Coram Deo | ኮራም ዴኦ✨
СтатистикаCoram Deo — Living before the face of God. Puritian✨ Soli Deo Gloria
- Последний пост
- 10:53
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 9
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 283
- 1/48двое суток
- 324
- 1/72трое суток
- 349
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
መጽሐፈ ምሳሌ 14:11 (AMH) •••••••••• ¹¹ የኅጥኣን ቤት ይፈርሳል፤ የቅኖች ማደሪያ ግን ያብባል።
“ያመናችሁት በከንቱ ነው” (1ቆሮንቶስ 15 : 2 ) ከተስፋዬ ሮበሌ ስንቶቻችን በትንሣኤ ሙታን ላይ የዳበረ ትምህርት ሰምተን የምናውቃለን? ክርስቶስ ኢየሱስ የሞተውና ሞትን ድል አድርጎ የተነሣው፣ እኔና እናንተ በምንኖርበት ምድር ላይ ነው! እውነቱ ይህ ከሆነ በዚያን ዘመን የነበሩ ግሪካውያን፣ ሮማውያን፣ አይሁዳውያን …የታሪክ ጸሓፊዎች ስለዚህ ትንግርታዊ ክሥተት በርግጥ ምን አሉ? ታሪክ ቀናትንና ክሥተቶችን በቃል ከመሸምደድ ያለፈ የምርምር ዘርፍ ከሆነ፣ በጥሩ ቃላት ተከሽኖ የቀረበን አፈ ታሪክ (ልብ ወለድ) ከእውነተኛ ክሥተት የሚለየው እንዴት ነው? የታሪክ ፍልስፍና ከዚህ አንጻር ምን ይላል? ዐላፊ ክሥተቶችን መመርመር የታሪክ ጥናት ዘርፍ ብቻ ሳይሆን፣ የወንጀል መርማሪዎችም ግብር ነው? እንግዲያው የአንድን ታሪክ ክሥተት እንዴት ነው የምንመረምረው? የክርስቶስ ትንሣኤ ከዚህ አንጻር እንዴት የመረመራል? በምዕራቡ ዓለም የክርስቶስ ትንሣኤን በተመለከተ ለረጅም ዓመታት እጅግ ሰፊ የሚባሉ ምርምሮች ተካሂደዋል! በታዋቂ ዩኒቨርሲቲ የታተሙ እጅግ በርካታ መጻሕፍት ለንባብ ቀርበዋል! እስከ ዛሬ በዚህ ረገድ የተመዘገበው ግኝት ምን እንደሚል ኢትዮጵያውያን የመጽሐፍ ቅዱስ መምህራን እነዚህን ጥናት አጣቅሰው ረብ ያለው ነገር ሲነግሩን አልታየም! በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የዕቅበተ እምነት ድጋፍ ሰጪ ቡድን፣ በዚህ ብርቱ ርእስ ጉዳይ ላይ የሚመክር የሁለት ቀን ዐውደ ጥናት አዘጋጅቶአል! የፊታችን ቅዳሜና እሑድ! በአትላንታ ከተማ! ቅዱሳት መጻሕፍት በርእሰ ጉዳዩ ላይ የሚሰጡት ትምህርት በጥልቀት ይመረመራል! የተለያዩ ሃይማኖቶች የሚያቀርቧቸው የግራና ቀኝ ክርክሮች ይመረመራሉ! ሐዋርያው ጳውሎስ እንዳለው፣ ክርስቶስ ኢየሱስ ሞትን ድል አድርጎ ካልተነሣ “እምነታችን ከንቱ ነው!” “እኛም በኀጢአታችን ነው ያለነው!” እንዲያውም የክርስትናን ንጽሮተ ዓለም የሕይወታችን አልፋና ዖሜጋ በማድረጋችን፣ “ከማንም ይልቅ ምስኪኖች ነን!” ኑ ይህን ብርቱ ርእስ ጉዳይ በአንእክሮ እንመርምረው! ኑ ሌሎችንም ጋብዙ! ሠናይ ውእቱ!
видео или голосовое, без подписи
ቆይ ግን በጣም የdevilን ስራ የሚሰሩለት እና ለህዝብ የሚያውጁለት አገልጋዩ የሆኑ ሰዎችን የእግዚአብሔር ድንቅ የሆኑ ስራዎቹን ለማፈራረስ ቆርጠው የተነሱ ሰዎችን የሆነ መልካም ነገርን ፤ ለህሊና የሚመቸን ነገር ሲያወሩልንን wow እያልን አብረን እናጨበጭባለን እንዴ? ለምን አሉ? ምን ገዷቸው ብለን አንጠይቅም እንዴ እንደ ክርስቲያን አንጠነቀቅም እንዴ? ለምሳሌ ሐሳውያን የስህተት ትምህርት ዋና አቀንቃኞች መምህራን ደግ ነገር ያወሩ ቀን እሱን ሳደንቅ እንዲህ እናርግ ሲሉ ስተባበራቸው መልካም እኮ ነው እያልኩ ፤ ይሄ እንዴት ሆኖ ልክ ይሆናል? ወይ ያንን መልካሙን ነገር በራሴ መንገድ መከወን ነው እንጂ እንዴት ነው አብሬያቸው የምቆመው? በፍፁም አብረናቸው የምንቆማቸውን ሰዎች መጠንቀቅ አለብን ወይ ደግሞ መናገር "እነዚህን ሰዎች አብሬያቸው ቆሜ ስታዩኝ የነሱን ነገር በፍፁም እንደምቃወም እወቁ ለምን ይህን አጀንዳ መደገፍ እንደፈለጉም አላውቅም ለራሳቸው አጀንዳም ፈልገውት ስለሚሆን ግን ለዚህ ጉዳይ እንዲህ እላለው" ብለን መናገር ይበጀናል! ልክ ባለፈው ቃለህይወት ቤተ ክርስቲያን እንዳደረገችው ማለት ነው "ካውንስሉ ላይ ስታዩኝ በፍፁም አብረውኝ ያሉት ሰዎች ለነሱ አጀንዳ የምቆምላቸው በወንጌሉ ጉዳይ አብረን አይደለንም!" በደንብ መጠንቀቅ አለብን!
እውነተኛ ክርስቲያናዊ ሕይወት በየዕለቱ ክርስቶስን በመምሰል በቃልና በምስክርነት የሚያድግ ነው። እርሱን አዳኝና ጌታ አድርገን በተቀበልንበት እውነት ባለተቆጠበ መሰጠት ልንኖር ተጠርተናል። አዳኝነቱና ጌትነቱ የሚለያዩ አይደሉም። በመስቀሉ ቤዛዊ ሞትና በትንሣኤው ድነት ማግኘታችን፣ ክርስቶስን በሁሉ ነገር ጌታና ገዢ ባደረገ ሕይወት ሊገለጥ ይገባዋል። ያም ማለት ለእርሱ ፈቃድ ሁለንተናን አሳልፎ በመስጠት መኖር ማለት ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ ይህንኑ እውነት ለቈላስይስ አማኞች እንዲህ በማለት በአጽንዖት ያሳስባል፦ "እንግዲህ ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት እንዲሁ በእርሱ ኑሩ፤ በእርሱ ተተክላችሁና ታንጻችሁ እንደ ተማራችሁት በእምነት ጸንታችሁ፣ የተትረፈረፈ ምስጋና እያቀረባችሁ ኑሩ።" (ቈላስይስ 2፡6-7) "በእርሱ ተተክላችሁና ታንጻችሁ" የሚሉት መንታ ቃላት የሚያሳዩን ስለማይታዩት ሁለት መሠረታዊ እውነቶች ነው። የመጀመሪያው የዛፍን ሥር የሚያመለክት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ የቤትን ወይም የሕንጻን መሠረት የሚያሳይ ነው። ለዛፍ ሕይወትና ልምላሜ ሥሩ ለም መሬት ውስጥ መስደድ አለበት፤ ሕይወት የሚያገኘው ከሥሩ ነውና! በነፋስ ተገፍቶ እንዳይወድቅ የሚጠብቀውም ሥር ሰዶ በመተከሉ ነው። ልክ እንዲሁ “ታንጻችሁ” የሚለው ሁለተኛው ቃል የሚያመለክተው የማይታየውንና ሕንጻውን ደግፎ የሚይዘውን ጽኑ መሠረት ነው። አንድ ቤት በነፋስና በጐርፍ የመወደቁ ወይም ያለመወደቁ ብርታት የሚለካው በመሠረቱ ጥንካሬ ነው። በተመሳሳይ መልኩ ጌታችን እንዲህ ይላል፦ “እንግዲህ ይህን ቃሌን ሰምቶ በተግባር የሚያውል፣ ቤቱን በዐለት ላይ የሠራን ብልኅ ሰው ይመስላል። ዶፍ ወረደ፤ ጐርፍም ጐረፈ፤ ነፋስም ነፈሰ፤ ያን ቤት መታው፤ በዐለትም ላይ ስለ ተመሠረተ አልወደቀም።" (ማቴ. 7፥24-25) የአማኝም ሕይወት እንዲሁ ሊሆን ይገባዋል። ሥርና መሠረታችን (የማይታየው ሕይወታችን) በክርስቶስ ሕይወት፣ ሥራና ትምህርት ላይ ሊመሠረትና ሥር ሊሰድ ይገባዋል። ሕይወታችን ፍሬያማ ሊሆን የሚችለው ክርስቶስን በተቀበልንበት መጠን ስንኖር ነው። ያም በተግባር የሚከተሉትን ያጠቃልላል፦ ⚓️ በቃሉ የበላይ ባለሥልጣንነት መኖርን ⚓️ በመንፈስ ቅዱስ መመራትን ⚓️ በቅዱሳን ኅብረት (በክርስቶስ አካል) ውስጥ መኖርን ⚓️ ኀጢአትን መደበኛ ካደረገ የሕይወት ዘይቤ በመለየት በቅድስና መኖርን ⚓️ በቃልና በምስክርነት ሥርዐት ባለው የደቀ መዝሙርነት ሕይወት መመሥረትን "እንደ ተማራችሁት በእምነት ጸንታችሁ፣ የተትረፈረፈ ምስጋና እያቀረባችሁ ኑሩ" — በእውነተኛና ጤናማ አስተምህሮ መጽናት፣ እንዲሁም እግዚአብሔር በክርስቶስ ስለ ሰጠን የዘላለም ሕይወት፣ ልጅነት፣ ተስፋና ቅድስና በየዕለቱ እያመሰገኑ መኖር ማለት ነው። ክርስትና ስሜት ሲኖረን ብቻ የሚኖር ሕይወት አይደለም፤ ከባዶ ስሜታዊነት ያለፈና በፍሬያማነት በየጊዜው የሚያድግ ሕያውነት እንጂ! በራስ ጽድቅ ላይ በተመሠረተ “አድርግና አታድርግ” ሕግጋት የሚመራ ደረቅ ሃይማኖተኝነት ሳይሆን፣ እግዚአብሔርን ከመውደዳችን የተነሣ ራሳችንን ለእርሱ ጌትነት አሳልፈን በመስጠት የምንኖረው የምስጋና ሕይወት ነው። ለእግዚአብሔር ወሰን የሌለው ፍቅር የምንሰጠው ምላሽ እውነተኛና ያልተበረዘ ሕያው አምልኮ ነው። ይህም ማለት፣ በግልጽ ከሚታይ ዓለማዊነት በመለየት በሁሉ ረገድ በቅድስና ለእግዚአብሔር ክብር ለመኖር መወሰን ማለት ነው። ቅርንጫፍ ሕያውነቱ የሚለካው ከግንዱ ጋር በተጣበቀበት ልክ እንደ ሆነ ሁሉ፣ የሕንጻም ጽናት በመሠረቱ ጥንካሬ እንደሚወሰን ሁሉ፣ የእኛም ፍሬያማነትና ጥንካሬ የሚወሰነው በክርስቶስ ላይ ተመሥርተን ሥር በሰደድንበት መጠን ያህል ብቻ ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዳለው “በእምነት፣ በቃል፣ በዕውቀት፣ በፍጹም ትጋትና በፍቅር” ማደግ አለብን። (2 ቆሮ. 8፥7) ጌታ ሆይ ጸጋህን ስጠን። አሜን!
видео или голосовое, без подписи
እግዚአብሔር ቀሪ ዘመናችሁን ይባርክላችሁ የከሰራችሁ የሚመስላችሁን እነዚያን ዘመናት ብዙ መልካምን ነገር አድርጎ ይካስላችሁ ተያይዞ ለበጎ ይሁንላችሁ የማትፀፀቱበት ቀሪ ዘመን ይስጣችሁ።
✨
https://youtu.be/IzhPEVArpKU
"... ዕለት በዕለት “አምላክ እንዲህ ይልሃል…” መባል የለመደ ሰው፣ ለምን ብሎ መጽሐፍ ቅዱሱን ያነባል? ክርስቲያን ቅዱሳት መጸሕፍትን የሚያነበው መለኮታዊ ዕውቀት ለመቅስም ብቻ ሳይሆን፣ መለኮታዊ ምሪት ለማግኘት ጭምር ነው፡፡ አምላክ አፍ ለአፍ፣ ዕለት በዕለት ይናገረኛል የሚሉ፣ ዐይነ ደረቅ ቈርጦ ቀጥሎች እንደ ጭስ አፍነውት፣ በምን ቀዳዳ ቃለ እግዚአብሔርን የማጥናት ትንፋሽና ብርታት ሊያገኝ ይችላል? ብዙዎች በውል ያላስተዋሉት ትልቁ እንቈቅልሽ ይህ ነው፡፡ ... ክርስቲያኖች ሁሉ ካህናት ናቸው።ከዚህም የተነሣ ያለ አንድ መካከለኛ ክርስቶስ ኢየሱስ ዘንድ በቀጥታ መቅረብ ይችላሉ ፤ አምላክን ማናገር ይችላሉ'' የሚለውን ትምህርት በማመናችን ከካቶሊክና ከኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ተለይተን ነበር። ዛሬ ግን የታሪክ ምጸት ወድቆብን አባይ ነባዮችን የየቀን ካህን አድርገን ሹመናል። አባይ ነባይ ``የየቀን ውሎህን ወለል አድርጌ እነግርሃለሁ'' የሚለው ትውልድ ከቅዱሳት መጻሕፍት የመሟገት ዐቅም ከየት ሊያመጣ ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት በመሄድ በኩረ ጽሑፋትን ለመመርመር ብርታቱን ከየት ሊያገኝ ይችላል? የሕይወት ፍልስፍናውን ለማጥለል ሊቃውንትን መጻሕፍት በምን ጉልበት ይመረምራል? መጠይቃዊ ህይወትንስ የጉዞ መስመሩ እንዴት ማድረግ ይቻለዋል? ይህን እንቆቅልሽ በትክክል ሳንፈታና ሳናስፈታ ትውልዱን በትክክል ማገልገል እንችላለን ማለት ሲበዛ ዘበት ነው።ይህ ሁነኛ ጥያቄ በትክክል የማይመለስ አገልግሎት ለትውልዱ ነቀርሳ ፍቱን መድኀኒት ሊያመጣ አይችልም። አባይ ነባይ [ዶ/ር Tesfaye Robele ፤ ገጽ 12]
"የእኛ የነፍስ አባት፣ የእኛ ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ነው!" "እኛ የነፍስ አባት የሌለን ዓይደለንም፣ ካህን የሌለን ዓይደለንም ፤ ዝርው፣ ሃይማኖት አልባ ዓይደለንም። ሃይማኖት አለን፣ ያውም ርትዕት የሆነች። አዎ ጥርት ያለ፣ ቀጥ ያለ፣ ኦርቶዶክሲ! "ብዙ ሰዎች ኦርቶዶክስ ሲባል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ነው የሚታያቸው። ኦርቶዶክስ ማለት ግን ቀጥ ያለ፣ ልክ የሆነ ማለት ነው። የእኛም እምነት እንዲሁ ቀጥ ያለ ነው፣ ኢየሱስ እና እየሱስ ብቻ! "ሃይማኖት አለን፣ እምነት አለን። ጌታ ኢየሱስ የእምነታችን ሐዋርያ ነው። ከእርሱ ሰምተናል፣ ተምረናል። እርሱ ያስተማራቸውን፣ ሐዋርያት የጻፉልንን አንብበን ተረድተናል። በደንብ ስሙኝ...ካህን አለን፥ ያውም ሊቀ ካህናት፣ እንደ መልከጸዴቅ የተሾመ! እግዚአብሔር በመሀላ በቀኙ ያስቀመጠው ሊቀ ካህን!" አሰግድ ሳህሉ
እግዚአብሔር ፊቱን ያብራላችሁ። በጨለመ አለም የርሱ ፊት ዘውትር በእናንተ ላይ ይሁን። የእግዚአብሔር ፊት የበራለት ምነኛ ታደለ✨
ብወድህ ምን ይገርማል!
የእግዚአብሄር ሰው.... 1, በግል ጸሎቱ ትጉ ነው፤ 2, የሚያደርገውን ሁሉ ለእግዚአብሄር ክብር የሚያደርግ ነው፤ 3, በደስታው ቀን ሆነ በክፉ ቀን ስንፍናን የሚናገር ሳይሆን አምላኩን በንጽህና የሚያመሰግን ነው፤ 4, በቅንጦትና በምቾት ራሱን የሚያቀብጥ ሳይሆን ቀለልና ልከኛ ያለ ህይወት የሚኖር ነው፤ 5, በቃሉ እውቀት የበለጠገና በነገሮች ሁሉ ትጉ ሰራተኛ ነው፤ 6, ስለ ማንም ሰው ክፉ የማይናገርና ስለ ሰዎች ምልጃን የሚያቀርብ ነው፤ 7, ዘወትር ሃጢአቱን ለአምላኩ የሚናዘዝ ነው.... ✍️ሸልፌክስ
!
#ካነበብሁት
ከሳምንቱ ድካም ይልቅ ከቅዱሳን ጋር የሚደረግ ህብረት ነፍስን ያድሳል፤ መንፈስንም ያረካል። ዛሬ ወደ አባታችን ቤት ጎራ ብለን በምስጋና፣ በጸሎትና በፍቅር የምንታደስበት ልዩ ቀን ነው። በህብረት ውስጥ ሰላም አለ፤ በህብረት ውስጥ በረከት አለ። እንኪያስ ጉዟችንን ወደ ቅዱሳን ህብረት እናድርግ!
እርቃኑን ሆኖ ሸለመን እየደከመ አቆመን እርሱ በመስቀል ሲሞት እኛ ተጻፍን በህይወት
እርቃኑን ሆኖ ሸለመን እየደከመ አቆመን እርሱ በመስቀል ሲሞት እኛ ተጻፍን በህይወት