ETH ZEMA
Статистика- Последний пост
- 25 июл.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 117
- 1/48двое суток
- 134
- 1/72трое суток
- 144
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
"ሕፃን ልጅ እንደ ትልቅ ሰው ሲናገር ያስደንቃል። ትልቅ ሰው እንደ ሕፃን ሲናገር ግን ያሳቅቃል"። ዛሬ ብላቴናው ቂርቆስ፥ "እናቴ ሆይ ገድላችንን እንፈጽም ዘንድ ጨክኚ"። ብሎ እንደ ትልቅ ሰው የተናገረበት ዕለት ነው። ትልቅ ሰው ሆነው እንደ ሕፃን የሚናገሩትን ያሳድግልን።
ፍቅር ቊስል ነው እውነቱ ይህ ነው ፣ ፍቅር የሚለካው በልባችን ላይ በተወው ቊስል ልክ ነው። እጅግ የምንወዳቸው ሰዎች አሳምመውን ይሆናል። እኛም እጅግ የሚወዱንን ሰዎች አሳምመን ይሆናል። ምክንያቱም ፍቅር የሚታየው በታገስነው ቊስል ውስጥ ነው:: ፍቅር የሚታወቀው በተለዋወጥናቸው ቃላት ሳይሆን በታገስነው ቊስል ፣ በተሰማን የውስጥ ሕመም ፣ በከፈልነው መሥዋዕትነትና በተካፈልነው ብርሃን ነው። ከትንሣኤው በኋላ በሐዋርያቱ ፊት የተገለጠው ክርስቶስ እርሱ የሚወዱት ጌታ እንደሆነ ለማስረዳት ያሳያቸው የትንሣኤውን ድል ማብሠሪያ መለከት ሳይሆን ፣ የፍቅሩ ማስረጃው ቁስሉ ነበር።
በአብርሃም ደጅ የተገለጡ ሥላሴ ብቻ አይደሉም። እኒህ ሁሉ ተገልጠዋል እንጂ። 1ኛ ምስጢረ ሥላሴ፦ "ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ" ዘፍጥረት ምዕ 18፥2 ይህ መገለጥ ምስጢረ ሥላሴ ይባላል። ጥንት ሰውን በአምሳላቸው የፈጠሩ ሥላሴ፥ዛሬም ለአብርሃም በሰው አምሳል ተገልጠዋል። መሆንና መምሰል እንደሚለያይ ልብ ይሏል። 2ኛ ምስጢረ ሥጋዌ/የአምላክ ሰው መሆን ምስጢር፦ ልጁ ይሥሐቅን ሊሠዋ ወደሞርያም ተራራ ወጥቶ ነበር። በልጁ ፈንታ በግ ሠውቶ ተመለሰ። ዘፍጥረት 22፥1-14። ይህ ምስጢረ ሥጋዌ ይባላል።በእኛ ስለእኛ የሚሰዋው የቀራንዮ በግ- ክርስቶስ ምሳሌውን በዚያ ተራራ አሳይቶናልና። በደጁ ምስጢረ ሥላሴን በልጁ ምስጢረ ሥጋዌን ተረዳን። 3ኛ ምስጢረ ጥምቀት፦ በኋላ ጌታችን የሚጠመቅበትን ዮርዳኖስን ተሻግሮ ሄዶ ካህኑ መልከጼደቅን አግኝቶት ነበር። ይህ ጉዞው የጥምቀት ምሳሌ ሆኖ ተተርጉሟል። ዘፍጥረት 14፥17-20፡፡ 4ኛ ምስጢረ ቁርባን፦ አብርሃም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ያገኘው ካህን ለሐዲስ ኪዳን ምሳሌ የሆነውን ቁርባን ሰጥቶታል። 5ኛ ምስጢረ ትንሣኤ ሙታን፦ ልጁን ሊሠዋ ወደሞርያ ተራራ በሄደ ጊዜ፥ ልጁ ሞቶ እንደማይቀር እንደሚነሣ ያምን ነበር። ዕብ11፥19::
https://youtu.be/YJBguvLOSx0?si=SmFIYmggk1Wmg0kH
➾"ጠባቂ እንደሌለው በግ እንዳንኾን አባግዕን በዚያም፥ በዚያም ዘልቀው አራዊት እንዲነጣጠቋቸው ተኵላ እንዳይነጥቀን አለ፤ መናፍቃን እንዳያስክዱን። በሃይማኖት ከኛ የተለዩ አሕዛብ መናፍቃን እንዳይነቅፉን። እኒኽ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ጳጳስ ደግ ንጉሥ የማያስነሣላቸው ሃይማኖታቸው የቀና ባይኾን እንጂ ነው ብለው፤ ሐተታ፦ ሕዝቡ ቢከፉ ባይመለሱ በሕዝቡ ክፋት ዓላዊ ንጉሥ መናፍቅ ጳጳስ ያስነሳባቸዋል። ወያነግሥ ብእሴ መደልወ በእንተ እከየ ሕዝብ እንዲል። ሕዝቡ ግን ደግ ቢኾኑ ቢመለሱ በሕዝቡ ደግነት ደግ ራትዕ ንጉሥ ሃይማኖታዊ ጳጳስ ያስነሳላቸዋል፤ ወያነግሥ ብእሴ ራትዓ በእንተ ሠናይተ ሕዝቡ እንዲል፤ ይኽ ከሞተበት ጀምሮ እስኪ ሾም ድረስ የሚጸልይ ነው።"[ሥርዐተ ቅዳሴ ንባቡና ትርጓሜው፤ ምዕራፍ ፰፤ ቍ.፷፭-፷፮፤ ገጽ ፷፱]
+ በእግዚአብሔር መንግሥት አንድ ቀን + ጸአተ ነፍስ (The departure of Soul) ከተሰኘው የኦርቶዶክስ ቴዎሎጂ ምሁራን የጋራ ሥራ የሆነ ዳጎስ ያለ ድንቅ መጽሐፍ መግቢያ ላይ አንድ አባት ስለ አንድ ሰው ታሪክ የጻፉት ነገር በጣም አስገራሚ ነበር:: እጅግ መጥፎ የነበረ አንድ ሰው ድንገት በጠና ይታመምና በአልጋ ላይ ይውላል:: ሕመሙ እጅግ የጠና ቢሆንም የማይገድለው ሆነና ለሠላሳ ዓመታት ተሠቃየ:: በክፉ አመል ላይ ክፉ ሕመም ተጨምሮ ለሌሎችም ችግር ሆነ:: በአልጋው ላይ ሆኖም ደጋግሞ ሰውንም ፈጣሪውንም ይሳደብ ነበር:: ከሠላሳ ዓመታት ሥቃይ በኁዋላ ግን ይህ ሰው ነፍሱ ከሥጋው ተለየች:: የመንደሩ ሰው ተሰበሰበና ማልቀስ ጀመረ:: "ውይ ተገላገለ" "ይኼ ክፉ አረፈ? ያረፍነውስ እኛም ነን!" እያለ በልቡ እያሸሞረ ቁጭ አለ:: አጅሬው ግን ሞተ ከተባለ ሦስት ሰዓታት ቆይታ በኁዋላ ድንገት እንደ እንቅልፍ ነቃ:: ሰዉ ድንጋጤም ደስታም ተቀላቅሎበት ተቀበለው:: ከዚያች ዕለት ጀምሮ ሞገደኛው ሰው እንደቀደመው መናከሱን ትቶ ትሑት ለሰው አዛኝ ሆኖ አረፈው:: የጠሉት ሁሉ ይቅርታ እስኪያደርጉለት ድረስ እጅግ መልካም ሰው ሆነ:: አንድ አባት በሰውዬው መለወጥ ተደንቆ ሞቶ በነበረበት ጊዜ ምን እንደገጠመው ጠየቀው:: እርሱም እንዲህ አለ :- "ከሞትሁ በኁዋላ ለሦስት ሰዓታት ያህል በሲኦል ሥቃይ ውስጥ ቆይቼ ነበር:: በሲኦል ካሳለፍሁት የሦስት ሰዓታት ሥቃይ የምድር ላይ የሠላሳ ዓመት ሥቃይ እጅግ ይሻለኛል:: በሲኦል ሦስት ሰዓት ከመቆየት በምድር ላይ የዕድሜ ልክ ሥቃይ ይሻላል" በእርግጥ የሲኦል የአንድ ሰዓት ሥቃይ ከዚህ ዓለም የዐሥር ዓመት ሥቃይ ከበለጠ ከዚህ ዓለም የዕድሜ ልክ ደስታም የመንግሥተ ሰማያት የአንዲት ቀን ደስታ ይበልጣል:: ንጉሥ ዳዊት "ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች" እንዳለ በመንግሥተ ሰማያት አንዲት ቀን መቆየት ደግሞ በዚህ ምድር ላይ ሺህ ዓመት ከመደሰት ይበልጣል:: “በዚህ ዓለም ብዙ ዘመን ከመኖር በገነት አንዲት ቀን ደስ መሰኘት ይሻላል:: ከብዙ ዘመኖችም አቤቱ ይቅርታህን ማግኘት ይሻላል" 2 መቃ. 13:4
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ልብን ሞቅ የሚያደርግ ዜና ! በዘንድሮው ዓመት ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ካዘጋጃቸው ➠18 ሜዳሊያ ዋንጫውን ጨምሮ ➠14ቱ በግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች የተወሰዱ መሆኑን በማኅበረ ቅዱሳን የባሕር ዳር ማእከል የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ዋና ክፍል ኀላፊ ቀሲስ ምሕረት እንዳለው ገልጸዋል።
ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች!!! "ያዘነች ስትሆን በልጅሽ በወዳጅሽ ትንሣኤ የተጽናናችው፡፡ የተዋረደች ስትሆን በድንግልናሽ ቡቃያ መውጣት ከፍ ከፍ ያለችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች፡፡በዕለተ ዓርብ ከልጅሽ ቀኝ በፈሰሰው ውኃ ተጠምቃ የውግታቱን ደም ተቀብታ ቅድስት ቤተክርስቲያን ታመሰግንሻለች።የልዑል እግዚአብሔር በግ የተባለ ልጅሽ አማኑኤል የተሞሸረባት መርዓዊ ሰማያዊ የተባለባት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች" አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንኳን እመቤታችን ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን!
https://youtu.be/m-gQFYAacdc?si=i2uqSfDXhfyVZLlG
ቤቱ ገብቷል
видео или голосовое, без подписи
የቅዱስ ጳውሎስ ልብስ! በዚህ የሐዋርያት ጾም ሐዋርያው ጳውሎስን እንዴት እያነበባችሁ ነው?
видео или голосовое, без подписи
🎈በምን እጽናናለሁ?🎈በዘማሪ ሚክያስ አረጋዊ 🎈አዲስ መዝሙር 🎈New Mezmur https://youtube.com/watch?v=dJieVgi0-84&si=bRCTL8gCgTZ8RV_m
መጤ እየተባባሉ መገዳደል.. ዘረኝነት በሽታ ነው! በማህበራዊ ሚድያ ላይ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ላይ በጆሀንስበርግ ሽጉጥ ሲተኩሱና ጉዳት ስያደርሱበት ሚታዩት ሁለቱ ወንጀለኞች በደ/ኣ ፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቹውን የሀገሪቱ ሚድያዎች በስፋት እየዘገቡ ነው። በአርሲ ትላንት በድጋሚ ኦርቶዶክሳውያን ተገድለዋል። #join👇👍
የአባታችን ጥፋታቸው ምንድነው????????
видео или голосовое, без подписи