Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS
СтатистикаEthiopian Pharmaceuticals Supply Service , EPSS, is a legal entity established under the law of the Federal Democratic Republic of Ethiopia Government to overcome the problems and assure uninterrupted supply of pharmaceuticals to the public.
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 12:41
- Постов за неделю
- 6
- Всего постов
- 27
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 471
- 1/48двое суток
- 1 685
- 1/72трое суток
- 1 818
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
አገልግሎቱ የቅርንጫፎቹን የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ገመገመ። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ከነሐሴ 4 ቀን ጀምሮ ሲያካሂድ የቆየውን የ2018 በጀት ዓመት የቅርንጫፎች የተቀናጀ የሥራ አፈጻጸም ምዘና አጠናቀቀ። የምዘናው ማጠናቀቂያ ፕሮግራም ከሁሉም ቅርንጫፍ ሠራተኞች ጋር በቪዲዮ ኮንፈረንስ (Town Hall Meeting) በተደረገ ውይይት ተካሂዷል። የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት፤ ምዘናው በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለመገምገም፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመቀመር፣ ክፍተቶችን ለመለየት እና የሪፖርቶችን ተጨባጭነት ለማረጋገጥ ያስቻለ ነው ሲሉ ገልፀዋል። አገልግሎቱ ከባለፈው ዓመት አንጻር የተሻለ የህክምና ግብአቶች የማቅረብ አፈጻጸም ማስመዝገቡን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ይህም የመላው ሠራተኞች የጋራ ጥረት ድምር ውጤት መሆኑን ገልጸዋል። ቅርንጫፎችም ለማህበረሰቡ መሠረታዊ መድኃኒቶችን የምናደርስበት ማእከሎች በመሆናቸው ሀገራዊ ተልእኮቻቸው ለጤና ስረዓቱ መጠናከር ትልቅ ነው ብለዋል። አክለውም በ2019 በጀት ዓመት በምዘናው የተለዩ ክፍተቶችን በማረም የዲጂታል አሠራሮችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ባለፉት አራት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የቅርጫፎች ግምገማ ከ60 በላይ ገምጋሚዎች የተሳተፉ ሲሆን በመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት ላይ የሚያተኩሩ 100 መመዘኛ ቸክ ሊስት መጠይቆች ተዘጋጅቶ በጋራ መግባባት ተጠናቋል። #ማገልገል ክብር ነው ሠላም ይደግ
без подписи
без подписи
без подписи
በአገልግሎቱ ሁሉም ቅርንጫፎች የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ምዘና እየተካሄደ ነው ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት አገልግሎት በሁሉም ቅርንጫፎች የ2018 በጀት ዓመት የተቀናጀ የሥራ አፈጻጸም ምዘና (Performance Evaluation) ማካሄድ የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ኦረንቴሽን ለተሳታፊዎች ተሰጠ። ምዘናውን ከዋናው መሥሪያ ቤት የተውጣጡ የማኔጅመንት አባላትና ባለሙያዎች የሚያካሂዱት ይሆናል። የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ በዙም (Zoom) ባስተላለፉት መልዕክት፤ ግምገማው ከነሐሴ 4 እስከ 8/2018 ዓ.ም. በሁሉም ቅርንጫፎች እንደሚካሄድ ገልጸዋል። በሂደቱም የመጋዘን አሠራር፣ የቆጠራ ትክክለኛነት፣ የጥራት ቁጥጥር፣ የፋይናንስና የሰው ሀብት አስተዳደርን ጨምሮ በሌሎችም ቁልፍ ተግባራት ላይ ሰፊ ምዘና እንደሚደረግ ተናግረዋል። ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፣ ምዘናው ስትራቴጂካዊ ችግሮችን በጥልቀት በመለየት ዘላቂ መፍትሔ ለማስቀመጥ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን ጠቁመው፤ እያንዳንዱ ተሳታፊ በተመደበበት ቅርንጫፍ ሥራውን በጥንቃቄ፣ በተቀናጀ እና ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ እንዲያከናውን አደራ ብለዋል። በመድረኩም በግምገማው ትኩረት በሚሹ ዋና ዋና ዘርፎች እና ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ዲጂታል ቼክሊስት አጠቃቀም ላይ ለተሳታፊዎች ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል። #ማገልገል_ክብር_ነው ሰላም ይደግ
የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በባህር ዳር ዘመናዊ የሕፃናት ማቆያ ማዕከል አስመረቀ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የባህር ዳር ቅርንጫፍ የሠራተኞችን የሥራና የቤተሰብ ሕይወት ለማመጣጠን እንዲሁም የሕፃናትን ደህንነትና እንክብካቤ ለማረጋገጥ ያስገነባውን ዘመናዊ የሕፃናት ማቆያና መንከባከቢያ ማዕከል በይፋ አስመረቀ። በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የጤና ሚኒስቴር ዴኤታዎች ክብርት ፍሬህይወት አበበ እና ክብርት ሰሀርላ አብዱላሂ፣ የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ፣ የሴቶችና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ዓለምፀሐይ ዳታን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ፣ ማዕከሉ ሠራተኞች ልጆቻቸውን በአቅራቢያቸው በደህንነት እያስቀመጡ ሥራቸውን በተሻለ ትኩረትና እፎይታ እንዲያከናውኑ የሚያስችል ነው ብለዋል። አክለውም ፕሮጀክቱ መንግሥት ለሴቶች፣ ሕፃናትና ቤተሰብ ምቹ የሥራ አካባቢ ለመፍጠር የያዘውን አቅጣጫ በተግባር ያሳየ መሆኑን በመግለጽ፣ ለቅርንጫፉ ሠራተኞች "እንኳን ደስ አላችሁ" ብለዋል። በሥነ-ሥርዓቱ ማጠቃለያ የክብር እንግዶቹ በቅርንጫፉ ግቢ ውስጥ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በማከናወን ለአካባቢ ጥበቃና ለአረንጓዴ ልማት ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል። በሌላ በኩል የባህር ዳር ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ አምሳሉ ጫኔ፣ ቅርንጫፉ በበጀት ዓመቱ የ7.8 ቢሊዮን ብር መድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶችን ማሰራጨቱን ይፋ አድርገዋል። ሥራ አስኪያጁ ለተገኘው ውጤት ከዋናው መሥሪያ ቤትና ከአጋር ድርጅቶች ከፍተኛ ድጋፍ እንደነበረ ጠቅሰው፣ ለክብር እንግዶችና ለፕሮጀክቱ ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል። መረጃው ከቅርንጫፉ የህዝብ ግንኙነት ተወካይ ከአቶ ሀይማኖት አሰፍ የተገኘ ነው። #ማገልገልክብር ነው!
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
አቶ ታሪኩ በላቸው በአብክመ ጤና ቢሮ ላበረከቱት ላቅ ያለ አገልግሎት የእውቅና የምስክር ወረቀት እና ሽልማት ተበረከተላቸው ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት (አብክመ) ርዕሰ መስተዳድር እና ጤና ቢሮ ለኢትዮጵያ መድኃኂት አቅራቢ አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር ለሆኑት ለአቶ ታሪኩ በላቸው የላቀ አገልግሎት ዕውቅና መስጠቱን ሠሞኑን ባህር ዳር በተደረገ ስነ ሰርዓት ላይ አስታወቀ። አቶ ታሪኩ በላቻው ከታህሳስ ወር 2009 ዓ.ም እስከ ጥቅምት ወር 2014 ዓ.ም ድረስ በክልሉ ጤና ቢሮ በምክትል ቢሮ ኃላፊነት ተመድበው ላበረከቱት ላቅ ያለ አገልግሎት፣ ለአመራር ብቃታቸው እንዲሁም ለዘርፉ ዕድገት ላደረጉት አስተዋጽኦ ነው ይህ የምስክር ወረቀት የተሰጣቸው። የእውቅና ሽልማቹ ከአብክመ መስተዳድር ሀላፊዎች አሁን ላይ በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ታሪኩ በላቻው በተደረገላቸው አቀባበልና ሽልማት ና ዕውቅና የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል። አቶ ታሪኩ በሰጡት አስተያየት፦ "የአማራ ክልል ጤና ቢሮ እድሳትና ማስፋፊያ ለሥራ ኃላፊዎችና ለሠራተኞቹ ምቹ የሥራ ከባቢ በመፍጠርና በቴክኖሎጂ ቢሮውን በማዘመን ለተሠራው እጅግ ድንቅ ሥራ የሚያስደምም ነው" ብለዋል። አክለውም፦ "በተለያዩ ጊዜያት ቢሮውን ለመራን ሰዎች ለነበረን አስተዋፅኦ የተሰጠን ዕውቅናና ሽልማት የሚያኮራ ነበረ፤ ከልብ እናመሰግናለን! ይህ ትልቅ ከፍታ አሁን ያለው አመራርና ማኔጅመንት እንዲሁም የመላው ሠራተኞች ቅንጅትና ጥንካሬ ውጤት ነው፤ በርቱ!" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። #ማገልገል ክብር ነው!
без подписи
без подписи
без подписи