Dire Dawa Polytechnic College
Статистика- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 18
- Всего постов
- 41
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 122
- 1/48двое суток
- 139
- 1/72трое суток
- 150
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ባለፉት አምስት አመታት ከ70 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች ቋሚ የስራ እድል መፍጠር መቻሉ ተገለፀ " የድሬ ወጣቶች የስራ ባህል ሽግግር ከስራ ጠባቂነት ወደ ስራ ፈጣሪነት " በሚል መሪ-ሀሳብ በዛሬው እለት የብቃት ፕሮጀክት 4 ተኛ ዙርን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ-ግብር ተካሂዷል ። መድረኩ ወጣቶች ወደ ስራ ከመሰማራታቸው በፊት የስራ ላይ ልምምድ በማድረግ በቀጣይ ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ ወደ ስራ እንዲሰማሩ ለማስቻል ያለመ መድረክ ነው። በመርሀ-ግብሩ ላይም በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር በዚህ ፕሮጀክት ተጠቃሚ የሚሆኑ ወጣቶች በሚሰማሩበት የስራ መስክ ውጤታማ በመሆን ከራሳቸው አልፈው ቤተሰቦቻቸውንም በኢኮኖሚ በማገዝ እንዲሁም ደግሞ ከተማቸውን እና ሀገራቸውን የሚጠቅሙ ወጣቶች መሆን እንዳለባቸውም ነው ክቡር ከንቲባው በእለቱ ያስታወቁት ። የድሬዳዋ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ባለፍት ሶስት አመታት ወጣቶችን በስራ ብቁ አድርጎ ወደ ስራ እንዲሰማሩ ከማድረግ አኳያ በርካታ ስራዎችን መስራቱን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ሀርቢ ቡህ አስታውቀው በአራተኛ ዙርም ከአንድ ሺህ ስምንት መቶ በላይ የሚሆኑ ወጣቶች በተመሳሳይ ሰልጥነው ወደ ስራ እንዲሰማሩ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አድንቀዋል ። ባለፍት አምስት አመታት በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገራት ከ 70 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች ቋሚ የስራ እድል መፍጠር ከመቻሉም በላይ በሁለቱም ቴክኒክ እና ሞያ ኮሌጆች በአጫጭር እና መደበኛ ከ 30 ሺህ በላይ ወጣቶችን በማሰልጠን ለስራ ብቁ ማድረግ መቻሉንም ነው የድሬዳዋ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ሮቤል ጌታቸው በእለቱ ያስታወቁት ። አቶ ሮቤል ጌታቸው አክለውም አሁን ላይ ካለው የስራ አጥነት ቁጥር አንፃር እንዲሁም በየጊዜው እየጨመረ ካለው የወጣቶች ቁጥር አንፃር እየተፈጠረ ያለው የስራ እድል በቂ አለመሆኑን ተናግረው ይህንንም ለመፍታት ተቋሙ ዘርፈ-ብዙ ስራዎችን እየሰራ መሆኑንም ነው አቶ ሮቤል ጌታቸው ያስታወቁት ። በመድረኩም በብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ የድሬዳዋ ወጣቶች የስራ ባህል ሽግግር አመለካከትን ከመቀየር አዲስ የኢኮኖሚ ምዕራፍ እስከመክፈት በሚል ርዕስ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን ሰነዱንም መነሻ በማድረግም ውይይት ተካሂዷል ። በተያያዘ ዘገባ በእለቱ በተዘጋጀው የቴክኖሎጂ ኤግዝቢሽን ላይ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅን በመወከል ለማህበረሰቡ እንዲሁም ለኢንዱስትሪው የሚጠቅሙና ለስራ እድል ፈጠራው የሚያግዙ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ማቅረብ የተቻለ ሲሆን በዚህም ስራ ኮሌጁን ለማህበረሰቡ ማስተዋወቅ ተችሏል፡፡ ©️ DGC ነሐሴ 7/2018
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
በድሬዳዋ "ክረምትን በክህሎት" በሚል መሪ ቃል ከ600 በላይ ተማሪዎች የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና እየወሰዱ መሆኑ ተገለጸ በድሬዳዋ አስተዳደር "ክረምትን በክህሎት" በተሰኘው መርሃ-ግብር 607 የወጣት ተማሪዎች በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ዘርፍ ሥልጠና እየወሰዱ እንደሚገኝ ተገልጿል። ይህ የአጭር ጊዜ የሙያ ሥልጠና ተማሪዎች ከንድፈ-ሀሳብ ይልቅ በተግባር ላይ እንዲያተኩሩና ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር መሆኑ ተጠቁሟል።
без подписи
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ወጣቶችን ለማብቃት ከሚሰራው The Horn of Africa Youth Empowerment Academy ጋር በመተባበር ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና በዛሬው እለት አጠናቀቀ፡፡ የአፍሪካ ቀንድ ላይ የሚገኙ ወጣቶችን በተለያዩ ዘርፎች ላይ የማብቃት ስራ የሚሰራው HOAY(Horn of Africa Youth Empowerment Academy) ጋር በመተባበር በኮሌጁ ለሚገኙ ሰልጣኝ ተማሪዎች ለ3 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና በዛሬው እለት የተጠናቀቀ፡፡ በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ በመገኘት ለሰልጣኞች መልእክት ያስተላለፉትና ስልጠናውን በስኬት ላጠናቀቁ ሰልጣኞች የእውቅና ሰርተፍኬት የሰጡት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ በንግግራቸውም ለተከታታይ ሶስት ቀን ሲሰጥ የነበረው ይህ ስልጠና የኮሌጁን ሰልጣኞች የአመራርነት፣የተግባቦት እንዲሁም በራስ የመተማመንን ችሎታ እንድታዳብሩ የረዳ እንደመሆኑ መጠን የሰለጠናችሁትን ስልጠና ፍሬ በቀጣይ ወደ ተግባር ልትለውጡት ይገባል ብለዋል፡፡ ለሶሰት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ይህ ስልጠና ወጣቶችን ለአካዳሚክ፣ ለሙያዊ እና ለሲቪክ ስኬት የሚያዘጋጃቸውን ተግባራዊ የአመራርነት፣ የግንኙነት እና የሙያ ልማት ክህሎቶችን ለማስታጠቅ ያለመ ስልጠና ሲሆን የስልጠናው ተሳታፊዎችም በቡድን ስራ፣በፈጠራ እንዱሁም በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች አጠቃቀም ላይ የነበራቸውን ክፍተት መሙላት እንደቻሉ አስረድተዋል፡፡ የስልጠናው ተሳታፊዎች የሙያ ኔትወርኮቻቸውን የማስፋት፣ ክህሎቶቻቸውን ማዳበር እና በማህበረሰባቸው እና በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚረዱ ተግባራዊ ሀሳቦችን ማዳበር የሚያስችል አቅም መፍጠሪያ ስልጠና እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ሀምሌ 29/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ