tgindex
📚📚 የመፅሐፍ ድምፅ ( The sound of a book ) 📚📚

📚📚 የመፅሐፍ ድምፅ ( The sound of a book ) 📚📚

Статистика

መፅሐፍ የማይቀያየር ቋሚ ወዳጅ ነው

Последний пост
31 мая 2025 г.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Книги
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 050
+2 Са 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
—
 
Месяц
—
 
Просмотров на пост
1 525
20 постов
Вовлечённость
74,4%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всогО 20
УпОПинаниК
0
канаНОв
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
—
1/48двое суток
—
1/72трое суток
—

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ልናውቋቸው የሚገቡ 17 የእስያ ሀገራት አባባሎች 1. #ቻይና: "ዛፍ ለመትከል ምርጡ ጊዜ ከ20 ዓመት በፊት ነበር። ሁለተኛው ምርጥ ጊዜ ግን አሁን ነው።" (ማብራሪያ: አንድን ነገር ለማድረግ ጊዜው አሁን መሆኑንና መዘግየት እንደሌለበት ያሳያል።) 2. #ጃፓን: "ሰባት ጊዜ ውደቅ፣ በስምንተኛው ተነስ።" (ማብራሪያ: በችግር ውስጥ መጽናትንና ተስፋ አለመቁረጥን ያበረታታል።) 3. #ህንድ: "ዛፍ ስለሚረግፉ አበቦች አይጨነቅም።" (ማብራሪያ: ከቁጥጥር ውጪ በሆኑ ነገሮች ላይ አለመጨነቅንና ነገሮችን መተው/መልቀቅን ያስተምራል።) 4. #ኮሪያ: "ዝንጀሮም እንኳ ከዛፍ ላይ ይወድቃል።" (ማብራሪያ: ማንም ሰው ፍጹም እንዳልሆነና ስህተት ሊሰራ እንደሚችል ያመለክታል።) 5. #ቬትናም: "ወንድሞችና እህቶች እንደ እጅና እግር ቅርብ ናቸው።" (ማብራሪያ: የቤተሰብን የጠበቀ ትስስርና ቅርበት ያጎላል።) 6 #ታይላንድ: "የዱላን አንዱን ጫፍ ስታነሳ፣ ሌላኛውንም ጫፍ አብረህ ታነሳለህ።" (ማብራሪያ: ማንኛውም ድርጊት የራሱ የሆነ መዘዝ ወይም ውጤት እንዳለው ያስረዳል።) 7. #ፋርስ (ፐርሺያ): "በተሳሳተ ጊዜ ከሚሰጥ ወርቅ፣ በተገቢው ጊዜ የተወረወረ ድንጋይ ይሻላል።" (ማብራሪያ: የጊዜን አስፈላጊነትና ትክክለኛ ወቅት ላይ የሚደረግ ነገር ዋጋ እንዳለው ያሳያል።) 8. #ፊሊፒንስ: "ከየት እንደመጣ ወደ ኋላ የማያይ፣ መድረሻው ላይ መቼም አይደርስም።" (ማብራሪያ: ምስጋናን፣ ትህትናንና ያለፉበትን መንገድ ማስታወስ ያለውን ዋጋ ያሳያል።) 9. #ቻይና: "ወደፊት ያለውን መንገድ ለማወቅ፣ ወደ ኋላ የሚመለሱትን ጠይቅ።" (ማብራሪያ: ከሌሎች ሰዎች ልምድ መማር ጠቃሚ መሆኑን ያሳስባል።) 10. #ጃፓን: "አንድ ፍላጻ በቀላሉ ይሰበራል፣ በአንድ ላይ የታሰሩ አስር ፍላጻዎች ግን አይሰበሩም።" (ማብራሪያ: የአንድነትን ኃይልና አስፈላጊነት ያሳያል።) 11. #ህንድ: "ትምህርት ባለቤቱን በሄደበት ሁሉ የሚከተል ውድ ሀብት ነው።" (ማብራሪያ: ለትምህርትና ለእውቀት ዋጋ መስጠትና ዘላቂነታቸውን ያሳያል።) 12. #ኮሪያ: "የነብር ዝንጉርጉርነቱ ውጪ ነው፣ የሰው (ባህሪው) ግን ውስጡ ነው።" (ማብራሪያ: የአንድን ሰው እውነተኛ ማንነት የሚወስነው ውስጣዊ ባህሪው እንጂ ውጫዊ ገጽታው እንዳልሆነ ይናገራል።) 13. #ቬትናም: "ፍሬ ስትበላ፣ ዛፉን የተከለውን ሰው አስታውስ።" (ማብራሪያ: ለቀደሙት ሰዎች ጥረትና ላገኘነው በረከት ምስጋና ማቅረብን ያስተምራል።) 14. #ታይላንድ: "ጥላህ እንዲመራህ አትፍቀድ።" (ማብራሪያ: ፍርሃት ወይም ያለፈው ህይወትህ የአሁኑን ውሳኔህንና አካሄድህን እንዲቆጣጠረው አትፍቀድ።) 15. #ሞንጎሊያ: "የመጀመሪያው ብርጭቆ ለእንግዳ ነው፣ ሁለተኛው ለመደሰቻ፣ ሶስተኛው ለትርምስ።" (ማብራሪያ: በሁሉም ነገር ልክንና መጠንን ማወቅ ቁልፍ መሆኑን ያሳያል፤ ከልክ ማለፍ ወደ ችግር ይመራል።) 16. #ቲቤት: "መቶ የወንድና መቶ የሴት (የተለያዩ) ባህሪያቶች ፍጹም ሰውን ይፈጥራሉ።" (ማብራሪያ: ሚዛናዊነትና የተለያዩ በጎ ባህሪያትን በአንድ ላይ መያዝ ወደ ፍጹምነት እንደሚያደርስ ያሳያል።) 17. #ቻይና: "የሺህ ማይል መንገድ በአንድ እርምጃ ይጀምራል።" (ማብራሪያ: ማንኛውም ትልቅ ነገር የሚጀምረው በትንሽ እርምጃ መሆኑንና መጀመር በራሱ ቁልፍ መሆኑን ያሳያል።) ©️Habesha Son

  • " ያለፈው በሚመጣው ላይ ምንም ጥቀርሻ መተው የለበትም ብዬ ያለፈውን ከኔ አርቄ የጣልኩ ይመስለኝ ነበር። ምናልባት አይቻል ይሆናል። ዛሬ ከተከሰተው ክስተት ምኑ ከኔጋ እንደሚያያዝ አላውቅም። የሰው ልጅ ሁሉ ከትላንቱ ተጋብቶ ሳይሆን አይቀርም የሚኖረው። ዛሬው የትላንት ጭማቂ ነዋ!! የዛሬ ግቡ የትናንት ምክኒያቱ ነበራ! ከዓመታት በፊት እናቴ ወይ አባቴ ያነቡት እንባ ምክንያቱን እንኳን ሳይቀይር በልጃቸው  ጉንጭ ላይ ሊወርድ ይችላል። አባቶች በበሉት መልር ፍሬ የልጆች ጥርስ በለዘ አይነት ሆኖብኝ ትላንት ትዝታ ብቻ አለመሆኑ የገባኝ ዛሬ ነው፡፡ ትናንት ትውልድን እንኳን ጥሶ እንደሚያልፍ አስቤ አላውቅም ነበር፡፡ ሀበሻ ሙዚቃው ውስጥ እንኳን ትዝታ ስልት መኖሩ ከትናንት መፋታት አለመፈለጉ ወይ አለመቻሉ ይሆናል። " ✍️ ጠበኛ እውነቶች

  • 😂 ይህን በተግባር አይተናል ብዙ ሰዎች ሽጠውን መልሰው ራሳቸው ከስረዋል የከሰሩት ኪሳራ እንደ ንግዱ ዓለም ዛሬ ከስረው ነገ ማትረፍ ሳይሆን እኛን የሸጡን ሰዎች ሁሉ እኛን ከሸጡን በኋላ ላያገግሙ ከስረዋል። እኛም በሚገባ ጥሩ ዋጋ አውጥተንላቸዋል እነሱ ግን ከእኛ ያገኙትን የሽያጭ ዋጋ ሳይጠቀሙበት ከስረዋል እንግዲህ ህይወት ይቀጥላል። 🙏 በዚህ ዓለም፣ በታማኝነት ስም ከሐሰተኛ ባልንጀሮች ጋር ከመጓዝ ይልቅ በክብር ብቻን መሄድ ይሻላል። ልባቸው በቅናት፣ በምቀኝነትና በክህደት እንደ እባብ መርዝ የተሞሉ ብዙ የምታውቃቸው ሰዎች ከሚኖሩህ ይልቅ፣ ጥቂት ግን እንደ ብረት የጠነከሩ እውነተኛ ወዳጆች ያሉት ትንሽ የጓደኛ ክበብ መያዝ እጅግ የተሻለ ነው። 👉👉👉👉 https://t.me/damtad

  • видоО иНи гОНОсОвОо, йоС пОдписи

  • 👇👇 #ሕይወት_ምንድን_ነው? 👇👇 👉 ዶስቶየቭስኪ፦ #ሲኦል_ነው። 👉 ሶቅራጥስ፦ #ፈተና_ነው። 👉 አርስቶትል፦ #አእምሮ_ነው። 👉 ኒቼ፦ #ኃይል_ነው። 👉 ፍሮይድ፦ #ሞት_ነው። 👉 ማርክስ፦ #ሃሳቡ_ነው። 👉 ፒካሶ፦ #ጥበብ_ነው። 👉 ጋንዲ፡- #ፍቅር_ነው። 👉 ሾፐንሃወር፦ #መከራ_ነው። 👉 በርትራንድ ራስል፦ #ውድድር_ነው። 👉 ስቲቭ ስራዎች፦ #እምነት_ነው። 👉 አንስታይን፡- #እውቀት_ነው። 👉 እስጢፋኖስ ሃውኪንግ፦ #ተስፋ_ነው። 👉 ካፍካ፦ #ገና_ጅምር_ነው። 🙏 አስባችሁታል እነዚህ ህይወት ሰጥቶ ጠቢብ እና ሃሳባዊያን አድርጎ በዓለም ከመታወቅ በላይ እስከመመለክ የደረሱ ትልልቅ ሰዎች ናቸው። በነፃ ፍቃድ ህግ የፈጠረ አምላክ ህይወት እሱ ብቻ መሆኑን ባለመቀበላቸው ምክንያት ለምን እውቅናቸውን አልነሳም፤ ለምንስ አልቀናም? ምክንያቱም እሱ የፍቅር አምላክ ነውና በፍቅሬ ኑሩ ስላለ ብቻ ነው። ፍቅር አይታበይም አይቀናም ክፉን በክፉ አይመልስም። ስለዚህ ህይወት ገና ምንነቷ አልታወቀምና በፍቅር እያመሰገንን እንኑር። ✍️ አሹ አባይ

  • видоО иНи гОНОсОвОо, йоС пОдписи

  • видоО иНи гОНОсОвОо, йоС пОдписи

  • видоО иНи гОНОсОвОо, йоС пОдписи

  • видоО иНи гОНОсОвОо, йоС пОдписи

  • видоО иНи гОНОсОвОо, йоС пОдписи

  • видоО иНи гОНОсОвОо, йоС пОдписи

  • видоО иНи гОНОсОвОо, йоС пОдписи

  • видоО иНи гОНОсОвОо, йоС пОдписи

  • ♦♦♦ አንድ ሽማግሌ ውሃ ውስጥ ሊሰምጥ ያለ ጊንጥ ያዩና ሊያድኑት ይፈልጋሉ፡፡ ከዚያም ጊንጡን ከውሃው ለማውጣት እጃቸውን ዘርግተው አነሱት በዚህ ጊዜ ጊንጡ ነደፋቸው:: እሳቸውም ደንግጠው ለቀቁት ጊንጡም ተመልሶ ወደውሃው ገባ፡፡ ሽማግሌው አሁንም የጊንጡን ውሃ ውስጥ መስመጥ ተመልክተው ድጋሚ እጃቸውን ለእርዳታ ዘረጉለት አሁንም በድጋሚ ጊንጡ ነደፋቸው ሲለቁት አሁንም ውሃ ውስጥ ገባ፡፡ ይህንን የሽማግሌውን ትእይንት የሚመለከት አንድ ሰው ወደ ሽማግሌው ጠጋ ይልና ‹‹ይህ እኮ ክፉ ፍጥረት ነው! ጊንጥ እሱን ለማዳን ሲሉ እርሶ እየተጎዱ እኮ ነው›› አላቸው። ሽማግሌውም እንዲህ ሲሉ መለሹ ‹‹የጊንጡ ተፈጥሮ መናደፍ ነው፡ የኔ ተፈጥሮ ደግሞ መርዳትና ማገዝ ነው፡ ስለዚህ ተፈጥሮዬ ክፉ አደለምና ጊንጡን ከመርዳት አላቋርጥም #አረዳዴን ግን አስተካክላለሁ›› አሉና ጥቂት አሰብ አድርገው ተነስተው ከዛፉ ላይ አንድ ቅጠል ቀንጥሰው በቅጠሉ ጊንጡን ይዘው አወጡትና ህይወቱን አተረፉለት፡፡ እኛም እንዲህ ነን ሰውን ለመርዳት ስንሄድ ብዙ ጊንጦች ይነድፉናል፡ ደግ ልናደርግ ስንጓዝ ብዙ እንቅፋቶች ይመቱናል፡፡ ነገር ግን ጊንጡ እንዳይነድፈን እናደርጋለን እንጂ እንቅፋቱ እንዳይመታን እንጠነቀቃለን እንጂ እንዴት ደግ ማድረግ እናቆማለን ? አንተም አንቺም ሁላችንም እዚህ ምድር ላይ ያለን ሰዎች በሙሉ ስንፈጠር ደግና መልካም ነን፡፡ ግን ሰውን ክፉ የሚያደርገው ተፈጥሮው ሳይሆን መጥፎ አጋጣሚ ነው፡፡ ለዛ እኮ ነው በነዚህ ጊንጦች ስለተነደፍን መልካም ለማድረግ ቅስቀሳ በጎ ለመስራት ማጣራት መጠራጠር በሌላ አይን መመልከት ጀመርን፡፡ እስኪ የዛሬዋን አዲስ ቀናችንን እንዲህ ብንውላትስ ሰው ስንረዳ እንደጊንጥ በሚሆኑ ሰዎች ተሸንፈን መልካም ከማድረግ ከምንቆጠብ የምንረዳበትን መንገድ ለይተን ብናውቅስ፡፡ በነገራችን ላይ ለሰው በጎ ማድረግ ሲባል በገንዘብ ብቻ ይመስለናል አይደለም:: በየቤቱ ገንዘብ ኖሮት ሰው የናፈቀው ህሊና አለ:: ስለዚህ አንዳንዶች ፈገግታችንን አንዳንዶች እኛነታችንን አንዳንዶች መሰማትን ይፈልጋሉና በየደረስንበት ለመልካም ነገር ጊንጥ ፈርተን እምቢ እንዳንል፡፡ መልካም የምታደርጉ ሁሉ ግን ጊንጡንም ቢሆን ከማዳን አትቦዝኑ። ✍️ ኡስታዛ ያሲን ኑሩ

  • ጊንጥ(scorpion) ልጆቿን ከጥቃት ለመከላከል በጀርባዋ አዝላቸዉ ትንቀሳቀሳለች።ልጆቹም እናታቸዉ ጀርባ ላይ ሆነዉ፣የሚመገቡት እናታቸው አካል ላይ ያለዉን ስጋ ነዉ። እናታቸዉ ጀርቧዋ ላይ ሆነዉ አካሏን እየቦጨቁ የሚበሉትን ልጆቿን፣ ከአደጋ ለመጠበቅ ስትል ህመሟን ትችላለች....ቀናቶች ባለፉ ቁጥር ልጆቿ እየጠነከሩ እሷ ደግሞ እየደከመች ትመጣለች፤ ቀስ በቀሰም መንቀሳቀስ ይሳናታል። ልጆቿ ብቻቸዉ መንቀሳቀስ ፣እራሳቸዉን ከአደጋ መከላከል በሚጀምሩበት ወቅት፣ድካሟ፣ህመሟ በዝቶ ትሞታለች።ልጆቿ እንዲኖሩላት እሷ ትሞታለች.... የሚያሳዝነዉ እዉነት... አብዛኞቻችን ልክ እንደ ጊንጧ ልጆች እየሆንን መምጣታችን ነዉ።ከተወለድንበት ቀን ጀምሮ ቤተሰቦቻችን ያለማቋረጥ ዋጋ ሲከፍሉልን ኖረዋል፤እንድንማርላቸዉ፣ከጠረንጴዛችን ላይ ምግብ እንዳይጠፋ...ሲሉ ያለ እረፍት ደክመዉ እኛን አጠንክረዉናል። ይሁን እንጂ....የጉብዝና ወቅታቸዉ አልፎ የእድሜ ጀንበር ልትጠልቅ ባዘቀዘቀችበት የእርጅና ዘመናቸዉ፣ደግፈዉ ያሳደጉት ልጅ ድጋፍ ይሆነናል ብለዉ ሲያስቡ በልጃቸዉ የተካዱ ብዙዎች ናቸዉ። አብዛኞቻችን የህልማችንን መንገድ ስንከተል፣ ህልማችን እዉን እንዲሆን ፍቅራቸዉን፣ገንዘባቸዉን፣ጉልበታቸዉን...ሳይሰስቱ የለገሱንን ቤተሰቦቻችንን ዘንግተናል። let's not wait until it's to late to honour them with comfort. ✍️ fb

  • "ፍቅረኛው ከልብ ጓደኛው ጋር ማግጣበታለች ! " : በሕይወት ከባድ የሚባሉ ውጣውረዶችን አልፏል ። ከልጅነት እስከ እውቀት ተደራራቢ ፈተናዎችን ተጋፍጧል ፤ ቤልጄማዊው ኮከብ ኬቨን ደ ብሩይነ ። የማንቸስተር ሲቲው አማካኝ ኬቨን ደ ሩይነ በእግር ኳሱ ሆኑ በግል ሕይወቱ ተስፋ አስቆራጭ ጊዜያትን አሳልፏል ። ከነዚህ ውስጥ አሳዳጊ ቤተሰቡ በልጅነቱ እንደማይፈልጉት ነገሩት ፤ ፍቅረኛው ከልብ ጓደኛው ከነበረው ቲቦ ኮርትዋ ጋር ማገጠችበት ፤ ጆዜ ሞሪንሆ ለኔ አታስፈልገኝም ብሎ ከቼልሲ አስወጣው ፤ የልብ ጏደኛው የነበረው ማላንዳን በድንገተኛ አደጋ አጣው ። እነዚህ ፈተናዎች ከባድና መቋቁም የሚከብዱ ቢሆኑም እሱ ግን በጥበብ ማለፍ ችሏል ። የሕይወት ውጣውረዶቹን ታግሎ በማለፍ " ዓይንህን ላፈር " ያሉትን አሳዳጊ ቤተሰቦቹን ፣ ጆዜ ሞሪንሆን ፣ ቼልሲ ቀና ብለው እንዲያዩት አድርጓል ። ከማንቸስተር ሲቲ ጋር 6 የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ እና አንድ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን ዋንጫዎችን ማሸነፍ ችሏል። ፍቅረኛው ከልብ ጓደኛው ጋር በመ ማገጧ የተሰበረው ልቡ ተጠግኖ ሚስትም አግብቶ 3 ልጅ መውለድ ችሏል ። እንደ ኬቨን ደ ሩይነ ጊዜ ይጥላል ፥ ጊዜ ያነሳል ። ሕይወትም ይቀጥላል !! ✍️ ትዝብታችን እናውጋ።

  • ወደ ገነት የገባው የመጀመሪያው ሰው ወንበዴ ነበር ።ወደ ሲኦል የገባው የመጀመሪያው ሰው የጌታ ሐዋርያ ነበር ስለዚህ ልትጨነቁ የሚገባው እናንተ በሰው አይን ማን እንደሆናችሁ ሳይሆን በፈጣሪ አይን እኔ ማነኝ ብላችሁ መሆን አለበት። "ኦሾ"

  • видоО иНи гОНОсОвОо, йоС пОдписи

  • видоО иНи гОНОсОвОо, йоС пОдписи

  • 🙏 ልጃገረድ ነበርኩ ... አሁን ልጅነቱ አልፎ ገረድነቱ ብቻ ቀርቶኛል፤ በአርባ አምስት አመቴ ከተማ መሐል እየተመላለስኩ ‘ወንድ አላውቅም’ ብል ማን ያምነኛል? ማንም። ስለዚህ አሳማኝ ታሪክ እየፈጠርኩ አወራለሁ … እንዲህ እላለሁ 👉 የመጀመሪያው ... በጣም ነበር የምንዋደደው ምን ዋጋ አለው ያው ልጅነት፤ አያያዙን አላወቅንበትም’ 👉 ሁለተኛው ... ይኼ እንኳ እሱ ነው እስከሚያብድ ድረስ የሚወደኝ ምን ዋጋ አለው ደሃ ነበር’ 👉 ሶስተኛው ... ለካ አግብቶ የፈታ ነው ዋሽቶኛል። ልጆችም አሉት ኧረ ምን ዋጋ አለው? እንኳን ለእኔ ለልጆቹም እናት አልሆነም …’ እል እልና ከዛ መቁጠር አቆምኩ እላለሁ ታሪኩ እንደ ጠያቂው እና እንደ ሁኔታው ይለያያል አንዱ ጥሎኝ ውጪ አገር ሄደ ሌላውን ሲወሰልት ደረስኩበት አንዱ መልኩ አያምርም ሌላው በእምነት አንድ አይደለንም እያልኩ ታሪክ እፈጥራለሁ ከሰው እኩል ለመሆን ከሴቶች በታች ላለመሆን ከልጃገረድነቴ ጥለት ላይ ልጅነትን ከገረድነት ነጥዬ እመዛለሁ፤ ነጠላነቴን፣ ነጠላዬን በሌላ የታሪክ ጥለት ለማሽሞንምን እሞክራለሁ 'ፈላጊም የላት?' 'ጠያቂም የላት ?' 'ዘንድሮም ብቻዋን ናት?' ላለመባል። "እስቲ ይቺን አምስት አመት አይቼ" ... እላለሁ ደሞ ምን ዋጋ አለው ላለፈው ሃያ አመት ያልተፈጠረ ነገር በቀጣይ አምስት አመት ምን ይፈጠራል? "እስቲ ይቺን አምስት አመት አይቼ ገዳም እገባና ለምንኩስና ደጅ እጠናለሁ።"ዳሩ ምን ዋጋ አለው ገዳም አለምን ለናቁ እንጂ ዓለም ለናቀቻቸው አይደለም። ✍️ ጠይም ፅጌሬዳ ጎንፋ