የኔ ዜማ የአድማጮች የሙዚቃ ምርጫ
Статистика- በፌስቡክ👇 https://www.facebook.com/100022318509408/posts/1859085851512014/?app=fbl https://www.facebook.com/share/1AMgudXhJr/ - በቴሌግራም ገፅ👇 https://t.me/biggrs - ቲክቶክ ገፅ 👇 tiktok.com/@temesgen_ukare - በዩትዮብ ተከታተሉን👇 https://youtube.com/@temuyehag
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 32
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 18
- 1/48двое суток
- 20
- 1/72трое суток
- 22
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የመሐሪ ብራዘርስ ባንድ አባላት የባለብዙ ሙያ ባለቤቱን ወላጅ አባታቸውን ተወዳጅ የሙዚቃ ሥራዎች በአዲስ መልክ አዘጋጅተው በአዲሱ ዓመት መግቢያ ላይ ለአድማጮች ሊያደርሱ ነው፤ ባንዱ ከተመሰረተ 20ኛ ዓመቱን በሚይዝበት በዚህ ወቅት በሔኖክ መሐሪ ዋና አዘጋጅነት ለአምስት ዓመታት ሲዘጋጅ የቆየውንና 12 የተመረጡ ዜማዎችን ያካተተውን "መሐሪኖ" የተሰኘ አልበም በራሳቸው የዩቲዩብ ገፅ ይለቃሉ። የዝጅቱን ሁኔታ አስመልክቶ ድምፃዊ ሄኖክ መሐሪ ከአራዳ ኤፍ ጋር ቆይታ አድርጓል። ተመስገን ኡካሬ የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1 Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical Telegram:-https://t.me/Arada_Fm Telegram:-https://t.me/aradaFmdigital Facebook:-https://web.facebook.com/aradafm @Arada_Fm
የህብረት ዜማዎች ተመስገን ኡካሬ የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1 Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical Telegram:-https://t.me/Arada_Fm Telegram:-https://t.me/aradaFmdigital Facebook:-https://web.facebook.com/aradafm @Arada_Fm
ድምፃዊ ኬኔዲ መንገሻ ሲታወስ ተመስገን ኡካሬ የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1 Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical Telegram:-https://t.me/Arada_Fm Telegram:-https://t.me/aradaFmdigital Facebook:-https://web.facebook.com/aradafm @Arada_Fm
без подписи
የሰንበት ሙዚቃ ለማን ልማሽ በክረምቱ ከዝናቡ ጋር የሁለት ንጉሳዊያን ስራ ስትሰሙ ቴዲ እና ኤሉ ስለ ሀገሬ በዚህ ልክ ገልፀዋል፡፡🙏 "ዞሮ መግጠም ላይቀር አንድ ቀን ምንድነው ሀሜት ብዙ ያሳያል ማን እንደ ጊዜ እንደ መሰንበት በሚወዱት አያምርም ሐሜት ለሰሚም አይበጅ ትርፍ የለውም የራስ ሰው ቢያሙት ያስገምታል እንጂ" አይሆንለት ሆዴ አንቺን ርቆ መቻል ያውቃል ማሳለፍ ስቆ… ግጥም እና ዜማ:ቴዎድሮስ ካሳሁን ቅንብር፡ኤልያስ መልካ
አርቲስት አልማዝ ተፈራ፤ “ጅማ ላይ ነው ቤቱ" እና "የፍቅር ጽገሬዳ”ን ጨምሮ ሦስት ተወዳጅ አልበሞችን ለአድማጭ ያበረከተች ሲሆን፣ ለድምጻዊት ሂሩት በቀለ ላሉ ታዋቂ አርቲስቶችም የማይረሱ ዜማዎችንና ግጥሞችን ጽፋለች ተመስገን ኡካሬ የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1 Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical Telegram:-https://t.me/Arada_Fm Telegram:-https://t.me/aradaFmdigital Facebook:-https://web.facebook.com/aradafm @Arada_Fm
ይድረስ ለአራቱ ድምፃውያን – “ማንም የላት” ከተሰኘው የኅብረት ዜማ ጋር በተያያዘ ከተመስገን ኡካሬ (የሐጌ ልጅ)
ይድረስ ለአራቱ ድምፃውያን – “ማንም የላት” ከተሰኘው የኅብረት ዜማ ጋር በተያያዘ ከተመስገን ኡካሬ (የሐጌ ልጅ) "ማንም የላት" የተሰኘው የኅብረት ዜማ ሙዚቃ ብቻ አይደለም፤ የህሊና ጥሪ፣ የማህበራዊ ኃላፊነት ማንቂያ እና የሰብአዊነት መልዕክት ነው። ይህ ስራ የአካል ጉዳተኞችንና የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያላቸውን ወገኖች በርኅራኄ ከመመልከት ይልቅ፣ እንደ ሙሉ መብት ባለቤቶች እንድናያቸው ያስጠይቃል። ሙዚቃው የሚያነሳው ዋና ጥያቄ አካል ጉዳተኝነት ሳይሆን፣ እኛ እንደ ማህበረሰብ የፈጠርነው የመዳረሻ እጥረት ነው። ትራንስፖርት፣ ትምህርት፣ ስራ፣ የህዝብ አገልግሎቶች እና ማህበራዊ ተሳትፎ ለሁሉም እኩል ተደራሽ ናቸው ወይ? የሚለውን ጥያቄ በጥልቅ ያቀርባል። የኅብረት ዜማዎች ሁልጊዜም የዘመናቸውን ማህበራዊ ጉዳይ ያንጸባርቃሉ። "ማለባበስ ይቅር"፣ "ስደት"፣ "ሰላም ለሀገራችን" እና ሌሎችም እንደ ነበሩት ሁሉ፣ "ማንም የላት" ደግሞ የዚህ ዘመን የህሊና ጥሪ ሆኖ ተገኝቷል። ይህ ስራ በስሜት ብቻ የተሞላ አይደለም፤ መፍትሄ የሚፈልግ ጥያቄ ያቀርባል። "ማንም የላት" የሚለውን አባባል "እኛም አለን" በሚል ተግባራዊ መልስ እንድንተካው ይጋብዘናል። በዚህ ዜማ ላይ የተሳተፉት ድምፃዊ ማስተዋል እያዩ፣ ድምፃዊት ሀና ግርማ፣ ድምፃዊ አብርሃም በላይነህ (ሻላዬ) እና ድምፃዊት ሄዋን ገብረወልድ እያንዳንዳቸው መልዕክቱን በሚመጥን ስሜት አቅርበዋል። ግጥሙን ናትናኤል ግርማቸው፣ ዜማውን አህመድ ተሾመ (ዲንቢ)፣ ቅንብሩን ደግሞ ታምሩ አማረ (ቶሚ) በሙያዊ ብቃት አስውበውታል። የግጥሙ፣ የዜማው፣ የድምፅ አቀራረቡና የቅንብሩ መዋሃድ ሙዚቃውን ከመዝናኛነት በላይ ወደ ማህበራዊ ንቅናቄ አሳድጎታል። ይህ ዜማ የሚያስታውሰን አንድ እውነት አለ፤ ሰብአዊነት በቃላት ሳይሆን በተግባር ይለካል። አካል ጉዳተኞች ርኅራኄ አይፈልጉም፤ እኩል ዕድል፣ ተደራሽነትና ክብር ይፈልጋሉ። ይድረስ ለአራቱ ድምፃውያን፤ ለህዝብ የሚያስብ፣ ህሊናን የሚያነቃ እና ማህበረሰብን ወደ በጎ ለውጥ የሚጋብዝ ስራ ስላቀረባችሁ ምስጋና ይገባችኋል። ይህ ዜማ በሙዚቃ ታሪክ ውስጥ እንደ ዜማ ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ማህበራዊ ጥሪ የሚታወስ ስራ ይሆናል። አቶ ሳሚ ተድላ ( የተድላ አምቡላንስ መሥራችና ባለቤት ) "ማንም የላት" የተሰኘው የኅብረት ዜማ ፕሮውዲሰር ምስጋና ይገባቸዋል። በተለይም ጥበብንና በጎ አድራጎትን አጣምሮ በመያዝ፣ አቅም የሌላቸውንና ረዳት ያጡ ወገኖችን ድምፅ ለማሰማት ያደረጉት ጥረትና ያወጡት ወጪ የሚወደስ ነው። በተጨማሪም በተድላ አምቡላንስ በኩል የሚያደርጉት ድገስ የሕክምና አገልግሎትና የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴ፣ በኅብረተሰቡ ዘንድ ትልቅ አክብሮትና ምስጋና የሚያሰጣቸው ያደርጋቸዋል። እንደዚህ ያሉ በጎ አድራጊ ባለሃብቶችና ድርጅቶች ለሌላውም አርአያ የሚሆኑ ናቸው።
ይድረስ ለአራቱ ድምፃውያን – “ማንም የላት” ከተሰኘው የኅብረት ዜማ ጋር በተያያዘ ከተመስገን ኡካሬ (የሐጌ ልጅ)
ይድረስ ለአራቱ ድምፃውያን(ማንም የላት) (ከተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ) ጠያቂ ትውልድ ካልኖረ ያስፈራኛል… የትውልድ ድምፅ… ጠያቂ ትውልድ… ሰሚ ጆሮ ፈላጊ የኅብረት ሙዚቃ ዘመን እየተወለደ፣ ሙዚቃ አብቦና ጎምርቶ እየወጣ፣ የሙዚቃ የዱላ ቅብብሎሹ በዛሬው ትውልድ ላይ አርፏል፡፡ የኅብረት ዜማዎች በዘመን እርምጃዎች ውስጥ የተለያየ መልክና መንገድ ይዘው ይወለዳሉ፡፡ ለምሳሌ፦ «ማለባበስ ይቅር»፣ «ኑር ባታምንም»፣ «ስደት»፣ «መላ መላ»፣ «እኔ ነኝ ደራሽ ለወገኔ»፣ «ሁሉ ቢተባበር»፣ «የሀገር ካስማ»፣ «እኛም ኮራን በእናንተ»፣ «ከፍ ከፍ እንበል»፣ «ሰላም ለሀገራችን» እና የመሳሰሉት በልካቸውና በመልዕክታቸው ለሚመለከተው አካል አድርሰዋል፤ እያደረሱም ይገኛሉ፡፡ አሁን ደግሞ ተራው የዚህ ዘመን ትውልድ ነው፤ ለመሆኑ የኅብረት ዜማ ለምን ይሰራል? በዚህ ሙዚቃ ላይ የታዘብኩትን ላካፍላችሁ። «ማንም የላት» የሚለው ሙዚቃ በዋናነት የሚያጠነጥነው የአካል ጉዳተኞች እና የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያላቸው ወገኖቻችን ዋና ፈተና አካላዊ ወይም አእምሮአዊ ሁኔታቸው ብቻ ሳይሆን፣ «እኛ እንደ ሕብረተሰብ የፈጠርንላቸው ምቹ ነገር አለ ወይ?» በሚለው ጥያቄ ላይ ነው፡፡ የትራንስፖርት አገልግሎት እጦት፣ የወገን ድጋፍ ማነስና የመሳሰሉትን በማንሳት «እስካሁን የት ነን?» የሚል ልብ የሚነካ መልዕክት ያስ አስተላልፋል፤ መልስም ይሻል። Voice of the World (ለዓለም ድምፅ የሚሆን)፦ አጣዳፊ እና ተፈላጊ ነገር ሲኖር፣ በእኛነት ስሜትና በተለያዩ ድምፆች በጥምረት ለዓለም ማስተጋባት ይገባል፡፡ የሚተላለፈው መልዕክትና ድጋፍ ክብደቱ እንዲመዘን ጥሪ ያስተላልፋል፡፡ *A Generation Driven by Emotion and Resentment (በስሜታዊነት እና በቁጭት ያገነፈለ ትውልድ)፦ ሙዚቃው ገና ሲጀምር ስሜትን አዝሎ ምልከታውን ያደርሳል፡፡ ለብቻ አጥር ሰርቶ መኖር ሳይሆን፣ በእኩልነት የመኖር ደረጃችን ቢለያይም ዝቅ ብለን ጥያቄያቸውን መመለስ አለብን፡፡ ፈገግታቸውን ከእኛ ጋር እኩል ማስቀጠል ይኖርብናል፤ "ማንም የላት" የሚለውን አባባል አፍርሰን "እኛም አለን" እንበል፡፡ *A Questioning Generation (ጠያቂ ትውልድ)፦ ስንቶቻችን ነን ነገን በተማርነው ልክ ለመናገር የፈለግን? በችግሮች መካከል ለመሻገር ቆርጠን የተነሳን? በእኔነት ሳይሆን በእኛነት አስበን የምንኖር የት ነን? ሰው የመሆን ጥማታችን የሚጀምረው ራስን ከማስተካከል ነው፡፡ በራሳችን ቆመን ስንቱን በኅብረት እንዲሻገር አድርገናል? ልባችንን እንጠይቅ፡፡ ጥያቄዎችን በአንድነት ለመፍታት ተዘጋጅተናል? ለእነሱሳ ዕድል ሰጥተናል? እራሳችንን እንጠይቅ፡፡ *Character-driven / Realistic (ገፀ-ባህርይን የተላበሰ)፦ ከእውነታ የተቀዱ ሙዚቃዎች ለኅብረት ዜማዎች በጣም ምቹ ናቸው፡፡ የጠነከረ እና በአንድነት የመጮኽ ኃይል የሚሰጠውም ይህ ነው፡፡ ሙሉ አካል የነበረው ሰው በአንድ አጋጣሚ አካሉ ሲጎደል የሚደርስበት ጉዳት እንዳለ ሆኖ፣ እኛ ደግሞ የጎደለውን ለመሙላት የምንጓዝ እና የመፍትሔ ሰው እንድንሆን ይመክረናል፡፡… "ተምሮ ለማወቅ፣ ሰርቶ ለመሻሻልሁሉም በየመስኩ መንቀሳቀስ ይሻልእንደ ሌላው ሁሉ እንደ መጓጓዣየታለ ለእነሱ መነሻ መድረሻው?"… *Alarm Clock (ማንቂያ ደውል)፦ የሕልምና የመኖር ትግል፣ ራስን የመሸነፍ ቁልፍ ፍለጋ፣ ዳገቱን አብሮ ለመውጣት ዝግጁ መሆን፣ ለመማርና ለማስተማር ሁላችንም እንንቃ! ጉዳዩ እያንዳንዱ ቤት የሚገባና የሚገኝ በመሆኑ በራችንን ገርበብ ሳይሆን ቦርቀቅ አድርገን እጆቻችንን እንዘርጋ፡፡ *Arrangement Technique (የቅንብር ቴክኒክ)፦ ፍሰቱን እና ስሜቱን በጠበቀ መልኩ፣ በባህሪው ልክ የተሰፋ ነው፡፡ ለድምፅ ቅጂው መመጣጠን፣ ድምፁ እና ገፀ-ባህሪው ጎልተው እንዲወጡ ረድቶታል፤ ከእኛ ጋር ቁርኝት እንዲፈጥር ስሜቱን ጠብቆ አዝልቆታል፡፡ «የለም የላት» በሚለው በዚህ ሙዚቃ ላይ ድምፃዊ ማስተዋል እያዩ፣ ድምፃዊት ሀና ግርማ፣ ድምፃዊ አብርሃም በላይነህ (ሻላዬ) እና ድምፃዊት ሄዋን ገብረወልድ ተሳትፈውበታል፡፡ ግጥሙን ስሜታችንን በያዘ መልኩ የቃኘው ናትናኤል ግርማቸው ሲሆን፣ ዜማው ደግሞ የአህመድ ተሾመ (ዲንቢ) ነው—አብሮ የመኖር ሚስጥር የወለደው ጥበብ! ቅንብሩ በታምሩ አማረ (ቶሚ) የተሰራ ሲሆን፣ የራሱ የሆነ የድምፅ ቀለም እንዳለው ሆኖ እንደ ሙዚቃው ገፀ-ባህሪ ውበት ሰጥቶት ሰርቶታል፡፡ "የሀገር አስተዋፅኦ ሰርተን ለማበርከት አለን እኛም እኩል የመንቀሳቀስ መብት"… ይድረስ ለአራቱ ሙዚቀኞች(ከተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ)
ይድረስ ለአራቱ ድምፃውያን (ማንም የላት) (ከተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ)
ክረምት እና ሙዚቃ በኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ታሪክ በተለይም በሙዚቃ ታሪክ ውስጥ "ክረምት" ተራ የተፈጥሮ ወቅት መፈራረቅ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም የሰዎች ስሜት፣ የፍቅር፣ የናፍቆትና የህይወት ውጣ ውረድ የሚገለጥበት ጥበባዊ መስታወት እንጂ። *ድምፃዊ አህመድ ተሾመ "ተጠየቂ ናዝሬት":- "ይህ ዘፈን በክረምት ወቅት የሚከሰት አካላዊ ና መንፈሳዊ ብቸኝነት በጥበብ የሚያሳይ ነው:: ድምፃዊው የአዲስ አበባ ደመናማ ና ቀዝቃዛ ዓየር የፍቅረኛውን እቅፍ ና ናፍቆት አብዝቶ እንዲናፍቅ ሲያደርገው፣ ሞቃታማዋን ናዝሬት (አዳማ) ደግሞ የፍቅር፣ የደስታና የሙቀት ምሳሌ አድርጎ ይስላታል። ሙዚቃው የአየር ጠባይ ልዩነት እና በውስጥ ስሜት መካከል ያለውን ቁርኝት የሚያሳይ ሲሆን፣ አዳማን እንደ ፍቅር መፈለግያ ብሎም ማረፊያና የክረምት ብርድ መሸሸጊያ አድርጎ አቅርቦታል:: *ድምፃዊ አበበ ቀበታ "ክረምት ያልፋል" የተሰኘው ሥራ የክረምቱን ተፈጥሮአዊ ባህሪ መሠረት በማድረግ የተፃፈ ጥልቅ ፍልስፍናዊ ና ተስፋ አዘል ሙዚቃ ነው:: በብዙ የኢትዮጵያ ባህላዊ ና ማህበራዊ እይታዎች ክረምት የጭጋግ ና የመከራ ምሳሌ ተደርጎ ሲወሰድ፣ በጋ ደግሞ የብርሃን ና የደስታ ወቅት ተደርጎ ይታያል:: ሙዚቃው ይህንን የተፈጥሮ ህግ የሰው ልጅ ህይወት ውጣ ውረድ መግለጫ አድርጎ ይጠቀምበታል:: በክረምት ወቅት የሚጥለው ከባድ ዝናብ ና ሰማዩን የሚጋርደው ደመና ሁሉ ጊዜያዊ እንደሆኑ ና በእርግጥም የብርሃን በጋ እንደሚተካ በማበሰር፣ ለተከፋ ና ተስፋ ለቆረጠ ሰው ትልቅ መንፈሳዊ ጥንካሬና ብርሃን የሚያስጨብጥ ምልከታ አለው፡፡ *ድምፃዊት አስቴር አወቀ "ብርዱ አልተስማማኝም" የክረምትን አየር ጠባይ ከውስጣዊ የፍቅር ስሜት ጋር በማያያዝ የተሰራ የሙዚቃ ስራ ነው:: ዘፈኑ የክረምቱን ቅዝቃዜ እንደ ተራ የተፈጥሮ ሁኔታ ሳይሆን፣ የተወደደውን ሰው በማጣት የሚፈጠርን ጥልቅ ባዶነት ና የልብ ብርድ ለማሳየት ይጠቀምበታል:: ውጭ ያለው አካላዊ ብርድ ና ዝናብ የውስጥን የፍቅር ናፍቆት ይበልጥ የሚያጋግለው ሲሆን፣ የአስቴር ድምፅ ና የአቀራረብ ስልት በብቸኝነትና በቅዝቃዜ ውስጥ ያለችውን ሴት ስሜታዊ ስቃይ በግልጽ ያሳያል፡፡ ይህን ሙዚቃ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ታደሰ በአጋጣሚ ከአበበ መለሰ ጋር መስራታቸውን ገልፆ ነበር፡፡ *ድምፃዊት ነፃነት መለሰ በሙዚቃዋ የሀምሌን ወር የፀሐይ ባህሪ ለፍቅር ምሳሌነት ተጠቅማዋለች:: በሀምሌ ወር ከባድ ዝናብና ደመና የሚበዛበት በመሆኑ ፀሐይ ብቅ የምትለው አልፎ አልፎ ና ለጥቂት ደቂቃዎች ብቻ እንደመሆኑ መጠን፣ ድምፃዊቷ የፍቅረኛዋን መመላለስና በፍጥነት መሸሸግ ከዚህ የሀምሌ ፀሐይ ባህሪ ጋር ታነጻጽረዋለች:: የሀምሌ ፀሐይ ለጥቂት ጊዜ ብቅ ስትል ትልቅ ደስታ ና ሞቅታ እንደምትሰጥ ሁሉ፣ ፍቅረኛዋ ለጥቂት ጊዜም ቢሆን ብቅ ማለቱ በክረምቱ ጨለማ ውስጥ ትልቅ የብርሃን ደስታ ይዞላት ይመጣል:: ሆኖም እንደ ሀምሌ ፀሐይ ብቅ ብሎ መሸሸጉ የናፍቆት ስቃይን ስለሚፈጥር ጸንቶ እንዲኖርላት የምትማጸንበት ልኬታ ነው፡: መስፍን በቀለ፣ጎሳዬ ተስፋዬ እና ታምራት ደስታ እና ሌሎችም ስለክረምት ዘፍነዋል፡፡ በጥቅሉ ክረምት ለተስፋ፣ ለወዋደድ እና ወደ አዲሱ አመት በንጹህ ልብ ለመሻገር ስንቅ ሆኖ የቀረቡ ናቸው፡፡ ተመስገን ኡካሬ @aradafm
без подписи
без подписи
без подписи
የድምፃዊ ፍቃዱ ትዛዙ አዲስ ነጠላ ሙዚቃ ሊለቅ ነው ሐምሌ 21፣ 2018 (አራዳ ኤፍ ኤም) ድምፃዊ ፍቃዱ ትዛዙ “ቁንጅና" የተሰኘ አዲስ የሙዚቃ ቪዲዮ በቅርብ ቀን ለተመልካች ለማብቃት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡ ግጥም እና ዜማ በራሱ በድምፃዊ ፍቃዱ ትዛዙ የተደረሰ ሲሆን፣ በሙዚቃ ቅንብርና ሚክሲንግ በአቤል ጳውሎስ ተከናውኗል፡፡ “ቁንጅና” የተሰኘው አዲስ ሙዚቃ በቅርብ ቀን በናሆም ሪከርድስ በይፋ ይለቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ድምፃዊው ከዚህ ቀደም ዘንድሮ የተሰኘ አልበም በናሆም ሪከርድስ አማካኝነት መልቀቁ አይዘነጋም፡፡ ተመስገን ኡካሬ የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1 Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical Telegram:-https://t.me/Arada_Fm Telegram:-https://t.me/aradaFmdigital Facebook:-https://web.facebook.com/aradafm @Arada_Fm
ሙዚቃ እና ክረምት ተመሰገን ኡካሬ የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1 Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical Telegram:-https://t.me/Arada_Fm Telegram:-https://t.me/aradaFmdigital Facebook:-https://web.facebook.com/aradafm @Arada_Fm
ማክሰኞ ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም አራዳ ኤፍኤም 95.1 ፤ ውለው የሚያመሹበት! መልካም ቀን ! @Arada_Fm
ይድረስ ለድምፃዊ ሐብታሙ ይሄነው (ከተመስገን ኡካሬ) የድምፃዊ ሀብታሙ ይሄነ ከልፋት ወደ መድረክ ብርሃን በዚህ ጣፋጭ ሕይወት መጎናፀፍ "የአንተ ነገህ በግልጽ ይታያል፤ በቃ ጎበዝ ነህ፣ ትችላለህ!" — ይለው ነበር አቤል ሙሉጌታ (ለሀብታሙ ይሄነው የሰጠው አስተያየት ነው) በቅርበት አውቀዋለው ሐብታሙ ከከባድ የሕይወት መሰናክሎችን ያለፈ ደግሞም በፋና ላምሮ ውድድር ወቅት አሳማኝ ዘፋኝ ሆኖ ያስመሰከረበት ነው፡፡ የጫኝ-አውራጅነት ድካም እስከ መድረክ ላይ ኮከብነት የተጓዘው የድምፃዊ ሀብታሙ ይሄነው ህይወት፣ ከልጅነቱ ጀምሮ ከሙዚቃ ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ነው። ተወዳጁ ድምፃዊ ሀብታሙ ይሄነው ተወልዶ ያደገው ከአዲስ አበባ ወጣ ብላ በምትገኘው ብርሸለቆ ሲሆን፣ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱንም በዚሁ አካባቢ አጠናቋል። የኑሮን ውጣ ውረድ ለመጋፈጥና ህይወቱን ለመለወጥ ወደ አዲስ አበባ በመጣበት ወቅት ያልሰራው ስራ፣ ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም። ከጫኝ-አውራጅነት እስከ ጋራዥ ሰራተኝነት ባሉት አጋጣሚዎች ሁሉ እግሮቹ ቢደክሙም ተስፋ ሳይቆርጥ ታግሏል። ሀብታሙ ገና ከልጅነቱ ጀምሮ የሙዚቃ ፍቅር በልቡ ስለነበር፣ የተለያዩ ዜማዎችን በስሜት ያንጎራጉር ነበር። የጥላሁን ገሰሰ፣ የሙሐሙድ አህመድ፣ የምኒልክ ወስናቸውን እና የኤልያስ ተባበልን ዘፈኖች በጥ በጥ አድርጎ በመጫወት የሙዚቃ ክህሎቱን አዳበረ። አጋጣሚዎች የራሳቸው ውበት አላቸውና፣ ሀብታሙ ድምፁን ለማስመሰከር በፋና ላምሮት የሙዚቃ ውድድር ምዕራፍ 13 ላይ ተሳተፈ። በመድረኩም አስደናቂ ብቃቱን አሳይቶ የሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የብዙዎችን ፍቅርና አድናቆት አተረፈ። የውድድሩ ዳኞችም " የመድረክ አያያዝህ፣ የአቀራረብ ስልትህና የድምፅ ቴክኒክ ቁጥጥርህ እጅግ የሚደነቅ ነው!" ሲሉ አወደሱት።የሀብታሙ የስኬት ጉዞ በዚህ አላበቃም። በፋና ላምሮት 4ኛው 'የአሸናፊዎች አሸናፊ' ውድድር ላይ ከ16ቱ ምርጥ ተወዳዳሪዎች መካከል ዳግም ሁለተኛ በመውጣት የ1 ሚሊዮን ብር ተሸላሚ ለመሆን በቃ። ሀብታሙ በአንድ በኩል በእጆቹ የተበላሹ መኪኖችን እያከመ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በጣፋጭ ጉሮሮው የሰዎችን ስሜት የሚያስጠፋ የሀሴት ምንጭ ሆኗል። እጆቹንና ጉሮሮውን በስራ አጥምዶ ለዚህ ደረጃ የበቃው ሀብታሙ ይሄነው—የጽናት፣ የልፋትና የታላቅ ጥበብ ማሳያ ነው።-
без подписи