Comparative Religion
Статистика{እዚሁ ውስጥ ያላችሁ ክርስቲያን ወገኖቻችን በእስልምና ዙሪያ ጥያቄ ካላችሁ,መስለም ከፈለጋችሁ እና በተጨማሪ ነፃ የምክር አገልግሎት ከፈለጋችሁ በውስጥ መስመር ጥቆማ መስጣት ትችላላችሁ ።} @AMDALA6_BOT
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 4
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 196
- 1/48двое суток
- 224
- 1/72трое суток
- 242
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የሰው ልጅ በተፈጥሮው ስሜታዊ ፍጡር ነው። በዘመናዊው የሥነ-ልቦና እና የፊዚዮሎጂ ሳይንስ እንደተረጋገጠው፣ በአካል መነካካት በሰውነታችን ውስጥ እንደ "ኦክሲቶሲን" እና "ዶፓሚን" ያሉ የቅርበት እና የስሜት መነሳሳትን የሚፈጥሩ ሆርሞኖች እንዲመረቱ ያደርጋል። ንክኪ በሁለት ሰዎች መካከል ያለውን ሥነ-ልቦናዊ የርቀት ግድግዳ የማፍረስ ከፍተኛ ኃይል አለው። እስልምና ይህንን የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ዝንባሌ (ፍትወተ-ሥጋ) በሚገባ ያውቃል። በመሆኑም ሎጂኩ እጅግ ግልጽ ነው፦ "አንድን አደጋ ለመከላከል፣ ወደ አደጋው የሚያደርሱትን መንገዶች በሙሉ መዝጋት ያስፈልጋል።" አንድ ሰው በሚያዳልጥ ጭቃ ላይ እየተንሸራተተ "አልወድቅም" ብሎ ማሰብ እንደማይችለው ሁሉ፣ የሰውን ልጅ ከተፈጥሯዊ ስሜቱ ጋር እያጋጩ "በንጹህ ልብ ከተደረገ ችግር የለውም" ማለት ምክንያታዊነት የጎደለው የዋህነት ነው። ለዚህም ነው እስልምና መጨባበጥን እንደ አንድ የዝሙት መግቢያ በመቁጠር አስቀድሞ በር የሚዘጋው። መጽሀፍ ቅዱስ በማቴዎስ ወንጌል፣ ምዕራፍ 5፣ ቁጥር 28 ፦ "ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል"። ይላል። እዚህ ላይ አንድ መሠረታዊ ጥያቄ እናንሳ፤ መጽሐፍ ቅዱስ "ማየት" ብቻውን የልብን ንጽህና አጉድፎ ወደ "ልብ ዝሙት" ያደርሳል ብሎ ካመነ፣ ከእይታ በበለጠ እጅግ ጠንካራ ስሜትን የሚቀሰቅሰው "አካላዊ ንክኪ (መጨባበጥ)" እንዴት "በንጹህ ልብ" በሚል ሰበብ ችላ ሊባል ይችላል? እይታ ኃጢአት ከሆነ፣ መነካካት በሎጂክ ደረጃ የከፋ ነው። አላህ የሰው ልጅን የፈጠረ ጌታ እንደመሆኑ፣ ለሰው ልጅ የቱ እንደሚበጀው አስቀድሞ በማወቅ መከላከያ አጥርን አበጅቶለታል። እስልምና እጅግ ተግባራዊ (Practical) የሆነ ዲን ነው። በሽታው ከመጣ በኋላ መድኃኒት ከመፈለግ፣ በሽታው የሚመጣበትን መንገድ አስቀድሞ ማድረቅን የሚመርጥ መለኮታዊ ሀይማኖት ነው። © የሕያ ኢብኑ ኑህ t.me/comparativeRelgion
видео или голосовое, без подписи
በእለተ ማክሰኞ በቀን 05/12/2018 ከጡዋቱ 11:45-50 አካባቢ ላይ የእናቴ እናት አያቴ በሞት ተለዩኝ። በዱዓችሁ አስታውሱዋቸው። 📗ወንድም አምዳላ ናሲር
የወንዱ ጾታ በ XY ክሮሞሶሞች የሚገለጽ ሲሆን፣ የሴቷ ጾታ ደግሞ በ XX ክሮሞሶሞች ይገለጻል። የወንድ እና የሴት ዘር ሴሎች በሚፈጠሩበት ጊዜ፣ የወንዱ XY ክሮሞሶሞች ተለያይተው X ወይም Y ክሮሞሶም የያዙ የወንድ ዘሮችን ያመርታሉ። የሴቷ XX ክሮሞሶሞች ደግሞ ሁልጊዜ X ክሮሞሶም የያዙ የእንቁላል ሴሎችን ያመርታሉ። ፅንስ በሚፈጠርበት ጊዜ የወንዱ ዘር ከሴቷ እንቁላል ጋር ሲዋሃድ፣ የፅንሱን ጾታ የሚወስነው የወንዱ ዘር የሚይዘው ክሮሞሶም ነው። • ከወንዱ ዘር X ክሮሞሶም ከመጣ፣ ከሴቷም X ክሮሞሶም ጋር በመዋሃድ XX (ሴት) ፅንስ ይፈጠራል። • ከወንዱ ዘር Y ክሮሞሶም ከመጣ ግን፣ ከሴቷ X ክሮሞሶም ጋር በመዋሃድ XY (ወንድ) ፅንስ ይፈጠራል። ቁርአን በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ይል ይሁን? በዚህ ርዕስ ሰፊ ትምህርት ለቀናል ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ያንብቡ ለሌሎችም በማስነበብ የሕዳያ ሰበብ ይሁኑ። -------------------------------------------- የጾታ ውሳኔ በጄኔቲክስና በቁርአን 📗ወንድም አምዳላ ናሲር
አንድ ቀን አንድ ሰው ከባድ የጨው ሸክም ተሸክሞ ወደ ገበያ ይሄድ ነበር። መንገዱ አሰልቺና ሸክሙም በጣም ከባድ ስለነበር ሰውየው በብርቱ ደክሞታል። በመንገዱ ላይ አንድ ወንዝ ሲሻገር ድንገት እግሩ አንሸራቶት ወንዙ ውስጥ ወደቀ። ሰውየው ከወንዙ ውስጥ ተነስተው እስኪወጣ ድረስ ተሸክሞት የነበረው ጨው በውሃው ውስጥ ስለቀለጠለት፣ ሲነሳ ሸክሙ በጣም ቀሎት አገኘው። በዚህም ተደስቶ መንገዱን ቀጠለ። እየሄደ ሳለ፣ ሌላ ሰው ጉልህ የሆነ የጥጥ ሸክም ተሸክሞ ሲመጣ ተመለከተ። ጥጡ መጠኑ ትልቅ ስለነበር ጨው ተሸካሚው ሰውዬ «በጣም ከብዶታል» ብሎ አሰበ። በመሆኑም ለራሱ የሆነለትን በማሰብ፦ «ወንድሜ! ሸክምህ ከብዶህ ከሆነ እዚያ ወንዝ ውስጥ ገብተህ ውጣ፤ ሸክምህ ይቃለልሃል» ሲል መከረው። ጥጥ ተሸካሚውም የቀረበለትን ምክር ሳያመዛዝን አምኖ ወደ ወንዙ በመግባት ጥጡን ውሃ ውስጥ ዘፈቀው። ነገር ግን ጥጡ ውሃውን በከፍተኛ ሁኔታ ስለሳበ አብጦ ከመቀለል ይልቅ ከመጀመሪያው እጥፍ ድርብ ከበደው። ጥጥ ተሸካሚውም ሸክሙን መሸከም አቅቶት በብርቱ ተቸገረ። ለአንድ ሰው ወይም ለአንድ ሁኔታ የሰራ መፍትሔ ለሌላው ይሰራል ማለት አይደለም። ጨው በውሃ ስለሚቀልል ሸክሙ ይቃለላል፤ ጥጥ ግን ውሃ ስለሚስብ ይከብዳል። ስለዚህ የማንኛውንም ነገር ወይም ችግር ተፈጥሮና ባህሪ አስቀድሞ መረዳት ያስፈልጋል። የሰዎችን ምክር ከመቀበላችን ወይም ከመተግበራችን በፊት ከራሳችን ሁኔታ ጋር ይሄዳል ወይስ አይሄድም ብለን ማሰብና መመርመር አለብን። 📕ወንድም አምዳላ ናሲር t.me/comparativeRelgion
видео или голосовое, без подписи
ይሄንን የቁርአን አንቀፅ ነጥብ በነጥብ አንናያለን። በዚህ የቁርአን አንቀፅ ላይ የሚነሱ ካለ መረዳት ችግር«Misunderstand» ወይም ለእስልምና ጭፍን ጥላቻ «Islamophobia» ላይ ተንተርሰው ሚሽነሪዎች የሚያነሱዋቸው ሙግቶች በpdf እንዳስሳለን። በቅርብ ቀን በ "pdf" 📕ወንድም አምዳላ ናሲር
እነዚህን pdf ተጭናችሁ አንብቡ ለሌሎችም አስነብቡ። ➔ በወንጌል ፍረዱ pdf! ➔ ከእረሱ በሆነ ቃል pdf! ➔ በጀነት ጠጅ አለን pdf? ➔ የነብያት ሀይማኖት pdf 📕ወንድም አምዳላ ናሲር
መህዲ ማን ነው? ‹‹መህዲ›› በመጨረሻው ዘመን ከደጃልና ዒሳ መምጣት አስቀድሞ የሚነሳ ታላቅ ‹‹ኸሊፋ›› ነው። ‹‹መህዲ›› የማዕረግ ስሙ ሲሆን ‹‹ሁዳ›› ከሚለው ቃል የተገኘና ‹‹የተመራ ቅን ኸሊፋ›› ማለት ነው። መጠሪያ ሙሉ ስሙ ደግሞ ‹‹ሙሐመድ ኢብን አብዱላህ አል-መህዲ›› ነው። ስለ መህዲ በቁርኣን የተነገረ ምንም ነገር አናገኝም። መረጃዎቹ በሙሉ ከሐዲስ የተገኙ ሲሆን ከሃያ በላይ የተረጋገጡ…
መህዲ ማን ነው? ‹‹መህዲ›› በመጨረሻው ዘመን ከደጃልና ዒሳ መምጣት አስቀድሞ የሚነሳ ታላቅ ‹‹ኸሊፋ›› ነው። ‹‹መህዲ›› የማዕረግ ስሙ ሲሆን ‹‹ሁዳ›› ከሚለው ቃል የተገኘና ‹‹የተመራ ቅን ኸሊፋ›› ማለት ነው። መጠሪያ ሙሉ ስሙ ደግሞ ‹‹ሙሐመድ ኢብን አብዱላህ አል-መህዲ›› ነው። ስለ መህዲ በቁርኣን የተነገረ ምንም ነገር አናገኝም። መረጃዎቹ በሙሉ ከሐዲስ የተገኙ ሲሆን ከሃያ በላይ የተረጋገጡ ዘገባዎች ይገኛሉ። ብዙ የሱንና ዑለማዎች ስለ መህዲ የፃፉ ሲሆን ቲርሚዚና አቡ-ዳውድ ራሱን የቻለ ምዕራፍ ሰጥተውታል። ከሁሉም ታዋቂው ሐዲስ አቡ-ዳውድ የዘገቡት ሲሆን ነቢዩ (ዐሰወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ትንሳኤ ሊቆም አንድ ቀን ቢቀረው እንኳን አላህ ከቤተሰቤ የሆነን፤ ስሙ ከእኔና ከአባቴ ጋር የሚመሳሰል መሪን ሳያስነሳና በበደል የተዋጠችውን ምድር በፍትህ ሳይሞላት አይተዋትም።›› (አቡ-ዳውድ 4282) ከዚህ ሐዲስ እንደምንረዳው መህዲ የነቢዩ (ዐሰወ) ቤተሰብ ነው። ስሙም የነቢዩን (ዐሰወ) እና አባታቸውን የያዘ ሲሆን ‹‹ሙሐመድ ኢብን አብዱላህ›› ወይም ‹‹አህመድ ኢብን አብዱላህ›› ነው። የሚመጣውም ዓለም በዙልም በተዋጠችበት በመጨረሻው ዘመን ሲሆን የአላህን ቃል ከፍ በማድረግ ፍትህን ያነግሳል። ኡሙ ሰላማ (ረዐ) እንደተናገረችው ነቢዩ (ዐሰወ) ‹‹መህዲ በፋጡማ በኩል የሚገኝ ቤተሰቤ ነው።›› ብለዋል። ኢብኑል ቀይም ይሄንን ሐዲስ ሲያብራሩ ‹‹መህዲ የሐሰን ዘር ሲሆን አል-ሐሰን ለሙስሊሙ አንድነት ሲሉ ኸሊፋነታቸውን አሳልፈው በመስጠታቸው ምክንያት አላህም በመጨረሻው ዘመን ከቤተሰባቸው ታላቅ ኸሊፋ በማስነሳት ክሷቸዋል።›› ሲሉ ፅፈዋል። (አቡ-ዳወድ 11/373) አቡ-ሰዓድ አልኩድሪ በዘገቡት ሐዲስ ነቢዩ (ዐሰወ) ስለ መህዲ ገፅታ ሲናገሩ ‹‹ቁመቱ ረጂም፣ ትከሻው ሰፊ፣ አፍንጫው አጠፍ ያለ ነው።›› ብለዋል። (አቡ-ዳውድ 4265) መህዲ የሚነሳበትን ቦታ በተመለከተ የተለያዩ ዘገባዎች አሉ። ከፊሎቹ ከሻም ከፊሉ ከኹራሳን ሌላው ደግሞ ከመዲና እንደሆነ ይናገራሉ። ኢብን ከሲር የሁሉንም ሐዲሶች ጥቅል ሀሳብ ሲያስቀምጡ ‹‹የሚነሳው ከምስራቅ ነው። ከዚያም ወደ መካ ይሄዳል። ሰዎችም በከዓባ ዙሪያ ቃልኪዳን ይገቡለታል።›› ብለዋል። እንዲሁም በሌላ መጽሐፋቸው ‹‹በሐዲስ በተጠቀሰው መሰረት ባንዲራው ጥቁር ነው።›› በማለት አብራርተዋል። (አልቢዳያህ ወልኒያህ 19/63፤ አልፊታን ወልመላሂም 1/49) ኢማም አህመድ እንደዘገቡት መህዲ መሪነት ሲመረጥ ፍላጎቱም ክህሎቱም አልነበረውም። እናም ‹‹አላህ በአንድ ሌሊት ይመራዋል።›› ብለዋል (ዐሰወ)። ኢብን ከሲር ሐዲሱን ሲያብራሩ፡- ‹‹ይህ ማለት አላህ ይረዳዋል፣ ከዚህ በፊት ያልነበረውን ችሎታም ይሰጠዋል ማለት ነው።›› ብለዋል። (አህመድ 2/58/ አልፊታን ወልመላሂም 1/29) መህዲ ኸሊፋነትን ከተረከበ በኋላ ሙስሊም አገራትን በአንድ በማፅናት በቀደመው ኢስላማዊ አስተዳደር ስር ያስገባቸዋል። ከዚያም በቡኻሪ እና ሙስሊም (2897) እንደተዘገበው ከሮማውያን ጋር የመጨረሻው ታላቁ ጦርነት ‹‹አል-መልሃማ አል-ኩብራ›› ይካሄዳል። ሙስሊሞችም ዳቢቅ ላይ ድል ደርጋሉ። ከዚህ በፊት ያልተከፈቱ አገራትንም ይከፍታሉ። ከዚያ በኋላ ሙስሊሞች በየትኛውም ኃይል አይሸነፉም። አላህ አማኞችን ከፍተኛ የሀብት መትረፍረፍ ይባርካቸዋል። ሸይህ ዑመር ሱለይማን አል-አሽቀር ሐዲሱን መሰረት በማድረግ እንደተናገሩት ‹‹ይህ ጦርነት ከባድ ውድመትን ስለሚያስከትል ዓለም አሁን ካለችው ስልጣኔ ወደኋላ በመመለስ እንደ ጥንቱ በጦር በጋሻ በፈረስ መጠቀም ይጀምራሉ።›› ብለዋል። (አል-ቂያማህ አስ-ሱግራ 275) መህዲ ታላቅ ጦርነት አድርጎ ሙስሊሞችን የበላይ ቢያደርግም ጊዜው የቂያማህ ቀን መቃረቢያ በመሆኑ ከባባዶቹ ፊትናዎች ይከሰታሉ። ከእነዚህም መካከል ቀዳሚው የደጃል መነሳት ነው። እሱን ተከትለው የዕጁጅና መዕጁጆች ከጉድጓዳቸው ይወጣሉ። በዚህ ጊዜ አላህ ዒሳን (ዐሰ) ለእርዳታ ይልከዋል። በሐዲስ እንደተጠቀሰው ዒሳ (ዐሰ) ወደ ምድር የሚወርደው በፈጅር ሰላት ወቅት ነው። ነቢዩ (ዐሰወ) ስናገሩ ‹‹መህዲ ዒሳን አሰግደን ይለዋል። ዒሳም እናንተ መሪዎች መሆናችሁ ከቂያማህ ምልክቱ ነውና አንተ አሰግደን ይለዋል። ዒሳም ከመህዲ ኋላ ተከትሎ ይሰግዳል።›› ብለዋል። (ሙስሊም 225) ከዚያ በኋላ ዒሳ ከሙስሊሞች ጋር በመሆን የዕጁጆችንና ደጃልን በመጋደል በአላህ ዕርዳታ ያጠፋቸዋል። ነቢዩ (ዐሰወ) እንደተናገሩት ‹‹ሙስሊሞች ለሰባት ዓመታት ያህል የየዕጁጆችን አጥንት ቀስትና ጋሻ ለማገዶነት ይጠቀሙበታል። መህዲ በኸሊፋነት የሚቆይባቸው ዓመታት ‹‹ሰባት›› እንደሆኑ አብዛኛዎቹ የሐዲስ ምሁራን ይናገራሉ። ከእነሱ መካከል አንዱ የኢብኑ ማጃህ ሲሆኑ ነቢዩ (ዐሰወ) ‹‹መህዲ ሰባት አጭር ጊዜያትን ይቆያል።›› ማለታቸውን ዘግበዋል። (ኢብን ማጃህ 4039)© ሰልማን t.me/comparativeRelgion t.me/comparativeRelgion
ወንድም ለወንድሙ ልክ እንደ መስታወት ነው። ይሁን እንጂ መስታወቱ ፊትህ ላይ ያለብህን ቆሻሻ ሲያሳይህ "አይ መስታወቱ ነው የተሳሳተው እንጂ ፊቴ ምንም የለበትም"። ካልክ የመስታወት መቀያያር ለውጥ አያመጣም። ለዚህ ሀሳብ የሚያደርገን አንድ ትልቅ በሽታ "ተከቡር" ነው።ተከቡር ማለት "እኔ አዋቂ ነኝ። ከእኔ በላይ የለም።" ማለት ነው። የመጀመሪያው ኩራት የታየው በኢብሊስ (ሰይጣን) ላይ ነው። ለአዳም እንዲሰግድ በታዘዘ ጊዜ "እኔ ከእሱ እበልጣለሁ፤ እኔን ከእሳት ፈጠርከኝ እሱን ግን ከጭቃ ፈጠርከው" በማለት በኩራት እምቢ አለ። ስለዚህ ኩራት የሰይጣን ባህሪ ነው። አብረሃቸው በደዕዋ ዘርፍ በተለይም በንፅፅር እየተንቀሳቀስክ ያለሃቸውን ወንድሞች ላጠፋሀው ጥፋት እና ስህተት በምክንያታዊነት ስነገርህ "አይ ጥፋት የለብኝም" ማለት መስታወቱ ያሳይኝ የነበረው ቆሻሻ ቆሻሻ አይደለም ብሎ እነደመከራከር ነው። ይህ በእስልምና "ተከቡር" تكبر ይባላል። ይህ በሽታ ስጠራቀም "ጥላቻን ይወልዳል" የሚባለው ለዛ ነው። "الکبر يورث البغض" ወላሂ ስም መጥቀስ ስላልፈለኩኝ እንጂ በስመ ንፅፅር ውስጥ ሆነን ይሄንን አረማመድ የምናራምድ ወንድሞች ልንቆጠብ ይገባል። ስህተትህን የሚያርሙ ወንድሞች ላይ በምክንያታዊነት መሟገት እያለብህ ከነ ጭራሹም "እኔ ብቻ ልክ ነኝ" ብሎ በ block መሸኘት የጅህልና አስተሳሰብ ነው። ኢማሙ ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ ላይ ነብዩ እንዲህ ይላሉ ፦ «الْكِبْرُ بَطَرُ الْحَقِّ، وَغَمْطُ النَّاسِ» "ትዕቢት ማለት እውነትን መቃወም (አለመቀበል) እና ሰዎችን መናቅ (ማሳነስ) ነው።" ለዚህ አይነት አመለካከት ግን ተከታዮቹን ሁለት የነብዩን ሀዲስ ማስታወስ በቂ ነበር። «لَا يَدْخُلُ الْجَنَّةَ مَنْ كَانَ فِي قَلْبِهِ مِثْقَالُ ذَرَّةٍ مِنْ كِبْرٍ» "በልቡ ውስጥ የብናኝ ያህል ኩራት (ትዕቢት) ያለበት ሰው ጀነት (ገነት) አይገባም"። «أَلَا أُخْبِرُكُمْ بِأَهْلِ النَّارِ؟ كُلُّ عُتُلٍّ جَوَّاظٍ مُسْتَكْبِرٍ» (رواه البخاري ومسلم) «የጀሀነምን ሰዎች ልንገራችሁን? እነርሱም፡ ጨካኝ፣ ስግብግብ እና ትዕቢተኛ (እብሪተኛ) የሆኑት ናቸው።» (ቡኻሪና ሙስሊም) ማጠቃለያ እነዚህ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አስተምህሮቶች እንደሚያሳዩት «تكبر» (ትዕቢት) የአላህን ቁጣ የሚያስከትል፣ ሰውን ወደ ጀሀነም የሚነዳ እና በዱንያም በአኼራም ውርደትን የሚያከናንብ መጥፎ ተግባር ነው። የዚህ ተቃራኒ የሆነው «ተዋዱዕ» (ትሕትና) ደግሞ ሰውን ከፍ የሚያደርግና የጀነት የሚያደርግ የተወደደ ባህሪ ነው። ስለዚህ ሀቅ እንደ ሀቅነቱ ከማንም ይምጣ ሀቅ ነው። የመቀበልም ግዴታ አለብን። አይ "እኔ ብቻ ልክ ነኝ" ብሎ በ block መሸኘት የጅህልና አስተሳሰብ ነው። ይሄንን ለመፃፍ የተገደድኩት በንፅፅር ስም ውስጥ በወንድሞች መካከል "እኔ ካለሁኝ እኔን አዳምጡ ማውራትም ይሁን መፃፍ አይቻል" የሚል አመለካከት ያለው እና ራሱን እንደ አዋቂ ሌሎችን ደሞ ጃሂል አድርጎ በሚያስብ ግለሰብ ነው።ይሁን አንጂ መልዕክቱ ለሁሉም ነው።በውስጥ አንዳይመከር በ "block" ስለተሸኜሁኝ ነው። 📕ወንድም አምዳላ ናሲር t.me/comparativeRelgion
ተጭናችሁ አንብቡ ለሌሎችም አስነብቡ። ➔ ነብዩ ﷺ ማን ናቸው?⁴ ➔ ነብዩ ﷺ ማን ናቸው?³ ➔ ነብዩ ﷺ ማን ናቸው?² ➔ ነብዩ ﷺ ማን ናቸው?¹ ➔ ቁርአን እና ሳይንስ³ ➔ ቁርአን እና ሳይንስ² ➔ ቁርአን እና ሳይንስ¹ 📕ወንድም አምዳላ ናሲር t.me/comparativeRelgion
አረቦች እንዲህ ይላሉ። " الصمت أبلغ من الكلام " «አንዳንዴ ዝምታ ከንግግር ይበልጣል» " الصمت زينة للعالم وستر للجاهل" ዝምታ የጥበበኛ ሰው ጌጥ፣ የሰነፍ ሰው ደግሞ መከለያ (መሸሸጊያ) ነው። ስለዚህ በነገሮች ላይ ፊትናን ላለመጫር እስከ ግዜው ዝምታን መርጠናል። 📕ወንድም አምዳላ ናሲር t.me/comparativeRelgion
በንፅፅር ዘርፍ ጥያቄ ላለችሁ እና መሰራት አለበት የምትሉዋቸውን ጥያቄዎች ካሉ አንድ ሰዎ እስከ አምስት ጥያቄዎችን የሚያቀርብበት ሁኔታ ተመቻችቷል። ስለሆነም ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ(link) ነክታችሁ አጠር እና ግልፅ በሆነ መልኩ ጥያቄያቹሁን በቀረቡ ተረቁጥሮች ላይ ማቅረብ ትችላላችሁ። ከጥያቄዎቹ መሃል ወሳኝ ወሳኞችን መርጠን ከተለያዩ ኡስታዞች ጋር በመሆን ምላሽ እንሰጥባቸዋለን። https://forms.gle/aUdcqJAcLuJDZmNv6 ጥያቄ አለኝ ለሚል ሁሉ ፎርሙን ያዳርሱ።
ለአንዳንድ ሰዎች ለትችታቸው እና ለቅጥፈታቸው መልስ መስጣት በራሱ እነሱን ማስተዋወቅ ነው። አንድ የቤተክርስቲያን መምህር መምህር በትረ ማርያም አበባው በፌስቡክ ገፁ ላይ የሚከተለውን ንግግር ተናግሮ ነበር፦ «ለእግዚአብሔር እንደሰው የተወሰነ፣ የተከፋፈለ፣ ቅርጽ ያለው አካል የለውም አልን እንጂ አካል የለውም አላልንም። ያ አካሉ ደግሞ ድንቡልቡል ነው አንልም። ያ በምልአት ያለው አካል ወሰን የሌለበት ዓይን፣ እጅ፣ እግር አለው። ሃይማኖተ አበው የሚገልጽልን ይህንን ነው። ዐይኑ ከሆነ ቦታ፣ እጁ ከሆነ ቦታ፣ እግሩ ከሆነ ቦታ ተከፋፍሎ አለ ማለት ግን ክሕደት ይሆናል። ዐይኑ ካለበት ቦታ ሁሉ እጁ እግሩ አለ። አንዱ ኖሮ ሌላው የሌለበት ቦታ የለም። ይህንን ካልን መከፋፈል፣ ቅርጽ ማውጣት ውስጥ መግባት ነውና። ይህ ደግሞ አእምሯችን የፈጠረው እንጂ ለእግዚአብሔር አይነገርም። ዐይን፣ እጅ፣ እግር፣...ወዘተ እንዳለው እናምናለን። ዐይኑ፣ እጁ፣ እግሩ፣...ግን የተከፋፈለ፣ ቅርጽ ያለው፣ የተወሰነ ነው አንልም» ይሄንን ያነበቡ አንዳንድ ተሳዳቢዎች እና አላዋቂዎች(ስማቸውን መጥቀስ ስለመያስፈልግ ነው) ምላሽ በሚል ይሄንን ፅፈው አገኜሁት፦ «ለሥላሴ የክፍል አካላት የሚሰጡ አንዳንድ መምህራን መኖራቸው ሲያስገርመን የነበረ ቢሆንም ጭራሽ ጾታ አላቸው የሚሉ... በመስማታችን አስደንግጦናል» ይሄንን ንግግሩ ይዘው የኛ የንፅፅር ወንድሞች እና እህቶች ከቴሌግራም ገፁ ላይ አንዳለ screenshot አድርገው የቻናሉን ስም ሰያጠፉ በተለያዩ የሚድያ ገፆች ላይ ስበትኑት የእሱ የቻናሉ ተከታይ(subscribe) 6,117 ነበር። ከተበተነ በሁለት እና በሥስት ቀን ውስጥ ግን 7,841 ደረሰ። ስለዚህ ምን ለማለት ፈልገህ ነው? ካላችሁኝ የተኛውም ሰው ስህተት ቢናገር እና ቢቀጥፍ ለእሱ መልስ በተሰጠው ቁጥር በሌላ መንገድ ማስታወቂያ(promotion) እየተሰራለት መሆኑን አውቀን ቢያንስ ቻናሉ ላይ ያለውን የቴሌግራም ስም ማጥፈ አለብን። አላዋቂዎች በተሰየመው የቴሌግራም ቻናል ስም እየፈለጉ(search) አድረገው የሚገቡ ብዙዎች አሉ። የእነሱ መግባት ግን እሱን ያበረታታዋል። ማጠቃለያ ይህ መልዕክት በዋናነት ንፅፅር ላይ ያለን ወንድም እና እህቶች ብሆንም በተጨማሪም የኢስላም ዳዒዎች አንድን ሙብተዲዕ ሙብተዲዕነቱን ስታስጠነቅቁ በሌላ መንገድ ለእሱ ማስታወቂያ(promotion) እያደረጋችሁ እንደሆነ ተገንዝባችሁ ለቀጠፈው ቅጥፈት ሀሳቡን እና የቀጠፈውን ደሞ ከገፁ ላይ እንደ ማስረጃነት ስታቀርቡ ቢያንስ የቻናሉን ስም እጥፍታችሁ ብሆን ይመረጣል።ይህ መልዕክት የግል አመለካከቴ እንደመሆኑ መጠን ተጠያቂውም እኔ ነኝ። 📕ወንድም አምዳላ ናሲር t.me/comparativeRelgion
❝ጳውሎስ ማን ነው? በሚል ከክፍል አንድ እስከ ክፍል ሥድስት ተዳስሷል ተጭነው ያንብቡ ለሌሎችም በማስነበብ የሕዳያ ሠበብ ይሁኑ❞ ~ ጳውሎስ ማን ነው ¹ ? ~ ጳውሎስ ማን ነው ² ? ~ ጳውሎስ ማን ነው ³ ? ~ ጳውሎስ ማን ነው ⁴ ? ~ ጳውሎስ ማን ነው ⁵ ? ~ ጳውሎስ ማን ነው ⁶ ? 📕ወንድም አምዳላ ናሲር
የቁርኣን አንጸባራቂ ቃላት "በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡" (بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ) (ቁርኣን 1፡1) "ቢስሚላህ" በመጠኑ አጭር ቢመስልም፣ በውስጡ እጅግ ሰፊ ትርጉምን እና ጥልቅ የቋንቋ አወቃቀርን ያዘለ መለኮታዊ ቃል ነው። ይህችን አንቀጽ በቋንቋ፣ በታሪክ እና በተፍሲር መነጽር የተደረጉ እይታዎችን ስንመለከት አእምሮን የሚያስደምም ጥበብ እናገኛለን። በዓረብኛ ሰዋስው "ቢ" (بِ) የሚለው ፊደል መስተዋድድ ነው። በቋንቋው ህግ መሰረት፣ ማንኛውም መስተዋድድ ከእርሱ በፊት ወይም በኋላ የሚመጣ "አድራጊ ግስ" ያስፈልገዋል። ነገር ግን ቁርኣን "በአላህ ስም..." አለ እንጂ፣ በአላህ ስም ምን እንደምናደርግ (እበላለሁ፣ አነባለሁ፣ እጓዛለሁ) የሚለውን ግስ አልገለጸም። ይህ ለምን ሆነ? የተፍሲር ሊቃውንት ይህንን ሲያብራሩ፤ ግሱ ሆን ተብሎ የተደበቀው ቃሉ ለሁሉም ሁኔታዎች አገልጋይ እንዲሆን ነው ይላሉ። አንባቢው የሚያደርገውን ማንኛውንም በጎ ተግባር በዚያ ባዶ ቦታ ላይ መሙላት ይችላል። በተጨማሪም፣ ሐሳቡን ቀጥታ በ"አላህ ስም" በማስጀመር ሌላ ማንኛውም ነገር ከእርሱ ስም እንዳይቀድም እና በረካው ሙሉ እንዲሆን የተደረገበት እጅግ ውብ የቋንቋ ስልት ነው። በአንቀጹ ውስጥ ሶስት ታላላቅ የአላህ ስሞች በተከታታይ መጥተዋል፦ አላህ፣ በመቀጠል አር-ረሕማን፣ ከዚያም አር-ረሒም። ይህ ቅደም ተከተል ድንገተኛ አይደለም። • መጀመሪያ "አላህ" (اللَّه) የሚለው የባህሪያቱ ሁሉ ሰብሳቢ የሆነው እና የፈጣሪነት ምንነቱ ተገለጸ። • ቀጥሎ "አር-ረሕማን" (الرَّحْمَٰن) የሚለው፣ አላህ ለፍጡራኑ ሁሉ ያካተተውን እጅግ ሰፊ እና አጠቃላይ የሆነውን እዝነቱን የሚያሳየው ስም መጣ። • በመጨረሻም "አር-ረሒም" (الرَّحِيم) የሚለው፣ አላህ በተለየ ሁኔታ ዘላቂ፣ ቀጣይነት ያለው እና ለምእመናን የሚያደርገውን ልዩ እዝነት የሚያሳየው ስም ተከተለ። ይህ ከጠቅላላው ወደ ዝርዝሩ፣ ከሰፊው ወደ ቋሚው የሚሄድ ማራኪ የቋንቋ አገላለጽን ይፈጥራል። ቁርኣን "ቢስሚላህ"ን ሲገልጽ አዲስ ቃል ተፈጥሮ ሳይሆን፣ ከእርሱ በፊት በነበሩት ነቢያት ሲወርድ የነበረውን መለኮታዊ እውነት ማረጋገጡን እናያለን። • ነቢዩ ኑህ (ዐ.ሰ) መርከቢቱን ሲያሽከረክሩ፦ "መሄዷም መቆሟም በአላህ ስም ነው..." (بِسْمِ اللَّهِ مَجْرَاهَا) (ቁርኣን 11፡41) በማለት ተጠቅመውታል። • ነቢዩ ሱለይማንም ለንግስት ቢልቂስ በላኩት ደብዳቤ ላይ፦ "እርሱም በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡... (بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ)" (ቁርኣን 27፡30) በማለት ጀምረዋል። ከዚህም ባሻገር፣ ዕብራይስጥ፣ አራማይክ እና ዓረብኛ ሁሉም የሴማዊ ቋንቋ ቤተሰቦች ናቸው። ‹ር-ሕ-ም› (ر ح م) የሚለው የስርወ-ቃል በነዚህ ሁሉ ቋንቋዎች ውስጥ ለፈጣሪ እዝነት መግለጫነት ያገለግላል። ይህም ይህ ቃል በነቢዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) እና በሌሎችም ነቢያት በኩል ሲወራረስ የመጣ ጥንታዊ እና መለኮታዊ ሀረግ መሆኑን በታሪክ ያረጋግጥልናል። ቢስሚላህ በሐዲስ የቢስሚላህን ታላቅነት በተመለከተ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በተለያዩ ሐዲሶቻቸው አስተምረውናል። ከነዚህም ውስጥ የሰው ልጅ ይህንን ቃል ሲጠቀም የሚኖረውን መለኮታዊ ጥበቃ በተመለከተ ጃቢር ኢብኑ አብዲላህ (ረ.ዐ) ባስተላለፉት ሶሒሕ ሐዲስ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ "አንድ ሰው ወደ ቤቱ ሲገባ እና ምግቡን ሲበላ የአላህን ስም (ቢስሚላህ) ካወሳ፤ ሸይጧን (ለተከታዮቹ)፡- ‹ለእናንተ እዚህ ቤት ማደሪያም ሆነ እራት የላችሁም› ይላቸዋል።" (ሶሒሕ ሙስሊም፥ 2018) ይህ የሚያሳየን "ቢስሚላህ" ሸይጧንን ጭምር የሚያግድ ትልቅ ጋሻ መሆኑን ነው! ©የሕያ ኢብኑ ኑህ t.me/comparativeRelgion t.me/comparativeRelgion
🌟 ነፃ የትምህርት ዕድል! 🌟 የ«አል-ኢዝሃር ኢስላማዊ ጥናት እና ምርምር ተቋም» የ4ተኛ ዙር የንፅፅር ትምህርት (Comparative Religion) ምዝገባ ጀምሯል! 💫 ምን ይማራሉ? በእስልምና እና በክርስትና መካከል ያለውን አንድነትና ልዩነት በንፅፅር። 🔹 ቆይታ፦ ለ5 ወራት (weekly 2-3) 🔹 ክፍያ፦ ሙሉ በሙሉ ነፃ (Free)! 🔹 የት?፦ በኦንላይን (online)። 🔹የምስክርነት ወረቀት፦ በአግባቡ ተምረው ካለፉ በሰርተፍኬት ይመረቃሉ። ➔ ልዩ ትኩረት ለመንግስት ሰራተኞች፣ ለተማሪዎችና ለእህቶች ልዩ ክትትል እናደርጋለን። ➔ የምዝገባ ጊዜ፦ ከዛሬ ሰኔ 3 ጀምሮ እስከ ሰኔ 8 ለ አምስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ያለን ቦታ ውስን በመሆኑ ፈጥነው ይመዝገቡ። የምንሰጣቸው የትምህርት ዓይነቶች ➔ ነገረ-ክርስቶስ(christology) ሙሉ ጥናት ➔ ሥላሴ(Trinity) ሙሉ ጥናት ➔ መሰረታዊ የግሪክ ቋንቋ--- ናቸው አል-ኢዝሃር ኢስላማዊ ጥናት እና ምርምር ተቋም ሰኔ 03/2018 ዓ.ል ይሄንን ሊንክ በመንካት ወደ መመዝገቢያ ግሩፕ ይግቡ። https://t.me/+WxUlgdaUFsU5MjQ0
ጎሽተ ሞተ ነቃን? በአላህ ሱም ስረም ጥሽት ሩህሩህ ስረም ጥሽት ተመራሪ በሆነይ፡፡ እነይ ቡቆ መንቄ ባሶት በሼሽት ኡስቤ ላፍታትነ ሊንዤነይሙ ኡሁንም፦ የቂነም ጎሽተ ሞታን? ፣ የሞተቢ መሰከ ምንግዝን? ሀቀም ጎሽተ ሼሽተ አሮት ዋ ሼሽተ ማልተ በቀብር ኡስጥ ናረን? ሊሎነይ ሱልቸ ቡርኩት ኩችብቸ ለንቀልነ ሊንዥነ። 1,የቂነም ጎሽተ ሞታን? ሰመዬይ፣ ደቼይ፤ ከልቀይ በሁንዱሉሌከ የሀለቀይ ጎሽተ ኡሀ በሀለቀይ ከልቅ ሞተ እላነይ የነሳራሮይ አሽር «ኡማር በፈየ አፍሸ እሶከ ትበላት» ኢላነይ መክማቾት ያቴክሳን።መሳምከ በፈያይ አፍ ቦዝ አሳወ በሎትም ጎሽተ ሞተ በሎትኒ። ቁርአን ዋ ሀዲስ ምን እላን? መውት፦ በሎት « م و ت » ቲላን የአረብኘ ቀውል የትረሀበ ቲዮን ቡር ቀውልከ «موت»ን። መውት "የሀቂቀኜ መውት "الموت الحقيقي/الطبيعي ዋ "ቀሊ መውት (ሚኜት)"الموتة الصغرى በበሎት በሆሽት ሳድነ ልንዥነይሙ።ጎሽተ ተእታይ ቶሆሽትሚ የጠለለን። የሀቂቀኜ መውት ሀቂቀኜ መውት እሉያነይ በአረብኘ «الموت الحقيقي» በበሎት እጠሩያ ቲዮን ሂነይ መንቄ ባሶት አሏህ ሂንኩ እላን ሱራ አል-አንዓም (6)፥ 61 "...حَتَّىٰ إِذَا جَاءَ أَحَدَكُمُ الْمَوْتُ تَوَفَّتْهُ رُسُلُنَا وَهُمْ لَا يُفَرِّطُونَ" "...ተአቱሙም አደይ መውትት በመጠቢ ወክት መላይካኮይ ዮስዱያን፤ ኡሁኑም እለዛገጉ፡፡" ቢእታይ ቁርአን ኡስጥ «مَوْتُ» የትባለይ ሀቂቀኜኒ መውት። ጎሽተንገ ተሀቂቀኜም ዋ ተቀልሚ (ተምኜት) የጠለለን። ለእታመይኮ አሏህ በቀውልከ ኡስጥ ሂንኩ ኢላነይ፦ ሱረቱል 25:58 وَتَوَكَّلْ عَلَى الْحَيِّ الَّذِي لَا يَمُوتُ وَسَبِّحْ بِحَمْدِهِ ۚ وَكَفَىٰ بِهِ بِذُنُوبِ عِبَادِهِ خَبِيرًا ነሳራርቸንገ «ጎሽተ ሞታኔ በሼሽት ማልት ዋ አሮት ዞፎ ተሞተ ነቃን» እሎን።ሀቀም ሼሽተ ማልተ ዋ አሮት ቄራን? ሊላነይ ሱል በገነ አሽር ሙሻወሬ እልነብያን።እነካሌይ አሳወ ቡርኩት ሱልቸ እነቅላን። ለባይትከ ጎሽተ በሞተቢ ሳት ጎሽታይ ማኒ ናር? ፣ ጎሽታን ኡሀ የሀለቀይ ከልቅ ቀተለይ በሎት መቅቡልነት አለይ? በኪታብኒሙ ኡስጥ በ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥17 “ብቸከ ጎሽተ ለሆነይ ለይጠፋነይ ለይትራነይ----"ኢላን። በእታይ ኤት «ለይጠፋነይ» ሊላነይ ቀውል በፈረንጂ አፍ(እንግሊዝኛይ፦ KJV, NIV, ESV) የገበይ ቀውል «immortal» ቲዮን የቀውሊ አወል(ቃሙሰኜ) አነግን ሰተተኜ ማእነከ "አይሞታን ፣ኢነብራን" በሎትን።ዡቦይ የበዘ ላትፋህሞት የ ግሪኪ ኪታብ "ለይጠፋነይ" ሊላነይ የገበይ ቀውል "ἀφθάρτῳ" (አፍታርቶ) ኢላነኒ። ይታይ ቀውል በአማራይ አፍ "የማይጠፋው" ቢለይም በፈረንጂ አፍ ዋ በግሪኪ አፍ በጠቀለ ሃለት "አይሞታነይ" በበሎት ተከተባን። Οἴδαμεν δὲ ὅτι καλὸς ὁ νόμος, ἐάν τις αὐτῷ νομίμως χρῆται, Τῷ δὲ βασιλεῖ τῶν αἰώνων, ἀφθάρτῳ, ἀοράτῳ, μόνῳ σοφῷ Θεῷ, τιμὴ καὶ δόξα εἰς τοὺς αἰῶνας τῶν αἰώνων· ἀμήν. Α Προσ Τιμοθεον Επιστολη 1,17 እታይ አይጠፋነይ ጉሽተ ለሼሽት አሮት ዋ ማልት ሞተ ነቃን በሎተ ተሀቅ የራቀን ዡቦ። ሆነም ታሌ የመርየምነ ልጅ ኢሰ (ዐ.ሰ) የልሞተኮ ዋ የልትሰቀለኮ በቁርአን ኡስጥ በቡርኩት ኤትቸ ተጬቀማን።ለባይትከ፦ሱረቱል ኒሳ 4:157 وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا الْمَسِيحَ عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ اللَّهِ وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ وَلَٰكِن شُبِّهَ لَهُمْ ۚ وَإِنَّ الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ لَفِي شَكٍّ مِّنْهُ ۚ مَا لَهُم بِهِ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا اتِّبَاعَ الظَّنِّ ۚ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًا «እኘ የአለሃነይ ሉክተኘ የመርየምነ ልጄ አልመሲሕ ኢሳነ ቀተልነ» በበሎትኒሙ ( አጠፋነይሙ)፡፡ አልቀተሉያነም አልሰቀሉያነም፡፡---- ቢእታይ ቁርአን ኡስጥ «وَمَا قَتَلُوهُ» በሎትም «አልቀተሉያነም» ቲል በመንቄም አለህ የገበኒ አህድ ናረ። ኢታሚ አህድ ዩሃነ (ሆሽትለኜይ ሰመይ) ኤት ሊነቅለይ አህደ የገበኒኮ በቁርአኒ ኡስጥ ኢንኩ በበሎት ተጎበላን(ተከተባን)፦ ሱረቱል አል-ኢምራን 3:55 إِذْ قَالَ اللَّهُ يَا عِيسَىٰ إِنِّي مُتَوَفِّيكَ وَرَافِعُكَ إِلَيَّ وَمُطَهِّرُكَ مِنَ الَّذِينَ كَفَرُوا ---- «--- አላሀም በባለ ወክት ኢክስ ኢሳ ሆይ! እሄ ዮስደሃው የሄነም ኤት እነቅለሃው፡፡---» በኢታይ ቁርአን ኡስጥ አላህ የገበኒ አህድ «مُتَوَفِّيكَ» "ዮስደሃው" ዋ «وَرَافِعُكَ» "እነቅለሃው" እሎነን ሱር። ኢነይ አህደ በሱረቱል ኒሳ 4:158 بَل رَّفَعَهُ اللَّهُ إِلَيْهِ ۚ وَكَانَ اللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمًا « አላህ (ኢሳን) ዩሃን ኤት ነቀለይ፡፡»---- አላህ የገበኒ አህደ «رَّفَعَهُ اللَّهُ» በሎትም «ነቀለይ» በበሎት አትጎበለያን።በእታይ ዱም በሎትም «የሀቂቀኜ መው» በጎሽተ ዬለቢኮ ዋ ሂንኩምንገ በመሪያም ልጅ በኢሰ(አ.ሰ) አኩ ጃንጎ ባለይ ሀቂቀኜ መውት የልነቼይኮ አንዤናን። ሆነምታሌ የገናሚ ሰበኮ ኡሃም ኢሞትቢያን ወክት ያለይኮ ያለሃይ ሉክተኘ ኤወዱናን። ቀሊ መውት (ምኜት)"الموتة الصغرى ምኜተኝ በቁአን ኡስጥ በቡርኩት ኤትቸ "መውት" በበሎት አላህ ጠራያን። ለባይትከ፦ اللَّهُ يَتَوَفَّى الْأَنفُسَ حِينَ مَوْتِهَا وَالَّتِي لَمْ تَمُتْ فِي مَنَامِهَا ۖ 39:42 « አላህ ሩህቻይ በሞቱ ወክት ዮስደይማን፡፡----» በእታይ ቁርአን ኡስጥ «حِينَ مَوْتِهَا» የትባለይ)"الموتة الصغرى" በሎትም ምኜተይኒ። የመርየም ልጅ ኢሰ(አ.ሰ) ምኜት ናረቢ። ነሳራርቸ ኢሰ ጎሽታን ባሎ ያምኖን። ጎሽተንገ ተምኜት የጠለለን። የነሳራርቻይ ኪታብ ኢሰ አነግነ ቡሁኒ መጥሬ ኢየሱስ እኛኔ ሰብ ነቀለይ እላን። ሀቀም ሰመዬይ ዋ ደቼይ(አርዱላን) የሀለቀይ ጎሽተ ዪኛኔ ኡሀ በሀለቀይ ከልቅ ኢብራጋን? ማርቆስ 4:38 "ቢእታሚ ወክት ኢየሱስ፥ በሰፊናይ በሬር አዘርከ ትራስ ተራሳኔ እኜ ነር፤ ተኬታይቻምከ አብራገጉይ-" መስበቼ (አክቾት) ለደር በነቀልነይ ዱም በሎትም «የቂነም ጎሽተ ሞታነን? ቢላነይ ኩትብ "መውት በሎት ምን በሎት ዮነኮ" ዋ መውትንገ የሮሬ(ሀቂቀኜ) "الموت الحقيقي" ዋ ቀሊ መውት(ምኜት) "الموتة الصغرى" በበሎት በሆሽት እትሳዳነኩ አንዤናን። ጎሽተ ቲእታይ ግዝቸ የጠለለ ቲዮን ገሽተ ኢሞታን ዋ ዪኛን በሎት በጎሽተ ደር ክዝበ አዋልኮት። ሊእታይኮ የመሪየም ልጅ ኢሰ(አ.ሰ) የሁዳዶ የልቀተሉይኮ ዋ የልሰቀሉይኮ በቁርአን ዋ በፎልኒሙይ ኪታብ ተከተባን አንዤናነም ጃንጎ። የመሪየም ልጅ ኢሰ(አ.ሰ) ዪኝ የናረኮ በኪታብኒሙ አንዤናን። ጎሽተ ቢኜ የሀለቀይ ከልቅ ማኒ ኢቄራይ ናር? ኢላነይ ሱል ኢነቅላን። ጎሽተነ «لَا تَأْخُذُهُ سِنَةٌ وَلَا نَوْمٌ» በበሎት ተከተባን። ቢቄጥላነይ ኩትብ የቀሩይ ሆሽተይ ዱምቸ ያንዥናን። አስናጂሎ የናሲሪ አምዳለ t.me/comparativeRelgion
видео или голосовое, без подписи