Meleket Tube
Статистикаመንፈሳዊ መረጃዎችን እንዲሁም ዝማሬዎችና የወንጌል ትምህርቶች በየእለቱ ከዚህ ገፅ ያገኛሉ። ኢየሱስ በክብር ይመጣል! Find us on more- https://linktr.ee/meleket_tube
- Последний пост
- 31 авг. 2025 г.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ። ከኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን። ነሐሴ 23 ቀን 2017 ዓ.ም @meleket_tube
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
" የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ" በሚል መሪ ቃል ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው አመታዊ የሚሲዮናውያን ስልጠና ተጠናቀቀ። የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ላሰማራቻቸው ሚሲዮናውያን የምትሰጠው አመታዊ ስልጠና ላለፉት ሶስት ቀናት በመሠረተ ክርስቶስ ሴሚናሪ ቢሾፍቱ ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ በድምቀት ተጠናቋል። ከነሃሴ 13-15/2017 ዓ.ም የተካሄደው ይህ ስልጠና ሚሲዮናውያኑ እያከናወኑ ለሚገኘው የወንጌል ተልዕኮ አገልግሎት ክህሎታቸውን ከፍ ያደረገና በአካባቢያቸው ለሚገኙ ማህበረሰቦች በቀላሉ ወንጌልን ለማድረስ የሚያግዙ ቁሳቁሶች ያገኙበት እንደነበር ሰልጣኞች ገልጸዋል። ስልጠናው ዛሬ ሲጠናቀቅ የቤተክርስቲያናችን ወንጌል ስርጭትና ቤተክርስቲያን ተከላ መምሪያ ከግሬት ኮምሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ሚሲዮናውያኑ ለማህበረሰባቸው የኢየሱስን ፊልም በቀላሉ ለማሳየት የሚረዷቸውን ታብሌቶች እንዲያገኙ አድርጓል። "#የወንጌል_ሰባኪነትን_ሥራ_አድርግ_አገልግሎትህን_ፈጽም።" 2ኛ ጢሞቴዎስ 4÷5 ምንጭ: መሰረተ ክርስቶስ ቤ/ክ @meleket_tube
ወዳጆች ሆይ የእግዚአብሔር ሰላምና ፀጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን እያልኩ እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንኖር በቅርብ ወደ እናንተ ስለማቀርበው ስለ አዲሱ ቁጥር ስምንት (Vol. 8 የዝማሬ ሰንዱቅ (አልበም) መልካም ዜና ሳካፍላችሁ በደስታ ነው:: አስጀምሮ የሚያስጨርስ እግዚአብሔር ነውና ክብር ለስሙ ይሁን!! በዚህ አገልግሎት ሙዚቃውን በማቀናበር በሪኮርዲንግ በሚክሲንግ በግራፊክስ ስራ አብረውኝ የደከሙትን በፀሎት እና በምክር በሚያስፈልገኝ ነገር ሁሉ የደገፉኝን እንዲሁም ለዚህ ስራ መሳካት ከጎኔ በመቆም ያበረታታችኝን አብራኝ አገልጋይ የሆነች ውዷን ባለቤቴን እንዲሁም ልጆቼን እና አብረውኝ አገልጋይ የሆኑ የዳላስ ቤተክርስቲያን አገልጋዮችን ከልቤ አመሰግናለሁ!! መዝሙሮቹን በሚለቀቁበት ጊዜ በ Daniel Amdemichael YouTube channel እንዲሁም iTunes, Spotify, google play, Amazon Music እና የመሳሰሉት ላይ ታገኛላችሁ:: የኔን YouTube channel ሰብስክራብ እንድታደርጉ በትህትና አበረታታለሁ:: ሰብስክራይብ ስታደርጉ ከጎን ያለችውን የደውል ምልክት መጫናችሁን አትርሱ ይህን ብታደርጉ YouTube channel ላይ አዳዲስ ነገሮችን ሳቀርብ ወዲያውኑ ማግኘት ትችላላችሁ:: እግዚአብሔር ይባርካችሁ!! - Daniel Amdemichael Join➴ @MELEKET_TUBE @MELEKET_TUBE @MELEKET_TUBE
Hanna Tekle መሥዋዕት! ቁጥር 4 ሰንዱቅ በቅርብ ጊዜ Join➴ @MELEKET_TUBE
#ካውንስሉ_አስቸኳይ_መግለጫ_ሰጠ በወንጌላዊያን አማኞች እና አብያተክርስቲናት ላይ እየደረሰ ስላለዉ ጥቃት ህዳር 27 ቀን 2016ዓ/ም መግለጫ_ሰጠ። 1-ባለፋት ዘመናት በተለይ በደርግ ዘመን የተወረሱ የቤተክርስቲያን ይዞታዎች በኢሕአዴግ ዘመን በከፊል ቢመለሱም እስካሁን ያልተመለሱ የኦሎምፒያ መሰረተክርስቶስ፣ የአዲስ ከተማ ገነት፣ የኢትዮጵያ ወንንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ብረት የሆነው የጉድ ሼፐርድ ማዕከል ፣ቄራ አካባቢ ያለው የብርሃነ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ፣እና ሌሎች እስካሁን ያልተመለሱ ይዞታዎች ሲሆኑ እነዚህ ይዞታዎች የቤተክርስቲያን ንብረት በመሆናቸዉ እንዲመለሱ ተጠይቋል። 2-የድሬዳዋ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ይዞታዋን ለቃ እንድትነሳ የከተማዉ አስተዳደር የወሰንኑ ቢሆንም የከተማዉ አስተዳደር እና የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች እንዲሁም የካውንስሉ አመራሮች ሰፊ ዉይይት አድርገዉ የከተማዉ አስተዳደር ጉዳዩን እየመከረበት ይገኛል።የከተማዉ አስተዳደር የደረሰበትን ደረጃ በአጭር ጊዜ ግልፅ እንዲያደርግ ተጠይቋል። 3-የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ይዞታ ነጥቆ የራሱ ጽህፈት ቤት አድርጎት ይገኛል።እንዲሁም የቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ይዞታ የሆነዉን የኩሪፍቱ የጸሎት ማዕከል በተመለከተም በማእከሉ ምንም አይነት የልማት ስራ ቤተ ክርስቲያን እንዳታከናወን በማገድ የቤተክርስቲያኑን ይዞታ ለመንጠቅ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝኝ ተገልጾ የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከዚህ ህገወጥ ድርጊቱ እንዲቆጠብ እና የወሰደዉን የቤተክርስቲያን ንብረት እንዲመልስ ተጠይቋል። 4-በአዲስ አበባ ዙሪያ ባለችው የሸገር ከተማም የፈረሱ የወንጌላዊያን የእምነት ተቋማት ይዞታቸዉ እንዲመለስ እንዲሁም በከተማዋ ለ23 አብያተክርስቲያናት ከካቢኔ ቦታ ተወስኖላቸዉ ቦታቸዉን መረከብ ላልቻሉ በአፋጣኝ ካቢኔ የወሰነዉ ዉሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ተጠይቋል። 5-የመቃብር ስፍራን ጥሶ በመግባት እየተደረገ የሚገኘዉ አግባብ ያልሆነ ተግባር በአስቸኳይ እንዲቆም 6-በምዕራብ ኢትዮጵያ በቄለም ወለጋ ዞን በጊዳሜ ወረዳ ዘጠኝ ምእመናንን የአምልኮ ስነስርአት እየፈፀሙ ካሉበት ሌሊት ላይ ተወስደዉ መረሸናችው እጅግ አሳዛኝ እንደሆነና ለነዚህ ንፁሃን ፍትህ እንዲሰጥ ተጠይቋል። በአጠቃላይ ፍትህ ያስፈልጋል ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት ሊከበሩ ይገባል ይህ ሁሉ እየሆነ ያለዉ የታችኛዉ የመንግስት አካል የመንግስትን ስልጣን በመጠቀም ጥቂት ግለሰቦች የግል አጀንዳ ይዘዉ የሚፈፅሙት ተግባር ነዉ። የፌደራል መንግስት ጣልቃ በመግባት ፍትህ ሊያሰፍን ይገባል ሲል የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል በመግለጫዉ አስታዉቋል። Join➴ @MELEKET_TUBE
без подписи
አስደሳች ዜና! እንደ "ዴስፓሲቶ" እና "ጋሶሊና" በመሳሰሉት በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂው ሙዚቃዎቹ የሚታወቀው የአለማዊ ዘፈን አቀንቃኝ የነበረው የፖርቶ ሪኮ ራፐር ዳዲ ያንኪ ህይወቱን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለመስጠት እንደወሰነ እና ከአለማዊው ሙዚቃ እራሱን እንዳገለለ አሳውቋል። "እንደ ሙዚቃ፣ ማህበራዊ ሚዲያ፣ መድረኮች፣ ማይክራፎን ኢየሱስ የሰጠኝ በእጄ ውስጥ ያሉኝ መሳሪያዎች ሁሉ አሁን ለመንግስቱ ነው ሲል ተናግሯል።" Join➴ @MELEKET_TUBE
без подписи
Godina Qellem Wallagaa, Aanaa Gidaamiitti ajjeechaa Amantoota irratti raawwate ilaalchise Ibsa WKWW Mekane Yesus Itiyoophiyaatiin kenname. Sadaasa 24-2016 ህዳር 25 ቀን 2016 የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በቄለም ወለጋ ዞን በተለይም በጊዳሚ አውራጃ በአባላቶቹ ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል። Join➴ @MELEKET_TUBE
ራሴን ስመለከት እንዴት ልድን እንደምችል አይታየኝም ክርስቶስን ስመለከት እንዴት ልጠፋ እንደምችል አይታየኝም፡፡ ማርቲን ሉተር Join➴ @MELEKET_TUBE
без подписи
без подписи
#ይድረስ_ለወንጌል_አማኞች_በሙሉ📌📌 (እባክዎ መልዕክቱን ሼር ያድርጉ) በቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘው ኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ኩሪፍቱ ማዕከል የቃለህይወት ቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን የሁሉም ወንጌላውያን አማኞች ንብረት የሆነ፣ ብዙዎቻችን በግል እና በቡድን እየሄድን ለቀናት የፀለይንበት ስፍራ ነው። በዚህ ስፍራ ሄዶ ያልተገለገለ፣ ያልፀለዬ አማኝ ይኖራል ማለት ዘበትነው። በአዲሳባ ያሉ ሁሉም ቸርቾች ወጣ ብለው የሪትሪት፣ የፆምፀሎት ፣ የህብረት ጊዜ ማሳለፍ ሲፈልጉ የመጀመሪያም የመጨረሻም ተመራጩ ቦታ ይህ የኩሪፍቱ ቃለህይወት ነው። ይህ ስፍራ በከተማ አስተዳደሩ ከቸርች ተነጥቆ ለግለሰቦች ሊሰጥ መሆኑን በትናንትናው ዕለት ቸርቿ ይፋ አድርጋለች። ይህ የሁሉም አማኝ ቅርስ ከቤተክርስቲያን በግፍ ከመነጠቁ በፊት ሁላችሁም የወንጌል አማኞች ድምፃችሁን እንድታሰሙ ጥሪ እናቀርባለን። እባኮ መልዕክቱን ሼር ያድርጉ Join➴ @MELEKET_TUBE
#ቤቱ_ራሱ_ይናገራል፤ ለጸሎት ቤት እንጂ ለሌላ አልተፈጠርኩም ይላል። በአዲስአበባ ከተማ ከ1954 ዓም አንስቶ የመጀመሪያው የመሠረተ ክርስቶስ ጸሎት ቤት በደርግ ያለሕግ ወርሶ ግቢውን ትምህርት ቤት "#የአብዮት_እርምጃ" ብሎ ሰየሙት ጸሎት ቤቱን ግን የስፖርት መሥሪያ አደረጉት። #ቤቱ_የጸሎት_ቤት_ይሁን!! #MKCchurch @meleket_tube