tgindex
Tikvah-University

Tikvah-University

Статистика

I blog about marketing and sales Buy ads: https://telega.io/c/Tikvah_University

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
17
Всего постов
91
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Образование
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
4 618
+5 за 5 дн.
Сутки
+4
+0,09%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
405
40 постов
Вовлечённость
8,8%
к подписчикам
Постов в день
2,4
всего 91
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
343
1/48двое суток
393
1/72трое суток
423

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በመደበኛ ስርዓተ ትምህርት ውስጥ ተግባራዊ በሚደረጉ 11 የሙያ ዘርፎች ላይ የምክክር መድረክ ተካሒዷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ፣ የከተማ አስተዳደሩ የሥራና ክህሎት ቢሮ እንዲሁም የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ዲኖች በተገኙበት በሙያ ዘርፎቹ ላይ ውይይት ተካሒዷል። የሙያ ዘርፎቹን ለመተግበር የሚያስችል የስርዓተ ትምህርት፣ የተማሪ ሞጁል እና የመምህር መመሪያ ዝግጅት በትምህርት ሚኒስቴር መጠናቀቁ ተገልጿል፡፡ ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ብረታ ብረት፣ ቴክኖሎጂ፣ አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ፣ አልባሳት ቴክኖሎጂ፣ ህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ፣ ቧንቧ ሥራ፣ ሶፍትዌር ማበልጸግ፣ ሰብል አመራረት፣ ጤና ክብካቤ አገልግሎት፣ ሆቴል አገልግሎት፣ ፀጉር ሥራና ውበት አገልግሎት እንዲሁም ምግብ ዝግጅት የመደበኛ የትምህርት መርሐግብር አካል ሆነው ይሰጣሉ ተብሏል። @tikvahuniversity

  • без подписи

  • የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል። ፈተናውን ከወሰዱ 31,159 ተማሪዎች መካከል 20,618 ተማሪዎች (66.2%) ማለፋቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል። በክልሉ የመደበኛ ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ 50% እና ከዚያ በላይ ሲሆን፣ ለአርብቶ አደር እና ልዩ ድጋፍ ለሚሹ አካባቢዎች ተማሪዎች 47% እና ከዚያ በላይ መሆኑ ተገልጿል። ውጤት ለማየት 👇 https://sw.ministry.et/#/result አድራሻውን ከተጫኑ በኋላ የተማሪውን መለያ ቁጥር እና ስም በአማርኛ በማስገባት 'Check My Result' የሚለውን በመጫን ውጤትዎን ማየት ይችላሉ፡፡ @tikvahuniversity

  • የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የክረምት ሰልጣኞች ለምዝገባ ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት እሑድ ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ 👇 በኢንስቲትዩቱ ዋናው ግቢ ሬጅስትራርና አለምናይ ዳይሬክቶሬት በሚሰሩበት ተቋም ወይም ኮሌጅ አሁናዊ የቅጥር ሁኔታዎን የሚገልፁ አስፈላጊ ሰነዶች ይዘው መገኘት ይኖርብዎታል፡፡ @tikvahuniversity

  • ትምህርት ሚኒስቴር በፌደራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ ብቃት ያላቸው ተጨማሪ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን እና ርዕሰ መምህራንን አወዳድሮ ለመቅጠር የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም ማውጣጡ ይታወቃል፡፡   ለምዝገባ የተሰጠው 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጊዜ ነገ ነሐሴ 08/2018 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡     ይመዝገቡ 👇 https://sbs.moe.gov.et/directors   ይመዝገቡ 👇 https://sbs.moe.gov.et/career/teacher @tikvahuniversity

  • #ተጨማሪ   ከነሐሴ 13-15/2018 ዓ.ም በሚሰጠው የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ወቅት ተፈታኞች የብሔራዊ መታወቂያ (National ID) እንዲሁም ሲስተሙ የሚሰጠውን QR Code ያለው የፈተና መግቢያ (ስሊፕ) ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡ ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች፣ ምንም አይነት ማጣቀሻዎች እንዲሁም ባዶ ወረቀቶች፣ ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ወደ መፈተኛ ክፍል ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡ በፈተናው ወቅት ተመዛኞች በሁለቱም ክፍለ-ጊዜ (ጠዋት እና ከሰዓት) የፈተና ክፍሉን ለቀው ከመውጣታቸው በፊት አቴንዳንስ ላይ መፈረም ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተመዛኞች የመረጣችሁትን የፈተና ማዕከል ለማየት፦ https://t.me/M0H_EThiopia/3191 ተመዛኞች ስማችሁ ከተጠቀሰበት የመፈተኛ ጣቢያ (ተቋም) ውጪ በፍጹም ፈተናውን መውሰድ እንደማይፈቀድላችሁ ተገልጿል፡፡   @tikvahuniversity

  • የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና መርሐግብር   የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከነሐሴ 13-15/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል፡፡   ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም Medicine, Pharmacy, Anesthesia, Environmental Health, Human Nutrition, Emergency and Critical Care Nursing, Dental Medicine and Optometry. ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም Medical Laboratory Science, Public Health, Midwifery, Medical Radiology Technology, Pediatric and Child Health Nursing, Psychiatric Nursing, Physiotherapy and Surgical Nursing. ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም - Nursing ተፈታኞች ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አጠቃላይ ቅድመ ገለጻ (Orientation) መከታተል ይጠበቅባችኋል፡፡   @tikvahuniversity

  • без подписи

  • #AREB የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2019 የትምህርት ዘመን በክልሉ በሚገኙ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ለሚገቡ ተማሪዎች የምዝገባ ጥሪ አድርጓል፡፡ የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ አዳሪ ትምህርት ቤት - ደሴ፣ የክቡር ዶ/ር ሐዲስ አለማየሁ - ደብረማርቆስ፣ እንዲሁም አዲስ የተገነቡ የደብረ ታቦር እና የሰቆጣ አዳሪ ትምህርት ቤቶች አዲስ ተማሪዎችን ተቀብለው ለማስተማር ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በመሆኑም በ2018 ዓ.ም በክልሉ ከሚገኙ የመንግሥት እንዲሁም የግል ትምህርት ቤቶች ተምራችሁ፣ ክልላዊ ፈተና የወሰዳችሁና የተቀመጡ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተማሪዎች በትምህርት ቤቶቹ ምዝገባ እንድታደርጉ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ጥሪ አስተላልፏል፡፡ መሰፈርቶች ● የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና አማካይ ውጤት ለሴቶች 80% እና ለወንዶች 82% ● የ7ኛ እና የ8ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት አማካይ ውጤት ለሴቶች 83% እና ለወንዶች 85% የምዝገባ ጊዜ 👇 ከነሐሴ 06-15/2018 ዓ.ም የምዝገባ ቦታ 👇 በአማራ ክልል በሚገኙ በሁሉም የወረዳ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤቶች የመግቢያ ፈተና በዞን ዋና ከተሞች ነሐሴ 25/ 2018 ዓ.ም ይሰጣል ተብሏል፡፡ (ተጨማሪ መረጃ ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ፡፡) @tikvahuniversity

  • ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ባለሙያዎችን ሙያዊ አቅም ለማሳደግ የሚረዱ ተንቀሳቃሽ የአይሲቲ ቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን ለሚመለከታቸው ተቋማት ማስረከቡን ገልጿል። ሚኒስቴሩ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚሠሩ መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎችን ሙያዊ አቅም ለማሳደግ የሚረዳ የአይሲቲ ቴክኖሎጂ ፕሮጀክትን ወደ ተግባር ለማስገባት እየሠራ መሆኑን በሚኒስቴሩ በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት ተ/መሪ ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሮ አሰግድ ምሬሳ ገልፀዋል። ፕሮጀክቱ ከተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (UNESCO) እና ከጃፓን መንግሥት ጋር በመተባበር የሚተገበር ነው፡፡ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች 35 የሚደርሱ የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች እና በመምህራን ትምህርት ላይ ትኩረት አድርገው እየሠሩ ያሉ አምስት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች መሆናቸው ተጠቁሟል። @tikvahuniversity

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • 5ኛው ዙር የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተጀምሯል፡፡ የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ፕሮግራሙ ከዚህ ቀደም በሁለት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ይሰጥ የነበረ ሲሆን፣ ዘንድሮ በሰባት ማዕከላት መሰጠት ጀምሯል፡፡ ስልጠናው በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በባሕር ዳር፣ በሐረማያ፣ በጅማ፣ በደብረ ብርሃን እና በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም በኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር (ኢመደአ) የታለንት ማዕከል በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡ ለዘንድሮው መርሐግብር ከ14 ሺህ በላይ ወጣቶች ምዝገባ በማድረግ መሳተፋቸው ተገልጿል፡፡ @tikvahuniversity

  • በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተለያዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡና በሳይንስ ትምህርቶች እና በፈጠራ ልዩ ተሰጥኦ ላላቸው 40 ተማሪዎች የተዘጋጀ ስልጠና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እየተሰጠ ነው፡፡ ስልጠናው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት እንዲሁም ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው፡፡ ለ45 ቀናት የሚቆየው የንድፈ-ሐሳብ እና የተግባር ስልጠናው፤ በአስትሮኖሚ፣ በሮኬት ሳይንስ፣ በድሮን (UAV)፣ በጂአይኤስ እና በሳታላይት ሲስተም ላይ ትኩረተት ያደርጋል፡፡ ስልጠናው በክልሉ ባሉ አራቱም ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡ @tikvahuniversity

  • ትምህርት ሚኒስቴር በፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ9ኛ እና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ በነፃ ማስተማር ይፈልጋል። 🔔 ሙሉ የትምህርት ክፍያ ሽፋን እንዲሁም ነፃ የመኝታ እና የምግብ አገልግሎት በነፃ ትምህርት ዕድሉ ይሰጣል፡፡ 9ኛ ክፍል ብቻ የሚቀበሉ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ● አርባ ምንጭ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ● ድሬዳዋ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ● አሶሳ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ● ባህር ዳር ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት 9ኛ እና 10ኛ ክፍል የሚቀበሉ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ● ቡኢ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ● ጅግጅጋ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ● ጋምቤላ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ● ወሊሶ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ● ቦንጋ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ለ9ኛ ክፍል የመመዝገቢያ መስፈርቶች ● በ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና 85 እና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች ● በሂሳብ እና እንግሊዝኛ የትምህርት ዓይነቶች 80 እና በላይያመጣ/ያመጣች ● ጥሩ ስነ-ምግባር ያለው/ያላት ለ10ኛ ክፍል የመመዝገቢያ መስፈርቶች ● በ2017 ዓ.ም በ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና 70 እና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች ● በ9ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት 85 እና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች ● በሂሳብ እና እንግሊዝኛ የትምህርት ዓይነት 80 እና በላይ ያመጣ/ያመጣች ● ጥሩ ስነ-ምግባር ያለው/ያላት ኦንላይን ይመዝገቡ 👇 https://sbs.moe.gov.et/apply የመመዝገቢያ ጊዜ 👇 እስከ ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም ለፈተና የሚቀርቡ ተማሪዎች ዝርዝር እና የፈተና ጊዜ ወደፊት ይገለፃል፡፡ የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ ተማሪዎች በሚደቡበት ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ለመማር ፈቃደኛ የሆኑ መሆን አለባቸው ተብሏል፡፡ @tikvahuniversity

  • #ጥቆማ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ ትምህርት ቤት (ASTU-Community School) ከቅድመ 1ኛ ደረጃ እስከ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የ2019 የትምህርት ዘመን የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 06-15/2018 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል፡፡ (የክፍያ ሁኔታ እና ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ፡፡) @tikvahuniversity

  • #ጥቆማ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ክልላዊ ፈተና ተፈትናችሁ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎችን ለ2019 ዓ.ም ባለው ክፍት ቦታ አወዳድሮ መቀበል ይፈልጋል፡፡ መስፈርቶች፦ ➻ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና አመካይ ውጤት ለወንድ 83% ፤ ለሴት 80% ➻ የ7ኛ-8ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት አማካይ ውጤት ለወንድ 85% ፤ ለሴት 75% ➻ የ7ኛ-8ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት የእንግሊዘኛ እና ሒሳብ ትምህርት አይነቶች አማካይ ውጤት ለወንድ 75% ፤ ለሴት 70% ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦ ➻ የ8ኛ ክፍል ውጤት ሰርቲፊኬት ➻ የ7ኛ-8ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት የምዝገባ ቀናት፦ ከነሐሴ 05-12/2018 ዓ.ም ባሉት የሥራ ቀናት የምዝገባ ቦታ፦ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን እና ቦታ ወደፊት ይገለጻል ተብሏል። (ትምህርት ቤቱ አዳሪ ትምህርት ቤት አይደለም።) @tikvahuniversity

  • без подписи

  • #ጥቆማ   የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2019 የትምህርት ዘመን በምስራቅ ጎህ የሳይንስ ልህቀት ማዕከል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ይፈልጋል፡፡   በሳይንስ ልህቀት ትምህርት ቤቱ ለመማር የምትፈልጉ ተማሪዎች እስከ ነሐሴ 07/2018 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ቢሮው ገልጿል፡፡   የመመዝገቢያ ሊንክ 👇 https://bs.ministry.et   (ዝርዝር መስፈርቶችን ከላይ ከተያያዙት የቢሮው ማስታወቂያ ይመልከቱ፡፡)   @tikvahuniversity