Ethiopian Public Health Institute | የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
СтатистикаEPHI one of the oldest and known public health institutes in Africa. It is open 24/7 for public health emergency management through Emergency Operation Center. For any information and help call 8335 or send us a message through ephieoc@gmail.com
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 21:39
- Постов за неделю
- 38
- Всего постов
- 53
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 664
- 1/48двое суток
- 1 906
- 1/72трое суток
- 2 056
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የጤና መረጃን አስመልክቶ ከሕብረተሰቡ የሚሰጡ ጥቆማዎችን ተገቢ ምላሽ ለመስጠት ወቅታዊ የጤና መረጃዎችን ተደራሽነት ማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ Health information sharing and timely responses to community feedback is said to be crucial ------------------------------ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የቅድመ ማስጠንቀቂያና ቅኝት ዳይሬክቶሬት የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ስጋት ተግባቦትና የማህበረሰብ ተሳትፎ ዲቪዥን ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የሕብረተሰብ ጤና አደጋ መከላከልና ምላሽ አሰጣጥ ላይ ያለውን የማሕበረሰብ አቀፍ የዲጂታል የመረጃ ልውውጥ ሥርዓትን ለማሻሻል የሚያስችል የጋራ መልዕክት መለዋወጫ ስልት ለማዘጋጀት ከነሀሴ 6 እስከ 8/2018 ዓ.ም በአዳማ ከተማ አውደ ጥናት አካሄደ፡፡ የአውደ ጥናቱ ዋና ዓላማ የመንግስት ተቋማትን፣ የማህበረሰብ ተወካዮችን እና አጋሮችን በማሳተፍ አገልግሎት የሚሰጥበትን ሞዴል በጋራ በመፍጠር፣ የተቀናጀ እና ፈጣን የአደጋ ስጋት መረጃ መልዕክት መለዋወጫ ደረጃዎችን የያዘ የመተግበሪያ ፍኖተ-ካርታ (roadmap) ለማዘጋጀት ያለመ ነው። ዶ/ር መልካሙ አብቴ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር የምክክር አውደ ጥናቱን የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት እንደተናገሩት የሚዘጋጀው የሕብረተሰብ ጤና አደጋ መረጃዎችን ለማሻሻል የሚያስችል የመልዕክት መለዋወጫ ፍኖተ ካርታ ኢንስቲትዩታችን ቀደም ሲል በተቋሙ እንዲለሙ በማድረግ ወደ ትግበራ ከገቡ ዲጅታል መተግበሪያዎች ጋር ተመጋጋቢ እንዲሆን በማደረግ፣ በተለይም ማህበረሰቡ የሚሰጣቸዉን ጥቆማዎችና አስተያየቶች በፍጥነት ምላሽ ለመስጠትና ወቅቱ በሚጠይቀዉ ደረጃ የጤና መረጃዎችን ተደራሽ ለማድረግ ወሳኝ ሚና የሚጫወት መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡ አቶ ይበይን ሙሉአልም የኢንስቲትዩቱ የቅድመ ማስጠንቀቂያና ቅኝት ዳይሬክቶሬት ተወካይ አውደ ጥናቱን አስመልክቶ ማብራሪ ሰጥተዋል፡፡ የዩኒሴፍ ኢትዮጵያ የድንገተኛ አደጋዎች እና ክትባት ማናጀር ዶ/ር ሻሂራ ማልም በበኩላቸው የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ አመራሮች የመረጃ ልውውጥን ለማሻሻል የሰጡት ልዩ ትኩረት አድናቆት የሚገባው መሆኑን ገልጸው፣ ዩኒሴፍ የሚያበለጽገውን የማሕበረሰብ አቀፍ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ማዕከል ያደረገ የመረጃ ልውውጥ እና ግብረመልስ ሥርዓት በአጭር ጊዜ ወደ ትግበራ እንዲለወጥ ለማደረግ ለሚደረገው ጥረት አስፈላጊውን ድጋፍ በመስጠት በትኩረት እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል። ወቅታዊ መረጃ ልውውጥ ስረዓት ላይ የተደረገ የጥናት ውጤት በመድረኩ ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን በጥናቱ ውጤት መሰረት ዲዛይን ተዘጋጅቶ፣ በትግበራ ወቅት ስለሚኖረው ውጤታማነት የመረጃ ልውውጥ ስርዓቱን ሙከራ ተደርጎ ወደ ትግበራ ለመለወጥ የ90 ቀናት የትግበራ ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀት አውደ-ጥናቱ ተጠናቋል፡፡ https://ephi.gov.et/10035-2/ https://x.com/i/status/2088625596435714331 Health information sharing and timely responses to community feedback is said to be crucial ---------------------------- It was stated that ensuring access to up-to-date health information is crucial in order to provide appropriate responses to public comments and rumours related to health. The Ethiopia Health Society’s Community Health Risk Communication and Community Participation Directorate, in collaboration with UNICEF Ethiopia, conducted a workshop from August 6 to 8 2026 to develop a joint engagement strategy and prepare a roadmap for improving the community-wide digital information exchange system related to preventing and responding to community health risks. The main objective of the workshop was to create, through the participation of government institutions, community representatives, and partners, an integrated and fast risk-information message exchange roadmap/application framework that includes steps for implementation. Dr. Melkamu Abte, the Deputy Director General of the Institute, stated during the opening remarks of the workshop that the message-exchange roadmap to enhance community health risk communications will be made compatible with digital applications already underway or planned within the Institute, and that it will play an important role in quickly responding to the advice and comments the community provides, as well as making health information accessible at the appropriate time and in line with what is required. Yibeyin Mulualem, a representative from the Institute’s Early Warning and Surveillance Directorate, also provided explanations regarding the workshop. The study findings conducted on the existing information sharing system were presented at the forum and discussed. Based on the study results, the design was prepared, and a 90-day implementation roadmap was developed to transition the information exchange system into practice by testing its effectiveness during implementation. https://ephi.gov.et/10035-2/ https://x.com/i/status/2088625596435714331
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጤና ዘርፍ ሪፎርምን በተግባር ለማስፈጸም የጋራ ግንዛቤ ፈጠረ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጤና ዘርፍ ሪፎርምን በተመለከተ ለኢንስቲትዩቱ አመራርና ሠራተኞች የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል። በመድረኩ የጤና ዘርፍ ሪፎርሙ የዝግጅት፣ የትግበራ፣ የማፅናትና የኢንተርፕሬነርሺፕ የሥራ አቅጣጫዎች ላይ በማተኮር የጤና ሥርዓቱን የበለጠ ፍትሐዊ፣ ቀልጣፋ፣ ተደራሽና በዲጂታል ሥርዓት የታገዘ ለማድረግ የታቀደ መሆኑ የገለፁት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ የጤና ዘርፍ ሪፎርሙ የጤና ሥርዓቱን ለማዘመን፣ ያሉ ክፍተቶችን ለይቶ ለመሙላትና ተቋማት ከዘመናዊ የዲጂታል ሥርዓት ጋር ተጣጥመው ተወዳዳሪና ውጤታማ እንዲሆኑ ወሳኝ ነው ብለዋል። ዶ/ር መሳይ ሠራተኞች የሥራ ዝርዝራቸውንና የብቃት መስፈርታቸውን በግልጽ በመረዳት ለሚመጣው የብቃት ምዘና መዘጋጀት፣ ከአሉቧልታ ይልቅ ትክክለኛ መረጃን መከተልና ሪፎርሙን በጋራ በመረዳት በተግባር ማስፈጸም እንደሚገባ አሳስበዋል። የጤና ሚኒስቴር የሰው ሀብት ብቃትና አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሀብታሙ ደምሴ ሰነዱን ሲያቀርቡ፣ የሪፎርሙን የብቃት ማዕቀፍ፣ የሥራ ዝርዝርና የዲጂታል እና መሶብ አገልግሎቶች አቅጣጫዎችን አብራርተዋል። በመድረኩ የሪፎርሙ ዋና ዓላማ የጤና አገልግሎትን ማሻሻል፣ ብቃት ያለውና ተነሳሽነት ያለው የጤና ዘርፍ የሰው ኃይል መገንባት፣ የጤና ዲጂታላይዜሽንን ማጠናከር፣ ሀገር በቀል የጤና ግብዓቶችን ማሳደግና ዘላቂ የፋይናንስ ምንጭ በማሳለጥ የጤና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ መሆኑ ተጠቁሟል። በተጨማሪም ሠራተኞች ያነሷቸውን ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮችና ጥያቄዎች በተመለከተ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቷል። ይህም በሪፎርሙ ዓላማ፣ አቅጣጫ፣ ትግበራና በሠራተኞች ሚና ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲፈጠር አስችሏል። በመጨረሻም እስካሁን የተገኙ ስኬቶችን በማፅናት፣ የተቋማዊ አሠራርንና የፖሊሲ ማዕቀፎችን በማጠናከር፣ ብቃትን፣ ጥራትን፣ ብዝሃነትንና አካታችነትን በማስቀደም የሪፎርሙን ዓላማ ወደ ተግባር ለማሸጋገር የኢንስቲትዩቱ አመራርና ሠራተኞች የጋራ ኃላፊነት እንዳለባቸው ተገልጿል።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
በድንገተኛ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ወቅት የመሠረታዊ የጤና አገልግሎቶችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተዘጋጀውን መመሪያ ለማጽደቅ ወርክሾፕ ተካሄደ በድንገተኛ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ወቅት የመሠረታዊ የጤና አገልግሎቶችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተዘጋጀውን መመሪያ ለማጽደቅ እና ለማሰራጨት የሚያስችል የሦስት ቀን ወርክሾፕ ከነሐሴ 4 እስከ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ተካሂዷል። በወርክሾፑ የጤና ሚኒስቴር፣ የክልል ጤና ቢሮዎች፣ የክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶች፣ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክቶሬቶች፣ አጋር ድርጅቶች እና የዓለም ጤና ድርጅት ተወካዮች ተሳትፈዋል። የወርክሾፑን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ በድንገተኛ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ወቅት ሕብረተሰቡ መሠረታዊ የጤና አገልግሎቶችን እንዲያገኝ ማረጋገጥ የጤና ሥርዓቱ ዋነኛ ተግባር መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ በተለያዩ ወቅቶች የተለያዩ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን የተጋፈጠች መሆኗን ያነሱት ዶ/ር መሳይ፣ ከእነዚህም መካከል እንደ ኮቪድ-19፣ ኤምፖክስ፣ ማርበርግ፣ ወባ እና ኩፍኝ ያሉ ወረርሽኞች፣ እንዲሁም ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያያዙ ክስተቶችን ለአብነት አንስተዋል። በእነዚህ የአደጋ ጊዜያት የጤና ሥርዓቱ ውጤታማ ምላሽ ለመስጠት ከፍተኛ የቅንጅት ሥራ ማከናወኑን ጠቁመው፣ ከተከናወኑት የዝግጁነትና የምላሽ ሥራዎች ጠቃሚ ልምዶችን መውሰድ መቻሉን ገልጸዋል። ከተገኙ ልምዶች በመማር የጤና ሥርዓቱን ቀጣይነትና የመቋቋም አቅም የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል። እንደ ዶ/ር መሳይ ገለጻ፣ የጤና የአደጋ ሁኔታዎች ሲከስቱም በቅድመ ዝግጁነት፣ በተቀናጀ ምላሽና በጠንካራ ተቋማዊ አሠራር ወሳኝ የጤና አገልግሎቶችን ማስቀጠል ይቻላል። ይህንንም ለማረጋገጥ ኢንስቲትዩቱ ፣ የጤና ተቋማት፣ የአጋር ድርጅቶችና የሌሎች ባለድርሻዎች በትብብር መስራት ወሳኝ ነው። በተለይም ጠንካራ የጤና ተቋማትን መገንባት፣ የጤና ባለሙያዎችን አቅምና ደህንነት ማጠናከር፣ አስፈላጊ መድኃኒቶችና የጤና ግብዓቶች በበቂ ሁኔታ መኖራቸውን ማረጋገጥ፣ የሪፈራል ሥርዓትን ማጠናከርና አማራጭ የአገልግሎት አሰጣጥ ዘዴዎችን ማቀናጀት የጤና ሥርዓቱን የመቋቋም አቅም የሚያጠናክሩ ቁልፍ ተግባራት መሆናቸውን ዶ/ር መሳይ አብራርተዋል:: የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መልካሙ አብቴ በበኩላቸው፣ በወረርሽኝ ወይም በሌላ ድንገተኛ አደጋ ወቅት ትኩረት ወደ አደጋው ምላሽ ብቻ በማድረግ መሠረታዊ የጤና አገልግሎቶች እንዳይቋረጡ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል። እንደ ዶ/ር መልካሙ ገለጻ፣ የመሠረታዊ ጤና አገልግሎቶች ሲቋረጡ ችግሩ ራሱ ወደ ሌላ የጤና አደጋ ሊቀየር ይችላል። ስለዚህ በግጭት፣ በወረርሽኝና በሌሎች የአደጋ ሁኔታዎች ወቅት መሠረታዊ የጤና አገልግሎቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸው መመሪያው የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም የአደጋ ጊዜ የማሀበረሰብ ግንዛቤና ተሳትፎ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው፣ ማኅበረሰቡ በአደጋ ጊዜ ምን ማድረግ እንዳለበት፣ ራሱን ከጤና አደጋዎች እንዴት መጠበቅ እንደሚችልና መቼ የጤና ተቋም መጎብኘት እንዳለበት ማስተማር እንደሚገባ አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥርና የቅድመ ዝግጁነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ነኢማ ዘይኑ በበኩላቸ መመሪያው ከአደጋ መከሰት በኋላ ብቻ ሳይሆን ከወረርሽኝ ወይም ከሌላ አደጋ መጀመሪያ ጀምሮ መሠረታዊ የጤና አገልግሎቶች በምን መንገድ መቀጠል እንደሚችሉ የሚያመላክት ተግባራዊ ማዕቀፍ ለመሆን እንደተዘጋጀ ያስረዱ ሲሆን መመሪያው በተግባር ሊውል የሚችል እንዲሆን ከተሳታፊዎች የሚቀርቡ አስተያየቶችና የሥራ ልምዶች በመመሪያው የመጨረሻ ሰነድ ውስጥ እንደሚካተቱ ገልጸዋል። አቶ እስራኤል አታሮ፣ በጤና ሚኒስቴር የማኅበረሰብ ተሳትፎና የመጀመሪያ ደረጃ ጤና እንክብካቤ መሪ ሥራ አስፈጻሚ፣ በወርክሾፑ ባስተላሊፉት መልዕክት የተሳታፊዎችን በጋራ መሥራትና የትብብር መንፈስ ላይ አጽንኦት የሰጡ ሲሆን በመተባበር አስፈላጊዎቹን የጤና አገልግሎቶች (essential services) ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል። ይህንንም ለማረጋገጥ በጋራ መሥራትና በተቀናጀ መንገድ መንቀሳቀስ የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል። የውይይቱ ዋና ዓላማ በአደጋ ወቅት እንደ የእናቶችና ሕፃናት ጤና፣ ክትባት እና ሌሎች ወሳኝ የጤና አገልግሎቶች እንዳይቋረጡ ሊወሰዱ የሚገቡ እርምጃዎችን በግልጽ ማስቀመጥ ሲሆን ከተሳታፊዎች የሚገኙ ግብዓቶችና ምክረ ሐሳቦች ተካተው በድንገተኛ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ወቅት የመሠረታዊ የጤና አገልግሎቶችን ቀጣይነት ማረጋገጥ የሚያስችል ተግባራዊና ጠንካራ መመሪያ ለማጽደቅ ያለመ ነው። https://ephi.gov.et/በድንገተኛ-የሕብረተሰብ-ጤና-አደጋ-ወቅት/
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи