል ፈጣሪውን ያመሰግናል ። ◉ያጋጠመው ነገር ሁሉ በህልም ዓለም የተከሰተ ቅዠት እንደሆነ አድርጎ ያስባል ። ◉እና አሁን ከሞት እንቅልፉ ነቅቷል፣ በመቃብሩ ውስጥ ያለውን ጨለማ አይቶ ሶስት ጊዜ ለመነሳት ይሞክራል ለመነሳት ሲሞክርም የመቃብሩ የላይኛው ክፍል ግንባሩን ይገጨዋል ◉ከዚያም በጨርቅ የተጠቀለለውን ገላውን መንካት ይጀምራል ⇛ይቀጥልና ለብሼ የነበረው ሸሚዜ የታለ? ⇛ቲሸርቴ የታአለ? ⇛ማነው እሱ እርቃኔን አስቀርቶኝ በጨርቅ የጠቀለለኝ ? ⇛የት ነኝ ያለሁት፣ ይህ ቦታ የት ነው? ⇛ይህ ቦታ ለምን ጨለመ ? ⇛ማን ነው ወደዚህ ድቅድቅ ጨለማ ቦታ ያመጣኝ ? ⇛እዚህ ምን እያደረግኩ ነው ይላል ? መልስ የሚሰጠው አካል የለም ◉እንደ እሱ አስተሳሰብ ከዚህ አስፈሪ ቦታ ሊያወጡኝ ይረዱኛል የሚላቸውን ቤተሰቦቹን፣ ዘመዶቹን አልያም የጓደኞቹን ስም እየተጣራ የቻለውን ያህል ይጮኻል!! ነገር ግን ማንም ሰው ምንም አይመልስለትም። ◉ከዚያም የሆነውን ነገር ሁሉ ይገነዘባል እርሱ ያለው በሙታን መንደር፣ ከመሬት በታች በመቃብር ውስጥ ነው ◉ይህን ጊዜ ያጋጠመው ነገር ሁሉ ህልም እንዳልሆነ ይረዳል በእርግጥ መሞቱን ይገነዘባል ◉ከዚያም በዚህ ክፉ ጊዜ የሚደርስለት ብቸኛው ተስፋ አላህ መሆኑን ያስታውሳል። ለአላህም እያለቀሰ ምህረትን ይጠይቃል፣እንዲህም ይላል ያ አላህ (አላህ ሆይ) ይቅር በለኝ ይላል ...!!! በህይወት ሳለ ከዚህ በፊት ተሰምቶት በማያውቀው እና በማይታመን ፍርሃት ተውጦ እጅጉን ይጮኻል። የሚደርስለት ግን አያገኝም ◉ይህ ሰው በህይወት እያለ አላህን የሚፈራ (አላህን የሚገዛ) እና ጥሩ ሰው ከነበረ፣ ለእርሱ ሁለት መላእክቶች ይመጡና ከጎኑ ተቀምጠው መልካምነቱን እያወሱ ያፅናኑታል በመልካምም ያገለግሉታል ◉በአንፃሩ ይህ ሰው በህይወት እያለ መልካም ስራ ካልነበረው ፣አላህን የሚያምፅ እና በሽርክ ውስጥ ሆኖ (አላህን ያጋራ) ከነበረ ሁለት አስቀያሚ እና አስፈሪ የፊት ገፅታ ያላቸው መልአክቶች እርሱን በማሰቃየት ህመሙንና ፍርሃቱን ለመጨመር ይመጣሉ። ◉በዚያ ጭንቅ ጊዜ ሟች እያለቀሰ የአላህን ምህረት እና እዝነት ይለምናል !! ነገር ግን ምንም አይጠቅመውም ምናልባት ከአላህ ምህረት የሚጠይቅበት ትክክለኛው ጊዜ በምድር ላይ በህይወት እያለ ፣ወጣት እና ጤናማ በሆነ ጊዜ ነበር ።ነገር ግን ሁሉም ነገር አክትሟል ◉አላህ በቁርዓን ውስጥ እንዲህ በሏል... ሰዓቲቱም በድንገት ልትመጣባቸው እንጂ ይጠባበቃሉን? ከአንቀጾቿም በእርግጥ መጣች። ከዚያም ለነሱ በመጣች ጊዜ መገሰጻቸው ምን ይጠቅማቸው?" (ቁርኣን 47፡18) ◉አሏህ ሆይ እኔም፣ እናቶቻችን፣ አባቶቻችን፣ ቤተሰቦቻችን፣ ጓደኞቻችን እና ውድ ዘመዶቻችን፣በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በትንሹ እና በትልቁ የሰራነውን ወንጀላችንን በእዝነትህ ማርልን !! አላህ ሆይ ይቅር በለን 🙏🏻 አላህ ሆይ እምነታችን በአንድ አላህ አሟሟታችንን በላኢላሀ ኢለላህ አርግልን 🤲🤲🤲 #አሚን #አሚን https://t.me/bedru511111

  • видео или голосовое, без подписи