tgindex
🔉ድምፀ ተዋህዶ

🔉ድምፀ ተዋህዶ

Статистика

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች፣ ምስባክ፣ መዝሙራት እና ወረባትን፣ ወቅቱን የጠበቁ ትምህርቶችን ለማግኘት ቻናላችንን አሁኑኑ መቀላቀሎን አይዘንጉ!!

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
4
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 123
−1 за 3 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
—
 
Месяц
—
 
Просмотров на пост
114
20 постов
Вовлечённость
10,2%
к подписчикам
Постов в день
0,6
всогО 20
УпОПинаниК
0
канаНОв
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
25
1/48двое суток
28
1/72трое суток
30

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ምስባክ አመ ፯ ለነሐሴ ምንጭ :- ቅዱስ እግዚአብሔር ቲዩብ         ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥   ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧       ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ

  • ግጻዌ አመ ፯ ለነሐሴ             ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥   ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧       ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ

  • ምስባክ አመ ፭ ለነሐሴ ምንጭ :- ቅዱስ እግዚአብሔር ቲዩብ     🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪            ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥   ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧       ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ

  • ግጻዌ አመ ፭ ለነሐሴ     🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪            ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥   ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧       ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᾃʳ

  • ምስባክ አመ ፬ ለነሐሴ ምንጭ :- ቅዱስ እግዚአብሔር ቲዩብ

  • ግጻዌ አመ ፬ ለነሐሴ ምስባክ "እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሣሕ ንጉሥ ወብዙኃ ይትሐሠይ በአድኅኖትከ ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ"መዝ ፳÷፩     🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪            ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥   ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧       ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ

  • #የመጨረሻ ክፍል በልመና የጀመረው ግንኙነት የዘላለምን ሕይወት በመስጠት ተደመደመ። በውኃ የጀመረው ርእስ መሢሕና መድኃኔዓለም በማለት ተፈጸመ። አንዲትን ሴት በመማረክ መላው ከተማ ተማረከች። ለናቋት ሰዎች የእርቅ ምክንያት ሆነች። በሚያስጠማው ውኃ የሸሿት ሳምራውያን በሕይወት ውኃ ግን ተከተሏት። አንድ ጽዋ ውኃ ለመስጠት የተከራከረች እንስራዋን ጥላ ሄደች። ብዙ የተተወለት በብዙ ይወዳልና። ብዙ ኃጢአቷ ተትቶላታልና ወደ ከተማ ገብታ ድምጿን ከፍ አድርጋ መሰከረች። ☦️☦️ወስብሀት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር☦️☦️

  • #የቀጠለ ልባቸው ቢቀደስ ለውኃ ብቻ ሳይሆን ሕይወታቸውን ለመስጠትም አይሰስቱም ። የመጨረሻውን ስጦታ የዘላለም ሕይወትን የሚሰጠው ጌታችን የመጨረሻውን ትንሽ ስጦታ ውኃን ለመነ ።ውኃን የለመነባቸው ሰዓቶች በሰማርያ ደክሞ ፣ በመስቀል ላይ ታሞ ነው ። ከግለሰብ እስከ ሕዝብ ፣ ከሳምራውያን እስከ አይሁዳውያን ውኃን ነፈጉት ። ልሹ የፈጠረውን ውኃ ተነፈገ። ዛሬ ያልፈጠርነውን ቢነፍጉን ታዲያ ለምን ደነቀን ? ጌታችን ይህችን ሴት ብዙ መንገድ ተጉዞ ፣ በሐሩር ተቃጥሎ ፣ በብርቱ ደክሞ ሊያገኛት መጣ ። ምሥጢሯን እንዳይሰሙ ደቀ መዛሙርቱን የማይበላውን ምግብ እንዲገዙ ወደ ከተማ ላካቸው ። ደቀ መዛሙርቱ የመጡት ይህች ሴት አምና ለምስክርነት ልትሰማራ ስትል ነው ። ምን ያህል ሰዓት እንደሚያናግራት ያውቅ ነበር ። ይህን ሁሉ የሕሊና ጥበቃ ካደረገላት በኋላ አሁን ደግሞ እንዳትደናገር ውኃ አጠጪኝ አላት ። በውኃ ጉድጓድ አጠገብ የውኃ ጥያቄ ማንሣት የሚያግባባ ርእስ ነው ። ጌታችን ትልቅ የስብከት ዘዴ እንደ ተጠቀመ እንረዳለን ። የስብከት ዘዴ ማለት ከሚያግባባው ርእስ መነሣት ማለት ነው ። የሰውን ሕሊናና ክብር ጠብቆ ለንስሐ ማብቃት ፣ በመራራት ሰዎችን ማከም ማለት ነው ። ሰው ማለት ነጻ ፈቃድ ያለው ፤ ለባዊት ፣ ነባቢትና ሕያዊት ነፍስን የተቀዳጀ ፣ በአምላክ የፍርድ ዙፋን ፊትም ራሱን ችሎ የሚቆም ክቡር ፍጥረት ነው ። ይህንን ሰው  እንደ እንስሳ ንቆ ፣ እንደ ጣዖት ፈርቶ ሳይሆን እንደ ሰው አክብሮ ማነጋገር ይገባል ። ዛሬ ዛሬ ደኃውን የሚንቁ፣ለባለጸጋ የሚያሸረግዱ ብዙዎች ናቸው። ክርስትና ግን ሰውን በሰውነቱ ብቻ ማክበር ነው። ስለዚህም ለሰው ስሜት መጠንቀቅ ተገቢ ነው። ስብከት ማለትም ሰውን በፈቃዱ የምንማርክበት መለኮታዊ መሣሪያ ነው ። ይልቁንም ያለንበት ዘመን የሰዎች አእምሮ በብዙ የሕሊና ትግል ውስጥ የሚያልፍበት ፣ በሕመምና በጭንቀት የተጎዱበት በመሆኑ በጥንቃቄና በፍቅር ልናክማቸው ይገባል እንጂ በጭካኔ ቊስላቸውን ልንነካቸው አይገባም። “እናትና ልጅ ሲጣሉ ሞኝ እውነት ይመስለዋል” ይባላል ። እግዚአብሔርና ሰውም በጣም ይዋደዳሉና ሲጣሉ እንደ ሞኝ ልናስብ አይገባም ። ነቢዩ ዮናስ የእግዚአብሔርን ምሕረቱን ብቻ ማሰቡ ፍርዱን እንዳስረሳው ፣ እኛም ፍርዱን ብቻ ማሰብ ምሕረቱን እንዳያስረሳን መጠንቀቅ አለብን ። “ካነጋገር ይፈረዳል ካያያዝ ይቀደዳል” የሚባለው ለዚህ ነው ። ንግግር ራሱን የቻለ ጥበብ ይፈልጋል ። ጥበብ ውሸት አይደለም ። ለማን ምን መናገር ፣ እንዴት መናገር እንዳለብን የምናውቅበት ነው። ስብከት ማለት ሰውና እግዚአብሔርን ማስታረቅ ማለት ነው።  ሰው የበዳይ አኩራፊ ሁኖ ተቀምጧል ። እግዚአብሔር ደግሞ ከልጄ አስታርቁኝ ብሏል ። አስታራቂ ሰው ሽማግሌ ነውና ጠንቃቃ ፣ ንግግር አዋቂ መሆን አለበት። አሊያ አባትና ልጅን አለያይቶ ሊቀር ይችላል። ተወዳጆች ሆይ ሁላችን ክርስቲያኖች የክርስቶስ መልእክተኞች ነንና ለኃጢአተኞች በመራራት ልንመላለስ ይገባል። በፍቅርና በመውደድ ወንጌል ልንሰብካቸው ይገባል። ጌታችን በወቅቱ ከሚያግባባው ርእስ ከውኃ በመነሣት ትልቅ የስብከት ጎዳናን አሳየን። እንዴት እንደ ተጠነቀቀላት ተመልከቱ። ይህች ሴት ከዚህ በፊት አይታው የማታውቀው ፣ የአለባበሱ ሁኔታ አይሁዳዊ የሚመስል ሰው በማየቷ መደንገጧ እርግጥ ነው ። የንግግሩ መክፈቻ ግን የሚያግባባ በመሆኑ ድንጋጤዋ ወደ መገረም ተለወጠ። ወገኖቼ ሳምራውያን እንኳን እኔ ባጠለቅሁበት መቅጂያ አይቀዱም፣ እርሱ አይሁዳዊው እንዴት በእኔ ማጥለቂያ ውኃ ይጠጣል ? ወደሚል አግራሞት ተሻገረች ። ምከንያቱም  በዚያች ከተማ የእርስዋን ሕመም ሳይረዳ እንደ ርካሽ የሚቆጥራት ብዙ ነው። ዝሙተኛ አድርጎ የሚያስባት ፣ ዕድለ ቢስ አድርጎ የሚፈርጃት በንቀት፤ በአሽሙር አምስት ባሎቿን የቀበረች ገፊ አድርጎ የሚነቁራት እልፍ ነው። ይህ ነው በቀትር በጠራራ ጸሐይ ማድጋዋን አዝላ ከሰው ተደብቃ ለብቻዋ ወንዝ እንድትወርድ ያደረጋት። ከሰው አፍ ጠራራ ጸሐይን መረጠች። ጸሐይ አካሏን ሲያደክማት የሰው አፍ ግን ልብ ይሰብራልና ከሚሰብረው የሰው ቃል፣የምታቃጥለውን ጸሐይን መረጠች። ጌታ ይህ የልብ ስብራቷን ያውቃልና በፍቅር ቀረባት። ሕሊናን የፈጠረው የሕሊናን ምቾት ይጠብቃልና በብዙ ትዕግሥት እምነትዋን አሳደገላት። የሚፈለገው ጌታ በመፈለግ መጣ ። የሚጠየቀው ጌታ ጥያቄዋንና መልሷን ይዞ ተገለጠ ። የሚሰጠው ጌታ በልመና ጀመረ ። ፍጻሜው ምን ሆነ? #ይቀጥላል@mr_ebek

  • #የቀጠለ ውኃ የጠማው ሁሉ በነጻ የሚያገኘው የእግዚአብሔር ስጦታ ነው።በድሮ ዘመን በሀገራችን  ሰው ሊጠማው ይችላል ተብሎ ቀዝቃዛ ውኃ ከነመጠጫው ደጅ ላይ ይቀመጣል ። መንገደኛውም ቀድቶ እየጠጣ ያልፋል ። በእስራኤል ልማድም እንዲሁ ነው።ዛሬ ግን የምናውቀው ነው። የቀደመ ፍቅራችንን ይመልስልን። ጌታችንም ይህን ቃል ደግሞታል፡-“የእግዚአብሔርን ስጦታና፡- ውኃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር አላት” /ዮሐ. 4፥10/ ። ውኃ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው ። እኛን ተጠምቶ ሰው የሆነ ጌታ በመዋዕለ ሥጋዌ ሲመላለስ ሁለት ጊዜ ውኃ እንደ ለመነ ተጽፏል ። የመጀመሪያው በያዕቆብ ጉድጓድ አጠገብ ሲሆን ሁለተኛው በመስቀል ላይ “ተጠማሁ” በሚለው ጩኸቱ ነው ። ሁለት ጊዜም ውኃ አላገኘም ። ውኃ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው ብሎ የሚያስበው ማኅበረሰብ ጌታችን ሲለምነው ለመስጠት ፈቃደኛ አልነበረም ። ጌታችን እንኳን የአምላክነቱን አይደለም የሰው ልጅን ያህል እንኳ አቀባበል አላገኘም ። ትንሽ የሚመስለውን ነገር ለተነፈጉ ቤዛ ሊሆናቸው ትንሹንም ትልቁንም ጥቅም አጣ ። ሁለቱንም ጊዜ ከውኃው በላይ የተጠማው የሰዎቹን መልካምነት ነው ። ሳምራዊቷ ሴት ካመነች በኋላም ውኃውን አልጠጣም ። በመስቀል ላይም በውኃው ፈንታ ሆምጣጤ ቢያቀርቡለት አልጠጣውም ። ውኃን ለመስጠት ዘርን ጎሣን የሚያስጠይቅ ማንነት በሳምራዊቷ ሴት ነበረ ። ውኃን ለለመነ ሆምጣጤ የሚያቀርብ ማንነት በሰቃዮች ውስጥ ነበረ ። ከስጦታው በላይ ስጦታው የሚወጣበት ልብ እንዲቀደስ ጌታችን ፈለገ ። #ይቀጥላል

  • " ውኃ አጠጪኝ " የዩሀንስ ወንጌል ምእራፍ 4 ከቁጥር 7 ጀምሮ ..................... ጌታ ሆይ እኔን የተጠማህ አንተ "ውኃ አጠጣኝ ብለህ ወደ እልፍኜ ጓዳ መጥተህ ስንት ጊዜ ከልክዬህ ይሆን? “ከሰማርያ አንዲት ሴት ውኃ ልትቀዳ መጣች። ኢየሱስም፦ ውኃ አጠጪኝ አላት” /ዮሐ. 4፥7/ ። በአምላክ ሰው መሆን እጅግ ከሚያስደንቁ ነገሮች አንዱ ለሁሉ የሚሰጥ የማያልቅበት ባለጸጋ ሆኖ ሳለ መለመኑ ነው። ከእናቱ ድንግልናዊ ወተትን እየለመነ ያደገው ጌታችን አሁን ደግሞ ውኃ አጠጪኝ በማለት ሳምራዊቷን ሴት ለመነ ። ውኃ ነጻ ስጦታ ነው አይሸጥም።ውኃ ሕይወት ነው። ውኃ በቀላሉ ለሁሉም በሁሉም ቦታ የሚገኝ ነው። ውኃ ምድር የጸናችበት ነው።ውኃ በመጀመሪያው ቀን ሰማይና ምድር ሲፈጠር አብሮ የተፈጠረ ነው፡፡ ውኃ ዛሬም የምድርን ሦስት አራተኛ ሲሸፍን የሰውነታችን ሁለት ሶስተኛ (67%) ደግሞ ውኃ ነው፡፡ የሰው ልጅ ከተሠራባቸው አራቱ ባህርያተ ሥጋ መካከልም አንዱ ውኃ ነው፡፡ #ይቀጥላል

  • ሰኔ ፳፫ /23/ በዚች ቀን በእስራኤል ሁሉ ላይ የነገሠ የዳዊት ልጅ የሰሎሞን የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። የዚህ የሰሎሞንም የእናቱ ስም ቤርሳቤህ ነው ዳዊትም ሕግ ተላልፎ ከእሷ ጋራ ሾለ መበደሉ ባሏንም ሾለ ማስገደሉ ጌታ በገሠጸው ጊዜ ንስሓ ገብቶ መሪር ልቅሶን አለቀሰ ጌታም ንጹሕ ስለሆነ ንስሓው ይቅር አለው ። ከዚህም በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ እርሷን አገባትና ሰሎሞንን ወለደችው ንጉሥ ዳዊትም ከእርሱ በኋላ ልጅዋ ሰሎሞን እንዲነግሥና በዙፋኑ ላይ እንዲቀመጥ ቃል ገባላት። ከብዙ ጊዜ በኋላ በእግዚአብሔር ፊት እንደማልኩልሽ አሁንም በዚች ቀን እንደዚሁ እንዳደርግ ሰውነቴን ከመከራዬ ሁሉ ያዳናት የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕያው ነው ብሎ ማለ ። ቤርሳቤህም አንገቷን ደፍታ በግምባርዋ በመሬት ወድቃ ለንጉሡ ሰገደች ጌታዬ ንጉሥ ዳዊት ለዘላለም ኑር አለች። ካህኑ ሳዶቅንና ነቢዩ ናታንንም ጠርቶ ሰለሞንን እንዲያነግሱ አዘዛቸውና አነገሱት። እግዚአብሔር ለሰለሞን ጥበብን ሰጠው። በንግስና ጊዜውም የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስ ሰራ። ሰሎሞንም አርባ ዘመን ነገሠ ከመንገሡም በፊት ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረ መላ ዕድሜውም ሃምሳ ሁለት ዓመት ነበር። በመጨረሻም በሰላም አረፈ። ይህም ጥበብ የተሰጠው ንጉሥ ሰሎሞን ጥቅም ያላቸው ብዙዎች መጻሕፍትን ደርሶአል ። እሊህም ትንቢትና ትምህርት ያለባቸው ምሳሌዎችና መኃልዮች ናቸው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር Share @mr_ebek

  • 11 апр.3266иС dimitse_tewahdo

    ሥርዓተ ማኅሌት ዘትንሣኤ (ግእዝና አማርኛ) ደወል እንደተደወለ ከኹሉ አስቀድሞ ነቢያት ተደግሞ ውዳሴ ማርያም በዜማ ይደርሳል። "ተፈሥሂ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ" ይባላል። መልክአ ሥዕል አይባልም። ከዚያም ተአምረ ማርያም እና ተአምረ ኢየሱስ ይነበባል። ቀጥሎም ወተንሥአ ይሰበክና ከአራቱ ወንጌላት 3ቱ ተነበው "አርያም" በተባለው ምስጋና ማኅሌቱ ይጀመራል። ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፸፯ : ፷፭ ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እምንዋም፤ ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን፤ ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ። እግዚአብሔር ከእንቅልፉ እንደሚነቃ ተነሣ የወይንም ስካር እንደተወው እንደ ኃያል ሰው ጠላቶቹንም በኋላው መታ አርያም፦ ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ ቀዳሚ ዜማ ግበሩ በዓለ  በትፍሥሕት እስከ አቅርንቲሁ ለምሥዋዕ፤ ዛቲ ፋሲካ ቀዳሚት ሕግ። ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ፤   ይገብሩ በዓለ ሰማያት፤ ይገብሩ በዓለ ደመናት፤ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ። ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ በመጀመሪያ ዜማ በደስታ እስከ መሠዊያው ቀንዶች ድረስ በዓልን አድርጉ እርሷም የመጀመሪያዋ ሕግ ፋሲካ ናት። ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ በሰማያት በዓልን ያደርጋሉ፤ በደመናት በዓልን ያደርጋሉ፤ ምድርም ፋሲካን(ደስታን) ታደርጋለች በክርስቶስ ደም ታጥባለችና። ምልጣን፦ ዮም ፍሥሐ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን፤ እስመ ተንሥአ ክርስቶስ እሙታን፤ ቀደሳ ወአክበራ እምኲሎን መዋዕል አልዓላ፤ አማን ተንሥአ እምነ ሙታን። ዛሬ በክርስቲያን ሰንበት ደስታ ኾነ፤ ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቷልና፤ ከቀናቶች ኹሉ ቀደሳት፣ አከበራት፣ ከፍ ከፍም አደረጋት፤ በእውነት ከሙታን ተነሥቷል። 'አማን በአማን'/፪/ ተንሥአ 'አማን በአማን'/፪/ ተንሥአ እምነ ሙታን/፬/ 'እውነት በእውነት'/2/ ተነሣ 'እውነት በእውነት"/2/ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ /4/ ወረብ፦ ዮም ፍሥሐ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን/፪/ ቀደሳ ወአክበራ እምኲሎን መዋዕል/፪/ ዛሬ በክርስቲያን ሰንበት ደስታ ኾነ /2/ ከቀናት ኹሉ ቀደሳት አከበራትም /2/ እስመ ለዓለም፦ ትንሣኤከ ለእለ አመነ፤ ብርሃንከ ፈኑ ዲቤነ። ትንሣኤህን ለምናምን፤ ብርሃንህን ወደእኛ ላክልን። አመላለስ፦ ትንሣኤከ ለእለ አመነ/፪/ ፈኑ ዲቤነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ/፪/ ትንሣኤህን ለምናምን/2/ ብርሃንህን ወደእኛ ላክልን/2/ ከእስመ ለዓለሙ ጋር ተያይዞ  ሰላም ይፃፋል ሰላም፦ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ይእቲ ማርያም እምነ፤ ወእሙ ለእግዚእነ፤ ሰአሊ በእንቲአነ፤ ከመ ይምሐረነ ወይሣሐለነ፤ ያስተርኢ ኂሮቶ ላዕሌነ፤ ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ ፍሥሐ ወሰላም ለእለ አመነ። ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ማርያም እናታችን ናት፤ ለጌታችንም እናቱ፤ ስለእኛ ለምኚ፤ ይምረን እና ርቅር ይለን ዘንድ፤ ቸርነቱንም በእኛ ላይ ያሳይ ዘንድ፤ ሰንበትን ለዕረፍታችን ሠራልን፤ ለምናምን ደስታ እና ሰላም ይኾነን ዘንድ። አመላለስ፦ ሠርዓ ለነ ሰንበት ለዕረፍተ ዚአነ/፪/ ሠርዓ ለነ ሰንበት ለዕረፍተ ዚአነ/፬/ ሰንበትን ለዕረፍታችን ሠራልን/2/ ሰንበትን ለዕረፍታችን ሠራልን/4/ ኪዳንን ከተደረሰ በኃላ መዝሙር በ፩፦ ሃሌ ሉያ ይትፌሣሕ ሰማይ ወትትኃሠይ ምድር፤ ወይንፍሑ ቀርነ መሠረታተ ሕምዝ፤ ወይወውኡ አድባር ወአውግር፤ ወኲሉ ዕፀወ ገዳም ወዮምሰ ዓባይ ፍሥሐ በሰማያት፤ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ። ሃሌሉያ ሰማይ ይደሰት ምድርም ሃሴትን ታድርግ፤ የጭፍሮች መሠረቶችም ኹሉ መለከትን ይንፉ፤ ተራሮች እና ቁልቁለቶችም ይደንፉ፤ የምድረ በዳ ዕፅዋትም በሙሉ ዛሬ በሰማያት ታላቅ ደስታ ነው፤ ምድርም ፋሲካን(ደስታን) ታደርጋለች በክርስቶስ ደም ታጥባለችና። አመላለስ፦ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ፤/2/ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ/4/ ምድርም ፋሲካን ታደርጋለች/2/ በከርስቶስ ደም ስለታጠበች /4/ ሰላም ፍጹመ ንጉሠ ኮነንዎ አይሁድ፤ ተካፈሉ አልባሲሁ ሐራ ሠገራት፤ ወኮርዕዎ ርእሶ በኅለት፤ ረገዝዎ ገቦሁ በኲናት፤ ትንሣኤሁ ገብረ በሰንበት፤ ሰላመ ይጸጉ ለነገሥት፤ ለአሕዛብ ወለበሐውርት። ፍጹም ነጉሥ ላይ አይሁድ ፈረዱ፤ ወታደሮችም ልብሶቹን ተካፈሉ፤ ራሱንም በዘንግ መቱት፤ በጦርም ጎኑን ወጉት፤ ትንሣኤውንም በሰንበት አደረገ፤ ለነገሥታት፤ ለአህዛብ እና ለሕዝቦች በሙሉ ሰላምን ይሰጥ ዘንድ። ከዚህ በኃላ ወደ ሥርዓተ ቅዳሴ።

  • 11 апр.2492иС dimitse_tewahdo

    ምስባክ ዘትንሣኤ (ዘማሕሌት)              መዝ 77÷65 ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃህ እምንዋም። ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን። ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ። 11/08/17 ዓ.ም ዕለተ ትንሣኤሁ ለክርስቶስ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበ መልዕክታት ወንጌልና ምስባክ፡፡ ዲ/ን - ቆሮ15÷20-41 ን/ዲ - 1ጴጥ 1÷1-13 ን/ካ - ግብ፡ሐዋ 2÷22-37 የዕለቱ ምስባክ:- መዝ 117÷24 ዛቲ ዕለት እንተ ገብረ እግዚአብሔር ። ንትፈሣሕ ወንትሐሠይ ባቲ። ኦ እግዚኦ አድኅንሶ። (ነገር ግን በአንዳንድ ደብር ወተንስአ ሊሰበክም ይችላል) ትርጒም፦ እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት። ሐሴትን እናድርግ በእርሷም ደስ ይበለን። አቤቱ እባክህ አሁን አድን። የዕለቱ ወንጌል፦ ዮሐ፥20 ÷1- 19 ቅዳሴ፦  ዘዲዮስቆሮስ

  • ዓርብ ዘጠኝ ሰዓት በዚህች ዕለት በዚህች ሰዓት የዓለም መድኃኒት ጌታችን ኢየሱስ ለአዳም ልጆች ድኅነት በመስቀል ላይ ሆኖ በታላቅ ድምፅ ጮሆ “ኤሎሄ ኤሎሄ” ብሎ “ሁሉ ተፈጸመ” በማለት በባሕርይው ሞት የሌለበት አምላክ ነፍሱን በፈቃዱ ለሞት አሳልፎ ሰጠ። “ቀትር በሆነ ጊዜም በስድስት ሰዓት ፀሐይ ጨለመ፤ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስም ዓለም ሁሉ ጨለማ ሆነ። ፀሐዩም በጨለመ ጊዜ የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከመካከሉ ተቀደደ። ያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ድምፁን ከፍ አድርጎ፥ “አባት ሆይ፥ ነፍሴን በአንተ እጅ አደራ እሰጣለሁ”’ ብሎ ጮኸ፤ ይህንም ብሎ ነፍሱን ሰጠ።” (ሉቃ.፳፫÷፵፬-፵፮)

  • ​​​​👉 ሰባቱ የመስቀሉ ቃላት 1. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ (ማቴ 27፡46) 2. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው (ሉቃ 23፡34) 3. ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር እንድትኖር በእውነት እነግርሃለሁ (ሉቃ 23፡43) 4. እነሆ ልጅሽ አነኋት እናትህ (ዮሐ 19፡26-27) 5. ተጠማሁ (ዮሐ 19፡28) 6. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ (ሉቃ 23፡46) 7. የተጻፈው ሁሉ ደረሰ ተፈጸመ አለ (ዮሐ 19፡30) 👉 ሰባቱ ተዐምራት ጌታ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈጸሙ ተዐምራት 1. ፀሐይ ጨልሟል 2. ጨረቃ ደም ሆነ 3. ከዋክብት ረገፉ 4. ዐለቶች ተሠነጠቁ 5. መቃብራት ተከፈቱ 6. ሙታን ተነሡ 7. የቤተ መቅደስም መጋረጃ ለሁለት ተቀደደ 👉 አምስቱ ችንካሮች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸው አምስቱ ችንካሮች 1. ሳዶር ፦ በሚባል ችንካር ቀኝ እጁን ቸነከሩት 2. አላዶር ፦ በሚባል ችንካር ግራ እጁን ቸነከሩት 3. ዳናት ፦ በሚባል ችንካር ሁለት እግሩን ቸነከሩት 4. አዴራ ፦ በሚባል ችንካር ማሀል ልቡን ቸነከሩት 5. ሮዳስ ፦ በሚባል ችንካር ደረቱን ቸነከሩት

  • አምንስቲቲ ሙኪርያ አንቲ ፋሲልያሱ። አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ። አምንስቲቲ ሙዐግያ አንቲ ፋሲልያሱ።

  • ​​​​ዕለተ ዓርብ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕለት ዕለተ ዓርብ ይባላል፡፡ ይህ ዕለት ክርስቶስ ከተሰቀለበት ጊዜ ጀምሮ እሰከ አሁን ድረስ በክርስቲያኖች ዘንድ በጾምና በስግደት በየዓመቱ ይከበራል፡፡ በመጀመሪያ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ የተሰቀለው ትንቢቱን ለመፈጸም ነው፡፡ ሙሴ "ስቅልተ ትሬእያ እስራኤል ለሕይወትከ ቅድመ አዕይንቲከ ወኢትትአመና" "እስራኤል ሆይ ሕይወትህ /ክርስቶስ/ በዓይኖችህ ፊት በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ታየዋለህ፡፡ ግን አታምነውም፡፡" /ዘዳግ. 28/ ታላቁ ነቢይ ኢሳይያስም "መጽአ ከመ በግዕ ይጠባሕ ወከመ በግዕ ዘኢይነብብ በቅድመ ዘይቀርጾ ከማሁኢከሠተ አፍሁ በሕማሙ በቅድመ እለ ይረግዝዎ፤ ወበ ኃጢአተ ሕዝብየ በጽሐ እስከ ለሞት፣ ነሥአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ" አኮ በመልአክ ወአኮ በተንባል አላ ለሊሁ እግዚእ መጽአ ወአድኀነነ ተብሎ በሰፊው ተናግሯል፡፡ ጥቅሶቹ ብዙ ናቸው፡፡ ኢሳ. 53፡1-6 ነቢዩ ዳዊትም "አገቱኒ ከለባት ብዙኃን፣ ወአዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን" ቀነውኒ እደውየ ወእገርየ ወኆ ለቁ ኵሎ አዕጽምትየ" "እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ፡፡ አጥንቶቼ ሁሉ ተቈጠሩ፤ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም" እንዳለው፡፡ 6666 ጊዜ በገረፉት ጊዜ አጥንቱ ተቆጥሮዋል፣ ይኸ አስቀድሞ ቅዱስ ዳዊት የተናገረው ነው፡፡ 6666 ጊዜ ለመገረፉ ግብረ ሕማማት ይገልጻል፡፡ መዝ. 21/22 ቁጥር 17-18 ክርስቶስ ለምን ሞቱ በመስቀል ሆነ? ከመስቀል በሌላ ማዳን አይችልም ነበር ወይ? ቢባል በዘመኑ የነበረው የበደለኛ አገዳደል ሥርዓት እንደየሀገሩ ሁኔታ የተለያየ ነበር፡፡ ለምሳሌ የሮማውያን ሥርዓታቸው መስቀል ነው፡፡ የአይሁድ "ውግረተ ዕብን" ነበር፡፡ የባቢሎናውያን እሳት አንድዶ እዚያ መክተት ነው፡፡ ፋርስ ለአንበሳ መጣል ነው፡፡ ጌታም በሮማውያንም ሥርዓት ተሰቅሎ ሞተ፣ ለዚህም ልሹ ጌታ ሞቱ በመስቀል እንደሚሆን አስቀድሞ ተናግሯል፡፡ ዮሐ. 3፡14፡፡ ባይሰቀል፣ ጎኑ ባይወጋ ማይ ለሕጽበት፣ ደም ለጥምቀት ባልተገኘ ነበር፡፡ ብለው መምህራን ተርጉመዋል፡፡ አይ፣ በውግረትም ደሙን አይታጣም ብለው ትንቢትን ለመፈጸም ተሰቀለ ብሎ አስታርቀውታል እንጂ፡፡ የአይሁድ ሥርዓት በድንጋይ ወግሮ መግደል ነው፡፡ ጌታ የተሰቀለው በሮማውያን ሥርዓት ነው፡፡ "ኲሉ ሰቁል ዲበ ዕፀመስቀል ርጉም ውእቱ" "ሠርቶ ቀምቶ የተሰቀለ ሰው የተረገመ ነው" ትላለች ኦሪት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም "ወፆረ መርግማ ለኦሪት" አለ፡፡ ርጉም ተብሎ የአዳምን መርገም ለማጥፋት በአዳም የተፈረደው ሁሉ ተቀብሎ አዳምን ከመርገመ ነፍስ አዳነው፡፡ "ወሠዓረ መርገመ እምኔነ" ከእኛ መርገመ ኃጢአትን ደመሰሰ፣ አጠፋ ያለው ስለዚህ ነው፡፡ ዛሬ ክርስቶስ ከተሰቀለ፤ ልጅነት ከተመለሰ ወዲህ ወደ ሲኦል መውረድ ቀርቷል፡፡ ይህም ዮሐንስ አፈወርቅ ገልጦታል፡፡ "እንከሰ ኢንወርድ ታሕተ አላ ፈድፋደ ንተልዎ ለዘፈጠረነ ወንበውእ ኀበ ቦአ ሐዋርያነ ህየ ንበውእ ኵልነ" ይላል፡፡ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ጠፋልን የተባለው አምኖ፣ ተጠምቆ ፣ ጥሩ ሼል ከሠራ ወደታች መውረድ የለም ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት ነው፡፡ ቀድሞ በዘመነ ብሉይ መልካም ሼል ቢሠሩም እነ አብርሃም ይስሐቅ፣ ያዕቆብ ሁሉ በሲኦል ነበሩ፡፡ የአዳምን መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ አጠፋ የሚለው ስለዚህ ነው፡፡ "ወበመንፈቃ ለዕለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ ወእድኅክ ውስተ መርህብከ ወእትቤዘወከ በሞትየ ወበመስቀልየ" ቀሌምንጦስ፤ "ወለትከ" የተባለችው ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፡፡ ገድለ አዳም ገጽ 105፡125፡፡ መጽሐፈ ቀሌምንጦስ ገጽ 54፡8 ቀደም ብሎ እንደተገለጸው "ከመይሥዓር መርግማ ለኦሪት" በተባለው መሠረት አዳም ተርግሞ ነበር ወይ? ሲባል መልሱ አዎ ነው፡፡ ከገነት ሲኖር "ይችን ዕፅ የበላህ እንደሆነ ትመውት ሞተ" ሞትን ትሞታለህ በሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ፣ በርደተ መቃብር ርደተ ሲኦል ያገኝሃል ነው ያለው፡፡ "ወአልበሶሙ አእዳለ ማዕስ" ያብርሃን የነበረው፣ እንደብርሌ፣ እንደ ብርጭቶ ንጹሕ የነበረው እሾኽ እማይወጋው፣ እንቅፋት የማይመታው፣ እማያደማው፣ ብርድ የሌለበት የነበር በኋላ መርገም ሲያድርብት እሾክ የሚወጋው፣ እንቅፋት የሚመታው፣ ብርድ የሚሰማው ልጅነት የሌለው ቁርበት አለበሰው፡፡ እሱ ባይረገም፣ ወደ ምድር ባይወርድ፣ በዘፍጥረት 1፡28 "ብዙ፣ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት ግዙአትም" ብሎ ነበረ አዳም ባያጠፋ ኑሮ ሰው እንዴት ሊበዛ ይችል ነበረ ቢሉ? ይኸማ መጀመሪያ አዳም በሥልጣነ እግዚአብሔር ተገኘ እንጂ ከሴት አልተገኘም፡፡ ሔዋንም ያለ ወንድ በሥልጣነ እግዚአብሔር ተገኘች እንጂ ሴትና ወንድ ተገናኝተው አልተፈጠሩም፡፡ ባይበድሉ በሥልጣነ እግዚአብሔር ወንድም በአዳም አምሳል፣ ሴቱም በሔዋን አምሳል በሥልጣነ እግዚአብሔር እየተባዛ፣ ዕፀ ሕይወትን እየበላ ሺህ ዘመን ሲሞላው መንግሥተ ሰማያትን ሊገባ ተፈጥሮ ነበር፡፡ እንግዲህ ለአዳም ዕፅዋትን ሰጠው፤ አንዱ የሚመገበው በመዓዛው ይጠግባል ሁለተኛው ሕግ ሊጠብቅለት ይችን ዕፅ አትብላ ብሎ፤ ሦስተኛው ሺህ ዘመን ኑሮ ያን ሲበላ ተሐድሶ መንግሥተ ሰማይ ሊገባ ፈጥሮት ነበር፡፡ ይኸንንም ሰሎሞን ገልጦታል "እግዚአብሔርሰ ኢገብረ ሞተ አላ ረሲአን ሰብእ አምጽእዎ በቃሎሙ ወዓርከ አምስልዎ" እግዚአብሔር ጥንቱን ሲፈጥረው ሞት እንዲሞት እንዲቀበር ወደሲኦል እንዲወርድ አልፈጠረውም፡፡ ሕጉን እንዲጠበቅ ሺህ ዘመን በሕይወት እየተቀመጠ ወደ መንግሥተ ሰማይ ሊገባ ተፈቅዶ ነበር፡፡ "ኢትብልዑ እምዕፅ" ይችን እንጨት አትብሉ ያለውን የዘነጉ አዳምና ሔዋን ሞትን፣ መቃብርን፣ ስበው ጎትተው አመጡት፡፡ "ወአርከአምስልዎ" ወዳጅ አስመሰሉት አለ ወዳጅ እንዳይለይ እንዳይለይ አደረጉት፡፡ ቀጥሎ ልጆቻቸውን፣ ይህንም ቅዱስ ጳውሎስ ገልጦታል፡፡ "ወሶበ ኵነኔ ኃጢአት ወጽአ እምላዕለ አሐዱ ብእሲ ተቀሰፈ ባቲ ኩሉ ፍጥረት" ሮሜ. 5፡12፡፡ ከአንዱ አዳም የተገኘች ኃጢአት ሁሉን /መላውን/ አደረሰች፣ ከአንድ ዛፍ በተቈረጠ ጨንገር ብዙ ሕፃናት እንደሚገረፋ ኃጢአትም ከአዳም ተገኝታ ሁሉን ያዘች፡፡ መባዛት በዘር በሩካቤ የሆነው ከመርገም በኋላ ነው፡፡ በገነት ሳሉ ወንድና ሴት መሆናቸው አይተዋወቁም፡፡ አዳም እኔ ብቻ ነኝ ሲል ረዳት እንድትሆነው ፈጠረለት እንጂ በዘር በሩካቤ ሊገናኙ አይደለም፡፡ ለምን ተባዙ አለ በሥልጣኑ ያበዛቸዋል። እግዚአብሔር ሁሉን አንድ አንድ ጊዜ ነው የተናገረው "ለታብቁል ምድር" አለ ይኸ መሬት ሁል ጊዜ ታበቅላለች፡፡ "ለያብርኁ ብርሃናት" አለ እነሆ ፀሐይና ጨረቃ፣ ከያለበት ሲያበሩ ይኖራሉ፡፡ "ለታውጽእ ባሕር ዘቦ መንፈሰ ሕይወት" ሲል አዞ፣ ጉማሬ አንድ ጊዜ ሲባዙ ይኖራሉ፡፡

  • መዝ 68á21 ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ። ወአስተዩኒ ብሒዐ ለጽምዕየ። ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ። 25/08/16 ዓ.ም ✝ በዕለቱ በ9 ሰዓት የሚሰበክ ምስባክ።

  • መዝ 21á16 ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ። ወኋለቁ ኵሎ አዕፅምትየ። ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ። 25/08/16 ዓ.ም ✝ በዕለቱ በ6 ሰዓት የሚሰበክ ምስባክ።

  • መዝ 27á17 ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን። ወአኀዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን። ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን። 25/08/16 ዓ.ም ✝ በዕለቱ በ3 ሰዓት የሚሰበክ ምስባክ