መዝሙር ዘፈለገ ቅዱሳን
Статистика✝️🙏 የቦሌ ቡልቡላ ፍኖተ ሕይወት ቅድስት ድንግል ማርያም እና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ፈለገ ቅዱሳን ሰንበት ት/ቤት ✟በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ስርአቱን በጠበቀ በሰንበት ት/ቤቶች የሚዘመሩ መዝሙራትን እና ወረባት ከነ ግጥማቸው እና ዜማቸው ለማግኘት ይቀላቀሉን join us 👇👇👇 @fkss21 ሃሳብ አስተያየት ጥያቄ ካላቹህ በዚህ አሳውቁን @Anteneh2112 @Ad199419
- Последний пост
- 14 июл.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
እንደምን አመሻቹ ለማእከላዊያን ክፍል በሙሉ በፈተና ምክንያት መዝሙር ጥናት ቀን ተዘግቶ መሆኑ ይታወቃል በመሆኑም የመዝሙር ጥናት ሰኞ የተጀመረ ሲሆን ያልሰሙ አባላት ስላሉ ለነሱ በማሰማት ነገ 10፡30 እንድትገኙ እናሳስባለን!!
видео или голосовое, без подписи
✨"የጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ!"✨ 🔔2 ቀን ብቻ ቀረው🔔 🗳እሑድ ሠኔ 28/2018 ዓ.ም🗳 🗳 መንፈሳዊ ምርጫ 🗳 የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተወካዮች÷ የደብሩ አስተዳዳሪ የደብሩ ፀሐፊ ÷ የሰበካ ጉባዔ ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በሚታደሙበት፤ የመጨረሻው ምርጫ (9 ሥራ አመራሮች) እና 4 የአፈጻጸም ክትትል ጉባዔ አባላት፤ በአባቶች ጸሎት ተደርጎ እሑድ ሠኔ 28/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት በዕጣ ይመረጣሉ፡፡ 🗓 እሑድ ሠኔ 28/2018ዓ.ም ⏰ ከ 3:00 ሰዓት ጀምሮ ✅ቦታ - ፈለገ ቅዱሳን ሰ/ት/ቤት አዳራሽ 👉 በዕለቱ በሰንበት ት/ቤታችን በመገኘት የዚህ ታሪካዊ ኹነት አካል ሁኑ 🔴 ሁላችንም በፈለገ ቅዱሳን ሰ/ት/ቤት አዳራሽ በሰዓቱ እንገናኝ!!!
видео или голосовое, без подписи
https://www.instagram.com/p/DaGRJYTMlr3/?utm_source=ig_web_copy_link&igsh=NTc4MTIwNjQ2YQ== ይህ የፈለገ ቅዱሳን የinstagram ገፅ ነዉ ሁላችሁም follow,like and share እንድታረጉ እናሳስባለን 🙏🙏
видео или голосовое, без подписи
ሕንጸተ ቤተክርስቲያን ሰኔ ሃያ በዚች ቀን በኬልቄዶን አውራጃ በቂሣርያ አገር የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ያለ ዕንጨት ያለ ጭቃና ውኃ በሦስት ደንጊያዎች በተወደደ ልጅዋ እጅ የታነፀችበት ነው። ይኽም በዓል ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው። ‹‹ሕንጸተ ቤተ ክርስቲያን›› ይባላል። የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን የታነጸችው በሰኔ 20 ቀን ነው። ያነጸውም እራሱ ባለቤቱ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጲስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው። እመቤታችን ካረገች በ4ኛ ዓመት ጳውሎስና በርናባስ በፊሊጲስዩስ ገብተው አስተምረው ሕዝቡን አሳምነው ካጠመቁ በኋላ ‹‹እንግዲህ ወደ ቤተ ጣዖት አትሂዱ›› አሏቸው። አሕዛብ የነበሩትና አምነው የተጠመቁትም ‹‹የለመድነውን ከከለከላችሁን መካነ ጸሎት ስጡን›› አሏቸው። የከበሩ ሐዋርያትም ወደ ጴጥሮስና ዮሐንስ መልእክት ላኩባቸው። ጴጥሮስና ዮሐንስም ‹‹ያለ ጌታችን ፈቃድ አንዳች ልታደርጉ አይገባምና ጸልዩ እኛም እንጸልያለን›› ብለው መለሱላቸው። ሁሉም ሱባኤ ይዘው በጸሎት ተጉ። ጸሎትና ሱባኤያቸውን ከጨረሱ በኋላ ጌታችን በሞት ያረፉትን አስነሥቶ በሕይወት ያሉትንም ደቀመዛሙርቱን በደመና ጠቅሶ ፊልጵስዩስ ሰበሰባቸው። ጌታችን በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መላእክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች። ቅዱስ ዮሐንስም ‹‹ጌታዬ ለምን ሰበሰብከን?›› ብሎ ጠየቀ። ጌታችንም ‹‹በእናቴ ስም ከጽንፍ እስከ ጽንፍ አብያተ ክርስቲያናት እንዲታነጹ ፈቃዴ ነውና ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ላሳያችሁ ሥርዓት ላስተምራችሁ ነው›› አለው። ይህንን ብሎ ወደ ምሥራቅ ወሰዳቸው። በዚያም ተራርቀው የነበሩ 3 ደንጊያዎች ነበሩ። ጌታችንም ሦስቱን ድንጋዮችን በተአምራት አቀራርቦ አንሥቶ ጎተታቸው። ድንጋዮቹም እንደ ሰም ተለጠጡ፣ እንደ ግድግዳም ሆኑ። ቁመቱን ወርዱን መጥኖ ለሐዋርያቱ ሠጣቸው። እነርሱም እሳት እንዳየው ሰም ከእጃቸው እየለመለሙ (እየተሳቡ) ቁመቱን 24 ወርዱን 12 ክንድ አድርገው ሠርተውታል። ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም አምሳያ አድርጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ። ከዚህም በኋላ ጌታችን ለሐዋርያቱ ‹‹እንግዲህ እናንተም እንዲህ አድርጋችሁ ሥሩ›› ብሏቸው ዐረገ። ሦስቱ ድንጋዮች የሥላሴን ሦስትነት ወደ አንድ ሆነው አንድ ሕንፃ መታጹ የሥላሴን አንድነት ያስረዳል። በአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን መታነጽ ለኛ ለክርስቲያኖች እጅግ ታላቅ በዓልና ደስታ ነው። ስለዚች ቤተ ክርስቲያን አባቶች ደማቸውን አፍስሰውላታል፣ አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተውላታል፣ አጥንታቸውን ከስክሰውላታል፣ ቆዳቸው ተገፏል፣ በድንጋይ ተወግረዋል፣ በእሳት ተቃጥለዋል፣ በአውሬ ተበልተዋል። ቤተ ክርስቲያን ግድግዳዋ ውኃ መሠረቷ ደም ነው። የማትታደስ ነገር ግን ከኃጢአት ከበደል የሚታደሱባት ርትዕት ናት። ይህች ቤተ ክርስቲያን ‹‹የክርስቶስ አካሉና ሙላቱ ናት።›› እናም የዚህችን ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መጣስና ትምህርቷን መቆነጻጸል የክርስቶስን አካል ማድማት ነው። ዳግመኛም በማግሥቱ ሰኔ 21 ቀን ጌታችን ድንግል እናቱን እመቤታችንንና ቅዱሳን መላእክትን አስከትሎ ወረደ። እመቤታችንን መንበር፣ ጴጥሮስን ተራዳኢ ካህን፣ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቁርቧቸዋልና ፍጹም ደስታም ሆነ። ዳግመኛም ጴጥሮስን እጁን ጭኖ ፓትርያርክ አድርጎ ሾሞታል። በዚህም ጊዜ ሰማያውያን መላእክት ምድራውያን ሐዋርያት አንድ ሆነው አመስግነዋል። ከዚህ በኋላ ሐዋርያት ከጌታችን እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተ ክርስቲያን አንጸዋል። ከዚያ በፊት የነበረው የእነ ሰሎሞን ቤተ መቅደስ፣ የአይሁድ ምኲራብ፣ የአይሁድ ሥርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ሥርዓት መፈጸሚያ አልነበረም። እንኪያስ ‹‹ሐዋርያት የት ነበር ሕዝቡን የሚያጠምቁትና የሚያቆርቡት?›› ከተባለ እንደ ማርቆስ እናት ቤታቸውን ለሐዋርያት በሰጡ ‹‹በየአማኞቹ ቤት›› ይከናወን ነበር። ሰኔ 20 ቀን ሕንጸተ ቤተክርስቲያን (የቤተ ክርስቲያን መታነጽ) ታላቅ በዓል ነው። ቤተ ክርስቲያን እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሻሽ የመጣችና ሩቅ ብእሲ የመሠረታት ሳትሆን እራሱ ጌታችን አምላካችን በገዛ ደሙ የመሠረታት ናት። ሐዋ 20÷28 በዕለተ ዐርብ በዕፀ መስቀል ላይ ከጌታችን የፈሰሰው ቅዱስ ደም ቅዱሳን መላእክት በብርሃን ፅዋ ቀድተው በዓለም ሁሉ ረጭተውታል። ስለሆነም የጌታችን ወርቀ ደም በነጠበባቸው ቦታዎች ሁሉ ላይ ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያን ይሠራባቸዋል። ቅዱስ እግዚአብሔር አምላካችን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም እና ከቅድስት ቤተክርስቲያን በረከት ያሳትፈን አሜን!! @fkss21 @fkss30
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ከዚህ በታች ስማችሁ የተዘረዘረ አባላት እሁድ ሰኔ 21 አገልጋዮች ናችሁ። 1 ማህሌት ይግረማቸው 2ትዕግስት አበራ 3 ሰብለ ዋሴ 4ራሄል አንዱዓለም 5መቅደላዊት አቢይ 6ቴዎድሮስ አራጋው 7አቦነሽ ለገሰ 8ጌጤነሽ ንጉሴ 9ህይወት ወንድሙ 10 ዘመናይ አጥናፉ ወረብተኛ 1 ፈጠነ አመነ 2 የአብስራ ተስፋዬ 3 የአብስራ ፍስሃ 4 ትንሳኤ ተካልኝ 5 ፀጋዬ ካሳ 6 ዘሪሁን ተስፋዬ 7 ናትናኤል ብርሃነ 8 አማኑኤል አሰፋ 9 ወርቁ አለልኝ 10 ታመነ ፈንታ 11ሲሳይ ሙለታ 12 ሱራፌል ጌትዬ 13 ብሩክ ተሾመ ( ከበሮ መቺ የወረብ) 14 ልዑል ዘሪሁን 15 ሮቤል አለባቸው 16 ዋሲሁን ፍቃዱ (ከበሮ መቺ የወረብ) 17 ቃለአብ በላይ 1 ትህትና ተስፋዬ 2 ሰላማዊት ገ/መድህን 3 ቤተልሔም ፍቅረ 4 ፋሲካ ሞገስ 5 ቤርሳቤህ ወንድሜነህ 6 ኤፍራታ ግርማቸው 7 ቤተልሔም አለም 8 ቅድስት ፅጌ 9 አስቴር አስራት 10 ቃልኪዳን ገ/መስቀል 11 ኢየሩሳሌም በላይ 12 ሰላም አሰማ 13 ሬኒ ኃያል 14 ፂሆን ወንድማቸው 15 ሃብቴነሽ ደምሴ 16 ሶስና ወ/ዮሐንስ 17 በዕምነት ኃይሉ 18 ብሌን መለሰ 19 አፎሚያ ደመቀ 20 ብሩክታዊት ተስፋዬ 21 ደስታ አዲስ 22 ደስታ ሰፊው 23 ለምለም ጉማታው 24 ምህረት ንጉሴ 25 ህይወት ደንድር 26 ዳናዊት ጌታቸው 27 ደስታ ቶሎሳ 28 ሄራን ቶሎሳ 29 እድላዊት መስፍን መዝሙር መሪ:-አንተነህ ትዕግስቱ እና እድላዊት መስፍን ሰልፍ መሪ:- ታደሰ አብርሃም እና ጌትነት ኃ/ ማርያም ማሳሰቢያ:- ነገ የመጨረሻ ጥናት ስለሆነ ሁላችሁም 12:30 እንድትገኙ እንዲሁም በመረሳት ስማችሁ ያልተፃፈ ካለ በአካል መጥታችሁ አናግሩን። እግዚአብሔር አምላክ አገልግሎታችንን ይቀበልልን!!
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ቀን:12/10/2018ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ አዲስ በወረደው የሰንበት ትምህርት ቤቶች ተቋማዊ አደረጃጀት መሠረት የቦ/ቡ/ፍ/ሕ/ቅ ማርያም እና መ/መ/ቅ ዮሐንስ የፈለገ ቅዱሳን ሰንበት ትምህርት ቤት ከክ/ከ/ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ተወካይ በአደረጃጀቱ እና በምርጫ ማስፈፀሚያ ሰነዱ በሚያዝያ 25፣2018 ዓ.ም ለጠቅላላ የሰ/ት/ቤቱ አባላት ግንዛቤ ከተፈጠረ በኋላ አስመራጭ ኮሚቴ ተመርጦ ወድያውኑ ወደ ስራ ከገባበት ቀን ጀምሮ እስከ አሁን በርካ ጥሩ እና ፈታኝ ተግባራት በፈጣሪ ቅዱስ ፍቃድ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ ደርሷል። #ግንቦት 30 የእጩ ሥራ አመራር ጉባኤ አባላትና የኦዲት እና ኢንስፔክሽን አመራር አባላት ልየታ ስራ ተሰርቷል። በዕለቱ 18 የሥራ አመራር እጩዎችና እና 4 የኦዲትና ኢንስፔክሽን አመራር አባላት ተመርጠዋል። የሰንበት ት/ቤታችን የዕጩ ብዛት ከሚፈለገው 9 ተመራጭ በእጥፍ (100%) ማለትም 18 እጩ ስም ለጸሎት እንዲላክ ታስቦ የነበረ ቢሆንም ከሰንበት ት/ቤታችን አቅም አንፃር ብዙ በጀት የሚጠይቅ በመሆኑ፣ሁለት ጊዜ ከእጩ ተመራጭ ባደረግነው ውይይት እጩ አባላት ያሉበት ዝግጁነት ሙሉ ለመረዳት ስላልተቻለ እና ከ33ዓመት በላይ ለብቻ ባለመለየቱ ምክንያት፡ #፩.የእጩ ሥራ አመራር ጉባኤ አባላት መጀመሪያ ከተለዩት 18ቱ ውስጥ ቀሲስ አለሙ ቦጋለ በመቀነስ የ17ቱ 75% በመቀነስ በቅደም ተከተል አባሉ በሰጣቸው ነጥብ 12ቱ (ከ33ዓመት በታች) እንዲሆኑ፣ #፪.ከ33ዓመት በላይ የሆኑ እጩዎች 10% በጠቅላላ ጉባኤ በተወሰነው ማግኘት ባይቻልም፡ቀሲስ አለሙ ቦጋለ እና ዮሐንስ ታደሰ እንዲሆኑ፣ #፫.የኦዲትና ኢንስፔክሽን እጩ አመራር አራት፣ #በአጠቃላይ 12 ከ33ዓመት በታች፣2 ከ33ዓመት በላይ እንዲሁም 4 የኦዲትና ኢንስፔክሽን ድምር 18 እጩ አመራር አባላት ወደ ጸሎት ስመ ክርስትናቸው ከተቻለ ለሁለት ሱባኤ ካልሆነ ግን ለአንድ ሱባኤ ለደብሩ እና ለአንድ ገዳም እንዲላክ የአስመራጭ ኮሜቴ ወስኗል።በመሆኑም ዝርዝራቸው ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለፁት እጩ አመራር መሆናቸውን እናሳውቃለን። ##እጩ የሥራ አመራር ጉባኤ አባላት፡ #፩ከ33ዓመት በላይ ፩.ቀሲስ አለሙ ቦጋለ እና ፪.ዮሐንስ ታደሰ #፪ከ33ዓመት በታች ፩. አብራሃም ደስታው ፪.ትንሣኤ ተካልኝ ፫.ዲ/ን ትንሣኤ ፀጋዬ ፬.ናትናኤል ብርሃነ ፭. አዱኛ ጌታቸው ፮.ኤፍራታ ቶሌራ ፯.ቤተልሔም አለም ፰.ሱራፌል ጌትዬ ፱.ቴዎድሮስ አራጋው ፲.ሲሳይ ሙለታ ፲፩.አንተነህ ትዕግስቱ እና ፲፪.ሀብቴነሽ ደምሴ #፫የኦዲት እና ኢንስፔክሽን እጩ አመራር አባላት፡ ፩.ብሩክ ተሸመ ፪.ታደሰ አብርሃም ፫.ዲ/ን ጌትነት ሳህሌ እና ፬.አቦነሽ ለገሠ ከምርጫ ጋር ተያይዞ የሚኖረው ቀጣይ መርሐግብር ሰኔ 28 ሲሆን በዕለቱ በእጣ 9 የስራ አመራር አባላት እና 3 የኦዲትና ኢንስፔክሽን ተመራጮች ከደብሩ ሰበካ ጉባኤ ተወካዮች፣ከክፍለ ከተማ የሰ/ቤቶች አንድነት ተወካይ፣ሌሎች ታዛቢዎች እና የፈ/ቅ/ሰ/ቤት አባላት ሁሉ በተገኙበት ጠቅላላ ጉባኤው በጸሎት እና በታላቅ መንፈሳዊ ሥነሥርዓት የሚመረጡ ይሆናል። © የፈ/ቅ/ሰ/ት/ቤት አስመራጭ ኮሚቴ
ልዩ ቀን ነበር! በተለያዩ የፈለገ ቅዱሳን የሶሻል ሚዲያ አካውንቶች በተደጋጋሚ ስለ ሰኔ 14 ሲነገር ነበር፡፡ የእግዚአብሔር ጸጋ እና በረከት ተጨምሮበት ከታሰበው በላይ ድንቅ ቀን አሳልፈናል፡፡ በጠዋቱ መርሐግብር በተጋባዥነት እነ መጋቢ ሀይማኖት መምህር እዮብ ይመኑ፣ ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ ተገኝተው በክብር እንግድነት ደግሞ የደብራችን አስተዳዳሪ ሊቀ ማእምራን ለይኩን አያሌው እና የደብራችን ጸሐፊ መጋቤ ሚሥጥር መምህር ዳዊት ጌትነት የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ፕሬዝዳንት ሊቀ ኅሩያን ይልማ ጌታሁን እና ሌሎች ታላላቅ የቤተክርስትያናችን ሊቃውንት አባቶች እንዲኹም በተለያየ ደረጃ የሚያገለግሉ የሰበካ ጉባኤ አባላት፣ የማኅበር ተወካዮች ሌሎች ከቅርብም ከሩቅም የመጡ እንግዶች የተገኙበት ትልቅ መርሐግብር ነበር፡፡ ምናልባት አንድ ሰው የሰንበት ት/ቤት አዳራሽ ለማስመረቅ ይኼ ኹሉ እንግዳ እንዴት መጣ ብሎ ሊገረም ይችላል፡፡ መልሱ ብዙ ሊኾን ይችላል፤ በጥቂቱ ለማጠቃለል ግን 1• ከዚህ ሰንበት ት/ቤት ትልቅ ነገር እየተጠበቀ ነው 2• በሰንበት ት/ቤቷ እና በደብሩ መካከል ያለው ፍቅር እጅግ ኃያል ነው 3• በሰንበት ት/ቤቷ ዕድገት ውስጥ እንዲሳተፉ ለምእመናን በሩ ክፍት ኾኗል። መርሐግብሩ በብዙ ነገር ደረጃውን ጠብቆ የተዘጋጀ ሲኾን፤ ከምንም በላይ ግን አዳራሹ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ላደረጉ አካላት እና ለአዳራሽ አሠሪ ኮሚቴው የተዘጋጀው የምስጋና ሥጦታ እጅግ ደስ በሚል ስሜት ታዳሚው ላይ ፈጥሮ ነበር፡፡ በመርሐ ግብሩ ላይ በኢትዮጵያ በሰንበት ት/ቤት ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በልዩ ኹኔታ የበለጸገው የዳታቤዝ ሲስተም የተመረቀ ሲኾን በአጠቃላይ ታዳሚው እና የሰንበት ት/ቤቷ አባላት ስለ ሰንበት ት/ቤታቸው ብሩህ ነገርን እንዲጠብቁ ያደረጋቸው ትልቅ ቀን ነበር- ሰኔ 14፡፡ ስለኹሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን፡ ስለወደፊቱም እርሱ ያውቃል፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር🙏
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи