Addis Admass
Статистикаየአዲስ አድማስ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ ===== አዲስ አድማስ https://bit.ly/2V1zyZQ ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2V0I6jx ትዊተር↠ https://bit.ly/33fDhaP ቴሌግራም↠ https://bit.ly/2JgeCvG ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3q2hXiv የእርስዎና የቤተሰብዎ
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 107
- Всего постов
- 451
- Тип
- открытый
- Язык
- om
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 12 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 256
- 1/48двое суток
- 1 439
- 1/72трое суток
- 1 552
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ቡርኪና ፋሶ ለጋዜጠኞች የ«ሀገር ፍቅር» ስልጠና መስጠት ጀመረች የቡርኪና ፋሶ ወታደራዊ መንግሥት በግልና በመንግስት ሚዲያ ለሚሠሩ ጋዜጠኞች አስገዳጅ የሆነ ወታደራዊ የ«ሀገር ፍቅር» ሥልጠና መስጠቱን የጀርመን ዜና ወኪል ዘግቧል፡፡ 44 የሚሆኑ የሴትና የወንድ ጋዜጠኞች ቡድን ከዋና ከተማዋ ኦዋጋዱጉ አጠገብ በሚገኝ የፖሊስ አካዳሚ የስድስት ቀናት ሥልጠና አጠናቀዋል። ቪዲዮዎች እንደሚያሳዩት ፣ ተሳታፊዎቹ ወታደራዊ ልብስ ለብሰው ጠመንጃ ይዘዋል። መንግሥት ይህ ሥልጠና የተዘጋጀው አገሪቱ ከሽብርተኞች ጋር እያደረገች ያለውን ጦርነት ለመደገፍና የሀገር ፍቅር ስሜት ለመፍጠር ነው ብሏል። የፕሬስ ነፃነት ተሟጋቾች ይህንን እርምጃ በመቃወም ጋዜጠኞች ወታደሮች መሆን የለባቸውም ሲሉ አስጠንቅቀዋል። በተጨማሪም መንግሥትን የሚተቹ አንዳንድ ጋዜጠኞች በግዳጅ ወደ ሠራዊቱ ገብተው ወደ ጦር ግንባር መላካቸው ተነግሯል። የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
አራት ኪሎ ግራም ጥፍጥፍ ወርቅ በቁጥጥር ስር ዋለ ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ላይ በነበረ ተሳፋሪ በኩል በህገ-ወጥ መንገድ ሊዘዋወር የነበረ አራት ኪሎ ግራም ጥፍጥፍ ወርቅ በአዲስ አበባ ኤርፖርት በቁጥጥር ስር ውሏል። ግለሰቡ ወርቁን በለበሰው ውስጥ ሱሪ ውስጥ ደብቆ ለማሳለፍ ሲሞክር በጉምሩክ ሠራተኞች ጥብቅ ፍተሻ ተይዞ አሁን ላይ በህግ ጥላ ሥር ሆኖ ምርመራ እየተደረገበት ነው። ሕገ-ወጥ ንግድ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ፣ ይህንን ለመከላከል ከጉምሩክ በተጨማሪ ሁሉም ኅብረተሰብ እና ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ኃላፊነት ሊወጡ ይገባል ተብሏል። ጉምሩክ ኮሚሽን የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas #ጉምሩክኮሚሽን #ኮንትሮባንድ #ወርቅ #አዲስአበባኤርፖርት #ኢትዮጵያ #BreakingNews
የባህር ዳር ስታዲየም የካፍ መስፈርቶችን አሟላ የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገለት ሰፊና ዘመናዊ የሁለተኛ ምዕራፍ የማሻሻያና የግንባታ ሥራ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) መስፈርቶችን ሙሉ በሙሉ በማሟላት ለዓለም አቀፍ ውድድሮች ዝግጁ መሆኑን የአማራ ክልል ባህል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ መልካሙ ጸጋዬ ገለጹ። ለበርካታ ዓመታት በኢንተርናሽናል ውድድሮች እገዳ ተጥሎበት የቆየው ይህ ስታዲየም መታደሱ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ትልቅ መነቃቃትን ይፈጥራል። ይህ ታሪካዊ የስፖርት ስኬት የሀገራችን ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) እና ክለቦቻችን በሜዳቸውና በደጋፊያቸው ፊት የመጫወት ዕድላቸውን የሚመልስ ከመሆኑም በላይ፣ ኢትዮጵያ ወደፊት አበይት አህጉር አቀፍ ውድድሮችን ለማስተናገድ የምታደርገውን ጉዞ በእጅጉ ያፋጥነዋል።
የሁቲ ታጣቂዎች በቀይ ባሕር ወደብ ላይ ጥቃት መፈጸማቸው ተነገረ በኢራን የሚደገፉት የሁቲ ታጣቂዎች የየመን መንግሥት በሚቆጣጠረው የሞቻ ወደብ ላይ ባደረሱት ጥቃት አንድ የደኅንነት አባል መገደሉን የየመን ጦር አስታወቀ። ታጣቂዎቹ አርብ ምሽት ወደ ወደቡ ስድስት ባሊስቲክ ሚሳዔሎችን እና በርካታ ድሮኖችን የተኮሱ ሲሆን፣ በዚህም ሰላማዊ ሰዎች መጎዳታቸውንና የአገሪቱ መከላከያም ከድሮኖቹ ውስጥ 15ቱን መትቶ መጣሉን ቢቢሲ ዘግቧል። በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለው ውጥረት እየባባሰ ባለበት በዚህ ወቅት የሁቲዎች እና የየመን መንግሥት ግጭትም አገር አቀፍ ትኩረት አግኝቷል። ሳዑዲ አረቢያ የየንን ወደቦች በመዝጋቷ ምክንያት ሁቲዎች በበቀል መልክ የሳዑዲ መርከቦች በቀይ ባሕር እንዳያልፉ እገዳ መጣላቸውን ቢቢሲ አመልክቷል።
ለመሆኑ መኪና በ30 እና በ50 ኪሎ ሜትር በሰዓት ንዱ የሚል ምልክት ነጻ ጎዳና ላይ ለጥፋችሁ፣ መኪና በረረ ብላችሁ መሃል ስትገቡ መኪናው ወድያው እንደሚቆም አምናችሁ ነው አይደል? ታድያ በቀላሉ ለሚቆም መኪና ፍጥነት ቀንስ ማለትን ምን አመጣው? ከ80 ኪሎ ሜትር በሰዓት በታች ፍጥነትን መገደብ የመኪና ኢነርሽያን አለማገናዘብ ነው። ኋላ ላይ ሰውየው "ቀቢ ቀቢ ድርር" እያለ ሲያስቆም የቆሙ መኪኖችን ከርቀት እያዩ ሌሎች ሾፌሮች ነገሩ ገባቸውና ዝግ ብለው መምጣት ጀመሩ። ይሄኔ ለቅጣት ከወረዱት መካከል አንዱ ሾፌር "መኪኖቹን አሰልፈህ የቀብር ነው የሠርግ አጃቢ አስመሰልካቸው እኮ?" ሲለው የተሰበሰበው ሁሉ ሳቀ። ፖሊሱም ተናዶ "አንተ ሰውዬ ከዚህ ዞር በልልኝ" አለና የቆመትን እንዳያባርራቸው ለክፍያ የቆሙ ናቸው። አንዳንዴ እንዲህ ያለ ወጊ ያጋጥማል። የትራፊክ ፖሊስ ዓላማ አደጋ እንዳይደርስ መኪኖችን ማስተላለፍ እንጂ ቅጣት መጻፍ አልነበረም። በኩሽ ምድር ግን "ትራፊክ_ፖሊስ" ወደ "ፔናሊቲ_ፖሊስ" ተቀይሯል። ፔናሊቲ ፖሊስ ዓላማው መኪኖች ማስተላለፍ ወይም አደጋ መቀነስ አይደለም። ፔናሊቲ ፖሊስ ዓላማው በቅጣት ብዙ ገንዘብ መሰብሰብ ነው። ፔናሊቲ ፖሊስ ብዙ ሰው ሲቀጣ ደስ ይለዋል። ሰው ሲቀጣ ፔናሊቲ ፖሊስ "ቀቢ ቀቢ ድርርር" ይልና መሃል አስፋልት ውስጥ ይገባል። ይህንን የፍጥነት ወሰን ጉዳይ ሳይ ሁሌም ትዝ የሚለኝ ጣልያን ሮም ውስጥ ወደ ፉሙቺኖ አየር ማረፊያ ያደረግሁት ጉዞ ነው። እኛ በፍጥነት እየተጓዝን እያለ ሌላ መኪና በአጠገባችን እንደጥይት ተተኩሶ አለፈ። ይሄኔ የእኛን መኪና ፍጥነት ሳይ 120 ይላል። ያኛው ከ150 ኪሎ ሜትር በሰዓት በላይ እየሄደ እንደሆነ ለመገመት አልከበደኝም። ይሄ ቀቢ ቀቢ የሚለው ትራፊክ እዚያ ቢሆን አየር ላይ ተሰጥቶ ይሆን እንደነበር ሳስብ ዘገነነኝ። ነገሩ በዚህ ከቅጠለ የአቡሴራ አየር ማረፊያ ሥራ ሲጀምር መኪኖቹ በዚህ የፍጥነት ቁጥጥር ምክንያት ዝግ ብለው ከሄዱ ብዙ ሰው ከበረራ መሰናከሉ አይቀርም። ነገርን ማገናዘብ፣ ህዝብን ማክበርና feedback ሰምቶ ህግን ማሻሻል ከሚያስብ ሰው የሚጠበቅ ነው። ፍጥነት ጥቅምም ጉዳትም አለው። ነገር ግን ፍጥነት ጉዳት አለው ተብሎ አውሮፕላን በ50 km/H ብቻ ብረር ቢባል አውሮፕላኑ ከመሬት አይነሳም። መኪናም ከ180 እስከ 220 km/H የሚያሳይ የፍጥነት ጌጅ የተገጠመለት በምክንያት ነው። 30 የሆነው በምክንያት ነው የሚለው አባባል አይሠራም። እስኪ ይህንን ምክንያት ለአውሮፕላን አድርጋችሁ አሳምኑን? ቴክኖሎጂን በትክክል የሚረዱ የትራፊክ አስተዳዳሪዎች እና አስተናባሪዎች እስኪመጡ ድረስ በዚህ አስቸጋሪ ህግ ህዝብ እያዘነ መጓዙ እስከ መቼ ይቀጥላል? እኔ ግን እንዲህ ሆኖ ብዙ የሚቀጥል አይመስለኝም። አይቀጥልም! የትራፊክ ፖሊስን አስፈላጊነት የሚያስቀር ቴክኖሎጂ ይመጣል። ያውም በቅርቡ! ያኔ ህዝቤ "እፎይ" ይላል። እስከዚያው ግን "ቀቢ ቀቢ ድርርር" ማለት ይቀጥላል። Get Toughe Zer- ሁሌም እንደምለው ነጻ አውጪያችን ቴክኖሎጂ ነው።
"ትራፊክ ፖሊስ" ወይስ "ፔናሊቲ ፖሊስ" ? ሰውየው "ቀቢ ቀቢ ድርርር!" ይልና መሃል አስፋልት መንገድ ውስጥ ሮጦ ይገባል። እንዲህ የሚለው ሰው ከአሊ ቢራ አደባባይ ወደ ዩኒሳ አደባባይ በሚወስደው አውራ ጎዳና ላይ ያለ አንድ ትራፊክ ፖሊስ ነው። እንዲህ ያለ ሁኔታ ያየሁት ድሮ ገጠር እናቴ አገር ሄጄ እረኞች ሲጫወቱ ነው። ይሄ ሰውዬ የፍጥነት መለኪያ ራዳር ይዟል። መኪኖች ለመንገዱ ከተወሰነው ፍጥነት በላይ ተጉዘው ሲያገኝ ደስታው ለጉድ ነው። "ቀቢ ቀቢ ድርርር" ይልና መሃል አስፋልት ውስጥ ሮጦ ገብቶ መኪና ያስቆማል። የትራፊክ ፖሊሱ ሁኔታ ሳትወዱ በግድ ያስቃል። የሆነ ሰርከስ ጨዋታ ውስጥ ያለ ይመስላል። ለሱ ነገሩ ጨዋታ ሆኖለታል። ለIsuzu ሾፌሮች ግን ትልቅ ቅጣት ነው። 1500 ብር ይቀጣቸዋል። አንዳንዱን ደግሞ ጓዱን ልኮ ትንሽ አውርተው ይሳሳቁና "ሳይቀጣው" ይለቀዋል። ያው ሁላችንም ነገሩ ይገባናል። እንዲያው ግን የመኪና ፍጥነት ምልክት የሚያስቀምጡትና እነዚህን ትራፊኮች የሚመድቡት ሰዎች ዓላማቸው ምን ይሆን? መኪና በፍጥነት እንዳይሄድ ካስፈለገ መንገዱ ላይ የፍጥነት መቀነሻ ማድረግ እንጂ የትራፊክ ራዳር መፍትሔ አይደለም። ለዚህ ማሳያው ደግሞ ሁሉም ሾፌር ከራዳር መለኪያው በኋላ ፍጥነቱን ጨምሮ እብስ ማለቱ ነው። ይህን ያየ አንዱ "ሰዉ ከራዳሩ በኋላ ፍጥነት ከጨመረ ታድያ የራዳሩ ጥቅም ምንድን ነው?" አለ። ሌላው ሲመልስ "ራዳሩማ የገንዘብ መብያ፣ የጉቦ ምንጭ እና ህዝብን ማሰቃያ ነው" አለ። እውነት ነው። ይህንን ማስተባበል አይቻልም። ⬇️⬇️
ኑ ደበበን እንዘክረዉ ! የመድረክ እና የፊልም ተዋናዩ ፤ የትያትር እና የመፅሀፍ ተርጓሚዉ ፤ የመድረክ ትያትር አዘጋጅ ደበበ እሸቱ የዚህን አለም ቆይታ አጠናቆ ከተለየን እነሆ አመት ሞላዉ። ህልፈተ አመቱን ምክንያት በማድረግ የፎቶ አዉደ ትይንት ፤ ተውኖባቸው ከነበሩት ገፀ ባህርያት ከናትናኤል ጠቢቡ ከእናት አለም ጠኑ ፤ ከቬንሱ ነጋዴ እና ከአዛዉንቶች ክበብ የተቀነጨበ ትርኢቶች ፤ግጥም እና ዘጋቢ ፊልም ይቀርባል። ኑ ደበበን ሰኞ ነሀሴ 11 በ11:00 ሰዓት በኢትዮጵያ ብሄራዊ ትያትር እንዘክረዉ ! ቤተሰቦቹና የሙያ ባልደረቦቹ ኑ ደበበን እንዘክረዉ ! የመድረክ እና የፊልም ተዋናዩ ፤ የትያትር እና የመፅሀፍ ተርጓሚዉ ፤ የመድረክ ትያትር አዘጋጅ ደበበ እሸቱ የዚህን አለም ቆይታ አጠናቆ ከተለየን እነሆ አመት ሞላዉ። ህልፈተ አመቱን ምክንያት በማድረግ የፎቶ አዉደ ትይንት ፤ ተውኖባቸው ከነበሩት ገፀ ባህርያት ከናትናኤል ጠቢቡ ከእናት አለም ጠኑ ፤ ከቬንሱ ነጋዴ እና ከአዛዉንቶች ክበብ የተቀነጨበ ትርኢቶች ፤ግጥም እና ዘጋቢ ፊልም ይቀርባል። ኑ ደበበን ሰኞ ነሀሴ 11 በ11:00 ሰዓት በኢትዮጵያ ብሄራዊ ትያትር እንዘክረዉ ! ቤተሰቦቹና የሙያ ባልደረቦቹ
видео или голосовое, без подписи
የኢትዮጵያ የባሕር ኃይል ዳግም ምሥረታ፡ ለህልውና እና ለሉዓላዊነት የተደረገ ታሪካዊ እርምጃ! ኢትዮጵያ በታሪኳ ከአፄ ካሌብ ዘመን ጀምሮ ቀይ ባሕርን በመቆጣጠር ጠንካራ የባሕር ኃይል የነበራት ሲሆን፤ በዘመናዊውም ታሪክ በ1947 ዓ.ም የተቋቋመውና በደርግ ዘመነ መንግሥት በአፍሪካ ስመ-ጥር የነበረው ኃይል በ1983 ዓ.ም በተፈጠረው የፖለቲካ ስህተትና የባሕር በር መክሰም ምክንያት እንዲፈርስ ተደርጎ ነበር። ይህ ውሳኔ ሀገራችንን ወደብ አልባ በማድረግ የገቢና ወጪ ንግዷን ከ90 በመቶ በላይ ለአደጋ ያጋለጠ ሲሆን፤ በቀይ ባሕር አካባቢ የሚታዩ የወንብድና፣ የሽብርተኝነትና የውጭ ኃይሎች ስጋቶች ጉዳዩን የቁጭት ብቻ ሳይሆን የህልውና ጥያቄ አድርጎታል። ይህንን ስልታዊ ክፍተት ለመሙላት በ2011 ዓ.ም በወጣው አዋጅ መሠረት የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል በቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ አመራር ዳግም ተቋቁሟል። በአሁኑ ወቅትም አባላቱን በናቪጌሽን፣ በኢንጂነሪንግ፣ በፈጣን ጀልባ ማሪን ኮማንዶዎችና ከውሃ በታች ዳይቨር ማሰልጠን የቻለ ሲሆን፤ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የብሪክስ የባሕር ላይ ወታደራዊ ልምምድ ላይ በመሳተፍ ዓለም አቀፍ ዝግጁነቱን በተግባር አሳይቷል። የባሕር ኃይሉን መልሶ ማደራጀትና ማዘመን የ130 ሚሊዮን ሕዝብን ኢኮኖሚያዊ ደህንነት ለመጠበቅና የሀገሪቱን ታሪካዊ ጥቅም ለማስከበር ወሳኝ አደራ ነው። ebc- የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas #Ethiopia #EthiopianNavy #RedSea #EthiopianDefense #Geopolitics #EastAfrica #NationalSecurity
ሀገሬ ቲቪ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን በነጻ ሊያስተላልፍ ነው ሀገሬ ቲቪ የዓለማችን ቁጥር አንድ ውድድር የሆነውን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ያለ ምንም ክፍያ በነጻ አየር ስርጭት (FTA) ለተመልካቾቹ እንደሚያቀርብ ይፋ አድርጓል። ይህ ታሪካዊ ስምምነት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የስፖርት አፍቃሪዎች በቤታቸው ሆነው ጨዋታዎችን ያለ ክፍያ እንዲከታተሉ የሚያስችል ነው። በዚህም መሰረት በየሳምንቱ ቅዳሜ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ የተመረጡ ቀጥታ ጨዋታዎች ይተላለፋሉ፤ እንዲሁም ሰኞ ምሽት ማጠቃለያ (Highlights)፣ እሮብ ምሽት ማራኪ ፕሮግራሞች እና አርብ ምሽት ጥልቅ የቅድመ-ጨዋታ ትንታኔዎች በሀገር ውስጥ ተንታኞች ይቀርባሉ። የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
видео или голосовое, без подписи
በ640 ሚ. ብር የተገነባው ግዙፍ የሶላር ኃይል ማመንጫ ተመረቀ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ቁንቢ ወረዳ በሚገኙት ሀሮሪ እና ሀሮ ጉራቲ ቀበሌዎች በ640 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነቡት ሁለት የሶላር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቀዋል። በውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴዔታ ኢንጂነር ሱልጣን ወሊን (ዶ/ር) እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች የተመረቁት እነዚህ የንፁህ ኢነርጂ ማመንጫዎች፣ የአካባቢውን ማህበረሰብ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ጥያቄ በዘላቂነት የሚመልሱ ናቸው ተብሏል። አጠቃላይ 850 ኪሎ ዋት የማመንጨት አቅም ያላቸው እነዚህ ፕሮጀክቶች 3 ሺህ 646 ለሚሆኑ አባዎራዎች አስተማማኝ የብርሃን ምንጭ በመሆን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ህይወታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ ይሆናሉ። የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas #Ethiopia #SolarEnergy #RenewableEnergy #CleanEnergy #Development
የአዲስ አድማስ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ ===== አዲስ አድማስ https://bit.ly/2V1zyZQ ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2V0I6jx ትዊተር↠ https://bit.ly/33fDhaP ቴሌግራም↠ https://bit.ly/2JgeCvG ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3q2hXiv
видео или голосовое, без подписи
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ «የመረጃ ሳምንት» ተጀመረ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2019 (2026/27) ትምህርት ዘመን የትምህርት ፕሮግራሞቹን የሚያስተዋውቅበት «የመረጃ ሳምንት» ከነሐሴ 8 እስከ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. በስድስት ኪሎ ዋና ግቢ ፎረም ሕንፃ መካሄድ ጀምሯል። መርሃ-ግብሩ በተለይም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ላጠናቀቁና ለድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የተዘጋጀ ሲሆን፣ ስለ ቅድመና ድህረ-ምረቃ የመግቢያ መስፈርቶች፣ የማመልከቻ ሂደቶች፣ የመግቢያ ፈተናዎች እና ስለ ስኮላርሺፕ (የመንግስት፣ የግልና ፕሬዝዳንታዊ) አማራጮች ሰፊ መረጃ የሚሰጥበት ነው። በዚህ ኤክስፖ ላይ የሚታደሙ ጎብኚዎች ከየኮሌጆቹ ከተወከሉ ባለሙያዎች ጋር በቀጥታ በመገናኘት የገፅ-ለገፅ ማብራሪያና የምክር አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ። «አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይማሩ፤ ሕልምዎን ያሳኩ!» በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው በዚህ መርሃ-ግብር ተማሪዎችና ወላጆች ወደ ስድስት ኪሎ ግቢ በመሔድ የወደፊት የትምህርት እድላቸውን የሚያመቻቹበትን መረጃ እንዲወስዱ ጥሪ ተላልፏል። የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas #AAU #አዲስአበባዩኒቨርሲቲ #የመረጃሳምንት #ትምህርት2019 #12ኛክፍል #AAUInfoWeek
ቻይና የዓለማችን ግዙፉን የኃይል ማመንጫ ግድብ መገንባት ጀመረች ቻይና በቲቤት በሚገኘው ያርሉንግ ጻንግፖ ወንዝ ላይ በዓለማችን ትልቁ የሆነውን የውኃ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ በመገንባት ላይ ትገኛለች። ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ እስከ 60,000 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም ይኖረዋል። ይህ የኃይል መጠን በአሁኑ ወቅት በዓለም ትልቁ ከሚባለው የቻይናው የሦስቱ ተሸለቆዎች (Three Gorges) ግድብ በሦስት እጥፍ ይበልጣል። ስለዚህ ግንባታው ሲያልቅ በዓለማችን ትልቁ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ይሆናል። ግድቡ የቻይናን የታዳሽ ኃይል አቅም በጣም የሚያሳድገው ቢሆንም፤ በአካባቢ ጥበቃ እና በወንዙ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ላይ ጉዳት ያደርሳል በሚል ሥጋት ፈጥሯል። የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas #ቻይና #ታዳሽኃይል #የዓለምትልቁግድብ #ChinaHydropower #MegaProject #GreenEnergy
ጋዜጠኞቹ ፍርድ ቤት የካዱትን የወንጀል ክስ እንዲያምኑ እየተገደዱ ነው -ሲፒጄ ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች (CPJ)፣ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በሽብር የተከሰሱ አምስት ጋዜጠኞች በይቅርታ ከእስር እንዲፈቱ በአማራ ክልል ለተፈጠረው ቀውስና ለጠፋው የሰው ሕይወት "ይቅርታ" እንዲጠይቁና "ኃላፊነት" እንዲወስዱ ግፊት እያደረጉ ነው ሲል ወቀሰ። ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፣ መስከረም አበራ፣ ገነት አስማማው፣ ዳዊት በጋሻው እና ዓባይ ዘውዱ "ራሳችንን ጥፋተኛ አድርገን የይቅርታ ደብዳቤ አንጽፍም" ማለታቸውን ቡድኑ ከጋዜጠኞቹ ጠበቃ መስማቱን ጠቁሟል። የሲፒጄ የአፍሪካ ኃላፊ ሙቶኪ ሙሞ፤ ጋዜጠኞቹ ፍርድ ቤት ውስጥ የካዱትን የወንጀል ክስ አሁን እንዲያምኑ ባለሥልጣናት እያስፈራሯቸው ነው ሲሉ ገልጸዋል። በመሆኑም የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ጋዜጠኞቹን ከማዋረድና እጃቸውን ከመጠምዘዝ እንዲቆጠቡ፣ እንዲሁም ክሱን እንዲያነሱና ከእስር እንዲለቋቸው ሲፒጄ ጥሪ አቅርቧል። የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
በአሜሪካ የቀረችው አትሌት ፃድቃን መኮንን የደረሰባትን ተናገረች በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ለመወዳደር ወደ አሜሪካ ያቀናችው አትሌት ፃድቃን መኮንን፤ አሜሪካ ከደረሰች በኋላ በሌላ አትሌት መተካቷና ከውድድር ውጪ መደረጓ እንደተነገራት ገልጻለች። በሂደቱም በሌላ ሰው ባጅ ስታዲየም እንድትገባ መደረጉና ጥያቄዎቿን የሚመልስ አካል ማጣቷ ውስጧን እንዳሳዘነው የገለጸች ሲሆን፣ ውሳኔውንም የወሰነችው ተገዳ እንደሆነ በተጎዳ መንፈስ ተናግራለች። አትሌቷ በመጨረሻም ከቡድኑ ጋር ቺካጎ ከገባች በኋላ ከስፖርት ቡድኑ በመለየት በአሜሪካ ለመቅረት ወስናለች። እንደ ኢትዮ ስፖርት ዘገባ፤ ከዚሁ ጉዞ ጋር ተያይዞ አትሌት ፃድቃን መኮንንን ጨምሮ ነጋሄ እያሱ፣ እመቤት ጥላሁን እና ነገሮ አዱኛን ጨምሮ በጠቅላላው 7 የቡድኑ አባላት በአሜሪካ ቀርተዋል። በአሁኑ ሰዓት እነዚህ አትሌቶችና የቡድኑ አባላት በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የመረጃ ምንጮችን ጠቅሶ ኢትዮ ስፖርት ዘግቧል። የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
видео или голосовое, без подписи
የቱሪዝም ሚኒስቴር ለሼፎች ልዩ ስልጠና መስጠት ጀመረ 🍽 የቱሪዝም ሚኒስቴር ከ"Resolve to Save Lives" ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ለሚገኙ ባለኮከብ ሆቴሎች የምግብ ዝግጅት ባለሙያዎች (ሼፎች) የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል። ስልጠናው በጤናማ የአመጋገብ ዘይቤ፣ በጥራት አሰጣጥ፣ በምግብ ዝግጅት ቁጥጥር እና በኩሽና ንፅህና አደረጃጀት ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ ሆቴሎች ለአለም አቀፍና አህጉር አቀፍ እንግዶች ጥራቱን የጠበቀና አስተማማኝ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ያለመ እንደሆነ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ብቃት ማረጋገጫ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ታሪኩ ደምሴ ገልፀዋል። የ"Resolve to Save Lives" ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ ግርማ አሰፋ በበኩላቸው፣ ተቋማቸው ጤናማ የአመጋገብ ስርዓትን በማስረፅ ረገድ ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ጥናቶችን እንደሚያካሂድ እና ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎችን እንደሚሰራ አስረድተዋል። አክለውም ይህ ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር የተጀመረው የምግብ አብሳይ ባለሙያዎች ስልጠና በቀጣይነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas #ቱሪዝምሚኒስቴር #አዲስአበባ #ጤናማአመጋገብ #ሆቴሎች #EthiopianTourism #ResolveToSaveLives