Gurage Zone Government Communication Affairs
СтатистикаGurage Zone Government Communication Affairs
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 47
- Всего постов
- 50
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 148
- 1/48двое суток
- 169
- 1/72трое суток
- 182
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
ወሄም ሳረናሁም፣ወሄም ሳረነም እንኳን ደስ አላችሁ ፣እንኳን ደስ አለን!! በጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኮሚሽን በክልሉ ካሉ የዞን መዋቅሮች በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገቡ አንደኝነት በመውጣት ተሸላሚ ሆነ! ነሀሴ 8/2018 ዓ•ም(ወልቂጤ) በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኮሚሽን "ሁሉ አቀፍ እመርታ ለሁለንተናዊ ከፍታ" በሚል መሪ ሀሳብ የ2018 ዓ.ም አጠቃላይ የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ተግባቦት መድረክ በሆሳዕና ከተማ አካሂዷል። ኮምሽኑ ዛሬ ባካሄደው አመታዊ ጉባኤ በጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኮሚሽን በክልሉ ካሉ የዞን መዋቅሮች 1ኛ ሆኖ በማጠናቀቅ የዋንጫና የሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆኖዋል። እውቅናው ኮምሽኑ በቀጣይ ስራውን በተሻለና በላቀ ሁኔታ ለመስራት የሚያግዘው እንደሆነ ተመላክቷል። በጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኮሚሽን ለተገኘው ውጤት አስተዋጽኦ ለነበራቸውን ባለድርሻ አካላትን በሙሉ በማመስገን ፣በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ደስ አለን ብሏል። "ለጠንካራ ፓርቲ መመስረት የኢንስፔክሽንና የስነምግባር ስራዎቻችን ወሳኝ ናቸው!!"
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
በጉራጌ ዞን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በሚገኙ የማዘጋጃ ከተሞች ከ325 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ከ20 በላይ ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ፕሮጀክቶች ማከናወን መቻሉ ተነገረ። ነሐሴ 7/2018(ወልቂጤ) የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በስድስቱም ማዘጋጃ ቤቶች እየተሰሩ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን የመስክ ጉብኝት አድርጓል። የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የድጋፍና ክትትል ስራ ተጠናክሮ እየተሰራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል። የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ሀላፊ ወይዘሮ ትብለጥ እስጢፋኖስ በጉብኝቱ ላይ እንደተናገሩት በተለያዩ አካባቢዎች እየተሰሩ የሚገኙ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ መምሪያው የድጋፍና ክትትል ስራ አጠናክሮ እየሰራ ይገኛል። በተለያዩ ከተሞች የሚሰሩ የአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት የህብረተሰቡን የመልማት ጥያቄዎችን የሚመልሱ በመሆናቸው በደንብ ትኩረት እንደሚያሻው አስረድተዋል። ወይዘሮ ትብለጥ አክለውም የገጠር ኮሪደር ልማት የገጠር መንደሮችን ከመሠረተ ልማት ጋር በማስተሳሰር የአካባቢውን ህብረተሰብ ከዘመናዊው አኗኗር የሚያገናኝ በመሆኑ በዞኑ በተመረጡ ሞዴል መንደሮች እየተተገበረ መሆኑን ገልጸዋል። የወረዳው አርሶአደር ሰብል አምራች በመሆኑ የአካባቢው ተወላጅ ባለሀብቶችን አስተባብሮ የመንገድ መሰረተ ልማት ላይ ትኩረት እንዲደረግ አሳስበዋል። የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳደሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን እንደገለጹት በወረዳው በሚገኙ በማዘጋጃ ከተሞች በ2018 በጀት ዓመት ብቻ ከባለሀብትና ከህብረተሰቡ 260 ሚሊየን ብር በላይ በመሰብሰብና ከመንግስት ከ65 ሚሊየን ብር በላይ በጀት በመመደብ በጥቅሉ ከ325 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ከ20 በላይ የልማት ፕሮጀክቶች ማከናወን መቻሉን ተናግረዋል። በወረዳው ከተሞች የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ የመንገድ፣የአገልግሎት መስጫ ተቋማት፣የመብራት ተደራሽነት፣የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ ሌሎችም የማት ስራዎች መከናወናቸውን አብራርተዋል። ዋና አስተዳዳሪው አክለውም የተለያዩ አካባቢዎች የህብረተሰቡ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ የሆነው የመብራት አገልግሎት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ በመሆኑ አመርቂ ውጤቶች እየመጡ መሆናቸውን አስረድተዋል። በዛሬው እለት ከተጎበኙ ፕሮጀክት መካከል የወለጋ ዲሴ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ግንባታ የኢንጌ ከተማ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንዲሁም በተለያዩ የመዘጋጃ ቤቶች የሚገኙ የአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክቶች ተጎብኝተዋል። በመጨረሻም አመራሮቹ የአረንጓዴ አሻራቸውን በመሀልአምባ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አሳርፈዋል።
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи