ልብ ወለድ fiction? ስለፍቅር
Статистика❤️✅ያልተነበቡ ድርሰቶችን..ግጥሞችን..የፍቅር ታሪኮችንና ሌሎች መጻጽፎችን ያገኙበታል። Page Join ብለው ይቋደሱ። . . . በfacebook ለመከታተል ከታች ያለውን Link ይንኩት 👇 👉www.facebook.com/fictional27 👇 👇 👉ለማነኛውም ሀሳብ አስተያይት!!! 👇 👇 👉https://t.me/Groups16
- Последний пост
- 15 апр.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
እንኳንስ ሊዘፍን - ሲጠርግ ጉሮሮ አዲስ ዘመን ቢያነብ - ጋዜጣ ደርድሮ ቴዎድሮስ ካሳሁን - ህዝብ ነው ስሜቱ የሀገር ንጉስ ነው - አዋጅ ነው መልዕክቱ። 8 8 8 2018 ስምንት ስምንት ስምንት - ሀያ አስራ ስምንት ንጉሱ ሊያገሳ - ቀርተው ሰዓታት ሀብታም ምን ጎደለው - ድሀ ምን ቸገረው ንጉሱ ሊነግስ - አንድ ሀሙስ ሲቀረው ድግሱ ለወዳጅ - በጣም ነው ያማረው ሀገሩን ሰብስቦ - ህዝቡን ሊያስጨፍረው። ቅኔ ለሚፈሩት - ዘፈን ለሚጠሉት መልስ አለው ንጉሱ - ኃጢአት ነው ለሚሉት። ዘፈን እና ኃጢአት - ምን አገናኛቸው ቴዎድሮስ ገጣጥሞ - ዜማ ከቀባቸው ያሬዳዊ ዜማው - ሀገራዊው ፍቅር ዳዊት በበገናው - አይላቸውም ይቅር። ኢትዮጵያዊው መንፈስ - ያመጣው ደመና ድንገት ከጣላቸው - ለጥበብ ልመና የቴዲ ዘፈኖች አጥንት ይሰብራሉ - መቅኔ ነው ቁርሳቸው ሀገር ነው፣ ህዝብ ነው - የሚጣፍጣቸው። አቡጊዳ ብሎ - በአስራ ሰባት መርፌ በሰባ ደረጃው - ሲያደክመኝ አርፌ ጃንሆይ ኃይሌ እያለ - ምኒልክ ጥቁር ሰው ታጠቅ አባነፍሶ እያለ ከጠራ - ቴዲ ምን አነሰው በእስራ ስምንት ቁጥር - ለምን ተመሰሉ የምን ፍሬ ናቸው - ቀድመው የበሰሉ? አለማወቅ ደጉ - አልመርጥም ቀድሜ በመድረክ አያለሁ - በዕለቱ ታድሜ። ቴዲ አፍሮ ሲዘፍን - አንድ ዘለላ አልመርጥም መሸምደዴ አይቀርም - ጠቅላላውን ግጥም። ኢትዮጵያ ካለ - ኢትዮጵያ እላለሁ ትቅደም ካለ ድንገት - ቦክሴን አሳያለሁ "ኢቶሪካ" ይላል - እቀበለዋለሁ ትርጉሙን አላውቅም ቴዎድሮስ ራስ ነው -ሳባ ወ ህንደኬ - ልብ የሚለቃቅም። 💚💛❤️ በፌስቡክ ለመከታተል https://www.facebook.com/Fictional27
14. የናቅናቸው ወላጆች በወጣትነት ጊዜ ወላጆችን መናቅ ቀላል ነው፤ ወላጆቻችሁ ምን ያውቃሉ? እነሱ የድሮ ዘመን ሰዎች፣ የማይገቡና ጠባብ አስተሳሰብ ያላቸው ናቸው። ነገር ግን ወላጆቻችሁ ብትስማሙባቸውም ባትስማሙባቸውም፣ የአኗኗር ዘይቤያቸው ምንም ይሁን ምን አሁንም ወላጆቻችሁ ናቸው። ወላጆቻችሁ ሳይሞቱ ወይም ከእናንተ ተለይተው ሳያረጁ አትተዋቸው፣ ታረቁ እና ተስማሙ። ስታረጁ፣ ወላጆቻችሁ ለምን ወደ እናንተ መቅረብ እንደፈለጉ ትገነዘባላችሁ። ዕድሜያችሁ በጨመረ ቁጥር ዋጋቸውን የበለጠ ትረዳላችሁ። ስላነበባችሁት አመሰግናለሁ! የእህትን ወይም የወንድምን ዋጋ ለማወቅ የሌለውን ሰው ጠይቁ። የአስር ዓመትን ዋጋ ለማወቅ፦ አዲስ የተፋቱ ጥንዶችን ጠይቁ። የአራት ዓመትን ዋጋ ለማወቅ፦ ተመራቂን ጠይቁ። የአንድ ዓመትን ዋጋ ለማወቅ፦ የማጠቃለያ ፈተና የወደቀ ተማሪን ጠይቁ። የዘጠኝ ወርን ዋጋ ለማወቅ፦ በሞት ና በህይወት መካከል የተወለደ ልጅን የወለደች እናትን ጠይቁ። የአንድ ወርን ዋጋ ለማወቅ፦ ወሩ ሳይደርስ የተወለደ ልጅ የወለደች እናትን ጠይቁ። የአንድ ሳምንትን ዋጋ ለማወቅ፦ የሳምንታዊ ጋዜጣ አዘጋጅን ጠይቁ። የአንድ ደቂቃን ዋጋ ለማወቅ፦ ባቡር፣ አውቶቡስ ወይም አውሮፕላን ያመለጠውን ሰው ጠይቁ። የአንድ ሰከንድን ዋጋ ለማወቅ፦ ከአደጋ የተረፈን ሰው ጠይቁ። አሁንም የአንድ ሰከንድን ዋጋ ለማወቅ፦ ኃይሌን ወይም ቀነኒሳን ወይንም ቦልትን ጠይቁ። ጊዜ ማንንም አይጠብቅም። ያላችሁን እያንዳንዱን ቅጽበት ከፍ አድርጋችሁ ተንከባከቡት (ዋጋ ስጡት)። ተባረኩ🙏❤️ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ በFacebook ለመከታተል http://www.facebook.com/fictional27 በቴሌግራም ለመከታተል https://t.me/fictional27 ለበለጠ ሀሳብ እና አስተያየት https://t.me/Groups16
በእርጅና ዕድሜ ላይ ጸጸትን የሚያስከትሉ ነገሮች በወጣትነት ጊዜያችን ስለ ወደፊቱ ብዙም ሳናስብ የተለያዩ ውሳኔዎችን እናደርጋለን። አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ውሳኔዎች በመካከለኛ ዕድሜያችን ላይ ክፉኛ ዋጋ ያስከፍሉናል። አንድ ሰው ሲያረጅ ሊጸጸትባቸው ከሚችላቸው ነገሮች መካከል ጥቂቶቹ እነዚህ ናቸው፦ 1. የተሳሳተ ሰውን ማግባት በወጣትነት ጊዜ፣ የማግባት ዝንባሌያችሁን መርምሩ። እኩዮቻችሁን ለመፎካከር፣ ለማህበራዊ ክብር ወይም በጫና ምክንያት አታግቡ። ለፍቅርና ለጓደኝነት ብላችሁ አግቡ፣ ትክክለኛውን ሰው አግቡ፣ የልብ ጓደኛችሁን አግቡ። ምክንያቱም የተሳሳተውን ሰው ወይም በተሳሳተ ምክንያት ካገባችሁ፣ ቀሪውን ህይወታችሁን ከዛ ሰው ጋር መጋፈጥ ይኖርባችኋል። በሁለታችሁ መካከል ነገሮች ሊከፉ ይችላሉ፤ ከዚያም በመካከለኛ ዕድሜያችሁ ድብርት፣ አካላዊ ጥቃት፣ ምንዝርነት፣ ህመም፣ እፍረት፣ የፍርድ ቤት ጉዳዮች፣ ምሬት የህይወታችሁ መገለጫ ይሆናሉ፤ ይህ ሁሉ የሆነው የተሳሳተውን ሰው ስለመረጣችሁ ነው። ልጆች ሲኖሩ ደግሞ ነገሮች ይበልጥ ይከፋሉ። በወጣትነታችሁ ትክክለኛውን የትዳር አጋር ምረጡ። 2. ያልተጠቀምንባቸው አጋጣሚዎች በወጣትነታችሁ ብዙ በሮች ይከፈታሉ፣ ብዙ እድሎች ታገኛላችሁ። ብዙ ወጣቶች በፍርሃት፣ በስንፍና ወይም በትዕቢት ምክንያት እነዚህን አጋጣሚዎች ያልፏቸዋል። ነገር ግን ወጣትነትና ጉልበት እያለ አዲስ ሥራ ለመጀመርና ለራሳችሁ ስም ለመገንባት ምርጡ ጊዜ ነው። አንዳንዶች እድሎቹ ለእነርሱ በጣም ትልቅ እንደሆኑ ያስባሉ። እነዚህን አጋጣሚዎች ተጠቀሙባቸው፤ አለበለዚያ አንድ ቀን ስታረጁ ወደ ኋላ ተመልሳችሁ እነዚያን ያመለጡ እድሎች ለመያዝ ትመኛላችሁ። 3. ያፈረስናቸው ድልድዮች (ያቋረጥናቸው ግንኙነቶች) በወጣትነት ጊዜያችን ለግንኙነቶች ብዙም አንጨነቅም፤ አብዛኛው ሰው የሚያስበው በማንኛውም ዋጋ ገንዘብ ማግኘትና የስኬት መሰላልን መውጣት ነው። ብዙዎች ለመሻሻል ሲሉ ሰዎችን ይጠቀማሉ ይረግጣሉም፤ ግንኙነቶችን እንደ ቀላል ነገር ይቆጥራሉ፣ ትስስሮችን ያበላሻሉ፣ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ከሰዎች ጋር ይተኛሉ። ነገር ግን እነዚህ መጥፎ ድርጊቶች ወደፊት ዋጋ ያስከፍሏችኋል። ህይወት ያለ ፍቅርና ጓደኞች ምን ያህል ባዶ እንደሆነ ስትገነዘቡ። ስኬታማ ስትሆኑ ነገር ግን በዙሪያችሁ ማንም ሳይኖር ወይም የሚታመን ሰው ስታጡ። 4. ያስወረድነው ጽንስ በወጣትነት ጊዜ እርግዝና ተከስቶ ፍርሃት ሲኖር፣ ስለዚያች ቅጽበት ብቻ በማሰብ የጽንስ ማቋረጥ አማራጭ በፍጥነት ሊወሰድ ይችላል። ነገር ግን ዕድሜ ገፍቶ በእጅጉ ሲያረጁ፣ ወደ ኋላ መለስ ብሎ ያንን ህጻን ቢይዙት ኖሮ ይመኛሉ። ሀብታም እና ስኬታማ ሲሆኑ፣ ያ የተዉት ልጅ አብሯቸው ሆኖ የልፋታቸውን ፍሬ ቢደሰት ይመኛሉ። ነጠላ ወላጅ መሆን በህይወት ስኬታማ መሆንን ወይም ወደፊት አጋር ማግኘትን አያግድም። 5. የካድነው ልጅ አንድ ሰው ሴትን አስረግዞ፣ ልጅ እንደፀነሰች ስትነግረው ኃላፊነትን ሳይወስድ ሲቀር። ነገር ግን ከዓመታት በኋላ በ50ዎቹ ዕድሜ ላይ ስትሆኑ፣ ኃላፊነት ቢሰማችሁ ኖሮ ትመኛላችሁ፣ ለዚያ ልጅ ወላጅ ብትሆኑ ኖሮ ትመኛላችሁ። ያ ልጅ ሲያድግና ትልቅ ሰው ሲሆን ታያላችሁ ነገር ግን ከመጀመሪያው የካዱት ያደገ ልጅ ላይ ምንም አይነት የወላጅነት መብት አይኖራችሁም። በራስ ምርጫ ኃላፊነት የጎደለ ወላጅ በመሆን ትጸጸታላችሁ። 6. ያፈረስነው ትዳር ጥሩ እጮኛችሁን አገባችሁ፤ በትዳር የመጀመሪያዎቹ ወራት ጥሩ ነበሩ ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ፣ በገንዘባችሁና በመልካችሁ ምክንያት፣ ምንዝርና ጀመራችሁ። ታማኝ አልነበራችሁም። የትዳር አጋራችሁ ለመኗችሁ፣ ልጆቻችሁ መጎዳት ጀመሩ፣ ትዳራችሁ እየፈረሰ ነበር። አንድ ቀን ስታረጁ፣ ያንን መገንባት የጀመራችሁትን ጥሩ ትዳር ምንም ላልጠቀሟችሁ ጊዜያዊ የውጭ ግንኙነት ደስታዎች ስትሉ እንዴት በሞኝነት እንዳፈረሳችሁት ይገለጽላችኋል። በልጆቻችሁና በትዳር አጋራችሁ ላይ ያደረሳችሁትን ጉዳት ትገነዘባላችሁ። 7. የካድነው አምላክ/እግዚአብሔር በእጅጉ ስታረጁ የበለጠ ጠቢብ ትሆናላችሁ፣ ህይወትን ይበልጥ ትርጉም ባለው መንገድ ስትመለከቱ እግዚአብሔር የበለጠ እውን ይሆናል። ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር ባለው ግንኙነት ለመደሰት እርጅናን አትጠብቁ። በወጣትነታችሁ እግዚአብሔርን እወቁ፣ የወደፊት ህይወታችሁን ከእግዚአብሔር ጋር ገንቡ። ዕድሜ ሲደርስባችሁ ወደ እግዚአብሔር የምትመለሱ ወጣት ዓመጸኞች አትሁኑ። 8. ያበላሸነው ሰውነት በሙሉ ህይወታችሁ የምትኖሩበት አንድ ሰውነት ብቻ ነው ያላችሁ። የምታጨሱት ሲጋራ፣ አብዝታችሁ የምትጠጡት አልኮል፣ የምትወስዱት አደንዛዥ ዕፅ፣ የምትመገቡት ጤናማ ያልሆነ ምግብ፤ ይህ ሁሉ ቀስ በቀስ ያጠፋችኋል። በ50 ዓመታችሁ የአኗኗር ዘይቤ በሽታዎች ሲይዟችሁ፣ በወጣትነታችሁ ሰውነታችሁን ብትንከባከቡት ኖሮ፣ የበለጠ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ብትሰሩ ኖሮ ትመኛላችሁ፤ ነገር ግን ያኔ ጉዳቱ ደርሷል። 9. ያባከንነው ጊዜ በወጣትነታችሁ በጭንቀት፣ በተሳሳቱ ግንኙነቶች፣ በስንፍና፣ ሶፋ ላይ ተለጥፎ በመዋል፣ ሰበብ በመስጠትና ትርጉም የለሽ ነገሮችን በማሳደድ የምታባክኑትን ጊዜ፤ መቼም አታገኙትም። 10. የቀበርናቸው/ያልተጠቀምንባቸው ተሰጥኦዎችና ህልሞች በወጣትነታችሁ ተሰጥኦ አላችሁ? ልታደርጓቸው የምትወዷቸውና የተካናችሁባቸው ነገሮች አሉ? እነዚያን ተሰጥኦዎች አዳብሯቸው፣ ተጠቀሙባቸው፣ እንቅፋቶች ቢያጋጥሟችሁም ተስፋ አትቁረጡ፣ በህልሞቻችሁ ተስፋ አትቁረጡ። ተስፋ ከቆረጣችሁ፣ ስታረጁ ከሚወዱት ነገር ጋር ጸንተው የቆዩና ስኬታማ የሆኑ እኩዮቻችሁን አይታችሁ "ይህ እኔ ልሆን እችል ነበር" ብላችሁ ታስባላችሁ። የምትወዱትን ሙያ ተከታተሉ፣ የምትወዱትን የትምህርት መስክ አጥኑ። የማያስደስታችሁን መስክ ውስጥ የህይወታችሁን ዓመታት አታባክኑ። 11. ያጎደፍነው ስም ስታረጁ፣ ውርስ (legacy) በጣም አስፈላጊ ነው፣ የስማችሁ ዋጋ ወሳኝ ነው። ዝናችሁ ምንድን ነው፣ ምን ትታችሁ ነው የምታልፉት? ብላችሁ ራሳችሁን ትጠይቃላችሁ። ውርሳችሁ ከወጣትነታችሁ ጀምሮ የሰራችኋቸው ድርጊቶች ድምር ውጤት ነው። የህይወት ታሪካችንን የምንጽፈው በየዕለቱ በምንኖረው ህይወት ነው። የሄዳችሁበትን መንገድ መለስ ብላችሁ ስትመለከቱና በራሳችሁ ስም ላይ የወረወራችሁትን ጭቃ፣ የሳባችሁትን ውርደትና ለአለም የጨመራችሁትን ትንሽ ዋጋ ስታዩ፤ ትጸጸታላችሁ። 12. በከንቱ ያጠፋነው ሀብት በምርታማ የሥራ ዘመናችሁ ጥሩ ገንዘብ እያገኛችሁ ነው? ጥሩ ገንዘብ ታገኛላችሁ? ያንን ገንዘብ በክለቦች፣ በግዴለሽነት አኗኗር እና አባካኝ ግዢዎች አታጥፉት። በዚያ ገንዘብ ኢንቨስት አድርጉ፣ የገቢ ምንጫችሁን አስፉ፣ ያ ገንዘብ ለእናንተ እንዲሰራ አድርጉ እና በእርጅና ዘመናችሁ እንዲንከባከቧችሁ በአስተማማኝ ቦታ አስቀምጡት። ለምትወዷቸው ሰዎች ውርስ ተዉ፤ በዚህም "ምነው ባውቅ ኖሮ" እንዳትሉ። 13. ያመለጠን/ያስከፋነው ጥሩ ፍቅር በህይወታችሁ ውስጥ በጥሩ ሁኔታ የሚወዳችሁ ታላቅ ሰው አለ? ያንን ሰው አትግፉት፤ አለበለዚያ ያ ሰው ከህይወታችሁ ይወጣል እናም እንደዚህ አይነት አስደናቂ እና በሙሉ ህይወታችሁ የሚስማማችሁን ሰው መቼም አታገኙም። "ከዚያ ሰው ጋር አሁንም ብሆን ኖሮስ?" በሚሉ ሀሳቦች እያረጁ መሄድ ያሰቃያችኋል።
видео или голосовое, без подписи
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ አጭር የፍቅር ታሪክ ...💑💋 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ በአንድ ወቅት ሁለት እጅግ የሚዋደዱ ፍቅረኛማቾች ነበሩ፡፡ በፍቅራቸው ሙሉ አካባቢው ይቀናባቸዋል፡፡ ከእለታት አንድ ቀን ግን በአንድ ሆቴል ልጆቷ በድንገት ከሌላ ወንድ ጋር ትታያለች፡፡ በዚህ ሰአት የሆነ ሰው ደውሎ "ና የፍቅረኛህን ቅሌት ተመልከት" ብሎ ይነግረዋል፡፡ ልጁም ካለበት በፍጥነት ሲመጣ ክፍል ይዘው ገብተዋል፡፡ ገቡ ወደ ተባለበት ክፍል ቀርቦ ሲያዳምጥ ከውስጥ ይሳሳቃሉ። እስከመጨረሻው የመታገስ አቅም አልነበረውም፡፡ በኔ ላይ ሌላ ወንድ ? ሲል ይናደዳል ፡፡ በዚህ ግዜ የሷ ጉዋደኛ የሆነች ልታፅናናው ትቀርበዋለች፡፡ እሱም አጋጣሚውን በመጠቀም እንደውም ላስቀናት በሚል እሷ በምታየው ቦታ ጓደኛዋን እየወሰደ ያዝናናታል እንደፍቅረኛ አድርጎ ለሰው ያወራል፡፡ ከ ወር ቡሀላ ፍቅረኛው ሞተች፡፡ በዚህ ግዜ በእናቷ በኩል አንድ ደብዳቤ አስቀምጣለት ነበር፡፡ እሱ የኔ ግፍ ነው ብሎ በቀብር ስርአቱ ላይ እንኳን አልተገኘም፡፡ እናትየዋ ባለበት ሄዳ የልጇ አደራ የሆነውን ደብዳቤውን ሰጠችው፡፡ ደብዳቤው ይህን ይላል፡፡ "ውዴ የኔ ፍቅር አንተ አዝነክብኛል እኔ ግን ተደስቻለው፡፡ ያን ቀን ሆቴል ደውዬ እንድትመጣ ያደረኩት እኔ ነኝ፡፡ በዛ ክፍል ውስጥ ምንም አልተፈጠረም፡፡ አንተ በኔ ተናደክ ወደሌላ ሴት እንድትሄድ የሰራውት ድራማ ነበር፡፡ በሀዘንህ ሰአት ያፅናናችክ ጉዋደኛዬ እኔ ነኝ የላኳት፡፡ እሷ በጣም ትወድካለች ፡፡ እንዳትተዋት፡፡ አንተ እኔን ለማስቀናት ፍቅር ስትሰጣት ሳይ እኔ እደሰት ነበር ያንን ፍቅር ከልብህ አድርገው፡፡ ደስታህን አይቼ በመሞቴ እድለኛ ነኝ፡፡ ቢያንስ ብቻክን አልተውኩህም፡፡ ይሄንን ያደረኩት ዶክተሩ ባለብኝ ካንሰር ምክንያት ለመሞት ቢበዛ 30 ቀን ብቻ እንደቀረኝ ስለነገረኝ ነው፡፡" "ፍቅር ማለት አብረው ላሉት ብቻ ሳይሆን ትተውት ለሚሄዱትም ደስታ መጨነቅ ነው፡፡" ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ በFacebook ለመከታተል http://www.facebook.com/fictional27 በቴሌግራም ለመከታተል https://t.me/fictional27 ለበለጠ ሀሳብ እና አስተያየት https://t.me/Groups16 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይጠብቅልን አሜን ❥❥_🇪🇹_❥❥
እ-ረ-ስ-ቼ-ዋ-ለ-ሁ! #Ethiopia | አንድ ሴት ወደ አንድ መንፈሳዊ አባት ዘንድ ቀርባ "እግዚአብሔር ሁሌም ያናግረኛል" ትላቸዋለች። በሴትዮዋ ሁኔታ ግራ የተጋቡት እኚህ አባትም በሁኔታው ተበሳጭተው ጥለዋት ይሄዳሉ። ከዚያን ቀን በኋላ እቺ ሴት እየደጋገመች በመምጣት "እግዚአብሔር ማታ ማታ እየመጣ ያናግረኛል" ትላቸዋለች። በሴትየዋ ጭቅጭቅ የተሰላቹት እኚህ አባትም እንደለመደችው አንድ ቀን መጥታ ስታናግራቸው እንዲህ አሏት .... "እውነት አንቺን እለት እለት እየመጣ ፈጣሪ የሚያናግርሽ ከሆነ አምንሽ ዘንድ ሁለት የቤት ሥራ ልስጥሽ" አሏት ትኩር ብለው እየተመለከቷት! ሴትዮዋም የሚሏትን ሁሉ ለማድረግ ቃል ገባች! ፡ እኚህ አባትም ከዚች ሴት ጭቅጭቅ ይገላግለኛል ያሉትን ጥያቄ አቀረቡላት እንዲህ በማለት "እውነት አንቺን እግዚአብሔር የሚያናግርሽ ከሆነ እስቲ ዛሬ ማታ ሁለት ጥያቄ ጠይቂልኝ" አሏት። ሴትየዋም በእርጋታ "ምን ልጠይቅልዎ አባቴ?" አለቻቸው። አባትም ጥያቄያቸውን እንዲህ ሲሉ ቀጠሉ አንደኛው የቤት ስራሽ "አንዲት ሴት ከእኔ ዘንድ በተደጋጋሚ እየመጣች አንድ በጣም ህመም የሆነባትን ችግሯን እያነባች እየነገረቺኝ ትሄዳለች። እኔም ይሄ ችግሯ ይወገድላት ዘንድ እየጸለይሁላት ነው፡፡ እስቲ እውነት ፈጣሪ ካንቺ ጋር የሚያወራ ከሆነ ይህቺ ሴት ለኔ አንብታ የነገረቺኝ ችግሯ ምን እንደሆነ ጠይቂልኝ አሏት፡፡ ሁለተኛው የቤት ስራሽ "ለረጅም አመት ልተወው ያልቻልኩት የዛሬ ወር ገደማ ግን ንስሀ ገብቼ የተውኩት አንድ ከኃጢያት እሰራ ነበር። ያ በፊት እሰራው የነበረ አሁን ግን ንሰሀ ገብቼ የተውኩት ኃጢያት ምን እንደነበረ ጠይቀሽ ንገሪኝ። እነዚህ ሁለቱን ጥያቄዎች በትክክል ከነገርሺኝ እውነትም ላንቺ እግዚአብሔር እንደሚናገር አምናለሁ" አሏት። ሴትዬይቱም ወደ ቤቷ ሄደች። አባት ተመልሳ እንደማትመጣ ገምተው ነበር። ዳሩ ግን በንጋታው ያቺ ሴት መጥታ አባን አስጠራቻቸው። አባም ሴቲዮይቱን ሲያዩ በጣም ተገርመው ወደ እርሷ በመሄድ በፌዝ መልክ "እህስ ልጄ! ... እግዚአብሔርን የሴትቷን ችግር ምን እንደ ሆነና እኔም እግዚአብሔርን ንስሀ ገብቼ ያቆምኩት ኃጢያት ምን እንደነበር ጠየቅሺው?" አሏት ሳቅ እያሉ፤ "አዎን አባ" አለቻቸው ሴትየዋ አንገቷን እንዳቀረቀረች ... "እህሳ ምን አለሽ?" አሏት አባ በመጓጓት ... "የሴቷ ችግርና ጭንቀት ልጅ መውለድ አለመቻሏ ሲሆን የእርስዎን ግን እረስቼዋለሁ አለኝ" አለቻቸው፡፡ እኚህ መንፈሳዊ አባት ባልገመቱት ሁኔታ እውነተኛውን የልጅቷን ጭንቀት ሲሰሙ እጅግ ደነገጡና ለእርሳቸው ኃጥያት የእግዚአብሔር ምላሽ ልባቸው ተነክቶ ስቅስቅ ብለው እያለቀሱ ወደ ደረታቸው አስጠግተው አቀፏት! እ.. ረ .. ስ .. ቼ .. ዋ .. ለ .. ሁ ..!! ሰው እንጂ እግዚአብሔር ያለፈ ስህተትህን አያስብም ወይም እንደ ፍርድ ቤት የሰራሃውን ነገር ፋይል አድርጎ መዝገብ ቤት አያስቀምጠውም.... በቃ ወደ እርሱ በንስሃ ስትቀርብ ጥፋትህን ሙሉ ለሙሉ ይረሳዋል። ይቅርታዉ ትላንትን አያስብም። የሰው ልጅ ግን ሙሉ ይቅርታ የለውም። ዛሬ ምን ፍሪዳ አርዶ ቢታረቅህ፣ ምን በልቅሶ ታጅበህ እየተንፈራፈርክ ይቅር በለኝ ብትለው "ይቅር ብዬሀለሁ" ይልህና የሆነ ቀን ስታስቀይመው ይቅር ያለውን በደልህን እየቆጠረ ሲወቅስህ ይውላል! በአንድ ወቅት ያደረግከኝን የረሳሁት እንዳይመስልህ ይልሃል። እግዚአብሔር ግን ይቅር ካለህ በቃ ረሳው! ፍቅር ነዋ! ታዲያ ስንቶቻችን እንሆን እግዚአብሄርን በኛ መጠን መትረን ንስሀ በገባንበት ኃጢያት ዘወትር የምናለቅስ? ስንቶቻችን እንሆን እግዚአብሔር እንደኛ ቂመኛ መስሎን በፍቅር ያጠበውን ኃጢያታችንን እያስታወስን ዘወትር በፀፀት አለንጋ ራሳችንን የምንገርፍ? ... ይቅርታ ከመለመን እኮ ይቅር ማለት ይከብዳል! ምሬሀለሁ ከማለት ማረኝ እያሉ እግር ስር መደፋት አቤት በቀለለ! በህይወታችን የገፋንና ያቆሰለንን ሰው በደል ከመርሳት እኮ ሺህ ጊዜ ፍሪዳ እያረዱ "እንታረቅ" ማለቱ እጅግ ቀላል ነው...! ለዚያም ነው መሰል ኢየሱስ ክርስቶስ ፀሎት አስተምረን ባሉት ጊዜ "እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል አንተም ይቅር በለን" ብላችሁ ፀልዩ ያለን ... "እግዚአብሔር ይቅርታን የሚጠይቅ አንደበት እና ይቅርታን የሚያደርግ ልብ ይስጠን!" አሜን! በፌስቡክ ለመከታተል http://www.facebook.com/fictional27 በቴሌግራም ለመከታተል https://t.me/fictional27 ለበለጠ ሀሳብ እና አስተያየት https://t.me/Groups16 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ መልካም ጊዜ ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይጠብቅልን አሜን ❥❥__⚘_❥❥
የአንድ የታወቀ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆነ ፕሮፌሰር የሚከተለውን ድንቅ ጥናት እንዳገኘ በቅርቡ ይፋ አድርጓል!! ጥናቱም የእንግሊዘኛ ፊደሎችን ከመጀመሪያው አስከመጨረሻው በቅደም ተከተል አስቀመጠA b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z። የነዚን ፊደላት አሃዳዊ ቅደም ተከተል ኣስቀመጠ 1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17 18 19 20 21 22 23 24 25 26 በጥናቱም ለያንዳንዱ ፊደላት በቁጥር ቅደም ተከተል ሚዛን ሰጠ ለ"A"=1 ፣ ለ"B"=2 ......... እያለ አስከ "Z" =26ን ሰጠ።በመጨረሻም የቃላት ደረጃን መመዘን ያዘ። 1. ትጉ ስራ (H+a+r+d+w+o+r+k) (8+1+18+4++23+15++18+11)=98% 2. እውቀት (K+n+o+w+l+e+d+g+e) (11+14+15+23+12+5+4+7+5)=96% 3. ፍቅር (L+o+v+e) (12+15+22+5)=54% 4. እድል (L+u+c+k)=47% በዚህ መሰረት ከላይ የጠቀስናቸው ቃላት አንዳቸውም ለውጥ መቶ ፐርሰንት(100%)ሊሰጡ አንደማይችሉ አስቀመጠ። ታዲያ (100%)ሊሰጠን ሚችለው ጉዳይ ምንድን ነው? ብር ይሁን እንዴ?? 5. ገንዘብ (M+o+n+e+y) (13+15+14+5+25)=72% አይደለም ምን አልባት አመራር ይሁን? 6. አመራር (L+e+a+d+e+r+s+h+i+p) (12+5+1+4+5+18+19+8+9+16)=97% አሁንም አይደለም! ለሁሉም ነገራት መፍትሄ አለው። አስተሳሰብ፣አካሄድ አኳኋናችንን ስንቀይር ይቀየራል። ስለዚህ አስተሳሰብ ሁኔታን ሞከረ። 7. አስተሳሰብ (A+t+t+i+t+u+d+e) (1+20+20+9+20+21+4+5)=100% እናም ወዳጄ ውጤትና የ100% ለውጥ ሊያመጣልን የሚችለው የአስተሳሰብ ለውጥ መሆኑን አረጋገጠ። © ከወደዱት Share,Like and comment ያድርጉ😍 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይጠብቅልን ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ❥❥________⚘_______❥❥
😘የከንቲባው ልጅ😘 ✍ደራሲ ተስፋዬ በትሩ #የመጨረሻው ክፍል አሜሪካ እንደማትሄድ ለአባቷ አሳውቃ በሰላምና በዕንባ ተለያይተዋል ። አባቷም ከሚስቱና ከህፃን ልጁ ጋር ወደ አሜሪካ በረዋል ። ከሰኔ #13 እስከ #21 final ፈተና ተፈትነን ስንጨርስ ከመሄዳቸው በፊት አባቷን አግኝቼ አነጋግሬያቸው ነበር ። ስለ ሁሉም ነገር እንዲህ ብለው ነገሩኝ ። "ከአራት ዓመት በፊት ወደ ስልጣን እንደመጣሁ አካባቢ በስራ ላይ አንዲት ሴትን ተዋወኩኝ ። በድሬዳዋ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር ናት ። ሁለታችንን አንድ የሚያመሳስለን ነገር ነበር ። እሷ ባሏን እኔ ደግሞ ሚስቴን በሞት አጥተናል ። በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ውስጤን ሰርስራ ገባች ። በስራና በኑሮዬ ጭምር ገብታ ታግዘኝና ትረዳኝ ጀመር ። በዚህ መሀል ግን አንድ ችግር ነበር ። እሱም በዙሪያችን ያሉ ሰዎች በኛ ስራና ግኑኝነት አለመደሰት ነበር ። የሚገርምህ ሁሉም በአንድነት ይቺን ምስኪን ከተማ ለራሳቸው ጥቅም ለማዋል ሲስማሙ እሷ ብቻ ነበረች ከጎኔ የነበረችው ። ድሬዳዋ ከተማ በሁለት ክልል መሃል ያለች በመሆኗ በየ አራት ዓመቱ ባለስልጣናት አንዴ ከኦሮሚያ ከአራት ዓመት በዋላ ደግሞ ከሶማሌ ክልል እያለ ተራ በተራ #4 ዓመት እየጠበቀ ስለሚፈራረቅ ሁሉም ባለስልጣናት ሀሳባቸው ድሬን ማልማት ሳይሆን እራሳቸውን ማልማት ነበር ። እኔ ደግሞ ከንቲባ የሆንኩበት ዋነኛው ምክንያት ይህንኑን ስርዓት ለማጥፋት ነበር ። ከዛ በዋላ ያለው ታሪክ ህይወት እንደነገረችህ ነው ። የኛን መንገድ የማይከተሉ ሰዎች በበቀል ተነሳስተው ልጄን ለመግደል ብለው አቤልን ቀጠፉ ። እናም ወጣት ተስፋዬ ባለፈው ተከትለኸኝ ያየሀት ሴት በዛ አስቸጋሪ ጊዜ ከጎኔ የነበረች ጀግና ሴት ናት ። በዛው ወቅት በመሃላችን በተፈጠረው የፍቅር ግኑኝነት ልጅ ፀነሰችልኝና ተወለደ ። ይሄን ሁሉ ታሪክ ደግሞ ለልጄ በጊዜው እንዳልነግራት ለራሷ በጣም መጥፎ ሁኔታ ውስጥ ነበረች ። እንዴት ልጄ ላይ የመግደል ሙከራ ተደርጎ በጣም የምትወደው ጓደኛዋ ሞቶ ስለራሴ ደስታና ሀሴት እነግራታለሁ ...? ምን አይነት ስቃይ ውስጥ እንደነበረች ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው ። አሁን አንተን ስታገኝ ነው እንደዚህ ተቀይራ ያየሀት ። ለማንኛውም ሁሉንም ነገር ወደ ውጪ ስንሄድ ላሳውቃት ነበር የፈለኩት ። ባለቤቴንና ትንሹ ልጄን ከህይወት ጋር አንድላይ አሜሪካ ወስጄ ለሁሉም እውነታውን ልገልጽ ነበር እቅዴ ። እንደምታየው አሁን ሁሉም ነገር ተበላሽቷል ። ልጄም አኩርፋኝ ሸሽታኛለች" አሉኝ በሀዘን ። በስተመጨረሻ ልንለያይ ስንል ያሉኝን ግን እስካሁን ድረስ አምኜ አልተቀበልኩትም ። እንዲህ ነበር ያሉኝ "የህይወትን በህይወት መኖር ከኔና ካንተ ውጪ ማንም ሰው አያውቅም ። ለህይወት በህይወት መኖር ሲባል ይህ ምስጢር እንዲቀጥል እፈልጋለሁ ። እሷን ካንተ ለይቼ ወደ ውጪ ልወስዳት አልችልም ። ስለዚህ ልጄን ላንተ ሰጥቼሃለሁ ። ይዘሃት ወደ ሀገርህ ሂድ ። ከፈለጋችሁ እዛው ፤ ካልሆነም ደግሞ አዲስ አበባ ደስ የሚል ኑሮ መኖር ትችላላችሁ ። ዕድሜያችሁ ከ #20 ስላለፈ እራሳችሁን ችላችሁ መኖር አይከብዳችሁም ። ለብር ደግሞ ብዙም አትጨነቁ ። በባንኳ ውስጥ አንቀባሮ የሚያኖራችሁ በቂ ገንዘብ አለ" ። ታድያ የህይወት አባት እንዲህ ብለው መርቀው ልጃቸውን ሲሰጡኝ እንዴት ብዬ ልመን ...? በሌላ በኩል ደግሞ ማራኪዬ ስለኔ ምን እያሰበች እንደሆነ ለማወቅ በስልክ ሳዋራት "ሙሉ በሙሉ እንደረሳችኝና ሌላ ህንወት እንደጀመረች" ነገረቸኝ ። አሁን ከህይወት ጋር ነኝ ። ከቤተሰቦቼ ጋር አስተዋወኳት ። ለቤተሰቦቼም ሁሉን ነገር ነግሬያቸው ተስማምተን አዲስ አበባ አዲስ ህይወት ከህይወት ጋር ለመጀመር ተዘጋጅተናል ። ልክ እንደባልና ሚስት ሳይሆን እንደ ፍቅር ለመኖር ጉዞ ጀምረናል ። ከህይወት ጋር ስትኖር ፤ በህይወት መኖርህን ትወደዋለህ ። ስለ ህይወት ለማውራት ፣ እኔ ቃል የለኝም ፤ እሷ ካለች አለሁ ፣ ያለዚያ ግን የለሁም ። ህይወት መዝሙር ነች ፤ ዘምራት ህይወት ሰቀቀን ነች ፤ ቻላት ህይወት ተግባር ነች ፤ ተወጣት ህይወት ሽፍንፍን ነች ፤ ግለጣት ህይወት ሀዘን ነች ፤ ተቋቋማት ህይወት ስጦታ ነች ፤ ተቀበላት ህይወት ውርርድ ነች ፤ ተወራረዳት ህይወት ትግል ነች ፤ ታገላት ህይወት ምስጢር ነች ፤ ፍታት ህይወት ውበት ነች ፤ አጊጣት ህይወት ጉዞ ነች ፤ አጠናቃት ህይወት ቃል ነች ፤ አሟላት ህይወት አጋጣሚ ነች ፤ ተጠቀማት ህይወት ጀብዱ ነች ፤ ድፈራት ህይወት ፍቅር ነች ፤ ፈልጋት ። . . . . ✍🏽~~~ተፈፀመ~~~~✍🏽 ☞ የስው ልጅ መጨረሻው ሲያምር ነውና ፤ ፈጣሪ መጨረሻችንን ያሳምርልን! እኔ አሜን ብያለሁ፡፡ #ይሄ የባለታሪኩ የተስፋዬ በትሩ መገኛ አድራሻ ነው...ገንቢ አስተያየታችሁን እንደምታደርሱት...መልካም ምኞታችሁን እንደምትገልጹለት አምናለሁ።👇👇 #እኔም የተስፋዬና የህይወት ፍቅር አብቦ ወደሌላኛው የህይወት ምእራፍ እንደሚሸጋገሩ...ትዳራቸው ሰምሮም ፍሬ እንደሚያዩ ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ ...አመሰግናልሁ።።😘 ውድ Fictional27 ፔጅ ተከታታዮች ፦ ደበረን ሰለቸን ሳትሉ ወርቅ ግዜያቹን ሰውታቹ ጀምሬ እስከምጨርስ ድረስ ስለተከታተላችሁኝ ፣ እንዲሁም በውስጥ መሰመር እየገባቹ ላስተካክለው የሚገባኝን እንዳስተካክል ስለረዳቹኝ ከልብ አመሰግናለሁ እወዳችዋለሁ፣ አከብራችዋለሁ በሌላ ታሪክ እስከምንገናኝ መልካሙን ተመኘሁላቹ፡፡ ©fictional27 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ መልካም ንባብ ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይጠብቅልን አሜን ❥❥________⚘_______❥❥
😘የከንቲባው ልጅ😘 🔥ክፍል 40 ✍ደራሲ ተስፋዬ በትሩ #ሊጠናቀቅ 1 የመጨረሻ ክፍል ብቻ ይቀረዋል.. ህይወት ለጊዜው ሆቴል ይዤ መረጋጋት ይኖርብኛል ብላኝ ነበር ። እኔ ግን ለብቻዋ እንድትሆን ስላልፈለኩኝ ከሷ ጋር ተቀራራቢ መልክ ካላት የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ልጅ ID card ለምኜ ወደ ጊቢ ይዣት ገባሁ ። በር ላይ መታወቂያውን ልብ ብለው ስለማያዩት ማንም በማንም ሰው ID መግባት ይችላል ። በህይወቷ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዩኒቨርሲቲ ስትገባ ደንግጣ ነበር ። እንደ high school ጠባብ አይደለም ። በዛላይ ከ #15 ሺህ በላይ ተማሪዎች በአንድ ጊቢ ውስጥ ስለሚኖሩ ብዛታቸው ትንሽ ግር ይላል ። ሰዓቱም ወደ ምሽት እየተጠጋ በመሆኑ አብዛኛው ተማሪ ለእራት ከጊቢ እየወጣ ነበር ። ለተባበረችን ልጅ Id መልሼ ፡ እኛ እንደነገሩ ጊቢ ውስጥ ካለው ላውንጅ እራት በልተን ከዚህ በፊት ብቻዬን አዘውትሬ የምቀመጥባት ፣ ከማራኪዬ ጋርም ስልክ የማወራባት የነበረው ቦታ ወሰድኳት ። ቦታው ጨረቃን ወለል አድርጎ ከማሳየቱም በተጨማሪ ጭር ያለና ፀጥታ የሰፈነበት ፣ በዛላይ ደግሞ እራስን ለማዳመጥ በጣም አመቺ ነው ። "ሳልማር ዩኒቨርሲቲ ገባሁ አይደል...?" አለችኝ ህይወት በተከፋ ድምፅ ። እንዳይሰማት ብዬ 'እኛ ተምረን ይመስልሻል እዚህ የደረስነው ...? ዩኒቨርስቲ ከገባ ውስጥ #10% አይሆንም ተምሮና በራሱ ጥረት እዚህ የገባው ። አብዛኛው ኮርጆ ፣ አንዳንዱ ደግሞ ሳያስበው ነው እራሱን እዚህ ቦታ ላይ ያገኘው ። ዞረሽ ብትጠይቂያቸው "እኔ ለቤተሰቦቼ ብዬ ነው የምማረው ፡ እኔ ላይፉን ለማየት ነው የመጣሁት ፣ እኔ ከ famly ርቄ ነፃነቴን ለማግኘት ነው የመጣሁት ፣ ወዘተ ይሉሻል ። አላማ አለኝ ፣ ትምህርቴን ጠንክሬ ጨርሼ ለሀገሬና ለወገኔ እንደዚህ ላደርግ ነው የመጣሁት የሚልሽ በጣት የሚቆጠሩ ልጆች ብቻ ናቸው ። ታዲያ አንቺስ እንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ባለመግባትሽ ማመስገን እንጂ ማማረር ነበረብሽ ...?' አልኳት ። ደግሞም የምሬን ነው ። የከሰረ ትውልድ ይዛ ፣ ትርፍ ለማግኘት የምትሯሯጥ ሀገር ላይ ነን ። ይሄንን ትውልድ ማስተማር ያለብን physics ፣ chemistry ፣ biology ሳይሆን ትምህርት ምን እንደሆነ ፣ ምን ምን ጥቅም እንዳለው ፣ በወሬ ብቻ ሳይሆን በተግባር ጭምር ማሳየት አለብን ። ከሁሉ ነገር መቅደም ያለበት ለትምህርት ያለን ፍቅርና ፍላጎት ነው ። እሱ ላይ ከተሰራ ሌላው ሁሉ በራሱ ጊዜ ይመጣል ። ይሄ ትውልድ ትምህርት የሚለውን ቃል እራሱ መስማት አይፈልግም ። በቃ ከሰይጣን በላይ ጠልቶታል ። ስለዚህ የጠላውን ነገር በግድ ተማር ከምንለው ፡ ለምን እንደጠላ መርምረን ፣ ምን ብናደርግ ደግሞ መውደድ እንደሚችል አስበን ወደ ቀልቡ መመለስ የተሻለ ይሆናል ። እንዲሁ ስለ ዩኒቨርስቲ እያወራን እያለ #01:30 ላይ የህይወት አባት እቤት ገብተው አጧት መሠለኝ ስልኳ ላይ ደወሉ ። አንስታው እንድሰማቸው ነው መሠለኝ loud speaker ላይ አደረገች ። "የኔ ህይወት ፡ የት ሄደሽ ነው ፣ ከቤት አጣውሽ እኮ ...?" ሲሏት "አያይ ብዙም አልራኩም ፡ ባሌንና ልጄን አይቼ ለመመለስ ብዬ ነው" አለቻቸው ፈርጠም ብላ ። "ስለምን ባልና ልጅ ነው የምታወሪው ልጄ ...?" አሏት መልሰው ። ህይወትም ትንሽ የፌዝ ሳቅ እንደመሳቅ አለችና "ለካ አልነገርኩህም ፡ ባል አለኝ እኮ ፣ ለዛውም አንድ ቆንጂዬ ህፃን ልጅ ከሶስት ዓመት በፊት ወልደናል" አለቻቸው ። ምንም መልስ የለም ፣ ፀጥ ፡ ሴኮንዱ ይቆጥራል ፡ አሁንም ግን ምንም አይነት መልስ ከህይወት አባት አልመጣም ። ህይወት ዝምታው ሲበዛባት "አየህ ፡ ምንም መልስ የለህም ። ቆይ ግን እስከመች ነበር እኔን ለመደበቅ ያሰብከው ፣ እስከዘላለም ...? ንገረኛ ...? ለማንኛውም ከኔጋር ከምታሳልፈው ቅዳሜና እሁድ ይልቅ ከነሱ ጋር የምታሳልፋቸው አምስት ቀናት የተሻሉ ስለሆኑ እነሱ ይሻሉሀል ። ቆይ ግን ልጅ አለኝ ፣ ሚስት አለኝ ብትል የምቃወምህ መስሎህ ነበር ...?" ስትላቸው "የኔ ልጅ እቤት ተመለሺና እናውራ" ብለው ይማፀኗት ጀመር ። "ሶስት ዓመት ሙሉ እኮ እቤት ነበርኩ ። ያኔ የት ነበርክ ። ለማንኛውም አትፈልገኝ ፣ የተሻለ ቦታ ላይ ነው ያለሁት ። መገናኘት ሲያስፈልገን እራሴው እቤት እመጣለሁ" ብላ ስልኩን ዘጋችው ።ምንድነው ሰው ሁሉ ነጫጭ ክንፍ አብቅሎ መላክ የመሰለው ፣ እንዴት ነው ሰማዩ እንዲህ ተጠቅልሎ በእጄ የምይዘው መሀረብ ያከለው ፣ ኧረ ምን ተዓምር ነው ፡ መሬት መዞር ትታ በእፎይታ ያቆማት ፣ ምንድነው ጨረቃን ከሰማይ አውርዶ ምድር ያሳረፋት...? እያልኩ አስባለሁ ። ደግሞም አላቆምም መልሼ መላልሼ አሁንም አስባለሁ ። ማነው በመንገዴ ሳልፍ እልል የሚለው አበባ ነስንሶ ፣ ማንስ ነው ግማሽ ልቤን ሸርፎ የወሰደው ፡ በትልቁ ቆርሶ ፣ መንገደኛው ሁሉ የተከፋ ፊቱን በማን ተነጠቀ ፣ ከጨፍጋጋ ፊት ላይ እንዲህ ያለ ብርሃን እንዴት ፈነጠቀ ፣ ሚሊዮን ህፃናት ከልብ በሚነሳ ስርቅርቅ ድምፃቸው ፡ የት ቢዘምሩ ነው ልቤ ሚሰማቸው ፣ እኮ በምን ምክንያት ይህ ሁሉ ተቀየረ ፣ ያልነበረ ወደነበረ እንዴት ተመለሰ ...? እያልኩ አስባለሁ ። አሁንም አስባለሁ ። ምንድነው እንደዚህ ፊቴን በብርሃን ፡ ከንፈሬን በውብ ሳቅ የሚያጥለቀልቀው ፣ እንዴትስ ነው ከልቤ ኮለል ያለ ሰላም በጠዋት የሚፈልቀው ፣ የጠሉኝን ሁሉ ድንገት መውደዴ ፡ መሬቱን ለቅቄ አየር ላይ መንጎዴ ፡ ምንድነው ምስጢሩ ፣ ቆይ ውስጤን ምን ነካው ...? አለም እንዲህ ጠቦ በእርምጃ የሚለካው ፣ ውቅያኖስ በእፍኝ ተጨልፎ የሚደርቅ ፣ ተራራው በክንዴ ተጎሽሞ የሚደቅ ፣ ኧረ ምን ተዓምር ነው እያልኩ አስባለሁ ። እኔ ደግሞ ቤሳቤስቲን ሳንቲም ኪሴ ሳይጨመር ፣ ዓመት የለበስኩት ልብሴ ሳይቀየር ፣ የዘውትር ጉርሴ ጣዕሙ ሳይነካ ፣ እኔነት እኔ ውስጥ ተቀይሯል ለካ ። እኮ በምን ምክንያት እኔ ተቀየርኩኝ ፣ እንዴት እኔ ነኝ ስል ፡ እኔ ሌላ ሆንኩኝ እያልኩ አስባለሁ ። ለካስ ከህይወት ጋር ስለሆንኩኝ ነው ። ያውም ከአባቷ ተለይታ ከድሬዳዋ ለቃ ከዩኒቨርስቲ የዚህን ዓመት ትምህርት ጨርሼ ስመለስ አብራኝ ወደ ትውልድ ቦታዬ ወደ ሙገር መጥታ ። አሜሪካ እንደማትሄድ ለአባቷ አሳውቃ በሰላምና በዕንባ ተለያይተዋል ።ይቀጥላል... ©fictional27 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ መልካም ንባብ ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይጠብቅልን አሜን ❥❥________⚘_______❥❥
ነገር ብቻ ልለምንህ ፡ ከዚህ ቦታ ይዘህኝ ሂድ" ብላ ተማፀነችኝ ።ይቀጥላል... ©fictional27 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ መልካም ንባብ ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይጠብቅልን አሜን ❥❥________⚘_______❥❥
😘የከንቲባው ልጅ😘 🔥ክፍል 39 የነ ህይወት በር ላይ ደርሼ የእጅ ሰዓቴን ሳይ ከምሽቱ #12:00 ሰዓት አልፏል ። ሰማዩም እየጠቆረ ነው ። እዚህ ከቆየሁ ደግሞ የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ጊቢ በወቅታዊው ችግር ምክንያት በጊዜ ስለሚዘጋ ማደሪያ አጣለሁ ። ሲጀምር እነ ህይወት ቤት ገብቼ ምን ልላቸው ነው ...? ለማንኛውም አሁን ቤታቸውን ስላወኩኝ የማደርገውን ሁሉ በደንብ አስቤበት ነገ ተመልሼ ብመጣ ነው የሚሻለው ብዬ ወደ ጊቢ ተመለስኩኝ ። ደስ የሚለው ዛሬ ጠዋት ነበር የዘንድሮውን በጀት ዓመት class ያጠናቀቅነው ። final exam ከአስር ቀን በዋላ እንጀምራለን ። መሽቶ ሲነጋ ቁጥር አንድ አላማ ያደረኩት ትናንት የህይወት አባት መጀመሪያ ላይ የሄደበት ቤት መሄድ ነበርና ወደዛው አመራሁ ። ደብተርና ብዕር ይዤ በሩን አንኳኳሁ ። ትናንት የህይወት አባት ስመዋት የነበረችው ሴት ናት ። ሰላምታ ተለዋውጠን "ምን እንደምፈልግ ጠየቀችኝ" ። እኔም የመመረቅያ ፅሁፌን ድሬዳዋ ላይ እየሰራሁ እንደሆነ ነገርኳትና ምናልባት አሁን ስላለንበት ሰፈር አመሠራረትና ለየት ያለ ታሪክ ካወቀች እንድትነግረኝ ጠየኳት ። የድሬ ሰው ደግም አይደል ...? እሷም "የድሬ ፀሃይ እረፍት የላት መቼም ፡ በር ላይ ከማቆምህ ወደ ውስጥ ብትገባ የተሻለ ይሆናል" አለችኝና ወደ ቤታቸው ጋበዘችኝ ። እኔም ሳላቅማማ ገባሁ ። ሳሎናቸው ውስጥ ስዘልቅ የትናንቱ ህፃን ልጅ ቁጭ ብሎ carton network እያየ ነበር ። ቁጭ በል አለችኝና "ስለ ለገሀሬ ብዙም አላውቅም ግን አባቶቻችን እንደነገሩን ከሆነ...!" ብላ የሆነ ታሪክ ነገረችን ። የኔ ፍላጎት እሱ ስላልሆነ ብዙም ትኩረት ሰጥቼ አላዳመጥኳትም ። አይኔ ቤት ውስጥ ያሉትን ነገሮች search እያደረገ እያለ አንድ ፎቶ ላይ ፍዝዝ ብዬ ቀረሁ ። ሴትዮዋ ፣ ህፃኑና የህይወት አባት በጣም የሚያምር የቤተሰብ ፎቶ ተነስተው ቁጭ ። ማፍጠጤ የታወቀኝ ሴትዮዋ "ምነው ፎቶው ላይ ፈዘዝክ" ስትለኝ ነበር ። 'አያይ ምንም' አልኳትና ቀጥዬ ወደ ጉዳዬ ለመግባት መንገድ ስለሆነኝ 'ትዳራችሁ በጣም ያስቀናል ፣ ስንት ጊዜያቹ ነው ...?' ስላት ፤ "መጀመሪያ ግን ፎቶው ላይ ያለው ሰው ማን እንደሆነ አውቀሃል...?" አለችኝ ። 'ካልተሳሳትኩኝ ከንቲባው ናቸው አይደል ...!' አልኳት እያወኩ እንዳላኩ እየሆንኩ ። "ልክ ነህ ፡ አሁን ግን የስልጣን ዘመኑ ስላበቃ ከቦታው ላይ በዚሁ ወር ለቋል ። እና ፎቶው ላይ አይተኸው ትዳራችሁ ያስቀናል ላልከው ፡ ባንተ እይታ ሊሆን ይችላል ። እንዳልከውም ግን የኛ ትዳር ያስቀናል ። ብዙ መስዋዕትነት ተከፍሎበታልና ። ከአራት ዓመት በፊት በኛ ምክንያት ምንም የማታውቅ የአንድ ፍሬ ልጅ ህይወት ሰዋን" ብላ ትክዝ ስትል ሁኔታው ይበልጡኑ አጓግቶኝ 'ማለት ፡ ምን ተፈጠረ' አልኳት ሰፈፍ ብዬ ። ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ሰው ብንን አለችና "ምንድነው የምቀባጥረው ፡ ተወው እርሳው በቃ ዝም ብዬ ነው" አለችኝ መናገር የሌለባትን ነገር እንደ ተናገረች በሚያስታውቅባት አነጋገር ። ጫን ብዬ ከጠየኳት ማንነቴ ላይ ችግር ስለሚያስከትል ተውኩትና እንዳይነቃብኝ ስለ ድሬዳዋ ጥቂት ጥያቄዎችን ጠይቄ አመስግኜ ልወጣ ስል ሴትዮዋ ህፃኑን "አቤል ፡ ቻው አትላቸውም አንግዳውን" አለችው ። ህፃኑም የእናቱን ቃል ተቀብሎ በሚያሳሳ ድምፅ "ቻው" አለኝና ፈገግ ብዬ ወጣሁ ። አንድ ነገር ግን ጥያቄ ሆኖብኛል ። የልጁ ስም ። አቤል ። የህይወት ጓደኛ የነበረው ፣ በሷ ፋንታ የተሰዋው ፣ ያ ምስኪኑ ልጅም ስሙ አቤል ነበር ። ሴትዮዋ ካለችኝ ነገር ጋር ተደምሮ ሁሉም ነገር ዝብርቅርቅ አለብኝ ። "ከአራት ዓመት በፊት በኛ ምክንያት ምንም የማታውቅ የአንድ ፍሬ ልጅ ህይወት ሰዋን" ። ምን ማለቷ ነው ...?ሳስበው ሴትዮዋ ልትለኝ የነበረው ስለ ህይወት ሞት ነውና ፤ የህይወት አባት ሚስት ሆና እንዴት በህይወት ፋንታ አቤል መሞቱን እንዳላወቀች ገርሞኛል ። የህይወት አባት ደግሞ ሆን ብሎ በህይወት ፋንታ የተገደለውን ልጅ ለማስታወስ አቤል የሚል ስም ለልጁ እንዳወጣም ይሰማኛል ። ስገምት ሴትዮዋ የህይወትን በህይወት መኖር የምታውቀው ነገር የለም ። ህይወትም እንደዛው ስለዚህ ቤተሰብ ምንም መረጃ የላትም ። ይሄን ያክል ምን ቢፈጠር ነው ግን ከንቲባው በእነዚህ ሰዎች መሀል ድንበር ሰርቶ እንዳይተዋወቁ ያደረገው ። መልሱንም ከራሱና ከፈጣሪ ውጪ ማንም አያውቅ ። ለማንኛውም ሁሉም ነገር ለበጎ ነው በሚለው ቃል በማመኔ እያተረፍኩኝ ነው ። ይህ አጋጣሚ ህይወት ትኩረት ሰጥታ እንድታዳምጠኝ ይረዳኛል ። ላወራህ አልፈልግም ብትል እንኳን የአባቷን ከሌላ ቤተሰብ ጋር ሲገናኝ የሚያሳይ photo ሳሳያት ደንግጣ ከኔጋር መስማማቷ አይቀርም ። ከሴትዮዋ ቤት እንደወጣሁ ቅድምያ ወደ ፎቶ ቤት ነበር የሄድኩት ። ከዛ መልስ #08:00 ሰዓት አካባቢ ወደ አዲሱ የነ ህይወት ቤት ሄጄ ትንፋሼን ሰበሰብኩና በራቸውን አንኳኳሁ ። ብዙም ሳያስጠብቁኝ በሩ ተከፈተ ። ህይወት ናት ። ልክ እንዳየችኝ ነበር ደንግጣ በሩን በሀይል መልሳ የዘጋችው ። በሩን ክፈቺና እናውራ ስላት ፡ ልትሰማኝ እራሱ ፍቃደኛ ልትሆን አልቻለችም ። እንባ በተናነቀው ድምፅ "ፀባይህ መቼም አይገባኝም ፣ መተሀል ስል ትሄዳለህ ፤ ሄደሃል ስል ትመጣለህ ። ለምንድነው ግን የምታሰቃየኝ ...? እባክህ ላይህ አልፈልግም ፤ ሂድልኝ" አለችኝ ። በቃ ደጋግማ የምትለኝ ቃል ቢኖር "ሂድልኝ" የሚለው ብቻ ነው ። 'እሺ በቃ ይቅርታ' አልኳትና ፎቶ ቤት ሄጄ ከስልኬ ላይ ያሳጠብኩትን የአባቷንና የሌላኛው ቤተሰቡ ፎቶ በበሩ ስር ወርውሬላት ወደ ጊቢ ለመመለስ መንገዴን ጀመርኩኝ ። አስር እርምጃ ሳልራመድ ከዋላዬ "ጥለኸኝ አትሂድ" የሚል ከዚህ በፊት የማውቀው አሳዛኝ ድምፅ ከጆሮዬ ገባ ። ዞር ስል ህይወት ናት ። ቀጥ ብላ ቆማ ወደኔ እያየች ነው ። በጣም ናፍቃኝ ስለነበር በሩጫ ተመልሼ እቅፌ ውስጥ አስገባዋት ። ምን እየተሰማት እንደሆነ መገመት ቀላል ነው ። ሁሉ ነገሯ የሆነው አባቷ እሷ ሳታውቅ ከአንዲት ሴትና ህፃን ልጅ ጋር እየተሳሳሙ የሚያሳይ ፎቶ ስታይ ልቧ እንደሚሰበር ግልጽ ነው ። ቀና ብላ አየችኝና "እነዚህ ሰዎች ማናቸው ፡ ፎቶውንስ ከየት አገኘህ ...?" አለችኝ ። 'ውስጥ ገብተን ብናወራ አባትሽ ይመጡብን ይሆን ወይስ እቤት ናቸው ...?' ስላት "በቅርብ ሰዓት ስለወጣ ቶሎ አይመጣም ፡ ስለዚህ ወደ ውስጥ ብንገባ ይሻላል ። ሲጀምር መምጣትም ይችላል ። ስለ ሁሉም ነገር ልጠይቀው እፈልጋለሁ" አለችኝና ወደ አዲሱ ቤታቸው አብረን ገባን ። የማውቀውንና ያየሁትን ሁሉ በቅደም ተከተል ስነግራት ፡ ስለ አባቷ የማታውቀው ነገር በመኖሩ በጣም ተገረመች ። "ቆይ እንዴት ይደብቀኛል ፣ ሚስት ቢያገባ እኔ ለሱ የማልደሰት መስሎት ነው ...?" ትላለች አንዴ ወደዚህ ፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ወደዛ እየሄደች ፡ ያሳጠብኩትን ፎቶ ደግሞ ትኩር ብላ እያየች ። አንዴ ደግሞ ትቀመጥና "ቆይ እሺ ፡ በኛ ምክንያት የአንዲት ፍሬ ልጅ ህይወት ሰዋን ማለትስ ምን ማለት ነው ...?" ትልና ድጋሜ ደግሞ ከተቀመጠችበት ተነስታ "በኛ ምክንያት ካለች ፡ በሷና በአባቴ ምክንያት ማለቷ ነው" አለችና ትንሽ እንደ ማሰብ ብላ "የኔ ህይወት እንደዚህ የመሆኑ ጉዳይ ላይ የአባቴም እጅ አለበት ለማለት ፈልጋ ብቻ እንዳይሆን ...?" አለች እኔ ላይ አፍጥጣ ። ለማረጋጋት ብዬ 'በቃ ተረጋጊ ፡ ለጊዜው ስለምንም ነገር በእርግጠኝነት ስለማናውቅ ምንም ማድረግ አንችልም' ስላት "የኔ ጌታ አንድ
😘የከንቲባው ልጅ😘 🔥ክፍል 38 ✍ደራሲ ተስፋዬ በትሩ . ደንግጬ ቀጥ ብዬ ቆምኩኝ ። ቁጭ ብዬ እንደነበር እራሱ አላወኩም ነበር የእጅ battery አበራና ፡ "push up ሲራ" አለኝ ። አንድ ሁለት መስሎኝ ዝቅ ብዬ ተፍ ተፍ ስል እሱ ይበቃል ሊል ነው ...? በግምት ከ #40 በላይ የሚሆን ሰርቼ እጄን ደክሞኝ ስንቀጠቀጥ አይቶኝ አዘነልኝ መሠለኝ "ቤቃ ቴኔስ" አለኝ ። ደስ ብሎኝ ስነሳ "አሁን ዴሞ sit up ጄምር" አለኝ ። እንደዛው ከሃያ ደቂቃ በላይ ሲያፈጋኝ ከቆየ በዋላ "ካውን ቤዋላ እንደቂዲሙ ቲሆኒና ፡ ዋ" አለኝና "ሂድ አውን" ሲለኝ ደስ ብሎኝ ወደ ቶኒ በር በፈገግታ ስሮጥ የቅድሙ ጥበቃ እየሳቀብኝ "መጀመሪያ ሱሬውን ቀይረህ ና" አለኝ ። የእጅ ሰዓቴን ሳይ #07:44 ይላል ። ዶርም ደርሼ እስክመለስ #08 ሰዓት ይሆናል ። በ #1 ደቂቃ ውስጥ ደግሞ በ plane እራሱ ድሬዳዋ ራስ ሆቴል መድረስ አልችልም ። ቢያንስ ከቶኒ እስከ ሆቴሉ ለመድረስ ከ #20 ደቂቃ በላይ ይወስድብኛል ። ጥበቃው እሺ ብሎ ቢለቀኝ ኖሮ #4 ደቂቃ ባረፍድ ነበር ። አሁን ግን ተስፋ በቆረጠ መንፈስ ወደ ዶርም በሩጫ ተመልሼ ሱሪ ቀይሬ ተመለስኩኝና ፡ በባጃጅ ከቶኒ እሸት ፣ ከእሸት ሼል ተሳፍሬ ድሬዳዋ ራስ ሆቴል ፊትለፊት ስወርድ #08:20 ሆነ ። በበሩ ወደ ሆቴሉ ልገባ ስል የሆቴሉ ጥበቃ ትኩር ብሎ ካየኝ በዋላ "ተስፋዬ ነህ...?" ሲለኝ 'አዎ ነኝ' አልኩት ። "እንካ ይሄ ላንተ ነው" ብሎኝ ሁለቴ የታጠፈ ወረቀት ሰጠኝ ። ገልጬ ለማንበብ ደቂቃ አላባከንኩም ። የህይወት እጅ ፅሁፍ ነው ። አንድ አረፍተ ነገር ብቻ ነው የተፃፈበት ። እሱም "እኔም በጣም እወድሃለሁ" የሚል ነው ። ጥበቃውን የት እንደሄደች ስጠይቀው "ከትንሽ ደቂቃ በፊት ነው በዚህ በኩል በባጃጅ የሄደችው" ብሎኝ ወደ ከዚራ የሚወስደውን መንገድ ጠቆመኝ ። ጥበቃውን አመስግኜ ባጃጅ ውስጥ ገባሁና ወደዚያው አመራሁ ። ከዚራ ስወርድ ግን የት መሄድ እንዳለብኝ ዞሮብኝ ባለሁበት ቦታ ቁጭ ብዬ ለማሰብ ሞከርኩኝ ። ሳወጣ ሳወርድ በስተመጨረሻ አሪፍ ሀሳብ ጭንቅላቴ ውስጥ ብልጭ አለልኝ ። በደስታ ብድግ አልኩኝና ስልኬን ከኪሴ ውስጥ አውጥቼ የነ ህይወት ቤት ላይ የተለጠፈውን የቤት ሽያጭ ማስታወቂያ ፎቶ አውጥቼ ስልኩ ላይ ደወልኩኝ ። እድሜ ለ technology እያልኩ የኔን ድምፅ ወደ ትልቅ ሰው የሚቀይረው option ላይ አደረኩት ። የህይወት አባት ስልኩን አነሱትና ማውራት ጀመርን ። ቤታቸውን ለመግዛት እንደምፈልግና ከዛ በፊት ግን በአካል ቢቻል ዛሬውኑ ተገናኝተን እንድናወራ ጠየኳቸው ። የመሄጃቸው ቀን እየደረሰ ስለሆነ ነው መሠለኝ በደስታ ተስማሙ ። በአቅራቢያቸው ወዳለው ቦታ መምጣት እንደምችል ስነግራቸው ከዚራ እንደሆኑ ነገሩኝ ። ነገር ቀለለ ብዬ #10:00 ሰዓት ላይ ቀጠሮ ይዘን ስልኩን ዘጋሁት ። የኔ አላማ እንዳልኩትም ቤታቸውን መግዛት አይደለም ። የህይወት አባት በቀጠሮው ቦታ ላይ ሲገኙ እኔ ሰበብ ፈጥሬ እንደቀረሁ እነግራችኋለሁ ። ከዛን እሳቸው ደግሞ ተናደው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ከዋላቸው ተከትያቸው ቤታቸው የት እንደሆነ ማወቅ ። ቤታቸውን ካወኩኝ ህይወትን በቀላሉ አገኘዋት ማለት አይደለም...? ከአንድ ሰዓት በዋላ የቀጠሮው ሰዓት ሲደርስ ከተባባልንበት ቦታ በቅርብ ርቀት ላይ ተደብቄ ቁጭ አልኩኝ ። የህይወት አባት ልክ በሰዓቱ ወደ ቦታው ከዚህ በፊት በማውቃት የቤት መኪና መጡ....በእቅዴ መሠረት ስልኬን አውጥቼ ለህይወት አባት ደወልኩኝ ። አስቸኳይ ጉዳይ እንደገጠመኝና ለዛሬ እንደማይመቸኝ ስነግራቸው ፡ "ይሁን" የሚል መልስ ቢሰጡኝም ፣ በትንሹም ቢሆን ድምፃቸው ላይ የቅሬታ አይነት ሁኔታ ይሰማል ። ስልኩን ዘጋሁና ተነስተው ወደሚሄዱበት ቦታ ለመሄድ ከተቀመጥኩበት ቦታ ተነሳሁ ። በመኪና ስለሆነ የሚሄዱት እንዳያመልጡኝና ለመከታተል እንዲያመቸኝ ያለችኝን #100 ብር ለባጃጅ ኮንትራት ከፍዬ የግል ሹፌር ቀጥሬያለሁ ። እና አሁን የህይወት አባት በ rava #4 ፊትለፊቴ ፣ እኔ ደግሞ በባጃጅ ከዋላቸው ነኝ ። መኪናቸውን ለገሀር/chemin de fer ወደ ሚወስደው መንገድ እየነዱት ይገኛሉ ። ለገሀር ከጊቢ በጣም ስለሚርቅ ፡ ከኔ ለመሸሽ ከሆነ ሰፈራቸው እዛ ሊሆን ይችላል አልኩኝ በልቤ ። ብዙ ደቂቃ ከተጓዝን በዋላ የህይወት አባት የሆነ ቤት አጠገብ መኪናቸውን አቆሙና ክላክስ አደረጉ ። አኔ ደግሞ ከባጃጁ ወርጄ በሆነ ግንብ ተከልዬ የሚያደርጉትን እያየሁ ነው ። ብዙም ሳይቆይ የቤቱ የውጪኛው በር ተከፈተና የሆነ ህፃን ልጅ እየሮጠ የመኪናውን በር ከፈተና ገባ ። ከዛን መኪናዋ ወደ ውስጥ ገብታ ከፊትለፊቴ ተሰወረች ። የሆነች ሴትም ውጪውን በሁለቱም አቅጣጫ ቃኘችውና በሩን ዘጋችው ። ጠጋ ብዬ ቤቱን በደንብ አየሁት ። ደስ የሚል የቤተሰብ አይነት ቤት ነው ። ህይወት እንደነገረችኝ ከሆነ ምንም አይነት ዘመድና የሚያውቁት ሰው የለም ። ታድያ እነዚህ ሰዎች እነማናቸው ...? የህይወት አባትስ እዚህ ምን ሊሰሩ መጡ ...? ብዙ ጥያቄዎች በጭንቅላቴ ውስጥ ሲመላለሱ ከቆዩ በዋላ የህይወት ስልክ ደወልኩኝ ። እንደተለመደው አይሰራም ። ስለዚህ ያለኝ ብቸኛ አማራጭ የህይወት አባት ከመምሸቱ በፊት ከቤቱ ወጥተው ሌላ ቦታ የሚሄዱ ከሆነ ጠብቆ መከታተል ። ካልወጡ ደግሞ ተስፋ ቆርጦ ወደ ጊቢ መመለስ ነው ። ከሰላሳ ደቂቃ በዋላ በሩ ሲከፈት ካለሁበት ደንግጬ ተነሳሁ ። የቅድሟ መኪና ተመልሳ ወጣች ። የህይወት አባት መኪናውን አቆሙትና ወርደው በሩ ፊትለፊት የቆሙትን አንዲት ሴትና ህፃን ለጥቂት ሴኮንድ ካወሩ በዋላ ግንባራቸውን ስመው ወደ መኪናው ተመለሱ ። ምናልባት ከጠቀመኝ ብዬ ትንሽ ራቅ ቢልም በስልኬ ፎቶ አንስቻለሁ ። ከዛን መኪናዋ እኛ ወዳለንበት መንገድ መምጣት ጀመረች ። በፍጥነት ባጃጁ ውስጥ ገባሁና ተደበኩኝ ። ሲያልፈን እኛም በሹፌሬ አማካኝነት መከታተሉን ተያያዝነው ። ጭንቅላቴ ግን ያለ እረፍት ያሰላስላል ። እነዚያ ሰዎች ማናቸው ...? ወደ ሰላሳ አምስት ዓመት የሚሆናት ሴት እና አንድ ወደ #4 ዓመት የሚጠጋ ህፃን ልጅ ። በውስጤ ሚስቱና ልጁ ይሆኑ እንዴ እላለሁ ። ግን ሳላረጋግጥ መፍረድም አልፈለኩም ። ብዙ ደቂቃዎችን ከሄደን በዋላ ወደ መጣንበት ወደ ከዚራ ተመልሰን የህይወት አባት አሁንም እንደ ቅድሙ የሆነ ቤት ፊትለፊት መኪናቸውን አቆሙና ከጥቂት ሴኮንድ በዋላ የውጪኛው በር ተከፍቶ መኪናዋ ወደ ውስጥ ገባች ። የድሬዳዋ ሰፈር አሰራር ደስ የሚለው መተጣጠፍ ስለሚበዛው ተደብቆ ለማየት በደንብ ያመቻል ። መኪናዋ ከገባች በዋላ በሩ ላይ አንዲት ቆንጅዬ ሴት ልጅ ቆማ እንደ ቅድሟ ሴትዮ ግራና ቀኙን ስትቃኝ የልብ ምቴ ከዚህ በፊት ታይቶብኝ በማያውቅ ሁኔታ እንደ ፈረስ ይጋልብ ጀመር ። በአካባቢው ከእኛ ውጪ ማንም ስላልነበረ በሩን ወዲያው ዘጋችው ። ልጅቷ ህይወት ናት ፡ አዎ ህይወት ። እኔም ባለ ባጃጁን ሸኘሁትና ወደነ ህይወት ቤት ጉዞ ጀመርኩኝ.....ይቀጥላል... ©fictional27 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ መልካም ንባብ ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይጠብቅልን አሜን ❥❥________⚘_______❥❥
ይቀጥላል... ©fictional27 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ መልካም ንባብ ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይጠብቅልን አሜን ❥❥________⚘_______❥❥
😘የከንቲባው ልጅ😘 🔥ክፍል 37 ✍ደራሲ ተስፋዬ በትሩ . ከቀጠሮው ቦታ በሰዓቱ ለመድረስ ስለፈለኩኝ #07 ሰዓት ላይ ከዶርም ወጥቼ በቶኒ በር ለመውጣት ጉዞ ጀመርኩኝ ። ቶኒ በር ላይ ስደርስ ግን ጥበቃው "ተመለስ" አለኝ በንቀት አይነት ድምፅ ። ደንግጬ ዞር ብዬ አየሁትና 'ምነው ያጠፋሁት ነገር አለ እንዴ ...?' አልኩት በትህትና ። "የለበስከው ልብስ ትክክል አይደለም" ሲለኝ ፡ በሆዴ 'ጌታ ሆይ ቀሚስ ነው የለበስከው እንዳትለኝ ብቻ' እያልኩኝ ዝቅ ብዬ የለበስኩትን ሾፍኩት ። በቅርቡ የገዛሁት አዲሱና የምወደው ጅንስ ሱሪ ነው ። ከላይም ቢሆን ካሉኝ ልብሶች ቆንጆ የምለውን ሸሚዝ ነው የለበስኩት ። ትንሽ እንደ መገረም ሆንኩኝና 'ልብሴ ምን ሆነ አልኩት ...?' በድጋሜ ትህትና በሞላው አነጋገር ። "አትሰማም እንዴ የምትባለውን ፡ ሱሪክ የተቀደደ ነው ። በእንደዚህ አይነት ልብስ ደግሞ መውጣትም ሆነ መግባት አይቻልም" አለኝ ቁጣ በተቀላቀለበት ድምፅ ። የተቀደደ ሱሪ እንደሆነ ስለማላውቅ በድጋሜ ዝቅ ብዬ አየሁት ። ሱሪው የተቀደደ ሳይሆን ትንሽ ጭረት ነገር ጉልበት ላይ አለው ። ትንሽ ቦታ ብቻ ነው ክሮቹ የተፈቱት እንጂ ምንም የተጋነነ ነገር የለውም ። እንደውም ከቅርብ እንጂ ከሩቅ መተልተሉ እራሱ አይታወቅም ። በጥበቃው ሁኔታ በጣም ስለተገረምኩኝ 'ኧረ የኔ ወንድም ብዙም እኮ አይደለም የተቀደደው ፡ ደግሞም የምቸኩልበት ቦታ ስላለኝ እንጂ ተመልሼ እቀይረው ነበር' አልኩት በመማፀኛ ቋንቋ ። እሱ ግን ሊሰማኝ ነው ...? ጭራሽ ከተቀመጠበት ተነስቶ "ለምንድነው ስራዬ ውስጥ ገብተህ የምትረብሸኝ ፡ ተመለስ አልኩህ አይደል እንዴ ...?" አለኝ ሸሚዜን ጨምድዶ ይዞት ። ከዚህ በፊትም በተሰጣቸው ትንሹ ስልጣን ተማሪዎች ላይ የሚያደርሱት አንዳንድ ያልተገባ ስራቸው ከዛሬው ጋር ተደምሮ በጣም ስላናደደኝ 'እመለሳለሁ አ ፡ ልቀቀኝ ወደዛ' አልኩትና ወደ መጣሁበት ልመለስ ስል ጊቢውን ከሚጠብቁት የመከላከያ ሰራዊት አባል አንዱ "ና ዌዴዚህ ...!" አለኝ በሃይለኛ ድምፅ ። ቆሌዬ ብቻ ሳይሆን ቆዳዬ ጭምር ነበር የተገፈፈው ። በልቤ 'አቤት የኔ ጌታ ፡ ምን አልከኝ' እያልኩ ድምፁን ወደ ሰማሁበት አቅጣጫ ሄጄ ፊትለፊቱ ሹክክ ብዬ ቆምኩኝ ። Ak4 የሚባለው መሳሪያ ይዟል ። ፊቱ ጠቆር ብሎ የሚያስፈራ ሲሆን ቁመቱ ደግሞ ረዘም ያለ ነው ። ፈራ ተባ እያልኩ ወደላይ እያየሁት 'አቤት ፡ ምን ነበር ...?' አልኩት ። ትንሽ የፌዝ ሳቅ ሳቀብኝና "ጢቤቃውን ሜን ሲቲሌው ኔበር ...?" አለኝ በተወላገደ አማርኛ ። 'ምን አልኩት ፡ ያው ፡ እእእ ፡ ምን መሠለህ ፡ እእእ ፡ ቸኩዬ ስለነበር የምለውን ነገር አላውቅም ነበር ፡ እእእ ፡ እና ካጠፋው በጣም ይቅርታ' አልኩት በየመሃሉ ምራቅ እየዋጥኩኝ ። "ኢሱን ፡ በዴንብ ኢናዎራሌን ፡ ና ፡ ቴኬቴሌኝ አሁን" ብሎኝ ቶኒ አዲሱ በር ላይ ከተሰሩት ወደ አንደኛው ክፍል እየመራኝ ይዞኝ ገባ ። ሰዓቴን ሳየው #07:21 ይላል ። በዚህች ምድር ላይ ከሁሉ በላይ ድንቅ የሚለኝ ነገር የሰዓት ጉዳይ ነው ። መች ነው የሚነጋው እያለን ስንጨነቅ ከቆመበት ንቅንቅ አይልም ። ቀጠሮ ኖሮን ቦታው ላይ ለመድረስ ችግር ሲገጥመን ግን ሰዓቱ እንደ ሴኮንድ መሮጥ ይጀምራል ። የቶኒ በር ገና ያላለቀና በመሠራት ላይ ያለ ስለሆነ ክፍሉ ባዶና ቀለም እንኳን ገና ያልተቀባ ፣ በዛላይ ደግሞ መብራት ጭምር የሌለው ጨለማ ክፍል ነው ። በሩ ላይ የተሰሩት ክፍሎች ለጥበቆች ሻዎር ፣ ልብስ መቀየሪያ ፣ መፀዳጃ እና እቃ ማስቀመጫ ይሆናሉ ተብለው የተሰሩ ቢሆኑም ፡ ለኔ ግን በአሁኑ ሰዓት ከማዕከላዊ አሳንሼ የማላየው አስር ቤት ሆነው እየታዩኝ ነው ። መሳሪያ የያዘው ሰውዬ ...ሰሚራ ትባላለች ። በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የአንደኛ ዓመት fashion design ተማሪ ናት ። ቤተሰቦቿ ሙስሊም እሷ ደግሞ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ናት ። በዚሁ ጉዳይ ነበር በቴሌግራም የተዋወቅነው ። ከሳምንት በዋላ ጊቢ ውስጥ ICT WAP አካባቢ ከምሽቱ #03:00 ላይ ተቀጣጠርንና ተገናኘን ። እያወራን እያለ ከጥቂት ደቂቃ በዋላ ሁለት ፌደራሎች አንደኛው መሣሪያ ሌላኛው ደግሞ የጎማ ገመድ ይዘው ወደኛ መጡ ። ያለንበት ቦታ እና ሰዓት በትምህርት ቤቱ ህግ መሠረት ወንጀል አይደለም ። ጊቢ ውስጥ እስከ #04:00 ሰዓት ድረስ እንደፈለግን መንቀሳቀስ ይቻላል ። ሲጀምር ያለንበት ቦታ ለመደበቅያነት የሚያመች ሳይሆን ለማንም ሰው የሚታይና ፊትለፊት የሆነ ቦታ ነው ። ፌደራሎቹ ኮስተር ብለው በጥያቄ ያፋጥጡን ጀመር ። "እዚህ ምን እየሰራችሁ ነው ...?" ሲለን አንዱ 'ምንም ፡ ዝምብለን እያወራን ነው' አልኩት ። "ID አምጡ" አለንና ሁለታችንም ሰጠነው ። ትኩር ብሎ አየና ብሔር የሚለውን ፈልጎ አጣ መሠለኝ "ከየት ነው የመጣችሁት ...?" ብሎ የማይመለከተውን ጥያቄ አቀረበልን ። እኔ 'ከአዲስ አበባ' ስለው ሰሚራ ደግሞ "ከመቱ" አለችው ። ሁለተኛው ፌደራል ወደኔ ተጠጋና በእርግጫ እናቴን መታኝ ። ምን እንዳጠፋው ባይገባኝም ዋጥ አድርጌ ዝም አልኩኝ ። ሰሚራ ግን በድንጋጤ ልትጮህ ብላ አፏን አፍና ያዘች ። "አንቺ አፍሽን ዝጊ" አላትና አንደኛው በጥፊ መታኝ ። ጉልበታቸውን እና ስልጣናቸውን ሊያሳዩን ስለፈለጉ ሞኝነታቸውን በልቤ አምቄ ተሸነፍኩላቸው ። ባላጠፋነው ነገር ሁለታችንም "እሺ በቃ አጥፍተናል ፡ ይቅርታ" እያለን መለመን ጀመርን ። ጭራሽ ብሶባቸው በእርግጫ የመታኝ ፌደራል ፀጉሬን ይዞኝ መሬት ላይ ጎተተኝ ። አስቡት እንግዲህ ፡ ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ጊቢ ውስጥ ፡ ያውም በ FB library እና ICT WAP መሀል በሚገኘው ቦታ ላይ ሆነን ። እንደ አጋጣሚ ሆኖ ተማሪዎች በቦታው ላይ የሉም ። ለነገሩ ቢኖሩም ከመሸሽ ውጪ ምንም የሚረዱን ነገር አይኖርም ። ሰሚራ እያለቀሰች ነው ። እኔ ደግሞ የፌደራሎቹ ጅልነት አናቴ ላይ ወጥቶ በብስጭት ልፈነዳ ነው ። እነሱ አቅማቸውን እያሳዩን ፡ እኛ ደግሞ ምንም አቅም እንደሌለን act እያደረግን ወደ #10 ደቂቃ ሆነን ። የመፍራት ስሜት አልተሰማኝም ። እነሱ በዚህ ሰዓት ከኛ የሚፈልጉት ከነሱ በታች መሆናችንን እንድናሳያቸው ስለሆነ ፡ እነሱ የሚሉንን ሁሉ አዎ ልክ ናችሁ ፡ እኛ ነን ጥፋተኞቹ እያልን ነው ። ህገ መንግሥት እንጂ ህግ የሌላት ሀገር ፣ ትንሹም ትልቁም ባለው ትንሽ ስልጣን ፈጣሪ ካልሆንኩ የሚልባት ምድር ። በስተመጨረሻ "በቃ ሂዱ ከዚህ" አሉን ID ሳይመልሱልን ። ለሱም ከደቂቃዎች በላይ የሚሆን ከስግደት ያልተናነሰ ልመና አቅርበን መለሱልን ። እንድንሄድ የፈቀዱልን በምን ምክንያት እንደሆነ ሳውቅ ግን በጣም አፈርኩኝ ። እነሱ የሚፈልጉትን ቋንቋ ስንናገር ነበር ደንግጠው የተውን ። እስካሁን በኛ ላይ ሲፈፅሙ የነበረው በሌላ ብሔር ላይ እያደረጉ ያሉ መስሎአቸው ነበር ። ግን በተቃራኒው የሁለታችንም እና የፌደራሎቹ መገኛ ፡ እነሱ በሚያስቡት መንገድ ከአንድ ብሔር ነው ። ደግነቱ እኔ እንደነሱ ብሔር አለመቁጠሬ ነበር ። ፈልገን ባላገኘነው ነገር መኩራትም ማፈርም ጅልነት ነው ። የዚህችን ቀን ትውስታ ቶኒ በር ጭለማ ክፍል ውስጥ ሆኜ ሳስብ ቆየሁና ፡ አሁን ደግሞ ፊትለፊቴ የቆመው መከላከያ ምን ያደርገኝ ይሆን እያልኩ ሳወጣ ሳወርድ "ተነስ" የሚል የሚያስፈራ ድምፅ ከጆሮዬ ገባ ።
😘የከንቲባው ልጅ😘 🔥ክፍል 36 ✍ደራሲ ተስፋዬ በትሩ . ስልክ ቁጥሩ ከጠቀመኝ ብዬ ቤታቸው ላይ የተለጠፈውን ማስታወቂያ በስልኬ ፎቶ አነሳሁትና ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተመለስኩኝ ። #10 ሰዓት ላይ class ነበረኝና በፍጥነት ቁና ቁና እየተነፈስኩ ክፍላችን ደረስኩኝ ። #20 ደቂቃ አርፍጃለው ። ሆኖም ግን አስተማሪው ተንበርከክ ሳይለኝ አስገባኝ ። የ machine element መምህራችን ህንዳዊ ዜጋ ነው ። ያው የሱ ትምህርት ትርጉም በስለሺ እስኪመጣልን ድረስ ምንም እየገባን አይደለም ። ድንጋዩ ማነው እንዳትሉኝ እንጂ ድንጋይ ላይ ውሃ እያፈሰሰ ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም ። ሰውዬው ከሚያወራቸው ነገሮች አንዲት እንኳን አትሰማም ። ከሱ እንግሊዝኛ ይልቅ የ shah rhuk khan ህንደኛ በስንት ጣዕሙ ። ደግሞ መቸክቸክ አይደክመውም ። አንድ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አምስት ጊዜ black board እያጠፋ እየፃፈ ፡ እኛንም ያለ ሞያችን ደራሲ አርጎናል ። እኔ ለሰባቱም ትምህርቶች ትበቃለች ብዬ የገዛዋትን አንዷን ባለ #50 ወረቀት ደብተር እሱ በአንደኛው ቀኑ ነበር ብቻውን መሃል ላይ ያደረሳት ። anyways ግን ከህንድ የሚመጡት አስተማሪዎች ይሄን ሁሉ km አቋርጠው የሚመጡበት ምክንያት አይገባኝም ። ሀገር ውስጥ አስተማሪ ጠፍቶ ነው እንዳንል ስንቱ ተመርቆ ስራ ጠፍቶ እቤት ውስጥ ተጎልቷል ። የማስተማር ብቃት ፈልገውም ከሆነ የኛዎቹን የሚበልጡበት አንድም የተለየ ብቃታቸው አይታየኝም ። እንግሊዝኛቸው ግራ የሆነ ። ከኛ ጋር መማር ማስተማሩ ላይ በቋንቋ ካልተግባባን ምኑን ተማርን ። በቋንቋም ብንግባባ ደግሞ የትምህርት አሰጣታቸው የህፃን ጨዋታ ነው ። ሰሌዳው ላይ የሀገር Note ይፅፉና እሱኑ መልሰው ያነቡልናል ። አለቀ ፡ ደቀቀ ። እኛ ማንበብ ከብዶን ነው እንዴ የመጣነው ...? እንዳልኩትም ራጅ ኩማር ሰሌዳው ላይ የቸከቸከውን አንብቦልን መጨረሻ ላይ quiz ፈተነን ። ከፈለጋችሁ ከደብተር ላይ ስሩ ሲለን እኔ ደግሞ የትልቅ ሰው ምክር አይናቅም ብዬ እሱ እንዳለን ከደብተር ላይ copy paste አደረኩት ። ድፍን ምስር ሳልበላ የደፈንኩት የመጀመሪያው ፈተና ሆኖም በ UNESCO ላይ ተመዝግቦልኛል ። በጣም ደክሞኝ ስለነበር ከ class መልስ ወደ ዶርም ገባሁ ። እንዲህ ደክሞኝ እያለም ግን የያዘኝ ሱስ ሊያስተኛኝ አልቻለም ። high school እያለሁ በጣም ሱሰኛ ነበርኩኝ ። ቤተሰብ እንኳን እስኪማረርብኝ ድረስ የጦፈ ሱስ ውስጥ ገብቼ ነበር ። የተያዝኩት #9ነኛ ክፍል እያለሁ ነው ። ያለሱ አይሆንልኝምና ቤተሰቦቼ በጣም ስለሚያዝኑብኝ ከነሱ ተደብቄ እጠቀም ነበር ። ለሱሴ የሚሆን ገንዘብ አላጣም ። ያለኝን ብር በሙሉ እሱላይ ነበር የማጠፋው ። እንደምንም እየቆጠብኩም ቢሆን ከወር ወር ያደርሰኛል ። campus ስገባ ደግሞ እሱኛውን ሱስ ትቼ ሌላ ሱስ ውስጥ ወደኩኝ ። ይሄ ደግሞ ጭራሽ ከድሮው ሱሴ የባሰ ሆነብኝ ። ስራዬ ሁሉ እሱ ብቻ ነው ። ማጥናት ፣ መማር ፣ ምናምን የለም ። ሙሉ ሰዓቴን እሱ ላይ ነው የማሳልፈው ። ዛሬ ግን ለመተው አስቤአለሁ ። ከቻልኩ እስከነጭራሹ ላለመጠቀም ፤ ካልሆነም በየቀኑ ላለመጠቀም ወስኛለሁ ። ብዙ መጎዳትን እንጂ ጥቅምን አላገኘሁበትም ። ያተረፍኩት ነገር ቢኖር ገንዘቤን ለ tele መገበር ብቻ ነው ። #9ነኛ ክፍል እያለሁ የጀመረኝ የ facebook ሱሴ ካምፓስ ስገባ ወደ telegram ተቀይሮ ይሄው አይኔ እስኪጠፋ ድረስ ስበላ ፣ ስጠጣ ፣ ስማር ፣ ስሄድ ፣ ስቀመጥ ፣ ስተኛ ፣ ብቻ ምን አለፋችሁ #24 ሰዓት ከስልኬ ጋር እንደተቃቀፍኩ ነው የምውለው ።የሰው ልጅ ብዙ አስደናቂ ነገሮችን ፈጥሯል ። ለኔ ግን እስካሁን ድረስ ወደር ያልተገኘለት ፣ የትኛውም ፈጠራ የማይተካከለው ነገር ቢኖር #መተኛት ነው ። እዚጋ አንድ ጊዜ ተረጋጉና ሌላ አለም ውስጥ ሳትገቡ በፊት ነገሩን ላስረዳችሁ ። "መተኛት" የሚለው ቃል ተኛ ፣ ደቀሰ ፣ ወገቡን ፈተሸ ፣ አንሶላ ውስጥ ገባ ፣ አሸለበ እና ከመሳሰሉት የግሪክ ግሶች የወጣ ሲሆን ትርጓሜውም ያው ግሪኮች ከላይ ያሉት ነው ። መተኛት በሶስት ይከፈላል ። አንደኛው ፦ የህዝብና ቤት ቁጠራን ለማባዛት የሚተኛው መተኛት ነው ። ምሳሌ ፦ ባልና ሚስት ። ሁለተኛው ፦ ፈጣሪ የማይወደው ፡ እኛ ሰዎች ግን ደስ ብሎን የምንተኛው መተኛት ነው ። ምሳሌ ፦ ከጋብቻ በፊት ወንድና ሴት የሚተኙት ። ሶስተኛው እና ወሳኙ መተኛት ደግሞ ብቻህን በር ዘግተህ ለጥ የምትለው መተኛት ነው ። ምሳሌ ፦ ተስፋዬ የሚተኛው ። እና ዛሬ ቀኑን ሙሉ ስተኛ ነው የዋልኩት ። እናንተ ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ አልጋ ሂዱ ፤ እሱም ያሳርፋችዋል የተባለ ይመስል ለምሳና ለእራት ብቻ ነበር ከአልጋዬ ላይ የወረድኩት ። አልጋም ላይ ብውልም ግን ምንም አልተኛሁም ። ማሰብ ፣ ማሰብ ፣ እንደገና ማሰብ ። ብዙ ካሰብኩኝ በዋላ የሆነ ነገር ትዝ ብሎኝ በራሴ አፈርኩኝ ። ፍቅር እውር ያደርጋል የሚሉት ተረት በኔ ላይ ሲደርስ አየሁኝ ። ቆይ ከነ ህይወት ጋር ለመሄድ ሳስብ እንዴት ቤተሰቦቼን ዘነጋዋቸው ...? ዝም ብዬ እንደ በግ ለማንም ምኑንም ሳልተነፍስ እብስ ብዬ ልጥፋ ነበር እንዴ ...! አባቷ እንኳን ይሁን የኔን ስም process ውስጥ ለማስገባት ብለው ነው አስቀድመው ከመሄዳቸው በፊት የኔን ውሳኔ ለመስማት የፈለጉት ። እኔስ ምን አስቤ ነው ...? anyways አሁን ግን መሄድ እንኳን ብፈልግ መሄድ የማልችልበት ሁኔታ ላይ ነው ያለሁት ። ይሄን ደግሞ ለህይወት እንዳልነግራት ስልኳንና በሯን ዘግታብኛለች ። የማገኝህ አብረኸኝ እንደምትሄድ ከወሰንክ ብቻ ነው ብላኛለች ። ለዚህ ብዬ ከቀጠሮው ቦታ ከቀረሁ ለዘለዓለም ከህይወት ጋር መቆራረጤ ነው ። በቦታው ላይ ተገኝቼ አልሄድም ካልኳት ደግሞ ቅስሟን መስበር ይሆንብኛል ። ልክ በቀጠሮው ቦታ እንደተገኘሁ ስታየኝ በቃ አብሮን ሊሄድ ወስኖ ነው የመጣው ብላ በደስታ ታብዳለች ። እኔ ደግሞ በተቃራኒው እንደቀረሁ ስነግራት ከመቅረቴ ይልቅ በቦታው ላይ መገኘቴ ይበልጡኑ ያሳብዳታል ። እንደማልሄድ ነግሬያት ለምን እንደቀረሁ ቁጭ ብላ ምክንያቴን የምትሰማኝ አይመስለኝም ። ብትሰማኝም ግን ለመቅረት ምክንያት የምደረድር ነው የሚመስላት ። ሁሌም ህይወት በኔ ላይ እንዲህ ነች ። መምረጥ የማልችላቸውን ሁለት ነገሮች ፈትፍታ ታቀርብልኛለች ። እኔ ደግሞ የትኛውን መጉረስ እንዳለብኝ አላውቅም ። ለአንድ በሽታ ሁለት መዳኒቶች ቀርበውልኝ የትኛውን እንደ ምውጥ ግራ ገብቶኛል ። ሁለቱም እኔን የማዳን ትልቅ ሀይል አላቸው ። ነገር ግን ሁለቱም በአንድ ላይ አይወሰዱም ። የግድ አንዱን መምረጥ ይኖርብኛል ። የቀጠሮው ቀን ደረሰ ። ህይወት #08 ሰዓት ላይ ድሬዳዋ ራስ ሆቴል እጠብቅሃለሁ ባለችኝ መሠረት ዛሬ በቦታው ላይ በተስፋ እንደምትጠብቀኝ አውቃለሁ ። አሁን የቀረው የኔ ወስኖ መሄድ ወይም የኔ ጨክኖ መቅረት ብቻ ነው ። "ያም ቆንጆ ይሄም ቆንጆ ፡ ያም ቆንጆ ይሄም ቆንጆ ፣ ልቤ አላርፍ አለኝ ከአንድ ጎጆ ፡ ከቶ አላርፍ አለኝ ከአንድ ጎጆ ። ስቋጥር ስፈታ ፡ ሳሰላስል ፡ አንዱን ይዤ ፡ አንዱን ስጥል ፣ ዞሬ ዞሬ ከሁለት ሰው ፡ መምረጥ አንዱን ተቸግሬአለሁ ።ይቀጥላል... ©fictional27 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ መልካም ንባብ ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይጠብቅልን አሜን ❥❥________⚘_______❥❥
ሰላም ሰላም ውድ ተከታታዮቼ እንዴት ናችሁልኝ? 10k ደርሰናል እንኳን ደስ አለን? የእናንተ ድጋፍና ገንቢ ሃሳባችሁ ነው እዚህ ያደረሰኝ እና ሁሌም ሀሳብ ድጋፋችሁ እንዳይለየኝ በማለት ለሌሎች ጓደኞቻችሁ በመጋበዝ (Invite) በማድረግ ፖለቲካን ለፖለቲከኞች ትተን ፍቅርን እንዝራ፣ፍቅርን እናቀንቅን? ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋልና ያላወቅነውን እንወቅ፣እናሳውቅ ሰላማችሁ ይብዛልኝ አመሰግናለሁ!!! ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fictional27 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅልን ❥❥________⚘_______❥❥
😘የከንቲባው ልጅ 😘 🔥ክፍል 35 ✍ደራሲ ተስፋዬ በትሩ . ጠዋት እንደተለመደው ወደ ክፍል ሄጄ እስከ ምሳ ሰዓት ተምረን ፣ ቶኒ ምሳ በልተን ወደ ዶርም ገባሁ ። Telegram መጠቀም በጣም ስለምወድ ስልኬን አወጣሁና ገባሁ ። ትናንት በተላከልኝ ፣ መልሼ ስደውል እምቢ ባለኝ ስልክ ቁጥር አዲስ መልዕክት ተላከልኝ ። "እንዴት ነህ የኔ ጌታ ፡ በመጀመሪያ የሚያናድድህ ነገር አድርጌ ከሆነ በጣም ይቅርታ ። ትናንት ያንን መልዕክት እኔ ነኝ አዲስ ሲም ካርድ አውጥቼ የኩልህህ ። ሁለት ልብ ሆነህ ሳይክ በመሀል ተጨነኩና እንዲቆርጥልህ ብዬ እንደዛ አደረኩ ። ስለ ፍቅር ካንተ አንድ የተማርኩት ትልቅ ነገር ቢኖር 'እራስ ወዳድ መሆን የለብንም' የሚለው ነው ። እኔም እራስ ወዳድ መሆን አልፈለኩም ። ከኔ ይልቅ ለማራኪክ የበለጠ ስሜት እንዳለህ በትንሹም ቢሆን አውቅ ነበር ። ትናንት ግን ሙሉ በሙሉ አረጋገጥኩኝ ። መልዕክቱንም እኛው ቤት እያለህ ልልክልህ የፈለኩት ፊትህ ላይ ምን አይነት ስሜት እንደሚፈጠር ለማየት ነበር ፤ ደግሞም አየሁት ። አውቃለሁ ምናልባት አንተ ትናንት ስትመጣ ከናንተጋር እሄዳለሁ ልትለን ይሆናል ። እንደዛ የምታደርገው ደግሞ የማራኪክ ፍቅር ሳይወጣልህ ፣ ለኔ ስትል ብቻ እንደሆነ ግልፅ ነው ። ይሄ ደግሞ የኔን ራስ ወዳድነት አጉልቶ ያሳያል ። አንተ በህይወቴ ከመጣህ ጀምሮ እንደ አዲስ መኖር ጀመርኩኝ ፣ ብዙ ነገር አደረክልኝ ። አንተ ያደረክልኝ ነገር ላንተ ምንም መስሎ ሊታይህ ይችላል ። ለኔ ግን ብዙ ነገር ነው ። ብቻዬን ነበርኩኝ ፤ ያውም እስር ቤት ውስጥ ። አንተ ግን መተህ ፈታኸኝ ። ፈተኸኝም ዝም አላልከኝም ፤ አለሜን አሳየኸኝ ። በአንድ ቤት ውስጥ ለአራት ዓመታት ተዘግቶብኝ በፊልም ፣ በመፅሐፍ እና በሙዚቃ የማውቀውን አለም እጄን ይዘህ አሳየኸኝ ። በልቦለድ ላይ የምመኘውን ገፀባህሪ አለበስከኝ ። እናቴ ሰጥታኝ ሰዎች የነጠቁኝን ህይወት መልሰህ ሰጠኸኝ ። ታውቃለህ ፡ ካንተ ጋር ያሳለፍኳት እያንዳንዷ ቅፅበት አሁንም ድረስ ፊቴ ላይ እየተመላለሱ እንደ አዲስ ነፍሴን ወደ ሰማይ ይልኳታል ። ልለይህ መቼም አልፈልግም ነበር ። ይህ ግን ሊሆን አይችልም ። ከዚህ በዋላ እንደ በፊቱ ልጫንህ አልፈልግም ። እኔ ያንተ ብሆንም ፤ አንተ ግን የኔ አይደለህም ። በግድ ደግሞ የኔ ላደርግህ አልሻም ። ምናልባት የፈጣሪ ስራ አይታወቅምና ወደፊት አንድ ቀን አንተን ለኔ ካለ ተመልሰን ልንገናኝ እንችላለን ። ይህ ደግሞ የኔ የወደፊቱ ብቸኛው ምኞቴ ነው ። አሁን ስለኔ ይቅርና ካንተ አንድ የምፈልገው ነገር አለ ። ማራኪህን በጣም ትወዳታለህ ። እሷን እንደ ቀድሞህ ለመመለስ ደግሞ የሚቻልህን ማድረግ አለብህ ። ለፍቅር የሚከፈለውን ማንኛውንም መስዋዕትነት ከፍለህ የራስህ እንድታደርጋት እፈልጋለሁ ። ይሄን ካደረክ ሌላው ሁሉ ትርፍ ነው ። ከዚህ ውጪ ግን ከሶስት ዓመት በዋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሼ እመጣለሁ ። ያኔ ግን ብቻህን ሆነህ ካገኘሁክ የእናቴን ቀን ይስጠኝ አለቅህም ። ድል ባለ ሰርግ አግብቼህ የራሴ አደርግሃለሁ ። እስከዚያው ግን ፈጣሪ መላዕክቶቹን ልኮ ይጠብቅህ ። መልሼ እስካገኝህ በጣም ትናፍቀኛለህ የኔ ጌታ" ይላል መልዕክቱ ። ባለሁበት ደንዝዤ ቀረሁ ። እንደምንም ወደ ራሴ ተመለስኩና ፡ ከዶርም ወጥጬ ወደነ ህይወት ቤት በረርኩኝ ። ቤታቸው በር ላይ ስደርስ ግን ...ያጋጠመኝ ፡ ህይወትን ለማግኘት ተስፋ አስቆራጭ የሆነ ነገር ነው ። ቤታቸው ላይ በትልቁ በፖስተር ተደርጎና በር ላይ ደግሞ ወረቀት ላይ ማስታወቂያ ተፅፎ ተለጥፏል ። "for sell ፡ የሚሸጥ ፣ kan gurguramu" የሚል በሶስት ቋንቋ የተፃፈ ነው ። ከስር ደግሞ ስልክ ቁጥር ተፅፎበታል ። ይሄ ማለት እነ ህይወት ቤቱን ለቀው ወጥተዋል ማለት ነው ። ምናልባት ካሉ ብዬ በሩን በደንብ አንኳኳሁ ፤ ግን ሰሚ የለም ። የህይወት ስልክ ላይ ደወልኩ ፤ ጭራሽኑ አይሰራም ። ተስፋ በቆረጠ አንጀቴ ወደ መጣሁበት ልመለስ አንድ እርምጃ ሳነሳ ከበራቸው ስር የሆነ ፖስታ አየሁኝና ዝቅ ብዬ አነሳሁት ። ገና ስከፍተው የህይወት እንደሆነ በእጅ ፅሁፏ አወኩኝ ። "እዚህ እንደምትመጣ ስላወኩኝ ነው ይሄን ደብዳቤ የፃፍኩልህ ። አየህ አንተ አሁንም ድረስ ሁለት ልብ እንደሆንክ ነው ያለኸው ። ትናንት እንደ ማራኪክ ሆኜ መልዕክት ስልክልህ ወዲያውኑ ፊትህ ተቀያይሮ አባቴ ጋር ጥለኸኝ ሄድክ ። አሁን ደግሞ መልዕክቱ የተላከልህ ከማራኪክ እንዳልሆነ ስትረዳ ወደኔ ሮጠህ መጣህ ። እየወቀስኩህ አይደለም ። እራስህን በደንብ እንድታዳምጥ ስለፈለኩኝ ነው ። አንተ በሁለት ሰዎች መካከል ቆመህ ልብህ እንደ pendulum ወደዛ ወደዚህ እያለብህ ነው ። ይሄ ደግሞ ላንተም ጥሩ አይደለም ። መወሰን አለብህ ፣ መቁረጥ አለብህ ፤ ለዛ ደግሞ ጊዜው አሁን ነው ። ማንንም ጣልቃ ሳታስገባ ከራስህ ጋር የራስህ የሆነ ንግግር አድርግ ። አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን አንድ መቶ አንድ ጊዜ አስብ ። ሁሉንም መርምር ፤ የሚበጀውን ደግሞ ምረጥ ። ያኔ ያንተ ብቻ ሳይሆን የብዙ ሰው ልብ ያርፋል ። በዚች ምድር ላይ ከአስከፊ በሽታዎች ሁሉ የላቀ ህመም ፤ ቁርጡን ሳያውቁ ዝም ብሎ በተስፋ መቀመጥ ነው ። አገኘው ይሁን ፡ አጣው ይሁን ...? ፣ የኔ ይሁን ወይስ የሌላ እያሉ ቀን ከለሊት ያለ እረፍት ማሰብና መጨነቅ የህመሞች ሁሉ አስከፊው ህመም ነው ። እኔ ደግሞ የዚህ በሽታ ተጠቂ መሆን አልፈልግም ። ወይ አንተን ብቻ ማሰብ ወይም ደግሞ አንተን እስከነ መፈጠርህ መርሳት ይኖርብኛል ። ይሄን ደግሞ ለማድረግ ያንተ እርዳታ ያስፈልገኛል ። አንተ በኔ ላይ ያለህ ተስፋና ለኔ ያለህ ፍቅር ለውሳኔዬ ይረዳኛል ። ለዚሁ መልስ ደግሞ ከመሄዴ በፊት አንድ ዕድል እሰጥህና ለመጨረሻ ጊዜ እንድንገናኝ አደርጋለሁ ። የማገኝህ ያንተን የመጨረሻ ውሳኔ ለማወቅ ብቻ ነው ። ያንቺ ነኝ ወይም ያንቺ አይደለሁም የሚለውን እንድታሳውቀኝ ብቻ ። ይሄን ለማድረግ ደግሞ ግዴታ ቃል ማውጣት አይጠበቅብህም ። ሰኞ #08:00 ሰዓት ላይ ድሬዳዋ ራስ ሆቴል እጠብቅሃለሁ ። በቦታው ላይ በሰዓቱ ከተገኘህ ከኔጋር ለመሆን ፍቃደኛ እንደሆንክ እቆጥረዋለሁ ። ከኔጋር ለመሆን ካልፈለክ ግን ወደ ቦታው መምጣት እራሱ አይጠበቅብህም ። ለብዙ ደቂቃ የምጠብቅህ እንዳይመስልህ ። ባልኩህበት ቦታና ጊዜ በተስፋ እጠብቅሃለው ። እስከዚያው ግን በአካልም ሆነ በስልክ መገናኘት የለብንም ። ከሁሉም ነገር ተገልለህና ብቻህን ሆነህ በንፁህ ህሊናና ልብ በደንብ አስበህበት ላንተም የሚበጀውን ውሳኔ ትወስናለህ ብዬ አስባለሁ ። ስለሁኔታው አባዬ ምንም አያውቅም ። ይሄንን የማደርገው ከሱ ተደብቄ ነው ። ስላንተ ሁሉንም ነገር ነግሬው በጣም ተናዷል ። ፍቅረኛ እንዳለህ ሲሰማ ፊቱ እንዴት እንደተለዋወጠ ብታየው አታውቀውም ። ካሁን በዋላ እንዳገኝህ እንደማይፈልግም ነግሮኛል ። እንደ ምንገናኝ ካወቀ ምን እንደሚያደርግ አላውቅም ። ለማንኛውም እራስህን ጠብቅ ። እስከዚያው ግን ... ። #ህይወት" ።ይቀጥላል.... . . ©fictional27 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ መልካም ንባብ ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይጠብቅልን አሜን ❥❥________⚘_______❥❥
😘የከንቲባው ልጅ😘 🔥ክፍል 34 ✍ደራሲ ተስፋዬ በትሩ . የጠዋቱን ክፍለ ጊዜ እስከ #5 ሰዓት ተማርኩኝና በግብዣዬ መሠረት ምሳ ሰዓት ላይ ወደነ ህይወት ቤት ሄድኩኝ ። አባትና ልጅ ደስ በሚል ፈገግታ እሷ ከውጪ ከአጥሩ በር ፣ አባቷ ደግሞ ከቤቱ መግቢያ በር ላይ ተቀበሉኝ ። አባቷ በኔና በእሳቸው መካከል ስለነበረው ግኑኝነት በሙሉ ስለነገሯት ከህይወት ጋር ምንም አይነት ድብብቆሽ መጫወት አይጠበቅብንም ። ምሳ እኔም ስላልበላሁ ፣ እነሱም እየጠበቁኝ ስለነበር የምግብ ጠረጴዛውን ከበን የቀረቡትን የምግብ አይነቶች መርጠን አነሳንና ለመብላት ተዘጋጀን ። አባትና ልጅ ምግቡን ባርከው ተጎራርሰው መብላቱን ቀጠሉ ። እኔ ደግሞ ስርዓቴን ጠብቄ ብቻዬን እየበላሁ ነው ። ማን ያውቃል ምናልባት የወደፊት አማቼም ሊሆኑ ስለሚችሉ በወግ ልማዳችን መሠረት ሰብሰብ ብዬአለሁ ። ምግቡም አለቀና ፣ ጨዋታ ጀመርን ። ስለ ትምህርት ፣ ቤተሰቦቼ ፣ ወቅታዊ ጉዳይ ፣ ምን ያላወራነው ነገር አለ...! በስተ መጨረሻ ህይወት "መጣሁ ተጫወቱ" ብላ ተነስታ ወደ ኩሽና አመራች ። አባቷም ከዚህ በፊት በደምብ አስብበት ብለው የጠየቁኝን ጥያቄ አስታውሰውኝ መልስ መጠበቅ ጀመሩ ። ማታ በዚሁ ጉዳይ እንቅልፍ አልተኛሁም ነበር ። ሳወጣ ሳወርድ ፣ በሀሳብ ስሄድ ስመለስ ነው ያነጋሁት ። በብዙ አቅጣጫ ለማሰብ ሞከርኩኝ ። ወደ ውስጥም አስቤ ልቤን በደንብ ለማዳመጥ ሞክሬ ነበር ። ጭንቅላቴ ውስጥ 'ሂድ ፡ ቅር ፣ ሂድ ፡ ቅር' የሚል ድምፅ ከጩኸት በላይ እየተሰማኝ እንዲሁ ፍዝዝ ብዬ ነው ያደርኩት ። ስለ ማራኪዬ በደምብ አሰብኩኝ ። ስልኬን ካላነሳች ፣ txt ካልመለሰች ፣ በጓደኞቿ በኩል ላገኛት ስሞክር ካልተሳካልኝ ፣ ታድያ በሷ ላይ የቀረኝ ተስፋ ምንድነው ...? ብዬ በጣም ለማሰብ ሞከርኩኝ ። ከማንምና ከምንም በላይና በፊት አሰቀድማ እኔን ነው የምታምነው ያልኳት ልጅ ፤ እምነቱ ቀርቶብኝ ስልኬን እንኳን ለአንድ ደቂቃ የማንሳት አቅም አጣች ። ሁለታችንም ቃል ነበረን ። በማንምና በምንም አይፈርስም ብለን የተሳሰርንበት ቃል ። በመሃላችን ስለሚፈጠረው ማንኛውም ነገር ፣ ከሰዎች ምንም ይምጣ ምንም ፣ ከሁለታችን አፍ ሳንሰማ ላንከዳዳ ቃል ተግባብተን ነበር ። አሁን ግን ሁለታችንም ስለተፈጠረው ነገር ምንም ሳንባባል ፣ ለመባባልም ጊዜ አጥተን ተለያይተናል ። በሷ ተስፋ ለመቁረጥ ጫፍ ላይ ደረስኩኝ ፤ ግን አልቆረጥኩም ። "ልጅ ተስፋዬ" አሉኝ የህይወት አባት ። ከእንቅልፍ እንደሚባንን ሰው ከሀሳቤ ነቃሁ ። "ምነው ጥለኸኝ ጠፋህ እኮ" አሉኝ አስከትለው ። እኔም ፈራ ተባ እያልኩ 'አያይ እዚሁ ነኝ ፤ የትም አልሄድኩም' አልኳቸውና ለጥያቄያቸው መልስ ልሰጥ ስል ስልኬ ላይ መልዕክት ገባ ። ከኪሴ ውስጥ አውጥቼ ከፈትኩት ። የማላውቀው ቁጥር ነው ። "ማራኪዬ እንዴት ነህ ...? ደህና እንደሆንክ ተስፋ አደርጋለሁ ። እየውልህ ፡ በሰዓቱ ባንተ በጣም ተናድጄ ስለነበር ስልክህን ላለማንሳትና መልዕክትህን ላለመመለስ ለራሴ ቃል ገባሁ ። ጠልተህኛል ብዬ ጠላሁክ ። እንደውም ከጊዜ በዋላ ያንተን መልዕክት ላለማየት ብዬ ስልክ ቀየርኩኝ ። ለዛም ነው አሁን በአዲሱ ስልክ ቁጥሬ የማወራህ ። አንተ ምናልባት ረስታኛለች ብለህ ታስብ ይሆናል ። ማራኪዬ ፡ ስላንተ ላለማሰብና ላለማውራት ለራሴ ቃል ገብቼ ቢሆንም አሁንም ድረስ ግን ስላንተ ማሰብ ማቆም አልቻልኩም" ይላል መልዕክቱ ።በስንት መከራና ጭንቀት በስተመጨረሻ ፡ ለአባቷና ለህይወት ልክ እሺታዬን ላበስር ስል ረስታኛለችና ልርሳት ፣ ትታኛለችና ልተዋት ያልኳት ማራኪዬ "ልረሳህ አልቻልኩም" የሚል መልዕክት ልካልኝ ለእሺታ የተዘጋጀውን አፌን ቆለፈችው ። በድንገት 'መሄድ አለብኝ' ስላቸው ተደናግጠው "ምነው የተፈጠረ ችግር አለ እንዴ ...?" አሉኝ የህይወት አባት ። 'አያይ ምንም ችግር የለም' ብዬአቸው ተነሳሁ ። በሁኔታዬ ግራ ቢጋቡም በዝምታ ሸኝተውኝ ባሉበት ፍዝዝ ብለው እያዩኝ ከቤታቸው ከህይወት ጋር ወጣሁ ። "ምን ሆነሃል የኔ ጌታ...?" አለችኝ ህይወትም ። ስልኬን ሰጠዋትና መልዕክቱን አስነበብኳት ። አንብባ ስትጨርስ "እና ለዚህ ነው እንደዛ ባንዴ ተደናግጠህ የተነሳኸው ...?" ስትለኝ ፤ 'ታድያ በዚህ ሰዓት ከዚህ በላይ የሚያስደነግጥ ምን አለ ...?' አልኳት ። "ደስ ብሎሃል አይደል ...?" አለችኝ ቀጥላ ። እኔ ግን ያለሁበትን ሁኔታ እንዴት እንደ ምገልፀው ግራ ገብቶኛል ። መደሰት ይኑርብኝ መከፋት ፣ ማልቀስ ይኑርብኝ መሳቅ ፣ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እንኳን አላውቅም ። ግን አንድ ነገር ጭንቅላቴ ውስጥ እየተመላለሰ ይገኛል ። 'መሄድ የለብህም ፡ ለማራኪክ የገባኸውን ቃል አስታውስ ፣ ከዚህ በፊት አንቺ የልጆቼ እናት ነሽ ያልካትን አስታውሰህ ወደሷ ተመለስ ፣ መጀመሪያም ዝምታዋ ነበር እንድትሄድ ያስወሰነህ ፡ ይኸው አሁን ከአንደበቷ ሰምተሃል ፡ ስለዚህ ከህይወት ጋር ወደ ውጪ መሄድ የለብህም' ይለኛል ። ይሄን ውሳኔ ተቀብዬ ለህይወት ማሳወቅ ደግሞ ለኔ ከሞት በላይ ያስፈራኛል ። ዝም ብላ ካየችኝ በዋላ "ከኔጋር መሄድ አትፈልግም አይደል ...?" አለችኝ ። አይኖቿን እያየሁ መመለስ ስለከበደኝ 'አላውቅም ህይወት ፣ አላውቅም' አልኳት አንገቴን ደፍቼ ። "ስሜትህ ይገባኛል ። ማራኪክ አንተጋ ምን ያክል ቦታ እንዳላት መገመት አይከብደኝም ። ለመጀመሪያ ጊዜ ከንፈሯን የሳምካት ልጅ ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ፊልም ላይ የምታውቀውን የፍቅር ህይወት በእውን ያሳየችህ ሴት ፣ በፍቅርም ለሁለት ዓመታት ርቀት ሳይበግራችሁ በስልክ ብቻ እያወራችሁ ያልተለያያችሁ ጥንዶች ፣ በስልክም ከአምስት ሺህ በላይ መልዕክት የተፃፃፋችሁ ፣ በየ ሳምንቱም ተደዋውላችሁ የምታወሩ ፣ በመሃላችሁ በተፈጠረው አለመነጋገር ምክንያት ብቻ ለወራት ሳታወሩ ብትቀሩም በስተመጨረሻ ግን ረስታኛለች ብለክ የደመደምከው ነገር በተቃራኒው ከልብህ ከማንም በላይ የምትወዳት ፍቅርህ "ልረሳህ አልቻልኩም" ስትልክ ምን እንደ ሚሰማክ አውቃለሁ ። አንተ ለሷ ያለህ ስሜት ፡ እኔ ላንተ ያለኝ ስሜት ስለሆነ በደንብ ይገባኛል ። ሲጀምርም አባቴ ከኛ ጋር ሂድ ማለት አልነበረበትም ። እኔኮ በጣም ደህና ነኝ ። አንተን ባጣ እራሴን የማጠፋ መስሏችሁ ነው ...? በፍፁም እንደዛ አላደርግም" ። አለችኝና እስኪጨንቀኝ ድረስ ጥብቅ አርጋ አቅፋኝ ፣ ጉንጬንም ስማኝ በቆምኩበት ትታኝ ወደ በሩ ሄደች ። በሩ ጋር ስትደርስ ዞር ብላ አየችኝ ። ፊቷ በእንባ ተሸፍኗል ። ልቤን ስትበላኝ ወደሷ ሄጄ ላቅፋት ስል ወደ ውስጥ ገብታ በሩን ዘጋችው ። እኔም ሰፈራቸውን ለቅቄ ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አመራሁ ። መልዕክቱ በተላከልኝ ስልክ ላይ ደወልኩኝ ። ነገር ግን ቴሌ "አሁን ማግኘት አይችሉም" አለችኝ ። እስከ ምተኛበት ሰዓት ድረስ ደጋግሜ ብደውልም ሊሰራልኝ አልቻለም ። ምን እየተካሄደ ነው ...? መልዕክት ልኮ ስልክ ማጥፋት ምን የሚሉት ጉዳይ ነው ...? ይቀጥላል.... . . ©fictional27 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ መልካም ንባብ ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይጠብቅልን አሜን ❥❥________⚘_______❥❥
😘የከንቲባው ልጅ😘 🔥ክፍል 33 ✍ደራሲ ተስፋዬ በትሩ ተነሳሁ አፌም ተከፈተ ። 'ለዚህ ሁሉ ነገር ሶስት አካላትን መውቀስ እፈልጋለሁ ። (ጥቅም ባይኖረውም ...😢) ። #1ኛው :- ያው ሁላችንም በስም ብቻ የምናውቀው መንግስት ተብዬው ነው ። ወንጀል በማንኛውም ሁኔታ ፣ ቦታና ፣ ጊዜ ፡ በሆነ ሰው/ቡድን ሊፈፀም ይችላል ። የመንግሥት ዋነኛ ስራው ወንጀል እንዳይፈጸም መከላከል ፤ ካልሆነም ወንጀለኞቹን ይዞ ህግ ፊት ማቅረብ ነው ። ይህን ካላደረገ መንግስት የለም ማለት ነው ። እባክህ መንግስት ሆይ ፡ ከሰማኸኝ በጣም ናፍቀህኛል ፡ ላገኝህ እፈልጋለሁ ። ብቻህን ቢሆን ይመረጣል ስል ሁሉም ባንድነት አሽካኩ ። #2ኛው :- ከሁሉ ደግሞ የገረመኝ ነገር ፡ የሚዲያዎቹ ነው ። "በኮርያ በተቀሰቀሰው የተማሪዎች ግጭት የሁለት ተማሪ ህይወት አልፏል" EBC ። ስንቱ ምስኪን ሀገሩ ላይ እየሞተ እያለ ስለማያገባን ፈረንጅ ይተርክልናል ። ምናለበት እስኪ ብያንስ እንኳን ነፍስ ይማር ቢል ...?😢 ። ነው ወይስ ግዴታ ባለስልጣን ወይንም አርቲስት መሆን አለብን ...? ። ለስሙ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ነው ። እኔ ግን የመንግስት ቴሌቪዥን ብዬዋለሁ ። እስቲ እውነት የኛ ሚዲያ ከሆኑ "ተማሪዎች ላይ ስቃይ እየደረሰ ነው ፡ መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል" ይበሉ ። #3ኛው :- ህዝብ ነው ። ምነው ይህ ህዝብ ለስንቱ እንዳልተሰለፈ ፡ ዛሬ ለተማሪ ሲሆን ዝም አለ ። ለዘይት ፣ ስኳር ፣ አብይ ፣ ኦነግ ፣ ግንቦት #7 ፣ ጃዋር ፣ እንደዛ በየ አደባባዩ እንዳላሽቃበጠ ፡ ምነው ዛሬ የራሱ ልጅ ባደባባይ ሲገደል ፀጥ አለ ...?😥 ። ብያውቁ ሁላቸሁም ተማሪ ሆነው አልፈዋል ። ተማሪዎች ሲገደሉ ፣ ሲሰደዱ ፣ ሲደበደቡ ፣ ሲሰደቡ እያዩ ባልሰማ ዝም ፤ በተቃራኒው ግን ለአንድ ለማይረባ ነገር ብለው #5 ሚሊዮን ሆነው አደባባዩን ይሞሉታል ። እስቲ የተማሪዎች ህመም ከተሰማቸው ለምን "እኔም ተማሪ ነኝ" ብለው አደባባይ አይወጡም ። ለማንኛውም ፡ በዚህ ዘመን ሰው አለኝ ማለት ከንቱ ነው ። መንግስትም ህዝብም ያጣ generation ...😔 ። እንደኔ የዚህ ክፉ ዘመን የዩኒቨርስቲ ተማሪ ለሆናችሁ ተስፋችሁን እግዚአብሔር ብቻ አድርጉ ። "አሁንስ ተስፋዬ ማነው ፡ እግዚአብሔር አይደለምን ...?" አይደል ቅዱሱ መፅሐፍም የሚለው ። ይህን ስናገር ታዛቢ እንጂ ሰሚ እንደሌለኝ እያወኩኝ ነው ። ግን ብያንስ ስለተነፈስኩኝ ቀሎኛል ። እውነቱን ሸሽገህ የህሊና እስር ቤት ከምትገባ ፡ እውነቱን ተናግረህ የመንግስት እስር ቤት ብትገባ ይሻልሀል' ብዬ ስቀመጥ ሁሉም ተማሪዎች በጭብጨባ ክፍሉን አናወጡት ። እኔም 'አመሰግናለሁ ፣ ኧረ አይገባም አመሰግናለሁ' እያልኩ አሽቃበጥኩ ። ወዲያው ግን ግንባሬን የሆነ ነገር ቋ ሲያደርገኝ ደንግጬ ከተቀመጥኩበት ብድግ አልኩኝ ። ከዛን የ Fluid አስተማሪያችን "ምንድነው የምታመሰግነው ...?" አለኝ ኮስተር ብሎ ። ለካ ያን ሁሉ ስብሰባው ላይ ያወራሁት ክፍል ውስጥ ሆኜ ስቃዥና ሳንቀላፋ ነበር ። ውሃ በላኝ ።.... ከህይወት ጋር የልደቴ ቀን ለመጨረሻ ጊዜ ከተያየን እንደ ቀልድ አምስት ቀናት ተቆጠሩ ። በጣም እንደናፈቀችኝ ያወኩት ክፍል ውስጥ ሴት መምህራችን ስታስተምረን መልኳ ወደ ህይወት ፊት ተቀይሮ ፈገግ ብዬ በፍቅር አይን ስመለከታት ተገርማ "ተስፋዬ ምን ፈገግ የሚያስብል ነገር ተገኘ ...?" ስትለኝ ነበር ። ጥቁር ሰሌዳው ላይ ፣ ደብተሬ ላይ ፣ ጠረጴዛ ላይ ፣ ግድግዳ ላይ ፣ በሄድኩበት ሁሉ የምትታየኝ እሷ ብቻ ሆናለች ። ከሷ ጋር ያሳላፍኳቸውን እያንዳንዷን ቅፅበት ሳስታውስ ነፍሴ በደስታ ትፈነድቃለች ። ለሊት ብቻዬን በዶርማችን በር በኩል ሽቅብ ከማያቸው እልፍ አእላፍ ከዋክብት ይልቅ በልቤ ውስጥ የምታንፀባርቀው እሷ ሆናለች ። ከሷ ጋር ሳሳልፍ የተሻሉ ቃላትን ተጠቅሜ ደስ ላላሰኛት እችላለሁ ። ነገር ግን በክንዶቼ መሃል አስገብቻት ፣ ደረቴ ላይ ተለጥፋ ፣ ጆሮዎቼ የሷን ድምፅ ብቻ ሲሰሙ ፣ አይኖቼም እሷኑ ብቻ እያዩ ፣ ከልቤ ሃሳቧን ፣ ጭንቀቷን ፣ ሀዘኗን ፣ ደስታዋን ፣ ሳቅና ሰቀቀንዋን ሁሉ ስካፈላት ከምን ጊዜውም በላይ ስለምትደሰት ፤ ደስታዋ ደስታዬ ሆኖ ከዋለ ካደረ ቀናቶች ተቆጥረዋል ። ከረገጠችው መሬት በላይ በኔ ላይ ዕምነት ኖሯት ሳያት ታስደምመኛለች ። እኔም ልክ እጆቿን ይዤ አይኖቿ ን ስመለከት ብርሃን ይታየኛል ፤ ጉልበት ይኖረኛል ። እራሷ ደካማ ጎኔ ሆኗ እራሷ ታበረታኛለች ። በስልክ በየ ሰዓቱ እናወራለን ። አባቷ ያንኑ ዕለት እሁድ ምሽት ወደ ቤት እንደ ተመለሱና የዛሬ ሳምንት ማለትም ልክ እኔና እሷ በተዋወቅን በወሩ ግንቦት #30 ወደ አሜሪካ እንደ ሚበሩ ነግራኛለች ። ልክ ይሄንን ነገር ለመጀመሪያ ጊዜ ስሰማ ልቤ ለሁለት ስንጥቅ ብሎ ነበር ። ከአካላቶቼ መሃል አንዱ የተቆረጠ ያህል ህመም ተሰማኝ ። የመጨረሻ ውሳኔዬን ነገ እቤታቸው ሄጄ እንዳሳውቃቸው አባቷ ደውለው ነገሩኝ ። በህይወት መንገድ ላይ መመለስ የለም ። ጉዞው ሁሉ ወደፊት ብቻ ነው ። በመንገዴ ውስጥ ብዙ ሰው ላይኖር ይችላል ። እኔን እሱ አያሳስበኝም ። ነገር ግን የሷ አለመኖር ያማል ። የኔ አለም ለመሆን በተቃረበች ማግስት ከተለየችኝ ከአለም ጋር መጣላት ይሆንብኛል ። እሷን በፀሃይ ፋንታ እንደ ምትክ ሆና በተሰጠችኝ በመጨረሻዋ ሰዓት መሄጃዋ ሲደርስ ብርሃን ማጣት ይሆንብኛል ። ትታኝ መሄዷን ሳስብ ፀሃይ ፊቷን አዙራብኝ ፣ ጨለማ የዋጠኝ ያክል ተሰማኝ ። ጨለማ ውስጥ ወደኩኝ ፣ ምንም አይታየኝም ። ጭር ያለ ቦታ ላይ ተጣልኩኝ ፣ ምንም አይሰማኝም ። እልም ያለ በረሃ ውስጥ ነኝ ፣ በናፍቆት ውሃ ጥም ልሞት ነው ። ቀኑን እና ለሊቱን መለየት ከብዶኛል ። አሁንስ ነጋልኝ ስል ተመልሶ ይጨልምብኛል ። እኔ እሷን ካጣሁ እንኳን ቀኑን እራሴንም መርሳቴ አይቀርም ። የኔና የሷ ፍቅር ቀናት ስለተቆጠሩ አይደለም ። ፍቅር የጊዜ ማጠርና መርዘም አይደለም ። ፍቅር ማለት ፡ ያ በማንኛውም አጋጣሚ ፣ በማንኛውም ሁኔታ ፣ በየትኛውም ቦታ ላይ ያሳለፍናት ያቺ ጊዜ ፣ ደቂቃም ትሁን ቅፅበት የማይረሳ ትዝታን ያሳለፍንባት ፣ በልቤ በልቧ የተነጋገርንባት ፣ በደስታ ሰክረን ያሳለፍናት ፣ አዎ እሷ ናት ። ልክ ፀሃይ አለምን ለማብራት እንደ ተፈጠረች ፣ ህይወትም ለመኖር ፣ ዝናቡም ሊዘንብ ፣ አበቦች ሊፈነዱ ፣ ሌሎችም ሌሎችም ለአላማቸው ልክ እንደተፈጠሩ ፣ የኔ መፈጠርም እሷን ለማፍቀር ቢሆንስ እያለ ልቤ ከራሴ ጋር ይሟገቱ ጀመር ።ይቀጥላል... . . ©fictional27 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ መልካም ንባብ ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቧቿን ይጠብቅልን አሜን ❥❥________⚘_______❥❥
ሳውዲ አዲስ መረጃ በትንሹ ከ 33ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን * ህፃናት * ሴቶች * ወንዶች በስሞኑን አፈሳ በሳውዲ እስር ቤት ውስጥ ገብተዋል:: ጉዳዩን የሰላም ሚኒስቴር እየተክታተልኩት ነው ቢልም * ኢቢስ * ፋና ቢዘግቡም ጉዳዮን ግን እጅግ አሳሳቢ ነው በአስቸኳይ መፍትሄ ካልተወሰደ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በእስር ቤት * በበሽታ * በጭንቀት እስከ ሞትም ሊያደርሳቸው የሚችል ደረጃ ላይ ሊደርሱ ይችላሉ:: አስቸኳይ የሆነ መፍትሄ የኢትዮጵያ መንግስት እንዲሰጥልን? * መረጃ ተለዋወጡ * ሼር አድርጉ ድምፅ ሁኑ አሁንም ቢሆን ተሰፋችን ፈጣሪያችን ብቻ ነው . . . ©fictional27 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ http://t.me/fictional27 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቧቿን ይጠብቅልን አሜን ❥❥________⚘_______❥❥