tgindex
ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ

ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ

Статистика

@ethioterkaa

Последний пост
14 июл.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 781
+8 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 911
20 постов
Вовлечённость
107,3%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • "በህይወት ስትኖር ምንም ነገር ሊገጥም ይችላል። ሰው ነህ በቃ አለም ላይ ያሉ ሰዎች የገጠማቸው ነገር በጠቅላላ አንተ ህይወት ውስጥ ሲደገም ልታይ ትችላለህ።እንደ አደገኛ እኔ ምናምን አትበል" ይለኛል እየተቆጣ ሊያረጋጋኝ እየሞከረ። . . "ለምሳሌ አሁን እኔን ተመልከተኝ..."ይላል የሁልጊዜው ምሳሌ እራሱ ነው። "... በህይወት ዘመኔ ደደብ የሆነች ሴት ልቤን ትሰብረዋለች ብዬ በጭራሽ ገምቼ አላውቅም። በጭራሽ.. ግን ደግሞ ፍቅር መምጫው አይታወቅም አይደለ ያቺ ልቤን ትሰብረዋለች ብዬ አስቤያት የማላቃት ሴት እጅ ላይ ጣለኝ። ለስሙ ፊደል ቆጥራለችኮ ግን ከእሷ ጋር በቴክስት አውርቶ ለመግባባት በራሱ በጣም ብዙ ጊዜ ነው የፈጀብኝ። በዛ ላይ እንደዛም ሆኖ ትንሽ እንግሊዘኛ ጣል እንደምታደርግ ሳስበው ያስቀኛል። ባይነበብም ከነጉድለቱም ቢሆን አስተካክዬ አነበው ነበር። ለምን ብትለኝ ፍቅር ለሚሉት ነገር ብዬ..." እያለ ስለበፊት ፍቅረኛው ይነግረኛል። ስለየትኛዋ እንደሆነች አላውቅም። ብቻ ዝም ብዬ እሰማዋለው። . . "እና እንዳልኩህ ነው በህይወቴ ውዴ(Wde) ብሎ ለመፃፍ Wda የምትል አንተ(Ante) ለማለት Anta እያለች የምትፅፍ ሴት ልቤን ትሰብረዋለች ብዬ በስህተት አስቤ አላውቅም። በዛ የተወላገደ አፃፃፏ እንለያይ ብላ ልቤን ሰበረችው" ብሎ ከት ብሎ ሳቀ። አነጋገሩና አሳሳቁ ሳልፈልግ አሳቀኝ። . . ቀጠለና "እሷን ሳስታውስ ትዝ የሚለኝ ዘፈን አለ" አለኝ። "ምን የሚለው ነው?"አልኩት ከብዙዎቹ የፍቅር ዘፈኖች አንዱ እንሚሆን እየገመትኩ። "የአለማየው እሸቴ ተማር ልጄ ተማር ልጄ..."ብሎኝ ሳቀ። "አንተ እውነትም ለይቶልሀል"ብዬው እየሳኩኝ ተነስቼ ልሄድ ስል"ስማ ነገም ፊትህን ዘፍዝፈህ እንዳትመጣብኝ በቃ ተዋት አለም ከእሷ በበለጡ በብዙ እንስቶች ተባርካለች። አታስብ" አለኝ። . . @ethioterkaa @ethioterkaa @ethioterkaa

  • 24 июн.1 01711

    "ድህነት ድሀ ብቻ ሳይሆን ፈሪም ያደርጋል" ዳኒ ጡሞ 😔

  • 3 июн.1 55896

    "ሰኔ እና ሰኞ... አይግጠም" ሰኔ እና ሰኞ አይግጠም የሚለው የቆየ የአባቶቻችን አባባል ዘንድሮም በ 2018 ዓ.ም. በአይናችን ልናየው በትክክል ገጥሟል። ሰኔ 1 ቀን ሰኞ ይውላሎል። ከ 1979 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ዛሬ... በከፊል እንይ እስኪ.. 1)1979 ዓ.ም. ( ዘመነ ማቲዎስ) በ1979 ዓ.ም. ሰኔ እና ሰኞ ሲገጥም አገሪቱ በከባድ ፈተና ውስጥ ነበረች የ1977ቱ ታላቁ ድርቅ መዘዝ እና በወቅቱ የነበረው የዝናብ እጥረት ተከስቶ ነበረ። 2) 1984 ዓ.ም.( ዘመነ ማርቆስ) በዚህ ወቅት ሰኔ እና ሰኞ በድጋሜ ገጠሙ። ህይ ዓመት የሽግግር ወቅት ቀውስ እንደነበረ የታሪክ መዛግብቶች በጥልቀት ያወሱናል። በዚህም ወቅት በመላው አገሪቱ ከፍተኛ የጸጥታ መደፍረስ ና ግጭት ነገሰ። 3) 1990 ዓ.ም. ( ዘመነ ማርቆስ) በዚህም ወቅት ሰኔ እና ሰኞ ሲገጥም በአገሪቱ ላይ ሊላ የደም ምዕራፍ ተከፈተ።በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተነሳው እጅግ አስከፊ የነበረው የባድሜ የድንበር ጦርነት በዚሁ አመት ፈነዳ። 4) 1997 ዓ.ም. ( ዘመነ ዮሐንስ) በ 1997 ላይ ደግሞ ታሪኩ ይበልጥ ልብ ሰባሪ ሆኗል።1997 ሰኔ እና ሰኞ ገጠመ። ያ ታዋቂው እና ውጥረት የበዛበት አገራዊ ምርጫ 97 የተካሄደው በዚህ ወቅት ነበር። 5) በ2007 ዓ.ም. (ዘመነ ዮሐንስ) ከ 10 ዓመታት በኋላ በ 2007 ዓ.ም. በድጋሜ በዘመነ ዮሐንስ ሰኔ እና ሰኞ ገጠሙ። 6) 2013 ዓ.ም. (ዘመነ ማርቆስ) በቅርብ ጊዜ ትውስታችን በሆነው በ 2013 ዓ.ም. ሰኔ እና ሰኞ በድጋሜ ገጠሙ። በዚህም ወቀት የጦርነት የጭንቀት የከበሮ ድምፅ የነበረ መሆኑን ሁላችንም እናስታውሳለን። የታሪክ ፍሰት አያችሁ? አሁን ደግሞ ወደ ዘንድሮ እንምጣ። ዘንድሮ 2018 ዓ.ም. ነው።አመቱም ድጋሜ ዘመነ ማርቆስ ነው! ሰኔ እና ሰኞ ገጥመዋል። እንደ 1997ቱ, እና 2007ቱ ሁሉ:ዘንድሮም ሰኔ እና ሰኞ በዘመነ ማርቆስ ላይ መውደቃቸው ታዘባቸሁ? ታሪክ እራሱን ይደግማል? ወይንስ እኛ ካለፈው ተምረን ራሳችንን እና አገራችንን እንጠብቃለን? የዘንድሮው የሰኔ እና ሰኞ ገጠመኝ ለኢትዮጵያ ወጣቶች የጥንቃቄ የማስተዋል እና የሰላም ጊዜ ይሁንልን። አባቶቻችን በምክንያት ነው << ሰኔ እና ሰኞ >> ያሉት አስተውሉ ! ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅ!🇪🇹🇪🇹

  • 30 мая1 4274

    ቃላት እማይገልፃቸው አንዳንድ ነገር አለ በቃ ዝም ብለን ተመልክተን ከንፈራችንን እምንመጥበት አይ ሰው እምንልበት ከሁሉ በላይ ግን የተረዳሁት ሁሉም ነገር ጊዜያዊ ነው ይጠፋል 🙏 ፈጣሪ ምህረቱን ይላክልህ

  • 27 мая1 4693

    видео или голосовое, без подписи

  • 14 апр.2 196103

    👑 "ዘፈን ሲያስፈራ ያየሁት ቴዲ አፍሮ ሙዚቃ ሲያወጣ ነው!" 👑 ​እውነት ግን... የሙያ አጋሮቹ ስለ ኪነ-ጥበቡ ንጉስ ቴድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ምን ይላሉ? የደረሰበት የከፍታ ማማ እና ክብርስ ዝም ብሎ የመጣ ነው? እስኪ የቅርብ ሰዎቹን አስገራሚ ምስክርነት እንስማ👇 ​🎙 ልዑል ኃይሉ (እሳቱ ሰዓት)፦ ስለ ድካሙ እና ስኬቱ "ቴዲ ዘፈን ሲለቅ ከተማውን እንዴት ያምሰው እንደነበር ታውቃላችሁ? 'አበባዬሆሽ' ሲወጣ ሰው በደስታ ሲያብድ አይቻለሁ!" ይላል ልዑል በመገረም። አክሎም የቴዲ ስኬት የዕጣ (ሎተሪ) ሳይሆን የላብ ውጤት መሆኑን ሲመሰክር፦ "በዓመት 365 ቀንም አርት ሲሰራ ነው የምታየው። ዝም ብሎ መሬት የዘገነው ዝና አይደለም፤ የመጨረሻ ዋጋ ከፍሎ ያገኘው ክብር ነው!" ይለዋል ነጭ ነጯን። ​🎩 ጆሲ ገብሬ (Jossy In Z House)፦ ስለ ሞገሱ (Aura) ዘናጩ ጆሲ ደግሞ ቴዲን የሙዚቃው ዓለም ልዩ ሞገስ አድርጎ ይገልጸዋል። "ቴዲ አፍሮ በቃ የዘፋኞች Aura ነው! ሁላችንም ዘፈን ምን እንደሆነ ሳናውቅ በሙዚቃው ትልቅ ስራ የሰራ ታላቃችን ነው። እንደ ሀገር አይኮን (Icon) እና ሌጀንድ (Legend) የምናከብረው ትልቅ ሰው ነው!" ብሎታል። ​🎵 ሸዋንዳኝ ኃይሉ፦ ስለ ንፁህ ልቡ እና ስብዕናው (በነገራችን ላይ አብዛኛዎቹ የሸዋንዳኝ ተወዳጅ ስራዎች የቴዲ ግጥምና ዜማዎች መሆናቸውን ልብ ይሏል) "ቴዲ ጠንካራ ሰራተኛ፣ ጓደኝነትን የሚያውቅና ጨዋታ አዋቂ ነው። ከምንም በላይ ግን ልቡ ንፁህ ነው!" ይላል ሸዋንዳኝ። የሚያስገርመው ደግሞ ራስ ወዳድ አለመሆኑ ነው... "ግጥምና ዜማ ሰርቶልኝ... በጣም አሪፍ ዘፈን እንኳ ቢሆን ወደራሱ አይወስድም፤ 'ያንተ ዕድል ያመጣው ላንተ ነው' ብሎ ይሰጠኛል። ለጓደኛው ከራሱ በላይ የሚደሰት ባለ ትልቅ ስብዕና ባለቤት ነው!" ​✨ በአጭሩ ቴዲ አፍሮ ማለት በችሎታው ብቻ ሳይሆን በስብዕናውም የገዘፈ አርቲስት ነው! ​🗣 እስኪ እናንተስ ስለ ቴዲ አፍሮ ምን ትላላችሁ? ከስራዎቹ ሁሉ ሁሌም ብትሰሙት የማይሰለቻችሁ የትኛው ዘፈን ነው? ሀሳባችሁን ኮመንት ላይ አጋሩን! 👇🎤 ​#TeddyAfro @ethioterkaa @ethioterkaa

  • 27 янв.2 66175

    የሞት መድሀኒት በጥበበኛው ሰለሞን ቪታሊያ ዘላለም የመኖርን ሚስጥራዊ ጥበብ አወቀች። አሁን ላይ ግን ይህንን ጥበብ ለማጥፋት ቆርጣ ተነስታለች። ከሁለት መቶ አመታት በፊት ዘላለም ለመኖር የሚያስችላትን መድሃኒት (ኤሌክሰር) እንዴት መስራት እንደምትችል አወቀች። ወጣት እና ሞኝ ነበረችና መድሃኒቱን አዘጋጅታ ጠጣችው። አሁን ላይ ያቺን ቀን ደጋግማ ትረግማታለች። ወዳጆቿ፣ አፍቃሪዎቿ እና ዘመድ አዝማዷ ሁሉ ትተዋት ሄደዋል፡፡ ሞት እርሷን እያሳደዳት አይደለምና የመኖር ፍላጎቷ ጠፍቷል፡፡ አዲስ ነገር ለመጀመር ታቅድና ትርጉም አልባ እንደሆነ አስባ ትተወዋለች። ሕይወቷም ድብርት ውጦታል᎓᎓ ባይመጣም ሞቷን ብቻ ትጠባበቃለች። ማንኛችንም ብንሆን ለሕይወት ትርጉም የምንሰጣት እና የምንሯሯጠው አላማችንን ለማሳካት የሚሆን በቂ ጊዜን ስለማናገኝ ነው ሩጫችንም ከሞት እና እርጅና አንጻር ነው፡፡ ቪታልያ በመጨረሻም የመድሃኒቱን ማርከሻ አገኘች፤ ሳታቅማማም ጨለጠችው። በቀናቶችም ውስጥ ፊቷ እየተሸበሸበ እና እያረጀች መጣች᎓᎓ አሁን ላይ ምኞቷ መሞት ብቻ ነው። ማንም ቢሆን ያለፍቃዷ ምድር ላይ እንዲያቆያት አትፈልግም። ኤሌክሴሩም ቢሆን ከምድረ ገጽ ከጠፋ ቆይቷል። አሁን የኤሌክሴር መስሪያ ግብዓቶችን የጻፈችበትን ወረቀት አንስታ እሳት ውስጥ ዶለችው። ወረቀቱ ሲነድም ቆማ ተመለከተች፤ ከስንት ዘመንም በኋላ ፈገግ አለች:: ሰዎች እርግጠኛ ሆነው መናገር የሚችሉት ስለ ሞት ነው፤ ሞት በእድሜያችን ማብቂያ ላይ እንደሚከሰት እርግጠኞች ነን፡፡ እናም የቪታልያ ታሪክ ዘላለማዊነት እርግማን መሆኑን ያሳየናል። ሕይወታችንን ቅርጽ ለማስያዝ እና ትርጉም ለመስጠት ሞት ያስፈልገናል። ሞት ከሌለ ሕይወት ትርጉም አልባ እና ልጓም አልባ ትሆናለች:: ሲኦልም ዘላለማዊ የሆነ ቅጣት ያለበት ስፍራ ከሆነ ዘላለማዊ መሆኑ በራሱ ቅጣት ነው፡፡ ሰዎች ዘላለማዊ የሆነ ሕይወትን እንወርሳለን ብለው ማሰባቸው እና ዘላለምን መመኘታቸው ተፈጥሯዊ ነው። ከሁሉም ነገር በላይ ሰዎች አመታትን መኖር ይፈልጋሉ፡፡ ሰባትም ይሁን ሰባ አመት በሕይወታችን ላይ ቢጨመር እንወዳለን፡፡ ከመሞታችን በፊትም ማየት የምንፈልጋቸው ስፍራዎች፣ ማድረግ የምንፈልጋቸው እልፍ ተግባራት አሉን፡፡ ሆኖም በተቻለን አቅም እቅዶቻችንን እንቆራርጣቸዋለን፤ በዚህችም አጭር እድሜያችን ብዙ ተግባራትን ለመፈጸም እንሞክራለን። እንዲህም ሆኖ የቀሩን ነገሮች እንዳሉ ማሰባችንን አናቆምም፡፡ ከአመታት በፊት የነበረው ሰው በሃያዎቹ እድሜው ወይም አስቀድሞ ትዳር ይይዛል፤ ልጆችንም ይወልዳል። አሁን ላይ ሰዎች በአርባዎቹ እድሜያቸው የሚሞቱበት ጊዜ ላይ አይደለንም። የአገራችንን ኢትዮጵያን አማካይ የመኖሪያ እድሜ እንኳ ብናስበው ቀድሞ ከነበረበት አርባ አምስት አመት አሁን ላይ ወደ ስልሳ ስምንት አመት አድጓል። ብዙ አመታትንም እንደመኖራችን የማግባት እና ልጆችን የመውለድ እቅዳችን ወደ ሰላሳዎቹ እድሜያችን ተሸጋሽጓል፡፡ ይህም የጉርምስና እና የኮረዳነት ጊዜያችንን ያራዝመዋል፡፡ ቀድሞ ከነበረውም ትውልድ በተቃራኒው፣ ይህ ትውልድ ለጭፈራም ይሁን ለመዝናኛ የሚሆነውን ጊዜ ያገኛል፡፡ ነገር ግን እርካታን አግኝቷል ብለን ማሰብ እንችላለን? እንዲያውም በጭራሽ ፍላጎቶቹ ከቀድሞ አያቶቹ ብሰዋል፡፡ ምንም ያህል ዘመን በእድሜያችን ላይ ቢጨመርልንም አንረካም። ብዙ ያላደረግናቸው እና ያላሳካናቸው ነገሮች እንዳሉ ይሰማናል፡፡ ይህም ለስኬት መራብን እና ለመኖር መጓጓትን ይሰጠናል፡፡ ሆኖም ዘላለም መኖር ቢፈቀድልን ምኞታችንም ሆነ መጓጓታችን ገደል ይገባሉ። መኖራችንም ትርጉም ያጣል፤ ከምንም በላይ መሰልቸት ያሰቃየናል:: የሚቃጠል ጊዜ አይኖርም፤ ጊዜም ወርቅ አይደለም። ትርጉም አልባ ተግባራት... የምንኖርበትም ምክንያት ካጣን ሕይወት ትዶለድማለች አሰልቺ እና ዘላለማዊ የሆነን ድራማ እንደመመልከት ይሆንብናል፡፡ አሁን ላይ የመኖሪያ እድሜያችን ማጠር እና የጊዜ አለመኖርን እንደ ችግር እናነሳዋለን፡፡ ሆኖም ይህ ራስን ማታለል ነው፡፡ የተሰጡንንም የእድሜ ቁጥሮች ማሳጠርም ሆነ ማስረዘም አንችልም፤ ይህንንም ሰበብ አድርገን እንሰንፋለን፡፡ እቅዶችን እናቅድና መተግበሩ ዳገት ይሆንብናል:: ለራሳችንም “ጊዜ ቢኖረኝ እኮ...” እንለዋለን።        @ethioterkaa      @ethioterkaa

  • 27 янв.2 0243

    ሰው 😭

  • 23 янв.2 279162

    ቢወድቀሸብህም ብትወድቅበትም የምትሰበረው አንተ ከሆንክ በደንብ አስብበት @ethioterkaa @ethioterkaa

  • 16 янв.2 448131

    😏አለሁ ማለት ከንቱ መኖር ምንድነው ትርጉሙ  ቆይ ይቺ አለም ምን እሚሏት ከሀዲ ናት ተስፋ ትሰጥህ ና ተስፋህን ትነጥቅሀለች እውነት ከሀዲ ናት ነፃነትህን ለማወጅ ስትነሳ   በወርቅ ያማሩ በዳይንድ የተንቆጠቆጡ ቀለበት በእጆቾህ 💍ላይ ታስሮ ታየዋለህ ህይወት ጥቁር እና ነጭ አንዳንዴም ግራጫ ናት😔 ነፍስህ በሰላም ትረፍ   ነፂ😭 @ethioterkaa @ethioterkaa

  • 9 янв.2 22362

    "የኔ ቆንጆ" ሳልልሽ ሳልሸነግልሽ ልውደድሽ ወይስ በአባይ ምላሴ አባብዬ ስሜትሽን ልኮርኩርው! አንቺም ተቀባብተሽ እና ተሽቀርቅረሽ የውሸት መልክ ተላብሰሽ ቆንጆ መስለሽ እንዳይሽ አፈር-ድሜ ልትበዪ ነው? የቱ ይሻላል? ሁለታችንም ከእነ-አስቀያሚነታችን ብንዋደድ አይሻለንም ወይ? ከቅጥፈት እኔ ይህንን መርጣለሁ! አየሽ? ሳትዋቢ ከወደድኩሽ የነጠረ ፍቅር ይህ ነው! እኔም ሳልዋሽ "ቆንጆ ነሽ" ካላልኩሽ ልታምኚኝ ይገባል። ቆንጆማ ቆንጆ ነሽ! ግን ጉዳዩ እሱ አይደለም... እመቤቴ ሆይ፥ እኔ ህይወት እና መንገድ አልያም ብርሐን አይደለሁም፤ "ነኝ" ብዬም አላታልልሽም፤ ቢሆንም የበለጠውን እነግርሻለሁ። ጠፍተሻል! የት እንዳለሽ እና ወደ የት እንደምትሄጂ አታውቂም። ቁንጅናሽም ብቻውን ውሸት ነው። ዓለምም እንዳንቺ ናት! ህይወትም አምሳያሽ። ምንም ያህል ብትቆነጅ ህይወት— ግድየለሽነቷን፥ ጭካኔዋን፥ በተቃርኖሽ የተሞላች እንቆቅልሽ መሆኗን መካድ አልችልም። ይህ ሐቅ ከሚፈጥርብን ሐዘን የሚያፅናናን ሁሉ በጣፋጭ ውሸት እየለወሰ አፋችንን እያበሰ ነው- በተረት ተረት። ህይወት በራሷ ትርጉም አላት? ለእኛ የተበጀ ዓላማ አላት? አይመስለኝም! መለኮት የፃፈልን እጣፈንታ አለ ብዬም አላምንም። ለፅድቃችን አክሊል ሚደፋልን ሊኖር? ከህይወት በላይ ክፋትን የተሞላ ኖሮ? እንግዲህ ይህንን ሐቅ መረዳት መቻል ምስኪንነት አይደለም። ቅዠቶችን ማፈረስና እንደ ትቢያ እንዲቦኑ ማድረግ ነው። እንዲህ ስናገር እያለቃቀስኩ ሳይሆን ቆፍጠን ብዬ በጀግንነት የማወራው ሐቄ ነው። ህይወት እንዲህ ናት! ቃልኪዳኖች ተሰባብረው ሲደቁ፤ የልፋታችን ውጤት መና ሲቀር? ፍቅር ሁሌም እየወጋ ሲያደማንና በሰው ፊት ሲያሳፍረን፤ ጥሩ ሰዎች ሲወድቁ ሳይ፥ ያ ፃድቅ ሰባቴ ወድቆ ለስምንተኛ ጊዜ መነሳት አቅቶት ሲንደፋደፍ ሳየው፤ ፃድቅ ሲራብ ዘሩም ሲለምን! እና ይህ ሁሉ በአለም ላይ ሲሆን ህይወት እኛን አላስፈቀደችንም። ቆይ አትደንግጪ! አትረበሺ በፍፁም። በተረታተረቶች ውስጥ አትደበቂ! ፀጥታውን ተጋፈጪው። ፀጥታው እኮ ከእናንተ ሰዎች ሆይሆይታ በላይ ይጮኻል? ስለምን ፈራሽው? ጭለማው እኮ ከእናንተ ሻማና ጧፍ በላይ ነገሮችን ይገልጣል! ለነገሮች የውሸት ትርጉም አይፈጥርም! ከንቱነታቸውን ያሳያል! ማሸብረቅ ውሸት ነው! እውነት እውነት ከሆነች ጌጥ ለምኗ? እዚህ ብቻዬንም ብቀር አልፈራም። የውሸትን ድንጋይ ተንተርሼ ከምቃዥ ጭለማው ላይ ባፈጥጥ እመርጣለሁ! ቢነጋም ነጋ ጠባ! ባይነጋም ጨለማው ቤቴ ነው። — ናኹ ሠናይ @ethioterkaa @ethioterkaa

  • 23 дек.2 12883

    #አዲስአበባ ከአየር ላይ ዕይታ-1947 ዓ.ም ►ጊዮርጊስ፤ምኒልክ ሐውልት፤አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት... 📸አልፍሬድአይዘንሽቴድ @ethioterkaa @ethioterkaa

  • 12 дек.2 16133

    видео или голосовое, без подписи

  • 6 дек.2 29967

    መቃብር ስፍራ… “ቪአይፒ” (VIP) የለም⁉️ •••••••••••••••••••••••••••••••••••• (ከፈላስፋው ጭሰኛ) ከተማ ውስጥ ትልልቅ አጥር አጥረን፣ በካሜራ እና በዘበኛ ተጠብቀን እንኖራለን። አንዱ “ጌታ”፣ አንዱ “ሎሌ” ሆኖ ይኖራል። አንዱ መርሴዲስ ውስጥ፣ አንዱ አውቶብስ ውስጥ ይጋፋል። ግን ወዳጄ… ይሄ ሁሉ ልዩነት እስከ “ቀብር ስነስርዓት” ድረስ ብቻ ነው። 1. የመጨረሻው እኩልነት መቃብር ስፍራ ሄዳችሁ ታውቃላችሁ? እዛ “የሚኒስትር አጥንት” እና “የጭሰኛ አጥንት” አይለይም። • የዚያ ሁሉ ዘረኛ አፈር፣ ከአንድ አይነት መሬት ጋር ተቀላቅሏል። • የዚያ ሁሉ ትዕቢተኛ አፍ፣ በአፈር ተሞልቶ ዝም ብሏል። • ያ ሁሉ “የኔ ነው” ሲል የነበረ እጅ፣ ባዶውን ተዘርግቷል። መቃብር ማለት… “የሰው ልጅ ትዕቢት የሚሰበርበት ሙዚየም” ነው! 2. ታዲያ ለምን እንገዳደላለን? የሚያሳዝነው… በህይወት እያለን “መሬት ይዞብኛል”፣ “ድንበር ገፍቶብኛል”፣ “ዘሬን ሐይማኖቴን ነክቶብኛል” ብለን የምንገዳደለው፣ መጨረሻ ላይ ሁላችንም የምንገባበትን “ሁለት ሜትር ጉድጓድ” ጠልተን አይደለም። በህይወት ሳለን የማንጠግበው መሬት፣ ስንሞት እንዴት ይበቃናል? መልሱ ቀላል ነው፦ “የሰው ልጅ አይኑ የሚሞላው በአፈር ብቻ ነው!” 3. የሀብታም ለቅሶ vs የድሃ ለቅሶ አዎ፣ ለቅሷችን ይለያይ ይሆናል። ሀብታሙ በሳጥን፣ ድሃው በሸማ በአቡጀዲ ይቀበር ይሆናል። ሀብታሙ ሀውልት ይቆምለታል፣ ድሃው ሳር ይበቅልበታል። ግን ከታች ያለው ትል… የሀብታሙን ስጋ “ኬክ” ብሎ አይበላም፤ የድሃውን ስጋ “ፍርፋሪ እንጀራ” ብሎ አይንቅም። ትሉ ሁሉንም እኩል ነው የሚበላው! ታዲያ በምድር ላይ የምናሳየው ይህ ሁሉ ድራማ፣ ይህ ሁሉ ማስመሰል፣ ይህ ሁሉ ጭካኔ እና ንቀት… ለማን ነው? መልሱን ለእናንተ ልተወው? የጭሰኛው ጥያቄ… ዛሬ ማታ አልጋህ ላይ ስትተኛ፣ እንደምትነቃ እርግጠኛ ነህ? ካልነቃህስ? የሰበሰብከው ብር፣ የገነባኸው ቤት፣ የተጣላኸው ሰው… ምን ዋጋ አላቸው? ወዳጄ… ሞት አይቀርም። የማይቀረውን ሞት እየጠበቅን፣ ለምንድነው የማይጠቅም ጠላትነት የምናተርፈው? እስኪ ሞትን እንደ “መካሪ” እንጂ እንደ “ጠላት” አትየው። ምክንያቱም ሞት… “ትዕቢትህን” ስለሚያስተነፍስልህ፣ ብቸኛው እውነተኛ ጓደኛህ እሱ ነው! “ጭሱ ከኔ፣ እሳቱ ከአንተ! @ethioterkaa @ethioterkaa @ethioterkaa

  • 3 дек.1 91084

    « ፨ ፨ ፨ #በጽኑ_ታማችኋል ፨ ፨ ፨ » አንድ ገዳማዊ አባት የዚህን ትውልድ አካሄድ ታዝበው እንዲህ አሉ . . . " . . በአፍላ ትጀምራላችሁ በወረት ትተውታላችሁ፤ ያወቃችሁትን ረስታችሁ ያላወቃችሁትን ለማወቅ ትጥራላችሁ፤ የያዛችሁትን ትረግጣላችሁ፣ የረገጣችሁትን ትይዛላችሁ፤ ምኞታችሁ ብዙ ነው፣ አምሮታችሁ ልክ የለውም። ያማራችሁን ስታገኙ ወዲያው ይሰለቻችኋል፣ ተው የተባላችሁትን ትሽራላችሁ፣ የተከለከላችሁትን ትደፍራላችሁ የተፈቀደላችሁን ችላ ትላላችሁ። ቤተ መቅደስ እንዳትገቡ ብትከለከሉ ወደ ፊት ቤተ መቅደሱን በመስታውት ሠርታችሁ መቅደስ ባትገቡም እንኳን ሁሉን ከውጭ ሆናችሁ ማየት ትፈልጋላችሁ። ሁሉን ማወቅ ትፈልጋላችሁ በአንዱም ግን አትጠቀሙበትም። ሁሉ አላችሁ ግን ባዷችሁን ናችሁ። ሃይማኖት እንጂ እምነት የላችሁም"። #አባ_ሰውነታቸውን_እንደ_ቅኔ_ዘራፊ በስሜት እየናጡ ቀጠሉ . . . "ተምራችሁ እውቀት ስታገኙ ሠርታችሁ ሀብት ስታፈሩ ከላይ የሆናችሁበትን ሀገር ለቃችሁ ሰፋ ወዳለው እንሂድ ብላችሁ እንደገና ከታች ትጀምራላችሁ፣ ትቀጥላላችሁ በመጨረሻ ከጀመራችሁበት ትገኛላችሁ። ቸኩላችሁ ትወስናላችሁ ወዲያው ትጸጸታላችሁ። በጽኑ ታማችኋል"። "ከታሪክ ፍቅርንና ልማትን ሳይሆን ጥላቻንና ጥፋትን ለይታችሁ ትቆፍራላችሁ። ከዚያም ቀጥላችሁ የከበረ ማዕድን እንዳወጣችሁ ሁሉ በኩራት ደረታችሁን ነፍታችሁ ሳትመርጡ ሁሉን በአደባባይ ትዘሩታላችሁ የአሸናፊነትንና የተሸናፊነትን ሃውልት በአንድ ላይ ታቆማላችሁ። ለግልፅነትና ለነፃነት እያላችሁ በምታደርጉት ሽኩቻ እርቃን ወደመሆን ወረዳችሁ። በዚህ አለም ጥድፊያ ታማችኋል ሀገራችሁን ትንቃላችሁ፣ ጥላችሁ ለመሄድ ትፈልጋላችሁ ከሄዳችሁ በኋላ ደግሞ አፍታ ሳትቆዩ ሀገሬ ናፈቀኝ ትላላችሁ በቁማችሁ የናቃችሁትን አፈር በሞታችሁ ልትለብሱት ትመኛላችሁ። ለሀገሬ አፈር አብቃኝ ብላችሁ በድናችሁን ልካችሁ የወገኖቻችሁን ልብ ትሰብራላችሁ። በዚህ የተነሳ ምሥጢር ለመካፈል ቅርስ ለመረከብ የሚያስችል ስብእና አልገነባችሁም። እኛ ገዳማውያን የመገናኛውን ድልድይ ስላልሠራንና ከእናንተ ስለራቅን ሳይሆን ስለማታዩት ወይም ማየት ስለማትፈልጉት አለበለዚያም እንደ ልቦለድ ገፀ ባህርይ የራሳችሁን ያሸበረቀ አስረካቢ ፈጥራችሁ እውኑን ሳይሆን ምናባችሁን መረከብ ፈለጋችሁ። እኛ ደግሞ እናንተ ታዩን ዘንድ አላሸበረቅንም ማሸብረቅም አንፈልግም በዚህ ምክንያት ለእናንተ ምሥጢር ለመንገር ቅርስ ለማውረስ ከባድ ሆኗል። እኛ አባቶቻችንን እናምናለን፤ በእነርሱም ደስ ይለናል የነገሩንን ተቀብለን ቃል ኪዳናቸውን ጠብቀን እንኖራለን። "ጽላተ ሙሴ አክሱም ጽዮን እንዳላች ሲነግሩን መጋረጃ ገልጠን ሳጥን ከፍተን እንይ አላልንም። "ጌታ የተሰቀለበት የግማደ መስቀሉ ክፋይ ግሸን ማርያም አለ ሲሉን ቆፍረን አውጥተን እንይ አላልንም። "ቅዱሱ ጽዋ መንዝ ውስጥ አለ ሲሉንም ዋሻ እናስስ አላልንም። አባቶቻችንን አምነን ሀገራችን የበረከት ምድር መሆኗን ተረድተን የጌታችንን የፀጋ ስጦታ ተቀብለን በእምነት እንኖራለን። ምንም የለንም፤ ሁሉ ግን የኛ ነው። ድሆች ብንባልም ባለጸጎችም ነን። የተራቆትን ብንመስልም የጸጋ ልብስ አለን። ሐዘንተኞች ብንመስልም ደስተኞች ነን። ስለ ሀገራችን መባረክ፣ ቅድስት ሀገር መሆን፣ ቅዱስ ቅርስ በእጃችን እንዳለ ዓለም እንዲያረጋግጥልን አንፈለግም"። አባ በአጭሩ የሚመለሱ አይመስሉም እንደ ጥሩ ተኳሽ ኢላማቸውን እያጠበቡ ይህን ትውልድ ይቀጠቅጡት ይዘዋል። #ከአርባ_ሃራ_መድኃኔዓለም_ገዳም #አባ_አክሊሉ 》#ከእመጓ መጽሀፍ የተወሰደ። @ethioterkaa @ethioterkaa @ethioterkaa

  • 25 нояб.1 86975

    ጊዜ "ጊዜ ከሁሉም ነገር በላይ የሚያስፈልገን ነገር ሆኖ ሳለ ከሁሉ ነገር በላይ ያላግባብ የምናባክነው ነገር ነው። ለሰው ልጆች ሁሉ በእኩልነት የተሰጣቸው ነገር ነው ጊዜ። ነገርግን የሰው ልጅ በሙሉ እኩል አይጠቀምበትም። በአሁኑ ሰዓት በአለማችን ላይ ያለው የሰው ልጆች የኑሮ ደረጃ ልዩነት የጊዜ አጠቃቀማችን እኩል አለመሆኑን ያሳያል። • የአንድ አመትን ጥቅም ለማወቅ ክፍሉን የደገመ ተማሪ ጠይቀው • የአንድ ወር ጥቅም ለማወቅ ካለ ወሩ ልጅ የወለደች እናትን ጠይቃት • የአንድ ሳምንት ጥቅም ለማወቅ ሳምንታዊ ጋዜጣ አሳታሚን ጠይቀው • የአንድ ደቂቃ ዋጋ ለማወቅ ለትንሽ ባስ ያመለጠውን ግለሰብ ጠይቅ • የአንድ ሰከንድ ዋጋ ለማወቅ ለትንሽ ከአደጋ የተረፈን ግለሰብ ጠይቀው • የአንድ ማይክሮ ሰከንድ ዋጋ ለማወቅ ሀይለ ገ\ስላሴን ጠይቀው እነዚህ ከላይ ያሉን በሙሉ የተጠቀሱት በምክንያት ነው። ህይወታችንን በአጋጣሚ ሳይሆን በእቅድ ነው መምራት ያለብን።" አዝማሪው የጊዜን ጥቅም ሲያስረዳ በስንኙ የሚከተለውን ብሏል ካልተሳፈሩበት ቶሎ ተሽቀዳድሞ፣ ጊዜ ታክሲ አይደለም አይጠብቅም ቆሞ። ✍ከማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተገኘ 🌟በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት ✨ሰናይ ምሽት ይሁንልን❤️❤️ join and follow our page @ethioterkaa @ethioterkaa @ethioterkaa

  • 25 нояб.1 71342

    መዝሙረኛው በሕይወት መንገድ ላይ በዝምታ የምታክመው ህመም ካለ ዝም በል። ዝምታህ ለምለምን ከወለደልህ የለመለመው ፍሬ የሚያፈራልህ ከሆነ በጥልቁ ዝምታ ውስጥ ዝም በል። በመናገርህ የምታቀናው ጠማማነት ካለ ተናገር። የቀናው ጥላ የሚሆንልህ ከሆነ ጉሮሮህ እስኪነቃ ቃላትን እያፈለቅክ ዝራ።   በመናገርህም፣ በዝምታህም ህመምን ካላከምክ፣ መንገድህን ካላቀናህ የቆምክበት መንገድ የንተን መኖር አልፈለገምና ፈቀቅ በል። ከዝምታህም ከንግግርህም ፈቅ ማለትህ ነውና ውበቱ ሻገር በል። ይሄ መንደር ነብይ በሀገሩ ሆኖብሀልና ተሻገር! ህልምሽ እሁድ ህዳር 7, 2018 ዓ.ም ምሽት 2:25 ወልቂጤ ethioterkaa  ethioterkaa    🌹@ethioterkaa

  • 4 нояб.1 980105

    ጥገኛን ተውና ታታሪውን አሳድገው! የሆነ ጊዜ የዩናይትድ አረብ ኤመሬትስ መስራች ሼህ ረሺድን ኢንተርቪው አድርጌው ነበር። ስለነገዋ ዱባይ ስጠይቀው የሰጠኝ መልስ አስገርሞኝም አስደንቆኝም ነበር ምን አለ? "አያቴ ግመል ይጋልብ ነበር፣ አባቴም ግመል ይጋልብ ነበር፣ እኔ ደግሞ መርሰዲስ እየነዳሁ ነው። የኔ ልጅ ላንድሮቨር ይነዳል። የልጅ ልጄም እንደዚያው ላንድሮቨር ይነዳል። የልጅ ልጅ ልጄ ግን ግመል መጋለቡ አይቀሬ ነው!" "ለምን ?" ለምን ካልከኝማ! "ክፉ ጊዜ ጠንካራ ሰዎችን ይፈጥራል። ጠንካራ ሰዎች ደግሞ ሁሉ ነገር ቀላል የሆነበትን ጊዜ ይፈጥራሉ።ቀላል ጊዜያት በተራቸው ደካማ ሰዎችን ይፈጥራሉ። ደካማ ሰዎች ደግሞ ክፉ ጊዜን መልሰው ያመጡታል።  ብዙዎች አይገነዘቡት ይሆናል ፣ ነገር ግን ይህ እንዳይመጣ  ታታሪዎችን ማሳደግ አለብን። ያ ሲሆን ጥገኞች አይፈጠሩም።" ( Source ; Shiv tandon-on UT&L) Via

  • ★★★ አንድ የህግ ባለሙያ በባቡር እየተጓዘ ሳለ አንድ በጣም ቆንጆ የሆነች ልጅ መጥታ ፊት ለፊቱ ከሚገኘው ወንበር ላይ ተቀመጠች። በዚህም የህግ ባለሙያው ደስ አለው። ቀና ብሎ ሲመለከታት አይን ለአይን ተያዩ ከዛም ፈገግ አለች። አሁን ደግሞ በይበልጥ ደስ አለው። ትንሽ ቆይታ አጠገቡ ሄዳ ተቀመጠች። በዚህን ጊዜ እጅግ በጣም ደስ አለው። ትንሽ ቆየችና ወደ ጆሮው ጠጋ ብላ በሹክሹክታ "ያለህን ገንዘብ; የATM ካርድህን ከነፓስ ዎርዱ እና የሞባይል ቀፎህን አሁኑኑ ካልሰጠኸኝ ስትጎነትለኝ እንደ ነበረና ፆታዊ ትንኮሳ እንደደረሰብኝ እዚህ ባቡር ውስጥ ላሉት ሁሉ በመንገር እጮኃለሁ።" አለችው። የህግ ባለሙያው በቸልተኝነት ቀና ብሎ ተመለከታትና ከቦርሳው ውስጥ ወረቀትና እስክሪብቶ አውጥቶ እንዲህ ብሎ ፃፈላት "ይቅርታ መናገርና መስማት የተሳነኝ ነኝ። እባክሽን ማለት የፈለግሽውን ሁሉ እዚህ ወረቀት ላይ ፃፊልኝ።"ልጅቷም ቀደም ብላ ስትነግረው የነበረውን ሁሉ ጽፋ ሰጠችው። የህግ ባለሙያው ወረቀቱን ተቀብሏት በጥሩ ሁኔታ አጥፎ ኪሱ ከከተተው በኋላ ከተቀመጠበት ተነስቶ ጎርነን ባለ ድምጽ ምን ቢላት ጥሩ ነው "አሁን እንደፈለግሽ መጮህ ትቺያለሽ።"የታሪኩ ምግባር: ሰነድን በአግባቡ መያዝ ምን ግዜም አስፈላጊ ነው። ካነበብኩት ✍️✍️✍️✍️✦✗✦✍️✍️✍️✍️     @ethioterkaa @ethioterkaa @ethioterkaa ✍️✍️✍️✍️✦✗✦✍️✍️✍️

  • በሰዓሊ ጉስታቭ ሞሬው የተሳለ በ1874 -1876 ዓ.ም  ስለ ስዕሉ ትርጉም በቀጣይ ይዘን እንመጣለን   🌹ሼር በማረግ ተባበሩን🌹 @ethioterkaa   @ethioterkaa @ethioterkaa

ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ — tgindex