tgindex
🇸🇦ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

🇸🇦ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

Статистика

ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው። ✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼ 👇🏾👇🏾👇🏾 @hamdquante አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል 👉🏿 @hamdquante_bot👈🏿

Последний пост
15 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
22
Всего постов
31
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
12 207
−6 за 3 дн.
Сутки
+5
+0,04%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 862
31 постов
Вовлечённость
15,3%
к подписчикам
Постов в день
3,1
всего 31
Упоминаний
4
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1 827
1/48двое суток
2 093
1/72трое суток
2 258

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 14 авг.1 325337

    ✍ ሙእሚን እና ወንጀል…………   አማኝ ሰው በሚሰራው ወንጀል ፈጽሞ ሙሉ ደስታን አያገኝም፤ ደስታውም ቢሆን ሙሉ አይሆንም። ይልቁንም፣ በልቡ ውስጥ ከሀዘን ስሜት ጋር ሳይቀላቀል ያንን ተግባር መፈጸም አይችልም። ምንም እንኳ የምኞት ስካር ያንን ስሜት እንዳይሰማው ሊጋርደው ቢችልም።      ልቡ ከዚህ የሀዘን ስሜት ነጻ በሆነበት ጊዜ ሁሉ የኢማኑ ሁኔታ መጠየቅ ይገባዋል። እንዲሁም ለልቡ መሞት ማልቀስ ይገባዋል። ምክንያቱም፦    ልቡ  ሕያው ቢሆን ኖሮ ያንን ኃጢአት መፈጸሙ ያስጨንቀው፣ ያሳዝነው እና በልቡ ላይ ከባድ ሸክም ይሆንበት ነበር።         [ኢማም ኢብኑል ቀይም] https://t.me/hamdquante/10922

  • 14 авг.1 563275

    ✍ ስሙ ሳይታወቅ በስራው ኡማ ቀንቶበታል!!     በቁርኣን ውስጥ ከተጠቀሱት እጅግ አስደናቂ ግለሰቦች መካከል አንዱ ስሙ ሳይጠቀስ በአማኝነቱ አላህ የገለጸው ሰው ነው። እርሱም ከፊርዓውን ወገን የሆነው አማኝ ነው!!    አላህ የዚህ  አማኝ ቃላቶቹን በታላቁ ቁርኣን ውስጥ ከብርሃን በተሰሩ ፊደላት ዘርዝሮ፣ በሱረቱል ጋፊር ውስጥ አኑሮለት እስከ ዕለተ ቂያማ ድረስ በአማኞች አንደበት እንዲዘከር አድርጎታል። በእርግጥም ይህ ክብር ከነቢያትና ከመልዕክተኞች በስተቀር ጥቂቶች ብቻ የደረሱበት ታላቅ ደረጃ ነው!! ይህ የሚያሳየው፦      ጽኑ የሆኑ ወንዶች እንጂ ማንም ሊቆምበት በማይችለው በዚያ ፈታኝ ወቅት እውነትን በመናገሩ ያሳየውን የታላቁን ሰው አሻራ ምን ያህል ከፍተኛ መሆኑን ነው። የሚገርመው ነገር ይህ ሰው ፊርዐውን…… {ذَرُونِي أَقْتُلْ مُوسَى وَلْيَدْعُ رَبَّهُ} {ተዉኝ ሙሳን ልግደለው፣ ጌታውንም ይጥራ} በሚልበት ጊዜ የሙሳ ሕይወት ለመታደግ ካልሆነ በስተቀር አማኝነቱን በግልጽ አላሳየም ነበር። በዚያች ቅጽበት ግን ስለ ራሱ ሕይወት መጨነቅ ትቶ የሚወሰድበት እርምጃ በማይታወቅ አምባገንኑ ፊት ስለ እውነት ሁሉንም ነገር ተናገረ። ንግግሩን የጀመረው በእነዚህ ወርቃማ ቃላቶች ነበር፦ {أَتَقْتُلُونَ رَجُلًا أَن يَقُولَ رَبِّيَ اللَّهُ} {አንድን ሰው "ጌታዬ አላህ ነው" በማለቱ ብቻ ትገድሉታላችሁን?} አላህም ውጤቱን ይህ አደረገለት፦ {فَوَقَاهُ اللَّهُ سَيِّئَاتِ مَا مَكَرُوا وَحَاقَ بِآلِ فِرْعَوْنَ سُوءُ الْعَذَابِ} {አላህም የሸረቡትን ተንኮል መጥፎ ነገር ጠበቀው፤ የፊርዓውንም ወገኖች መጥፎ ቅጣት ከበባቸው።}   ከሁሉ በላይ የሚያስገርመው ደግሞ ይህ ሰው ከዚያ በፊት ያለፉ ነብያቶችና ህዝቦቻቸው መሃል የተከሰተው የዳዕዋ ሂደት በሚገባ የሚያውቅ ነበር። ስለሆነም ነው ከአፉ የሚወጡ ቃላቶች በዕውቀትና በጥበብ የተዋቡ የሆኑለት። {وَقَالَ ٱلَّذِىٓ ءَامَنَ يَٰقَوْمِ إِنِّىٓ أَخَافُ عَلَيْكُم مِّثْلَ يَوْمِ ٱلْأَحْزَابِ}   {ያም ያመነው ሰው "እኔ በናንተ ላይ የአሕዛቦቹን ቀን ብጤ እፈራላችኋለሁ፡" አለ።} {مِثْلَ دَأْبِ قَوْمِ نُوحٍۢ وَعَادٍۢ وَثَمُودَ وَٱلَّذِينَ مِنۢ بَعْدِهِمْ ۚ وَمَا ٱللَّهُ يُرِيدُ ظُلْمًۭا لِّلْعِبَادِ}   {የኑኅ ሕዝቦች፣ የዓድንና የሰሙድንም፣ የእነዚያንም ከኋላቸው የነበሩትን ልማድ ብጤ (እፈራላችኋለሁ)፡፡ አላህም ለባሮቹ መበደልን የሚሻ አይደለም፡፡} {وَيَٰقَوْمِ إِنِّىٓ أَخَافُ عَلَيْكُمْ يَوْمَ ٱلتَّنَادِ}   {ወገኖቼ ሆይ! እኔ በእናንተ ላይ የመጠራሪያን ቀን እፈራለሁ፡፡} {يَوْمَ تُوَلُّونَ مُدْبِرِينَ مَا لَكُم مِّنَ ٱللَّهِ مِنْ عَاصِمٍۢ ۗ وَمَن يُضْلِلِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِنْ هَادٍۢ}   {ወደ ኋላ ዞራችሁ በምትሸሹበት ቀን፤ ለናንተ ከአላህ (ቅጣት) ምንም ጠባቂ የላችሁም፡፡ አላህም የሚያጠመው ሰው ለርሱ ምንም አቅኚ የለውም፡፡} {وَلَقَدْ جَآءَكُمْ يُوسُفُ مِن قَبْلُ بِٱلْبَيِّنَٰتِ فَمَا زِلْتُمْ فِى شَكٍّۢ مِّمَّا جَآءَكُم بِهِۦ ۖ حَتَّىٰٓ إِذَا هَلَكَ قُلْتُمْ لَن يَبْعَثَ ٱللَّهُ مِنۢ بَعْدِهِۦ رَسُولًۭا ۚ كَذَٰلِكَ يُضِلُّ ٱللَّهُ مَنْ هُوَ مُسْرِفٌۭ مُّرْتَابٌ}    {ዩሱፍም ከዚህ በፊት ግልጽ ማስረጃዎችን በእርግጥ አመጣላቸሁ፡፡ ከዚያም እርሱ ካመጣላችሁ ነገር ከመጠራጠር አልተወገዳችሁም፡፡ በጠፋም ጊዜ "አላህ ከእርሱ ኋላ መልክተኛን በጭራሽ አይልክም" አላችሁ፡፡ አላህ እንደዚሁ ድንበር አላፊ ተጠራጣሪ የሆነን ሰው ያጠማል፡፡}    በመቀጠልም ንግግሩን ዙሪያው በተቀመጡ ሰዎች ልብ ውስጥ ትልቅ ተፅዕኖ ባሳደረ ታላቅ ምክር ይደመድማል፦ {فَسَتَذْكُرُونَ مَآ أَقُولُ لَكُمْ ۚ وَأُفَوِّضُ أَمْرِىٓ إِلَى ٱللَّهِ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ بَصِيرٌۢ بِٱلْعِبَادِ}    {የምላችሁንም ነገር በእርግጥ ታስታውሳላችሁ፤ እኔም ነገሬን ወደ አላህ አስጠጋለሁ፤ አላህ ባሮቹን ተመልካች ነውና።}    ይህ ታላቅ ሰው ለእኛ ማንነቱ ያልታወቀ ሚስጥር ሆኖ ቢቀጥልም: አላህ ግን በዓለማት ውስጥ ከሁሉ በበለጡት መጽሐፎቹ ውስጥ ደረጃውን ከፍ ሊያደርገው፤ ለተመረጡ መልእክተኞቹ እንዲቀሩት ሊያወርድላቸውና ከእነሱ በኋላም አማኞች ምድርንና በእሷ ላይ ያለውን ሁሉ አላህ እስከሚወርስበት ቀን ድረስ በቁርኣን ንባብ እንዲያዜሙት ድንቅ ስራውን አስፍሮታል። 🤲አላህ    እነዚህን ደጋግ ሰዎች ጎራ ይቀስቅሰን፤ በጀነትም ያጎራብተን!! https://t.me/hamdquante/10921

  • 14 авг.1 47622

    ✍ የዛሬው ጁሙዐ በወስላም ይሁን በሽሮ ችግር የለውም!! ስለ እውነተኛው ወስላ 👉✍👇

  • 14 авг.1 55842

    🕋      የነሃሴው ምዝገባ ዘግተን የመስከረም ጀምረናል!! የሁል_ጊዜ ምርጡና ተመራጩ የለምለም ትራቭል     ለ9ኛ  ዙር አዘጋጅቶት የነበረው የክረምት ሁለተኛው ዙር የነሃሴ የዑምራ ፓኬጅ ምዝገባ በተሳካ ሁኔታ አጠናቆ;    ቪዛና ትኬቱ ወደ ሙዕተሚሮች;    መዝገቡም ወደ መዝገብ ቤት ተመልሷል። አልሐምዱ ሊላህ!!    ሁሉም ሙዕተሚሮቻችን ቪዛና ትኬታቸው ተቀብለው የጉዞ ቀናቸው በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ። በሙሉ ዐፊያ እና ኢማን ተቀባይነት ያለው ዑምራ አላህ እንዲወፍቃቸው ዱዐችንም ምኞታችንም ነው።    የዚህኛው ዙር ላመለጣችሁ ወይም ለሞላባችሁ ቤተሰቦቻችን በአጠቃላይ ሌላ የምስራች አለን 👇   👇   👇   👇   👇   👇   👇    በሀገራችን በተለያዩ ምክንያቶች በተከታታይ ስራ ዝግ በሚሆኑባቸው ቀናቶች;    ከመስከረም_14 እስከ መስከረም_24    የለምለም ትራቭል 10ኛው ዙር ልዩ የዑምራ ፓኬጅ አዘጋጅቶ ምዝገባው ከወዲሁ ጀምሯል!!     በተዘጋጀው ልዩ የዑምራ ፓኬጅ መሳተፍና መካተት የምትፈልጉ ከአሁኑ አስቀድማችሁ በመመዝገብ ኋላ ላይ ከሚፈጠር መጨናነቅ ራሳችሁን አሳርፉ!!    ለሁለቱም ሐረሞች ቅርብና ምቹ የሆኑ ሆቴሎች ከማዘጋጀት ጀምሮ;     ከየትኛውም ሙኻለፋና እንግልት የጠራ ዑምራ በማስፈፀም ብዙኃኖች ዘንድ ተወዳጅነትና ተመራጭነትን ያተረፈው ትራቭላችን:   እናንተም ተቀብሎ ለመኻደም በአክብሮት ይጋብዛችኋል!! ያስተውሉ…………     በምናዘጋጃቸው ፓኬጆች አባል ሆናችሁ ስትሄዱ: ረመዷንን ጨምሮ በየትኛውም ሰዓት ዑምራ ማድረግ የምትችሉበት ዓመታዊ ቪዛ እጃችሁ ውስጥ ይገባል!!    ከእርሶ ሚጠበቀው ለመሄድ በወሰኑ ጊዜ ወደ ትራቭላችን በመምጣት approve ማስደረግ ብቻ ነው። አሁኑኑ ይደውሉ  🤳  0911674580                        🤳  0911683917                       🤳  0922448888 ቤተል "ሚና_ሞል"  2ኛ ፎቅ ላይ እንገኛለን። ✈️የለምለም ትራቭል የትውልዱ ተስፋ!! https://t.me/Yelemlem_travel

  • 14 авг.1 502206

    ✍     ለሁሉም ችግሮች መፍትሔው እስልምና መተግበር ብቻ ነው!!    እስልምናችን ገና ድሮ……… በጣም ድሮ ድሮ «የሴት ልጅ ሙሉ ገላዋ ዐውራ (መሸፈን ያለበት) እንደሆነ ደንግጎ አስተላልፏል»  ልባቸው ውስጥ ባለው በሽታ አስተሳሰባቸው የተበለዙ ሰዎች ሴቶቹ የስሜታቸው መወጣጫ ሊያደርጓቸው ሲፈልጉ;    "ሴት ልጅ ከወንድ እኩል መብት አላት መገላለጥ ትችላለች" ብለው አብዮት አስነሱ።    የሚታሰብለትና የሚታሰብበት ለይቶ ማወቅ የማይችል ደናቁርት ሁሉ ተከተላቸውና አብዛኛው ምድር ላይ ያሉ ሴቶች ክብራቸው ጥለው፣ ማንነታቸው አዋርደው፣ የማንም መጫወቻ ሆኑ።     ከዚህ አልፈውም በየሱቁ፣ በየማስታወቂያው በአካልም ይሁን በፎቶ ከዕቃው የበለጠ ገላዋን እያሳየች ማሻሻጫ ተደረገች። በዚህም ሰበብ……………     የበሽታ መዓት፣ የዝሙት ገበያ፣ የዲቃላ ብዛት፣ በትዳር ላይ መወስለት እና የመሳሰሉ መዘዞች ትውልዱን አቃወሰው።    በመጨረሻም ቢያንስ የተወሰነ ሰውኛ አስተሳሰብ የቀራቸው ሰዎች "ሂጃባቸው ይልበሱ" ባይሉ እንኳ "ቢያንስ… ቢያንስ……… " ብለው ማሻሻያ አደረጉ። ገና……… ገና……… ገና ብዙ ይቀራል!!    ለየትኛውም ምድር ላይ ላሉ ብልሽቶች የእስልምና ህግና ትዕዛዝ ተግባራዊ እስካልተደረጉ ድረስ ሙሉ ሰላም ሊሰፍን አይችልም። ግን ግን……………     ብርሃኑ ነጋ የት ሊጠቀም (አስተናጋጆቹ ካልገላለጡለት ማለቴ ነው)???? https://t.me/hamdquante/10918

  • 13 авг.1 759359

    🥑 ምንም ልክ ያልሆነ ነገር ነው እኮ!!    ከራሱ ክብደት በላይ ፍሬ የታቀፈ አቮካዶ እስከነ ፍሬው መዝኖ መሸጥ።    ቢሞከር እርግጠኛ ነኝ ከ70% በላይ የሚመዝነው ፍሬው  ነው። ታድያ አብዛኛው ሊጣል ተመዝኖ መሸጡ አግባብ ነው ትላላችሁ??? የምክክር ኮሚሽኑ ሊያየው የሚገባ ነጥብ ነው። https://t.me/hamdquante/10917

  • 13 авг.1 869445

    ✍ በየትኛውም የታሪክ ማህደር…………     ሙሉ ባህሪው,  የተፈጥሮ ተክለ ቁመናው,  እያንዳንዱ የሕይወት እንቅስቃሴው,  ከሌሎች ጋ የነበረው አጠቃላይ የግንኙነት ሁኔታ,  ከቤት ውስጥ ጀምሮ እስከ ጦር_ሜዳ ተግባሩ, ከአመጋገቡ ጀምሮ የመፀደጃ ቤት ስርዓቱ,   ደስታውም ይሁን ሀዘኑ ያሳለፈበት መንገድ,  እያንዳንዷ ፈገግታውም ይሁን ያለቀሳት እንባ,  እያንዳንዷ የተናገራት ቃል በፊደል ተቆጥራ ተመዝግባ    እነዚህ ሁሉ ስብስቦች ከትውልድ ወደ ትውልድ አስተማማኝ በሆነ ጠንካራ የዘገባ ሰንሰለቶች ተጠብቆ የተሰበሰበለት;   ከነብዩ ሙሐመድﷺ በስተቀር አንድም ሰው የለም!!           صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا https://t.me/hamdquante/10916

  • 13 авг.1 994217

    🏹     ትልቁ የኡሑድ ዘመቻ!!  #⃣_9    የሙስሊሙ ጦር የተደረገበትን ከበባ በመስበር ተበታትኖ የነበረው ሰራዊት በአንድ ግንባር ተሰብስቦ እንዳዲስ ትግል ቢጀምርም ረሱልﷺ ዙሪያቸው በጠላት ተከቦ ውጊያው ተቀጣጠለ። ሙስሊሞች ላይ ከበባው ሲደረግባቸው ከረሱልﷺ ጋ የነበሩት ዘጠኝ ሰዎች ብቻ ነበሩ። ይህ በሆነበት ረሱል ባልደረቦቻቸውን ለመሰብሰብ «የአላህ ባሮች ሆይ! ኑ» ብለው ሲጣሩ: ሙሽሪኮቹ ሰምተዋቸው…

  • 12 авг.1 961386

    видео или голосовое, без подписи

  • 12 авг.2 1274513

    ✍ ተውበት የሚያዘወትሩ ሰዎችን ተቀማመጡ; ልባቸው ሁሌም ለስላሳ ነው!!       [ዑመር ኢብኑል ኸጣብ] https://t.me/hamdquante/10913

  • 12 авг.2 2543216

    👇 📖{وَمَن يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَل لَّهُ مَخْرَجًا ★ وَيَرْزُقْهُ مِنْ حَيْثُ لَا يَحْتَسِبُ} {…አላህን የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫ ያደርግለታል ★ ካላሰበው መልኩም ሲሳይ ያደርግለታል።…} አላህ………     እሱን ለሚፈሩ ባሮቹ ሰዎችን በሚቸጋገሩበት ጉዳይ ላይ መውጫ መዳኛ እንደሚያደርግላቸው  እና    ካላሰቡት ቦታ ሲሳይ እንደሚከፍትላቸው ዋስትና ሰጥቷቸዋል። አንድ ሰው ይህ ነገር ሳይሆንለት ከቀረ……     ለአላህ ባለው ፍራቻ ላይ ክፍተት እንዳለበት ያሳያልና ቶሎ ምህረትን ይጠይቅ።            [ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ] https://t.me/hamdquante/10912

  • 12 авг.2 2353917

    ✍      የፈጅር ሰላት በጀምዐ ለመስገድ ከወፈቀህ; አብሽር!!!      ያ..... ዱንያ እና በውስጧ ከያዘችው ነገር ሁሉ በላጭ የሆነውን የፈጅር ጀምዐ ያገራልህ;    ዱንያ እና በውስጧ የያዘችው ነገር ሊሰጥህ ቻይ ነው!! ነብዩﷺ እንዲህ ይላሉ፦    «የፈጅር ሁለት ረከዐዎች  ከዱንያና ከያዘችው ነገር ይበልጣሉ።»    ይህ ያሉት ከፈጅር በፊት ለሚሰገደው ሁለት ረከዐ ሱና ነው።     ዋናው የፈጅር ሰላት ምን ሊሆን ነው ታድያ???!!! https://t.me/hamdquante/10911

  • 11 авг.2 26821

    ✍ facebook ላይ አንዲት ሴት "በባሏ በግፍ ተገድላለች" ተብሎ ዜናዋ ተለቀቀ። ዜናው ከፎቶዋ ጋ ነው የተለቀቀው። የሚገርመው 👇ይህ ነው; Comment መስጫ ላይ ሁሉም "እቺ የመሰለች ልጅ?" አያሉ ሀዘናቸው ይገልፃሉ። እሺ ባትመስልስ ???????

  • 11 авг.2 5673020

    ✍ አለመስራትን እያሰብክ "ኢንሻ አላህ" ብሎ ቃል መግባት;            ንፍቅና ነው!! [ኢማሙ አውዛዒ] https://t.me/hamdquante/10909

  • 11 авг.2 5006911

    ✍ እንዲህ ያሉ እናቶች ናቸው የሚያስፈልጉን!!    የፈጅር አዛን ሲል ወደ ልጇ ክፍል ገብታ ቀሰቀሰችው; "እሺ" አላትና ሳይነሳ በዝያው ተኛ። ጀምዐ ካመለጠው በኋላም ተመልሳ ገብታ ቀሰቀሰችው; አሁንም "እሺ እነሳለሁ" አላትና በዝያው ተኛ።    ቤቷን አፀዳድታ ለሐጃዋ ከመውጣቷ በፊት ገብታ ስታየው እዛው ፍራሹ ላይ እንደተጋደመ ነው። ፀጥ ብላው ትታ ሄደች። ትምህርት ቤት የፋይናል ፈተና እንዳለው ብታውቅም ሳትቀሰቅሰው ትታው ወጣች; እሱ ግን ሰዐቱ ደርሶ ስትቀሰቅሰው ለመሄድ ነበር ንያው።    ከረፋፈደ በኋላ ከእንቅልፉ ሲነቃ የፈተናው ሰዐት አምልጦታል። በብስጭት እናቱ ጋ ደወለና;   "ማም ምን ሆነሽ ነው?? ፈተና እንደነበረኝ አላወቅሽም ነበር እንዴ?? ለምንድን ነው ያልቀሰቀስሽኝ" ሲል ጮኸባት። እናት በተረጋጋ መንፈስ………    "ለአኼራው ፈተና ስቀሰቅስህ መነሳት ሲያቅትህ ሳይ; የዱንያው ፈተና ብዙም አላሳሰበኝም!!" https://t.me/hamdquante/10908

  • 11 авг.2 3092212

    ✍ የከበዱ ወንጀሎች ለምን እንደሚቀሉን አይገባኝም!! ለምሳሌ ይህንን አስፈሪ ሐዲስ ተመልከቱ👇👇👇 ኢብኑ መስዑድ ከነብዩﷺ ባስተላለፈው፦   «الرِّبا ثلاثٌ وسبعونَ بابًا أيسَرُها مثلَ أن ينكِـحَ الرَّجلُ أُمَّـهُ»    «ወለድ ሰባ ሦሥት በሮች (ክፍሎች) አሉት: ከእነርሱ ቀላሉ      አንድ ሰው እናቱን የመገናኘቱ ያህል (የከፋ) ነው።» [صحيح الجامع:٣٥٣٩]    እኛ በምናውቀው እንኳ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የነበሩ ሙስሊሞች ምንም ያህል ኢማናቸው የደከመና ወንጀላቸው የበዛ ቢሆኑ እንኳ "ወለድን" እንደ አፀያፊ ተግባር እያዩ ይጠነቀቁት ነበር።    ዛሬ ላይ ግን የጀነት ሰዎች ልብስ ለብሰው በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ወደ ጀሀነም በሚጣሩ "ኡስታዝና ሼኽ" ተብዬዎች ሰበብ "ኢስላማዊ ባንክ" ለሚባሉ የወለድ ዘዴዎች ማስታወቂያ እየሰሩና በግልፅ ፈትዋ እየሰጡ ሙስሊሙን በአጠቃላይ [አላህ ያዘነለት ሲቀር] በዚህ አጥፊ ወንጀል እንዲጥለቀለቅ አድርገውታል። እነዚህ ባንኮች፦     "ኢስላማዊ" በሚል ቅጥያ ቢጋጌጡም እውነታቸው ግን ወለድን በዘዴ የሚያገላብጡ እንጂ ከወለድ የጠሩ አይደሉም። ሌላው ከባዱ አደጋ ደግሞ………     አንድን ወንጀል ቀጥታ ከመስራት ይልቅ ያንን ወንጀል ዘዴ ተዘይዶለት ሲሰራ የበለጠ አላህን የሚያስቆጣ ይሆናል። ምክንያቱም፦    ወንጀሉን በዘዴ ቀይረህ ስትሰራው ባትናገረው እንኳ በተግባርህ ግን አላህን ለመሸወድ እየሞከርክ ነው። ለዚህም ነው…………    የተለያዩ ወንጀሎች በግልፅ የሰሩ ህዝቦች አላህ በተለያየ ቅጣት ሲቀጣቸው;    ወንጀልን ዘይደው ለመስራት የሞከሩ በኑ ኢስራኢሎች ግን አስደንጋጭ በሆነ መልኩ ወደ ዝንጀሮነት ተቀየሩ። https://t.me/hamdquante/10907

  • 11 авг.2 4704227

    ✍     መንገዱን ጠበባት፣ አጋዥም የላት፣ ወደ ፊት መሄድ አይጠቅማት; መመለስም አይበጃት፤ ብትቆይ ትሞታለች; ብትዘል ትወድቃለች፤   አንዳንዴ ሕይወት እንዲህ ትሆንብሃለች። አጋዥ ይርቅሃል፤ መወሰን ይከብድሃል፤ መፈፀም ያስፈራሃል፤ መቆየቱ ያሳስብሃል። ሆኖም ግን; አንድ ነገር ላይ እርግጠኛ ሁን፦   የጭንቀት መዳኛና የችግር መፍትሔ ያለው ወደ ☝️አላህ በመመለስ ብቻ ነው!!     📖{رَبَّنَا وَلَا تُحَمِّلْنَا مَا لَا طَاقَةَ لَنَا بِهِ} https://t.me/hamdquante/10906

  • 10 авг.2 3144113

    ✍      ከአቡ ለኸብ ልጆች አምስቶች እስልምና ተቀብለዋል። እነሱም፦     ዑትባ፣ መዓተብ፣ ዱራ፣ ኻሊዳ እና ዑዛ ሲሆኑ ሁሉም ሰሓብይ ናቸው። ሁሉም………… 📖 { تَبَّتْ يَدَا أَبِي لَهَبٍ وَتَبَّ } { የአቡ ለኸብ ሁለቱ እጆች ከሰሩ } እያሉ ይቀራሉ። ምክንያቱም፦     ዲን ላይ ምንም ዓይነት ድርድር የለም!! https://t.me/hamdquante/10905

🇸🇦ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸 — tgindex