tgindex
Ethiopia Federal Police የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ

Ethiopia Federal Police የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ

Статистика

ተልዕኮ - ወንጀልን አስቀድሞ መከላከል እንዲሁም ተፈፅሞ ሲገኝ መመርመር የሚያስችል ሙያዊ ብቃት ያለው የፖሊስ ተቋምን በመገንባት በሀገሪቱ ሰላምን፣ደህንነትን እና የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ነው፡፡ መሪ ቃል - በጀግንነት መጠበቅ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!

Последний пост
19 мая
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
am
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
14 134
−3 за 4 дн.
Сутки
−2
−0,01%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
8 517
20 постов
Вовлечённость
60,3%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 19 мая11,1 тыс12

    видео или голосовое, без подписи

  • 19 мая10,9 тыс12

    видео или голосовое, без подписи

  • 19 мая10,8 тыс12

    видео или голосовое, без подписи

  • 19 мая9 73619612

    ‎ የኦሜድላ ስፖርት ክለብን ወደ ቀድሞ ዝናው ለመመለስ ከክለቡ የቦርድ አመራሮች፣ ከቀድሞ አትሌቶችና ታዋቂ ስፖርተኞች ጋር ውይይት ተካሄደ ‎አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢ.ፌ.ፖ.ሚ)፦ ‎​የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሠራዊት ግንባታ ዋና መምሪያ ኃላፊ ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ደቻሳ ቢቲማ ኦሜድላ ስፖርት ትልቅ ስምና ረጅም ታሪክ ያለው፤ በርካታ ስፖርተኞችን ያፈራ ታሪካዊ ክለብ በመሆኑ ከውጤት ማጣት ችግር ወጥቶ ወደ ቀደመ ከፍታና ዝናው እንዲመለስ በከፍተኛ ትኩረት እየተሠራ ነው ብለዋል። በዚህም ሂደት በሁሉም ዘርፍ የምትገኙ የስፖርት ቤተሰቦች ከጎናችን እንድትሆኑ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። ‎ ‎የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ክቡር ረዳት ኮሚሽነር እሸቱ ፊጣ በበኩላቸው በኦሜድላ የስፖርት ክለብ የሚነሱ የስፖርት ማቴርያል ችግሮች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳና ሌሎች ለክለቡ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን በማሟላት ክለቡን በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል። ‎ ‎የኦሜድላ ስፖርት የክለብ ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ የኦሜድላ ስፖርት ክለብ ታላላቅ አትሌቶችን ያፈራ፤ የሀገራችንን ሰንደቅ ዓላማ በዓለም አደባባይ ከፍ አድርገው ያውለበለቡ አትሌቶችን ለሀገር ያበረከተ ክለብ መሆኑን ተናግረዋል። አያይዘውም ይህ የሀገር ባለውለታ የስፖርት ክለብ ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ በፋይናንስ፣ በአስተዳደራዊ ጉዳዮችና በሌሎች ምክንያቶች በውጤታማነቱ እንዳይቀጥልና በስፖርቱ ዘርፍ የነበረው ስምና ዝናው እየቀነሰ መምጣቱን ገልፀው አሁን ላይ ችግሩን በመቅረፍ ወደ ቀደመ ክብሩ እንዲመለስ እየተሠራ ያለው የለውጥ ሥራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

  • 18 мая9 8235

    видео или голосовое, без подписи

  • 18 мая9 8265

    видео или голосовое, без подписи

  • 18 мая7 516565

    የዲጂታል ፋይናንስ ወንጀሎችን ለመመርመር የሚያስችል ስልጠና ተሰጠ አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢ.ፌ.ፖ.ሚ)፡- የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የዲጂታል ፋይናንስ ወንጀሎችን መመርመር የሚያስችል ስልጠና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ መርማሪዎችና የምርመራ ኃላፊዎች በጠቅላይ መምሪያው ቢሮ ሰጥቷል። በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የታክቲክ ወንጀሎች ምርመራ ምክትል ዋና መምሪያ ኃላፊ ክብር ረዳት ኮሚሽነር ከተማ ደባልቄ ስልጠናውን ባስጀመሩበት ወቅት ባደረጉት ንግግር በሀገራችን በ2030 ሁሉም አገልግሎቶች ዲጂታላይዝድ እንዲሆኑ ታቅዶ እየተሠራ እንደሆነ አስታውሰው አንዳንድ ግለሰቦች ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ያገኙትን ዕውቀት ላስተማራቸው ሕዝብ ጥቅም ከማዋል ይልቅ የዲጂታል ፋይናንስ ወንጀሎችን በመፈጸም በህዝብ ላይ ጉዳት እያደረሱ እንደሚገኙ ገልፀዋል። ግለሰቦቹ ዲጂታል የፋይናንስ ወንጀሎቹን የሚፈፅሙት በዜጎች የግል ስልክ ላይ በመደወል፣ ስልካቸውን በመስረቅ እና የተለያዩ መልዕክቶችን በመላክ ሲሆን በዚህ ሕገወጥ ተግባር በተለያዩ ጊዜያት በርካታ ገንዘቦችን መዝረፋቸውንና ወንጀሉ ከዕለት ወደዕለት እየጨመረ የመጣ የወንጀል አይነት በመሆኑ ክቡር ረዳት ኮሚሽነር ከተማ ደባልቄ ተናግረዋል። አያይዘውም ችግሩን ለመፍታት በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ተነሳሽነት የምርመራ ሥራው ተከፋፍሎ እንዲሠራ በውክልና ለአዲስ አበባ ፖሊስ እንዲሰጥ በመወሰናቸው ምርመራውን ለማስጀመር ስልጠና መሰጠቱን ገልፀዋል።

  • 16 мая8 2574

    видео или голосовое, без подписи

  • 16 мая8 8464

    видео или голосовое, без подписи

  • 16 мая8 7954

    видео или голосовое, без подписи

  • 16 мая6 904544

    የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኢንስፔክሽንና ስታንዳርድ መምሪያ ለባለሙያዎች የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ማሳደጊያ ሥልጠና ሰጠ ‎ ‎አዲስ አበባ፣ ግንቦት 07 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢ.ፌ.ፖ.ሚ)፦ ‎ ‎የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሠራዊት ግንባታ ዋና መምሪያ ኃላፊ ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ደቻሳ ቢቲማ በሥልጠናው ላይ በሰጡት የሥራ መመሪያ ዋና መምሪያው ከተቋቋመበት ዓላማ አንፃር የሠራዊቱን ሁለንተናዊ አቅም በመገንባትና የሥራ አፈጻጸምን በማሳደግ ተቋማዊ ተልዕኮዎች ውጤታማ እንዲሆኑ በቁርጠኝነት እየሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ሥልጠናዎች የአቅም ውስንነቶችን ለመቅረፍ የሚዘጋጁ በመሆናቸው ባለሙያዎች የቀሰሙትን ዕውቀት ተጠቅመው ሙያዊ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባም ክቡር ምክትል ኮሚሽነሩ አሳስበዋል። ‎ ‎የኢንስፔክሽንና ስታንዳርድ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር እስከዳር ብርሃን በበኩላቸው መምሪያው ተቋማዊ ስታንዳርዶችን በማዘጋጀትና የኢንስፔክሽን ሥራዎችን በማካሄድ ወጥ የሆነ የአሠራር ሥርዓት እንዲኖር በትኩረት እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል። አያይዘውም በቅርቡ በተቋሙ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች የተካሄደውን የባለሙያ ምደባ መሠረት በማድረግ በአመራሩና በፈጻሚው መካከል የተቀራረበ አቅም ለመፍጠርና ተቋማዊ ለውጡን ለማስቀጠል ሥልጠናው መሰጠቱን ጠቁመዋል። ‎ ‎ሥልጠናውን የሰጡት በኢንስፔክሽንና ስታንዳርድ መምሪያ የተቋማዊ ለውጥ ድጋፍና ክትትል ሥራዎች ዋና ክፍል ኃላፊ ኮማንደር አንዷለም ሽባባው ተቋሙ የጀመረውን የሪፎርም ጉዞ ይበልጥ ለማሳካትና የሕዝብን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ተልዕኮን በብቃት ለመወጣት ሥልጠናው ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ገልጸዋል።

  • 15 мая8 2674

    видео или голосовое, без подписи

  • 15 мая8 5944

    видео или голосовое, без подписи

  • 15 мая7 2054

    видео или голосовое, без подписи

  • 15 мая9 1684

    видео или голосовое, без подписи

  • 15 мая6 089424

    ‎ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በአድማ መከላከልና መቆጣጠር ያሰለጠነውን የፖሊስ ኃይል አስመረቀ ‎ ‎አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢ.ፌ.ፖ.ሚ)፦ ‎​በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው የሥራ መመሪያ የሰጡት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፤ ጠንካራ ሀገር እንዲኖር ጠንካራ መንግሥት እንደሚያስፈልግ ገልጸው፤ ጠንካራ መንግሥት እንዲኖር ደግሞ የሀገሪቱን ሕግና ሥርዓት የሚያስከብር፣ በቴክኖሎጂ የዘመነ፣ በሰው ኃይል የሰለጠነ፣ በሥነ-ምግባር የታነፀና ሙያዊ ብቃቱ የተረጋገጠ ፖሊስ መገንባት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። ‎ ‎​ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል አያይዘውም የአድማ መከላከልና መቆጣጠር በዛሬው ዕለት ባሳየው ከፍተኛ ብቃት የታየባቸው ልዩ ልዩ ወታደራዊ ትርዒቶች ሠራዊቱ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን የታጠቀ ብቻ ሳይሆን በቀጥታ ከዕዝ እና ቁጥጥር ማዕከል (Command and Control Center) ጋር የተገናኙ ድሮኖችን የታጠቀ መሆኑን ገልጸው፤ ይህም በሁከትና ብጥብጥ ወቅት ሰላማዊውን ዜጋና ሁከት ፈጣሪውን ለይቶ ለማወቅ እና ለፖሊስ ሠራዊቱ መረጃ ለመስጠት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል። ‎ ‎​የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ በበኩላቸው ዛሬ ያስመረቅነው የአድማ መከላከልና መቆጣጠር ፖሊስ ኃይላችን በየትኛውም ስፍራና በማንኛውም ጊዜ ከሀገራችን ሰላምና ደህንነት ጋር የተገናኙ ወይም በዜጎች ላይ የሚቃጡ ሕገ-ወጥ ተግባራት ሲኖሩ ዘመናዊ በሆነ አኳኋን አመጾችንና ሁከቶችን መቆጣጠር የሚያስችል ሁለንተናዊ ስልጠና የወሰዱ መሆኑን ተናግረዋል። ‎

  • 14 мая6 68541

    የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለፅንፈኛና ሽብር ቡድኖች ሊደርስ የነበረ በርካታ ተተኳሽ ጥይት ከነ-ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገለፀ አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢ.ፌ.ፖ.ሚ)፦የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለፅንፈኛና ሽብር ቡድኖች ሊደርስ የነበረ በርካታ ተተኳሽ ጥይት ከነ-ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገልጿል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም ከክልል የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ባደረገው ጥብቅ ክትትል፣ መነሻውን ከአማራ ክልል አዊ ዞን ጃዊ ወረዳ ያደረገ የጦር መሣሪያ ዝውውርን ማክሸፉን አስታውቋል። ሁለት ተጠርጣሪዎች ኮድ 3 ኢ.ት - 07453 በሆነ የማርቸድስ የጭነት ተሽከርካሪ 4 ሺህ 883 የብሬን እና 2 ሺህ 464 የክላሽንኮቭ ተተኳሽ፤ በድምሩ 7 ሺህ 347 ጥይት ከለውዝ ጋር ቀላቅለው በመጫን፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፓዊ ከተማ አድርገው ወደ አማራ ክልል ቻግኒ ከተማ በማስገባት ለፅንፈኛና ለሽብር ቡድኖች ለማድረስ ሲሞክሩ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል። በወንጀል ድርጊቱ ላይ በተሳተፉ ተጠርጣሪዎች ላይ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ አስፈላጊውን ምርመራ እያደረገ ይገኛል። የፀጥታ አካላት መሰል የሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውሮችን በመከላከልና የክልሉን ሰላምና ደህንነት ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ወንጀለኞችን በማጋለጥ ረገድ ያላቸውን ቁርጠኝነት አጠናክረው እየሰሩ እንደሚገኙ የተገለፀ ሲሆን የጸጥታ መዋቅሩ ሥራ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ህብረተሰቡ እያደረገ ያለውን ሁለንተናዊ ድጋፍና ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል።

  • 13 мая7 5893

    видео или голосовое, без подписи

  • 13 мая8 0503

    видео или голосовое, без подписи

  • 13 мая6 136483

    የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በሀገራችን ሰላም ዙሪያ በትብብር አብሮ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢ.ፌ.ፖ.ሚ)፡- የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በስምምነቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር የፖሊስ ዋና ስራው ወንጀልን መከላከል በመሆኑ ወንጀልን ለመከላከል ደግሞ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ማሳተፍ አስፈላጊ እንደሆነ አንስተው ለህዝባችን እንደ ትልቅ ምሰሶ ከሚታዩት አንዱ የማህበረሰብ ክፍል የሃይማኖት ተቋማት መሆናቸውን ገልፀዋል። ክብር ኮሚሽነር ጀነራል አያይዘውም የሃይማኖት ተቋማት ላይ ምንም አይነት ልዩነት ሳናደርግ ሁሉንም እንደ ሃይማኖት አባቶቻችን አክብረን ከሃይማኖት ተቋማት ጋር ተቀራርበን ከሰራን በወንጀል መከላከል ሥራችን ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት፣ ችግሮችን ተቀራርቦ ለመፍታት፣ ለሀገር ሰላም በሚደረገው ድካም በጋራ ለመቆም ስለሚረዳ እንደነዚህ አይነት ትብብሮች የፀጥታ ስራዎችን ያቀላል ብለዋል፡፡ ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ከሃይመኖት ጋር ተያይዘው የሚነሱ የተለያዩ ችግሮችን ለማስቀረት እና በአጠቃላይ ሀገራችን ሰላሟ ተከብሮ፣ ልማቷ በልፅጎ፣ ህዝባችን ከሀገራችን በሁለንተናዊ መልኩ መጠቀም እንዲችል ዋናው መሰረት ሰላም ስለሆነ ለዚህ ደግሞ የሃይማኖት ተቋማት ትልቅ አጋዥ እና ባለቤት መሆናቸውን ተናግረዋል። ጉባኤው የቤተ-እምነቶች የጋራ ውክልና ያለው ጉባኤ ከመሆኑ አንጻር የሰላም ጉዳይ ትልቁ አጀንዳ አድርጎ ችግሮችን ከመፍታት አኳያ ዘላቂ ሰላም በሀገሪቱ እንዲሰፍን ከማስቻሉም በላይ በተለይ ሃይማኖትን ሽፋን ያደረጉ ግጭቶችና ብሽሽቆች የሚስተዋሉ በመሆኑ ይህንን ከመፍታት አኳያ ሰነዱ የበለጠ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል።